ልሳነ ግእዝ ⛪️ @geeztheancient Channel on Telegram

ልሳነ ግእዝ ⛪️

@geeztheancient


📚 ከዚህ ቻናል የግእዝ ቋንቋ ይማራሉ ማጣቀሻ መጻሕፍት እንለቃለን ።

YouTube 👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow


Ads
https://telega.io/c/geeztheancient

ልሳነ ግእዝ ⛪️ (Amharic)

ግእዝ እናዝማለን! ይሔ በልሳነ ግእዝ ማመን ላይ ማየት በማለት ስለ ግእዝ ቋንቋ ይማራል። እንደ አዲስ ቻናል፣ መለያን እና አጋጣሚያዊ ተውጣጡልን። እርስዎን በ YouTube ሊቀርበዋብን በመቀጠል ግእዝ ማህበረሰብን ማጣቀሻ ብሎ ላይ ይገኛል። ማጣቀሻ መጻሕፍት እንለቃለን። በመሣሪያ ገጽ የተለያዩ ድጋፎችን እና ለመቅጣት በመስራት ከ እኛ ጋር በተመደበደው አድራሻ በከፍተኛ ለማየት ተዘጋጅቷል። በማጣቀሻ ላይ እንደገና አሳልፈን ማለት ነው። የግእዝ ባለስልጣንን እና ሌሎችን አገልግሎቶች ለመጀመር ከአንዴት እስኪ ሃገርን ድርሻ በቀላሉ ግእዝን ባለማጣቀሻ ይጠቀሙ። በስልጣንም ሊሆን እንደሚገባበት የግእዝ ስልጠና ከሆነ አንድ ስልጥና ጋር እንመለሳለን። ለተጨባነም የልሳነ ግእዝ ይሁኑ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

07 Dec, 17:49


Metropolitan pavel of Vyshgorod and chorn

ይባላሉ የሩሲያ እና ዩክሬን ሊቀጳጳስ ናቸው።
በወቅቱ በተፈጠረው ጦርነት የራሳችሁን ሲኖዶስ ካልመሠረታችሁ ብሎ የዩክሬን መንግሥት አስሮ አስደብድቦ ጨለማ ውስጥ አስሮ አሰቃይቷቸዋል። ሙሉውን ግን እስቲ ስሙት ትሕትናቸው ግን ....🙏

ልሳነ ግእዝ ⛪️

05 Dec, 07:22


በውስጡ የሌለው የለም
ጠቃሚ apk ነው።
ለAndroid ተጠቃሚዎች።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

04 Dec, 12:10


🌿🌿🌿ስርአተ ንባብ🌿🌿🌿


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የግእዝ ንባባት አራት ወገን ናቸው። ማን ማን ናቸው ቢሉ፦

1ኛ/ ተነሽ

2ኛ/ ተጣይ

3ኛ/ ሰያፍ

4ኛ/ ወዳቂ ናቸው።

👆👆 እነዚህም  መድረሻ ፊደላቸውን መሰረት በማድረግ መረዳት እንችላለን።

➡️ ተነሽ፦ በ5 ፊደላት ይነገራል

➡️ ተጣይ፦ በ1 ፊደል ብቻ ይነገራል

➡️ ሰያፍ፦ በ1 ፊደል ብቻ ይነገራል

➡️ ወዳቂ ፦ በ7ቱም ፊደላት ይነገራል


🌿🌿🌿ማስረጃ 🌿🌿🌿

1ኛ/ ተነሽ

ተነሽ በ5 ፊደላት የሚነገር ሲሆን ድምጹ በጣም ከፍ ብሎ ይነበባል።  ይህም ማለት

👉 በግእዝ

👉 በካዕብ

👉 በሣልስ

👉 በራብዕ እና

👉 በሳብዕ፦

በእነዚህ መድረሻነት ይነገራል።

ለምሳሌ፦

በግእዝ

ፈለጠ = ለየ
አእመረ = አወቀ
ተሰፈወ = ታመነ
ሌቀ === ላየ

በካዕብ

ፈለጡ = ለዩ

አእመሩ  = አወቁ

ተሰፈው = ታመኑ

ሌቁ = አለቃ ሆኑ

    በሣልስ

አንቲ = አንች

ይእቲ = ያች

ሑሪ = ሒጅ

ነጽሪ = እይ

   በራብዕ

ሑራ = ሒዱ (የቅርብ ሴቶች)

እቀባ = ጠብቃት

አእምራ = እበቃት

ነጽራ = እያት

   በሳብዕ

ሀቦ = ስጠው ?

እቀቦ = ጠብቀው?

በሎ = በለው?

ነጽሮ  =  እየው?

2ኛ ተጣይ

👉 ተጣይ፦  በአንድ በሳድስ ፊደላት መድረሻነት የሚነገር ሲሆን ድምጹም ዝቅ ብሎ ወይንም ለስለስ ብሎ የሚነበብ ነው።

ለምሳሌ፦

በግስ 👇👇👇👇

ሑር =ሂድ

ስሙር = የተወደደ

ቅዱስ = የተመሰገነ

ፍቁር = የተወደደ

በስም👇👇👇👇👇

ማርያም

ሚካኤል

ሰላም

አስራት

3ኛ/ ሰያፍ

ሰያፍ፦  በአንድ በሳድስ ይነገራል። ድምጹም ከፍ ብሎ ወይንም ጠምዘዝ ብሎ ይነገራል። ከተጣይ የሚለየው በንባብ ብቻ ነው።

ለምሳሌ፦ በግስ👇👇👇👇👇

ቀድስ = አመስግን ?

ተሴሰይ = ተመገብ ?

ንሑር  = እንሂድ.?

ኢትፍልጥ = አትለይ ?.....

  በስም 👇👇👇👇👇

ያዕቆብ

ይስሐቅ

አብርሃም

ዮናስ......

4ኛ/ ወዳቂ

ወዳቂ በ7ቱም ፊደላት መድረሻነት የሚነገር ሲሆን ድምጹም በጣም ዝቅ ብሎ ይነበባል። ለምሳሌ፦

👇👇👇በግእዝ 👇👇👇

እስፍንተ

እሎንተ

አሐደ

አሐተ......

👇👇👇በካዕብ👇👇👇

እስፍንቱ

እሎንቱ

ዝንቱ

ዳእሙ.....

👇👇👇በሣልስ👇👇👇

አሐቲ

አእማሪ

መሳቲ

መርቆሪ......

👇👇👇 በራብዕ👇👇👇

ሶልያና

መዲና

መባልና

ሐና.....

👇👇👇በኀምስ👇👇👇

ሥላሴ

ቢረሌ

ህጥጥሜ

ቅዳሴ

    👇በሳድስ👇

"ዝ"   ብቻና ብቻ ነች።  ትርጉሟም "ይህ" የሚል ይሆናል።

ለቡ👉  መድረሻ ፊደላቸው "ዝ" የሆነው ሁሉ  ግን ወዳቂ ነው ማለት አይደለም።

👇👇👇በሳብዕ👇👇👇

አእምሮ

ከበሮ

ሎ ፣ ቦ

ጸሮ

ለቡ👉 አንድ ቃል ከአንድ ፊደል ጀምሮ ወዳቂ መሆን ይችላህ።

👉 ተነሽና ተጣይ ለመሆን ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ ፊደላት  መሆን አለበባቸው።

👉 ሰያፍ ለመሆን  ደግሞ ሦስት ፊደላትና  ከዛ በላይ መሆን አለባቸው።

ስለሆነም  "ዝ" ብቸኛዋ ከሰማንያ አሐዱ (81)
መጽሐፍ  ውስጥ ብቸኛዋ ወዳቂ ቃል ነች።

ለቡ 👉 ጥገኛ መስተዋድዶች  ራሳቸውን ችለው  ከአራቱ ንባባት ውስጥ አይመደቡም  ምክንያቱም ካልተጠጉ በስተቀር ይኖራቸውም ወይንም ትርጉም አይሰጡም።
ወይንም በዐሥሩ መራህያን   መጣመር ወይንም መደመር አለባቸው ማለት ነው።

ለምሳሌ፦ ምስለ = ጋር
የብቻውን ምንም አይነት ትርጉም   አይሰጥም።  ግን በዐሥሩ መራሕያን ጠጋ ሲል
ህይወት ይኖረዋል  ወይንም ትርጉም ይሰጣል።

ምሳሌ፦

ምስሌየ = ከእኔ ጋር

ምስሌነ = ከእኛ ጋር

ምስሌከ = ከአንተ ጋር

ምስሌክሙ  = ከእናንተ ጋር
.
.
.

ከመ = እንደ

ይህም ለብቻውን ትርጉም አይሰጥም ከመራሕያኖች ጋር ሲጠጋ ግን  ትርጉም ይሰጣል። ከመራሕያን ጋር ብቻ አይደለም ከቃል ጋርም  ሲጠጉ ትርጉም ይሰጣሉ። ለጊዜው ግን ከመራሕያኑ  ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንይ 👇👇👇👇 ከመ = እነደ

ከማየ = እንደ እኔ

ከማነ = እንደ እኛ

ከማከ = እንደ አንተ
.
.
.
.

ስለዚህም  ጥገኛ ምእላዶች ከአራቱ ንባባት ውስጥ አይመደቡም ከቃል ካልተጠጉ በስተቀር።

🙏 ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

ልሳነ ግእዝ ⛪️

04 Dec, 10:25


https://t.me/geeztheancient

ልሳነ ግእዝ ⛪️

04 Dec, 10:24


#ደብረ #ብርሃን ስሟን እንዴት አገኘች?

✍️ በዐስራ ዐምስተኛው ምእት ዓመት አባ እስጢፋኖስ የተባሉ አባት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ብዙ ክርክርን ያስነሳ አዲስ የተሐድሶ እንቅስቃሴ ከጉንዳጉንዲ ይዘው ተነሱ። የአባ እስጢፋኖስ አቋም ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ለወላዲት አምላክ ሥዕል፣ ለመስቀል ፣ ለንጉሥ አንሰግድም። ከቤተክርስትያን መጻህፍት ውጪ የሆኑትን አንቀበልም የሚል ነበር።

ይህ አቋማቸው በተለይም ከንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ጋር ሊያግባባቸው አልቻለም። ደቂቀ እስጢፋኖስ በመባል የሚታወቁት የአባ እስጢፋኖስ ደቀመዛሙርትም በዚህ እምነታቸው የተነሳ ብዙ ፍዳና መከራን ተቀብለዋል።

ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ደቂቀ እስጢፋኖስን ከሊቃውንቱ ጋር ሁኖ በአደባባይ ተከራክሮ ቢረታም ደቂቀ እስጢፋኖስ አቋማቸውን አልቀየሩም ነበር። በዚህም የተነሳ በድንጋይ እንዲወገሩ ተፈርዶባቸው ሕዝብ በተሰበሰበበት በዕለተ ዓርብ የካቲት ኹለት ቀን ወገሯቸው። ደቂቀ እስጢፋኖስ በድንጋይ በተወገሩ በሰላሳ ስምንተኛው ቀን መጋቢት 10 ቀን ግን አንድ ተዓምር ታየ። በንጉሡ አደባባይ ላይና ከንጉሡ አደባባይ ሩቅ እስከሆነ ቀበሌ ድረስ ትልቅ ብርሃን ወጥቶ እንደ ጐርፍ ፈሰሰ፡፡ ያም ብርሃን በቤተ ክርስቲያኖች ላይ፥ በልብሳቸው፥ በውስጥ መጋረጃቸውና በውጭው በሐር መጋረጃ፥ በጥጥ መጋረጃም ላይ ተገለጠ፡፡ ዳግመኛም ያ ብርሃን በሰዎች ድንኳን ውስጥ፥ በመጋረጃቸው ላይ ፥ በሚለብሱት ልብሳቸው ላይ፥ በሚታጠቁበት ትጥቃቸው ላይ፥ በእቃውም ሁሉ ላይ ሰፍኖ ታየ፡፡ በንጉሡ ሰፈር ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡

የብርሃኑ መውረድ ለእስጢፋኖሳውያን ስሕተተኛነት ለካህናቱ ደግሞ ትክክለኛነት ምስክር ነው በሚል ተተርጉሟል።

ያ ብርሃን እየታየ ብዙ ቀን ቆየ፡፡ የብርሃኑ መልክ የእሳት ነበልባል ይመስላል፡፡ ነገር ግን አያቃጥልም፡፡ ሰውንም ሲቀርበው ፊቱን ያበራዋል፡፡ ብርሃኑን ማየት ልብ ያስደስታል:: ስለዚህ ያችን ኢባ የምትባለዋን ቦታ ሁሉም ወደዳት፣ ንጉሡም ደብረ ብርሃን ብሎ ጠራት፡፡” ንጉሡ የጥንት ስሟ ኢባ የነበረውን ቦታ ደብረ ብርሃን ቢላትም ደቂቀ እስጢፋኖስ “ ሃገረ ደም” ይሏታል።

✍️ እንግዲህ ደብረ ብርሃን የዛሬዋን ስያሜ ከመያዟ በፊት መጠሪያ ስሟ ኢባ ነበር። ለዛሬ ስሟ መጠሪያ የሆነውን ተአምር ንጉሡ ከሃዲዎችን በመቅጣቱ የታየ ምሕረት አድርጎ ሲቆጥረው ደቂቀ እስጢፋኖስ ግን የእግዜብሔር ቁጣ እንጂ ምሕረት አይሉትም።

ምንጭ
ደቂቀ እስጢፋኖስ መጽሐፍ በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

https://t.me/geeztheancient

ልሳነ ግእዝ ⛪️

03 Dec, 19:16


📚 ስምዐ፡ ጲላጦስ

በስመ፡አብ፡ወወልድ፡ወመንፈስ፡ቅዱስ አሐዱ፡አምላክ ድርሳን ዘደረሰ ቅዱስ ወብፁዕ፡ አባ፡ ህርያቆስ፡በሀገረ ብህንሳ በእንተ፡ ዘኮነ ስምዐ ጲላጦስ መስፍን በሀገረሮሜ፡ብእሲቱ:ወደቂቁ ፡ ወበእንተ ኵሉ ፡ ዘረከቦሙ፡ እምአይሁድ፡ እኩያን፡ወካዕበ ፡ በእንተ፡ዘረከቦሙ:ለንጹሐን ወብፁዓን ፡ አርድእተ ኢየሱስ ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ወረከቦሙ: አባ ህርያቆስ፡ጸሐፈ፡መጽሐፈ፡ ገማልያል ወአበዮስ፡በአንተ ተአምራት፡ ወመንክራት፡ እንተ፡ አስተርአየት ፡ እመቃብሩ፡ለእግዚእነ፡ወመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ እምድኅረ ትንሣኤሁ፡ እምውታን። በሰላም እንተ፡ እግዚአብሔር፡ አብ፡አሜን ፨

