*****
(ኢ ፕ ድ)
የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲፒ) የአፍሪካን የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከልን በአዲስ አበባ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ሳሙኤል ዶው
በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጅ ፈጠራ ሥራቸውን ለማጎልበት እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡
የአፍሪካ የቴክኖሎጅ ልህቀት ማዕከልን አዲስ አበባ ለመገንባት ጽኑ ፍላጎት እንዳለው በፊርማ ስነ ስርዓቱ ገልጿል፡፡
ማዕከሉ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ህዳር 12 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክhttps://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et