“የፈረስ ስሞች እና ታሪካዊ አመጣጣቸው!!”
…………የሀገራችን የጥንት ነገስታት፣ መሳፍንት፣ መኳንንት፣ ጀግኖች እና የጦር መሪዎች ፈረስ የመጋለብ ሙያ ነበራቸው።
የፈረስ ስም “አባ” የሚለውን ቃል በማስቀደም በአንዲት ቃል ብቻ የሚነገር ቢሆንም ጠለቅ ብለው ሲመረምሩት ግን ሰፊ ትርጉምና መግለጫ የያዘ ሆኖ ይገኛል። የፈረስ ስሞች የሚያመለክቱት የታዋቂ ሰዎችን የአስተዳደርና ዳኝነት ብቃታቸውን፣ ለጋስነታቸውን፣ ትክክለኛነታቸውን፣ ጀግንነታቸውን፣ ተንኮለኛነታቸውን፣ ቁጡነታቸውን፣ ሃይለኛነታቸውንና መሰል ባህሪያቸውን ነው።
…………አንዳንድ የፈረስ ስሞች ዘመኑን፣ ወቅቱን፣ ወይም የፈረሱን ባለቤት የግል ስብዕና ጭምር የሚያንፀባርቁ ናቸው። ለምሳሌ የእምዬ_ምኒሊክ ፈረስ…”አባ_ዳኘው” ሲባል በዘመኑ ዳግማዊ አፄ_ምኒሊክ የዳኝነትና የፍትሕ ስርዓት መዘርጋታቸውን ለማሳየት ተፈልጎ ነበር፣ የፈረስ ስም እንደክርስትና ስም ወይም አለማዊ ስም በካህናት ወይም በወላጅ የሚሰየም አይደለም።
……ብዙ ጊዜ የፈረስ ስሙ የሚወጣው ስራ አካባቢ ባሉ ሰዎች፣ በጦር መሪዎች ባልደረቦች……ሲሆን አንዳንዴም ሕዝቡ ያወጣል። ለምሳሌ የፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ የፈረስ ስም…”አባ_መቻል” ሆኖ ሳለ በፍርድ አዋቂነታቸውና በጦርነት ጊዜ መላ ስለማያጡ ሕዝቡ…”አባ_መላ” ብሏቸዋል።
……በተመሳሳይ የደጃዝማች በላይ_ዘለቀን ኮስታራነት የተመለከተው ሕዝቡ……”አባ_ኮስትር” በሚል ነበር ስያሜ ያወጣላቸው!!……ልጅ እያሱ በነገሱበት ዘመን ደግሞ ሀገሩ ሰላም የነበረ ሲሆን፣ በሰላም ወቅት ደግሞ አገር የሚያወራው ስለፍቅር እና ጤና ነውና በዚህ የሰላምና ጤና ዘመን ወደዙፋን የመጡት የልጅ እያሱ ፈረስም ይሄን መነሾ በማድረግ……”አባ_ጤና” የሚል የፈረስ ስያሜ ተሰጣቸው።
………የፈረስ ስሞች በጦር መሪዎች፣ ባልደረቦችና በህዝቡ ብቻ ሳይሆን የሚወጡት አንዳንድ ጊዜ አዝማሪዎች የሰጪውን ልብ ለመሳብና እጁን ፍራንካ ለማስፈታት በሚል……አባ_ባህር፣ አባ_ዝናብ፣ አባ_መንዝር በማለት መጠቀሚያ አድርገውት ነበር። ብዙ ጊዜ የፈረስ ስሞች የሚወጡት አንድን ጀግና ለማወደስ ሲሆን……ሁሉንም የፈረስ ስሞች ስንመለከት “አባ” የሚለው የኦሮምኛ ቅድመ_ግንድ ቅጥያ ምዕላድ አላቸው።
………በኦሮምኛ “አባ” ማለት አባት ወይም ባለቤት ማለት ሲሆን እነዚህ የኦሮሞ ባላባቶች ታዲያ ለፈረሶቻቸው ስም በማውጣት ፋና_ወጊ እንደሆኑ እና ከዚያም በኋላ የአማሮች እና የትግሬ ጦረኞች ፈረሶቻቸውን እና ራሳቸውን በዚህ የኦሮሞ ልማድ መጥራት መጀመራቸውን የታሪክ ድርሳናት ይናገራሉ።