[ክፍል ]

ወነበረ፡ ብእሲ እምድኅረ ትንሣኤሁ፡ ለእግዚእነ፡ ወመድኅኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ እምውታን ፡ ወዕርጉቱ ውስተ ሰማያት፡ በውዳሴሁ፡ ዘኢይትክሀል ይትናገር ወዘከመ ነበረ፡ ውስተ፡ አርያም ፡ በየማነ፡ አብ፡ወእምድኅረዝ፡ኵሉ፡አስተርአየ፡ተአምራተ፡ ወመንክራተ በዙኀን፡ እመቃብሩ፡ቅድስት፡ ወነበረ ብእሲ፡ ዘስሙ፡ጲላጦስ፡ መሥፍነ ኢየሩሳሌም፡ወብእሲቱ: አብሮቅላ ወይገይሱ፡ኀበ፡ መቃብሩ:ቅዱስ ወይጼልዩ፡በህየ ወሶበ ርእዩ ተአምራተ፡ወመንክራተ ዘያስተርእ አምኔሁ ነበሩ እንዘ፡ ይገብሩ ሠናያተ፡ብዙኅ፡ለነዳያን ወለምስኪናን።


https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

02 Dec, 07:53


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ' ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበረከተቻቸው ስጦታዎች ብዙ ናቸው፤
ከነዚህም፦
ሀ-ሙሉ ትምህርት
ለ-ፍጹም ቋንቋ ከነፊደሉ
ሐ-ስነ-ጽሑፍ ከነጠባዩ፡ ከነሙያው መ-ኪነ ጥበብ በየዓይነቱ
ሠ-ስነ-ጥበብ በየመልኩ ረ-ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርስ
ሰ- እምነት ከነፍልስፍናው ሸ-ነፃነት ከነክብሩ
ቀ- አንድነት ከነጀግንነቱ
በ-አገር ከነድንበሩ ከነፍቅሩ
ተ—ስም ከነምልክቱ «ከነትርጉሙ»
አሁንም ቢሆን ትውልዱ ጀግንነትን 'አገር ወዳድነትን ለታሪክ' ለባህልና ለሃይማኖት ተቆርቋሪነትን ይዞ እንዲያድግ በማስተማርና በማበረታታት ቤተ ክርስቲያን የበኩሏ ድርሻ አላት።

አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘሸዋ


https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

02 Dec, 07:28


ገጽ ፭

ቅኔ እም ኀበ መጋቤ ምስጢር ያሬድ ዘርአ ቡሩክ
➢#.፩. ዕዝል ጉባኤ ቃና

ከርካዐ ሃይማኖት ተክሊል እንተ ፈድፈደ ጸጋሁ፤
ጸገየ ጽጌ ተዋሕዶ ወፈረየ ናሁ፤


ጉባኤ ቃና
ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረክብነ፤
በኃይለ መስቀሉ ለወልድ ዘተቤዘወ ኪያነ።


ይላል ማለት ነዉ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

02 Dec, 07:24


አገባብ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

01 Dec, 11:56


#ሊቀ ትጉሃን መሪጌታ #ልዑል​ መኰንን የድሬዳዋ ሳባ ደብረ ሐይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ ሆነው ዛሬ ሕዳር ፳፫/፳፻፲፯ ዐ.ም ተመደቡ። በመድረኩም የሚከተለው ድንቅ ቅኔ ቀርቦላቸዋል።

.
.
.
.
ዕዝል ጉባኤ ቃና

• ኦ ቆሞስ ትባርከኒ በዘዚአከ መስቀል፥
•  አማሕፀንኩከ ለከ በእግዚአብሔር ልዑል።

ዕዝል ጉባኤ ቃና

•  መጋቤ ሠናያት ሠናይ ለገብርከ እስመ አልብየ ምንተኒ፥
•  በእግዚአብሔር ልዑል ሠናያቲከ ሀበኒ።

ሙሉውን ከታች ባለው ሊንክ ተከተሏቸው 👇
https://youtu.be/XKL0hGKDMGI?si=90bvkU26XAzPBvhy

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Nov, 09:10


Please Share it
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ከሌሎች ልዩ የሚያደርጋት እንደመላእክት ስቡሕ ወውዱስ ብላ በምታመሰግንበት ሥርዓተ ማኅሌቷ ነው። ይህ ሥርዓተ ማኅሌት ደግሞ በዋናነት አቋቋም በሚባለው የቤተክርስቲያን ትምህርት ይሰጣል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአቋቋም ምስክር መምህር የሆኑት የኔታ መጋቤ አእላፍ ክቡር ጥላሁን ናቸው። እርሳቸው የአቋቋም ትምህርት በጥራት ተደራሽ ይሆን ዘንድ በአቋቋም ትምህርት ዙሪያ መጻሕፍትን ጽፈዋል። በፎቶው የምትመለከቷቸው መጻሕፍት በቅርብ ያዘጋጇቸው መጻሕፍት ናቸው።
፩. ምሥጢረ ልቡና
፪. የመዋሥዕት አቋቋም
የመዋሥዕት አቋቋም በሥርዓተ ፍትሐት በየበዓሉና በየዘመኑ የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር አጠቃልሎ የያዘ መጽሐፍ ነው። ምሥጢረ ልቡና ደግሞ የቅኔ ፈጠራን የያዘ ድንቅ መጽሐፍ ነው። በነገራችን ላይ የኔታ መጋቤ አእላፍ ክቡር ጥላሁን ወደ 1400 (አንድ ሺ አራት መቶ የሚጠጉ) የአቋቋም መምህራንን አስተምረው ያስመረቁ ታላቅ የቤተክርስቲያን ሊቅ ናቸው። በመላው ሀገሪቱ በብዛት ቤተክርስቲያንን በማኅሌት የሚያሸበርቋት ሊቃውንት ወይ ከእርሳቸው የተማሩ ናቸው ወይም እርሳቸው አስተምረው ካስመረቋቸው መምህራን የተማሩ ናቸው። መጽሐፉን ማከፋፈል የምትፈልጉ የመጻሕፍት አከፋፋዮች በሚከተሉት አድራሻዎች ጠይቃችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።

መጋቤ አእላፍ ክቡር ጥላሁን
0918704187
ዘመን ሄኖክ
0911993368

በ መምህር
#Betremariam #Abebaw

ልሳነ ግእዝ ⛪️

29 Nov, 17:26


ነቢያት ፡ ይትፌስሑ ፡ ሐዋርያት ፡ ይትሐሰዩ ፡ በውስቴታ ፡ ወዳዊት ፡ ይዜምር ፡ በውስተ ፡ ማኅፈዲሃ፡፡

†††
ቅንዋት †††
ይቤ ፡ ዳዊት ፡ በመዝሙር ፡ ወሰብሒዮ ፡ ለአምላክኪ ፡ ጽዮን፤
ነቢይኑ ፡ ይቤ ፡ እግዚኦ ፡ ሰማዕኩ ፡ ድምፀከ ፡ ወፈራህኩ፤
እትመረጐዝ ፡ በዕፀ ፡ መስቀልከ፤
ስማዕ ፡ ጸሎተ ፡ ኵሉ ፡ ዘሥጋ ፡ ዘመጽአ ፡ ኀቤከ፡፡

†††
ሰላም †††
ዘካርያስ ፡ ርእየ ፡ ተቅዋመ ፡ ማኅቶት፤
ገነተ ፡ ትፍስሕት ፡ መካነ ፡ ዕረፍት፤
እንተ ፡ ይእቲ ፡ ማኅደር ፡ ለካህናት፤
ለእለ ፡ የኃድሩ ፡ በፈሪሃ ፡ እግዚአብሔር፤
ይእቲኬ ፡ ቤተ ክርስቲያን፤
በውስቴታ ፡ የዓርጉ ፡ ስብሐተ ፡ ካህናት ፡ በብዙኅ ፡ ትፍስሕት ፡ ወሰላም፡፡

†††††††††††††††

ልሳነ ግእዝ ⛪️

29 Nov, 17:26


ኅዳር ፳፩ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በማኅሌት ጊዜ የሚባል ወረብ ፡፡

ሙሉ የማኅሌቱን ዘር ለማግኘት 👇🏿👇🏿👇🏿


†† 1 ††
ሰላም ፡ ለኵልያቲክሙ ፡ እለ ፡ ዕሩያን ፡ በአካል፤
ዓለመክሙ ፡ ሥላሴ ፡ አመ ፡ ሐወፀ ፡ ለሣህል፤
እምኔክሙ ፡ አሐዱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ቃል፤
ተፈጸመ ፡ ተስፋ ፡ አበው ፡ በማርያም ፡ ድንግል፤
ወበቀራንዮ ፡ ተተክለ ፡ መድኃኒት ፡ መስቀል፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ፤
ዕዝራኒ ፡ ርእያ ፡ ለጽዮን ፡ ቅድስት፤
እንዘ ፡ ትበኪ ፡ከመ ፡ ብእሲት፡፡

††† 2 †††
ሰላም ፡ ለዝክር ፡ ስምኪ ፡ ዘመንክር ፡ ጣዕሙ ፤
ለወልድኪ ፡ አምሳለ ፡ ደሙ ፤
መሠረት ፡ ሕይወት ፡ ማርያም ፤
ወጥንተ ፡ መድኀኒት ፡ ዘእም ቀዲሙ፤
ኪያኪ ፡ ሠናይተ ፡ ዘፈጠረ ፡ ለቤዛ ፡ ዓለሙ ፤
እግዚአብሔር ፡ ይትባረክ ፡ ወይትአኰት ፡ ስሙ፡፡

ዚቅ
ዘዘካርያስ ፡ ተቅዋም ፡ ዘወርቅ፤
ዘሕዝቅኤል ፡ ነቢይ ፡ ዕፁት ፡ ምሥራቅ ፤
ለመሠረትኪ ፡ የኃቱ ፡ ዕንቈ፤
ሰአሊ ፡ ለነ ፡ ማርያም ፡ በአሚን ፡ ንጽደቅ፡፡

††† 3 †††
ነቢያተ ፡ እሥራኤል ፡ ጸሐፉ ፡ በመጽሐፎሙ ፡ እሙነ፤
ነገረ ፡ ሰቆቃው ፡ ወላህ ፡ በዘመኖሙ ፡ ዘኮነ፤
ውስተ ፡ አፍላጋ ፡ አመ ፡ በጼዋዌ ፡ ነበርነ፤
ውስተ ፡ ኵሃቲሃ ፡ እንዚራቲነ ፡ ሰቀልነ ፤
ሶበ ፡ ተዘከርናሃ ፡ ለጽዮን ፡ እምነ፡፡

ዚቅ
ወይቤላ ፡ ኢትሬእዪኑ ፡ ላሃ ፡ ዚአነ፤
እንተ ፡ ረከበተነ ፡ በእንተ ፡ ጽዮን፤
ዕዝራኒ ፡ ርእያ ፡ ወተናገራ ፡፡

ወረብ
ወይቤላ ፡ ኢትሬእዪኑ ፡ ላሃ ፡ ዚአነ ፡ እንተ ፡ ረከበተነ ፤
ዕዝራኒ ፡ ርእያ ፡ ወተናገራ ፡

††† መልክዓ ማርያም †††
††† 4 †††
ሰላም ፡ ሰላም ፡ ለዝክረ ፡ ስምኪ ፡ ሐዋዝ፤
እምነ ፡ ከልበኒ ፡ ወቍስጥ ፡ ወእምነ ፡ ሰንበልት ፡ ምዑዝ፤
ማርያም ፡ ድንግል ፡ ለባሲተ ፡ ዐቢይ ፡ ትዕዛዝ፤
ይስቅየኒ ፡ ለለጽባሑ ፡ ወይነ ፡ ፍቅርኪ ፡ አዚዝ፤
ከመ ፡ ይሰቅዮ ፡ ውኂዝ ፡ ለሠናይ ፡ አርዝ፡፡
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ፫ እምነ ጽዮን በሀ፤
ቅድስት ፡ ቤተ ክርስቲያን ፡ ሥርጉት ፡ በስብሐት፤
ዓረፋቲሃ ፡ ዘመረግድ ፡ ሥርጉት ፡ በስብሐት፤
ወማኅፈዲሃ ፡ ዘቢረሌ ፡ ሥርጉት ፡ በስብሐት፤
እምስነ ፡ ገድሎሙ ፡ ለሰማዕት ፡ ሥርጉት ፡ በስብሐት፤
ታቦተ ፡ ሕጉ ፡ ለንጉሥ ፡ ዐቢይ ፡ ሥርጉት ፡ በስብሐት፤
እንተ ፡ ክርስቶስ ፡ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ፡ ጽድቅ ፡ ያበርህ ፡ ለኪ፡፡
ወረብ
እንተ ፡ ክርስቶስ ፡ መሠረትኪ ፤ ፀሐየ ፡ ጽድቅ ፡ ያበርህ ፡ ለኪ ፡ ፀሐየ ፡ ጽድ(ቅ)፤
ለሰማዕት ፡ ሥርጉት ፡ በስብሐት፤ ሥርጉት ፡ በስብሐት፡፡

††† 5 †††
ሰላም ፡ ለአስናንኪ ፡ ሐሊበ ፡ ዕጐልት ፡ ዘተዛወጋ፤
ወመራዕየ ፡ ቅሩፃት ፡ እለ ፡ እምሕፃብ ፡ ዐርጋ፤
ማርያም ፡ ድንግል ፡ ለደብተራ ፡ ስምዕ ፡ ታቦተ ፡ ሕጋ ፤
አፍቅርኒ ፡ እንበለ ፡ ንትጋ ፡ ለብእሴ ፡ ደም ፡ ወሥጋ፤
ዘየዐቢ ፡ እምዝ ፡ ኢየኃሥሥ ፡ ጸጋ፡፡
ዚቅ
ታቦተ ፡ ሕጉ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ በካህናት ፡ ሕጽርት፤
ወበመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ክልልት፤
ንጉሥኪ ፡ ጽዮን ፡ ኢይትመዋዕ ፡ በፀር ፡ ወኢየኀድጋ ፡ ለሀገር፡፡
ወረብ
ታቦተ ፡ ሕጉ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ በካህናት ፡ ሕጽርት ፤ ወበመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ክልልት፤
ንጉሥኪ ፡ ጽዮን ፡ ኢይትመዋዕ ፡ በፀር ፡ ወኢየኀድጋ ፡ ለሀገር፡፡

