Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia @millsethiopia Channel on Telegram

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

@millsethiopia


MILLs Ethiopia

MILLs Ethiopia (English)

Are you interested in learning more about the Ministry of Irrigation and Lowlands in Ethiopia? Look no further than the MILLs Ethiopia Telegram channel, where you can stay up-to-date with the latest news, projects, and initiatives related to irrigation and lowlands in Ethiopia. The Ministry of Irrigation and Lowlands plays a crucial role in managing water resources and promoting sustainable development in Ethiopia, making this channel a valuable resource for anyone interested in these topics. MILLs Ethiopia provides regular updates on irrigation projects, water management strategies, and efforts to improve lowland areas in Ethiopia. Whether you are a student, researcher, or simply curious about the work being done in this field, this channel offers a wealth of information to keep you informed and engaged. Joining the MILLs Ethiopia Telegram channel also gives you the opportunity to connect with like-minded individuals who share your interest in irrigation and lowlands in Ethiopia. By becoming part of this community, you can engage in discussions, ask questions, and share your own insights and experiences with others who are passionate about these important issues. In addition to updates on current projects and initiatives, MILLs Ethiopia also provides valuable resources and educational materials to help you deepen your understanding of irrigation and lowlands in Ethiopia. Whether you are looking to expand your knowledge or stay informed about the latest developments in this field, this channel has something to offer for everyone. Don't miss out on the opportunity to join the MILLs Ethiopia Telegram channel and become part of a thriving community of individuals who are dedicated to promoting sustainable development and water management in Ethiopia. Stay informed, engaged, and inspired by connecting with the Ministry of Irrigation and Lowlands through this informative and enriching channel.

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

14 Feb, 14:07


Day 2 Afternoon Session Recap I
ICICRP
The session, moderated by Eng. Hizkyas Dufera, focused on The Role of the Private Sector, Climate Finance, and Technology in Irrigation. Panelists included:
- Support for the Development of Irrigation Standards and Regulation for Ethiopia – Mr. Abdo Kedir (FAO).
- Dr. Silwayiphi Samson Sithole, CEO, EWADE, Eswatini.
- Enas Abdulmalik, GEAPP.
- Private Sector Engagement in Climate-Resilient Irrigation – Mr. Henok Assefa (CEO, Precise).
- The Use of Technological Advancements for Climate-Resilient Irrigation – Mr. Hack Stiernblad (Chief Growth Officer, Sun Culture).
- Innovative Solutions for Sustainable Irrigation – Mr. Sandro Banda (Valmont Industries, USA).
- Capacity Building and Technical Assistance in Climate-Smart Irrigation – Mr. Oliver Kopsch (Antonia Ruut Stiftung).

WATCH THE FULL SESSION HERE: https://lnkd.in/ezTHrjs5

----
Website: https://mills.gov.et
FB/X/Tel: @MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

13 Feb, 17:49


Tour of the Adwa Museum and Entoto Natural Park with H.E. Dr. Goodluck Ebele Jonathan, Former President of the Republic of Nigeria, and H.E. Dr. Abraham Belay Berhe, Minister of Irrigation and Lowlands, FDRE.
------------
Follow our social media pages for the latest updates:
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://lnkd.in/eDRFqcFa
X: https://lnkd.in/eyCNA-rD
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

13 Feb, 11:12


Day 2 |International Conference on Irrigation & Climate-Resilient Production 2025
Morning Session Recap:
The morning session opened with introductory remarks by H.E. Dr. Endrias Geta Beldeda (PhD), State Minister, Ministry of Irrigation and Lowlands, followed by a presentation from Mr. Mawira Chitima, Country Director, IFAD setting the stage for discussions on Policy, Practice, and Trends in Irrigation Development and Climate Adaptation.
Key Insights:
-Best Practices and Policy Instruments for Climate Change Adaptation and Mitigation Across Africa–Dr. Tilahun Amede, AGRA
-National Climate Resilience & Food Sovereignty Initiatives: Irrigated Wheat Production Initiative – H.E. Dr. Meles Mekonnen, State Minister,MoA
-The Green Legacy Initiative – H.E. Prof. Eyasu Elias, State Minister,MoA
- UNICEF Panelist, Ciara Catherine Healy Silke - insights on Human Capital for Sustainable & Climate-Resilient Production – , UNICEF
Watch the full session here: https://web.facebook.com/100057309975167/videos/517012337631812

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

12 Feb, 20:54


DAY 01 | Ministerial Dialogue and Experience Sharing Session
International Conference on Irrigation and Climate Resilient Production 2025
Following the Presidential Plenary Session, the Ministerial Dialogue Session brought together esteemed African leaders, Excellencies, who shared valuable insights.
WATCH THE FULL VIDEO HERE: https://fb.watch/xILRawgBzr/
------------
Follow our social media pages for the latest updates:
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MILLsEthiopia
X: https://www.x.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

12 Feb, 12:11


Video Recap: International Conference on Climate Resilient Production 2025 Opening Ceremony

----------------
Follow our social media pages for the latest updates:
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MILLsEthiopia
X: https://www.x.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

12 Feb, 08:58


The inaugural International Conference on Irrigation and Climate Resilient Production 2025 was officially launched this morning, graced by the presence of H.E. Taye Atske Selassie, H.E. Abraham Belay Berhe (PhD), Minister of Irrigation and Lowlands, FDRE, H.E. Former Prime Minister Hailemariam Desalegn, FDRE, H.E. Dr. Goodluck Jonathan, Former President of the Federal Republic of Nigeria, H.E. Jakaya Kikwete, Former President of the United Republic of Tanzania, H.E. Dr. Ibrahim Assane Mayaki, Former Prime Minister of the Republic of Niger.
The event brings together esteemed dignitaries, including ambassadors, representatives of international organizations, policymakers, and development partners, marking a significant milestone in advancing discussions on climate resilient production.
#MILLs
----
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MILLsEthiopia
X: https://www.x.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

12 Feb, 03:48


Feb 12-14, 2025 | Adwa Victory Memorial
The wait is over! The inaugural International Conference on Irrigation and Climate-Resilient Production 2025 will officially kick off today. Stay tuned for live updates and key highlights.

#FDRE #ICICRP2025 #MILLs #Irrigation #ClimateResilience #FoodSovereignity
----------------
Follow our social media pages for the latest updates:
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MILLsEthiopia
X: https://www.x.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

11 Feb, 20:46


H.E. Ato Hailemariam Desalegn, Former Prime Minister of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, and H.E. Dr. Abraham Belay Berhe formally received H.E. Dr. Goodluck Ebele Jonathan, Former President of the Republic of Nigeria.
In just a few hours, the inaugural International Conference on Irrigation and Climate-Resilient Production 2025, the first of its kind, will officially commence.

#FDRE #ICICRP2025 #MILLs #Irrigation #ClimateResilience #FoodSovereignity
----------------
Follow our social media pages for the latest updates:
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MILLsEthiopia
X: https://www.x.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

11 Feb, 15:07


H.E. Ato Hailemariam Desalegn, Former Prime Minister of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, and H.E. Abraham Belay Berhe (PhD), along with accompanying delegates, formally received H.E. Jakaya Kikwete, Former President of the United Republic of Tanzania, and his delegation earlier today. The distinguished guests have arrived in Ethiopia to partake in the highly anticipated inaugural International Conference on Irrigation and Climate-Resilient Production.
#FDRE #ICICRP2025 #MILLs #Irrigation #ClimateResilience #FoodSovereignity
----------------
Follow our social media pages for the latest updates:
Website: https://mills.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MILLsEthiopia
X: https://www.x.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

20 Jan, 11:14


https://www.facebook.com/100057309975167/posts/1134166471837008/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

16 Jan, 08:59


የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ
ጥር 8/2017 ዓ/ም
ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎችና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሚኒስቴር መ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡ በእቅድ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ወቅት የሚኒስቴር መ/ቤቱ የመደበኛ ስራዎችና ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ከአሁን በፊቱ በጣም የተሸለ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም ከዚህ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ሁሉም የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተቀናጅተው መስራት እንደሚገባ ተገልፀዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

06 Jan, 11:13


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም በጤና አደረሳቹ አደረሰን ::
በዓሉ የሰላም ፣ ፍቅር እና የመተሳሰብ እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ::

ክቡር ዶክተር አብርሃም በላይ የ መስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

05 Jan, 06:07


በጎዴ ከተማ በመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር እየተገነባ ያለውን ' የአርብቶ አደር የተቀናጀ ዘመናዊ መንደር ' በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተጎብኝተዋል ::

