ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች @efremsyum Channel on Telegram

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

@efremsyum


እንኳን ወደ ኤፍሬም ስዩም እና የሌሎች ግጥም ባለቤቶች ተቀላቀሉን

እንዲለቀቅ ምትፈልጉት የማንኛውም ገጣሚ ግጥሞች ካሏችሁ እንዲሁም ለአስተያየት ያናግሩን 👉🏽 @mairmaid

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች (Amharic)

ኤፍሬም ስዩም የሚናገር ፕሮምካርሽን በእናንተዎች በመሰብሰብ ወደ የእኛ ጀማሪ ላይ ዘግተዋል። እናከላከል የአካባቢ ወሬ ሶስት ጊዜም የሚስፋፍን እንዴት እንደደገመን ይፈልጋል የሚባሉትን ግጥሞች በመቀላቀል እንቆጠቅጣለን። ይህ መሰብሰብ የታደሰ ወሬ በመንካት ከፍተኛ ነው።

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

18 Sep, 17:13


@eazope

Join for airdrop news

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

06 Jun, 19:18


https://t.me/catizenbot/gameapp?startapp=r_752_9058386

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

23 May, 09:51


https://t.me/Cryptouppeoplebot?start=6955566291

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

12 Mar, 12:00


አንዳንድ   ወዳጅማ

ወዳጅ መስሎ ቀርቦ ፣ ሀሳብን ጠይቆ
ማብዛት መሰናክል ፣ እንዳትጓዝ ርቆ
ለራስ ጥቅም ብሎ ፣ ሌላን ማሰናከል
እይታውን ጋርዶ ፣ እይታን መከለል

ልብን የምያየውን ፣ አምላክን ማይፈራ
አፈሙዝ አዙሮ ፣ የሚሸርብ ሴራ
ያስደሰተ መስሎ ፣ ምያበስር ምሥራች
ከላይ ሀውልት ሰርቶ ፣መቃብር ሥር ከታች

በልቡ ገንዞ ፣ ይመስላል አፍቃሪ
የሰው ልብ አስይዞ ፣ ህይወት ላይ ቆማሪ
ለጥቅሙ ይቀርባል ፣ አይቆይም ይሄዳል
እሱን ሸኘሁ ስትል ፣ ሌላኛው ይመጣል

በዝህም አያቆምም ፣ ህይወት ይቀጥላል
እኔ ያገኘኝ ፍቅር ፣ ከዚኛው ይለያል

ወዳጅ ሆኖ መቶ ፣ የሚሆነኝ ወዳጅ
በፍቅሩ ጠፍሮ ፣ ጠላትን አናዳጅ
ከቶ የማይለየው ፣ ኤኬለን ከኤኬሌ
ማስመሰል የሌለው ፣ የፍቅር ምሳሌ

ህይወትን የሰጠኝ ፣ ሞቴን ተቀብሎ
ፍጹም ያልቀረበኝ ፣ ለጥቅሙ ብሎ
ጠላትነት ልያስቀር ፣ ልያስታርቀን ከአብ
ሰማያዊ ዜጋ ፣ እኛን ልያደርግ ስያስብ

XY ከሚባል ፣ የባዮሎጂ ጣጣ
ቁርኝት ሳይፈጥር ፣ ወልድ ወደኛ መጣ

የማሪያም ልጅ እሱ ፣ መንፈስ የፀለለው
ስሙም ድንቅ መካር፣ቃላት የማይገልፀው
በእውነተኛ ፍቅር ፣ ልጆቹን የሚወድ
ነገስታትን ሿሚ ፣ በረት የሚወለድ

እውነተኛ ፍቅር ፣ እራስን ያሰጣል
ከሰው ፍቅር ይልቅ፣ የኢየሱስ ይበልጣል።

ፖm ባy ዳዊት ማዕረጉ ✍️🙏

@Henokashebir
@efremsyum

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

04 Nov, 09:16


ከእለታት አንድ ማታ!
(በእውቀቱ ስዩም)

ነግቶ፥ ተነሳሁኝ ካልጋየ
ከሰገባው  የሚመዘዝ  ፤ የንጉስ ሰይፍ መስየ
የሚያብረቀርቅ ፊቴን
የተትረፈረፈ ጉልበቴን
ያዝኩና  ከቤቴ ወጣሁ
ቡናየን በደስታ ጠጣሁ፤