††† 6 †††
ሰላም ፡ ለከርሥኪ ፡ ዘአፈድፈደ ፡ ተበጽዖ፤
እም ታቦተ ፡ ሙሴ ፡ ነቢይ ፡ ለጽሌ ፡ ትእዛዝ ፡ ዘየኀብኦ፤
ማርያም ፡ ድንግል ፡ ጊዜ ፡ ጸዋዕኩኪ ፡ በአስተብቍዖ፤
ለፀርየ ፡ ብእሴ ፡ አመጻ ፡ ኀይለ ፡ ዚአኪ ፡ ይጽበኦ፤
እስከነ ፡ ያሰቆቁ ፡ ጥቀ ፡ ድኅሪተ ፡ ገቢኦ፡፡
ዚቅ
ሃሌ ፡ ሃሌ ፡ ሉያ ፡ በጾም ፡ ወበጸሎት፤
ተመጠወ ፡ ሙሴ ፡ ኦሪተ፤ ጽላተ ፡ አሥሮነ ፡ ቃላተ፡፡
ወረብ
ሃሌ ፡ ሃሌ ፡ ሉያ ፡ በጾም ፡ ወበጸሎት፤
ተመጠወ ፡ ሙሴ ፡ ኦሪተ፤ ጽላተ ፡ አሥሮነ ፡ ቃላ(ተ)፡፡

††† መልክአ ማርያም †††
ሰላም ፡ ለመከየድኪ ፡ እለ ፡ ረከቦን ፡ መከራ፤
እምፍርሃተ ፡ ቀተልት ፡ ሐራ ፡ እንበለ ፡ አሣእን ፡ አመ ፡ ሖራ፤
ጽዮን ፡ ታቦተ ፡ ቃለ ፡ ጽድቅ ፡ መንፈቃ ፡ ዕሥራ፤
ዕጐላት ፡ እም ዕጐሊሆን ፡ ከመ ፡ ኪያኪ ፡ አፍቀራ፤
አፍቀርኩኪ ፡ አፍቅርኒ ፡ እም ይእዜ ፡ ለግሙራ፡፡
ወረብ
ማርያም ፡ ጽዮን ፡ ታቦተ ፡ ታቦተ ፡ ፋሲለደስ ወኢያሱ ፡ ታቦተ ፡ ቃለ ፡ ጽድቅ፤
ዕጐላት ፡ እም ዕጐሊሆን ፡ ከመ ፡ ኪያኪ ፡ አፍቀራ፤ አፍቀራ ፡ እም ዕጐሊሆ(ን) ፡፡
ዚቅ
ሃሌ ፡ ሉያ ፡ ወሪድየ ፡ ብሔረ ፡ ሮሜ፤
ለቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ርኢክዋ፤
አእመርክዋ ፡ አፍቀርክዋ፤ ከመ ፡ እኅትየ ፡ ኀለይኩ፤
እም ድኅረ ፡ ጉንዱይ ፡ መዋዕል፤
ወእምዝ ፡ እም ድኅረ ፡ ኅዳጥ ፡ ዓመታት፤
ካዕበ ፡ ርኢክዋ ፡ ወትትሐፀብ ፡ በፈለገ ፡ ጤግሮስ ፡፡
ወረብ
ሃሌ ፡ ሉያ ፡ ወሪድየ ፡ ብሔረ ፡ ሮሜ፤
ለቤተ ክርስቲያን ፡ ርኢክዋ፤ አእመርክዋ ፡ አፍቀርክዋ፤ ለቤተ ክርስቲያን ፡፡

††† መልክአ ማርያም †††
በዝንቱ ፡ ቃለ ፡ ማኅሌት ፡ ወበዝንቱ ፡ ይባቤ፤
ለዘይስእለኪ ፡ ብእሲ ፡ ጊዜ ፡ ረከቦ ፡ ምንዳቤ፤
ብጽሒ ፡ ፍጡነ ፡ ትሰጠዊዮ ፡ ዘይቤ ፤
ማርያም ፡ ዕንቍየ ፡ ክርስቲሎቤ ፡ ወምዕዝተ ፡ ምግባር ፡ እምከርቤ፤
ዘጸገየ ፡ ማኅጸንኪ ፡ አፈወ ፡ ነባቤ፡፡
ዚቅ
አብርሂ ፡ አብርሂ ፡ ጽዮን ፤ ዕንቍ ዘጳዝዮን፤ ዘኃረየኪ ፡ ሰሎሞን፡፡
ወረብ
አብርሂ ፡ አብርሂ ፡ ጽዮን ፤
ዕንቍ ዘጳዝዮን፤ ዘኃረየኪ ፡ ሰሎሞን ፡ ንጉሥ።

††† ማኅሌተ ጽጌ †††
††† 9 †††
ዘካርያስ ፡ ርእየ ፡ ለወርኃ ፡ ሳባጥ ፡ በሠርቁ፤
ተአምረኪ ፡ ለዘይት ፡ ማእከለ ፡ ክልኤ ፡ አዕጹቁ፤
ማርያም ፡ ጽዮን ፡ ለብርሃን ፡ ተቅዋመ ፡ ወርቁ፤
ዕዝራኒ ፡ በገዳም ፡ አመ ፡ ወዓለ ፡ ዉዱቁ፤
ለኅበረ ፡ ገጽኪ ፡ ጽጌ ፡ ሐተወ ፡ መብረቁ፡፡

ዚቅ
ለቅድስት ፡ ቤተ ክርስቲያን ፡ ፯ቱ ፡ መኃትዊሃ፤
ወ፯ቱ ፡ መሣውር ፡ ዘዲቤሃ፤
ዘካርያስ ፡ ርእየ ፡ ተቅዋመ ፡ ማኅቶት፤
ዘኩለንታሃ ፡ ወርቅ ፡ ወያክንት፤
ዕዝራኒ ፡ ርእያ ፡ ለጽዮን ፡ ቅድስት ፡ እንዘ ፡ ትበኪ ፡ ከመ ፡ ብእሲት፡፡

††† ምልጣን †††
ዓይ ፡ይእቲ ፡ዛቲ ፡እንተ ፡ታስተርኢ ፡እምርሑቅ፤
ከመ ፡ማኅቶት ፡ብርህት ፡ከመ ፡ ፀሐይ፤
ሙሴኒ ፡ርእያ ፡ ሀገር ፡ ቅድስት ፡ ዕዝራኒ ፡ ተናገራ ፡ ዳዊት ፡ ዘመራ፡፡
ወረብ
ሙሴኒ ፡ ርእያ ፡ ሀገር ፡ ቅድስ(ት)
ዕዝራኒ ፡ ተናገራ፡ ተናገራ ፡ ዘመራ ፡ ዳዊ(ት)

††† እስመ ለዓለም †††
ዘካርያስ ፡ ርእየ ፡ ተቅዋመ ፡ ማኅቶት፤
ኩለንታሃ ፡ ወርቅ ፡ በየማና ፡ ወበጸጋማ ፡ አዕጹቀ ፡ ዘይት ፤
ደብተራ ፡ ፍጽምት ፡ ሀገር ፡ ቅድስት፤
ነቢያት ፡ ይትፌሥሑ ፡ በውስቴታ፤
ሐዋርያት ፡ ይትኃሠዩ ፡ በውስቴታ፤
ወዳዊት ፡ ይዜምር ፡ በውስተ ፡ ማኅፈዲሃ፤
ዘበሰማይኒ ፡ ወዘበምድርኒ ፡ በቃለ ፡ ዳዊት ፡ ይሴብሑ፤
ወይብሉ ፡ ኵሎሙ ፡ ሃሌ ፡ ሉያ፡፡
ወረብ
ዘካርያስ ፡ ርእየ ፡ ተቅዋመ ፡ ማኅቶት ፡ ኩለንታሃ ፡ ወርቅ ፤ በየማና ፡ ወበጸጋማ ፡ አዕጹቀ ፡ ዘይ(ት)

ልሳነ ግእዝ ⛪️

22 Nov, 07:51


📚ርዕስ:- ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
📝 ቋንቋ ፦  ግእዝ 
📜ይዘት:-  ታሪክ 🏛️ 🏰
📖የገጽ ብዛት፦ ፪፻፵
ዓ.ም ፦ 1695 --


share  👈🏿
https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

21 Nov, 09:01


ግእዝ ቋንቋ መማሪያ ለ አንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች / Android users / የሚሆን።

#ሕጻናት መማሪያ
#ልሳነ #ግእዝ@geeztheancient #ግእዝ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

21 Nov, 08:55


ግእዝ ቋንቋ መማሪያ ለ አንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚዎች / Android users / የሚሆን።

#ልሳነ #ግእዝ@geeztheancient #ግእዝ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

19 Nov, 16:59


ማኅፀነ ለምለሟ (ወላዷ )ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መውለዷን አላቆመችም አታቆምም።
እግዚአብሔር ይጠብቅህ ለፍፃሜም ያብቃህ 🙏🙏🙏
ጎንደር መካነ ስብሐት ልደታ ለማርያም የዜማ ተማሪ

ኅዳር 7/2017 ዓመተ ምሕረት አበራ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን


ከየኔታ ኢሳይያስ ፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

18 Nov, 08:10


ተዝያንዎ /ንግግር /

👨 ሰላም ለከ ወልድየ፧
( ሰላም ላንተ ይኹን ልጄ? )

🧒 እግዚአብሔር ይሰባሕ ወሰላም ለከ አቡየ፧
( እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ላንተም አባቴ? )

👨 አብያፂከ፣ ሰብአ ቤትከ ዳኅና ውእቶሙ፧
( ጓደኞችኽ፣ ቤተሰቦችኽ ደኅና ናቸው? )

🧒 እዎ አቡየ ሎቱ ስብሐት
( አዎ አባቴ ለእርሱ ምስጋና )

👨 መጽሐፈ ጸሎት ብከ ፧
( የጸሎት መጽሐፍ አለኽ? )

🧒 እዎ ብየ
( አዎ አለኝ። )

👨 ልሳነ ግእዝ እፎ ውእቱ፧
( የግእዝ ቋንቋ እንዴት ነው ? )

🧒 ቀሊል ውእቱ።
( ቀላል ነው። )

👨 ናሁ ትትናገር ጥቀ፧
( አሁን በጣም ትናገራለኽ ? )

🧒 ንስቲት ንስቲት
( ትንሽ ፣ ትንሽ)

👨 ባሕቱ ምንተ ይገብር ለከ፧
( ነገር ግን ምን ያደርግልኻል? )

🧒 ይትሔደስ መንፈስየ አመ ሰማእኩ በእዝንየ ልሳነ ግእዝ።
(የግእዝ ቋንቅ በሰማሁ ጊዜ መንፈሴ ይታደሳል። )

👨 እንከሰ ኵሉ ሰብእ እመይትናገር ሠናይ ውእቱ፤
( እንግዲኽስ ኹሉ ሰው ቢናገር ጥሩ ነው፤ )

🧒 ተስፋየ ውእ።
( ተስፋዬ ነው። )

👨 ናሁ እለመኑ ይትናገሩ ልሳነ ግእዝ ብዙኃን፧
( አሁን እነማን የግእዝ ቋንቋን ይናገራሉ? )

🧒 ፬ ውእቶሙ አኮ ኣነ ባሕቲትየ፤ (ብዙ ናቸው እኔ ብቻ አይደለኹም፤ )

👨 ምንተ ትቤ አንተ እንዘ ይትናገሩ ልሳነ ግእዝ፧
(ግእዝ ሲናገሩ አንተ ምን አልኽ? )

🧒 ፍስሐ ፈድፈደ ሊተ
( ደስታ በዛልኝ )

👨 ማዕዜ ውእቱ ዘወጠኑ ተምህሮ፧
( መቼ ነው ለመማር የጀመሩ? )

🧒 በዝንቱ ዓመት።
( በዚኽ ዓመት። )
👨 እግዚአብሔር ያርእየነ ለፍሬሁ (እግዚአብሔር ፍሬውን ያሳየን። )

🧒 አሜን ለይኩን።
(አሜን ይኹንልን። )


ልሳነ ግእዝ


https://t.me/geeztheancient

Subscribe 👇
https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow

ልሳነ ግእዝ ⛪️

18 Nov, 00:41


ሥርዓተ ማሕሌት ዘኅዳር ሚካኤል

ልሳነ ግእዝ ⛪️

17 Nov, 18:31


📚ርዕስ:- ገድል
📝 ቋንቋ ፦  ግእዝ
📜ይዘት:-  ሃይማኖታዊ
📖የገጽ ብዛት፦ ፻፸፬

share  👈🏿
https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

17 Nov, 16:46


ልክ የዛሬ 104 ዓመት በዚህች እለት ኅዳር 9 ቀን
(1912) ታላቁ
#ኢትዮጵያዊ ምሑር: የሊቆች ሁሉ ሊቅ: ደግና ሐዋርያዊ አባት *#የኔታ #አካለ #ወልድ ዐርፈዋል::

=>ሊቃውንት
#የቀለም_ቀንድ ሲሏቸው #አፄ #ቴዎድሮስ ደግሞ:-

"ይማሯል እንደ አካልዬ::
ይዋጉዋል እንደ ገብርየ::" ብለው ፎክረውላቸዋል::

¤የቦሩ ሜዳው ኮከብ ይልቁኑ ለወሎ ሕዝብ ትልቅ አባት ነበሩ::

#በኢየሩሳሌሙ ጉባኤም እንዳኮሩን አንዘነጋም::

<<< የሊቁ አካለ ወልድ በረከታቸው ይደርብን:: >>>


@geeztheancient

ልሳነ ግእዝ ⛪️

17 Nov, 14:21


እንደ ሀሳብ

አለቃ ገብረ ሐና የአቡነ ሐራ ገዳም አስተዳዳሪ ነበሩ ፤ በዘመኑ።

የዛኔ ድርቅ ረሀብ ገብቶ የአነ ሐራን ገዳም ገንዘብ ለምእመኑ አከፋፍለውት ሰውም ያንን ክፉ ቀን አለፉበት። በዚህ ድርጊታቸው ተከሰው ከንጉሡ ፊት ቁመዋል።