ጉብኝቱ ፕሮጀክቱ በቆላማ አካባቢዎች የሚኖረውን ማህበረሰባችን የተሻሻለ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግና የተቀናጀ ልማት የማረጋገጥ ትልማችንን ለማሳካት አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደ መሆኑን ለመረዳት አስችሏል

በጉብኝቱ ወቅት ፕሮጀክቱ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ተጠናቆ እንደሚመረቅም የመስኖና ቆላማ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ለጎብኝዎች ገልፀዋል ::

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

04 Jan, 10:07


ባለፉት ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሠራተኞች ባለፉት ሁለት ቀናት በሙስና እና ብልሹ አሠራር ዙርያ ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ መፍጠሪያ ስልጠና ተጠናቋል፡፡ በማጠቃለያውም አመራሩና ሠራተኛው የሀገር ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም መንግሥት ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአዋጅ የሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ዕውን ለማድረግና ብልሹ አሠራርን ለመቅረፍ ፋይዳው ጉልህ መሆኑ ተብራርቷል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

04 Jan, 08:18


የመስኖ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መሥራት የጸረ-ሙስና ትግሉ አንዱ አካል ነው፡፡
ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
የመስኖ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ መሥራት፣ ድህነትን መቅረፍ፣ ኢኮኖሚን ማዳበርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የጸረ-ሙስና ትግሉ ቁልፍ ጉዳዮች መሆናቸውን ሠልጣኞች ተናገሩ፡፡ ሙስና የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ችግሮች የሚያስከትል ከመሆኑም ባሻገር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ሊያስከትል እንደሚችል በመገንዘብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ መታገል እንደሚገባቸውም በስልጠናው ላይ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ሙስና በባህሪው በወንጀሉ ቀጥተኛ ተጎጂ ግለሰብ አለመኖሩ፣ ድንበር ተሻጋሪ መሆኑ፣ ተላላፊ መሆኑና ምንጩ የማይታወቅ እና በንብረትና ገንዘብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያመጣ በመሆኑ የጸረ-ሙስና ትግሉን አዳጋች እንደሚያደርገውም ስልጠናውን የሰጡት ምሁራን ገልጸዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

03 Jan, 17:34


የ ጎዴ መስኖ ልማት ፕሮጀክት
ከ ፋና የተወሰደ

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

03 Jan, 11:35


ሁሌም እንደምንለው ዘንድሮም እናስመራቃለን ብለን ቃል በገባነው መሰረት የመጀመሪያ የሆነውን የ ምዕራብ ጎዴ መስኖ መሰረተ ልማት ፕሮጀክት አስመርቀናል
በቀጣይም በዚህ አግባብ አጠናክረን እንቀጥላለን
በሱማሌ ክልል  ካለው  ሰፊ    በመስኖ የመልማት ዓቅም  ካለው መሬት  ውስጥ ፤ በአሁኑ ሰዓት የሚኒስቴር መስራቤታችን   የምዕራብ ጎዴ ፕሮጀክትን ጨምሮ ከ112,000 ሄክ በላይ የሚሸፍን የመስኖ መሰረተልማት የጥነትና የዲዛይን ስራዎችን  በማከናወን ላይ ይገኛሉ ።ይህ የምዕራብ ጎዴ ፕሮጀክት ፤በምህንድስና ቋንቋ  ሄድ ወርክ ላይ በተሰራው Diversion Wear  ብቻ በመጠቀም ተጨማሪ ካናሎች በመስራት 27,600 ha ማልማት የሚያስችል አቅም ይኖረዋል።
አሁን በገነባናቸውና ጠግነን ወደ ስራ ባስገባናቸው ባጠቃላይ 146 ኪ/ሜ ርዝመት ያላቸው የተለያየ መጠን ያላቸው ካናሎች በመጠቀም 7,600 ሄክታር በስበት ሀይል  3,000 ሄክታር በፓምፕ ማልማት የሚያስችል አቅም መፍጠር ተችሏል ።
"ከዚህ በኃላ ባሉት ተከታታይ ስራዎች  የአከባቢውን ማህበረሰብ በተሻለ አቅም በማደራጀት እና ባለሃብቶች በተለይም አገር በቀል ባለሀብቶችን  በመጋበዝ የተዘጋጀውን መሬት ሙሉ በሙሉ ደረጃ በደረጃ ወደ ልማት በማስገባት የምግብ ሉአላዊነትን የማረጋገጥ ከፍ ያለ አገራዊ ትልማችንን በቅንጅት ለማሳካት ከዛሬ ጀምሮ የነቃ ርብርብ እንድናደርግ ስጠቁም ክልሉና የፌደራል ኢንቨስትመንት ተቋማት ማሳያ የሆነ ርብርብ እንደሚያደርጉ ሙሉ እምነት አለኝ።"ሲሉ የ መስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ተናግረዋል ::

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

26 Dec, 19:36


ብልፅግና ፓርቲ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በመፈጸም ዕዳ ሳይሆን ምንዳ እናወርሳለን ብሎ የገባውን ቃል በተግባር እያረጋገጠ ነው- አብርሃም በላይ (ዶ/ር)


ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም

ብልፅግና ፓርቲ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በመፈጸም ዕዳ ሳይሆን ምንዳ እናወርሳለን ብሎ የገባውን ቃል በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ በለውጡ ዓመታት በተለይም በፕሮጀክት ግንባታ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ከለውጡ በኋላ ብልጽግና ፓርቲ ትክክለኛ የፕሮጀክት አመራርና ውሳኔ በመስጠት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት የማከናወን አቅምን በተግባር ማሳየቱን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ቀደም ሲል በተለያዩ አካባቢዎች የመሰረተ ድንጋይ እየተቀመጠ በጅምር የሚቀሩ በርካታ ፕሮጀክቶች እንደነበሩ አስታውሰው ብልጽግና እንዲህ አይነት አሰራሮች ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል።

በዚህም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ጨምሮ የኮይሻ የሃይል ማመንጫ እና ከ15 ዓመት በላይ ግንባታው ተቋርጦ የነበረው የመገጭ የመስኖ ፕሮጀክ ግንባታቸው እንዲቀጥል ተደርጓል ብለዋል።

ለዚህም ብልፅግና ለህዝቡ በገባው ቃል መሰረት በጀት በመመደብ፣ የፕሮጀክት አመራር ለውጥ በማድረግ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ እንዲከናወን ማድረጉን አብራርተዋል።

በለውጡ ዓመታት ብልፅግና ፓርቲ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በመፈጸም ዕዳ ሳይሆን ምንዳ እናወርሳለን ብሎ የገባውን ቃል በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

የመስኖ ፕሮጀክቶች ለህዝብ ተጠቃሚነትና ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት ጥራታቸውን ጠብቀው በፍጥነት እንዲገነቡ እየተደረገ መሆኑንም ዶክተር አብርሃም አንስተዋል።

በዚህም ለዓመታት ተጀምረው የነበሩ የመስኖ ግድቦች ግንባታቸው በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህ ዓመት ብቻ የሶስት የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ዕምቅ የተፈጥሮ ሃብት፣ በቂ እና የሰለጠነ የሰው ሃብት መኖሩን ጠቅሰው በመስኖ ልማት ጭምር በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ በማምረት ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚያስችል ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
(የመረጃ ምንጭ :-አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ)

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

25 Dec, 09:19


በቀን 6 ሺ ኩንታል ስኳር ለማምረት እየተሰራ ነው
16/4/2017 ዓ/ም
የከሰም ስኳር ፋብሪካ በመጀመርያው ዙር የሸንኮራ አገዳ ማልማትና ማስፋፊያ ፕሮግራሙ እስከ 6 ሺህ ኩንታል ስኳር ለማምረት በእቅድ እየሰራ መሆኑን የፋብሪካው የእርሻ ኦፕሬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ጋኖሬ ተናግረዋል፡፡
የከሰም ግድብን ውሃን በመጠቀም 20 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ መገንባቱን የሚገልጹት የእርሻ ኦፕሬሽን ስራ አስኪያጁ አቶ ሰለሞን ጋኖሬ በመስኖ መሰረተ-ልማት አለመስፋፋት ምክንያት ለፋብሪካው የሚቀርበው የሸንኮራ አገዳ በቂ አለመሆኑን አያይዘው ገልጸዋል፡፡
በቂ መሬት፣ የሰው ሃይልና አስተማማኝ ሰላም በአካባቢያቸው እንዳለ የገለጹት አቶ ሰለሞን ጋኖሬ፣ ተጨማሪ መሬት ለማምረት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የዋናውን ካናል እንዲያራዝምልን እንፈልጋለን በማለትም ጠይቀዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመካከለኛው አዋሽ የመስኖ ልማት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በቀለ በርገና በበኩላቸው ተጨማሪ መሬት ወደ ልማት ለማስገባት የመስኖ መሠረተ-ልማት ማስፋፋት ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ከ4 ሺህ በላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች ያሉት የከሰም ስኳር ፋብሪካ፣ በግብአትነት ከሚጠቀምበት የሸንኮራ አገዳ ማልማት ባሻገር በ70 ሄክታር መሬት ላይ ፍራፍሬና አትክልት በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

