Ethiopian Architecture Construction and Urbanism @ethiopianarchitectureandurbanism Channel on Telegram

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

@ethiopianarchitectureandurbanism


It is a platform for information on historical and contemporary architecture, urbanism, landscape, and the construction industry inside Ethiopia. It will also include similar issues from across the world.

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism (English)

Are you fascinated by the beauty and history of architecture? Do you have a keen interest in urban planning and construction? If so, then the 'Ethiopian Architecture Construction and Urbanism' Telegram channel is the perfect place for you! This channel serves as a comprehensive platform for information on historical and contemporary architecture, urbanism, landscape, and the construction industry within Ethiopia. Whether you are an architecture enthusiast, a student studying urban planning, or a professional in the construction industry, this channel has something for everyone. By joining the 'Ethiopian Architecture Construction and Urbanism' channel, you will have access to a wealth of knowledge and resources about Ethiopian architectural heritage, innovative urban planning projects, and the latest trends in the construction industry. From ancient historical buildings to modern skyscrapers, this channel covers a wide range of topics that will captivate your interest. But the channel doesn't stop there! In addition to focusing on Ethiopian architecture and urbanism, it also includes content on similar issues from across the world. This means that you will not only learn about the unique architectural achievements in Ethiopia but also gain insights into global trends and developments in the field. The 'Ethiopian Architecture Construction and Urbanism' channel is curated by experts and enthusiasts who are passionate about sharing their knowledge and insights with a wider audience. By joining this channel, you will become part of a community that values learning, appreciation of beauty, and the importance of sustainable urban development. So, what are you waiting for? Join the 'Ethiopian Architecture Construction and Urbanism' Telegram channel today and immerse yourself in the fascinating world of architecture, construction, and urbanism. Whether you are looking for inspiration, information, or simply want to connect with like-minded individuals, this channel has it all. Don't miss out on this exciting opportunity to expand your knowledge and passion for architecture and urban planning!

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

17 Nov, 20:10


ድሮ እና ዘንድሮ

አድዋ ጎዳና ቲ ሩም አካባቢ

ምስል ምንጭ። Melaku Getahun. BCAA

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

17 Nov, 15:13


አሁናዊ ኪነህንጻ
አብርሆት ቤተመጻህፍት

በ ዮሴፍ በረደድ።

አውዳዊ እና የላቀ ጥበብ የሚታይበትን ይህንን ቤተመጻህፍት የመሳሰሉ ብዙ ጥበባዊ ህንጻዎች በከተማችን እንዲሁም በአገራችን ያስፈልጉናል።

በ ቲክታክ ይከታተሉን።

https://www.tiktok.com/@addisarch2?_t=8rTMdZuejah&_r=1

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

17 Nov, 12:44


እሳት አደጋ።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ዛሬ ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ሰዓት ላይ የተነሳዉ የእሳት አደጋ ሳይዛመትና የከፋ ጉዳት ሳያደር መቆጣጠር ተችሏል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን።
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

16 Nov, 21:11


ገበያ ቦታ
ከምባ፣ ጋሞ ዞን

ምንጭ። Hilena.Tafesse
@ethippianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

16 Nov, 20:57


ገበያ ቦታ
ቡታጅራ።
አርብ ገበያ ቡታጅራ

ምንጭ። Visit Gurage.
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

16 Nov, 11:13


የቆዩ የከተማ ምስሎች።
ጊምቢ

የተያያዘው ምስል ጊምቢን በምስል ለመቅረጽ የሞከረ ፖስታ ሲሆን የተላከው ፖስታ/ፖስትካርድ -ታህሳስ 1941 ዓ.ም ነበር።


David Steen Archive/Seventh Day Adventist/The Steen Years:
https://www.flickr.com/photos/davidsteen/12241784403/in/album-72157640360809833
ምንጭ። Historic Ethiopia Through The Camera Lens 1i60s-1990s
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

15 Nov, 15:22


ታዋቂ ነዳፊያን
ራሄል ሻውል።

ራሄል የዛሬ ስድስት አመት የሁለተኛ ዲግሪ የኪነህንጻ ተማሪዎችን በEiABC ተገኝታ ከሙያዋ እያካፈለች በምስሎቹ ይታያል።

ታዋቂ ነዳፍያን በ የትምህርትቤቱ እየተገኙ ለተማሪዎች የሚያደርጉት ገለጻ እጅግ ጠቃሚ ግብዓት ይሆናቸዋል።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

