Hebrew 🇮🇱 עברית @hebrewethio Channel on Telegram

Hebrew 🇮🇱 עברית

@hebrewethio


የዕብራይስጥ ቋንቋን ይማሩ
למדו איתנו את השפה עברית
study hebrew with us

Hebrew 🇮🇱 עברית (Hebrew)

🇮🇱 Welcome to our Telegram channel, @hebrewethio, where we invite you to learn and study the Hebrew language with us! Whether you are a beginner looking to start from scratch or someone looking to improve their skills, our channel is the perfect place for you. Our goal is to provide a welcoming and supportive environment for all language learners. nnWho is @hebrewethio? We are a community of language enthusiasts dedicated to helping others discover and appreciate the beauty of the Hebrew language. Our team of experienced educators and native speakers are here to guide you through your learning journey, providing valuable resources, tips, and practice exercises along the way. nnWhat can you expect from our channel? Joining @hebrewethio means gaining access to regular lessons, vocabulary drills, grammar explanations, cultural insights, and interactive activities to enhance your learning experience. Whether you prefer to study independently or engage with fellow members in practice sessions, we offer a variety of opportunities to suit your learning style. nnWhy learn Hebrew with us? Hebrew is not just a language; it is a gateway to understanding a rich and ancient culture. By learning Hebrew, you will not only gain a valuable new skill but also open yourself up to a world of literature, music, history, and traditions. Our channel is more than just a place to learn vocabulary and grammar rules; it is a community where you can connect with like-minded individuals, share your progress, and celebrate the joys of language learning together. nnJoin us on @hebrewethio and embark on a journey of discovery, growth, and connection through the beauty of the Hebrew language. Let's study Hebrew together and unlock the endless possibilities that come with mastering a new language! 🇮🇱📚✨

Hebrew 🇮🇱 עברית

17 Jun, 11:59


የጦር ካቢኔያቸው መበተኑ ተነግሯል

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የሀገሪቱን ጦር ካቢኔ መበተናቸው ተሰምቷል፡፡

ውሳኔው የእስራኤል የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ሥልጣን መልቀቃቸውን ተከትሎ የተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የጦር ካቢኔው መበተን ውሳኔ የእስራኤል የፖለቲካ እና ደህንነት ካቢኔ በጉዳዩ ላይ ከመከረ በኋላ የተላለፈ መሆኑንም አልጀዚራን ጠቅሶ ፋና ዘግቧል፡፡

የእስራኤል ጦር ካቢኔ ስድስት አባላት የነበሩት ሲሆን በቅርቡም አዲስ ካቢኔ እንደሚቋቋም ተጠቁሟል፡፡

በቅርቡ የጦር ካቢኔ ሚኒስትር ቤኒ ጋንትዝ ከስልጣን መልቀቅ ከጋዛ ጦርነት በኋላ ባለው ዕቅድ ላይ ከጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር የተፈጠረው ልዩነት ማሳያ ተደርጎ ሲነሳ መቆየቱ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

Hebrew 🇮🇱 עברית

04 Jun, 17:32


እስራኤል በጋዛ ምርኮኛ ከሆኑ ሰዎች መካከል ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት መሞታቸውን አስታወቀች

እስራኤል በጋዛ ከሚገኙ ምርኮኞች መካከል ከሲሶ በላይ የሚሆኑት ሞተዋል ብላ ታምናለች ሲል በመንግስት መረጃ የወጣዉ አሃዝ አመላክቷል፡፡በጥቅምት ሰባት በሃማስ ታግተዉ ከተወሰዱት 250 ሰዎች መካከል በህዳር ወር በተደረሰዉ የሰላም ስምምነት የተወሰኑት መለቀቃቸዉ ይታወሳል፡፡የእስራኤል ወታደሮች የተወሰኑ ምርኮኞች አስከሬን ወስደዋል።