24 Dec, 08:35


የመቼላ መስኖ ልማት ጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ተጠናቆ ወደ ግንባታ ሲገባ ከ9,900 ሔክታር በላይ የማልማት አቅም ይኖረዋል፡፡
ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
የመቼላ መስኖ ልማት ጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ፣ ለገሂዳና ወረዒሉ ወረዳዎች የአዋጭነት ጥናት ሥራው እየተከናወነ ሲሆን ፕሮጀክቱ የደረሰበት ሁኔታ ሪፖርት ቀርቦ መገምገሙ ይታወሳል፡፡
በሪፖርት ግምገማው ላይ የተገኙት የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ መቼላ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአማራ ክልል ከሚሠራቸው የመስኖ ልማት ጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸው ፕሮጀክቱ በደቡብ ወሎ ዞን ያለውን ማህብረሰብ የምግብ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ረገድ ፋይዳው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በክልሉ ለሚሠራቸው የግንባታ እና የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በተመሳሳይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ፕሮጀክቶች ጥናትና ዲዛይን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር ያሬድ ሙላት አማካሪ ድርጅቱ ዲ.ኤ.ች ኮንሰልት የግድብ፣ የመሠረተ ልማትና የፕሮጀክቱን የማልማት አቅም በጥልቀት በመሥራቱ አመስግነው በቀጣይ ለውሳኔ የሚቀርቡ ጉዳዮችን በማስተካከል ለዝርዝር ጥናት እንዲቀርብ አሳስበዋል፡፡
በሌላ በኩል የአማካሪ ድርጅቱ ዲ.ኤ.ች ኮንሰልት የመቼላ መስኖ ልማት ጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀማል ያሲን የፕሮጀክቱ አዋጭነት ጥናት ተጠናቆና ተገንብቶ ወደ ልማት ሲገባ ከ9,900 ሔክታር በላይ የማልማት አቅም እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
የመቼላ መስኖ ልማት ጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክት ግድቡ የሚያርፈው ለጋምቦ እና ለገሂዳ ወረዳዎች ሲሆን የሚያለማው ደግሞ ወረዒሉና ለገሂዳ ወረዳዎች ላይ ይሆናል፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአማራ ክልል የመቼላ፣ የሽንፋ፣ አንገረብ እና ተላ የመስኖ ልማት ጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

23 Dec, 07:58


የማኩዌይ እና መቼላ መስኖ ልማት የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ሪፖርት ግምገማ ተካሄደ፡፡
ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የማኩዌይ እና መቼላ መስኖ ልማት የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች የአዋጭነት ጥናት ሪፖርት ግምገማ ከታህሳስ 11-13 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የማኩዌይ መስኖ ልማት የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት በጋምቤላ ክልል ማኩዌይ ወረዳ እንዲሁም የመቼላ መስኖ ልማት የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ፣ ለገሂዳና ወረዒሉ ወረዳዎች እየተሠራ ነው፡፡
በአዋጭነት ጥናት ሪፖርት ግምገማው ላይ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የአየር ንብረት ሁኔታ፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የመሬትና አፈር ሁኔታ፣ አካባቢያዊ ሁኔታዎችና ፋይናንሺያል ጉዳዮች ቀርበው ውይይት የተካደባቸው ሲሆን የተወሰኑ ማስተካከያዎች ተደርገው ለዝርዝር ጥናት እንዲቀርቡም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

06 Dec, 07:08


የምርታማነት ማሳደጊያና የተማሩ ወጣቶች ሥራ ዕድል መፍጠሪያ ፕሮጀክት በ102.65 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እየተተገበረ ይገኛል፡፡
ሕዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም
የምርታማነት ማሳደጊያና የተማሩ ወጣቶች ሥራ ዕድል መፍጠሪያ ፕሮጀክት (ፔሳፔ) በ102.65 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እየተተገበረ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከአፍሪካ ልማት ባንክ 46.8 ሚሊዮን ዶላር እአአ ከ2021-2026፣ ከአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት (BADEA) 50 ሚሊዮን ዶላር እአአ ከ2024-2029፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት 5.25 ሚሊዮን ዶላር እና ከኮሪያ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትብብር ትረስት ፈንድ (Korean Africa Economic Cooperation Trust Fund) 598,859 ዶላር በትግበራ ላይ ይገኛል፡፡
ፕሮጀክቱ በ3,000 የተማሩ ወጣቶች የሚተገበር ሆኖ እነዚህ ወጣቶች ለሌሎች 25,000 ወጣቶች የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ፡፡
ፔሳፔ ከመስኖ ልማቱ 30,000 አባዎራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን 75,000 ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ፔሳፔ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ በልጪት የመስኖ አውታር 1,425 ሔክታር እና በአዋበል ወረዳ ጣባ የመስኖ አውታር 1,200 ሄክታር በድምሩ 2,625 ሔክታር በአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ፤ በኦሮሚያ ክልል አባያ ወረዳ 1,982 ሔክታር በአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍና 3,000 ሔክታር በአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት (BADEA) በድምሩ 4,982 ሔክታር እንዲሁም በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 5,000 ሔክታር በአረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት (BADEA) በአጠቃላይ ከ12,600 በላይ ሄክታር የሚያለማ ይሆናል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

04 Dec, 09:12


የምርታማነት ማሳደጊያና የተማሩ ወጣቶች ስራ ዕድል መፍጠሪያ ፕሮጀክት(ፔሳፔ) የ2017 በጀት ዓመት 5 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ፡፡
ሕዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም
የፔሳፔ የ2017 በጀት ዓመት 5 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ከአፍሪካ ልማት ባንክ በመጡ ልዑክ አባላት ተገምግሟል፡፡ በግምገማው ላይ የኮንስትራክሽንና ዋተርሼድ ሥራዎች፣ ወጣቶችን የማደራጀት፣ የወሰን ማስከበርና ፋይናንሽያል ጉዳዮች ተዳሰዋል፡፡ ፔሳፔ ድህነትን በመቀነስ፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማሳለጥና ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው ስፍራዎች የሚኖረውን ኅብረተሰብ ኑሮ በማሻሻል በተማሩ ወጣቶች የሚተገበር መሆኑን የፕሮጅክቱ አስተባባሪ አቶ ጌታሰው መኮንን ተናግረዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት የወጣቶችን አቅም በማጎልበት በአጠቃላይ ከ12,600 በላይ ሄክታር ማልማት የሚያስችል መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጌታሰው መኮንን የወጣቶች የአቅም ግንባታ ሥራዎችና የሥርዓተ-ጾታ ተግባራትን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን ከሚሰሩባቸው ፕሮጀክቶች አንዱ የአግሮ-ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርታማነት ማሳደጊያና የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክት (PESAPYE) መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በአማራ፣ በኦሮሚያና በሲዳማ ክልሎች የሚተገበር ሲሆን የግብርና ምርታማነትን በማሳደግና ለኢንደስትሪ ፓርኮች ጥሬ ዕቃ በማቅረብ የሥራ ዕድል መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