13 Nov, 20:50


የኢትዮጵያ ኪነህንጻ በ ቲክታክ።

በዋነኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የላቁ ዘመናዊ እንዲሁም ባህላዊ ህንጻዎችና ከተማ ቦታዎች በተንቀሳቃሽ የሰው እይታ (human eye view) ወጥ (original) ምስል የሚቀርብበት የ ቲክታክ ፕሮፋይል ማስፈንጠርያ ከታች ተያይዟል። ከምስሉ ጋር ጠቃሚ የሆነ የጽሁፍ መግለጫም የሚያያዝበት በመረጃ የበለጸገ የቲክታክ ፕሮፋይል ነው።

https://www.tiktok.com/@addisarch2?_t=8rMvocAwaVL&_r=1

@ethiopianarchitecture

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

13 Nov, 12:58


የባለሙያዎች ተሳትፎ

ለ፡ ሪል ስቴት፣ ቋሚ ንብረት ግመታ፣ የሕንጻ ዲዛይን እና ግንባታ ባለሙያዎች በሙሉ

የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ
የሰነዱ ሊንክ፡ https://cutt.ly/seH3lLNO

የሀሳብ መስጫ ሊንክ ፡ https://cutt.ly/5eH9GQT1

2017 ዓ.ም

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

13 Nov, 09:16


ኪነ ህንጻ ተማሪዎች እንዴት ይነድፋሉ?

ምንጭ። Leewardists

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

13 Nov, 06:15


የ ከተማ ቦታ ለውጥ።
አሮጌው ፖስታ ቤት ፊትለፊት።

ምስሎቹ የከተማ ቦታ እንዴት እንደሚለዋወጥ ያመለክታሉ።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

12 Nov, 10:40


ለፈገግታ ያህል።

ከዚህ➱
      ወደዚህ🤔

መጽሀፈ ሄኖክ በ BCAA በኩል
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

12 Nov, 09:29


ካዛኒሽ ፎረም
ካዛን፣ ሩስያ
ኢትዮጵያውያን ህንጻ ነዳፊዎች እንደ ሀገር መድረክ የተሰጣቸው የመጀመርያው አለም አቀፍ የኪነህንጻ ፎረም።

በካዛኒሽ ፎረም ከDecember  5-7 2024 በአዲሱ የካማላ ቲያትር ሕንፃ ውስጥ በሚካሄደው የካዛኒሽ ፎረም ላይ ከሌሎች ሀገራት የተውጣጡ ድንቅ የኪነ-ህንፃ ፕሮጀክቶች ይቀርባሉ። ከእነዚህም መካከል በቬትናም የሚገኘው “የድራጎን ግንብ”፣ የብራዚል የደመና ድንኳን፣ የኢራን “የሕይወት ድልድይ”፣ በኢትዮጵያ  የሚገኘው የዞማ ጥበብ ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል።

በቶኪዮ የኦሎምፒክ ስታዲየም እና በስኮትላንድ የሚገኘው የቪ ኤንድ ኤ ዱንዲ ሙዚየም ነዳፊ ጃፓናዊው ኬንጎ ኩማን እንዲሁም ታዋቂ የኢትዮጵያ ህንጻ ነዳፊዎች ጨምሮ የሌሎች ሀገራት ህንጻ ነዳፊዎች  ንግግር ያደርጋሉ።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

10 Nov, 00:30


ትምህርታዊ ንግግር።
ዘለቀ በላይ

ዘለቀ በላይ በካዛን፣ ሩስያ በሚካሄደው "International Architecture and Construction Forum" ላይ በስራዎቹ ዙርያ ንግግር ያደርጋል።


አገራችን እንደሌሎች ታዋቂ ጥበብ ሰዎች ሁሉ ህንጻ ነዳፊዎቿ በአለም መድረኮች ላይ መታየት መጀመራቸው እጅግ የሚያስደስት ነገር ነው።

Zeleke Belay will speak at Kazan.

Zeleke Belay, an architect and founder of Zeleke Belay Architects, will fly to Kazanysh from Ethiopia

The company implements large projects throughout Ethiopia, including office buildings, medical and educational institutions, stadiums and shopping centers.

In his work, the architect pays great attention to contextual architecture. Notable projects include the branches of Awash International Bank in Addis Ababa and the Stairs office building project, which explores the influence of climate on images in architecture.

"Each building should be a reflection of the local culture and climate, which makes it unique and important for the community. In Ethiopia, every room, every space would like to open outward to be able to breathe"

https://t.me/kazanush/345

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

08 Nov, 19:59


ታሪካዊ ኪነህንጻ።
ቤተክርስትያን።

ማርያም ኣይሮፈዳ፣ ገራዓልታ
ትግራይ

ምንጭ፦ The Living Churches of An Ancient Kingdom, Fitzgerald & Marsden, Architecture of The Tigre Ethiopia, Ruth Plant.

