ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ @wku_gg_media Channel on Telegram

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

@wku_gg_media


ይህ በወልቂጤ ማዕከል ግቢ ጉባኤ ማሰተባበሪያ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግ.ጉ አባላት መረጃ መለዋወጫ 'የቴሌግራም' ገፅ ነው።


👇👇👇ተከታዮቹን ገጾች ይቀላቀሉ 👇👇👇

Telegram፦ https://t.me/wku_gg_media

YouTube፦ https://www.youtube.com/@MKWolkiteGibiGubae

ለሃሳብና አስትያይቶ @wku_gg_media_bot

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ (Amharic)

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ለወልቂጤ ተማሪዎች የቴሌግራም ማለት እና ታሪኩ መረጃ መለዋወጫ እንዲሆኑ እና በዚህ በአጭሩ እናትዎን በእርምጃዎች እንዲለካለ፣ የትም ለማለት ብቻ ለሚመልከት ታሪኩን እና ባለፈውን ምላሽ ይምረጡ። በስልክ እና በድጋፍ እና ከደረት እንዲሁም አጠፋ ለቴሌግራም መረጃ መለዋወጫ ይበልጡ። ለአገልግሎት እና ዜና አቅምዎች በቴሌግራም ግን በውሃ ለመዋጋት በአገር አጠባበቅ ይቀጥሉ። ከዚህም ተጨማሪ መረጃ ፕሮአል ማፅዳት አለበት። በተጨማሪ መረጃ ፕሮአል ለማፅዳት በሚረዱበት ተጨማሪ የማድር ፕሮግራምን እና መረጃን እየማለት ይመልከቱ። ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ የቴሌግራምን በቴሌግራም ማህበ ያበረታታት እና የቴሌግራም በማናቸውም ስግደት በመታየት ማህበ እና ለተማሪዎች ምክር የሚያስተካክል ነገር ተጠቃል።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

21 Nov, 07:23


ዛሬ ቅዱስ ሚካኤል ነው ነገር ግን አስቀድመን ቅዱስ ገብርኤልን እናነሳ ::

ቅዱስ ገብርኤል ከአምልኩ ከእግዚአብሔር ወደ ነብዩ ዳንኤል ተልኮ ሲመጣ ሳለ ችግር ገጠመው:: በዚህም ምክንያት 21 ቀን ይህል መልዕክቱ ዘገየበት ይህንንም ለነብዩ ዳንኤል ሲያስረዳ

“የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት።”

የፋርስ መንግስት የተባለው ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ ነው :: ቅዱስ ገብርኤል ፈጥኖ ሊሄድበት ከወደደው ቦታ ቢያዘገየው ከአለቆች አንዱ ሚካኤል መጣልኝ በዚያ ተውሁት አለ :: ከጌታ ፍቅር ሚያዘገየን ቢኖር እንደ ቅዱስ ገብርኤል እኛም ቅዱስ ሚካኤልን ጠርተን በእርሱ ላይ እንተወው ::


✝️ወ▮ዩ▮ግቢ ጉባኤ✝️

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

20 Nov, 05:38


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ዐሥራ አንድ በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት።

ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት

💠 የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት
💠 ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ
💠 ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት

ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግልማርያምን ያገለገለቻት ናት።

ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ቅዱስ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት።

ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት

ሰሎሜ ፣ኤልሳቤጥ እና ቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

ይህችም ጻድቅ ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።🙏

(ስንክሳር_ዘወርኀ_ኅዳር_11)
▬▬▬▬▬▬◈◈◈▬▬▬▬▬
➣የወ/ዩ ግቢ ጉባኤ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

19 Nov, 09:53


🛑ማሳሰቢያ🛑

የዳቦ ምዝገባ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ ያልተመዘገባችሁ ወንድም እህቶች ካፌ በር ላይ ስለሚጠብቁን እየሄዳችሁ እንድትመዘገቡ!!!

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

17 Nov, 17:27


🥇🥈🥉🥇🥈🥉🥇🥈🥉

👆👆የ፩ ሳምንት ጥያቄና መልስ ውድድር ይሄን ይመስላል

፪ ዙር ቀጣይ ሳምንት ቀዳሚት ሰንበት ከምሽቱ 2:00 ስለሚቀጥል ለቀጣይ  ዙር ከዚህም በዝተን እንድንሳተፍ ለሌሎች ማጋራት እንዳይዘነጋ



ሐሳብ አስተያየትዎን በ  @wkugg_bot ይላኩልን

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

17 Nov, 03:13


👉👉 የእለቱ መልእክት 👈👈
ሰለመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን

1, የሁለተኛ አመት ኮርስ አይኖርም

2, የአራተኛ አመት ኮርስ በተለመደው
ቦታና ሰዓት ይቀጥላል

3, የንስሐ አባት መርሀግብር
በተለመደው ቦታና ሰዓት ይኖረናል

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 17:00


🎲 Quiz 'ወ/ዩ/ግ/ጉ የሳምንቱ ጥያቄ ክፍል ፩'
ይህ በየሳምንቱ በሚድያ ክፍል እየተዘጋጀ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ከምሽቱ 2:00 የሚቀርብላችሁ የሳምንቱ ጥያቄ የተሰኘ መርሐ ግብራችን ነው ይሳተፉ ሌሎችንም በመጋበዝ ያሳትፉ
🖊 5 questions · 45 sec

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

16 Nov, 07:27



ጥያቄ እና መልስ ውድድር

ዛሬ 2:00 ሰዓት በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ የጥያቄ ቦት ይለቀቃል:: በቦቱ እየገባችሁ እንድትሳተፉ እናሳስባለን ::

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

15 Nov, 06:17


በዓለ ደብረ ቁስቋም

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡
ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ግብፅ ይሰደዱ ዘንድ እንደነገራቸው ሁሉ ፵፪ ወራት (ሦስት ዓመት ከስድስት ወራት) ሲፈጸም የሄሮድስ መሞት እና ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሱ ዘንድ “የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሞተዋልና፥ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ” በማለት ነግሯቸዋል፡፡ (ማቴ.፪፥፲፱-፳፩) በዚህም መሠረት ኅዳር ፮ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተመለሱበትን ቀን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 18:08



ጥያቄ እና መልስ

ቅዳሜ 2 ሰዓት በዚሁ ቻናል ላይ ቀጠሮ አለን :: በተከታታይ ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ሽልማትም ይኖረናል::

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

14 Nov, 06:39


ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን
ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉዓን
እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን
ኢየሱስ ነግድ ወፈላሴ እንዘ ውእቱ ሕፃን
ወልደ አብ ፍቁር ዘበኀበ ሰብእ ምኑን
ማሕልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ሐዘን''

ሰቆቃወ ድንግል

ትርጉም
“ስደተኛው ኢየሱስ ለሚሰደዱት ተስፋቸው ነው፤ የተገፋው ኢየሱስ ለሚገፉት መጠጊያቸው ነው። እግዚአብሔር [ወልድ] እንደ ድኾች መጠጊያ የሌለው ኾነ። ኢየሱስ ሕፃን ሳለ እንግዳና መጻተኛ፥ የተወደደ የአብ ልጅ በሰው ዘንድ ግን የተናቀ ነበረ። የእናቱ ሐዘንም የልቅሶ መዝሙር ኾነኝ።”

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 08:34


ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ pinned «»

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ

09 Nov, 06:41


ጸሎት በምናደርግበት ወቅት አንዳንድ ጊዜ ውስጣችን የማይፈልጋቸው ጣልቃ ገብ (intrusive thoughts) ሃሳቦች ህሊናችንን ይረብሻሉ።

በእነዚህ ቅፅበቶች ከሰይጣን እንጅ ከእኛ ልብ ያልሆኑ እግዚአብሔርን እስከ መሳደብ የሚደርሱ በጣም ጸያፍ የሆኑ ቃላትና ምስሎች እየመጡብን እንታወካለን።

ቤተክርስቲያናችን አንድ ክርስቲያን ይህ አይነት ፈተና ሲመጣበት
#ነፍሴ_እግዚአብሔርን_ታከብረዋለች በሚል ማርያማዊ ቃል ሰይጣንን አሳፍሮ ጸሎቱን እንዲቀጥል ታዝዛለች።

አረጋዊ መንፈሳዊ

💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫

@wku_gg_media ተከታተሉን