የተከሰሱበት ምክንያትም " የአቡነ ሐራ ገዳም ገንዘብ ለምእመኑ አከፋፍለዋል " የሚል ነበረ።

የመለሱት መልስም

ድርቅ ቢበዛ ሰው በረኃብ ከሚያልቅ ብየ አዎ አከፋፍያለሁ ፤ አሉ። "ሰው ከሌለ አቡነ ሐራ ልጃቸውን አያሳድጉበት እሳቸው አይጦሩበት፤ ሰው ከሰነበተ ስለቱን በሌላ ጊዜ ያስገበዋል። " ማለታቸው ይነገራል። ( አረፈ ዐይኔ ሐጎስ ) ከጻፉት መጽሐፍ።


ወደ ነጥቡ ስመጣ ..
በዚህ ዘመንም ሀብታም አድባራት አሉ ለካህናት እና ሰባክያን ደመወዝ ተከፍሎ የተረፈ ይኖራል ያን ገንዘብ ቦታ ብታስይዙት የምናየው ነው የገጠር ቤተክርስቲያን በአንሶላ ሁሉ የሚቀድሱ እያየን ነው። ቋሚ ሥራ መስክ በመክፈት ለምሳሌ የልማት እርሻ ከመንግሥት ማስፈቀድ ( ሰሚ ካለ ) 🚜 በዚያ ውስጥም ሕዝበ ክርስቲያኑን ሥራ ማሠራት ከችግር ይወጣሉ ማለት ነው። ሰው የተባለን መሥራት የሚችልን ሁሉ ማሠማራት ይቻላል።

ገንዘብ ካለ ሰዎች እንዲሰነብቱ ቢደረግ።

በቅጥር ከመንግሥት ቀጥሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 2ኛውን ድርሻ ትይዛለች። የተማሩ ካህናትም የሚሰባሰቡበት መንገድ ተመቻችቶ እንደየ ችሎታቸው እንዲያስተምሩ እና ጠቀም ያለ ገቢ እንኳን ባይሆን ጊዜውን ማሳለፊያ ድጎማ ቢደረግ መልካም ነው እላለሁ።
ካህን ሁኖ መስቀል ይዞ የፖሊስ ሥራ ዘበኛ ሲሆኑ ደንብ አስከባሪ ሁነው ወዘተ.. እያየንም ነው። ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ይህንን እያየ ካህን የሚሆን ሊጠፋ ይችላል። እና በብዙ ድካም የተማሩ ልጆቿን የምትይዝበት አሠራር ቢፈጠር እላለሁ።

ከተሳሳትኩም እታረማለሁ።

✍️

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Nov, 07:41


እንኳን ለቁስቋም ማርያም አደረሰን። ስደትን ጭንቀትን የምታውቅ እናታችን፣ ጭንቀት እና መከራችንን ለልጇ ታሳስብልን። 💖

ልሳነ ግእዝ ⛪️

12 Nov, 10:02


የመምህር እንባቆም

✍️ ልሳነ ግእዝ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

12 Nov, 09:38


📚 ትንሳኤ ግእዝ
በመምህር ደሴ ቀለብ


✍️ ልሳነ ግእዝ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

11 Nov, 10:49


ኢዮብ ዘማርያም እንደ ጻፈው

👇
“The evil eye is real” ይላሉ ነጮቹ ጥሩ ባልሆነ አይን የሚመጣ መጥፎ ዕድልን ሲገልፁ! ወደኛ ሀገር ሲመጣ ደግሞ ስሙ “ቡዳ” ይባላል!...ዐይናቸው የተለየ ኃይል እንዳለው የሚታመንና በማየት ብቻ እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት ማድረስ የሚችሉ ሰዎች ናቸው!...ታሪኩ ብዙ ስለሆነ እዚህ ሐተታ ውስጥ አንገባም ዛሬ! ድሮ ትዝ ይለኛል ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ለእናቱ የነበረ ቴሌዢዥን ላይ የሚቀርቡ ሰዎች ሞት ፋሽን ሆኖ ነበር!...የሆነ ሰው ቲቪ ላይ እንግዳ ሆኖ ከቀረበ “በቃ ሊሞት ነው” ይባላል! ሰውየውም ከሳምንት ወይም ከ ዐስራ አምስት ቀን በኋላ ይሰናበታል! ይሄ ነገር ከጀርባው የሆነ ነገር ይኑር አጋጣሚ እንጃ! ።

ወደኛ ዘመን ስንመጣ ደግሞ ከ ቴሌዢዥን ይልቅ ሶሻል ሚዲያ ሁሉንም ነገር ተቆጣጥሮታል! በዛው ልክ “Privacy” የሚባል ነገር ጠፍቷል! ሁሉም ነገር የ አደባባይ ሚስጠር ነው! ሰዎች “ገመና” የሚባል ነገራቸውን ሳይቀር ገልጠው ያሳያሉ!...ልጅ ወልደው ገና ደሙ ሳይደርቅ ሶሻል ሚዲያ ላይ አምጥተው ይለጥፋሉ! በዛው ልክ ሰዎች ፍቅረኛቸውን ሚዲያ ላይ አምጥተው “እሱ ነው እዩልኝ” ብለው ያሰጣሉ!...መደበቅ የሚገባውን የሕይወታቸውን ክፍል አንዳች ሳይቀር ለሰው ይገልጣሉ!...ሶሻል ሚዲያ ላይ ከተገለጡ relationshi’ፓች መካከል አብዛኞቹ ደግሞ ከሽፈዋል! “እንዴት ነው ምታምሩት ከ ዐይን ያውጣቹ” ተብለው የተመረቁ ፍቅረኛሞች ከዐይን መውጣት ትስኗቸው ፍቅራቸው ከ መንገድ ላይ ተግትቷል!...ተጋብተው!...ልጅ ወልደው የነበሩም ብዙዎቹ ተፋተዋል!...ይህን ግዜ... “IS THE EVIL EYE IS REAL ?? " 

ብለን ብንጠይቅስ?

ልሳነ ግእዝ ⛪️

11 Nov, 06:47


ቅኔ
(መምህር  ሰሎሞን ተስፋዬ )

ሐመይኖ ኲልነ ለእግዚአብሔር አሐዱ፤
እመ ይከውነነ አበ ውስተ አፀዱ፤
በሞተ ወልዱ አማኑኤል ሐዋርያቲሁ ዘንዕዱ፤
እንዘ አንብዖሙ ያወርዱ፤
ምስለ ዘመዱ ገብርኤል ወምስለ ሚካኤል ዘመዱ፤
እስመ ጠብአ እግዚአብሔር በዋሕድ ወልዱ፤

መድኃኔዓለም ሐደገ ተሰዶ እምድረ ቦስተን ምክያዱ፤
ሶበ ነበቦ ይትመየጥ በቃሉ መልአከ ፀሐይ ነገዱ፤
ጸላእተ ቤቱ እመ ፈድፈዱ፤
እስመ ከመጢስ ሐልቁ እንዘ ይነድዱ፤
በፀሐይ ዘመዊዕ ልማዱ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

09 Nov, 09:11


ተመየጢ / ሰቆቃወ ድንግል /

ተመየጢ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፤
ወኢትጎንድዪ በግብፅ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤
በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤
ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤
በከመ ፤ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

09 Nov, 08:57


https://t.me/geeztheancient

ልሳነ ግእዝ ⛪️

09 Nov, 08:50


ወረብ ተፈጸመ / መምህር ቀለሙ እንዳለው /

ልሳነ ግእዝ ⛪️

09 Nov, 08:48


ዚቅ - አሠርገወ ገዳማተ ስን

ልሳነ ግእዝ ⛪️

09 Nov, 08:34


ጥቅምት ፴፦

✝️ማርያም ድንግል ደብረ ፋራን ዘዕንባቆም፤
ምድረ ቴማን ኅሪት ወግበ አናብስት ኅቱም፤
በከመ ይቤ ነቢይ እምድኅረ ብዙኅ ሕማም፤
በበዓትኪ ብሔረ አግአዚ ሃገረ ፍቅር ወሰላም፤
ደንገጻ አዕጻዳቲሃ እምግርማኪ መድምም!

✝️ሰላም ለልደትከ በቤተ ማርያም ቅድመ፤
ወበጸጋ ቅዱስ መንፈስ በጽርሐ ጽዮን ዳግመ፤
ማርቆስ ሐዋርያ እንተ ትኴንን አርያመ፤
ምስለ ዮሐንስ ወፋሲለደስ ዘኢፈርሃ ልጓመ፤
ወምስለ አብርሃም ነዓ ለባርኮ ዓለመ!

✝️ማርቆስ ዘአንበሳ ወልዱ ለአርጦቦሉስ፤
ወማርያም ብጽዕት አመተ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
ወዮሐንስ ግፉዕ ከመ አቡሁ ዘካርያስ፤
አበ ሰማዕታት ዘአንጾኪያ ሊቀ ሐራ ፋሲለደስ፤
አብርሃም ባሕታዊ ወይስሐቅ ንጉሥ!

(አርኬ - ዝክረ ቅዱሳን ርቱዓነ ሃይማኖት)

ልሳነ ግእዝ ⛪️

05 Nov, 20:20


የኔ እናት ዝማሬ መላእክት ያሰማልን

በtiktok follow አድርጓቸው
@adanechasfaw

ልሳነ ግእዝ ⛪️

05 Nov, 15:06


✍️እየተዳከሙ ያሉ የቆሎ ትምህርት ቤቶች ለመጭው ትውልድ እንዲተላለፉ ጥረት ማድረግ የጀመረችው ኔዘርላንዳዊት

christine chaillot
👇
https://www.tiktok.com/@niusane2112/video/7433810509255707909
እኛስ ብለን እንጠይቅ።

ሌላ ታሪክ ላይ ነን

ልሳነ ግእዝ ⛪️

05 Nov, 13:30


ዘመነ ሰዊት / እሸት /
😍

በፊት ጊዚያት እሸት አይከለከልም ነበረ 1 2 ይፈቀዳል። ለገበያ አይቀርብም ነበረ። ሰነባብቶ ግን ገበያ ቀረበ እሱም በ1 ብር በሸክም ነበረ የሚገዛው። አሁን በዚህ ዘመን ግን 1 ራስ በቆሎ ከ20_30ብር ነው።

እሸት ሲሸት ሲጎመራ ገበሬው መጀመሪያ ወስዶ ከሊቀ ጳጳሱ አስባርኮ እሸት ሰጥቶ ነበረ እሱም መጠቀም የሚጀምረው። አሁን አሁን በረከቱም የራቀ ስለማናስባርክ ጭምር ነው መሰል በቄት የለውም።

🌽

ልሳነ ግእዝ ⛪️

05 Nov, 10:47


ጥቅምት ፳፮፦

✝️ማርያም ድንግል ለኤርምያስ ጽርሐ ቅድሳቱ፤
ዘኃደረ ውስቴትኪ ፀሐየ አርያም ዘየኃቱ፤
በከመ በከየ ለሕዝቡ አመ አፍለሥዎ ሎቱ፤
ወላዲተ አምላክ ንጽሕት በድንግልና ክልኤቱ፤
በከይኪ ወአስቆቀውኪ ለወልድኪ በእንተ ሞቱ!
 
✝️ሰላም ለከ ረድአ ክርስቶስ ጢሞና፤
ዘሤሙከ ሐዋርያት ዘምስለ ኒቃሮን ወጳርሜና፤
ወያዕቆብ ወልደ ዮሴፍ ዘውገ ናትናኤል ዘቃና፤
በጾም ወበጸሎት ወበኲሉ ትኅትና፤
ከመ ፊልጶስ ወአግናጥዮስ ዘአርታእከ ፍና!

✝️ያዕቆብ ሐዋርያ ገባሬ ፍቅር ወሰላም፤
ዘነበረ ጽሙደ በሃገረ ንጉሥ ኢየሩሳሌም፤
ወዘተናከራ ነዋኃ ለዛቲ ዓለም፤
ጢሞና ሐዋርያ መፍቀሬ ምጽዋት ወጾም፤
ፊልጶስ ወአግናጥዮስ ክቡራነ ስም!


ዝክረ ቅዱሳን

ልሳነ ግእዝ ⛪️

05 Nov, 07:19


ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮጊስ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

02 Nov, 08:28


ጥቅምት ፳፫፦

✝️ማርያም ድንግል እንተ ኤልያስ ደመና፤
ወመሶበ ወርቅ ጽሪት ዘታስተፌስሒ ኅሊና፤
ከመ ይኩን ወልድኪ ሕብስተ ቁርባን ዘመና፤
አመ ተሦዐ በቀራንዮ ወተሰደ ውስተ ሲና፤
ያነድደኒ ብካይኪ ወዘረከበኪ ድክትምና!
 