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

08 Nov, 19:19


አሁናዊ ኪነህንጻ
በሰቃ ሀይቅ።

ምንጭ። የ ጠቅላይ ሚኒስትር ፌቡ ገጽ
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

08 Nov, 09:47


ታሪካዊ ህንጻዎች

የአብረሃ ግንብ (ካስትል)
መቐለ

1968 ዓም።
በ ጀማል አብዱልአዚዝ በኩል
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

08 Nov, 03:00


የቆዩ የከተማ ምስሎች።

ብሔራዊ ትያትር አካባቢ የቀድሞው አድዋ አደባባይ። አዲስ አበባ

በ1962/63 ዓም
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

07 Nov, 19:14


የ ቀርከሀ እልፍኝ ግንባታ ምርቃት።

ዞማ መንደር፣ እንጦጦ ብሔራዊ ፓርክ።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

07 Nov, 06:55


ትምህርታዊ ንግግር
በ አሉላ ተስፋይ (ፒኤጅዲ)
ቅርስ ጥበቃ መንገዶች እና አብነቶች ከትግራይ።
ቀን ጥቅምት 29 2017
ግዜ። ከጠዋቱ 5:00 ሰዐት
ቦታ ዋናው መሰብሰብያ አዳራሽ።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

06 Nov, 20:31


አሁናዊ የከተማ ምስል።
ገበያ ዶርዜ አካባቢ።

ምስል። ዮናስ አሰፋ BCAA
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

06 Nov, 13:06


አሁናዊ የከተማ እይታ

ኮምቦልቻ

ምንጭ። Abdilkasem Kedir
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

06 Nov, 11:03


የቆዩ የከተማ ምስሎች።

አራት ኪሎ ምኒልክ ቤተመንግስት መግቢያ ፊት በር - ከ1905 ዓ.ም በፊት የተነሳ ፎቶግራፍ። አዲስ አበባ።

Entrance gate of the Palace of Emperor Menelik II in Addis Abeba sometime between 1907 & 1913

Scanned Image from a book published in Berlin back in 1920

Abessinien. Eine Landeskunde nach Reisen und Studien in den Jahren 1907-1913/Abyssinia: A regional survey based on travels and studies in the years 1907-1913:
https://www.biblethiophile.com/document/abessinien-eine-landeskunde-nach-reisen-und-studien-in-den-jahren-1907-1913/

በ Historic Ethiopia Through The Camera Lens 1860s-1990s በኩል።
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

05 Nov, 08:21


የሕንፃ አዋጁን መሻር ለምን አስፈለገ?

አዋጅ አይሻርም፤ ይሻሻላል እንጂ። በርግጥ ሊደረግ የታሰበው  ግን ከመሻር ተለይቶ የሚታይ አይደለም። ረቂቁ የባለሞያውን  ማለትም የአርኪቴክቱን ፡ የኢንጂነሩን ድርሻና ኃላፊነት እንዲቀርፅ ተደርጎ የተዘጋጀን አዋጅ ለድርጅት አሳልፎ ለመስጠት የተቀረፀ ረቂቅ ነው።

አንድ ቀላል ማሳያ እንመልከት። አሁን በስራ ላይ ያለው አዋጅ (ቁጥር 624 /2001) አንቀፅ 26 ምን ይላል?

26 የተመዘገቡ ባለሞያዎችን ስለመቅጠር 

ለማንኛዉም ህንፃ ህንፃው ለሚገኝበት ምድብ የሚጠየቁ የዲዛይን አይነቶች ለየስራው በሚመጥኑ የተመዘገቡ ባለሞያዎች መሰራት አለባቸው፡፡ ዝርዝሩ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡ የሕንፃዉ ግ ንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስም የባለሞያዎቹ ቁጥጥር ሊኖር ይገባል፡፡ የሕንፃ ዲዛይኑን ቴክኒካል ስራ የሚያስተባብረው አርኪቴክቱ ይሆናል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ አዲሱ ማሻሻያ ረቂቅ በለሞያ የሚለውን በቀጥታ በድርጅት በመተካት አንዴት እንደተለወጠ እንመልከት:

