👉 ሁሉም የእርግዝና ምልክቶች ተሰምቷቸው ነገር ግን የምርመራ ውጤት እንደሌለ ሊያሳይ የሚችልባቸው አንዳንድ ምክንያቶች እነሆ፦
1. በጣም ቀደም ብሎ መመርመር፡ የእርግዝና ጊዜው በጣም አጭር ሊሆን ይችላል።መፍትሄው ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደገና መመርመር ነው!
2. ከምርመራው በፊት ብዙ ውሃ መጠጣት በሽንት እርግዝና የመታየት እድሉን ሊቀንስ ይችላል። የበለጠ ትክክለኛ ውጤት ለማግኘት ጠዋት የመጀመርያ ሽንት ላይ ይሞክሩት።
3. አንዳንድ ጊዜ ምርመራው በስህተት እንደሌለ ሊያሳይ ይችላል። የመረመሩበትን ምርት አይነት ወይም ላቦራቶሪ ቀይሮ መሞከር ፣ አስፈላጊ ከሆነ በደም ምርመራ ማድረግ።
4. የሆርሞን መዛባት፡- እንደ PCOS ያሉ ሁኔታዎች የእርግዝና ምልክቶችን ሊፈጥሩ ይችላሉ።
5. ስነ ልቦናዊ ምክንያቶች፡- ጭንቀት እና የመፀነስ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሴቶች ላይ አንዳንድ ጊዜ ሰውነት የእርግዝና ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል።
👉 ጥርጣሬ ካለብዎ በጣም ትክክለኛ የሆነ ምክር ለማግኘት ሁልጊዜ ከጤና ባለሙያ ጋር ይማክሩ።
👨⚕️ዶ/ር .ትዕዛዙ (የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት)
🏪 አዲስ ሕይወት ሆስፒታል(ሃያ ሁለት)
☎️ 0939011402