Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat @ethiopiaorthomazmur Channel on Telegram

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

@ethiopiaorthomazmur


"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ "
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መዝሙሮች ከነግጥሞቻቸው እና ስብከቶች ይሰጡበታል፡፡

For more contact
@eorthomazmur_Bot
👇👇👇👇 For Discussion👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/Fe77ilHyDcn-td_xDU8Tkg

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat (Amharic)

በዚህ ድንግል ሆይ እናቴ! 'አዛኝቱ ዛሬም እናትን ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ' ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን መዝሙሮች እና ስብከቶች ይሰጡበታል፡፡ በዚህ ሳምባና ደምተን በተለይም ድንግል ሆይ እናቴ! በፅሁፍ እና መዝሙር ከእርስዋና ፊት በኋላዬ እንድትወሸው በትክክል እንጠቀማለን ፡፡ አስተዋዅይ ፣ አስተዋዅይ።nnፈቃደ! @eorthomazmur_Botnn👇👇👇👇 For Discussion 👇👇👇👇nnበተለያዩ መጣጥም ቤተክርስቲያቸውን እና ዘርፍቅ የመዝሙር እና ግምት ያስተምራሉ፡፡ ለተጨባሪም መጽሐፍትን፣ ፅሁፉን እና አቶ ብርሀኔን የምጽፍል ተግባራትን ከአፌ አገናኝ፣ ከሚል ድንገት፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እስከ መጋንንት አሰድምም ከፈተና።nnለትምህርት እና ከምስጋናውያን ሆሳችንም የቴሌግራም መረጃዎችን በቀላሉ ያንብቡት፡፡nnhttps://t.me/joinchat/Fe77ilHyDcn-td_xDU8Tkg

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

24 Aug, 17:44


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ  
          #JOIN #OUR #CHANNEL  
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

21 Aug, 13:51


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ  
          #JOIN #OUR #CHANNEL  
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

15 Aug, 20:34


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ  
          #JOIN #OUR #CHANNEL  
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

05 Aug, 20:10


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ  
          #JOIN #OUR #CHANNEL  
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

25 Jul, 20:38


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ  
          #JOIN #OUR #CHANNEL  
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

25 Jul, 20:24


#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ  
          #JOIN #OUR #CHANNEL  
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
👉 @ethiopiaorthomazmur 🙏  
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

25 Jul, 19:52


ቅዱስ ገብርኤል
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ  አምላክ አሜን!!
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟
ገብርኤል (ቅዱስ ገብርኤል) 
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡

ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቅዱሳን ሰማእታት ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡

ከግብሩ በመነሳትም የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ለቅዱስ ገብርኤል ሌሎች የተፀውኦ ስሞችን ሰተውታል፡፡ ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ:-

1ኛ - ብስራታዊው (አብሳሪው) መልአክ - እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትን አብስሮአልና፡፡

2ኛ - የአርባብ አለቃ -
3ቱ አለመ መላእክት እየተባሉ የሚጠሩት ኢዮር ራማ ኤረር የየራሳቸው ክፍል ሲኖራቸው በራማ ካሉት 3 ክፍሎች (የመላእክት ከተሞች) አንዱ አርባብ እየተባለ የሚጠራው ሲሆን የዛ አለቃ ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

3ኛ - ጽኑው መልአክ -
"ንቁም በበኅላዌነ እስከ ንረከቦ ለአምላክነ" በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ጸንተን እንቁም በማለት መላእክትን አጽንቶአቸዋልና፡፡

4ኛ - ተራዳዩ መልአክ -
ዳን 3÷19-27፣ ዳን 8÷15 ፣ ዳን 9÷21 – 27

5ኛ - ሊቀ መላእክ -
ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነውና


ሐምሌ 19

  ቅዱስ እየሉጣንና ልጇ ህፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ያዳነበት እለት ነው፡፡ ገድሉ የተፈፀመው በዘመነ ሰማዕተት ነው፡፡ በወቅቱ ቂርቆስና ኢየሉጣ የሚባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ቅዱሳን ነበሩ፡፡ ቅዱስ ቂርቆስ ሀገሩ ሮም አንጌቤን ነው አባቱ ቆዝምሶ ይባላል እናቱ ኢየሉጣ በትውልዷ ከአዝማደ ነገስት ነች፡፡