19. የተመዘገበ አማካሪ ድርጅት ስለመቅጠር፡ 
ለማንኛውም ህንፃ ህንፃው በሚገኝበት ምድብ የሚጠየቁ የዲዛይን ዓይነቶች ለግንባታው በሚመጥን በተመዘገበ አማካሪ ድርጅት መሠራት አለበት፡፡ የህንፃ ዲዛይኑን ቴክኒካል ሥራ የሚያስተባብረው የዲዛይን ባለሙያ የምስክር ወረቀት ያለው ወይም አርክቴክቱ ነው፡፡ ዝርዝሩ ይህን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣው ደንብ ይወሰናል፡፡ የህንፃው ግንባታ እስኪጠናቀቅ ድረስ የቁጥጥር ስራውን የሚያከናውነው አማካሪ ድርጅት የሥራ ተቋራጩን የግንባታ ባለሙያዎችንም ይቆጣጠራል፡፡ የግንባታ ሥራው ሲጠናቀቅ አማካሪ ድርጅት የፈረመበትና መጠናቀቁን የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ለተቋሙ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

አማካሪ ድርጅት በባህሪው ተለዋዋጭ የሆነ ፤ ንግድን ማእከል አድርጎ የሚቋቋም ተቋም በመሆኑ ቋሚ በሆነ ህንጻ አዋጅ ውስጥ የሚታቀፍ አይደለም፡፡

ይህ ከባለሞያ ወደ ድርጅት እንዲዞር ተደርጎ የተቀረፀ የሕንፃ አዋጅ አደጋ ምንድን ነዉ? የሕንፃ ሙያ ልክ እንደ ህክምና ፡ እንደ ህግ ባለሞያ በህግ ሊጠበቅ የሚገባ የሙያ ዘርፍ ነው። ይሄ የሚደረገው ደግሞ ባለሞያውን ለመጥቀም አይደለም። በዋነኛነት ማህበረሰቡ ተገቢውን የሙያ አገልግሎት በትክክለኛው ባለሞያ እንዲያገኝ ለማድረግ ነው።

ከተሞቻችን የተሻሉ ከተሞችና ተወዳዳሪ፣ ጤናማና ደህነነታቸው የተጠበቁ ከተሞች እንዲሆኑ ለማድረግ አዋጁ ስራው በቀጥታ ባለሞያው እንዲሰራው መደረጉን ማረጋገጥ አለበት። ዛሬ የህንፃ ፡ የከተማ ጥራት ወድቋል ብለን የምናስብ ከሆነ ይህ አዋጅ ቢፀድቅ ደግሞ ጨርሶ ይሞታል።

አለም አንድ እየሆነች ባለችበት ፤ በስራ እና በንግድ የአለም ትስስር እየጨመረ በመጣበት በዚህ ዘመን ህጎቻችን ከአለማቀፍ ህግጋት ጋር መተሰሳር አለባቸው፡፡ የአለማቀፍ የህንጻ ኮድ ክፍል 107 እንዲሚያሳየው ሃላፊነቱን የሚሰጠው ለተመዘገበ ባለሞያ ነው፡፡በሁሉም የአለም ዙሪያ ብንሄድ የምናገኘው ይህንኑ ነው፡፡  
በመሠረቱ በስራ ላይ ያለውን አዋጅ ለመቀየር የሚያስፈልግ ምንም ምክንያት የለም። አዋጅ እንደ መዋቅር ነው። ቋሚ የሆነ መርህን ተከትሎ  የሚዘጋጅ ነው። መነካት አያስፈልገውም። መሻሻል የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ በደንቡ ላይ ወይም በመመሪየዎች ላይ  መካተት ይችላሉ። 

ረቂቁ በቅርቡ ለፓርላማ ቀርቦ ለከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ  መመራቱ ይታወሳል፡፡ ቋሚ ኮሚቴውም ከዚያ በኋላ የዘርፉን ባለሞያዎች ጠርቶ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የቀረቡትን ግብአቶች ለማካተት ከፍተኛ ፈቃደኝነት አሳይቷል፡፡

ይህ ማሻሻያ መሠረታዊ የመርህ መዛባት የታየበት በመሆኑ መስተካከል ይኖርበታል፡፡

በ ዘለቀ በላይ። ዘለቀ በላይ ታዋቂ አርክቴክት እና የዘለቀ በላይ አርክቴክት አማካሪ ድርጅት ባለቤት እና ስራአስኪያጅ ።
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

03 Nov, 17:54


ውስጣዊ ንድፍ
ብርሀን ንድፍ።

ተመካሪ እና ስሁት የመኝታ ቤት ብርሀን ንድፍ።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

03 Nov, 16:23


የቆዩ ታሪካዊ ህንጻዎች ምስል።

እቴጌ ጣይቱ ሆቴል፣ አዲስ አበባ።
ከ1905 ዓ.ም በፊት የተነሳ ምስል።

Etege Taitu hotel in Addis Abeba sometime before 1913

Scanned Image from a book published in Berlin in 1920

Abessinien. Eine Landeskunde nach Reisen und Studien in den Jahren 1907-1913/Abyssinia: A regional survey based on travels and studies in the years 1907-1913:
https://www.biblethiophile.com/document/abessinien-eine-landeskunde-nach-reisen-und-studien-in-den-jahren-1907-1913/

በ Historic Ethiopia Through The Camera Lens 18y0s-1990s በኩል።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

02 Nov, 18:31


በነጻ የቀረበ መጽሀፍ።

Politics and the Urban Frontier: Transformation and Divergence in Late Urbanizing East Africa

መጽሀፉ በበይነመረብ ላይ በነጻ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ ርዋንዳ እና ኡጋንዳ ከተማዎች ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በነዚህ አገራት ያለው የከተማ ልማት እና ከልማቱ ጀርባ ያለው ፖለቲካዊ እሳቤ በተነጻጻሪ የተተነተነበት መጽሀፍ ነው።

ረቂቁ በእንግሊዘኛ የተያያዘ ሲሆን የመጽሀፉ ፒዲኤፍ ፋይል ከታች ተያይዟል። አውርደው ያንብቡት።

Abstract
Despite the rise of global technocratic ideals of city-making, cities around the world are not merging into indistinguishable duplicates of one another. In fact, as the world urbanizes, urban formations remain diverse in their socio-economic and spatial characteristics, with varying potential to foster economic development and social justice. This book argues that these differences are primarily rooted in politics, and if we continue to view cities as economic and technological projects to be managed rather than terrains of political bargaining and contestation, the quest for better urban futures is doomed to fail. Dominant critical approaches to urban development tend to explain difference with reference to the variegated impacts of neoliberal regulatory institutions. This, however, neglects the multiple ways in which the wider politics of capital accumulation and distribution drive divergent forms of transformation in different urban places. In order to unpack the politics that shapes differential urban development, this book focuses on East Africa as the global urban frontier: the least urbanized but fastest urbanizing region in the world. Drawing on a decade of research spanning three case-study countries (Ethiopia, Rwanda, and Uganda), Politics and the Urban Frontier provides the first sustained, book-length comparative analysis of urban development trajectories in Eastern Africa and the political dynamics underpinning them. Through a focus on infrastructure investment, urban propertyscapes, street-level trading economies, and urban political protest, it offers a multi-scalar, historically grounded, and interdisciplinary analysis of the urban transformations unfolding in the world’s most dynamic crucible of urban change.
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

02 Nov, 06:05


የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ ቦታ ማስታወቅያ።

1. መገናኛ ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ
ከመገናኛ - ቃሊቲ
ከመገናኛ - ሳሪስ
ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች
በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን

2. ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው;
ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ)

3. ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች
ከመገናኛ - ገርጂ
ከመገናኛ-ጎሮ
ከመገናኛ - አያት እና
ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው ያሳውቃል።

ምንጭ። ትራንስፖርት ቢሮ
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

01 Nov, 07:16


ታሪካዊ ኪነህንጻ

ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ላሊበላ

ይምርሃነ ክርስቶስ በ ዓፄ ይምርሃነ ክርስቶስ አነሳሽነት በ12ኛው ክፍለ ዘመን በአቡነ ዮሴፍ ተራራ ውስጥ በሚገኝ ዋሻ ውስጥ የተሰራ ቤተክርስቲያንና በዚያው ዋሻ ውስጥ ከቤተርክስቲያኑ ፊትለፊት ያለ ቤተ መንግስት ህንጻ በአንድነት የሚጠሩበት ስም ነው። ዋሻው ከላሊበላ የ6 ሰዓት የእግር ጉዞ ርቀት ላይ ይሚገኝ ሲሆን 45ሜትር ርዝመት በ6 ሜትር ቁመትና 50ሜትር ጉድጉደት አለው። በዋሻው ውስጥና ውጭ ለጸበል የሚያገለግሉ ምንጮች ይፈልቁበታል። ዓፄ ይምርሃነ ክርስቶስ ከሮሃ ሆኖ አገሩን ያስተዳድር እንጂ ይሄው ቤተክርስቲያንና ቤተመንግስት ሲታነጽ መኖሪያውን ወደዚህ ዋሻ እንዳዛወረ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ የህይወት ታሪኩ ይገልጻል። በ16ኛው ክፍልዘመን መጀመሪያ ኢትዮጵያን ጎብኝቷት የነበረው አልቫሬዝ እንዲሁ በዚህ ቤተክርስቲያን ለ2 ቀን ቆይታ በማድረግ ገድለ ይምርሃነ ክርስቶስ የተሰኘ መጽሐፍ እንዳነበበና እንደመረመረ ያትታል።