✝️ሰላም ለመቃብሪከ በደብረ ሊባኖስ ገዳሙ፤
ለተክለ ሃይማኖት አቡከ ዘተሰብረ አጽሙ፤
ኤልሳዕ ዝክረ ስምከ ከመ ወይን ጣዕሙ፤
ከመ ዮሴፍ ወዲዮናስዮስ ዘተክዕወ ደሞሙ፤
ዘኃረየከ አምላክ ይትባረክ ስሙ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

31 Oct, 07:40


ራብዓይ
ጉ. ቃና

ኢትሕዝን ኢዮብ ንቡረ ብዙኅ ትካዜ፣
ለእመ ጊዜ ይገድፍ አምጣነ ያነሥእ ጊዜ ፤



©ቀሲስ ሰሎሞን ተስፋዬ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

31 Oct, 07:39


ሣልሳይ
ጉ. ቃና

ኢትመን ፍጽመ ለሐሳዌዓለም ጌዜ፤
እስመ በጌሰም ይክህድ፡ ቦኑ እመ አመንኮ  ይእዜ፤


©ዘያሬድ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

31 Oct, 07:30


ካልኣይ
ጉ. ቃና



ማርያም አልሀቀት ልደተ አምላክ እጓላ፤
በሥጋ ጥዑም ወበሀሊበ ቅብእ ወተድላ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

31 Oct, 07:27


ቅኔ
ጉባኤ ቃና

ሀሎ ነገር በቤተ ኢያቄም ወሀና፤
በሀዲሰ መሶብ አምጣነ ሀለፈ መና።


🖋
ተርጉሙ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Oct, 12:02


የጥቅምት  ፳፬  ማኅሌተ ጽጌ

/ https://youtu.be/335wUY0Rh_4?si=EoR7eYqfKb30W-Kg / 👈 ይወዳጁን

፩. ነግሥ

ሰላም ለአብ ገባሬ ኲሉ ዓለም፤
ለወልድ ሰላም ለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤
ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም
ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም ፤
ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም፡፡

ዚቅ፦

ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤
ወለተ ኄራን ነቢያት፤እሞሙ ለሐዋርያት፤
ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት፡፡

ዓዲ

ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ፤
ትሩፋተ ገድል ኵኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤
ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤
ጊዮርጊስ ኢወሰነ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ።

ዚቅ

ሃሌ ሉያ ለአብ፡ ሃሌ ሉያ ለወልድ፡ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፡
ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ፡፡ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ፤ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ፤
ምስለ ተክለ ሃይማኖት ንትፈሣሕ ኅቡረ፡፡

፪  እንዘ ተሐቅፊዮ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡

ወረብ

ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል፡ ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት

ዚቅ

በሰላም፡ ንዒ፡ ማርያም፡ ትናዝዝኒ፡ ኃዘነ፡ ልብየ፤
በሰላም፡ ንዒ፡ ምስለ፡ ሚካኤል፡ ወገብርኤል፤
በሰላም፡ ንዒ፡ ምስለ፡ ሱራፌል፡ ወኪሩቤል፤
በሰላም፡ ንዒ፡ ምስለ፡ ኩሎሙ፡ ቅዱሳን፡ በሰላም፡ ንዒ፡ ምስለ፡ ወልድኪ፡ አማኑኤል፤
በሰላም፡ ንዒ፡ ማርያም፡ ለናዝዞ፡ ኩሉ፡ ዓለም።

፫  ክበበ ጌራ ወርቅ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኃቱ እምዕንቈ ባሕርይ፤
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ ።

ዚቅ

ሰአሊ ለነ ማርያም ፨ አክሊለ ንጹሐን ብርሃነ ቅዱሳን።

፬ ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም 

ተአምረ ፍቅርኪ በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ፤
ወፈድፋደሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤
እስመ አሕየወ ሙታነ ወሕሙማነ ፈወሰ፤
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤
ወበ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ፡፡

ወረብ

ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ፤
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ

ዚቅ

ይዌድስዋ ኲሎሙ ወይብልዋ፡ እኅትነ ነያ፤
ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኲሎሙ መላእክት ይኬልልዋ፤
ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ ወበምድር ኲሎሙ ቅዱሳን ይቄድስዋ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ።

፭. ለምንት ሊተ ኢትበሊ

ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤
ይበቍዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤
ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረጽኪ እምሥርወ እሴ፤
እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤
ተአምረኪ የአኲት ብናሴ።

ወረብ

ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ፤
ይበቊዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን።

ዚቅ

አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን፤
አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን።

ሰቆቃወ ድንግል

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ፤
ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤
ለወልድኪ ሕጻን ዘስሙ ናዝራዊ፤
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

ወረብ

በከመ ይቤ ዖዝያን ዖዝያን ለክብረ ቅዱሳን ፤
እምግብፅ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡሁ።

ዚቅ

ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብጽ ጸዋዕክዎ፤ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ።

መዝሙር ጸገየ ወይን

ሃሌ ሉያ (በ፭)
ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን፡ ወፈርዩ ኲሉ ዕፀወ ገዳም
ቀንሞስ ዕቊረ ማየ ልብን ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ
ጸገዩ ጽጌያት ጸገዩ ደንጎላት ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ
ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በሥነ ጽጌያት  ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ
እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ
ሠርዐ ለነ ሰንበተ ለዕረፍት ወለመድኃኒት

ትርጉም፦

ወይኑ አበበ ሮማን አፈራ ማየ ልብን የተባለ ሽቱ የተከማቸበት ቀንሞስ ያለበት የምድረ በዳ ዛፎች ሁሉ አፈሩ ለእኛ ዕረፍት እንዲሆን ሰንበትን ሠራ አበቦች አበቡ ሱፎች አበቡ ክረምት አለፈ በረከት ቆመ (ሆነ) ምድር በአበቦች ውበት አጌጠች የሰንበት ጌታ የምሕረት አባት ለእኛ ዕረፍት ይሆን ዘንድ ሰንበትን ሠራ [ይኸውም]  ለዕረፍትና ለመድኃኒት [ለመድኃኒትነት ነው]።

+++++++++++++++ጸ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Oct, 10:58


ግስ አርዕስት 👇👇

https://youtu.be/335wUY0Rh_4?si=EoR7eYqfKb30W-Kg

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Oct, 09:33


.
.
.
    ◆የ8ቱ አርእስተ ግሶች ርባታ◆

◆ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቴሌግራም ገጽ
[
@Ethiogeezmedianibab ]

◆ ቴሌግራም መወያያ
[
@Ethiogeezmediachat ]

   ለሐሳብ  አስተያየትዎ
◎ ስልክ =[
0913514905]
◎ Telegram =[
@Ethiogeezmedia]
◎ ኢሜል= [
[email protected]]
.
.
.

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Oct, 06:54


ማርያም ድንግል ሠረገላሁ ለአሚናዳብ፤
ማኅደረ ቅዱስ መንፈስ ወኅሪተ ወላዲ አብ፤
ለወልደ አምላክ እሙ ዘሐጸንኪዮ በሐሊብ፤
እንዘ ትጸውሪ እግዚአ ገባሬ ብርሃናት ጠቢብ፤
ደክማ አብራክኪ በረዊጽ ወረሃብ!
 

ሰላም ለዮሐንስ እንተ ነጸረ በዐይኑ፤
አእላፈ አእላፋት መላእክት ኀበ ተዓየኑ፤
በጊዜ አዕረፈ እምጻማ በደብረ ቁልዝም መካኑ፤
በዝማሬ ወበማሕሌት ቀበርዎ ለበድኑ፤
እንዘ ያነክሩ ወይብሉ ከማከ መኑ!


ሰላም ሰላም ለዮሐንስ ሐጺር፤
ትኁት ወተአዛዚ ወበኀበ ኲሉ ፍቁር፤
ወዓዲ ሰላም ለባይሞይ መምህር፤
ለኤልሳዕ ረድአ ኤልያስ ዘተሰይመ አቃቤ ሀገር፤
ዘአንስአ ሙታነ እምድኅረ ሰከበ ውስተ መቃብር


#ስንክሳር
#ገድላት
#ድርሳናት
#ሃይማኖተ አበው
#መጽሐፍ #ቅዱስ #አበዊሆሙ #ለኲሎሙ #መጻሕፍት

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Oct, 06:39


ቀደሰ ----- አመሰገነነ

ቀደሰ ----- አመሰገነ
ይቄድስ ----- ያመስግን
ይቀድስ ---- ያመሰግን ዘንድ
ይቀድስ ---- ያመስግን
ቀድሶ ቀድሶት --- ማመስገን
ቀዳሲ ---- ያመሰገነ
ቀዳስያን ---- ያመሰገኑ
ቀዳሲት --- ያመሰገነች
ቀዳስያት --- ያመሰገኑ/ሴ
ቅዱስ --- ምስጉን
ቀዳሲ --- አመስጋኝ
ቅዳሴ ---- ምስጋና
መቅደስ ---- ማመስገኛ
ቅድስት ---- የተመሰገነች

ብህለ---አለ

ብህለ---አለ
ይብህል---ይላል
ይብሃል---ይልዘንድ
ይብሃል----ይበል
ብሂል ብሂሎት----ማለት
ባህሊ----ያለ
ባህልያን---ያሉ
ባህሊት---ያለች
ባህሊያት---ያሉ(ሴ)
ብሁል---የተባለ
ባሃሊ----የሚል
ባህል---አባባል


አእመረ --- አወቀ
አእመረ --- አወቀ
የአምር ---- ያውቃል
ያእምር ---- ያውቅ ዘንድ
ያእምር --- ይወቅ
አእምሮ/አእምሮት -- ማወቅ
አእማሪ --- ያወቀ
አእማርያን --- ያወቁ /ወ/
አእማሪት --- ያወቀች
አእማርያት --- ያወቁ /ሴ/
እሙር --- የታወቀ
አእማሪ --- አዋቂ
ማእምር ---- የሚያውቅ
አእምሮ --- እውቀት

አእመረን የሚመስሉ፣ አጥረየ፣ አመንተወ፣
አመክነየ፣ አመድበለና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

#EOTC #አብነት #ትምህርት #ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ
ሼር

https://t.me/geeztheancient

Subscribe YouTube

https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow

ልሳነ ግእዝ ⛪️

30 Oct, 05:29


ግስ ርባታ

✔️ሴመ --- ሾመ
ሴመ --- ሾመ
ይሰይም --- ይመሾማል
ይሲም --- ይሾም ዘ ን ድ
ይሲም --- ይሹም
ሰይም/ ሰይሞትት --- መሾም
ሰያሚ ---- የሾመ
ሰያሚያን ---የሾሙ
ሰያሚት ---- የ ተሾመችች
ሰያምያትት --- የ የተሾሙ /ሴ /
ስዩም --- የ የተሾመ /ሴ /
ሰያሚ ---- ሿሚ
ሲመት ---- ሹመት
..........................................

ቄቀሃ --- ፈተገ

ቄቀሃ --- ፈተገ
ይቄቅህ --- ይፈትጋል
ይቄቅህ --- ይፈትግ ዘንድ
ይቀቅህ --- ይፈትግ
ቄቅሆ/ ቄቅሆት --- መፈተግ
ቄቃሂ ---- የተፈተገ
ቄቃህያን ---የ ተተጉ
ቄቃሂት ---- የ ተፈተገች
ተቄቃሂት --- የ የተፈተጉ /ሴ /
ቂቁህ --- የ የተፈተገ
ቄቃሄ ---- ፈታጊ
ቄቅህ --- ፍትግ
..............................................
ዜነወ --- አወራ/ ነገረ

ዜነወ --- አወራ/ ነገረ
ይዜኑ --- ይፈትጋል
ይዜኑ --- ያወራ ዘንድ
ይዜኑ --- ያወራ
ይዜንሆ/ ይዜንሆት --- ማውራት
ዜኖ/ ዜኖት --- ማውራት
ዜናዊ ---- ያወራ
ዜናውያን ---ያወሩ
ዜናዊት ---- ያወራቺ
ዜናያት --- ያወሩ /ሴ /
ዜናዊ --- አውሪ/ ወሬኛ
ዜና ---- ወሬ/ ነገር
.........................................................
ጌገየ --- በደለ

ጌገየ --- በደለ
ይጌጊ --- ይበድላልል
ይጌጊ --- ይበድል ዘንድ
ይጌጊ --- ይበድል
ጌጊሆ/ ጌጊሆት --- መበደል
ጌጋኢ ---- የበደለ
ጌጋውያት ---የበደሉ
ጊጉይ ---በደለኛ
ጌጋይ ---- የሚበድል/ በዳይ

....................................................
ጼወወ --- ማረከ

ጼወወ --- ማረከ
ይጼውዕ --- ይማርካልል
ይጸውዕ --- ይማርክ ዘንድ
ይጸውዕ --- ይማርክ
ጼዋኦ/ ጼውኦት --- መማረክ
ጼዋዊ ---- የማረክ
ጼዋዊያን ---የማረኩ
ጽዋዊት ---የማረከች
ጼዋውያት ---የማረኩ(ሴ)
ጺውዕ ---የተማረከ
ጼዋዊ ---ማራኪ
ጼዋ ---ምርኮ

https://abrenendeg.com/.../geez.../geez-education-erbata/

share...
https://t.me/geeztheancient
subscribe
https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow

ልሳነ ግእዝ ⛪️

29 Oct, 15:29


ቅኔ

አመ ባእሰ ኤልዛቤል ጸንአ፤ ላዕለ ሕዝበ አዳም ዓለም፤
ተሰደ እምኢትዮጵያ ኤልያስ ሰላም።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

29 Oct, 09:52


የቀጠለ ...
የስምንቱን አርእስተ ግሥ በተለያዩ እርከኖች የሚረቡትን እርባታ ነው። የምናረባቸው በትንቢት አንቀጽ፣ በዘንድ አንቀጽ፣ በትእዛዝ አንቀጽ፣ ሣልስ ውስጠዘ፣ ሳድስ ውስጠዘ እና አርእስት ነው።

በሰንጠረዥ ስለተዘጋጀ ዌብሳይታችን ላይ ተከታተሉ

click the link bellow

https://abrenendeg.com/ethiopian-education/geez-ethiopia/geez-education-lesson-2/

ልሳነ ግእዝ ⛪️

29 Oct, 06:51


◎ ርእስ = ስንክሳር በልሳነ ግእዝ [ከዓመት እስከ ዓመት]
◎ የገጽ ብዛት = ፲፻፵፮



.
.