የማለዳ  ቡናየ ጢስ
እንደ ንግስት እሌኒ ደመራ
ወደ ምኞቴ አቅጣጫ ፥ ልቦናየን ሲመራ
ሺህ እቅዶች ነድፌ
ለሺህ ትግል ተሰልፌ

እምነት ኖሮኝ ፤ ቁና ሙሉ  ሰናፍጭ ያክል
ከስጋጃ  ልቆጥረው፥ የመንገዴን መሰናክል
ለድል ተሰናድቼ
ደረቴን ለመዳልያ፥ ኪሴን ላዱኛ አጭቼ
ጅንን እንዳልኩ፥ እንደኮራሁ
ወደ ኑሮ ተሰማራሁ፥

ከዚያ ትንሽ ቆይቶ
የሰከነው ጎዳና፤ በትርምስ   ጨቅይቶ
እንቅፋት ከየቤቱ ፥ እንደ ጥራጊ ወጥቶ
አሳር እና አሳርኛ ፥ በየርምጃው ተሰጥቶ 
ሳፊው አየር ተበርዞ
የኑሮ ሰልፍ ረዝሞ፤
ወረፋው ተበውዞ
ደረስሁ ስል እየጀመርሁ
በርምጃየ ጣልቃ መሀል፥ የምቧይ ጡቤን እየከመርሁ
የምችለው ባይሳካ፥ የማልችለውን ሞከርሁ::

ከዚያ መሼ
የተረፈ ተስፋየን ፤ እየቀበርሁ  አፈር ምሼ
ድምጤን አጥፍቼ አነባሁ፤
እንደ ሰይፍ ተመዝዤ ፥ እንደ ቀንዳውጣ ገባሁ ::

Join us

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

16 Apr, 00:50


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሠሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳቹ አደረሰን።

መልካም በዓል 🙏
Happy Holiday ( Easter )

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

14 Jul, 05:44


አትፅናኝ-መዘክር ግርማ
@satsun273

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

11 Jul, 22:11


አንዲት እናት ለልጇ ከፊታችን ወዳሉት ሰዎች እየጠቆመች ስለ ደግነታቸው ትነግረዋለች.....
የትኛው ደግነታቸው እንደሆነ ለመረዳት ደጋግሜ ወደጠቆመቻቸው የኔቢጤ እና መፅዋች ተመልክቻለው ግን አንድም ደግነት የተባለ ነገር አልታየኝም....
ደግነት በማድረግ ብቻ ሳይሆን በማውራትም ይገለፃል ካልከኝ እሱንም የሚያወሩትን ልብ ብየዋለሁ ቢሆንም ምንም አላገኘሁም....
መጨረሻ ላይ ትክት ሲለኝ እናትየው ስለታያት ደግነታቸው ለልጇ ሰትነግረው ልስማብዬ ጆሮዬን አዘነበልኩ
...እንደተረዳሁት ከሆነ እናትን ደግ ናቸው ያስባሉአት የመፅዋቹ መመፅወትና የተመፅዋቹ ማመስገን ነው

ይሄ እውነት ደግነትን ያሳያል መፅዋቹን ብናይ እኮ ፈጣሪውን አስቦ......ከላይ የሚጠብቀውን እሳት አውቆ አሊያም ህሊናውን ፈርቶ ነው ቢሰጥ
ተመፅዋቹም ማመስገኑ ይሉኝታን ፈርቶ ወይም እንደዛኛው ህሊናው
ታዲያ ለደግነት ምክንያት ከሰጠነው እንዴት ደግነት እንለዋለን
ደግነት አንጣን ማያስብ እንካን ብቻ ሚያቅ መልካም ስራ ነው
እንደኔ ወይ ግብሩን ወይ ስሙን እንቀይረው ባይ ነኝ