ዋቤ ድርሰት: ዊኪፔድያ

በምስሉ ላይ የሚታዩት የይምርሃነ ቤተክርስትያን ውጫዊና ውስጣዊ የኪነ-ሕንጻ ጥበባት ገጽታ ነው። ፎቶግራፎቹ ከ55 ዓመታት በፊት በኤድዋርድ ጉበሊን የተነሱ ነበሩ።

ምንጭ። ጀማል አብዱልአዚዝ
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

31 Oct, 20:06


የ ግንባታ ግብዓት ፋብሪካ ምርቃት።

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ምርት ለገበያ መቅረብ ጀመረ።

በቅርቡ ሥራውን የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በዛሬው ዕለት ምርት ለአከፋፋዮች ማስረከብና ማሰራጨት መጀመሩን አስታዉቁዋል

ለሚ ናሽናል የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ እህት ኩባንያ

ምንጭ። National Cement Share Company Dire Dawa.
@ethiopianarhitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

27 Oct, 12:19


ዘላቂ እና ታዳሽ የሀይል ምንጮች ንጽጽር።

ምንጭ። ዶ/ር ሞሀመድ ታሽ
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

27 Oct, 06:58


ለፈገግታ ያህል።

Less is More.

ምንጭ። architecturelab

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

26 Oct, 07:21


ህንጻ ብቃት ምርመራ።

በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ አንዱ ሂደት የህንጻ ብቃት ምርመራ (Property inspection Service ) ሲሆን ሁለቱ ወገኖች በዋጋና በክፍያ አፈጻጸም ሁኔታ ከተስማሙ በኋላ የሚደረግ ወይም ለአዳዲስ ቤቶች ግብይቱ ከተፈጸመ በኋላ ርክክብ ከመደረጉ በፊት የሚደረግ ምርመራ ነው።

ይህ ምርመራ በዘመናዊ መሳሪያዎች በመጠቀም የሚደረግ ሲሆን የሚያካትታቸው አገልግሎቶች መካከል የሚከተለሉት ይገኙበታል።የውሃ መስመር፣ የኤሌክትሪክ መስመርና ፣ መብራትና ሶኬት ላይ የሚደረግ የሃይል አቅርቦት መጠን ልኬታ፣ ግድዳና ኮርኒስ እንከኖች፣ የቀለም ውበት ይዘት አልጌና እርጥበት ፣ የተባይና ነፍሳት መኖር ለእነሱ መራቢያ ምቹ ሁኔታ መኖሩን ፣ በቂ የተፈጥሮ ብርሃን ማግኘቱን፣በርና መስኮት እንዲሁም ቁምሳጥኖች አገጣጠምና ተያያዥ እንከኖች.....

ይህንን አገልግሎት መሰረቱን አሜሪካ ያደረገው ኮረብታ ጎጆ (Korebta ጎጆ) በሃገራችን አስፈላጊ ዘመናዊ መሳሪያዎችን ከስልጡን ባለሙያዎች ጋር አዘጋጅቶ አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል። አገልግሎቱን በስልክ ቁጥሮቻቸው @0935271111 እና @0911342737 በመደወል ልታገኙ ትችላላችሁ።

የሚሰጡት አገልግሎትን ምን እንደሚመስል በዝርዝር ማወቅ የምትሹ የመረጃ ማቅረቢያ ገጽ ( Dashboard ) በማስፈንጠርያው ተያይዟል። የምርመራ ሪፖርቱ በአማኛም በእንግሊዝኛም ቋንቋ ይቀርባል።

https://korebta.com/inspector/dashboard/php/report_view.php?filename=reports_json%2Freport_670e3e8954142.json

ደሳለኝ ከበደ። መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ መሬትረገጥ ሀብት ልማት አማካሪ

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

26 Oct, 07:09


ዘመናዊ ኪነህንጻ።

አፍሪካ አዳራሽ።
የአዲስአበባን ዘመናዊነት ዘመን ያስከሰተው የመጀመርያው ባለብዙ ወለል የአፍሪካ አዳራሽ ህንጻ ነበር። በዚህም የባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ቴክኒካዊ ፋይዳው በተከታታይ በዚህ ጣብያ ይዘከራል።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

