በብልግና ሱስ የተፈተነው ወጣት
አስተማሪ ታሪክ
አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ ጃዛከሏሁ ኸይር አላህ መልካም ምንደህን ይክፈል እኔን ከመጥፎ ሱስ አላህ አንተን ሰባብ አድርጎ አሁን ማሻ አለህ ወጥቻለው አላህ ይጠብቀኝ ወደዛ ከመግባት። ምን መሰለክ በፊት ገና ተማሪ እየለው አንድ አስረኛ ክፍል የሚማር ልጅ የብልግና ቪዲዮ አሰየኝ ከዛም አዬውት ተመሰጥኩበት እንዴት ነው ምታገኘው ስለው በሚሞሪ ሞባይል ቤት ሄደክ አለኝ ካልሆነ በዚህ መንገድ ብሌ ሁኔታውን አሰየኝ ከዛም ያው ለኔ ስልክ የለኝም በገኘውት አገጣሚ ግን በፋዘርም ስልክ በወንድሜም እየገበው አያለው በቃ ሱስ ሆነብኝ ያኔ መንይም አልነበረኝም ግን አያደኩ ስመጣ መተው አልቻልኩም በክፍል ጎበዝ ሚባል ተማሪ ነበርኩ ከዛም የስምንተኝን ክፍል ምንስትሪ ተፈተንኩና ግን ያው ሱስ እንደነበረ 82Average እና 99 ፐርሰንተይል አመጣው ተወዳድሬ ስፔሻል ትምህርት ቤት ገባሁ። ከዛ ፈተናው ጀመረኝ ከቤት ስልክ ተገዘለኝ ምን ልበልህ ማጥናት የለ ሁሌ ስልኬን መነካካት የማይረበውን ዳውሎድ እየረኩ እያዬው ቀስ በቀስ ራሴን በራሴ መርካት ጀመርኩኝ ሁሌም ደጋጋምኩት በቀን ሁለቴ ለሶላት እታጠበለው ለፈጅርና ለአስር። በቃ ጭንቅለቴ፣ ስራዬ እሱ ሆነ ት/ት ተረሳ ሀሳቤም ሁሌ እዛው ነው። መርሳትም አበዛው እንደምንም አራት አመት አሳለፍኩና 12 ማትሪክ ተፈተንኩ ለጥቂት አለፍኩ። ወላሂ ነውምልህ ቤተሰብ ከ 600 በላይ ነው የጠበቁት እኔ ግን ለጥቂት አልፌ አሁን ዩንቨርስቲ ገባውና አንድቀን ያንተን ቻናል ተቀላቀልኩና ማንባብ ጀመርኩ ጉዳቱን ከዝሙት መራቅ እንዳለብኝ ሀራም እንደሆነ ተረደው እርግፍ አርጌ ተውኩት አሁን የ2 አመት የጤና ተማሪኝ አመሰግናለው።
ታሪኩ ባጭሩ ይሄን ይመስላል ፁሁፉን እንዳላረዝምባችሁ ልጁም ከጠቀሰው እንድ ሁለት መዘዞች እንመካከር እሱም የመርሳት ችግር ነው። ይሄ በሽታ ወይም ሱስ አእምሯችንን ስለሚቆጣጠረው የመርሳት ችግር እንዲፈጠርብን ትልቅ ሰበብ ይሆናል ይሄ ተጨባጭ እውነታ ነው።! ልባችንንም አእምሯችንንም እያደነዘዘውና አይደለም ሌላ ነገር ኢባዳ እንኳ እንዳያስደስተን ያደርጋል። ነገር ግን በዛ ቆሻሻ ምስል ውስጥ ሸይጧን ደስታ ያለ ያስመስልብናል እንጂ ምንም አይነት ደስታም እርካታም የለውም። ራሳችንን ሁሌም እንደቆሻሻ ሰው እንድናየውና እንድንጠላው፣ በህይወታችን ተሰፋ እንድንቆርጥ፣ ከሰዎችም እንድንገለል ያደርገናል።
እንዱሁም እነዚያ ልናሳክልቸው የምንፈልጋቸውን ህልሞቻችንን እና ትላልቅ አላማዎች እንድንተዋቸው ለመስራትም ምንም አይነት ሞራል እንዳይኖረን ትልቅ እንቅፋት ይሆናል። ስለዚህ ከዚህ ቀላል መስሎ ህይወታችንን ከሚያጨልም በሽታ ዛሬ ነገ ሳንል ልንወጣ ይገባናል። ካልሆነ በራሳችን እጅ ዱንያ አኼራችንን እናጨልመዋለን። አላህን ያመፅንበት መንገዶች መቸም ቢሆን ለህይወታችን መበላሸት ሰበብ እንጂ ጥቅም ኑሯቸው አያውቅም። አላህም ከትዕዛዜ ሚዞረውን የጥበትን የጭንቀትን ህይወት አኖረዋለሁ ብሎ ዝቶብናል። ራሳችንን እንጠብቅ ወደ አላህም እንመለስ። ወላሁ አእለም
Share🚨ሼር🚨 Share
በተከታታዩ ርእስ ሰፋ ያሉ ትምህርቶችን እንዱሁም በህይወታችን የሚያመጠብንን መዘዞች እንመካከራለን።
ወንድማችሁ ሙሁዱን ሰኢድ
በዝሙት አንዘምን ኢስላምዊ የቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሁኑን👇👇👇👍👍👍👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina