ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ @marakisport34 Channel on Telegram

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

@marakisport34


እንኳን በደህና ወደ ማራኪ ስፖርት የቴሌግራም ቻናል በሰላም መጣችሁ።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ (Amharic)

እንኳን በደህና ወደ ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ ላይ በመለየት አገልግሎታችንን። ይህ የቴሌግራም ቻናል ላይ እንዲከተለሉ ሳይሆን አዳዲስ እና ተመሳሳይ ስፖርት መረጃዎች እንደሚገኙ ሲያመነን እናመሰግናለን። በምንጮችዎ ግጥሞችና ምኞታዎ በሚያስፈልግ መረጃዎች ፈጥሯቸዋል እንደሆነ። ይህ ስፖርት በጉባኤውን እና ጥቃትን በመሕይወት ሲወክሉ መሰረታዊ ቪድዮዎችንም ይመልከቱ። ይህ ይዚህ ቻናሎችን ለአስፈላጊ ህትመት ማስጠበቅ ማንበብ እና ከሆነው ምርጫ ለማስገባት ወይም ለመረጃዎችን ማስቀመጥ ይችላሉ።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

10 Nov, 08:15


🔴👀 የማርሴው አስልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ቡድናቸው የ3-1 ሽንፈት ካስተናገደ በኃላ ከማንችስተር ዩናይትድ ቀርቦላቸው የነበረውን ውል ለተጫዋቾቹ እያሳዩ
"አሁን ቦታየ ይሄ ነበር(ማንችስተር ዩናይትድ)።ነገር ግን እኔ ከገንዘብ ይልቅ ስሜቴን አዳምጣለው።ወደ ማርሴ የመጣሁትም ለስሜቴ ነው።”

በዚህ ወር ሊስት ይደረጋል ስሙ ሲድ ይባላል ጥሩ ነው እየተባለ ነው ከፈለጋችሁ ታስክ እና ዴሊ ቼክን አድርጉ ከፈለጋችሁ ብቻ ስሩ በጣም ምርጥ ነው።

http://t.me/seed_coin_bot/app?startapp=389697849

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

06 Nov, 11:56


🔴ቡካዩ ሳካ በሰሞኑ ውጤት ምክንያት የአርሰናል ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች እንዲረጋጉ ጠየቀ።

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዮ ሳካ ቡድናቸው ባለፉት ጨዋታዎች ካስተናገዳቸው ሽንፈቶች ብዙ መማሩን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ከገጠሙን ሽንፈቶች በብዙ ተምረናል ያለው "ሳካ " አሁን ወደ አሸናፊነታችን ልንመለስ የሚገባን ጊዜ ላይ ደርሰናል" በማለት የዛሬው የኢንተር ሚላን ጨዋታ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።

ተጨዋቹ አያይዞም ቡድናቸው ዛሬ ከምርጥ ቡድን ጋር እንደሚጫወት በመጥቀስ " ነገር ግን እኛ የትኛውም ቡድንን የማሸነፍ አቅም አለን" ብሏል።

ቡካዩ ሳካ አያይዞም በሰሞኑ ውጤት ምክንያት የአርሰናል ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች እንዲረጋጉ በሰጠው አስተያየት ጠይቋል።

መድፈኞቹ ዛሬ ምሽት 5:00 በሻምፒዮንስ ሊጉ ከኢንተር ሚላን ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

31 Oct, 09:31


☝️☝️ይህ የውቡ ብዙዎችን በፍቅሩ እንዲወድቁለት ያደረገው የእግርኳስ ታሪክ በህይወት አንዴ የተከሰተ አጋጣሚ ነው ።👇👇

https://t.me/marakisport34
https://t.me/marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

30 Oct, 08:25


'ሮናልዲንሆ ጎቾ ዲያሲስ ሞሬራ' እንዲህ ሲል ይናገራል :- "የወርቅ ኳሴን ለእናቴ የምስጋና ስጦታ አድርጌ ሰጠኋት እንደ ተንኮለኛ ልጅ ተስፋ ቆርጬ አላውቅም። ለስኬታማነት መመሪያ ሰጠችኝ እናም ከድህነት ወጥተናል ምክንያቱም በፅናትዋ እና በችሎታዬ ላይ እምነት ስላላት ነው ። "

https://t.me/marakisport34
https://t.me/marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