የእስራኤል መንግስት እስካሁን 120 ያህል ሰዎች አሁንም በእስር ላይ እንደሚገኙ የገለፀ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 43ቱ ህይወታቸዉ ማለፉን በእስራኤል ባለስልጣናት በተለያዩ የመረጃ ምንጮች፣ የስለላ መረጃ፣ የደህንነት ካሜራ እና የፎረንሲክ ትንታኔዎች አረጋግጠዋል፡፡እስራኤል በጋዛ ሆስፒታሎችን ማጥቃት እና የህክምና ባለሙያዎችን መግደሏን በቀጠለችበት ወቅት በርካታ ምርኮኞች በእስራኤል የአየር ጥቃት መገደላቸውን አስታዉቋል፡፡ በጋዛ የጤና መሰረተ ልማቶች በመዉደማቸዉ የቆሰሉ ምርኮኞች መሞታቸውን ሃማስ ይፋ አድርጓል፡፡

በኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጅድ አል-አንሷሪ ጦርነቱን ለማቆም በድርድር ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ ስምምነት ላይ ከመድረስ በቀር ሌላ አማራጭ የለም ብለዋል።"በዚህ ጦርነት ማንም ኃይል ሙሉ በሙሉ ማሸነፍ አይችልም፤ ሃማስን ጠራርጎ ማጥፋት ወይም የፍልስጤምን ጉዳይ ወደጎን ማድረግ የበለጠ ብጥብጥ ብቻ እንደሚያመጣ እና ሊሳካ እንደማይችል ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ በጣም ግልፅ ይመስለኛል ሲሉ ተናግረዋል።

Hebrew 🇮🇱 עברית

03 Jun, 12:22


Try this.

የሰራችሁት 3USD ሲደርስ ማውጣት ይቻላል። ጎበዝ ከሆናችሁ በቀን እስከ 9USD መስራት ትችላላችሁ።

አሰራሩ invite ማድረግ ብቻ ነው።

https://t.me/preton_drop_bot?start=6e5a3bc0-eff7-475c-a303-9629b704d0bd

Hebrew 🇮🇱 עברית

03 Jun, 12:17


Notcoin እንዴት ነበር?

እኔ አሁን ባለው ዋጋ ከ 110 ሺህ ብር በላይ አግኝቼበታለሁ።

በዚህ ቻናል ላይ ባገኛችሁት refferal ጀምራችሁ ብዙ የሰራችሁ አላችሁ።

ለእናንተም አሪፍ ስላገኛችሁበት ደስ በሎኛል።
ቢረፍድም መልካም ምኞታችን ነው🙏

ከዕብራይስጥ ቋንቋ በተጨማሪ እንደ Notcoin አይነት ሌሎች Tokens እናጋራችኋለን።

Hebrew 🇮🇱 עברית

03 Jun, 12:10


ሰላም ቤተሰብ🫡

שלום מִשׁפַּחתִ' 👐

ወደ ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ ከሀገር ውጭ ነበርኩኝ።
ሀገር ውስጥ ስላልነበርኩ ነው የተጠፋፋነው።


አሁን በሰላም ተመልሰናል።
በቴሌግራም ቻነላችን አብረን እንቆያለን።
የ VIP Hebrew course ይቀጥላል።

Hebrew 🇮🇱 עברית

05 Apr, 13:43


“በመሬታቸውም እተክላቸዋለኹ፤ ዳግምም ከመሬታቸው ላይ አይነቀሉም...” ተብሎ በዓሞጽ የትንቢት መጽሐፍ ላይ ተጽፏል።

ልብ አድርጉ! ይህን የተናገረ ሰው ወይም ሐሳዊ ነቢይ አይደለም፤ ራሱ ሀሼም እንጂ፤ ጥቅሱ ሲጠናቀቅ “አማር ሀሼም ኤሎሄይኻ” ይላልና። ስለዚህ ዓለም ተሰብስቦ ምድሪቱ የእሥራኤል አይደለም ቢል ስንኳ ከጩኸት አይዘልም። የእኛ አምላክ የተናገረውን ሲፈጽም አይተናልና።



@Hebrewethio
@Hebrewethio

Hebrew 🇮🇱 עברית

01 Apr, 11:54


የስራ ዕድል በዱባይ!

