የግራ ክርኔ ላይ በላቲን ቋንቋ እንዲህ ይላል 'Veni Vidi Vici' "መጣሁ፣ አየሁ፣ አሸንፌ ሄድኩ" ዓይነት ነው ትርጉሙ። 'university' ተማሪ እያለሁ ነበር የተነቀስኩት ።
ድሮ ሕይወት ማሸነፍ ትመስለኝ ነበር። ዓለምን የማበጃጃት ይመስለኝ ነበር ።
ደርሼ ሳይ ግን እንደሱ አልሆነም!
መጀመሪያ የነቀሰኝ ልጅ ጋር ሄጄ የቀኝ ክርኔ ላይ 'Amor Fati' የሚል ተነቀስኩ፤ ይሄም ላቲንኛ ነው። "ዕድልን መውደድ" ይሉት ትርጉም አለው። ዕድል ሁሉ የሚወደድ መስሎኝ ነበር።
ምድር ርህራዬ ያላት፤ የምትሰጠው ሁሉ የምንችለውን፤ መስሎኝ ነበር...ግን ዕድል የሚሻሟትም እንደሆነ አየሁ።
ላስታውሰው የማልፈልገውን ሽንፈት ጠጣሁ። እየመረረኝ... እየጎመዘዘኝ...ተጋትኩ።
I stand alone and stumble.
ሦስተኛው እንደ ድሮ ንቅሳቴ ብዙ ሰው በማይረዳው ላቲንኛ አይደለም። በቲሸርት ስሆን በሚታይ መልኩ ተነቀስኩ። የማወሳስበው ነገር የለኝም። ለማጨስ ውሰጥ ለውስጥ አልሄድም። ሱቁ ጋር ነው ሲጋራዬን የምለኩሰው፤ ማንንም ለማስደመም ቃላት አላሳምርም። የጉብዝናዬን ወራት አልተርክም።
. . .
ለሦስተኛ ጊዘ ተነቀስኩ...
'Tired soul' ይላል።
'መሸነፍን ቆዳ ላይ ማሳል ምን ጥቅም ይሰጣል?' አለኝ ።
"ማሸነፍንስ ቆዳ ላይ ማሳል ምን ጥቅም አለው?" አልኩት።
'ጥሩ ጊዜ ሲመጣልህ፤ ንቅሳቱ ክፉ ነገርህን እንዳያስታውስህ ነው!' አለኝ።
አላመንኩትም!
ስንቴ ወድቄ እጅ እንደ ሰጠሁ አላወቀም። መውደቅን ማመን ካላስፈላጊ መጋጋጥ እንደሚያድን አላወቀም ። መውደቅን ማመን ካላስፈላጊ ትግል እንሚያድን አያውቅም።
ይልቅ...
እንዴት እንደወደኩ በጠይቀኝ ... !!
© Adhanom Mitiku