28 Oct, 15:48


ፖርቹጋላዊው የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የስንብት መልዕክቱን አስተላልፏል።

“ ለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ “ ሲል መልዕክቱን ያስተላለፈው ፈርናንዴዝ የተጋራናቸውን ጊዜያት አደንቃለሁ መልካሙን እመኝልሃለሁ ሲል ተናግሯል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ አክሎም ቡድኑ በጥሩ ሁኔታ ላይ ባይገኝም የክለቡ ደጋፊዎች ኤሪክ ቴንሀግ ለክለቡ የሰሯቸውን ጥሩ ነገሮች እንዲያቆዩ ጠይቋል።

የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ስንብት ያወቁት ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ ሲያደርገው መሆኑ ተገልጿል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

27 Oct, 12:38


አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድናቸው እያንዳንዱን ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚገባው ከዛሬው ጨዋታ በፊት አሳስበዋል።

እስከ አሁን ባለው የውድድር ዘመን ቡድናቸውን “ እኛን ማሸነፍ ከባድ ነው “ ሲሉ ሲገልፁት “ ነገር ግን ቡድኑ ተደጋጋሚ ድል እያስመዘገበ አለመሆኑን ገልፀዋል።

“ ጨዋታዎችን ማሸነፍ መቻል አለብን ፣ ይህን ለማድረግ ግብ ማስቆጠር መቻል አለብን “ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ

ዌስትሀም ከባድ ተጋጣሚ መሆኑን የጠቆሙት አሰልጣኙ “ ባለፉት ሁለት የውድድር ዓመታት ተሸንፈናል ፣ አስፈላጊውን ነጥብ ለመያዝ የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየት ይኖርብናል “ ብለዋል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

26 Oct, 18:13


የዛሬው ኤልክላሲኮ በፎቶ📸📸📸

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

25 Oct, 11:00


በዚህ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታዎች !

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

25 Oct, 10:17


የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል እሁድ ከአርሰናል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ ተገልጿል።

ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ዲያጎ ጆታ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

በተጨማሪም ብራድሌይ እና በዚሁ ክረምት ወደ ሊቩርፑል የተቀላቀልው ፌዴሪኮ ኬሳ ለአርሰናል ጨዋታ የመድረስ እድላቸው የጠበበ መሆኑን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አረጋግጠዋል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

24 Oct, 16:38


እንግሊዛዊው የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ፖል ሜርሰን አርሰናል እሁድ በሊቨርፑል ሽንፈት ከገጠመው ከሊጉ የዋንጫ ፉክክር ሊወጣ እንደሚችል ገልጿል።

የእሁዱ ጨዋታ ወሳኝ መሆኑን የገለፀው ፖል ሜርሰን የሚመዘገበው ውጤት በሊጉ የዋንጫ ፉክክር ላይም ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተናግሯል።

የቀድሞ ተጨዋቹ አክሎም " አርሰናል በጨዋታው ሽንፈት የሚያስተናግድ ከሆነ ከዋንጫ ፉክክሩ ውጪ ሊሆን ይችላል " ብሏል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

24 Oct, 10:35


የ ላሚን ያማል ያለፉት 30 ጨዋታዎች ያገኘው ሬቲንግ
😦
sofascore

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

24 Oct, 03:43


ሊቨርፑል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ካደረጋቸው የ መጀመርያ12 ጨዋታዎች 11ዱን አሸንፏል። 
እንዴት ያለ ጅምር ነው🔥

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

22 Oct, 19:53


#እረፍት

ሪያል ማድሪድ 0-2 ዶርትመንድ

             ማለን
             ጊቴንስ

አርሰናል 1-0 ሻክታር ዶኔስክ

ሪዝኒክ ( በራስ ላይ )

ጁቬንቱስ 0-0 ስቱትጋርት

ፒኤስጂ 0 - 1 ፒኤስቪ

                ላንግ

አስቶንቪላ 0-0 ቦሎኛ

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

22 Oct, 19:05


የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ኣርጀንቲናዊው የኢንተር ሚያሚ የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ የሜጀር ሊግ ሶከር የመስከረም ወር ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በወሩ ባደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች አምስት ግቦች አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

22 Oct, 05:44


ፈረንሳዊው የ ማንችሰተር ዩናይትድ ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ከረጅም ጉዳት በኋላ ወደ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን አሁን ላይ ለብቻው የተለያዩ ትሬይኒንጎችን እየሰራ ነው::
በቅርቡ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ እንደሚጀምር ታማኙ ጋዜጠኛ Fabrizio Romano ዘግቧል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

21 Oct, 16:55


የሎስ ብላንኮዎቹ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ስለ ነገ ተጋጣሚያቸው ቦርስያ ዶርትመንድ “ ሁሉንም እናውቃለን  መሰለል ኣይጠበቅብንም“ 😂😂

ቦርስያ ዶርትመንድ ሪያል ማድሪድ ይሰልለናል በሚል ፍራቻ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ልምምድ ላለመስራት መወሰናቸው መገለፁ ይታወሳል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ “ ስለ ዶርትመንድ ሁሉንም ነገር እናውቃለን እንዴት እንደሚጫወቱ ለማወቅ መሰለል አያስፈልገንም “ ብለዋል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

21 Oct, 08:02


X empire ያመለጣችሁ ስሩት በቀን አንዴ ብቻ daily check in ብቻ ነው የሚኖረው

http://t.me/hrummebot/game?startapp=ref389697849

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 19:08


ሊቩርፑል በ 8 የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ጨውታዎች 15 ግቦች ሲያስቆጥር 3ግቦች ተቀጥሮበታል::

ሳላህ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ በርካታ የፍፁም ቅጣት ምት ግቦችን ማስቆጠር የቻለ አምስተኛው ተጨዋች መሆን ችሏል።

የደረጃ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1⃣ ሊቨርፑል - 21 ነጥብ

2⃣ ማንችሰተር ሲቲ -20 ነጥብ

3⃣ አርሴናል - 17ነጥብ

ቀጣይ የ እንግሊዝ  ፕሪሜየር ሊጌ መርሐ ግብር ?

እሁድ 👉አርሰናል 🆚 ሊቨርፑል

እሁድ 👉 ቼልሲ 🆚 ኒውካስል ዩናይትድ

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 17:58


ሊቨርፑልን እየመሩ ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ኔዘርላንዳዊው አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አዲስ ታሪክ መፃፍ ችለዋል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከመጀመሪያ አስራ አንድ ጨዋታዎች አስሩን በአሸናፊነት መወጣት የቻሉ የመጀመሪያ የሊቨርፑል አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ሊቨርፑል ቼልሲን አሸንፎ በዘንድሮው የውድድር አመት ሁሉንም ከሜዳው ውጪ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች ያሸነፈ ብቸኛው ክለብ መሆኑን አረጋግጧል።

1: የፕርሚየር ሊጉ መሪ

2: ማንችስተር ዩናይትድ ፣ ቼልሲ እና ኤሲ ሚላንን አሸነፉ

3: ሁለቱንም የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች አሸነፉ

4:በውድድር አመቱ አንድ ሽንፈት ብቻ አስተናገዱ( ኖቲንግሃም ፎርስት

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 12:56


ታሪክን የዋሊት

የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት እና የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃ ከምንጊዜውም 50 ምርጥ የእግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል በስፖርት ኢሊስትሬት ተመርጧል። የስፖርት ኢላስትሬት የቀድሞዉን ላይቤሪያዊ አጥቂ በ43ኛ ደረጃ ስፖርቱን በመጫወት ከታላላቅ ተርታ አስቀምጧል። ስፖርት ኢለስትሬትድ ለመጀመሪያ ጊዜ በነሀሴ 1954 የታተመ የአሜሪካ የስፖርት መፅሄት ነው።በስቱዋርት ሼፍቴል የተመሰረተ፣ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ስርጭት ያለው የመጀመሪያው መጽሄት ለጄኔራል ልቀት የብሔራዊ መጽሔት ሽልማትን ሁለት ጊዜ አሸንፏል። ከ1964 ጀምሮ በሚታተመው አመታዊ የዋና ልብስ እትም ይታወቃል እና ሌሎች ተጓዳኝ የሚዲያ ስራዎችን እና ምርቶችን አፍርቷል።

https://t.me/marakisport34
https://t.me/marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 06:31


💥ዋልያዎቹ ከኤርትራ ጋር የሚያደርጉትን የቻን ማጣሪያ አዲስ አበባ እንዲሆን ጠይቀዋል!

🔛 ኢንስትራክተር አብርሃም ወይም አሰልጣኝ ስዩም ቀጣይ አሰልጣኝ?
👇

የ2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል። የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አዘጋጅነት በአስራ ዘጠኝ ሀገራት መካከል የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል።

ለዚህ የ2024 የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮና ቻን የማጣርያ ጨዋታዎች የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት እንደሚደርጉ
ይሆናል::

በዚህ መሠረት የማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር አዲስ አበባ ላይ የመልሱ ጨዋታ ህዳር 1 አስመራ ላይ ይካሄዳል። በኢትዮጵያ በኩል የመጀመሪያው፡ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየም እንዲካሄድ ፌዴሬሽኑ ካፍን የጠየቁ ሲሆን መልስ እየጠበቁ ይገኛል።
የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 - 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል።

በሌላ በኩል የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ የሃላፊነት ዘመን ጥቅምት 22/2017 የሚጠናቀቅ በመሆኑ ተከትሎ ከኤርትራ ጋር ያለው የቻን የማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ የመጀመሪያው ግጥሚያ አሰልጣኙ ቡድኑን ይዘው ጨዋታውን ያደርጋሉ ተብሎ ቢጠበቅም ከጥቅምት 23 በኃላ ለብሔራዊ ቡድኑ ቀጣይ አሰልጣኝ ለመምረጥ ሂደት ላይ ናቸው:: አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ወይም ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እንደታሰቡ ተሰምቷል::

© Ethio Kick off

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 06:31


💥አንዳንድ እድሎች ደግሞ . . .

ትላንት ምሽት በጣሊያን ሴር ኤ ኤሲሚላን በሜዳው ዩድኔዜን ጋብዞ 1 ለ 0 አሸንፏል።
ታዲያ ጨዋታው ተጠናቆ 7 ደቂቃ ይጨመራል፣ በ97ኛው ደቂቃ የዩድኔዜው ቤልጀማዊ ተጨዋች Christian Kabasele ጎል አስቆጥሮ አቻ ማድረግ ችሎ ነበር ።
ነገር ግን ከታች በምስሉ በምታዩት መልኩ ከጨዋታ ውጭ (Off side) ተብሎ ተሽሮበታል።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

20 Oct, 04:14


💥ለሊት ላይ ኢንተር ማያሚ ከ ኒው ኢንግላንድ ሪቮሊውሽን ጋር በተደረገ የ MLS ጨዋታ እስከ 57ተኛው ደቂቃ 2 አቻ ነበሩ።

ከዚህ በኋላ ሜሲ ተቀይሮ ገብቶ ሶስት ጎል አስቆጥሮ ሀትሪክ ሰርቷል።
ጨዋታውም 6-2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ሁለቱን ሊዊስ ሱዋሬዝ አንዱን ደግሞ ዮርዲ አልባ አመቻችተውለታል።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

19 Oct, 19:43


የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ቡድናቸው የሚደረግበት ነገር የሚያሳፍር መሆኑን ከጨዋታው በኋላ ሲናገር ተደምጧል።

ዴክላን ራይስ ከጨዋታው በኋላ ለዳኞች ቡድኑ “ በየሳምንቱ እኛ ላይ ይህ ነገር ይፈጠራል በጣም ያሳፍራል “ ሲል መናገሩ ተገልጿል።

በዚህ አመት በሁለት ጨዋታዎች ተመሳሳይ ነገር ተፈጥሮ ከሽንፈት መትረፋቸውን ያስታወሰው ራይስ “ ስህተቶችን መስራት ማቆም አለብን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ሁሉም ተጨዋቾች ያስፈልጉናል “ ብሏል።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

19 Oct, 19:20


ሰር አሌክስ ፈርጉሰን የቀድሞ ክለባቸውን ለመደገፍ በሴልቲክ እና በአበርዲን መካከል በተደርገው ጫወታ ተገኝተው ነበር።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

19 Oct, 19:12


ሜሰን ግሪንዉድ ከፍቅረኛው ጋር ሁለተኛ ልጃቸውን እየጠበቁ እንደሆን በማህበራዊ ገፆች ላይ እየተዘዋወረ ነው።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 09:43