23 Oct, 21:12


https://www.ena.et/web/amh/w/amh_5343245?p_l_back_url=https%3A%2F%2Fwww.ena.et%2Fweb%2Famh%2Fsearch

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

22 Oct, 07:29


ዘመናዊ ኪነህንጻ።

ንግድ ባንክ
በ ሄንሪ ሾሜ
በ 1965 እኤአ የተገነባ።

እስከአሁን የዚህን የጉልላት ጥበብ የሚልቅ ኪነህንጻ አልገነባንም።

#ኪነህንጻእንደገናይላቅ
#makearchitecturegreatagain

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

22 Oct, 06:42


የቆዩ የመኖርያ አካባቢ ምስሎች

የገጠር ቤት አካባቢ
ጥር 1972

በ ታሪካችን ገጽ በኩል
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

22 Oct, 04:14


የ ቆዩ ታሪካዊ ምስሎች።
ቀኃስ ስቴድየም፣ አዲስ አበባ

1959/60 ዓ.ም

ምንጭ። FIFA Museum በ ጀማል አብዱልአዚዝ በኩል።

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

21 Oct, 18:00


ዛሬ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ማምሻዉን በመርካቶ ሸማተራ አየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በንግድ ሱቆች ላይ የተነሳዉን የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ለማዋል የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ እያደረጉ ነዉ።

ለአምላ ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንባላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!

እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን።
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

21 Oct, 15:48


ዘመናዊ ኪነህንጻ

ጀርመን ቤተክርስትያን፣ አዲስ አበባ።
በ እውቁ ፈረንሳዊ ነዳፊ በ ሄንሪ ሾሜ በ1950ዎቹ የተነደፈ።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

20 Oct, 15:44


🏙 URBAN OCTOBER - 2024

This year's discussions will feature key topics like Cities and Jobs, Just Cities, and Education and Cities. Join us as we discuss urban employment, equity, and education's vital role in building inclusive cities.

Lock your Calendar!!!

🔗 Registration Link:
https://cutt.ly/3eSDtgLX

ምንጭ። The Urban Centre
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

19 Oct, 19:48


የ ስነጥበብ እቅድ ውድድር።

ምንጭ። European Union National Institute for Culture

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

19 Oct, 17:38


የመጽሀፍ ስዕሎች ሰአሊ።

Looking for a book illustrator.
Do we have any good ones in Malawi?
Any in Ethiopia?

Inbox her on the link written on the image.

Catherine Sani

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

19 Oct, 12:00


ለፈገግታ ያህል።

ፋሲካ ካሳሁን BCAA
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

19 Oct, 08:55


አሁናዊ ንድፍ።

ሊብያ ኤምባሲ፣ አዲስአበባ።

በ ጌረታ ኮንሰልት ኃ.የተ.የግማ.

ጌረታ አማካሪዎች በማማከር ዘርፍ ብዙ ልምድ ያለው ድርጅት ሲሆን ከዚህ በፊት የቡርኪና ፋሶ ኤምባሲንም መንደፉ ይታወሳል።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

18 Oct, 17:51


The United Nations Economic Commission for Africa (UNECA) has finalized the renovation works on the legendary UNECA building. This building was designed by the known architect Aurtro Mezzedimi.

AEA is proud to host a half day panel discussion with a tour to the newly renovated UNECA hall, on October 23rd starting from 9am to 11:30am.

We have a place for 100 participants; hence members shall register on the following link below until Friday October 17 12:00pm, to attend the event.
Register here

https://forms.gle/JZvamhGGpdGJPXvy8

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

18 Oct, 14:11


ክፍት የስራ ቦታ

Job Posting: Site Engineer

Position: Site Engineer

Location: Bishoftu

Company: K2N Architecture and Engineering PLC

Employment Type: Contract for a year

Experience Level: Junior

About the Role:

K2N Architecture and Engineering PLC is seeking a highly skilled and experienced Site Engineer to join our dynamic team. In this role, you will be responsible to supervise construction of projects closely. The project needs commitment and high dedication due to its large volume and limited implementation time. The candidate: therefore, should make himself ready to work in tight conditions and extra hours with provision of accommodation on site.