………ብዙን ጊዜ የፈረሶቹ ስሞች የፈረሱ ጌታ እንዲታወቅለት የሚፈልገውን ነገር እንዲያንፀባርቁ የሚደረግ ሲሆን ሰዎቹም ተለይተው ይታወቁበት ነበር። ቅፅል_ስሙ የሚሰጠው በቀጥታ ለፈረሱ ቢሆንም የባለቤቱን……ሙያ፣ ባህሪ፣ ስራ፣ ታታሪነት፣ ጀግንነት የሚገልፅና የሚያሞግስ ስለሆነ ሰውዬውን የሚያኮራ እና የሚያስደስት ነው።
………ሴቶች እንደወንዶች በጀግንነት ውሎ ተሳትፎ የነበራቸው ቢሆንም የፈረስ ስም ግን ወጥቶላቸው አያውቅም። እስኪ ከታሪክ ማህደር ወደኋላ ተሻግረን በሀገራችን የነበሩ የጥቂት ነገስታትን፣ መሳፍንትን፣መኳንንትን፣ የጦር መሪዎችን እና የጀግኖች አርበኞችን የፈረስ ስሞች እንመልከት……………
*, አባ_ዳኘው………ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ
*,አባ_ታጠቅ………አፄ ቴዎድሮስ
*,አባ_በዝብዝ………አፄ ዮሃንስ
*,አባ_ጠቅል………አፄ ሃይለስላሴ
*,አባ_ዳምጠው………ንጉስ ሃይለመለኮት
*,አባ_ሻንቆ………ንጉስ ሚካሄል
*,አባ_ጤና………ልጅ እያሱ
*,አባ_ነፍሶ………ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ
*,አባ_ኮስትር……ደጃዝማች በላይ ዘለቀ
*,አባ_መላ………ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ
*,አባ_ጎራው………ፊታውራሪ ገበየሁ
*,አባ_ዲና………ንጉስ ሣህለስላሴ
*,አባ_ገስጥ……ራስ አበበ አረጋይ
*,አባ_ንጠቅ ገብሬ………ደጃዝማች ገብረማርያም ጋሪ
*,አባ_ይትረፍ………ራስ አባተ
*,አባ_ግርሻ………ራስ ዳርጌ
*,አባ_ድልድል……ራስ ዘውዴ
*,አባ_ጥጉ………ራስ ጎበና
*,አባ_ጠጣው………ራስ ወሌ
*,አባ_ነጋ………ፊታውራሪ ሸዋዬ ጓንጉል
*,አባ_ኮራን………ደጃዝማች ዘውዴ
*,አባ_ቃኘው………ልዑል ራስ መኮንን
*,አባ_ጠቅልል………ራስ ስብሃት አረጋዊ
*,አባ_ነጋ………ራስ አሉላ
*,አባ_ቀስቅስ………ልዑል ራስ እምሩ ሃይለስላሴ
*,አባ_ይርጋ………ልዑል ራስ ስዩም መንገሻ
*,አባ_ቀማው………ራስ ደስታ
*,አባ_ትንታግ………ቀኛዝማች ታደሰ
*,አባ_ግርማ………ደጃዝማች ስዩም ሉልሰገድ
*,አባ_ሰይጣን………ደጃዝማች ወልደ ገብርሄል
*,አባ_መብረቅ………ራስ ናደው
*,አባ_ሙላት………ቢትወደድ ሃይለጊዮርጊስ
*,አባ_ደፋር………ደጃዝማች ባሻህ አቦዬ
*,አባ_ሰብስብ………ደጃዝማች በየነ
*,አባ_ክረምት………ደጃዝማች ስለሺ ወልደ ሰማዕት
ምንጭ - #(ተመስገን ባዲሶ) "የፈረስ ስሞች እና ታሪካዊ አመጣጣቸው!!
ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን !!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
YOUTUBE : https://youtube.com/@Historical_Ethiopia
ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion
የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia