አንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከጦር አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ ወደ ሌላ ሃገር ጉዞ ሲደርግ አንድ እጅግ አጥፊ የሆነ አውሎ ነፋስ ወደ እሱ አገር አቅጣጫ በመገስገስ ላይ እንዳለ ተመለከተና ባለው የጦር ኃይል አውሎ ነፋሱን አስቁሞ፣ “ወደ እኔ ሃገር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ነህ፡፡ ከእኔ ሃገር ሰው ማንንም እንዳማታጠፋ ቃል ካልገባህ አታልፍም አለው” አውሎ ነፋሱም፣ “በእርግጥ ነው ወደዚያ አቅጠጫ ነው የምሄደው፤ ነገር ግን የአንተን ሃገር ሕዝብ በፍጹም እንደማልነካ ቃል እገባልሃለሁ” አለው፡፡
ንጉሱ ከጉዞው ሲመለስ ከሃገሩ ሰዎች በርካታዎቹ እንደሞቱ ሰማ፡፡ በጣም በመቆጣት አውሎ ነፋሱን ተከታትሎ ደረሰበትና፣ “ማንንም እንደማትነካ ቃል ገብተህልኝ ለምንድን ነው ብዙ ሰው የገደልከው?” አለው፡፡ አውሎ ነፋሱም እዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ በሃገርህ አጠገብ አለፍኩኝ እንጂ የሃገርህን ህዝብ አንዱንም አልነካሁም፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ ግን ከባድ አውሎ ነፋስ መጣ የሚል ወሬ ተወርቶ በፍርሃትና በድንጋጤ አንዳንዱ በልብ ድካም፣ አንዳንዱ ሲሯሯጥ እርስ በርሱ ተረጋግጦ ነው የሞተው”፡፡
አንዳንዴ በሃገራችን ከሚከሰተው ችግር ይልቅ በችግሩ ላይ ያለን አመለካከት፣ የሚወርሰን ፍርሃት፣ የምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽና የፍርሃትና የድንጋጤ ስሜታችን ከማየሉ የተነሳ አዋቂዎቹ የሚነግሩንን መመሪያ በአአምሯችን አስበን አለመከተላችን ነው የሚያጠፋን፡፡
አንባቢዎቼ በወቅቱ በደረሰብን አስጊ ሁኔታ ስለራሳችንና ስለቤተሰቦቻችን የማሰባችን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምክንያት የለሽ ፍርሃት ከመተራመስና ራስን ለከፋ ነገር ከማጋለጥ እንጠበቅ፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ንስሐ ገብተን ፣ ቅዱስ ቁርባንን ተቀብለን እንዘጋጅ
ፈጣሪ እናንተንና የእናንተ የሆኑትን ሁሉ ይጠብቅላችሁ፡፡
╭══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╮
@Venisiya21 @Venisiya21
╰══•:|★✧♡💝♡✧★|: ══╯