የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም
በምዕራብ ሸዋ ዞን ኤጄሬ ወረዳ ሃማሮ ቀበሌ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በውይይቱ የ6ኛ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብርጋዲየር ጀኔራል መኮነን በንቲ የሜጀር ጀኔራል ሙልጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል አበበ ዋቅሹማ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዱኛ ብሩ እና የቀበሌው አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ብርጋዲየር ጀኔራል መኮነን በንቲ በአካባቢው የተጀመሩ የሰላምና የፀጥታ ተግባራት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማህበረሰቡ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር የሚያካሄደውን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ተናግረዋል።
የህዝብ ሰላም መሆን እረፍት የሚነሳቸው እንደ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ያሉ እና ከእነርሱ ጋር የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ሆድ አደር የውስጥ ጠላቶችን ህዝቡ ለፀጥታ ሃይሉ አጋልጦ በመስጠት ሰላምን በአካባቢያቸው ማፅናት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
ዘገባው የእዙ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official