♻️ሥራ - Typing and Online content creating

♻️ ደሞዝ - 3000 durham ( 90,000 ብር በብላክ ምንዛሬ )

♻️ ምግብ እና መኖሪያ የአፖርትመንት ዶርም ከድርጅቱ

በየሁለት ወር የአምስት ቀን ረፍት
( በአምስት ቀን ረፍት ጊዜ ወደ ሀገር መጥቶ ቤተሰብ ጠይቆ መመለስ የሚያስችል ወጭውን ድርጅቱ የሚሸፍነው )

የተፈላጊ መስፈርቶች

🔆 ፆታ አይለይም

🔆 ፓስፖርት ያለው

🔆 እንግሊዝኛ የሚችል እና ኮምፒውተር ላይ Type ማድረግ የሚችል ወይም የምትችል

🔆 ዲግሪ ያላቸው ይበረታታሉ። ዲግሪ የሌለው በቂ የእንግሊዝኛ ችሎታ ያለውም ይበረታታል።

🔆 የፕሮሰስ ጊዜ 2-3 ሳምንት

🔆አጠቃላይ የፕሮሰስ ወጪ 160 -165 ሺህ ብር

ከቪዛ በፊት ቅድመ ክፍያ የለውም።

መስራት የምትፈልጉ
👇
@Hebruat

Hebrew 🇮🇱 עברית

01 Apr, 11:17


💬💬💬💬💬💬💎
Good News notcoin Mine ስታደርጉ ለነበራችሁ....

April 20 ላይ List ይደረጋል👌

I guess its no more " probably nothing ". Feels like its becoming sth

Hebrew 🇮🇱 עברית

31 Mar, 19:46


በጣም ደስ ብሎናል😍

ከሦስት ቀን በፊት በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን ፖስት ለ 12 ሰዓታት ፖስት አድርገን ነበር።

ድርጅቱ የትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ ሸፍኖ በሁለት ዓመት የስራ ኮንትራንት ወደ ዱባይ የሚወስዳት ሴት መዝገብ ያዥ ማስታወቂያ አጋርተናችሁ ነበር።

21 ሴቶች በውስጥ መስመር ፍላጐታችሁን ነግራችሁኝ የድርጅቱን መስፈርቶች ልኬላችሁ ነበር።

ፍላጎት ካሳዩት ውስጥ 4 ሴቶች አልፈዋል።
ከአራቱ መካከል ፈተናውን የምታልፍ አንድ ሴት ብቻ ይህን የስራ ዕድል ታገኛለች።

አራቱም ካላለፉ ማስታወቂያውን በድጋሚ ለሌሎች ፈላጊዎች እንለቅላችኋለን።

ለእነዚህ አራት እህቶቻችን መልካም ምኞታችንን እናደርሳችኋለን።


ሌሎች የውጭ ሀገር የስራ ማስታወቂያዎች ሲመጡ እናሳውቃችኋለን።
መልካም ዕድል💙

Hebrew 🇮🇱 עברית

30 Mar, 19:42



-
አይሁድና አእምሮው
-
ከመላው ዓለም ሕዝብ ረገድ አይሁድ የዓለምን 0.2 በመቶ ብቻ የሕዝብ ድርሻ አለው፡፡ በእውነቱ እጅግ አነስተኛ ቍጥር ነው። ይኹን እንጂ ከ1901 እስከ 2020 ዓ/ም ባሉት 119 ዓመታት ውስጥ 900 የሚያኽሉ ሰዎች የኖቤል ሽልማትን አሸናፊነት ሲቀዳጁ ከእነዚያ ተሸላሚዎች ውስጥ 204 የሚኾኑቱ አይሁድ ናቸው፡፡ እንግዲህ ከሕዝባቸው አነስተኛ ርቢ አንጻር ለዚህች ዓለም ያበረከቱት አስተዋፅኦ ሲታሰብ (ሲብሰለሰል) ከሚጠበቀው በላይና በእጅጉ የላቀ ነው ያሠኛል፡፡
በሰላም 9 ፥ በኬሚስትሪ 36 ፥ በኢኮኖሚክስ 33 ፣ በሥነ ጽሑፍ 15 ፥ በፊዚክስ 55 ፣ በሥነ ሕይወትና በሕክምና 56 ፤ በጥቅሉ 204 አይሁድ በየዘርፉ የኖቤልን ሽልማት አሸንፈዋል፡፡ ለምሳሌ ያኽል ባያሌው የሚታወቁቱ፡— አልበርት አንስታይን (ፊዚሲስት) ፥ ኔልስ ቦህር (ፊዚሲስት) ፥ ሲግመን ፍሬድ (ሳይካትሪስት) ፣ ፍሪትዝ ሐበር (ኬሚስት) ፣ ሮሳሊንድ ፍራንክሊን (ባዮሎጂስት) እንዲሁ በሰላም ዘርፍ ያሸነፉት የእሥራኤሉ ጠ/ሚር ሚናሒም ቤጊንና ሺምዖን ፔሬትዝ የሚጠቀሱት ናቸው።
የአይሁድ ሳይንስ ዐዋቅያን ጭንቅላታቸውን (ጭንቅ—አልላት) በአግባቡ አውጠንጥነው በዓለም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በመፍጠር በተለይም ደግሞ የኹሉ በኾነው በሳይንሱ መስክ ላይ ያበቀሉት ሳይንሳዊ ዘር ፥ የሰው ልጅ የሚኖርባት ዓለም ረቂቅ ጥበብን እንድትጐናጸፍና የኋላ ቀር ኑሮ ቅዝቃዜ ዐጥንቷን እንዳይቈረጥመው አድርገዋል። በአንጐላቸው አብላልተው ካመጠቋቸው አይጠገቤ ሳይንሳዊ ዕውቀቶችም የተነሣ ሳይንስን ለአፍታ ሳይምሩ እንደ ኳስ አንዴ ወዲህ ፥ አንዴ ወዲያ እያንከባለሉ ምስጢሩን ኹሉ አዘርግፈውታል ቢባል የሚጋነን አይኾንም !
የኣዳም ልጅ ኹሉ ያውሬ ባሕርይ በተላመደበት በክፉው ዘመን ዐይናችኹን አልያችኹ የተባሉት አይሁድ ኑሯቸው የኢትዮጵያ አበው (አባቶች) እንደሚተርቱት ያለ ኾኖባቸው ነበር። አበው ኢትዮጵያውያን ሲተርቱ “ብዕር ዘኢተፈጸመ ዐጸባሁ ወእምድኅረ ዘሞተ ይጠፈር ቍርበቱ ለከበሮ” ይላሉ። “መከራው ያላለቀለት በሬ ከሞተም በኋላ ቈዳው ለከበሮ ይጠፈራል” ማለታቸው ነው። ምንም እንኳ የዓለም ልጆች ኹሉ በየአጽናፉ ‘አክ ፥ እንትፍ’ ቢሏቸው የአእምሯቸው ውጤት የኾነውን ብስል ፍሬ አላምጠው ወደ ከርሣቸው ለመዶል ግን አሻፈረኝ ማለት አልቻሉም ! እጅጉን ይጣፍጣልና።
እንሆ በዓለም ብረት (ብሌን) ሲታዩ እንደ ሕዋስ እጅጉን ንኡሳን የኾኑ እሊህ ምስኪናን አይሁድ አስደማሚ ግብር የገበሩ የዕውቀት አለቃ በመኾናቸው እንደ አገር ፈርጣማና ጕልበታም ኾነው እንዲታዩ አብቅቷቸዋል። እነኚሁን ፊደሎቼን እንኳ በተራ አስተባብሬ በዚሁ ፌስቡክ (መጽሐፈ ገጽ) በተባለ ባቡር ላሳፍራቸው የቻልኹት ፥ አንድ ማርክ ዙከርበርግ የተባለ አይሁዳዊ ካዳበረው ቍድስ ተቋዳሽ ኾኜ ነው።
(ፕኒኤል)