     ዲዩቅልጥያኖስ በነገሰ በ20ኛው ዓመት በክርስቲኖች ላይ ‹‹ቤተክርስቲኖችና ቅዱሳት መጻህፍቶቻቸው ይቃጠሉ፣ ክርስቲያኖችም ይገደሉ!›› የሚል አዋጅ አውጥቶ ነበርና በመፍራት እናት ስለልጇ ስትል ወደ ኢቆንዩን ሸሸች፡፡ መስፍኑ ብሔሩ እለእስክንድሮስ ክርስቶስን ካጂ ለጣኦት ስገጂ አላት፡፡ እርሷ ግን አይን እያለው የማያይ ጆሮ እያለው ለማይሰማ አንተ ለቆምከው ምስል አልሰግድም አለች፡፡ ንጉሱም በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ ቢያስፈራራት ሀሳቧን ልትለውጥ አልቻለችም፡፡
ህፃኑም ቢጠየቅ እንደ እናቱ መለሰላቸው፡፡ እሺ አለማለታቸውን ንጉስ ሲረዳ ለወታደሮቹ በብረት ጋን ውሃ አፍሉ ብሎ አዘዛቸው፡፡ የውሃው ፍላት እንደ ክረምት ነገድጓድ እስኪነድ ድረስ 42 ምዕራፍ ያህል ይሰማ ነበር፡፡ ወደውሃው ሊከቷቸው ባሉ ጊዜ ቅ.ኢየሉጣ ፈራች ነገር ግን አጠገቧ ያለው ህፃን
‹‹ቂርቆስ እናቴ አትፍሪ ዳግመኛ ሞት አንሞትም›› አላት አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል ብሎ አፀናት፡፡ ከዚህ በኋላ በፍፁም ልብ ተያይዘው ከእሳቱ (ውሃ)ገብተዋል፡፡

በዚህ ጊዜ አናንያ አዛሪያ ሚሳኤልን የተራዳ ታላቁና ገናናው መልአክ ቅ/ገብርኤል በመካከላቸው ተገኝቶ የፈላውን ውሃ አቀዝቅዞላቸዋል፡፡ ከውሃ በወጡም ጊዜ ልብሳቸውና ሰውነታቸው አንዳች ሳይሆን ምዕመናን አዩ፡፡ እነርሱ በሚያመልኩት አምላክም አምነው ብዞዎቹ በሰማዕትነት አርፈዋል፡፡
‹‹ቂርቆስ እየሉጣ ያወጣ ከሳት (2×)››
‹‹እኛንም አድነን (2)
ገብርኤል ሊቀ መላእክት››

ከእናታችን ከቅድስት ኢየሉጣና ከሰማዕቱ ቂርቆስ ከታደጋቸው ከቅዱስ ገብርኤል ረድኤት ፍቅር ያሳድርብን፡፡

አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

15 Jul, 18:48


ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተመደቡ!!

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሊቀ ጳጳስ የምዕራብ አርሲ (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲያገለግሉ በቅዱስ ሲኖዶስ መዘዋወራቸው ተገለጸ።

ብፁዕነታቸው የምዕራብ ሸዋ ፣ የሆሮ ጉዱሩ እና ምሥራቅ ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ላለፉት ዓመታት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።

የዝውውሩ ምክንያት ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አዳዲስ የሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት የሚመደቡበት ሀገረ ስብከት ለውጥ የተደረገበት መሆኑን ተከትሎ ነው።

የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ርዕሰ ከተማ ሻሸመኔ ከዚህ ቀደም በሕገወጦቹ አካላት በተደረገ ሢመት ቁጥራቸው ከ70 በላይ የሚሆኑ ምዕመናን ሰማዕትነት መቀበላቸው እና ከ450 በላይ የሚሆኑት ምዕመናን ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል።

Via፣ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

     -ETHIO-MEREJA-
   
T.me/ethio_mereja

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

08 Apr, 17:29


ሆሣዕና
‹ሆሣዕና› ስምንተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ሲኾን፣ የሰሙነ ሕማማት መጀመሪያ ነው፡፡ ሆሣዕና ስያሜው በማቴዎስ ወንጌል ፳፩፥፱ ከሚገኘው ትምህርት የተወሰደ ሲኾን ትርጕሙም ‹መድኀኒት ወይም ‹አሁን አድን› ማለት ነው፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ‹‹ሆሣዕና በአርያም›› የሚሉ የአዕሩግ፣ የሕፃናት ምስጋና እየቀረበለት ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ጉዞ ያደረገበት፤ ትሕትናውን የገለጠበት፤ ይህን ዓለም ከማዕሠረ ኃጢአት መፍታቱን በምሳሌ ያስረዳበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ተጽዕኖ›› ተብሎ ከሚጠራው የዐቢይ ጾም መጨረሻ (ዕለተ ዓርብ) እና ከሰሙነ ሕማማት መግቢያ ጀምሮ ያለው ሳምንት ሆሣዕና ይባላል፡፡ የክርስቶስን ነገረ ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤውን ሆሣዕና ተብሎ ዓለምን ማዳኑን የሚናገሩ ቅዱሳት መጻሕፍት የሚነበቡበት፤ አምላካችን ለሰው ልጅ መዳን መከራ መቀበሉና የማዳን ሥራው በሰፊው የሚታወጅት፤ በሰሙነ ሕማማት ለሚያርፉ ምእመናን ጸሎተ ፍትሐት የሚደረግበት፤ ወንጌል በአራቱ ማዕዘን የሚሰበክበት ሳምንት ነው – ሆሣዕና፡፡ ከዚያው አያይዞም ሰሙነ ሕማማት ይቀጥላል፤ ወቅቱም የክርስቶስን ነገረ ሕማሙንና ዓለምን ያዳነበት ጥበቡን የምንሰማበት ሳምንት ነው፡፡ በሞቱ ሞታችንን አጥፍቶ መንግሥቱን እንድንወርስ የፈቀደልን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይኹን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

02 Apr, 11:02


ሰባተኛው ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ›

ሰባተኛው ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ› የሚል ስያሜ ያለው ሲኾን፣ የስያሜው መነሻም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ የተመዘገበው ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ አለቃ ታሪክ ነው፡፡ ኒቆዲሞስ በሦስት መንገድ የአይሁድ አለቃ ነበር፤ በሥልጣን፣ በዕውቀትና በሀብት፡፡ ሰው ሥልጣን ቢኖረው ሀብትና ዕውቀት ላይኖረው ይችላል፡፡ ዕውቀት ቢኖረው ደግሞ ሀብትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ሀብት ቢኖረውም ዕውቀትና ሥልጣን ላይኖረው ይችላል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ሦስቱንም አንድ ላይ አስተባብሮ የያዘ የአይሁድ አለቃ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ወንጌልን ለመማር ከአይሁድ ዅሉ ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ይሔድ ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ ፈሪሳውያን ማመን ባልቻሉበት በዚያን ዘመን ጆሮውን ለቃለ እግዚአብሔር፤ ልቡን ለእምነት የከፈተ ሰው ነው፡፡ ብዙ ሰዎችን እናውቃለን ማለት ከመልካም ነገር ሲከለክላቸው ኒቆዲሞስ ግን ዐዋቂ ሳለ ራሱን ዝቅ አድርጎ፣ እምነት በማጣት የነጠፈችውን የፈሪሳውያንን ኅብረት ጥሎ፣ ሐዋርያትን መስሎ ጌታውን አግኝቶታል፡፡ ጌታችን ዓለምን ለማዳን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በለየባት በዚያች አስጨናቂ ሰዓት፤ ሐዋርያት በተበተኑባት አይሁድ በሠለጠኑባት በዕለተ ዓርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን በድርብ በፍታ ገንዞ የቀበረ፣ እሱን ያገኘ ያገኘኛል ሳይል በድፍረት ከእግረ መስቀሉ የተገኘ ሰው ነው – ኒቆዲሞስ፡፡ ስለዚህም ሰባተኛው ሳምንት በእርሱ ስም ተሰይሟል

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

25 Mar, 20:31


✝️ የዐቢይ ጾም (ስድስተኛ ሰንበት ገብርሔር) ✝️

የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሰንበት

ገብር ሔር (ቸር አገልጋይ) የተሰኘው ሲሆን ይህንን ስያሜ ያገኘበትም ምክንያት ከዋዜማው ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‹‹ገብር ሔር ወገብር ምእመን ገብር ዘአስመሮ ለእግዚኡ፤ ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው፡፡  ገብርሔር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡

ምስባክ     መዝ. 39÷8 

"ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ፡፡ 
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡
 ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ፡፡"


ትርጉም፦ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ለማድረግ መከርሁ፥

 ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው።
 በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህን አወራሁ።

ወንጌል ✝️

ማቴ. 25÷14-30 “መንገድ እንደሚሄድ÷ አገልጋዮቹንም ጠርቶ ሊያተርፉበት ገንዘቡን እንደ ሰጣቸው ሰው እንዲሁ ይሆናልና፤ ለእያንዳንዱ እንደ ችሎታው ለአንዱ አምስት÷ ለአንዱ ሁለት÷ ለአንዱም አንድ ሰጠና ወዲያውኑ ሄደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለውም ሄደ፤ ነግዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቈፈረና የጌታዉን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ጊዜም በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ ተቈጣጠራቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና፡- አቤቱ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ አምስት አተረፍሁ ብሎ አምስት መክሊት አስረከበ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ፡- አቤቱ÷ ሁለት መክሊትን ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ ሌላ ሁለት መክሊትን አተረፈሁ አለ፡፡ ጌታውም፡- መልካም÷ አንተ የታመንህ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንህ ስለ ሆንህ በብዙ አሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለውም መጣና እንዲህ አለ፡- አቤቱ÷ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ÷ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ስለ ፈራሁም ሄድሁና መክሊትህን በምድር ውስጥ ቀበርሁ፤ እንግዲህ እነሆ÷ መክሊትህ፡፡ ጌታውም መልሶ አለው፡- አንተ ክፉና ሰነፍ አገልጋይ÷ እኔ ካልዘራሁበት የማጭድ÷ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ ታውቃለህን? ገንዘቤን ለለዋጮች መስጠት በተገባህ ነበር፤ እኔም ራሴ መጥቼ ገንዘቤን ከትርፉ ጋር በወሰድሁ ነበር፡፡

 ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፤ ይህን መክሊት ከእርሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታልና፤ ይጨምሩለታልም፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን ይወስዱበታል፡፡ ክፉውን አገልጋይ ግን÷ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወደ አለ ጨለማ አውጡት፡፡


ዲያቆን (ምንባብ) ✝️

2ኛ ጢሞ.2÷1-15 ልጄ ሆይ÷ አንተም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በርታ፡፡ በብዙ ምስክሮች ፊት ከእኔ የሰማኸውን ትምህርት ለሌሎች ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች እርሱን አስተምራቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደሚያገለግል በጎ አርበኛ ሆነህ መከራ ተቀበል፡፡ ወደ ሰልፍ የሚሄድ÷ አለቃውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ነው እንጂ የዚህን ዓለም ኑሮ አያስብምና፡፡ የሚታገልም ቢሆን እንደ ሕጉ ካልታገለ አክሊልን አያገኝም፡፡ የሚደክም አራሽም አስቀድሞ ፍሬውን ሊያገኝ ግድ ነው፡፡ ያልሁህን አስተውል፤ እግዚአብሔርም በሁሉ ነገር ጥበብን ይስጥህ፡፡