ልሳነ ግእዝ ⛪️

28 Oct, 08:32


📚 ግስ
የግስ ምንነት
✔️ ግስ ከቃል ክፍሎች አንዱ ሲሆን በብዙ መንገድ ሊፈታ ይችላል። በዋናነት ግን ድርጊት አመልካች የሆነ በዐረፍተ ነገር ውስጥ የሐሳብ መደምደሚያ፣ ወይም የዐረፍተ ነገር ማሠሪያ ተብሎ ይተረጎማል። በርካታ ምሁራን በተለያየ መልኩ ስላብራሩት የምሁራኑን አገላለጽ እንደሚከተለው እንመልከት።

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በተባለ መጽሐፋቸው እንዲህ ያስረዳሉ።

ግስ ፡- መግሰስ፣ አንዱን ቃል ማርባት፣ ማብዛት፣ የሩቁን ለቅርብ፣ የወንዱን ለሴት፣ ያንዱን ለብዙ መስጠት፣ ማወራረስ፣ የቅኔ፣ የዚቅ፣ የወረብ፣ የለዘብ።

ግስ፡- ጓዝ፣ እክት፣ ግስንግስ ፣ ዕቃ፣ ግሴት የሚያዝና፣ የሚዳሰስ ኹሉ፣

ግስ፡- በቁሙ፣ የቋንቋ መጣፍ( መጽሐፍ )፣ የዘርና የነባር መድበል፣ መዝገበ ቃል፣ ንባቡ በፊደል ተራ የታከተ፣ የተከተተ። ምሥጢሩ ግን ተወራራሽ ቃል ማለት ነው። አንዱ አንቀጽ እስከ ሰማንያ ነባሩና ጥሬው እስከዐሥር መርባቱ በመወራረስ ነውና። (ኪዳነ ወልድ፣ ገጽ ፫፻፴፫-፫፻፴፬)

አለቃ ኪዳነ ወልድ በተለያየ አገላለጽ ቢገልጹትም በዋናነት ግን ግስ አንቀጽን ማርባት፣ መግሰስ፣ ጓዙን ማሳየት ወዘተ ማለት እንደሆነ እንረዳለን። በሌላ በኩል የአማርኛ ሰዋስውን በስፋት ያጠኑት ፕሮፌሰር ባየ ይማም ደግሞ የአማርኛ ሰዋስው በሚል መጽሐፋቸው እንደሚከተለው ያስረዳሉ።

ግስ፡- ማንኛውም በዐረፍተ ነገር መድረሻ ላይ ሊገባ የሚችልና እንደ /-ሁ/፣/-ህ/ ፣/-ሽ/ ወዘተ.... ያሉ መደብ አመልካች ምዕላዶችን ሊያስከትል የሚችል ቃል ሁሉ ግስ ተብሎ በዚህ ክፍል ውስጥ ሊመደብ ይችላል። (ፕሮፌሰር ባየ.ገጽ ፹፬) ይሉንና በሌላኛው ገጽ ደግሞ፥

ግሶች ለመደብ፣ ለጾታ ፣ለቍጥር፣ ለአንቀጽ፣ ለስልት፣ እንዲሁም ለጊዜ የተለያዩ ቅጣይ ምዕላዶችን፣ በማስቀደም ወይም በማስከተል ቅድመ መድረሻ ተናባቢያቸውን በማጥበቅ ወይም ባለማጥበቅ እንዲሁ ከተለያዩ ረዳት ግሶች ጋር በመጣመር ቅርጻቸውን ሊለዋውጡ ይችላሉ። (ፕሮፌሰር ባየ.ገጽ.፻፴፫) በማለት ያስረዳሉ።

ፕሮፌሰር ባየ ይማም ከመዋቅር አንጻር በአማርኛ ስለተመለከቱት እንጂ በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ ከግእዝ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ምክንያቱም በአማርኛ መዋቅር ግስ ወይም ማሰሪያ አንቀጽ ከዐረፍተ ነገር መጨረሻ ስለሚገባ ነው። በግእዝ ቋንቋ ግን በመጀመሪያም በመጨረሻም ሊገባ ይችላል። ሌላው መስፈርት ግን በመደብ፣ በጾታ በቁጥር ወዘተ መብዛቱና መደብ፣ ጾታ እና ቍጥር አመልካች ምዕላድ ማስከተሉ በሁለቱም ቋንቋ ተመሳሳይነት አለው። ምን አልባት አመልካች ምዕላዶች ይለያዩ ካልሆነ በቀር። ከላይ በኪዳነ ወልድ አገላለጽ የተመለከትነውም ማርባት፣ ማብዛት፣ መግሰስ ወዘተ የተባለው ይህን የሚያስረዳ ነው።

መምህር አስበ ድንግል ግእዝ ልሳነ ኢትዮጵያ በሚል መጽሐፋቸው ግስን እንደሚከተለው ገልጸውት እናገኛለን።

ግስ ድርጊትንና ሁኔታን የሚገልጽ የቋንቋ መዝገበ ቃል የምሥጢር መፍቻ ቁልፍ ነው። (አስበ ድንግል፣ገጽ፴፭)

ሌላው መምህር ዕንባቆም ገብረ ጻድቅ የግእዝ ቋንቋ የሰዋስው መጽሐፍ በሚል መጽሐፋቸው እንዲህ ገልጸውት እናገኛለን።

ግስ ማለት ጌሰ፤ ገሰገሰ፤ ተራመደ፤ ተስፋፋ፣ ከሚለው ግስ የተገኘ ዘመድ ዘር ሲሆን የአንድ ዐረፍተ ነገር (ኃይለ ቃል) ማሰሪያ አንቀጽ በመሆን ዐረፍተ ነገሩ ትርጉም እንዲኖረው የሚያደርግ ነው።

ግስ ማለት፡- ገሰሰ ዳሰሰ ከሚለው ግስ የወጣ ዘመድ ዘር ሲሆን የቃላት መራቢያ፣ ገስጋሽ፣ ተመላላሽና ተወራራሽ ቃል ነው። (ዕንባቆም፣፴፭)

ከመምህር ዕንባቆም አገላለጽም የምንረዳው ከላይ በተመለከትነው መሠረት ግስ የዐረፍተ ነገር ማሰሪያ አንቀጽ በመሆን የሚያገልግል፣ የሐሳብ መቋጫ የሚሆን፣ በብዙ መንገድ የሚረባ የቃላት ሁሉ መነሻ ማለት እንደሆነ ነው።

በሌላ መልኩ አንዳንድ መምህራን ግስን አንቀጽ በሚል ስያሜ ይጠሩታል።

አንቀጽ፡- የአድራጊ፣ የድርጊትና የሁኔታ፣ አንድና ብዙ ቍጥርን፣ ቅርብና ሩቅ መደብን፣ ተባዕታይና አንስታይ ጾታን፣ ሐላፊ፣ አሁንታና ትንቢት ጊዜያትን፣ ወዘተ የሚያስረዳ ቃል አንቀጽ ይባላል። አንቀጽ ማለት መግቢያ፣ መውጫ፣ መመላለሻ በር ማለት ነው።

አንቀጽ የተባለበት ምክንያትም፡- ይህ ዓይነት ቃል “አንቀጽ” ተብሎ የተሰየመበት ምክንያት በበር እንደሚገባበት፣ እንደሚወጣበት፣ እንደሚመላለሱበት፣ አእምሮ (ዕውቀት) የጠለቀ ምሥጢርን፣ የረቀቀ ጥበብን፣ ለመረዳት አንቀጽን እየመረመረ በምርምራዊ ሐሳብ ስለሚወጣበት፣ ስለሚገባበት፣ ስለሚመላለስበት ነው።

ጠቅለል ሲደረግ ግስ ድርጊት አመልካች የሆነ፣ በዐሥሩም መራሕያን እየረባ ለብዙ ቃላት መመሥረት መነሻ የሚሆን፣ መደብን ፣ ቍጥርን፣ ጾታን የሚያመለክቱ ምዕላዶችን እየጨመረ በልዩ ልዩ መልኩ የሚረባ ቃል ማለት ነው። አንቀጽ መባሉ አንቀጽ መግቢያ በር ማለት ሲሆን ግስም ቃላትን ለመመሥረት መነሻና መጀመሪያ በመሆን ስለሚያገለግል ነው።

የግስ ዓይነት፡-

የግስ ዓይነት ሲባል በልዩ ልዩ መልኩ ልንመለከተው እንችላለን። ይህም ከአርእስት አንጻር፣ ከመሳብና ካለመሳብ አንጻር፣ ልንመለከተው እንችላለን።

ከአርእስት አንጻር ስንመለከተው ስምንት ናቸው። ከመሳብና ካለመሳብ አንጻር ስንመለከተው ደግሞ ሁለት ናቸው ። እነርሱም ገቢርና ተገብሮ ይባላሉ። እንዲሁም ዘር አንቀጽና ነባር አናቅጽ ተብለውም በሁለት ይከፈላሉ። እያንዳንዱን ከምሳሌ ጋር እንመለከተዋለን።

ገቢርና ተገብሮ ግስ

ገቢር ግስ፡- ይህ ማለት ባለቤት አድራጊ የሆነበትና ግሱ ተሳቢ የሚፈልግ ማለት ነው። ለምሳሌ፡- ዳዊት ቀተለ ጎልያድሀ ቢል ዳዊት ጎልያድን ገደለ ማለት ነው። በዚህ ዐረፍተ ነገር ባለቤቱ ዳዊት ነው አድራጊ ነው። ግሱ ቀተለ ነው ተሳቢ ጎልያድን የሚፈልግ ወይም የሚሻ ማለት ነው።

ተገብሮ ግስ፡- ባለቤቱ ድርጊቱ የሚፈጸምበትና ግሱ ሌላ ተሳቢ የማይፈልግ ማለት ነው። ለምሳሌ ጎልያድ ተቀትለ ቢል ጎልያድ ተገደለ ማለት ሲሆን ባለቤቱ ራሱ ጎልያድና ድርጊት የሚፈጸምበትም ራሱ ነው ስለዚህ ግሱም ሌላ ተሳቢ አያስፈለገውም።

✔️ ዘር አንቀጽና ነባር አናቅጽ

ዘር አንቀጽ ፡-ይህ ማለት መነሻ አንቀጽ ያለው የሚረባ፣ የሚገሰስ ማለት ነው። ለምሳሌ ቀደሰ፣ ቀተለ፣ ተንበለ፣ ወዘተ. ሲሆን ዘር አንቀጽ በራሱ ዐበይትና ንኡሳን አናቅጽ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ። ዐበይት የሚባሉት ራሳቸውን ችለው ማሰር የሚችሉ ናቸው። ለምሳሌ ቀዳማይ አንቀጽ፣ ካልዓይ አንቀጽ፣ ሣልሳይ አንቀጽ ናቸው። ንኡሳን አናቅጽ የሚባሉት ግን የግስ ዘር ሁነው ግን ራሳቸውን ችለው ማሠር የማይችሉት ናቸው። ለምሳሌ ዘንድ አንቀጽ፣ ውስጠ ዘ፣ ሳቢዘር ወዘተ.

ነባር አንቀጽ፡- ይህ ማለት ደግሞ የሚረባ ግስ የሌለው በራሱ ማሰሪያ አንቀጽ የሚሆን ማለት ነው። ለምሳሌ ውእቱ፣ አልቦ፣ አኮ፣ ቦ ወዘተ

የግስ አርእስቶች
የግስ አርእስቶች ፰ ወገን ናቸው፡፡ ማን ማናቸው ቢሉ:-

ልሳነ ግእዝ ⛪️

28 Oct, 08:32


ቀተለ
ቀደሰ
ተንበለ
ባረከ
ማህረከ
ሴሰየ
ክህለ
ጦመረ
ናቸው፡፡
አርእስት ማለት አለቆች መሪዎች ማለት ነው፡ሁሉም ግስ በእነዚህ መሠረት ይገሠሣል፡፡ ለእነዚህም የየራሳቸው ሰራዊት አሏቸው፡፡

የቀተለ ሠራዊቶች፡- ኀቤተ፣ተኬሰ፣ሰኰተ ናቸው፡፡
የቀደሰ ሠርዌ ግን አንድ አንገለገ ብቻ ነው፡፡
የተንበለ ሰራዊት፡- ቀበያውበጠ፣ቀንጦሰጠ፣ዘርዜቀ ናቸው፡፡
ባረከና የክህለ ግን ራስ ራሳቸውን ከመሰለ በስተቀር ሌላ አመል ያለው ግስ አይገኝላቸውም፡፡
የማህረከ ሠራዊት፡- አንቃዕደወ፣ሰካዕለወ፣አናሕሰየ ናቸው፡፡
የሴሰየ ሠራዊት፡- አሌለየ፣አቅዜዘየ፣አንጌገየ ናቸው፡፡
የጦመረ ሠራዊት፡- አልኆሰሰ፣ አክሞሰሰ፣ሶርየመ፣ጎርየመ ናቸው፡፡

አዕማድ አርእስት
አዕማድ አርእስት የሚባሉ ቀለማት ፭(5) ናቸው፡፡

አዕማድ አርእስት ማለት የ፰ቱ ግሶች ምሰሶ ማለት ነው፡፡ ቤት በምሰሶ እንደሚሠራ ሁሉ ፰ቱ( አርእስተ ግሶች በእነዚህ አእማድ አርዕስት ይገሰሳሉ፡፡

ማን ማን ናቸው ቢሉ፡-

ቀተለ= አድራጊ
ተቀትለ=ተደራጊ
አቅተለ=አስደራጊ
ተቃተለ=ተደራራጊ
አስተቃተለ=አደራራጊ ይባላሉ፡፡

አሥራው ቀለማት
አሥራው ቀለማት የሚባሉት ፬(4) ናቸው፡፡

ማን ማን ናቸው ቢሉ፦ ተ፣ነ፣ አ፣ የ ናቸው፡፡

እነዚህም በግእዛቸው፣ በራብዓቸው፣ በሣድሳቸው ይነገራሉ፡፡ አሥራው ማለት ሥሮች ማለት ነው፡፡

"ሥርው" ያለውን ሲያበዛው "አሥራው" ይለዋል፡፡ ሥር ማለት መነሻ መሠረት ማለት ነው፡፡ አንድ ዛፍ ያለ ሥር ሊቆም እንደማይችል ሁሉ ከ እስከ ያሉት ግሶችም ያለ እነዚ አይገሰሱም፡፡

ግስ የሚያስጀምሩ ቀለማ ፭(5) ናቸው፡፡ ማን ማን ናቸው ቢሉ፦

ግእዝ፣
ራብዕ፣
ኃምስ፣
ሣድስ፣
ሳብዕ ናቸው፡፡
አነሳሳቸውም
በግእዝ ቀተለ
በራብዕ ባረከ
በኃምስ ሴሰየ
በሳድስ ክህለ
በሳብዕ ጦመረ
ናቸው፡፡ /
https://youtu.be/335wUY0Rh_4 /

✔️ ግስ የማያስነሱ ቀለማት ፪(2) ናቸው፡፡ ማን ማን ናቸው? ቢሉ፦ ካዕብና ሣልስ ናቸው፡፡ የዚህም ማስረጃ "ሖረ" "ቴሀ" ይላል እንጅ "ሑረ" "ቲሀ" አይልም፡፡
የግስ መድረሻ ቀለማት ፪(2) ናቸው፡፡ ማን ማን ናቸው ቢሉ፦ ግእዝ እና ኃምስ ናቸው፡፡ በግእዝ ከ ሀ አንስቶ እስከ ፐ ያለው ግስ ነው፡፡ በኃምስ ግን አንድ ይቤ ብቻ ነው፡፡ ይቤማ ነባር አንቀጽ አይደለምን ቢሉ ካልኣዩን፣ ዘንዱን፣ ትእዛዙን ይዞ ስለተገኘ ነው፡፡

፪(2) ቀለም ሆኖ በግእዝ ተነስቶ በግእዝ የደረሰ እሱም የጠበቀ መረ'ን፣ ነደ'ን፣ ጠበ'ን የመሳሰለ ግስ በቀተለ ቤት ይወርዳል፡፡
፪ (2) ቀለም ሆኖ በኃምስ ተነስቶ በግእዝ የደረሰ እሱም የላላ ዔለን፣ ዔመሤመን የመሳሰለ ግስ በቀተለ ቤት ይወርዳል፡፡
በካልዓዩ "ን" ይጨምራል፡፡ ሤመ ብሎ ይሠይም ስለሚል ነው፡፡ ዘንድና ትእዛዙ በሣልስ ይዘምታል፡፡ ካልዓዩ ይሠይም ብሎ ዘንድና ትእዛዙ ይሢም ይሢም ስለሚል ነው፡፡ ንኡስ አንቀጹ ሣድስ እንጅ ሣልስ አይሆንም፡፡ ይሄውም ሠይም ሰይሞት ይላል፡፡ ሣድስ ቅጽሉና ባዕድ ቅጽሉ በመጥበቅ ቀደሰን ይመስላል፡፡ ሥዩም መሠይም ይላል፡፡ ፪(2) ቀለም ሆኖ በሳብዕ ተነስቶ በግእዝ የደረሰ እሱም የላላ ሖረን፣ ቆመን፣ ጾመን የመሳሰለ ግስ በቀተለ ቤት ይወርዳል፡፡በካልዓዩ ውን ይደርባል፡፡ ቆመ ያለው ይቀውም ብሎ ውን ያመጣል፡፡ ዘንድና ትእዛዙ በካዕብ ይዘምታል፡፡ ንኡስ አንቀጹ እንደ ቀተለ ሳድስ ቅጽሉ እንደ ቀደሰ ነው፡፡ በቀተለ ቤት በወ በክህለ ቤት በው የተነሳ ግስ ዘንድና ትእዛዙ ይዘልቃልም ይጎርዳልም፡፡


/ ሼር / share 👇👇👇
https://t.me/geeztheancient

Subscribe Our YouTube
🛎🔔🔔 👇 ይወዳጁን
https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow

Read here for more
https://abrenendeg.com/ethiopian-education/geez-ethiopia/1824/

ልሳነ ግእዝ ⛪️

28 Oct, 07:38


.
.
.

◆የዓመቱ ስንክሳር በልሳነ ግእዝ◆

     ኢትዮ ግእዝ ሚዲያ ንባብ ቤት!
     [
@Ethiogeezmedianibab]

🔵 Online የግእዝ ንባብ ትምህርት
    
◆የሚሰጡ ትምህርቶች◆
◎ የዘወትር ጸሎት
◎ ውዳሴ ማርያም
◎ አንቀጸ ብርሃን
◎ መልክአ ቅዱሳን
◎ መዝሙረ ዳዊት
◎ ገድላት እና ድርሳናት
◎ አርባዕቱ ወንጌል
◎ ስንክሳር እንዲሁም ሌሎች የንባብ ትምህርቶች እንደ ተማሪው ምርጫ በግል እና በቡድን ይሰጣሉ።

[VIP Class ጀምረናል]
   ▪️ በ Telegram
   ▪️ በ Imo
   ▪️ በ WhatsApp
[በግል እናስጠናዎታለን!]



◆ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቴሌግራም ገጽ
[
@Ethiogeezmedianibab ]
◆ ቴሌግራም መወያያ
[
@Ethiogeezmediachat ]

   ለሐሳብ  አስተያየትዎ
◎ ስልክ =[0913514905]
◎ Telegram =[
@Ethiogeezmedia]
◎ ኢሜል= [
[email protected]]
.
.
.

ልሳነ ግእዝ ⛪️

28 Oct, 06:36


ጥቅምት ፲፰፦

መሶበ ወርቅ ማርያም እንተ አልብኪ አበሳ፤
ጎሞረ ወርቅ ኅሪት ወተቅዋመ ወርቅ ዘንኂሣ፤
ምስለ ወልድኪ ግሩም ዘተብህለ አንበሳ፤
እፎኑ ተሰደድኪ እምገጸ ሔሮድስ እንስሳ፤
መዋዕለ አዝማናት ሠለስቱ ወአኮ ሠላሳ!
 
ሰላም ለቴዎፍሎስ ዘኢነበበ ከንቶ፤
ምስለ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ እምጊዜ ረሰየ ንብረቶ፤
ወእምድኅረ ሐነጸ ቤታ ማርያም አስተርአየቶ፤
ሰላም ለሮማኖስ ብእሴ ስባሔ ወአእኲቶ፤
በአፈ መላእክት ወሰብእ ዘተነክረ ትእግስቶ!

ቴዎፍሎስ መምህር ፍቁረ ማርያም ድንግል፤
ዘርእየ እደ አምላክ እንዘ የአትብ በመስቀል፤
ወዘተናገረቶ ሶልያና እንዘ ይጼሊ በውስተ መርጡል፤
ሮማኖስ ሰማዕት መነኮስ ኃያል፤
ዘምስለ ሕጻን ዘተውህበ ለሕማም ወገድል!

@ዝክረ-ቅዱሳን

join 👇 ያድርጉት

https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

28 Oct, 06:09


📚ርዕስ:-ትርጓሜ ዳዊት
📝 ቋንቋ ፥ ግእዝ =አማርኛ
📜ይዘት:- ሃይማኖታዊ
📖የገፅ ብዛት:- 485
📆ዓ.ም:- -


ሼር ማድረግ አይርሱ
https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

28 Oct, 04:58


ሬስ ርኢ ሕማምየ ወአድኅነኒ።
ሕማሜን/ መከራየን አይተህ አድነኝ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

26 Oct, 06:18


📚ርዕስ:-የጳጳሳት ታሪክ
📝 ቋንቋ ፥ አማርኛ
📜ይዘት:- ታሪክ
📖የገፅ ብዛት:- 192
📆ዓ.ም:-

https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

26 Oct, 05:24


📚ርዕስ:-ግእዝ ቋንቋ
📝 ቋንቋ ፥ ግእዝ =አማርኛ
📜ይዘት:- ግእዝ ሰዋስው
📖የገፅ ብዛት:- 178
📆ዓ.ም:- - 1701 - 1800

https://t.me/BiranaEthio

ልሳነ ግእዝ ⛪️

25 Oct, 14:53


https://youtu.be/LD3I4ki4Tqc?si=Ksnsp6QJy8sGbKGj

ልሳነ ግእዝ ⛪️

25 Oct, 14:46


https://youtu.be/LH3wpE6t2TM?si=7BBRmR4HTqCnCN2l

ልሳነ ግእዝ ⛪️

25 Oct, 05:20


የጥቅምት 17 ማኅሌተ ጽጌ ቃለ እግዚአብሔር ።
ወረብ እና መዝሙር ለማድመጥ 👉https://www.youtube.com/channel/UC0AbE445q7l1pDutVwpw5Ow

Subscriber, like, share በማድረግ አገልግሎቱ እንዲጠናከር እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።


፩ ነግሥ

ሰላም፡ ለአፉክሙ፡ ዘማዕፆሁ፡ ሰላም፤
ጽጌያቲሁ፡ ሥላሴ፡ ለተዋሕዶ፡ ገዳም፤
መንገለ፡ አሐዱ፡ አምላክ፡ ንዋየ፡ መጻኢ፡ ዓለም፤
ወልጡ፡ አምልኮትየ፡ በጸጋክሙ፡ ፍጹም፤
እምአምልኮ፡ ጣዖት፡ ግሉፍ፡ አሐዱ፡ ድርኅም።

ዚቅ

ብፁዕ እስጢፋኖስ፡ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን፤
ለከ የዓርጉ ስብሐተ፡ እግዚኣ ከሰንበት አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት፤
ወሠራዕከ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ፡፡

፪  እንዘ ተሐቅፊዮ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡

ወረብ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ፤
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ፡፡

ዚቅ

ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ፡  ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን፡  አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና፡
እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት፡ ወእኅቶሙ ለመላእክት፡ አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናገሮ በዓምደ ደመና። 

፫. ክበበ ጌራ ወርቅ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ  ባሕርይ፤
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ።

ዚቅ

ይእቲ ፡ ተዓቢ ፡ እም አንስት፡ እሞሙ ፡ ለሰማዕት፤
ወእኅቶሙ ፡ ለመላእክት ፤ መድኀኒቶሙ ፡ ለነገሥት፤
አክሊል ፡ ንጹሕ ፡ ለካህናት፤ ብርሃኖሙ ፡ ለከዋክብት፡፡

፬  ተአምረ ፍቅርኪ

ተአምረ፡ ፍቅርኪ፡  ማርያም፡  ይገብር፡  መንክረ፤
እንዘ፡  ጻዕረ፡  ሞት፡  ያረስዕ፡  ወያስተጥዕም፡  መሪረ፤
በመዓዛ፡  ጽጌኪሰ፡  ለዘበአውደ፡  ስምዕ፡  ሰክረ፤
ውግረተ፡ አዕባን፡ ይመስሎ፡ ኀሠረ፤
እሳትኒ፡  ማየ፡  ባሕር፡  ቈሪረ።

ወረብ

ውግረተ፡  አዕባን፡  ውግረተ፡  አዕባን፡  ኀሠረ፡  ይመስሎ፡  ይመስሎ፡  ኀሠረ፤
ለዘበአውደ፡  ስምዕ፡  ሰክረ፡  በመዓዛ፡  ጽጌኪ፡  እሳትኒ፡  ማየ፡  ባሕር፡  ቈሪር።

ዚቅ

ሐሙ፡  ርኅቡ፡  ጸምዑ፡  ወተመንደቡ፤ ዘኢይደልዎ፡  ለዓለም፡  ረከቡ፤
ቦ፡  እለ፡ በእሳት፡  ወቦ፡  እለ፡  በኲናት፤ ቦ፡  እለ፡  በውግረተ፡  ዕብን፡  ወቦ፡  እለ፡  በመጥባሕት፤
ሃሌ፡  ሃሌ ሉያ፡  ሃሌ ሉያ፤ አስበ፡  ጻማሆሙ፡  ነሥኡ፡  ሰማዕት።

፭. ዘንተ ስብሐተ

ዘንተ ስብሐተ ወዘንተ ማኅሌተ፤
ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤
ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤
ምስለ እለ ሐፀቡ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤
ውስተ ባሕረ ማሕው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።

ወረብ

ምስለ እለ ሐፀቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ፤
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባሕረ ማሕው።

ዚቅ

ገጹ ፡ ብሩህ ፡ ከመ ፡ ፀሐይ ፡ ወእምኲሉ ፡ ስነ ሠርጐ ሰማይ፡
ለእስጢፋኖስ ፡ ኅሩይ ፡ ዘተወልደ ፡ እመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ወማይ፤
አልባሲሁ ፡ በደመ ፡ በግዕ ፡ ዘሐፀበ ፡ ወእምሰረቅት ፡ መርዔቶ  ፡ ዓቀበ፡፡

፮  ኢየሱስ ስዱድ  (ሰቆቃወ ድንግል)

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤
ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉዓን፤
እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤
ኢየሱስ ነግድ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕጻን፤
ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን፤
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን፡፡

ወረብ

ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን
መኃልየ ብካይ ኮነኒ ኮነኒ ዘእሙ ኃዘን

ዚቅ

አንተ ውእቱ ምርጒዞሙ ለጻድቃን፡ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤
መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፡ ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው።

መዝሙር ዘቅዱስ ያሬድ ጳጳሳት ጥቅምት 17 እሑድ በሚውልበት ሰንበት የሚባል

ሃሌ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፡ ሃሌ ሃሌ ሉያ
( https://youtu.be/LH3wpE6t2TM?si=7BBRmR4HTqCnCN2l )
ጳጳሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ሥዩማነ ቤተ ክርስቲያን፡ እለ ሎሙ ሕግ ወሎሙ ሥርዓት ብጹዕ እስጢፋኖስ ምስለ ኵሎሙ ቅዱሳን ለከ የዓርጉ ስብሐተ፡፡

እግዚአ ለሰንበት አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት፡ ወሠራዕከ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ ወብውህ ለከ ትኅድግ ኃጢአተ ረቢ ንብለከ ረቢ ሊቅ ነአምን ብከ፡፡

ልሳነ ግእዝ ⛪️

25 Oct, 03:09


.
.
.
  ◆ማኅሌተ ጽጌ◆

◆ ትምህርቱ የሚሰጥበት ቴሌግራም ገጽ
[
@Ethiogeezmedianibab ]
◆ ቴሌግራም መወያያ
[
@Ethiogeezmediachat ]

   ለሐሳብ  አስተያየትዎ
◎ ስልክ =[0913514905]
◎ Telegram =[
@Ethiogeezmedia]
◎ ኢሜል= [
[email protected]]
.
.
.

