የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች @eliasshitahun Channel on Telegram

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች

@eliasshitahun


ግጥም በድምጽ በጽሑፍ
ምርጥ አንድ ገፅ
በሰው የተነበቡ ግጥሞች
የአሪፍ መጽሐፍ ጥቁምታ
አጫጭር ታሪኮች

የሀሳብ ንሸጣዎችን ከሁሉም እንቃርማለን፡፡ፈጠራዎችን እንደመምባቸዋለን፡፡የኤልያስንም የሌሎችንም ከያነያንን ስራ እንታደማለን፡፡ ስለሀሳብ እንሰማለን፡፡ እናሰላስላለን፡፡ ሰክረን ሳይሆን ሰክነን፡፡ሀሳብን እናስበዋለን፡፡
ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች (Amharic)

ኤልያስ ሽታሁን ግጥም በድምጽ በጽሑፍ ምርጥ አንድ ገፅ በሰው የተነበቡ ግጥሞችን አጫጭር ታሪኮች እና እይታዎች፡፡ ለሀሳብ ንሸጣዎችና ፈጠራዎች ፣ ኤልያስ ሽታሁን በዕለት ካልሆነ ለያነያን ስራ እንቃርማለን፡፡ ሀሳብ ከሁሉም ተጠቃሚዎችን ለመምታት እንሰማለን፡፡ እናሰላስለማለን፡፡ ሀሳብን እናስበዋለን፡፡ ዘላለም የሚቆየው ሀሳብ ነው፡፡

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች

06 Oct, 18:48


"ለምን አትጸለይም?" አለው

አፉን ጠመም አርጎ
"ሙድ ትይዛለህ ኣ"

"እንዴት?"

"እንዴት ነው ምጸልየው
እየቃምቁ
ከስንቷ ጋ እየተኛሁ
እየጠጣሁ?"

አቀረቀረቀ።

"እና" ብሎ አየው

"እናማ እሱን እነዚን ስተው ወደፊት እጸልያለሁ" አለ

"የሚጸለየው እኮ እሱን ለመተው ነው።
"ኃጢያቴን ስተወው እጸለይያለሁ" ካልክ
መቼም ስለማትተተው አትጸለይም ማለት ነው።"

ቀና ማለት አቃተው።

ጓደኛው ወሬውን ቀጠለ
"ለመተው ስትጸለይ
ስለጸይክ ደሞ እሱ ይተውሀል።"


~ ~ ~ ~ ~

ኤልያስ ሽታኹን

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች

02 Oct, 20:06


"ሁሌ ባገኝህ አይሰለቸኝም" አለችው

"እውነትሽ ነው"

"አዎ ገና መተዋወቃችን ቢሆንም ደጋግሜ ላገኝህ እፈልጋለሁ"

ዝም ተባባሉ ረጅም ሰዓት።

"እኔ ምልህ ህይወት ላንተ ምንድነው አለችው?"

"ቀይሮ መድገም ነው" አላት

"ማለት"