04 Dec, 05:30


የአድዓ በቾ የከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታን ለማፋጠን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል፡፡
ህዳር 24/2017 ዓ/ም
ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች አማካሪ ክቡር ዶ/ር እንድርያስ ጌታ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የምስረቅ ሸዋ ዞን እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች የኦሮሚያ ክልል መስኖና አርብቶአደር ቢሮ ም/ኃላፊ እንዲሁም የሥራ ተቋራጭና አማካሪ ድርጅት የስራ ኃላፊዎች ፕሮጀክቱ የሚከናወንበት ወረዳ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለቤትነት የአድዓ በቾ የከርሰምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ግንባታን ለማፋጠን የምክክር ወርክ ሾፕ ዛሬ ህዳር 24/2017 ዓ/ም ተካሂደዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ በምክክር ወርክሾፑ ውይይት ወቅት እንዳሉት የአድዓ በቾ የከርሰ ምድር ውሃ መስኖ ልማት ፕሮጀክት በብዙ ነገሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ማሳያ ይሆናል ተብሎ እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ስለሆነም ከዚህ ፕሮጀክት ስኬት ተነስተን በሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋትን ታሳቢ ያደረገ ፕሮጀክት ነው፡፡ፕሮጀክቱ የሚከናወንነበትን አካባቢ ተጠቃሚ ከማድረግ አልፎ ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎችንም ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል ነው፡፡
በተጨማሪም ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የፕሮጀክቱን ግንባታ ለማፋጠን ሁሉም ባለድርሻ አካላት 24 ሰዓት ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ በቅንጅት መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የመሰረተልማት ፕሮጀክቶች አማካሪ ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ ከክልል እስከ ወረዳ ደረጃ በቅንጅት የሚሰራ እስትሪንግ ኮሚቴና የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ በአስቸኳይ ወደ ስራ በመግባት ለስራ ተቋራጩና ለአማካሪ ድርጅቱ ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር እንደዚሁም ስለፕሮጀክቱ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡
የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ 91.7 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከደቡብ ኮሪያ ኤግዚም ባንክ በአነስተኛ ወለድ የተገኘ ብድር ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ ሲጠናቀቅ 4995 ሄክታር በመስኖ ማልማት ያስችላል፡፡
የፕሮጀክቱ ግንባታ የሚያካትታቸው ስራዎች የክርሰ-ምድር ውሃ መስኖ ልማት፣ የመስኖ ልማት ፋሲሊቲ ተከላ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከልና ተያያዥ ፋሲሊቲዎች፣ የአግሮ- ፕሮሰሲንግ ፕላንት ፣ ፓይለት እስማርት የውሃ ማናጅመንት ሲስተም ፣ የግብርና ማሽነሪዎችና ተሸከሪካሪዎች አቅርቦት፣ የህብረተሰብ ድጋፍ ፣ የሙከራ ኦፕሬሽን ለግብርና ማሰልጠኛ ማዕከላትና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፕላንት ናቸው፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

25 Nov, 09:06


የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለአገራዊ መግባባት አስተዋጽዖው የላቀ ነው!
ህዳር 16/2017 ነዓ/ም
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በየዓመቱ ህዳር 29 ይከበራል፡፡ የኢፌዴሪ ህገመንግስት የፀደቀበትና ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ስርዓትን መከተል ከጀመረችበት ከህዳር 29/1987 ዓ.ም ጀምሮ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ይህ ቀን አገራዊ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ባለፉት ዓመታት ሀገራችን ያሳካቸቻው ታላላቅ ስኬቶች ምስከሮች ናቸው፡፡
በየዓመቱ በሚከበረው በዓል ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሚገናኙባቸው መድረኮች ስለሃገራቸው ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አንስተው ይመካከራሉ፣ ይወያያሉ፡፡ ለአንዲት የጋራ ቤታቸው በጋራ መክረው፣ በጋራ ይንቀሳቀሳሉ፡፡
በዚህ ረገድ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ መግባባት፣ በኅብረ-ብሄራዊ አንድነትና መተሳሰብ ካሳኳቸው ስኬቶች የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ቀን ኢትዮጵያውያን በጋራ፣ ለጋራ ጥቅም እጅ ለእጅ ተያይዘው ሃገራቸውን ወደፊት ለማላቅ ቃል የሚገቡበት ብቻ ሳይሆን ድንቅ የብሄር ብሄረሰበችና ህዝቦች ህብረ-ብሄራዊ አንድነት የሚገለፅበት፣ የሚጎለብትበት የሚያብብበት በዚህም ሃገራዊ መግባባትን የምናረጋግጥበት ነው፡፡
የ19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል “አገራዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድት” በሚል መሪ ቃል በሚኒስቴር መ/ቤታችን ህዳር 20/2017 ዓ/ም በሚኒስቴር መ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይከበራል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

21 Nov, 11:52


ቋሚ ኮሚቴው ፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊያሰራ የሚያስችል መዋቅር በመዘርጋት ሪፎርም ማድረጉን በጥንካሬ ተመለከተ
----------------------
ህዳር 11፣ 2017 ዓ/ም፤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የሩብ አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል።

በግምገማው ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሊያሰራ የሚያስችል መዋቅር በመዘርጋት ሪፎርም ማድረጉን ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ ተመልክቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ፈትያ አህመድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የውስጥ አሰራሩን መርምሮ እንዲሁም ፕሮጀክቶች ያሉበትን ሁኔታ መሬት ወርዶ በማየት በመምራት ረገድ አሁን ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕቅድና ሪፖርት መሬት ላይ ባለው እውነታ ልክ ከአፈፃፀሙ ጋር የተናበበ መሆን እንዳለበት ገልጸው ተቋሙ ያስቀመጣቸው ግቦች እና ዕቅዶች ከነአፈፃፀማቸው ግልፅ በሆነ መንገድ በሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው ልታሳውቁ ይገባል ብለዋል።

አክለውም ሚኒስቴር መ/ቤቱ የሃገራችንን የምግብ ዋስትና የማረጋገጥ ተልዕኮ ያለው በመሆኑ የሚጠበቅበትን ውጤት ለማምጣት ቅንጅታዊ አሰራሩን ሊያጠናክር እንደሚገባ ሰብሳቢዋ አስገንዝበዋል።

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የተያዙ ፕሮጀክቶችን በሚፈልገው ልክ ማቀድ እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ነገር ግን ሰህተቶች መቀጠል ስለሌለባቸው ይህን ለማስተካከል ሲባል የአሰራር ስርአቶችን ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ ውጤታማ ስራ መሰራት የሚያስችል አደረጃጀት ፀድቆ ወደ ስራ የተገባበት ሁኔታ መኖሩን ገልፀዋል።
መቀጠል እና መቋረጥ ያለባቸውን እንዲሁም በኮንትራክተር ድክመት ያልተሰሩትን ሳይቶች ወርደው ባደረጉት ክትትል መለየት መቻላቸውን አንስተው፣ በዚህ መልኩ ስራዎችን ለይተው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የማስቀጠል ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት እንዲፈጽም፤ ብሎም ተጠያቂነትን ከማስፈን ረገድ፤ እንዲሁም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎችን በሚፈልገው ልክ እንዲያጠናቅቅ ልዩ የበጀት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ገልጸው ለዚህም የቋሚ ኮሚቴው ድጋፍ ያስፈልገናል ሲሉ ጠይቀዋል።
(የመረጃ ምንጭ፡-የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ)

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

15 Nov, 14:01


የሀገርና የተቋሙን ተልዕኮ የሚረዳና የሚያውቅ፣ መፍጠርና መፍጠን የሚችል፣ ቁርጠኛና ቆሞ ቀር ያልሆነ አመራር እየገነባን ነው ፡፡
ሕዳር 06 ቀን 2017 ዓ/ም
የሀገርና የተቋሙን ተልዕኮ የሚረዳና የሚያውቅ፣ መፍጠርና መፍጠን የሚችል፣ ቁርጠኛ እንዲሁም ቆሞ ቀር ያልሆነ አመራር እየገነባን ነው ሲሉ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ ገለፁ፡፡
የተቋሙንና ሃገርን ተልዕኮ የሚያሳካ እንዲሁም የሀገርን ሀብትና የሰው ሀብትን መምራት የሚችል አርዓያ አመራር መፍጠር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን ምሰሶዎች ናቸው ያሉት ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ ግልጽ ተልዕኮ መስጠትና ውጤት መቀበል፣ ማቀድና መፈፀም፣ የአመራሩን የሥራ ውጤት ቆጥሮ መቀበል፣ በዲሲፕሊን እንዲሠሩና እንዲመሩ ማድረግ፣ ሀብትን በአግባቡ መጠቀም፣ አላስፈላጊ ወጪዎችን መቀነስ ከአመራሩ የሚጠበቅ ውጤት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
አነስተኛ መስኖን መምራትና ወደ ተግባር ማስገባት እንዲሁም የመስኖ መሠረተ ልማትን ማስተዳደር የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸው የገለጹት ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የጥናትና ዲዛይን ችግሮችን በአደረጃጀት፣ በአሠራርና በአመራር ለማስተካከል እየሠራን ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሳይንሳዊ አሠራርን ተከትሎ የሚሠራ ነው፤ የመስኖ መሠረተ ልማትን ማጥናት ዲዛይን ማድረግ እና ማስተዳደር ዋነኛ ሥራዎቻችን ናቸው፤ በመሆኑም ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጥራት የጊዜ ገደብና በጀት እንዲጠናቀቁ ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡
በአዲሱ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አወቃቀር ዙሪያ ከተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየት የቀረበላቸው ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ ተቋሙ ከፍተኛ የመንግሥት በጀት ተይዞለት የሚሠራና የኢንተርፕራይዝ ባህሪ ያለው በመሆኑ አመራሩና ባለሙያው በቅንጅት መሥራት ይኖርብናል፤ በአዲሱ አወቃቀር የአሠራር ሥርዓትን ተከትለን የሙያ የትምህርት ዝግጅት የሥራ ልምድ እና የፈጻሚው ዲሲፕሊን የሥራ ተነሳሽነትንና ስብጥር መሠረት በማድረግ ምደባ መደረጉን ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