🚨 ፔፕ ጋርዲዮላ ውሉን ካላራዘመ ማንቸስተር ሲቲ በሚቀጥለው ክረምት ዣቢ አሎንሶን ሊሾም ይችላል። 😨🩵

[ምንጭ: TheAthleticFC]

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 09:12


ጃክ ዊልሸር አዲሱ የኖርዊች ሲቲ ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ከጫፍ ደርሷል። [ Fabrizio Romano ]

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 04:34


በ 2015 በዛሬው ቀን ነበር ክርስቲያኖ ሮናልዶ የማድሪድ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ሪከርድ የያዘው ! 👏👏

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 04:33


🇬🇭 ኮቢ ማይኖ

"አባቴ የቅርብ ጓደኛው ለጋና ብሄራዊ ቡድን ሲጫወት እንዴት ጉዳት እንደደረሰበት ነገረኝ እና እራሱን ለማሳከም ብዙ ሞክሮ ነበር መድሃኒቱን መግዛት አልቻለም ነበር በደረሰበት ጉዳት በጣም ተሰቃይቶ በመጨረሻም በሞት ተለየ

"በአፍሪካ ብዙ ችግር አለ ሁሌም ተጨዋቾች ይወቀሳሉ ከትውልድ አገራቸው ይልቅ ላደጉበት አገር ይጫወታሉ ይባላል እውነታው ግን እነሱን መውቀስ አይገባም በሙስና ምክንያት ያሉትን ተጨዋቾች በደንብ መንከባከብ አልተቻለም።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 04:33


"ኮች ምክርህን ሳትለግሰኝ እንዳትሄድ"፦ ሎዛ

ረቡዕ ምሽት ዋሽንግተን ዲሲ አውዲ ፊልድ ስታዲየም ተገኘን፤ ኢትዮጵያዊቷ ሎዛ አበራ የምትጫወትበት ዲሲ ፓወር ከዳላስ ትሪንቲ ክለብ ጋር ጨዋታ ነበረው፤ 30 ቁጥር ለባሿ ሎዛ በመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ገብታለች፤ 64 ደቂቃ ሜዳ ላይ ቆይታ ጥሩ ተንቀሳቅሳ አራት የግብ ሙከራ አድርጋ ተቀየረች፤ ጨዋታው ያለ ግብ 0-0 ተጠናቀቀ

ሎዛን ለማበረታታት ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን ስታዲየም ታድመን ነበር፤ አራቱ የቅርብ ወዳጆቿና ቤተሰቦቿ ናቸው፤ በተጨማሪ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ፣ ሎዛን አሜሪካ ያመጣት የፊፋ የጨዎታዎች ኤጀንቱ መዝሙረዳዊት መኩሪያ፣ የስፖርት ፎር ቼንጅ መስራቹ አሀዱ ገብሩ፣ የዲያስፖራ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛው ካሳሁን ይልማና እኔ አውዲ ፊልድ ተገኝተናል

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ ሎዛ ከክለቡ ጋር እየተላመደች እንደሆነ፥ በሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች የመጀመሪያ ተሰላፊ መሆን እንደቻለችና አሁንም ጠንክራ እንደምትሰራ አጫወተችን፤ የክለቡ አሰልጣኝ ፈረንሳዊው ፍሬድሪክ ብሪሊየንት በበኩሉ በሎዛ ብቃት ደስተኛ መሆኑን ጠቁሞ ይበልጥ ስኬታማ ሆና ጎልታ እንደምትወጣ እምነቱን ነገረን

ሎዛ በእለቱ ለመጡ ወገኖቿ ምስጋናዋን አቅርባለች፤ በተለይ ለሌላ ጉዳይ አሜሪካ ብቅ ብሎ ሎዛን ማበረታታት አለብኝ በማለት ስታዲየም ለተገኘው ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ አክብሮቷን ገልፃለታለች፤ ከመጨዋወት ባለፈም "ምክርህን ሳትለግሰኝ እንዳትሄድ" ብላ አጥብቃ ጠይቃው ነበር፤ አሰልጣኙም የእለቱን እንቅስቃሴዋን ገምግሞ ሙያዊ ምክር ሰጥቷታል፤ በቀጣይም ሊያግዛት ቃል ገብቶላታል፤ ሎዛ በክለቡና በቡድን ጓደኞቿ እምነት የሚጣልባት በደጋፊው ደግሞ ተወዳጅ እየሆነች መጥታለች