"አሁን የሆነች ተራ ካፌ ቡና ትጠጪያለሽ ሲኖርሽ ሸራተን ነው ራሱን ቡና

አሁን አንድ ክፍል ቤትሽ ውሰጥ ትተኛለሽ
ሲኖርሽ አስር ክፍል ያለው ግን አንዱ ክፍል ብቻ ራሱን እንቅልፍ ትተኛለሽ

ደሀ ሆነሽ አረቄ ነው
ሀብታም ስትሆኚ ውስኪ ነው ቀይሮ መድገም

ሰው ለምን ይመስለሻል አንድ ደብር ደጋግሞ ከመሳለም ደብር የሚቀያይረው ቦታ ቀይሮ ጸሎት ለመድገም ነው።

በፊት የሆነ ልጅ ትወጃለሽ ስትለያይ
ልጅ የሆነ ትወጃለሽ
ያንኑ መውደድ ቀይሮ ነው መድገም ነው

የሆነ ዘፈን በሌላ ዘፈን ዘፋኝ ቀይሮ መድገም

የምታውቂውን ስብከት በሌላ ሰባኪ ወይም ቄስ ቀይሮ መድገም

በኢኮኖሚ ክላስ መሄድ ዝነኛ ስትሆኚ እዛው ፕሌን ውስጥ ቢዝነስ ክላስ ሆኖ ወንበር ቀይሮ በረራ መድገም

ሰው ሁሉ ገንዘብ የሚፈልገው የነበረውን ነገር ቀይሮ ለመድገም ነው።"

የሆነ ነገሯ ተዛባባት።

"በቃ የዘመኑን ከቨር ሙዚቃ ታውቂያለሽ?"

"አዎ" አለችው

"የኛ ሰው ህይወት እንደዛ ነው
የህይወት ከቨር በይው።
የሆነ የሆነ ነገር ቀንጭጮቦ መምጣት ቀጣጥሎ ማዜም
ቀያይሮ መድገም..."


"የሚቀጥለው አመት እደውልልሀለሁ" አለችው




(ኤልያስ ሽታሁን)

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች

30 Sep, 21:39


(የተሰዋ - ይዌድስዋ)

ኤልያስ ሽታኹን

-    -        -       -      -      -

ሰውነቱ  ወልቋል።

ተንበረከከ አጥንቱ ከወለሉ ሲጋጭ ይሰማል።

የሚናገረው ነገር ጠፋበት።

ልጅነቱ ትዝ አለው። በጣም ጎበዝ ተናጋሪ ነበር። ዛሬ አፉን የፈታበት ቋንቋው ጠፋው።

ፀጉሩን እየጠቀለለ
"ብሬን ስጨርስ መጣሁ"  አላት

ዝም አለችው።

"ደስታዬን ስጨርስ መጣሁ" አላት

ዝም።


"መልኬ ሲረገፍ መጣሁ
ጉልበቴን ስጨርስ መጣሁ
ጤናዬን ስጨርስ መጣሁ"
ብሎ  ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ!

ዝም አለችው።

ከውስጡ አንድ ድምጽ ሰማ

"እድሜህን ሳትጨርስ መምጣትህ ነው ደስታዬ" አለችው።

ጭራሽ ከፋው።

ዝም ብላ አየችው።

ዝም ብሎ አያት።

ሳቀ።

የልጅነቱ የአብነት ተማሪ እያለ የነበረው ስም ትዝ አለው። "ቄሴ"

እየሳቀ አለቀሰ።

የማይቆረጠው ፀጉሩ ትከሻውን ነክቶታል።

በፊት ተዓምረ ማርያም ሲነበብ ነበር ጃንጥላ የሚይዝበት እጁ አሁን
በሲጋራ የሚይዝበት  ጠቁሯል።

ሱሪውን ዝቅ አርጎት ሊወልቅ ደርሷል።

ለሎቲ የተበሳው ጆሮው ተደፍኗል።


ቅዱስ ዳዊት ከጠላቶቼ የተነሳ አረጀሁ እንዳለ
ገና በወጣትነቱ አርጅቷል።

ፊቱ ላይ አጥንት አለ።
ራሱን አየው።
አፈረበት በራሱ።

ጥግ ላይ የተቀመጡት ሽማግሌ ጋ አይኑ ተጋጨ። በግንባራቸው ጠሩት።...


"ጉዴ ነው" አለ በውስጡ።

"አቤት አባቴ...  እንኳን መጣህላት"

"ለማን"

"ለማርያም"

"ሰምተውኝ ነበር ማለት ነው አለ" ለራሱ

"ምን ዋጋ አለው ብለው ነው...አሁንማ ከረፈደ"

"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ፍቅሩ ለምን እንደማይቀንስ ታውቃለህ ?"