Hebrew 🇮🇱 עברית

28 Mar, 19:45


ኔታንያሁ እስራኤል እየጨመረ ለመጣው አለማቀፍ ጫና ሸብረክ እንደማትል ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ከተጀመረ 170 ቀናትን ያስቆጠረው የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ለእስራኤል ህልውና ሲባል ሀማስ ጨርሶ እስኪደመሰስ ድረስ ጥቃቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት ኔታንያሁ በገለፁት መሠረት የሌሎች አረብ ሐገራት መሪዎች እስራኤል በፍልስጥኤም ታጣቂ ላይ የምትወስደውን እርምጃ አጠናክራ መቀጠሏን እንደሚስማሙበት ገልጠዋል።

ምንም እንኳን የትኞቹ የአረብ ሐገራት የእስራኤልን ጥቃት እንደሚደግፉ ግልጽ ባያደርጉም ከኢራን ጋር ከፍተኛ ችግር ያለባቸው ሳዑዲ ዓረቢያ እና አረብ ኢምሬት እንደሆኑ አያጠያይቅም።

ልኡካቸው በዋሽንግተን ሊያደርገው የነበረው ጉዞ የተሰረዘውም የጋዛውን ጦርነት የሚያስቆመው እንደሌለ ለሃማስ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ብለዋል።

Hebrew 🇮🇱 עברית

27 Mar, 13:55


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ጦርነት ጉዳይ ተጣልተዋል
~~~~
ባይደን እና ኔታንያሁን ያጣላቸው ጉዳይ "ጆ ባይደን ባለፈው ሳምንት ኔታንያሁን እስራኤልን የጎዳ ሰው ነው ካሉ በኋላ ነው። ኔታንያሁ በምላሻቸውም ባይደን ይረፉ ሃማስን የማጥፋት ዘመቻችንን የሚያስቆመን የለም ብለው መልሰውላቸዋል።

ባይደን የእስራኤል ጦር ንፁኃንን መጠበቅ አለበት በጀምላ ንፁኃንን መግደል መቆም አለበት ይላሉ።

ኔታንያሁ ደግሞ ንፁኃንን እየጠበቅን ነው ሃማስ በንፁኃን ፍልስጤማዊያን ተከልሎ ነው ጥቃት የሚፈፅመው ሲሉ ያስረዳሉ።

ትናንት የሃማስ ጠንካራ ይዞታ ነው የሚባለው በደቡብ ጋዛ የእስራኤል ጦር ገብቷል። በጋዛ የሚገኘው ትልቁ የአልፋሻ ሆስፒታል የእስራኤል ጦር በመክበብ በሆስፒታሉ ተጠልለው ጥቃት የሚፈፅሙ የሃማስ አባላትን ደምስሷል።

የጋዛው ጦርነት እያለቀ ነው የሚሉ አሉ። የእስራኤል ጦር በዘመናዊ መሳሪያ በመታገዝ የሀማስ አመራሮችን እየገደለች ነው ሲሉ ያስረዳሉ።
ባለፈው ሳምንት የሃማስ ማስተር ማይንድ የሚባለው ማርዋን ኢሳ መገደሉ ይታወቃል።

አንዳንዶች ደግሞ የለም እስራኤል በጋዛ አታሸንፍም፣ የሀማስ ታጣቂዎች በደፈጣ ጥቃት አልተቻሉም ሲሉ ያስረዳሉ። ጦርነቱ በዙ ጊዜ ሊፈጅ ይችላል ይላሉ።

Hebrew 🇮🇱 עברית

26 Mar, 17:26


በብዙ Hollywood  celebrity ዎች  እጅ ላይ የምታዩት ቀይ አምባር or bracelet አመጣጡ ከአይሁዶች ነው እነሱም ሴጎላ ብለው ይጠሩታል ጥሩ እድል የሚያመጣና መጥፎ evil eyes የሰው አይን ጨምሮ መጥፎ ነገሮችን ሁሉ ያርቃል ብለው ያምናሉ

ሌላው ደሞ ሂንዱዎች ወይም የሂንዱ እምነት ተከታዮች ከቢጫ  ክር ጋር ይሄን ቀይ አምባር ያስራሉ ሃይማኖታዊው ፍቺ ከአይሁዶች ጋር ተመሳሳይ ነው

ብዙዎቻቹ ስለ ኢሉሚናቲ አለም አቀፍ ሃይማኖት ታውቃላቹ ግን ስለተመሳሳይ ወይም የሱ ቅርንጫፍ ስለሆነው Kabbalah Center ወይም ካባላህ ስለሚባል እምነት አታውቁ ይሆናል ብዙ የሆሊውድን ጨምሮ በአለም ላይ ያሉ የቢዝነስ የፖለቲካ ብቻ በተለያየ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ታዋቂ ሰዎች የሚከተሉት እምነት ፍልስፍና ነው ካባላህ እምነትም ይሄን ቀይ ክር ልክ እንደ ጅዊሾች እና ሂንዱዎች በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚያምኑበት ያ ብቻ ሳይሆን የዚ ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸውንም ለማሳየት እንደ ምልክት ይጠቀሙበታል

ቀይ አምባር ከክርስትና ጋር  በተያያዘ በበመፅሃፉ ቅዱስ ላይ የሰፈረ  ባይሆንም ጅዊሽ ክርስቲያኖችም ያስሩታል የነሱ ምክንያት ደሞ

ሙሴም እንደ ሕጉ ለሕዝቡ ሁሉ ትእዛዝን በተናገረ ጊዜ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውኃም ከቀይም የበግ ጠጕር ከሂሶጵም ጋር ወሰደ መጽሐፉንም ሕዝቡንም ሁሉ ረጨ እንዲህም አለ ይህ እግዚአብሔር ለእናንተ ያዘዛችሁ የኪዳኑ ደም ነው ደምም ሳይፈስ ስርየት የለም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም ደሙ መፍሰሱን እና መሞቱን ቀይ መጎናጸፍ የሚያመለክተው የክርስቶስን ደም ነው ብለው ያምናሉ  እንዲሁም የጴጤቆስጤ ምልክት ነው ተብሎ ይታመናል ለዚህም እስራኤል ውስጥ በየመንገዱ  ይሸጣል

በሺዓ እስልምና ቀይ ክር የከርበላላን ጦርነት ያስታውሳል ብለው ያምናሉ  ስለዚ ጦርነት ግንዛቤ ያለው ይረዳል እኔ አላውቅም  ቱርኮች በባህላቸው ሰማያዊ evil eyes ሰማያዊ በአይን ምልክት ያለው ጌጥ በቀይ ክር ያስራሉ ይሄም መጥፎ አይን እና እድልን ያባርራል ብለው ያምናሉ ጥሩ እድልም ያመጣል ብለው ያምናሉ ለዚህም ቤታቸው ላይ ይሄን ጌጥ ይሰቅላሉ እንደጌጥም  እጃቸው አንገታቸው ላይ ይጠቀሙታል።

Hebrew 🇮🇱 עברית

25 Mar, 22:21


ስለ ተወዳጇ እስራኤል አንዳንድ መረጃዎችን እንይ እስቲ!


🇮🇱 እስራኤል የህዝብ ቁጥሯ ከ 9 ሚልየን አይበልጥም።

🇮🇱 የእስራኤል ስፋት 22,072 sq km ነው።

🇮🇱 በእስራኤል 1 km sq ውስጥ በአማካይ 429 ሰዎች እንደሚኖሩ ይታመናል።

🇮🇱 የእስራኤል ዓመታዊ ገቢ 400 Billion dollar ነው።

🇮🇱 የእያንዳንዱ የእስራኤል ዜጋ ዓመታዊ ሃብት ( GDP per capita income ) 42,000 dollar ነው።

🇮🇱 የእስራኤል ኢኮኖሚ ዋና መሠረት ቴክኖሎጂ፣ ግብርና፣ ወታደራዊ ኢንደስትሪ፣ ቱሪዝም እና ፋይናንሻል ሰርቪስ ናቸው።

🇮🇱⚪️🔵⚪️🔵⚪️

Hebrew 🇮🇱 עברית

24 Mar, 14:37


እንግዲህ፥እስራኤል ሆይ፥ስማ መልካምም እንዲኾንልኽ፥የአባቶችኽም አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ወተትና ማር በምታፈሰ፟ው ምድር እጅግ እንድትበዛ፥ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ።


ዘዳ 6÷3

Hebrew 🇮🇱 עברית

23 Mar, 11:41


እስራኤል ወደ ኢትዮጵያ የላከችው ይህን አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ መንግስት አልቀበላቸውም ማለቱ ተሰማ።

ምክንያት በጎንደር አከባቢ በፈላሾች ቤት ተቃጠለ የሚል በቪድዮ የተሰራጨ ስም ማጥፋት ላይ ተሳታፊ ነበሩ የሚል ነው።

.

Hebrew 🇮🇱 עברית

22 Mar, 21:35


በልሳነ ዕብራይስጥ ወይስ ልሳነ ግእዝ ?
-
የእሥራኤል ቅዱስ መጽሐፍ በዕብራይስጥ እንጂ በግእዝ አልተጻፈም። አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በደረሱት መጽሐፈ ምስጢር ላይ እንዲህ ከትበዋል፡― “ወመክብበ መጻሕፍቲሃሰ ዘብሉይ ተዐልዋ እም ዕብራይስጢ ኀበ ግእዝ በመዋዕሊሃ ለንግሥት አዜብ እንተ ሐወጸቶ ለሰሎሞን. . .” (የብሉይ መጻሕፍቷስ ኹሉ ንግሥት አዜብ ሰሎሞንን በጐበኘችው ዘመን ከግእዝ ወደ ዕብራይስጥ ተቀዳች / ተመለሰች) ማለት ነው። ምንም እንኳ ርግጥ ኾኖ ቅዱስ መጽሐፍ ከዕብራይስጥ ባይተረጐምም ቅሉ አስቀድሞም ቢኾን ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት በዕብራይስጥ ስለ መኾኑ በኋለኛው ዘመን የነበሩት አባ ጊዮርጊስ ማረጋገጫ ናቸው።
እንዲሁ በድንግዝ “መጽሐፍ ቅዱስ ከሥር መሠረቱ የተጻፈው በግእዝ ነው ፤ ይኸውም ሙሴ ሲናይ (ሲና) ተራራ ከአዶናይ ጋራ ሳለ በዕብራይስጥ የሰማውን ኹሉ በግእዝ ከትቦ ሕዝበ እሥራኤል ኹሉ ዕውቀተ አዶናይን ቀሰመውበታል” ማለቱ ይቅርና የግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ የተተረጐመው ከዕብራይስጡ ነው ማለት እንኳ አግባብ አይዶለም። ከዕብራይስጡ አልተተረጐመምና። ደግሞስ ራቢው (መምህሩ) ሙሴ ድምፀ አዶናይን በዕብራይስጥ ቋንቋ በዦሮው እያዳመጠ ርሱና ሕዝቡ በማያውቁት በአሕዛብ ቋንቋ (በግእዝ) የሚጽፍበት ምክንያት ከወዴት ይፀነሳል ? ይልቁንም የግእዙ ቅዱስ መጽሐፍ የተቀዳው (የተተረጐመው) ከግሪኩ ቅዱስ መጽሐፍ እንጂ ከዕብራይስጡ አይዶለም።
አባ ጊዮርጊስ በመጽሐፋቸው እንዳሉት አኹን ያለው የግእዙ ቅዱስ መጽሐፍ ከዕብራይስጡ ተተርጕሞ ቢኾን ኖሮ እንደው እንደ ያለ አንዳች እንከን በምልአትና በርትዕና ባይተረጐም እንኳ ቢያንስ ቢያንስ ዕብራይስጣዊ ስሞች ጽርዓዊ (ግሪካዊ) መኾናቸው ቀርቶ በራሳቸው መጠሪያ ይቀዱ ነበር። ለምሳሌ፡― ዘካርያስ የሚለው በዝኻሪያ ፣ ይርሚያሁ የሚለው በኤርምያስ ፣ ይሻዕያሁ የሚለው በኢሳይያስ ፣ ይሆሹዐህ የሚለው በኢያሱ ... ወዘተርፈ የመሳሰሉት ስሞች በውስጣቸው የያዙትን ያህ የሚለውን ስመ አዶናይ ሳያጡና የጽርዕ አሻራ ሳያገኛቸው በተከተቡ ነበር።
እንደነ ታልሙድ ባሉ መሰል ቅዱሳት መጻሕፍት ዘአይሁድ “ዓለም የተፈጠረው በዕብራይስጥ ነው ፤ ዓለም ይፈጠርም ዘንድ ዕብራይስጥ መፈጠር ነበረበት። ስለዚያም ኤሎሂም ዕብራይስጥን ፈጠረ። ኋላም ፍጥረታትን ኹሉ ፈጠረ ይላል።” እንደ ማስረጃ የምንወስደውም ኤል ፣ ኤሎሂም ፣ ሀሼም ፣ ያህ ፣ ኤል ሻዳይና አዶናይ የሚሉ መሰል የአዶናይ ስሞች ዕብራይስጣዊ ኾነው መገኘታቸው ነው። ለምሳሌ፡― የመዠመሪያው ሥሪተ አዶናይ የኾነው ኣዳም אדם ስያሜው እንኳ አስገራሚ ምስጢርን መያዙ በሌሎች ያሕዛብ ልሳናት አለ መገኘቱ ነው። ይኸውም א አሌፍ የሚለው የዕብራይስጡ ቀዳሚ ፊደል የተሠራው ወይም የተዋቀረወሸ ከኹለት ዮድና י ከአንድ ቫቭ ו ነው። አንድ ዮድ ከላይ ፥ አንድ ዮድ ከታች ኾነው ቫቭን በሰያፉ አድርገው እንደማለት ነው። እኒህ ሲደመሩ አንድ ቫቭ (6) ፤ ኹለት ዮድ (20) = 26 የሚለውን ቍጥር ይሰጣሉ። 26 ደግሞ ሀሼም ከሚለው ስመ አዶናይ ጋራ ድማሬ ጋራ እኩል ነው። (ዮድ (10) + ሄ(5) + ቫቭ (6) + ሄ (5) = 26) እንግዲህ አሌፍ በውስጠ ዘ አዶናይን ይወክላል ካልን ቀሪው ዳም דם የሚለው በዕብራይስጥ ደም የሚል ትርጕም አለው። «ኣዳም» ስንል አዶናይና ደም ያላቸውን መስተጋብር እናስባለን ፤ በደም ውስጥም ነፍስን የቸረ አምላክ ስለ መኖሩ ዕብራይስጡ ይነግረናል። እውን ግእዙ በኣዳም ስያሜ ላይ እንዲህ ይራቀቃልን ?
ባጭሩ የኤሎሂም ድርሰት በግእዝ ቢጻፍና ኤሎሂምም ዓለምን በግእዝ ቢፈጥር እንደነ ዳንኤልና ሕዝቅኤል ያሉ ነብያን ኹሉ ደየነ እግዚአብሔርና ያጸንዕ እግዚአብሔር የሚሉ ስሞች ባለቤት ያሏቸው ዘርዐ ኢትዮጵያውያን በኾኑ ነበር። ድርሰተ ኤሎሂም በግእዝ መጻፉም ካልቀረ ኢትዮጵያውያኑ እሥራኤላውያኑን በተኩ ነበር። የሴማውያት ልሳናት ሊቁ አለቃ ኪዳነ ወልድም “የግእዝ ብሉያት በዘመነ ብሉይ ከዕብራይስጥ ተቀድተዋል ማለት ሳይከካና ሳይቦካ ሳይጋገር ምጣድ ሳይነካ እም ኀበ አልቦ የተገኘ የሕልም እንጀራ ነው። ትምርት ቀስቅሶት ከንዋመ ሀኬት ለነቃው ለዛሬ ዘመን ልጅ አያጠግብም” ይላሉ።
(ፕኒኤል)

1,797

subscribers

39

photos

1

videos