(ታምሩ ዓለሙ)

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 04:33


አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ የስፔኑ ጋዜጣ ማርካ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች የሚል ሽልማት ተብርክቶለታል።

ማርካ የምንግዜም ምርጥ ሲል ይፋ ባደረገው ዝርዝር ውስጥ
1⃣ ኛ: ሊዮኔል ሜሲ 🇦🇷
2⃣ኛ: ክርስቲያኖ ሮናልዶ 🇵🇹
3⃣ ኛ: ፔሌ 🇧🇷
4⃣ ኛ :ዲ ኢስቲፋኖ🇦🇷
5⃣ኛ: ማራዶና🇦🇷

ተቋሙ ወደ አሜሪካ በማቅናት ለሊዮኔል ሜሲ ያዘጋጀውን የምንግዜም ምርጥ እግርኳስ ተጨዋች ሽልማት አበርክቷል።

ሊዮኔል ሜሲ በሽልማቱ ላይ ምን አለ ?

" እግርኳስ የምወደው ነገር ነው ከሶስት አመቴ ጀምሮ ነበር እግርኳስን መጫወት የምወደው።

ከልጅነቴ ጀምሮ የነበሩኝን ህልሞች ሁሉ አሳክቻለሁ ፤ ሁሉም ማሸነፍ የሚመኘውን የአለም ዋንጫ አሸንፌያለሁ ከልጅነት ክለቤ ባርሴሎና ጋር ሁሉንም አሳክቻለሁ።

አርጀንቲና እና ባርሴሎና ቤቴ ናቸው አሁንም ደስታ እንዲሰማኝ በሚያደርገኝ ቦታ ነው ያለሁት።

በቀጣይ አለም ዋንጫ መሳተፌን ጊዜው ሲደርስ እናየዋለን ሁሉም የሚሆነው በምክንያት ነው።“ሲል ተደምጧል

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

18 Oct, 04:32


ቸልሲ የሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ መልማዮች ወደ ስታዲየሙ እንዳይገቡ ከልክሏል።ምክንያቱም ከህግ እና ስርዓት ውጭ ያሳደኳቸውን ታዳጊ ተጫዋቾቸን ነጥቀውኛል በሚል ነው።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 18:48


💥ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ በሊጉ 453 የጎል ዕድሎችን በመፍጠር ከየትኛው የሊጉ ተጨዋች ይበልጣል።
ከእሱ ቀጥሎ ያለውን ተጨዋች በ62 ይበልጠዋል ።

ነገር ግን በዚህ የውድድር ዘመን ያ የጎል ዕድል መፍጠር ችሎታው በዕጅጉ ወርዶ ይገኛል ከታች ተመለከቱት ።

[ Sky Sport ]

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 16:10


ይህ የ37 አመቱ ሉካ ሞድሪች በእግር ኳስ ህይወቱ እስካሁን በነበረባቸው ቶትነሃምና ሪ.ማድሪድ ላይ ያስመዘገበው የስኬት ቁጥራዊ መረጃ ነው።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 15:08


#ማስታወቂያ

የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከ 20 አመት በታች (U-20) የሆኑ ታዳጊ ተጫዋቾችን መልምሎ መያዝ ይፈለጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ታዳጊዎች መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ክለቡ ይገልፃል::

መስፈርቶቹ:-

1, ፆታ: ወንድ
2, እድሜ : ከ 20 አመት በታች
3, ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ MRI ምርመራ ውጤት ከ 20 አመት በታች መሆኑን የሚያረገግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
4, የ MRI ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የማይችል ከሆነ የልደት ካርድ ያለው
5, የ 8ኛ ክፍል ወይም የ 10ኛ ክፍል ማስረጃ ማምጣት የሚችል

የምዝገባ ቀን : ጥቅምት 07/2017 እስከ 09/2017
ከዚህ በታች በተቀመጠው ቁጥር የ ቴሌግራም አድራሻ (0927390207) ላይ አስፈላጊውን መረጃ በመላክ ወይም በአካል ወደ ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን::

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 14:20


የአርሰናሉ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤዱ ጋስፐር ፖርቱጋል ድረስ በመጓዝ ከቪክተር ጆከረሽ ወኪል ሀሰን ቼቲንካያ ጋር መነጋገራቸው ተዘግቧል! የአርሰናል እራዳር ውስጥ ያለ ተጫዋች ነው !