ዝም አላቸው።

"በፀጋ ስለሚያየን።
በዛሬ ማንነታችን ሳይሆን በፈጠረን ፀጋ ነው የሚያየን።  በልጀነት ንጽህናችን በበፊቱ ቀናነታችን በትንንሹ አግልግሎታችን ነው የሚያየው። አይኑ እስከዛሬ ከፀጋችን ተነስቶ አያውቅም።"

ልቡንም ጆሮውንም ሰጣቸው።

"በኛ ተስፋ የማይቆርጠው የልጅነት ፀጋችንን ስለሚያውቅ ነው። ሌብነትህን ሳይሆን ልጅ ሆነህ የዘመርከውን ዘማዊነትህን ሳይሆን ድሮ ፀበል የቀዳኸውን ገዳይነትህን ሳይሆን ቤተመቅደስ  መጥረግህን ነው የሚያየው። እግዚአብሔር ሰውን የሚያየው በፀጋው ነው።"

"እኔ ምን አለኝና ታዲያ ?"

ካንተ በላይ ያውቅሀል።
በፀጋህ ነው የሚያይህ ባሁኑ ኃጢያትህ አይደለም። እናት ልጇ ቢታሰር አትክደውም ልጅነቱን አስታውሳ ታዝናለች። ድሮኮ ተምሮ እንደዚህ ይሆንልኛል ብዬ ነበር የማስበው ብላ ልጅነቱን ነው የምታስታውስለት። አየህ እግዚአብሔር ልጅነታችን ጋ ነው አይኑም ልቡም።

ዕንባው ወረደ።


"ልጠይቅህ" አሉት

"ገብርኤል ማርያምን ከሰላምታ  በፊት ምንድነው ያላት"

ይዌድስዋ ትዝ አለው።
"ፀጋን የሞላብሽ ሰላምታ ይገባሻል"

"ጎበዝ
ማርያምም ፀጋን የሞላባት መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ናት። ሁሉንም የምታየው በፀጋ ነው። እንኳን አንተን ለሚቃወሟት ሳይቀር ሩህሩህ ናት። ለምን በልጅነት ፀጋቸው ነው የምታውቃቸው። ክፋት አታውቅም ቂም አታውቅም ለምን ፀጋን የሞላባት ናት።"

ጉልበታቸው ስር ወደቀ።
እጣን እጣን ሸተተው።

(ተፈጸመ)

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች

23 Sep, 19:31


ጸሎት እንደስካር
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~

ሀና በእግዚአብሔር ፊት አለቀሰች።
በደጁም ተንበረከከች።

ካህኑ ኤሊ
የአፏን እንቅስቃሴ አይቶ "ሰክራለች" አለ።

ያውም ካህን ነው።
ሲሆን ተጠግቶ ነው "ምነው" ሊላት ሲገባ ፈረደባት።
እንዲያውም ተናገራት "ወይን መጠጣት አቁሚ" አላት

ልክ ከዚህ በፊት ሰክራ የሚያውቃት ይመስል
"ስካርሽ እስከመቼ ነው" አላት

ይሄ በኛ ቢደርስ ይሄን ብንባል
አኩርፎ ለመውጣት ሀይማኖት ለመቀየር ሁለቴ ባላሰብን ነበር።

ሀና ግን አስረዳችው።

ታጋሽ ናትና እግዚአብሔር ባርያውን እንዲያየኝ ነው የምለምን አለችው።

አንዳንዴ እኮ
የናንተ ሀዘን የናንተ ለቅሶ ለአንዳንዶች ስካር ነው። ጤና ማጣትም ነው። ምን አልባትም ለብዙዎችም "ፋራነት" ነው።
ግን እንዲህ በሉት

"እኔስ ልቧ ያዘነበኝ ሴት ነኝ። ጠጅና የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈፈስሁ"

መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
1:15

የኤልያስ ሽታሁን ግጥሞች እና እይታዎች

21 Sep, 17:15


https://www.instagram.com/channel/AbYxgxZ8brld0Lk7/