15 Nov, 13:41


የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካትና ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅና ለማስተዳደር አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ተደር¹ል፡፡
ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም
ክቡር ዶ/ር አብርሃም  በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር  ሚኒስትር በመዋቅር ማሻሻያው  አዲስ ለተመደቡት መካከለኛ አመራሮች  የወደፊት የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አነስተኛ፣ መካከለኛና ትላልቅ የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት የሀገሪቱን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እየሠራ ሲሆን የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካትና ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅና ለማስተዳደር አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ ተሰርቶ አዲስ ለተመደቡ መካከለኛ አመራሮች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው ፡፡
አዲስ የተሰራው ተቋማዊ አደረጃጀት የመስኖ ልማት እንዲስፋፋ፣ የዘርፉ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎች በአግባቡ እንዲተገበሩ፣ በፌዴራል መንግሥት በጀት የተገነቡ ግድቦችና የውኃ ውቅሮችን ማስተዳደር እና ሌሎች ለሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአዋጅ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ዕውን ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
አዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ለማስተዳደርና የጥገና ሥራዎችን በራስ አቅም ለማከናወን፣ የቆላማና አርብቶአደር አካባቢ መስኖና ውኃን መሠረት ያደረጉ ሥራዎች ላይ ትኩረት ለመስጠት፣ የመስኖ ፕሮጀክቶች ከቅድመ ጥናት እስከ ዝርዝር ዲዛይን ዝግጅት የጥራት ደረጃን ለማስጠበቅ የተጀመሩና ሊጀመሩ የታቀዱ የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘው የግንባታ የጊዜ ገደብ ጥራት እና በተያዘላቸው በጀት ለማጠናቀቅ እንዲሁም የመስኖ መሰረተ ልማትን ለማስተዳደር ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሦስት ስትራቴጂካዊ የትኩረት መስኮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ ሲሆን አነርሱም  የመስኖ ልማት ዘርፍ፣ የምርምር ልማት ዘርፍና የአመራርና አስተዳደር ዘርፎች ናቸው፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

14 Nov, 14:32


የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት  በማል መሪ ቃል የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አደረጉ፡፡
ሕዳር 05 ቀን 2017
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች ጋር በዛሬ ዕለት  የህልም ጉልበት. ለእመርታዊ እድገት በሚል  መሪ ቃል የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አነስተኛ፣ መካከለኛና ትልልቅ የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት የሀገሪቱን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እያደረገ ባለው ከፍተኛ ርብርብ የተቋሙ አመራርና ሠራተኞች በቅንጅት እንዲሰሩ ታላሚ ተደርጎ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች መካከለኛ አመራሮችና ሠራተኞች ላነሷቸው ሃሳብና አስተያየቶች በከፍተኛ አመራሩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

13 Nov, 10:57


የምርታማነት ማሳደጊያና የተማሩ ወጣቶች ስራ ዕድል መፍጠሪያ ፕሮጀክት(ፔሳፔ) በ2017 በጀት ዓመት መጨረሻ ከ1,070 በላይ ሔክታር መሬት ለመስኖ ልማት ዝግጁ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡
ጥቅምት 04 ቀን 2017 ዓ.ም
በአማራ ክልል በፔሳፔ ፕሮጀክት እየተገነቡ ያሉት የጣባና በልጪት ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ልማት እንዲገቡና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ በፕሮጀክቱ ባለቤት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በኪም ኤፍ ሲ የውሃ ስራዎች አማካሪ ደርጅት በአያለው አዲሱ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ዮሴፍ  ተከተል  ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ድርጅቶች መካከል የሶስትዮሽ ስምምነት ፊርማ ተካሂዷል፡፡
ስምምነቱ በበጀት ዓመቱ በሶስትዮሽ የጋራ ሥራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 500 ሔክታር በጣባ እና 572 ሔክታር መሬት በበልጪት ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ከ1,070 በላይ ሔክታር መሬት ለመስኖ ልማት ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ በሶስትዮሽ ስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልፀዋል፡፡
በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሮጀክቶች በፍጥነት ተጠናቀው ወደ ልማት እንዲገቡ ሁላችንም የራሳችንን ድርሻ መወጣት አለብን ያሉት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ በአማካሪ ድርጅቱም ሆነ በሥራ ተቋራጮች በኩል እንደ ችግር የተነሱ ጉዳዮችን  በመለየት መፍትሔ ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
በጣባ እና በልጪት ፕሮጀክቶች የግብዓት አቅርቦትና የወሰን ማስከበር ችግሮችን ለመፍታት ተቀናጅተን መሥራት አለብን ያሉት የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ ዋናውን የግድብ ሥራ በፍጥነት በማጠናቀቅ ውኃ እንዲይዝና ለመስኖ ልማት ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡
የፔሳፔ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ጌታሰው መኮንን በበኩላቸው የወሰን ማስከበር ችግሮች እንዳይፈጠሩ እስከ ወረዳ ድረስ የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ  ከፍተኛ የንቅናቄ ሥራ መሠራቱን ገልጸው መሰል ችግሮች እንዳይከሰቱ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነቱን በአግባቡ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

13 Nov, 07:37


የምርታማነት ማሳደጊያና የተማሩ ወጣቶች ስራ ዕድል መፍጠሪያ ፕሮጀክት በአማራ ክልል ለተማሩ ወጣቶች የሥራ ዕድልን በመፍጠር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡
ሕዳር 04 ቀን 2017 ዓ.ም
የምርታማነት ማሳደጊያና የተማሩ ወጣቶች ስራ ዕድል መፍጠሪያ (የፔሳፔ) ፕሮጀክት በአማራ ክልል ለተማሩ ወጣቶች የሥራ ዕድልን በመፍጠር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ህዳር 3/2017 ዓ/ም  ከአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ከምስራቅ ጎጃም ዞን መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ፅ/ቤት ከደጀንና አዋበል ወረዳዎች ከአማካሪ ድርጅትና ስራተቋራጮች እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ስለፕሮጀክቱ ውይይት በተደረገበት ወቅት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ ገለጹ፡፡
በፔሳፔ ፕሮጀክት በአማራ ክልል እየተገነቡ ያሉት የጣባና በልጪት ፕሮጀክቶችን ለማጠናከር የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርገው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመመካከር ችግሮችን በመፍታት አፈጻጸሙን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው ፕሮጀክቱ በሚገነባባቸው አካባቢዎች የወሰን ማስከበር ሥራን ማሳለጥ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡
በአማራ ክልልም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሥራ አጥነት ችግሮች አሉ፤ ፔሳፔ የሥራ ዕድልን በመፍጠር ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው በመሆኑ በ1ኛ ሩብ ዓመት ግምገማ የታዩ ድክመቶችን በመቅረፍ ሥራ ተቋራጩና አማካሪ ድርጅቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡
በፕሮጀክቱ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው የተማሩ ወጣቶች የሚያመርቱት ምርት ከአግሮ ኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ በመፍጠር እንዲሁም የአካባቢውን ማህበረሰብ በመደገፍ ከፍተኛ ፋይዳ አለው ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው  ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ ተናግረዋል፡፡
የጣባና በልጪት ፕሮጀክት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በአማካሪ ድርጅቱና በስራ ተቋራጩ በኩል የተነሱ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