 በወንጌል እንደምሰብከው÷ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስበው፡፡ ስለ እርሱም እንደ ወንጀለኛ አስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም፡፡ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን ሕይወትና የዘለዓለም ክብር በሰማያት ያገኙ ዘንድ÷ ስለ ተመረጡት ሰዎች በሁሉ ነገር እታገሣለሁ፡፡ ነገሩ እውነት ነው፤ ከእርሱ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፡፡ ብንታገሥም ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው ግን እርሱም ይክደናል፡፡ ባናምነውም እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን መካድ አይቻለውምና፡፡

እንግዲህ ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ÷ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይጠቅም÷ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና፡፡የእግዚአብሔርን ቃል በእውነት አቃንቶ ሲያስተምር እንደማያፍር ሰራተኛ ሆነህ ፣ራስህን የተመረጠ አድርገህ  ለእግዚአብሔር ታቀርብ ዘንድ ትጋ።  


ንፍቅ ዲያቆን (ምንባብ) ✝️


 1ኛ ጴጥ.5÷1-11 እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ÷ የክርስቶስም መከራ ምስክር÷ ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግለዎችን እማልዳቸዋለሁ፡፡ በእናንተ ዘንድ ያሉትን የእግዚአብሔርን መንጋዎች ጠብቁ፤ ስትጠብቁአቸውም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ አይሁን፤ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘትም አይሁን፡፡ ለመንጋዉ ምሳሌ ሁኑ እንጂ ሕዝቡን በኀይል አትግዙ፡፡ የእረኞችም አለቃ በተገለጠ ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡ እንዲሁ እናንተ ጐልማሶች ሆይ÷ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ልበሷት፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ያዋርዳልና፤ ራሳቸውን ዝቅ የሚያደርጉትን ግን ያከብራቸዋል፡፡

እንግዲህ በጐበኛችሁ ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርጋችሁ ዘንድ ከጸናችው ከእግዚአብሔር ክንድ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፡፡ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡ እንግዲህ ዐዋቂዎች ሁኑ፤ ትጉም፤ ጠላታችሁ ጋኔን የሚውጠውን ፈልጎ÷ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና፡፡ እርሱንም በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት፤ እንዲህም ያለ መከራ በዓለም በአሉ ወንድሞቻችሁ ሁሉ እንደሚፈጸም ዕወቁ፤ ፍቅርንም አጽንታችሁ ያዙአት፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ልባሞችም ያደርጋችኋል፡፡ለእርሱ ክብርና ኅይል እስከ ዘለአለም ይሁን፤አሜን።

ንፍቅ ቄስ (ምንባብ) ✝️

የሐዋ.1÷6-8 እነርሱም ተሰብስበው ሳሉ÷ "ጌታ ሆይ÷ በዚህ ወራት ለእስራኤል ልጆች መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ቀኑንና ዘመኑን ልታውቁ አልተፈቀደላችሁም፡፡ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኅይልን ትቀበላላችሁ፤በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣በሰማሪያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮቸ ትሆኑኛላችሁ።"


ቅዳሴ
ዘባስልዮስ

Ethiopia Orthodox Mazmur & Sabkat

18 Mar, 17:15


ደብረ ዘይት የአቢይ ፆም ፭ተኛ ሳምንት
✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟✟

የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚነገርበት ሳምንት ነው።

በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ስምዖን፣ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ እንድርያስን ጨምሮ ቀርበው "ንገረን ይሄ መቼ ይሆናል" በማለት ጥያቄ ጠያቁት። ጥያቄውም የዓለም መጨረሻውና የመምጣህ ምልክቱ ምንድን ነው? የሚል ነበረ እርሱም የማይቀረውን የዓለም ፍጻሜና አስቀድመው የሚፈጸሙ ምልክቶችን አስረድቷቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ በደብረ ዘይት ሳምንት ታስበዋለች፤ ለምእመናኑም ከዘመኑ ሁኔታ አንጻር በመጻሕፍት የተጠቀሱትን የትንቢት ምልክቶቹን ከተግባራዊ የዓለም ክንዋኔዎች አንጻር በማገናዘብ ታስተምራለች መልካም የፆምና የፀሎት ግዜ ይሁንልን ቅዱስ እግዚአብሔር ፀሎት ልመናችንን ይቀበልልንን፡፡