ልሳነ ግእዝ ⛪️

23 Oct, 14:40


መልመጃውን ሁላችሁም ተሳተፉ የፊደላት ግድፈት ካለ ይቅር በሉን 🙏 ተወያዩበት ማብራሪያ እንሰጥበታለን።

ወደ ጥያቄው 👇

ልሳነ ግእዝ ⛪️

17 Oct, 18:05


ለሥራ ፈላጊዎች 👇🏿👇🏿
ትክክለኛ ነው ተከታተሉት
https://t.me/abrenjobs

ልሳነ ግእዝ ⛪️

16 Oct, 16:52


በመምህር ቀለሙ እንዳለው

https://youtu.be/j91MKMBlWaA?si=25C10vdLJ_HupqV1

ልሳነ ግእዝ ⛪️

16 Oct, 03:54


ከጠቀማቹህ እንደ ጥቆማ

📓የተለያዩ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ለማግኘት
👇🏿👇🏿
https://t.me/BiranaEthio

👇🏿👇🏿 ለተማሪዎች
📓የመማሪያ መጻሕፍት በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት (ከ1ኛ_12ኛ ክፍል ) እና አጋዥ የማጣቀሻ መጻሕፍት ማግኘት ከፈለጉ

https://t.me/YMechanical

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Oct, 10:11


https://youtu.be/VfYsm8nTLZ0

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Oct, 07:55


share
https://t.me/geeztheancient

subscribe YouTube
https://www.youtube.com/@yared2112

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Oct, 07:51


ገድለ ኢያሱ ንጉሠ ነገሥት አድያም ሰገድ መናኔ መንግሥት ወሰማእት

መጽሐፉን እነሆ 👇🏿

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Oct, 07:36


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ኢሖራ በፍናዊሃ፤
ለዛቲ ዓለም ዘዕበድ ጥበባቲሃ፤
ለኢትዮጵያ ምድርነብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያሃ፤
ውስተ ገፀ ኲሉ ደወላ ዜና ነገርከ በዝኃ፤
ወእስከ ጽንፋ ለምድር ነቢብከ በጽሐ።

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Oct, 07:18


❀እንኳን አደረሳችሁ!❀

#ጻድቅ #ወሰማዕት፥ ወመናኔ መንግሥት፥ ወንጉሠ #ኢትዮጵያ አፄ #ኢያሱ (አድያም ሰገድ)

ሰላም ለዝክረ ስምከ ግጽወ ፊደላት ሠለስቱ።
ወለሥዕርትከ ሰላም ዘተወደሰ ሲበቱ።
ንጉሠ ምናኔ ኢያሱ ወሰማዕት በላዕለ ዝንቱ።
ትብለከ ደብረ ብርሃን ለመርዓዌ ሰማይ መርዓቱ።
ወልድ እኁየ ወሪዶ ውስተ ገነቱ።
አፈዋተ ምዕዘ ልብሰቱ።

(መልክዐ ኢያሱ)

ብንተረጉመው ጣዕሙ ይጎድላል፤ ከበረከቱ ይክፈለነ፡፡

¤መንግስታቸውን ትተው በመነኑበት በክፉዎች ከተገደሉ እነሆ ዛሬ 318 ዓመት ሞላቸው::
¤ኢያሱ ቀዳማዊ ደግ: ምሑር: ለቤተ ክርስቲያንና ለሃገር ሞገስ ነበሩ::
¤ደብረ ብርሃንን: ክብራንን: ምዕራፈ ቅዱሳንን: ደቁዋን ጨምሮ ብዙ አብያተ መቃድስን አንጸዋል::

¤ይህ የምታዩት ደግሞ የጻድቁ ንጉሥ አካል ያረፈበት ሳጥን ነው::
¤የተመለከትኩት በምጥርሐ ደብረ ቂሳርያ ደሴት (ጣና) ውስጥ ሲሆን አቀማመጡ ያሳዝናል::
¤ለነገሩስ ገዳሙም የሚገኘው በብዙ ችግር ውስጥ ነው::

✿ስም አጠራሩ የከበረ ፡ ዜና ሕይወቱ ያማረ ፡ ደጉ ንጉሣችን #አድያም_ሰገድ_ኢያሱ ፡ (በ1698 (1699) ዓ/ም) በዚህች ቀን (ጥቅምት 5 ቀን) ዐርፈዋል፡፡✿

✿ጻድቅና ሰማዕቱ ንጉሥ የተሰቃየ በደቅ ደሴት ሲሆን የተገደለው በጨቅላ መንዞ ውስጥ ነበሩ፡፡

✿መቃብሩ ግን በፎቶው እንደምታዩት ያሳዝናል፡፡ የሚገኘው በምጽርሐ (ምጥርሐ) ደሴት ፡ ጣና ውስጥ ነው፡፡

✿ከደጉ ሰማዕት ንጉሥ በረከት ይክፈለን፡፡✿

©ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

15 Oct, 06:42


📖

ልሳነ ግእዝ ⛪️

14 Oct, 16:23


share
https://t.me/BiranaEthio
subscribe our YouTube
https://www.youtube.com/@yared2112

ልሳነ ግእዝ ⛪️

14 Oct, 14:30


ርዓተ ማኅሌት ዘጥቅምት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ወረቦቹን ለማድመጥ 👉🏿
https://youtu.be/5Jt58SPfbaU
መልክዓ ሥላሴ

ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።

ዚቅ
በአፍአኒ አንትሙ፣ ወበውሣጤኒ አንትሙ፤ በገዳምኒ አንትሙ፤ ብርሃኑ ለዓለም (ለኢያሱ) አንትሙ።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።

ዚቅ
ከመ መዓዛ ቅዱሳን፤ ውስተ አብያተ ክርስቲያን፤ ይሰምዖሙ ጸሎቶሙ ለንጹሐን ከመ መዓዛ ቅዱሳን።

ዘምንክር ጣዕሙ

ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
እስመ ርእየ ሕማማ ለዓመቱ፤ ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፤ መዝገቡ ለቃል ጽጌ እንተ ኢትትነገፍ መድኃኒተ ሕዝብ፤ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን።

መልክዓ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።

ዚቅ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።

ወረብ
ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ/፪/
ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ አማን በአማን ሐዋርያ/፪

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤ አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤ አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ።

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

ሰላም ለጒርኤከ ኅሩመ መብልዕ ዘኮነ፤ ወእስከ ስቴ ማይ መነነ፤ ሶበ ረድኤተከ ርእዩ ወኪዳነከ እሙነ፤ ይቤሉከ ኲሉ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡነ፤ በኪዳንከ አሥራተ ንሥአነ።

ወረብ
አሥራተ ንሥአነ አሥራተ ንሥአነ/፪/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ ንሥአነ/፪/

ዚቅ
በመንግሥተ ሰማያት ይነግሥ ምስሌከ፤ ኃጥእ ዘገብረ ተዝካረከ፤ ወጸውዓ ስመከ እንዘ ይብል አምላከ ተካየድከ፤ በእንተዝ ንሥአነ ለሕዝብከ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አሥራተ በኪዳንከ።


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ


ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ኢሖራ በፍናዊሃ፤ ለዛቲ ዓለም ዘዕበድ ጥበባቲሃ፤ ለኢትዮጵያ ምድርነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያሃ፤ ውስተ ገፀ ኲሉ ደወላ ዜና ነገርከ በዝኃ፤ ወእስከ ጽንፋ ለምድር ነቢብከ በጽሐ።

ዚቅ
ዝንቱሰ ብእሲ መምህርነ፤ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ፤ ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ፤ ሐዋርያ ዘኮነ ወተሰምዓ ዜናሁ፤ ውስተ ኲሉ ምድር።

ወረብ
ዝንቱሰ ገብረ ሕይወት ተፈነወ ውስተ ምድርነ/፪/
ይክሥት ብርሃነ ይፈውስ ዱያነ ሐዋርያ ሐዋርያ ዘኮነ/፪/

ሰቆቃወ ድንግል


እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

ወረብ
በከመይቤ"ኦዝያን"(፪) ለክብረ ቅዱሳን/2/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/2/

ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ


ማኅሌተ ጽጌ


እምደቂቀ ሕዝብኪ አነ እንዘ ነዳይ ወአባሲ፤ በብዕለ ዚአኪ ድንግል እትሜካሕ ከመ ነጋሢ፤ወበጽድቅኪ እትፌሣሕ አርአያ ጻድቅ ብእሲ፤እስመ ብየ ተአምርኪ ጌጋየ ኃጥአን ደምሳሲ፤ወመዝገበ ብዕል ጽጌኪ ለኲሉ ዘይሴሲ

ዚቅ
ማርያምሰ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤ወአነሂ እትፌሣሕ በእንቲአኪ፤እስመ ረከብኩ እምዉስተ ደቂቅኪ እለ የሐዉር በትእዛዝየ፤አምኂ አምኂ፤አምኂ ደቂቀ እኅትኪ ኅሪት።

 ምልጣን


ኮከብ ብሩህ ዘሠረቀ እምአቅሌስያ፤ ቤተ ክርስቲያን ዘንሰምያ፤ ኮኖሙ አበ ለሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ፤ አማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ።

አመላለስ


አማን በአማን/፬/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያ/፬/

እስመ ለዓለም


ንጉሥኪ ጽዮን አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ወለሰማይኒ በከዋክብት፤ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ብርሃኖሙ ለመሐይምናን፤ዘየአምር እምቅድመ ሕሊና፤ዘይሔሊ ልብ አርአየ ኃይሎ፤በላዕሌነ ወጸገወነ ሠናይቶ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

14 Oct, 13:11


share
https://t.me/geeztheancient
subscribe our YouTube
https://www.youtube.com/@yared2112

ልሳነ ግእዝ ⛪️

14 Oct, 06:14


አብርሃ ወአጽብሃ ነገሥት ጻድቃን፤
ዘመለኩ ኅቡረ በውስተ አሐቲ መካን፤
በርተሌሜዎስ ሰማዕት ወሐዋርያሁ ለብርሃን፤
ሐናንያ ዘደማስቆ ብእሲ ምዕመን፤
ዘአጥመቆ ለጳውሎስ በትእዛዘ አምላክ መድኅን!

ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ

ልሳነ ግእዝ ⛪️

13 Oct, 18:51


የማንቂያ ደወል ፕሮግራም በመምህር ምህረተ አብ መሪነት ይካሔድ የነበረው ለምንድን ነው የተቋረጠ?

ጃንደረባው ሚዲያስ የት ደረሰ ? ሚናቸው ምን ነበረ?

ልሳነ ግእዝ ⛪️

13 Oct, 06:05


https://youtu.be/X9x-_6Isxz0?si=2ShVbcYsS3rCsD3s

ልሳነ ግእዝ ⛪️

12 Oct, 17:03


ማኅሌተ ጽጌ አመ ፫ ለ ጥቅምት


መልክአ ሥላሴ


ሰላም ለኩልያቲክሙ እለ እሩያን በአካል። ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል። እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል። ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል። ወበቀራን ተተክለ መድኃኒት መስቀል።


ዚቅ
ሃሌ ሉያ (፱) ሐረገ ወይን እንተ በምድር ሥረዊሃ፡ ወበሰማይ አዕፁቂሃ፤
ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፡ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤
ሐረገ ወይን ፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን፤
ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፡ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

፪. በከመ ይቤ መጽሐፍ /ማኅሌተ ጽጌ/

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፤
ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ (ጽላተ) ኪዳን፤
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፤
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን፤
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡

ወረብ፦

በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን ዘኮንኪ ለዕረፍት ትእምርተ ኪዳን፤
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ብርሃን ዕለተ ብርሃን።

ዚቅ፦

ሰንበቶሙ ይእቲ ለጻድቃን ትፍሥሕት፨ ሰንበቶሙ ይእቲ ለኃጥአን ዕረፍት፨ ኅቡረ ንትፈሣሕ ዮም፨ በዛቲ ዕለት፡፡


ከመ ታቦት ሥርጉት /ማኅሌተ ጽጌ/

ከመ ታቦት ሥርጉት በወርቀ ዐረብ ወተርሴስ፤
በድንግልና ማርያም ሥርጉተ ሥጋ ወነፍስ፤
ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ፤
ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ።

ወረብ
እምዘጸገዩኪ ለጳጦስ በዓመት ሠላስ ኢያቄም ወሐና ቀንሞስ ቀናንሞስ፤
ተአምረ ነቢር አርአይኪ ተአምረ ነቢር አርአይኪ በቤተ መቅደስ።

ዚቅ
ሰአሉ ለነ ኢያቄም ወሐና፤
ዘፈረይክሙ በቅድስና፤
መሶበ ወርቅ

ዓዲ ዚቅ

አንቲ ዉእቱ ንጽሕት እምንጹሃን ድንግል ኅሪት ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት ዘግቡር እምእጽ ዘኢይነቅዝ ሥርግው በወርቅ ንጹፍ ወልቡጥ በእንቆ ባህርይ ዘየሃቱ ዘብዙኅ ሴጡ ከምዝ ነበርኪ ዉስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጻኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ዐሠርተ ወክሌተ ዐመተ እንዘ ትትናዘዚ እምሃበ መላእክት ስቴኪኒ ስቴ ህይወት ውእቱ ወመብለኪኒ ሕብስት ሰማያዊ ።



ወረቦቹን እና አቋቋሙን ለማድመጥ
Open 👈

እንዘ ተሐቅፊዮ

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ፤
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡፡

ወረብ፦

እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ፤
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ።


ዚቅ
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎኅ ሠናይት ፨ ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ፨ ዕፀ ጳጦስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት።

ዐዲ ዚቅ

ይዌድስዋ ትጉሃን ፤ ይቄድስዋ ቅዱሳን ፤
ሰሎሞን ይቤላ ርግብየ ሠናይት፤
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ፍጽምት፤
ዳዊትኒ ይቤላ ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ፡፡

ክበበ ጌራ ወርቅ

ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤
አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ
ዚቅ
ከርካዕ ዘተተክለት በቤተ መቅደስ፤
መራኁቱ ለጴጥሮስ፤
አንቲ ውእቱ ደብተራ ስምዕ ዘጳውሎስ፤
አማን አክሊሉ ለጊዮርጊስ።

ሰቆቃወ ድንግል
በቤተ መቅደስ ዘልሕቅተ ወለተ ካህናት እንዘ ትሌለይ ሥሩዐ፤ ኀብስተ ሰማይ ኀቡዐ ወጽዋዐ ወይን ምሉዓ፤ እፎ ከመ ነዳይ ሲሳየ ዕለት ዘኀጥአ፤ ተዐገሠት በብሔረ ግብፅ ለሀበ ወጽምዓ አልቦ ከማሃ ዘረከበ ግፍዓ።

ወረብ

እፎ ከመ ነዳይ ዘሀጥአ ሲሳየ ዕለት ፤ በቤተ መቅደስ ዘልህቀት ወለተ ካህናት ። እንዘ ትሴሰይ ህብስተ መና ህበዐ።

ዚቅ
እሴብህ ጸጋኪ ኦ ኡጽፍተ ልብሰ
ወርቅ እግዘትየ ወለተ ዳዊት ንጉሥ
ዘተሐጸንኪ በቤተ መቅደስ ወተአንገድኪ በፈሊስ
እምሃገርለሃገር እንዘተ አውዲ በተጽናስ ።

༒   ኪነ ጥበቡ መዝሙር / ዘበዓታ/ ༒  


ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ኪነ ጥበቡ መንክር ወዕጹብ ፣ ኪነ ጥበቡ መንክር ወዕጹብ ለዘሀሎ መልዕልተ አርያም፣ አርአየ ምሕረቱ በላዕሌነ፣ ዘከለሎ ለሰማይ በከዋክብት ብሩህ፣ አርአየ ምህረቱ በላዕሌነ፣ ወለምድርኒ አሠርገዋ በጽጌያት ንጹሕ፣ አርአየ ምሕረቱ በላዕሌነ፣ ወሠርዓ ሰንበተ ለነባሪ ያዕርፉ ባቲ፣ አርአየ ምሕረቱ በላዕሌነ፣ መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።

  ༒   + + + + + አመላለስ + + + +  + ༒
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጎላት ዘውስተ ቆላት፤
ጸገዩ ቀንሞስ ምስለ ናርዶስ።

                 👉    © ፍሬ ማኅሌት

https://t.me/geeztheancient



YouTube 👇👇
https://www.youtube.com/@yared2112

17,004

subscribers

1,593

photos

117

videos