Key Responsibilities:

Site Engineer:

Managing the daily operation of construction projects

Conducting regular site inspections to ensure adherence to health and safety regulations Interpreting and implementing construction plans as per the project blueprint
Liaising with subcontractors, architects, and other professional staff to ensure project requirements are met

Assessing potential risks and implementing preventive measures to mitigate them Ensuring materials and resources are used effectively and wastage is minimized Keeping accurate records of construction progress, changes, and other relevant information Resolving technical issues with the project team and offering advice on improvements and solutions Coordinate with clients, stakeholders, and local authorities to ensure smooth project execution Supervising and instructing the construction team as well as onsite laborers

Qualifications:

Education: Bachelor's degree in Civil engineering.

Experience: Minimum of six years of general experience and three years as assistant resident Engineer in a building project.

NB: The Candidate shall be willing to stay in camp at work site with the provision of all facilities. The candidate should also commit himself to work extended hour.

How to Apply:

If you are a strategic thinker with a passion for contract administration and a desire to make an impact, we want to hear from you! Please submit your resume and a brief cover letter through LinkedIn or directly to [[email protected]].
Application Deadline: [Oct 30,2024]

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

18 Oct, 09:05


የጋራ መኖርያ ቤቶች ጨረታ

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

18 Oct, 08:12


አዲስ መረጃ።

አዲሱ የይዞታ አስገዳጅ የ20 ሜትር የመንገድ አዋሳኝ ስፋት እና የ አነስተኛው የ500 ካሬ ሜትር ስፋት የማይተገበርባቸው ቦታዎች የተገለጹበት አግባብን የያዘ ደብዳቤ

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

16 Oct, 11:14


የመሬት አጠቃቀም ስርአት ወጥነት አለመኖር የብዝሀ ህይወት ላይ አደጋ ሆኗል ተባለ።

በምግብ ራስን ለመቻል እና ምርት በብዛት እና በስፋት ለማምረት የሚደረጉ ጥረቶች ምክንያት ብዝሃ ህይወት ችግር ገጥሞታል ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር መለሰ ማርዩ የደን መሬቶችን ወደ እርሻ መሬት መቀየር እና ረግረጋማ መሬቶች ላይ የሚደረጉ ሰፈራዎች በስፋት መታየታቸዉን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ የስነ ምህዳር መናጋቶች መግጠሙን የሚናገሩት ዶ/ር መለሰ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈጠሩ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ለዚህ ማሳያ ነዉ ብለዋል።

ዘለቄታዊ ያልሆነ የመሬት አያያዝ እና አጠቃቀም እንዲሁም ከህግ ዉጪ የሆኑ የአስተራረስ ልኬት የብዝሃ ህይወት መሠረቱን አሳጥቶታል ተብሏል።

በምግብ ራስን ለመቻል በሚል ሀሳብ የተፈጥሮ ደን መሬትን በማጥፋት ለምግብ ሰብል ምርት ማዋል በጥናት ሊመራ የሚገባ ነዉ ሲሉም ገልፀዋል።


ቁምነገር አየለ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Ethio FM 107.8
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

16 Oct, 06:26


ክፍት የስራ ቦታ

ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን።

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

16 Oct, 04:55


ባህላዊ ኪነህንጻ።

ጌይ ጋር (ሀረር ባህላዊ ቤት)

በ ጌይ ጋር ውስጥ ያሉ የመደብ ቦታ ስሞች
አሚር ነደባ፣ ጊዲር ነደባ፣ ጢት ነደባ፣ ሱትሪ ነደባ፣ ገብቲ ኤሔር ይባላሉ። እነዚህ የቦታ ስሞች በአራተኛው ምስል ላይ ተመልክተዋል።

ዋቢ። Harar Ethiopia Tour Services፣ ማህበራዊ ሚድያ

@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

15 Oct, 10:19


የቆዩ የከተማ ምስሎች።

አራት ኪሎ ላይ በ1923 ለቀኃስ ንግስና ተተክሎ የነበረው ቅስት ይሄን ይመስላል። ጣልያን በ1928 ሚያዝያ አዲስአበባ ከገባ በኋላ አፍርሶታል።

ምስሉ ከአራት ኪሎ ወደቤተመንግስት ሲታይ የተነሳ ነው።

ምስል በታሪካችን ገጽ በኩል
@ethiopianarchitectureandurbanism

Ethiopian Architecture Construction and Urbanism

14 Oct, 12:21


ለፈገግታ ያህል።

አሰሪ ደንበኞች ለንድፍ እና ለፈርኒቸርና ውስጣዊ ውበት ክፍያ ሲከፍሉ የሚሰማቸው ስሜቶች። 😂

ምስል። architecture lab
@ethiopianarchitectureandurbanism