09 Nov, 06:01


ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር ሚኒስትር ለሶስት ቀናት የቆየ የስራ ጉብኝት  በሶማሌ ክልል አካሂደዋል ::


በጉብኝታቸው ወቅት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተሰሩ የሚገኙትን የጎዴ የመስኖ መሰረተልማት ግንባታ ፕሮጀክት : በጎዴ ከተማ እየተገነባ ያለው ሞዴል የአርብቶአደር ዘመናዊ መኖርያ መንደር እና በሸቤሌ ዞን እየተሰራ የሚገኘውን በአነስተኛ ወጪ የሚገነቡ የመኖርያ ቤት ግንባታ ስራዎችን የስራ ላይ ግምገማ አካሂደዋል ::

ክቡር ሚንስትሩ  ከጉብኝታቸው ጎን ለጎን ከክልሉ አመራሮችና ከፍተኛ የፕሮጀክቶች አስፈጻሚ ሀላፊዎች ጋር ባደረግዋቸው ውይይቶች ዘርፈብዙና የተቀናጀ የልማት እንቅስቃሴ ትግበራ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ፈጥኖ ከማረጋገጥ ባሻገር ክልሎቻችን የታቀፋትን ሰፊ የልማት አቅም ማሳየት እንደሚችሉ ጠቅሰው አመራሩ በእውቀትና የተለየ ትጋት የሚያደርገውን ርብርብ አጠናክሮ እንዲቀጥል አበረታተዋል።

በውይይቶቹ ማብቂያ ላይም በሶስቱም ፕሮጀክቶች ስር የተካተቱ ቀሪ ስራዎችን በቀጣይ ሁለት ወራት ማጠናቀቅ የሚያስችል ዝርዝር የስራ እቅድን  በማጽደቅ ተጨማሪ  የስራ መመርያዎችና እና  አቅጣጫዎችንም  አስቀምጠዋል ::

ከዚህ ጎን ለጎን በሶማሌ ክልል እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር እና የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴዎችንም ከክልል አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ክልሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን እና የመሰረተልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት የመፈጸም የተሻሻለ ልምድ የተለየ ትኩረት ሊሰጥበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ::

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

06 Nov, 03:35


የሶስትዮሽ የስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሄደ
ጥቅምት 27/20-17 ዓ/ም
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ምርታማነትን ማሳደግ ለአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ድጋፍና የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት የኦሮሚያ ጊዳቦ ፕሮጀክትን የግንባታ ሂደት ለማፋጠን የሶስትዮሽ ስምምነት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በፋክት አማካሪ ድርጅት እንዲሁም በቤርሻኮን ስራ ተቋራጭ ድርጅት መካከል ጥቅምት 26/20-17 ዓ/ም ተፈርመዋል፡፡
የሶስትዮሽ የስምምነት ፊርማውን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ የፋክት አማካሪ ድርጅት ኃላፊ አቶ ታከለ ሂቃ እንዲሁም የቤርሻኮን ስራ ተቋራጭ ድርጅት ኃላፊ አቶ ውብሸት አወል ፈርመዋል፡፡
የምእራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ አዱላ ህርባይ የኦሮሚያ ክልል የመስኖና አርብቶአደር ልማት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከተማ ኡርጋ የአባያ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ በምስክርነት በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ፈርመዋል፡፡
የሶስትዮሽ ስምምነት ፊርማ ስነስርዓት ከመካሄዱ በፊት የኦሮሚያ ጊዳቦ ፕሮጀክት አሁናዊ ሪፖርት ቀርቦ በተደረገው ውይይት ስራ ተቋራጭ ድርጅቱ በ2017 በጀት ዓመት 853 ሄክታር በማጠናቀቅ ለመስኖ ልማት ዝግጁ እንደሚያደርግ ተገልፀዋል፡፡
የፕሮጀክቱ የፋይናንስ ምንጭ የአፍሪካ ልማት ባንክ ነው፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

05 Nov, 12:57


ምርታማነትን ማሳደግ ለአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ድጋፍና የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት የሶስትዮሽ ስብሰባ እየተካሄደ ነው
ጥቅምት 26/20-17 ዓ/ም
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ምርታማነትን ማሳደግ ለአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ድጋፍና የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክት /Productivity Enhancement Support to the Integrated Agro-Industrial parks and Youth Employment (PESAPYE)Project/ የሶስትዮሽ ስብሰባ ዛሬ ጥቅምት 26/2017 ዓ/ም እየተካሄደ ነው፡፡
በሶስትዮሽ ስብሰባው ላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ& የምእራብ ጉጂ ዞን ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ አዱላ ህርባይ የኦሮሚያ ክልል የመስኖና አርብቶአደር ልማት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከተማ ኡርጋ የምእራብ ጉጂ ዞን አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች& የአባያ ወረዳ አስተዳደር አመራሮች የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የፋክት አማካሪ ድርጅት እንዲሁም ቤርሻኮን ስራ ተቋራጭ ድርጅት ተገኝተዋል፡፡
የውይይቱ ዋና ዓላማ የኦሮሚያ ጊዳቦ ምርታማነትን ማሳደግ ለአግሮ ኢንደስትሪ ፓርኮች ድጋፍና የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክትን ግንባታ ሂደትን ለማፈጠን በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መግባባት ለመፍጠር ነው፡፡
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በግብርናና ኢንደስትሪ መካከል ትስስር የሚፈጥር ሲሆን በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚደገፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ የፕሮጀክቱን የግንባታ ሂደትን ለማፋጠን የምዕረብ ጉጂ ዞን እስተዳደር የአባያ ወረዳ አስተዳደር እንደዚሁም የአካባቢው ህብረተሰብ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ለአካባቢው እንደስትሪ ግብዓት ለማቅረብ እንዲሁም ለተማሩ ወጣቶችና የአካባቢው ህብረተሰብ የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ያለበት ደረጃ በፋክት አማካሪ ድርጅት ይቀርብና ውይይት በተሳታፊዎች ይደረጋል፡፡በተጨማሪም የሶስትዮሽ (የፕሮጀክት ባለቤት& የአማካሪ ድርጅትና የስራ ተkራጭ ድርጅት ) የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓት ይካሄዳል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

31 Oct, 18:03


በዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር የተመራ የአመራር እና ሙያተኞች ቡድን ዛሬ በምስራቅ ወለጋ ፣ በጅማ እና በበኖ በደሌ ዞኖች እየተከናወኑ ያሉትን ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በስፍራው ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

በሶስቱም ዞኖች የሚያርፈው እና ከ80,000 ሄክታር በላይ በመስኖ የማልማት አቅም ያለው የአርጆ ደዴሳ የመስኖ ፕሮጀክት ስራው የደረሰበት ደረጃ እና ቀሪ ስራዎቹ በቀጣይ ሁለት አመታት ማጠናቀቅ የሚቻልበትን ሁኔታ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በስፋት ተወያይተዋል።

ክቡር ሚንስትሩ ዶ/ር አብርሃም በጉብኝቱ ወቅት ባደረገት ንግግር  ይህ ፕሮጀክት ተቋሙ ከሚያስገነባቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ በሚያለማው የመሬት ስፋት የመጀመርያው ቢሆንም  ከአስር አመታት በላይ የተራዘመ በመሆኑ   የታለመለትን የመስኖ ልማት ጥቅም መስጠት ሳይችል በአከባቢው ማህበረሰብ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ  ሲነሳ መቆየቱን አስታውሰው ተቋሙ
ለረዥም አመት ሳይጠናቀቁ የቆዩ ፕሮጀክቶችን  በፍጥነት ለመጨረስ እንደ መንግስት  በተሰጠው ልዩ  ትኩረት እና አመራር ስራው ወደ ተሻለ እንቅስቃሴ የገባበት ሁኔታ መፈጠሩን በአበረታችነት አስታውሰዋል ::

ክቡር ሚኒስትሩ ከዚህ በተጨማሪ በበኖ በደሌ እና በጅማ  ዞኖች ያሉ የቡና ምርት : የሻይ ቅጠል ልማት እና የከተማና የገጠር ኮሪደር ስራዎችን ጉብኝት አድርገዋል::

ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው  ህዝቡ የልማቱ ዋና ባለቤት መሆኑን እንዲሁም በአርሶአደሩ እና በባለሃብቶች የሚሰሩ አስደናቂ ስራዎች ማየት መቻሉን ጠቅሰው  እያንዳንዱ ነዋሪ ከኮሪደር ልማቱ ጋር  ተናባቢ በሚሆን መልኩ ስራዎችን እየሰራ ያለ መሆኑን በማየታቸው መደሰታቸው እና ይህንን እየመሩ የሚገኙ የክልል እና የዞን አመራሮች ባሳዩት ተግባር መርካታቸውን ገልጸዋል።

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

31 Oct, 13:20


የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መቅረፍ የምንችለው ምርታማነትን በመጨመር ነው፡፡

ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መቅረፍ የምንችለው ምርታማነትን በመጨመር ነው፤ ለዚህም የንግድ ስርዓቱን ማዘመን ከፍተኛ ፋይዳ አለው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡ የኑሮ ውድነቱ እጅ አጠር ዜጎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር መንግስት ከ300 እስከ 400 ቢሊዮን ብር የድጎማ በጀት መድቧል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕድ ማጋራት፣ ትምህርት ቤት ምገባ እና እሁድ ገበያ መንግስት አቅመ ደካሞችን ለማገዝ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ብለዋል፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም 249 ሺህ አቅመ ደካማ ዜጎች መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ተደርጓል፤ ይህ መንግስት ባለሃብቶችን በማስተባበር ያከናወነው ስራ ነው በማለትም አብራርተዋል፡፡ የዋጋ ንረቱ አሁን ላይ ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፤ ይህን ወደ ነጠላ አሃዝ ማውረድ የመንግስት ቀዳሚ ትኩረት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በቀይ ባህር ላይ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዚህ ጉዳይ ወደ ኋላ የማይል ይፋዊ አቋም አለን፤ ነገር ግን ይህን ለማሳካት ጦርነትም ሆነ የኃይል አማራጭ አንፈልግም፤ ፍላጎታችንን ማሳካት የምንሻው በሰላማዊ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ምክንያታዊና ፍትሃዊ ጥያቄ ነው፤ እኛ ባናሳካው ልጆቻችን ያሳኩታል በማለት በዛሬው የፓርላማ ውሎ ላይ ተናግረዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

31 Oct, 12:54


"የሀገራዊ ምክክርን ዕድልን በአግባቡ መጠቀም ይገባል"
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጥቅምት 21/2017 ዓ/ም
የሀገራዊ ምክክር እድልን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡
እድልን አለመጠቀ ኢትዮጵያን ጎድቷታል። እያፈረሱ መስራት፣ እድልን አለመጠቀና መቆዘም የኢትዮጵያን ችግር ነው ያሉት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገራዊ ምክክር አሁን ላይ የተሰጠን እድል ነው ሲሉ ብለዋል።
በመሆኑም ይህን ዕድል በአግባቡ በመጠቀም ለሀገር ሰላም መሥራት ይገባል። ያለፉ ስህተቶችን በመረዳት አሁን ላይ ለችግሮች መፍትሔ ማበጀት ይገባል ብለዋል።
ከፋፋይ የሆኑ ሀሰቦችን እያጠፉ ሰብሰብ ማለት እንደሚያሰፈልግ ጠቅሰው፣የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣የእምነት ተቋማት፣ ሚዲያዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰብሰብ ለማለት የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት የጋራ ህልም መፍጠር ይገባል። ይህም ከአንድ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ከአንድ ትውልድ ይሻገራል ብለዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

31 Oct, 11:15


የመገጭ መስኖ ልማት ግድብን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ 7 ቢሊዮን ብር መድበን ቀን ከሌት እየገነባን ነው፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም
የመገጭ መስኖ ግድብን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ 7 ቢሊዮን ብር መድበን ቀን ከሌት እየገነባን ነው ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል ከየትኛውም መንግስት በላይ አሁን ያለው መንግስት በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወን ነው፤ በክልሉ ታላላቅ የመንገድ፣ የኢንዱስትሪ፣ የቱሪዝም ልማቶች እንዲሁም በዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ሲሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል፡፡
የፋሲል ቤተ-መንግስት እየታደሰ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክልሉን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነውም ብለዋል፡፡ ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን፤ መንግስት ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ ቅድሚያ ሰጥቶ ሰርቷል፤ አሁንም ያለን አቋም የትኛውም አይነት አለመግባባት በሰላም እንዲፈታ ነው፡፡ ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛ ነው ሲሉ በአማራ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አብራርተዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

31 Oct, 08:19


30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1.4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ጥቅምት 21/ 2017 ዓ/ም
በ2016 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ 8.1% ኢኮኖሚያዊ እድገት መመዝገቡን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ስኬት ነው፤ በዘንድሮው በጀት ዓመትም 8.4 % እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ ግብርና 6.1 % እንደሚያድግ የሚጠበቅ ሲሆን፤ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1.4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ ዘርፎች ሀገራዊ ሪፎርም ሲከናወን መቆየቱን የተናገሩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፎርሞችን አጠናቀን ሀገራዊ ማንሰራራት የምንጀምርበት ዘመን የመጀመሪያ ምእራፍ ላይ ተገኝተናል፤ በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ የምናስመዘግብ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ ከትናንት እሳቤ ወጥተን በጋራ ወደ ነገ መሻገር አለብን ብለዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት ከፍተኛ ስራ መከናወኑን አክለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለይ ከኃይል አቅርቦት ጋር ተያይዞ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የተሻለ ስራ የተከናወነ ሲሆን፤ አሁን ላይ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 67 % ማድረስ ተችሏል፡፡ የኢንዱስትሪ ዘርፉም በተያዘው በጀት ዓመት 12.8 % እንደሚያድግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

29 Oct, 12:05


https://www.facebook.com/PMOEthiopia/videos/511244908410626/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

29 Oct, 07:23


ሚኒስቴሩ የምርምር ቢሮና ሰርቶ ማሳያ ማዕከላትን ሟቋቋም እንዳበት ተጠቆመ፡፡
ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የምርምር ቢሮና ሰርቶ ማሳያ ማዕከላትን ካቋቋመ በተለምዶ የሚሰሩ ሥራዎችን ለማስተካከል እንደሚያግዘው በጥናትና ምርምር ዙሪያ ልምዳቸውን ለማካፈል ስልጠና የሰጡት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ወርቁ አስራቴ ይናገራሉ፡፡
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የምርምር ቢሮና ሰርቶ ማሳያ ማዕከላትን በማቋቋም ከሌሎች አቻ መ/ቤቶች ጋር በመቀናጀት መስኖ፣ አርብቶአደርና ቆላማ አካባቢን እንዲሁም ግብርናን ማዕከል ያደረገ የምርምር ማዕከል ፎረም በማቋቋም ለዘርፉ ዕድገት፣ ልምድና ተሞክሮዎችን ለመጋራት ያግዛል የሚሉት ዶ/ር ወርቁ አስራቴ ምርምርን ማስፋፋት፣ ማሳደግና ማጎልበት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ነው፤ ምርምር በራሱ አዳዲስ ሀብቶችን ለማወቅ፣ ለመለየትና ለመጠቀም ያግዛል ሲሉ ያብራራሉ፡፡
በሌላ በኩል በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ፣ አርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ ምርምር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዓለማየሁ ሳህሌ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን ያሉትን ሀብቶች በሳይንሳዊ መንገድ በጥናትና ምርምር ለይቶ መጠቀም ለነገ የማይባል የዛሬ የቤት ሥራችን ነው፤ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ ማሳደግ ላይም አበክረን እንሠራለን በማለት ይገልጻሉ፡፡
በመስኖ ዘርፍም ሆነ በአርብቶአደርና ቆላማ አካባቢ ልማት ላይ የዕውቀት ሽግግር እንደሚያስፈልግ የሚናገሩት አቶ ዓለማየሁ ሳህሌ የምንሰራቸው የጥናትና ምርምር ሥራዎች የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ፣ የአካባቢ ጥበቃና የኢኮኖሚ ልማት ትኩረት ያደረጉ እንዲሆኑ በማስቻል ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት ያግዘናል በማለት ሃሳባቸውን ያጠቃልላሉ፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

28 Oct, 17:32


#MILLs #USAID #PLRA #PolicyLINK #Lowlands
The 3-day Federal Multi-Stakeholder Coordination Platform for the Partnership for Lowlands Resilience Activity (PLRA) was officially kicked-off today by Pastoralist Elders and H.E. Dr. Endrias Geta Beldeda, State Minister of the Lowlands Research and Development Sector.
------

Funded by USAID, the Partnership for Livelihoods Resilience Activity (PLRA), part of the Champions for Food Security Activity #C4FS, aims to strategically plan and coordinate resilience initiatives to strengthen the resilience capacity of lowland communities. The project fosters a cohesive, impactful approach to building resilience among households, communities, and institutions in our country’s lowland areas.