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 14:20


ማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋች ማኑዌል ኡጋርቴ ኡራጓይ ከኢኳዶር ጋር ባደረገችው ጨዋታ ላይ ጉዳት እንዳጋጠመው ( ESPN UK ) ዘግቧል !

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 12:32


የጨዋታ መንገዴ Direct football ነው ይላሉ። ግን አልሰራለዎትም። ለምን ይህ ነገር ከሸፈበዎት ሲባሉ በሜዳችን መጫወት ስላልቻልን ነው። ይህ እንዲቀረፍ ጫና አድርጉ ሲሉ ነበር የገለፁት።

ጉራሲን ለመቆጣጠር ለምን አልተቻለም? ማርክ አድርገነው ነበር። ግን ልምዱ ጠቅሞታል።

የአቅም ልዩነት ስላለ ነው የተሸነፍነው ላሉት ስልጠናውን ዘመናዊ ብናደርገው መቆጣጠር አንችልም ወይ ተብለው ነበር። አንመጣጠጠንም አሉ። ሱዳን እኮ ጋናን ረትታለች ስለሰራች ተባሉ ጋና አሁን ላይ ደካማ ቡድን ነው ሲሉ ነገሩን።

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 12:32


💥'እለቅልሃለሁ፤ እለቅላችኋለሁን' ምን አመጣው?
ከ10 ጨዋታ አንድ የወዳጅነት ጨዋታ ያሸነፈ አሰልጣኝ ጋዜጠኞች ላይ ጣት መቀሰር እጅጉን ያሳዝናል።

ዛሬ ጧት በነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋዜጣዊ መግለጫን አስመልክቶ አሰልጣኙ ወንበሩ ላይ ተሰይመው ጥያቄ ጠይቁ ተባልን።
እድል ሲሰጠን መጠየቅ ጀመርን። አንድ ባልደረባችን እስኪ የእርሰዎ ስሜት እንጋራ ብሎ ጠየቃቸው። በጣም ተሰምቶኛል። እንደ ኢትዮጵያዊ፣ እንደ አሰልጣኝ ብለው መለሱ። ሸጋ መልስ ነበር።
የብሄራዊ ቡድኑ ቁልቁለት ያመናል። ህመማችንን እርሳቸውም እንደሚስማሙበት ማመናቸውን ነገሩን። ከዚያ ብዙ ጥያቄዎች ይነሳሉ። የእርሳቸው መልስ ግን በጓሮ በኩል ነበር።

አንደኛው ጥያቄ የነበረው ቀጣይ የብሄራዊ ቡድን ቆይታዎን በተመለከተ ምን ሀሳብ አለዎት? ሲባሉ ' እለቅልሃለሁ፤ እለቅላችኋለሁ' መባሉ ግን እስከአሁን እየገረመኝ ነው። የሚያበሳጭ አልነበረም እኮ። ያለውን ሁኔታ በመግለፅ መጨረስ ይቻል ነበር።

ቪዲዮ ትንተና፣ የስነልቦና ባለሙያ፣ የአካል ብቃት አሰልጣኝ ለምን አልተቀጠረለዎትም ሲባሉ አንዴ አያስፈልግም፣ ትንሽ ቆየት ብሎ ደግሞ ያስፈልጋል የሚል ጉራማይሌ መልስ ነቀር። በተለይ የአካል ብቃት አሰልጣኝ በአንዴ የሚሰራ ስላልሆነ አያስፈልግም ነበር ያሉት።

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 12:31


ዳኒ ኦልሞ ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ አገግሞ ወደ ቡድን ልምምድ መመለሱን አረጋግጧል!

