፡፡ ይኸውም ሊታወቅ ከዚህ አስቀድሞ ቤተ መቅደሱን ለማፍረስ ንዋየ ቅድሳቱን ለመዝረፍ ሕዝቡን ለመማረክ ምታ ነገሪት ብለው ይመጡ የነበሩ የሩቅ ምስራቅ /የፋርስ የባቢሎን ሰዎች በጌታችን ልደት ምክንያት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ "አይቴ ሃሎ ዘተወልደ ንጉሠ አይሁድ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው" (ማቴ.2፥4) እያሉ መጥተው ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ ገብረውለታል፡፡
✔ ነፍስና ሥጋ፡- በሲዖልና በመቃብር ተለያይተው የነበሩ ነፍስና ሥጋ ከእመቤታችን ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው በሆነ ጊዜ ነፍስና ሥጋን አስታርቋል፡፡
ሰውና እግዚአብሔር፡- አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በልቶ የሰውና የእግዚአብሔር የፍቅር ግንኙነት ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ተቋርጦ ነበርና ጌታችን የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በተወለደ ጊዜ እርቀ ሰላም ተገኝቷል፡፡
✔ ሰውና መላእክት፡- አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ጋር በተጣላ ጊዜ ቅዱሳን መላእክትም ስለተጣሉት በምትገለባበጥ ሰይፈ እሳት አስፈራርተው ከገነት ካስወጡት በኋላ ወደ ገነትም እንዳይገባ ገነትን ይጠብቁ ነበር፡፡ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አንድ ሆነው ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ይኸውም ዮም አሐደ መርኤተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብህዎ ለክርስቶስ እንዲል፡፡ ሰውና መላእክት ክርስቶስን ለማመስገን አንድ ሆኑ እንዳለ ሊቁ፡፡
✔ ቤተ ክርስቲያን ፤ ጌታችን የተወለደባት እና ሰባቱ መስተጻርራን አንድ የሆኑባት፤ ሰውና መላእክት የዘመሩባት የብርሃን ጎርፍ የጎረፈባት እንስሳት እስትንፋሳቸውን የገበሩባት ቤተልሔም በቤተ ክርስቲያን ትመሰላለች፡፡
✔ ቤተልሔም፡- ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ ፤ ሰውና እግዚአብሔር ፤ ነፍስና ሥጋ ፤ ሰውና መላእክት አንድ ሆነው በቤተልሔም እንደዘመሩ ዛሬም የፍቅር ተምሳሌትና የአማኞች ሁሉ እናት በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘር፣ በጎሣ፣ በጥቅም፣ በሥልጣን ሳንከፋፈል አንዲት ቤተ ክርስቲያንን በፍቅር እንድናገለግል በቤተልሔም የተደረገው የልደቱ ምሥጢር ይህን ያስተምረናል፡፡
ክርስቲያኖች የጌታን መወለድ የምናስበው በዚህ መንፈስ ነው፡፡
መልካም የልደት በዓል ይሁንልን አሜን !!!
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖
❖ ❖ ❖ የልደት በዓል ማኅሌት ❖ ❖ ❖
❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት ፤
ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ፡፡
ትርጉም፦ ቅድስት ድንግል ከሆነች ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት፤ እነሆ ዛሬ ሰማያዊው በበረት ተኛ፡፡
❖ ❖ ❖ ንግሥ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤
ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤
እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤
ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል፡፡
ትርጉም፦ በዘመናት የሸመገልክ መጀመርያና መጨረሻ የሆንክ አማኑኤል ሆይ ለልደት ሰላም እላለሁ የአብ ቃል የሆንክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ድንግል እንዴት ተሸከመችህ? አምላክስ ስትሆን እንዴት በበረት ተኛህ?
❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ፤
እፎ ተሴሰየ ሐሊብ ከመ ሕፃናት፡፡
ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ፤ በድንግል ማኅፀንም አደረ፤ እንደ ሕፃናት ወተትን እንዴት ተመገበ?