በነገው የተሻለ ሀሳብ እስከምሽረው በል ተመሠጥበት

......................✍🏽ፊያሜታ

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

11 Jul, 18:45


ትናፍቂኛለሽ.....አሌክስ አብርሀም

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

10 Jul, 15:24


በቃ ተመርጦል ሁለቱም ሰኞ ጀምሮ ይለቀቃሉ።



@satsun273
@satsun273
@satsun273

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

08 Jul, 11:58


https://t.me/SecretNft_bot?start=668613800

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

05 Jul, 13:34


ምርጫው እስከ አርብ ነው ወዳጆቻቸውን join እንዲያደርጉ እና እንዲመርጡ አድርጓቸው።


@satsun273
@satsun273
@satsun273
@efremsyum

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

05 Jul, 06:53


ለግጥም ቀረ መሰለኝ እሽ ለግጥም ምትሉ ይሄው

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

05 Jul, 06:32


ሰወች አሁን ጊዜው ደርሷል ትረካዎችን ምንጀምርበት መጀመሪያ ምርጫችሁን በምልክቶች አሳዩን።

👍-ማዕበል ብርሃኑ ዘሪሁን
😘-ኩሪብት አለማየሁ ገላጋይ
😄-ሮሚዬ እና ጁሌት ከበደ ሚካኤል
😊-ጨረቃ ስትወጣ ብርሀኑ ዘሪሁን
💎-የጡት አባት ወጋየሁ ተበጀ
🤷‍♂-ኤክሶድያ ሰለሞን አበበ
🙌-ግጥሞች

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

01 Jul, 20:45


በቃል ሲነገራት የፍቅር አጥናፉ፥
ደሞ እንደሚያስደስት በጋራ ሲከንፉ፤
አታምንም ልጅቱ...
ስለምትሰማ ነው ውሸት በየቤቱ፤
...
...
ማፍቀር መታደል ነው
መፈቀርም መክበር፤
የበደነ ገላ ሊሞት እንዲሳፈር፤
የቀናለት መስመር
ብለናትም ነበር .......
ግና የት አባቱን የፍቅር መጃጃል፤
በጠርጣሪ ልብ ውስጥ ፍርሃት ይዋጃል።
..
..
አጥብቃ ጠይቃ እምነትን ካልፃፈች፤
በፍርሀቷ ግርዶሽ ፍቅር ለምኔ ካለች፤
ያው መንገድ ጠቁሟት....
የጥላቻን ድልድይ
ደም የተፃፈበት የሚታይ እንደ እኩይ፤
ግሳት ብቻ ያለበት ጥጋብ ብቻ ቤቱ፤
በቀይ የተደራ የደም ልብስ ሌማቱ፤
የከበበውን ደጅ.....
እንኳንስ ለሰው ልጅ ለእንስሳም እማይበጅ፤
መሆኑን ስታየው .....
ፍቅር ወዴት አለህ ምትል ይመስለኛል፤
እሱ ካልቀረበ ሰላም የት ይገኛል።

#ሚኪ

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

18 Jun, 12:08


አዲስ group ነው እባካችሁ join አረጉ ይጠቅማችኋል።👇👇👇👇

https://t.me/aolmikiteam

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

18 Jun, 06:59


እስኪ አስተያየት ለግስኝ🙏🙏

ኤፍሬም ስዩም እና ሌሎች

17 Jun, 21:44


....⚣︎⚣︎.....

ድካም እየተሰማኝ
መንፈሴን ብርታት ሲነሳው፤
በጨለማ ዳዴ እያለ
ፀሃይ እንደሚናፍቅ ሰው፤
የጎኔ ጥንካሬ አቅም
በውድቀት እየደቀቀ፤
የማይሰንፈው ልቤ ግን ተስፋ የሚል ቃል ሰነቀ፤
..
እውንነት ምን ቢነሳው
የድካሜን ልፋት ውጤት፤
መጠበቅ ነው ጊዜ ከፍሎ
ሽንፈት እስኪሄድበት፤
..
አምናለሁ ፍቅሬ ሆይ
የስኬቴ ደጀን ለልቤ እንድትሆኝ፤
የመንፈሴን ድካም መጠሽ እንድትሸኝ፤
ለማታዬም ፀሃይ እንድትበሪ ውስጤ፤
ብርታት እንድትሆኝ ለተስፋ መቁረጤ፤
የተፃፍሽ እንደሆን.....
ምከንያቱም
ሁሉን የምረሳው በአንቺ ሀሳብ ስሆን።

©ሚኪ
@mikiendialem