@marakisport34
@marakisport34

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 10:44


“ በእርግጠኝነት ከበፊቱ የተሻለ ፖግባ ጠብቁ “ ፖል ፖግብ

ተጥሎበት የነበረው እግድ የተነሳለት ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ አዲስ ተጨዋች ሆኖ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ገልጿል።

“ በእርግጠኝነት አዲስ ፖግባን ትመለከታላችሁ “ ያለው ፖል ፖግባ “ ከበፊት የበለጠውን ፖግባ ጠብቁ “ ሲል በአዲስ መንፈስ ወደ ሜዳ ለመመለስ መዘጋጀቱን ተናግሯል።

“ ለጁቬንቱስ በድጋሜ መጫወት እፈልጋለሁ ለመቆየት የተወሰነውን ክፍያ ለመተው ዝግጁ ነኝ ፤ ከቲያጎ ሞታ ጋር እነጋገራለሁ እንደገና ታላቅ ተጨዋች ለመሆን ቃል እገባለሁ።“ ፖል ፖግባ

@marakisport_highlight
@marakisport_highlight

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 10:43


ኮቢ ማይኖ ጉዳት እንዳጋጠመው እየተነገረ ነዉ ምናልባት ከሜዳ ለሳምንታት ይርቃል!

@marakisport_highlight
@marakisport_highlight

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

17 Oct, 10:43


ሽንፈቱን የአለም ፍፃሜ አታድርጉ ገኒን የገጠምነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይዘን ነው ብለዋል አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ

"ምን እንደሚያስጨንቃችሁ አላውቅም ውሌ የሚጠናቀቅበት ጊዜ ጥቅምት 23 ነው አትጨነቁ እለቅላቹሀለው''

" በ2 ጨዋታ 4ለ1 እና 3ለ0 ተሸነፍን እንጂ ለማጋነን ተብሎ 7ለ1 መባል የለበትም ልክ አይደለም"

"7ለ1 ተሸነፍን ተብሎ መጋነን የለበትም ክሬዲት ለማሳጣት እንዳይህንባችሁ እሰጋለሁ 8 ለ0 ተሸንፈንም እናውቃለን''

"ሽንፈቱን የዓለም ፍጻሜ አታድርጉት ጊኒን የገጠምነው ትልቅ ቡድን ይዘን አይደለም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ይዘን ነው " ( ዮሴፍ ከፈለኝ )

@marakisport_highlight
@marakisport_highlight

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

16 Oct, 19:58


ሞሮኮ የ2024 የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድርን ታሰተናግዳለች፡፡ ከጥቅምት 30 እስከ ህዳር 14 ድረስ በሚካሄደው የክለቦች ውድድርም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተካፋይ ነው፡፡ በ2024 የሴቶች የቻምፒየንስ ሊግ ውድድር አሸናፊ የሚሆነው ክለብ 400ሺ ዶላር ሽልማት የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ከሳምንታት በኋላ በሚጀመረው የቻምፒየንስ ሊግ ውድድርም 8 የአፍሪካ ክለቦች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡

@marakisport_highlight
@marakisport_highlight

ማራኪ ስፖርት ኢትዮጵያ

16 Oct, 19:58


💥የ2024 ምርጡ ተጨዋች ማነው??

አራት አራት ሁለት (4-4-2) 100 ምርጥ ተጨዋቾችን ይፋ አድርጓል፣ ለዛሬ ሀያዎቹን እንንገራችሁ።

20. አንቶኒ ሩዲገር - Real Madrid
19. ዲክላይን ራይስ - Arsenal
18. ኮል ፓልመር - Chelsea
17. ፊል ፎደን - Man city
16. አሊሰን ቤከር - Liverpool
15. ቨርጂል ቫንዳይክ - Liverpool
14. ፌድሪኮ ቫልቬርዴ - Real madrid
13. ቡካዮ ሳካ - Arsenal
12. ላሚን ያማል- Barcelona
11. አሌክሳንደር አርኖልድ - Liverpool
10. ኬቨን ዲብሩየን - Man city
9. ጀማል ሙሴይላ - Bayern Munichen
8. ዊሊያም ሳሊባ - Arsenal
7. ሞ ሳላህ - Liverpool
6. ሀሪ ኬን - Bayern Munichen
5. ሮድሪ - Man city
4. ክሊያን ምባፔ - Real Madrid
3. ጁድ ቤሊንግሀም - Real Madrid
2. ኧርሊንግ ሀላንድ - Man city
1. ቪኒ ጁኒየር - Real Madrid

@marakisport_highlight
@marakisport_highlight

2,953

subscribers

1,738

photos

18

videos