❖ ❖ ❖ መልክአ ኢየሱስ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለአፅፋረ እዴከ ዘሕበሪሆን ጸዓዳ...
ትርጉም፦ቀለማቸው ነጭ ለሆኑት የእጆችህ ጥፍሮች ሰላም እላለሁ.....
❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል ፤
አምኃሆሙ አምፅኡ መድምመ ፤
ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ፡፡
ትርጉም፦ሰብአ ሰገል የተወለደልንን ሕፃን አገኙ በደስታም ዘለሉ ስጦታቸውንም አመጡ፡፡
❖ ❖ ❖ ምስባክ ❖ ❖ ❖
ዲያቆኑ በቅኔ ማኅሌቱ "መዝ 71:10" ይሰብካል።
“ነገሥተ ተርሴስ ወደሴያት አምኃ ያበውዑ ፤ ነገስተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመፅኡ ፤
ወይሰግዱ ሎቱ ኩሎሙ ነገሥተ ምድር ፡፡ ትርጉም፦ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ! ነገሥታት ኹሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ኹሉ ይገዙለታል፡፡
❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
መዘምራን (መሪጌቶች) መሪና ተመሪ ኾነው የሚዘምሩት ሲኾን በመቀጠልም ኹሉም በኅብረት እየደጋገመ የሚዘምረው ነው! እንዲህ ይላል.....
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ ፤
እም ቅድስት ድንግል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤
አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ፡፡
ትርጉም፦ እነሆ ዛሬ በክርስቶስ ልደት ምክንያት ደስታ ኾነ ከቅድስት ድንግል የተወለደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለእርሱ ሰብአ ሰገል ሰገዱለት!
በእውነት የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡
❖ ❖ ❖ እስመ ለዓለም ❖ ❖ ❖
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም ዘይሁዳ፤
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤
ሰብአ ሰገል አምፅኡ ሎቱ ጋዳ፤
ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ ፡፡
ትርጉም፦ኢየሱስ በይሁዳ ቤተልሔም ተወለደ፤ የጢሮስ ሴቶች ልጆችም በዚያ ይሰግዱለታል፤ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን አመጡለት፤ የይሁዳ ሴቶች ልጆችም ደስ ይላቸዋል፡፡
❖ ❖ ❖ ዑደት ❖ ❖ ❖
“ኹላችንም በልደቱን ብርሃን በማሰብና ጧፍ በማብራት "ሥዕለ አድኅኖ" ይዘው ከሚዞሩት ካህናት በስተኋላ ተሰልፈን እንዲኽ ይኼንን ዝማሬ እናቀርባለን!
“አማን በአማን አማን በአማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ ፡፡
ትርጉም፦እውነት በእውነት እውነት በእውነት፤ የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡
❖ ❖ ❖ ዕዝል ❖ ❖ ❖
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ፤
ዮም ተወልደ እግዚእ ወመድኅን ቤዛ ኩሉ ዓለም፡፡
ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ ፤ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ የዓለም ኹሉ ቤዛ የኾነው ጌታና አዳኝ ዛሬ ተወለደ፡፡
❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ተስሃልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤
ንሰብክ ወልደ እም ዘርዓ ዳዊት ዘመፅአ ወተወልደ በስጋ፤
ሰብእ እንዘ ኢየአርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ ስጋ ኮነ ወተወልደ፡፡
ትርጉም፦ ጌታ ሆይ ምድርህን ይቅር አልክ ሃሌ ሉያ ከዳዊት ዘር የመጣውንና በሥጋ የተወለደውን ወልድን እንሰብካለን ከምስጋናው ዙፋን የማይራቆት ሰው ነው! በድንግል ማኅፀን አደረ ሥጋ ኾኖም ተወለደ፡፡
የሚቀደሰው ቅዳሴ ☞ "ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልእ"
የቅዳሴው ምስባክ ☞ መዝ 71:15 ፤
የሚነበበው ወንጌል ☞ ሉቃ2:1-21
💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