PLRA is being implemented in four regions: Somali, Afar, Oromia, and South Ethiopia; across 12 pilot woredas. The project engages with regional, woreda, and federal government levels, development partners, the private sector, CSOs, and communities in lowland and pastoral areas.

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

21 Oct, 05:54


የሀዘን መግለጫ!
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ፕሮጀክቶች ዝግጅት መሪ ሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቀድሞ የመስኖ ልማት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር የነበሩት ኢንጂነር ሳሙዔል ሁሴን ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 9/2017 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች በኢንጂነር ሳሙዔል ሁሴን ሕልፈተ ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ፣ ለዘመዶቹና ለጓደኞቹ መፅናናትን እንመኛለን ፡፡

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

20 Oct, 15:56


https://www.facebook.com/100069403920568/posts/859727333017390/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

18 Oct, 07:47


በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡
**************************
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡ ከሥራዎቹ መካከልም የዳል ወንዝ መካከለኛ ድልድይ ግንባታ፣ የኪሉ አነስተኛ መስኖ ተቋም ግንባታ፣ የባቹማ ጨበራ የጠጠር መንገድ ግንባታ፣ የባሮ እና የቢያጌሊች የወፍጮ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ሥራ፣ የግጦሽ ማሻሻያ እና እንስሳት መኖ ልማት ስራዎች፣ የ1ኛ ደረኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ግንባታ፣ የሞዴል አርብቶ አደሮች የዶሮ እርባታ ሥራዎች፣ በሞዴል አርብቶ አደሮች በፕሮቲን የበለጸጉ ሰብሎች (የሥራስር፤ የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ) ሥራዎች ይገኙበታል፡፡
በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት (LLRP) ለአካባቢው ማህበረሰብ የገበያ ትስስር በመፍጠር የማህበረሰቡን ቁርኝት ከማሳደጉም ባሻገር በመስኖ የተለያዩ ሰብሎችን እንዲያመርት በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ለወጣቶች እና ለሴቶች የስራ እድልና የገቢ አማራጮ እየፈጠረ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ የተሻሻሉ የእንስሳት መኖዎችን በማልማት እንዲሁም የተጎዱ መሬቶችን በመጠበቅ የእንስሳት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የት/ቤቶች ተደራሽነት በሌለባቸው ቀበሌዎች ጥራታቸውን የጠበቀ ት/ቤቶች በመገንባት ለአርብቶ አደር ልጆች የትምህርት ዕድልን በመፍጠር እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የኅብረተሰቡን ኑሮ የሚያሻሽሉ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡
ጥቅምት 8/2016 ዓ.ም
----------------------------------
Join Our Social Media Community:
Website: https://mills.gov.et
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
X: https://x.com/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

17 Oct, 11:34


የታችኛው ገናሌ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የሎት ሁለት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ተጠናቋል፡፡
**************************
በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ባለቤትነት በሱማሌ ክልል ሊበን እና አፍዴር ዞኖች በዶሎ-ኦዶ እና ዶሎቤይ ወረዳዎች ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን እየተከናወነለት የነበረው የታችኛዉ ገናሌ መስኖ ልማት የጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ፕሮጀክት(ሎት 2) 100% ተጠናቋል፡፡
የፕሮጀክት ጥናቱ ዓላማ የግድብና ተያያዥ ስራዎች እንዲሁም የመስኖ መሰረተ ልማት ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን በማከናወን ለግንባታ ዝግጁ ማድረግ ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ጥናት የሚካሄደው የታችኛው ገናሌ ወንዝን ፍሰት በመመጠን 38 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታሳቢ የተደረገ ነው፡፡ የታችኛው ገናሌ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ውሃ የሚያገኘው ከገናሌ ዳዋ የሃይል ማመንጫ ግድብ ነው፡፡
ግድቡ የሚያርፍበት ቦታ በታችኛው ገናሌ ወንዝ ላይ ሲሆን የሚገኘውም በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የአገሪቱ አካባቢ ሆኖ በታችኛው ገናሌ ወንዝ ተፋሰስ ውስጥ በሱማሌ ክልል በሊበን ዞን እና በአፍዴር ዞን መካከል ነው፡፡
የፕሮጀክቱ ጥናት የተጀመረው ሰኔ 2013 ዓ/ም ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ሙሉ ለሙሉ በእቅዱ መሰረት ተጠናቋል፡፡
የፕሮጀክቱን ጥናትና ዝርዝር ዲዛይን ያካሄደው ኦሮሚያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ነው፡፡

ጥቅምት 7/2016 ዓ.ም
----------------------------------
Join Our Social Media Community:
Website: https://mills.gov.et
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
X: https://x.com/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

16 Oct, 10:52


የአልዌሮ ግድብ ለታለመለት የመስኖ ልማት ማዋል የሚቻልበትን ሁኔታ ለማየት በዶ/ር አብርሃም በላይ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና በክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ዑምድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የፌደራል እና የክልል አመራሮችና ሙያተኞች ቡድን ጉብኝት አካሂደዋል ::

የአልዌሮ ግድብ ከተገነባ ከሰላሳ አመት በላይ ሲሆን 10,000 ሄክታር በመስኖ ለማልማት ታስቦ የተገነባ ግድብ ነው ::
ሆኖም እስካሁን ድረስ ከ1500 ሄክታር በታች እያለማ የታለመለትን ያክል ምርት ሳይሰጥ መቆየቱን በጉብኝቱ ወቅት ተገልፆል::
የግድቡ የተለያዩ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ በጥልቀት በማጥናት አስፈላጊ የጥገና ስራን በማከናወን ወደ ሙሉ አቅሙ መመለስ እንዲቻል እና ከመስኖ ልማት ጎን ለጎን የአሳ ሃብትን የማልማት ሂደት ለማዘመን እንደሚሰራ ሚኒስትሩ ገልፀዋል ::

---
Join our social media community:
Web: https://mills.gov.et
FB: https://facebook.com/MILLsEthiopia/
X: https://twitter.com/MILLsEthiopia
Telegram: https://t.me/MILLsEthiopia
LinkedIn: https://bit.ly/3PW8TK9

Ministry of Irrigation and Lowlands- Ethiopia

14 Oct, 08:40


17ተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በውይይት ተከብሯል
ጥቅምት 4/2017ዓ/ም
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች 17ተኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሚኒስቴር መ/ቤቱ አዳራሽ በውይይት አክብረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ተስፋዬ ይገዙ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር  ሚኒስትር ዴኤታ፣ ለሃገራችን ክብርና ከፍታ ሁላችንም በተሰማራንበት የሙያ ዘርፍ ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ለሉዓላዊነቷና ለክብሯ ሲሉ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን፣ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንና በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ልጆች ውድ ህይወታቸውን ከፍለዋል፣ አሁንም በመክፈል ላይ ይገኛሉ ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፣ የመንግስት ሠራተኛውና አመራሩ ደግሞ ለመ/ቤቱ ተልዕኮዎች ታማኝ በመሆን ሙሉ ጊዜውን ተጠቅሞ በጥራት፣ በጊዜና በውጤታማነት በመንቀሳቀስ ለሃገሩ አንድነት፣ ሉዓላዊነትና ከፍታ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
አቶ ብዙነህ ቶልቻ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አስመልክቶ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ በብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን አስፈላጊነትና ምንነትን ዜጎች በጥልቀት አውቀው ሌላውም ተመሳሳይ አረዳድ እንዲኖራቸው ውይይት ማስፈለጉን አንስተዋል፡፡
በዕለቱም የቃለ መሃላ ስነስርዓትና  የኢትዮጵያ ህዝብ  መዝሙር  ተዘምሮዋል፡፡
ሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰንደቅ ዓላማ አዋጅ መሠረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር የመጀመሪያው ሰኞ የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ‘’ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል ለ17ተኛ ጊዜ በመላው ኢትዮጵያ ይከበራል፡፡