ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት @wuludeyared Channel on Telegram

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

@wuludeyared


“ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም” ቅዱስ ያሬድ

ይኽ በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን የውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያስተላልፋል፡፡
መልእክት ወይም አስተያየትና ጥቆማ ካሎት
⬇️⬇️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት (Amharic)

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት የህዝብ ስራዎችን አስመልክቶ ለቅዱስ ያሬድ ጽዮን ከእርስዎ የተወዳበንን መንግስት በቀላሉ ያቀረቡት እስካሁን ይገልጻል፡፡ በዚህ ቤት ተደምሳለሁ እና ኢትዮጵያውያንን ሲያገኙ ዘገባዎችንና ጥጃዎችን ለውሉደ ያሬድ ትምህርት ቤት ለጊዜው ደርሷል፡፡ ያሬድ ቤተክርስቲያን ጽዮንንና ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም በእርሳቸው ምክንያቶች ያሉትን ጽሑፎችን ለማግኘት ያግኙ፡፡ በእውነታው ላይ በመስራት እና አስተያያታቸውን የሚያደርግ ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት በኮምፒውተር የቴሌግራም እናት እየተገመቹ በዕውቀቶች ለመልእክት ይታየዋል፡፡ በጣጣነት እንዲሁም መሪጋቸውን ለመረጃ የሚሰጥ እና በኢንተርኔት የሚታየውን መልእክታችንን ለተግፈው የፈተና እንድንሆን እንጠንቀቅቅ፡፡

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

11 Jan, 02:34


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #በቤተ _ልሔምና_አውራጃው ላሉ ንጉሥ ኄሮድስ በግፍ ለገደላቸው #ለዐሥራ_አራት_እልፍ_አራት_ሺህ_ለንጹሐን_ሕፃናት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓልና  ከዘጠኙ ቅዱሳን ቀድመው ወደ አገራች ኢትዮጵያ ለመጡ #ደብረ_ሊባኖስ_ገዳም_በስማቸው ለተሰየመላቸው ከዐለት ጠበል እያፈለቁ ድውያንን ለሚፈውሱት ለተአምረኛው ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ሊባኖስ (መጣዕ) ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ የሴቶችን ጠጉር ሹሩባ ሲሠሩ ከኖሩ# ከአባ አሞን፣ ከታላቁ ነቢይ #ከቅዱስ_ኢሳይያስና_ከቅዱስ_ስምዖን ግብፃዊ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።


🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

10 Jan, 17:29


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ጥር 2''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

10 Jan, 13:37


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

10 Jan, 05:16


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጽያዊ_ጻድቅ በዓለም ላይ በንግሥና መኖርን ንቀው ለመነኑትና ብዙ ተአምራትን በማድረግ ለሚታወቁት #ለንጉሥ_ዐፄ_ይኩኖ_አምላክ ልጅ ለሆኑት #ለአቡነ_ገብረ_ክርስቶስ_ዘዳግና ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለሊቀ ሰማዕታት #ለቅዱስ_ጊዮርጊስ_ለልደት በዓል በሰላም አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Jan, 02:32


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለሊቀ_ዲያቆናት_ለቀዳሜ_ሰማዕት #ለቅዱስ_እስጢፋኖስ_ለልደቱና_ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ከሶርያ_አገር_ለሆነ በከሀዲው መክስምኖስ ዘመነ መንግስት ሰማዕትነት ለተበቀበለ #ለቅዱስ_ለውንድዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስክድርያ ስልሳ ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ከአባ_መቃርስ ዕረፍት፣ #ከከበሩ_ከአክሚም_ሰማዕታት የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ከፈጸሙ ስማቸው #ቅዱሳን_ዲዮስቆሮስና_ሰከላብዮስ ዕረፍት፣ በዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ቊጥራቸው #ከካህናት_ስምትት_መቶ፣ #ከዲያቆናት_መቶ_ሠላሳ_ከመምህራን_ኃምሳ፣ #ከሦስት_ከቤተ_ክርስቲያን_ሹማምንት_ከሰማንያ_መሳፍንት_ከሠላሳ_ሁለት_ንፍቅ_ዲያቆናትና_ከመቶ_ኃምሳ_ሕዝባውያን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።


🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Jan, 14:21


🕯🕯

የጌታችን ልደት በአበው

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “የቅድስና ኹሉ ሰጭ ወደዚህ ዓለም የገባው በንጹሑ ልደት በኩል ነው። የቀደመው አዳም ከድንግል መሬት ተገኘ፤ ከእርሱም ያለ ሴት ዕርዳታ ሴት ተገኘች። ልክ አዳም ያለ ሴት ሴትን እንዳስገኘ፤ ድንግልም ያለ ወንድ በዚህ ዕለት ወንድን አስገኘች። ስለዚህ ሴቶች ለወንዶች ዕዳቸውን ከፈሉ፤ አዳም ብቻውን ሔዋንን እንዳስገኘ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። አዳም ያለ ሴት ሴትን ስላስገኘ ሊኩራራ አይገባም፤ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። በምሥጢሩ ተመሳሳይነት የተፈጥሮው ተመሳሳይነት ተረጋገጠ። ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወሰደ ነገር ግን አዳም ጉድለት አልተገኘበትም÷ በተመሳሳይ ከድንግል ወንድ ልጅ ተወለደ ድንግልናዋ ግን አልተለወጠም” እያለ በሚያስደንቅ መንገድ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልናን በአዳም ኅቱመ ጎን በኩል ያሳየናል”። ይህ የልደት ቀን የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከማሳየቱም አልፎ ሴቶችን እንዴት እንደካሰቻቸው ፍንትው አድርጎ ያመለክተናል። የጌታችን የልደት ዕለት ማለት የሴቶች ክብር የተገለጠበትና ወንድና ሴት እኩል መኾናቸው የተረጋገጠበት ዕለት ነው። “ሴቶች ሆይ የሴትነትን ክብር ያስመለሰችላችሁን ቅድስት ድንግል ማርያምን ትረሷት ይኾንን?”። ድንግል በድንግልና ወለደች ሲባል ሰምተን እንዳንደናገጥና ወደ ጥርጣሬ ባሕር ውስጥ እንዳንገባ አስቀድሞ አዳም ብቻውን ሔዋንን ሲያስገኝ ያለውን ነገር በመጽሐፍ አጻፈልን። አዳም ሔዋንን ብቻውን ከጎኑ እንዳስገኘ አምኖ የተቀበለ ሰው እንዴት ድንግል ማርያም በድንግልና ወለደች ሲባል ለማመን ይከብደው ይኾን? በጣም የሚያስገርመው ሔዋን ከአዳም ጎን ብትወጣም ለአዳም ውድቀትም ምክንያት ኾና ነበር፤ ድንግል የወለደችው ግን ዓለምን በሙሉ የሚያድን አምላክ ነው።

🕯🕯
በዓለምም ከዓለም ውጭ ያለው ጌታ በቤተልሔም የታየበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ሲባል አጥርተው ማየት በማይችሉ ዘንድ ውስን ብቻ የሚመስል÷ ነገር ግን በቅድስና መስታወት ለሚያዩት በአርያምም እየተመሰገነ በቤተልሔም የተወለደበት ዕለት ነው። ሰይጣን የደነገጠበትና ኃይሉ የደከመበት ዕለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በልደቱ ስፍራ መኾን አጋንንትን እንዳይቀርቡን ያደርጋል እልፍ አእላፋት መላእክት በዚያ ከበው ይጠብቁናልና። ተፈጥሮአዊውን ሕግ የገለበጠው ጌታ የተፈጥሮን ሕግ የሠራውና እንደፈቃዱም የሚያደርገው እርሱ መኾኑን ያወቅንበት ዕለት ነው። እንኳን በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!

📚ትምህርተ ጽድቅ
📝ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

🕯🕯

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Jan, 02:32


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_አባት ለተመሰገኑ አባት አርባ ዓመት ሙሉ የሴቶች ፊት ሳያይ ለኖረ #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ በአባ መቃርስ ገዳም በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ለሆነ ለከበረ አባት #ለአቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል፣ ከመኰንኑ ከአርያኖስ የጭፍሮቹ ታላላቆች #ለቅዱሳን_ለኮርዮንና_ፊልሞና ከእናርሳቸው ጋር ካሉ #ከአርባ_ወታደሮች ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ተጋድይ ለሆነ #ለአባ_ዘካርያስ ዕረፍትና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ሄሮድስ ከገደላቸው #ከከበሩና_ከነጹ_ሕፃናት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።


🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Jan, 13:41


🕯🕯🕯🕯🕯

የጌታችን ልደት በአበው

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “የቅድስና ኹሉ ሰጭ ወደዚህ ዓለም የገባው በንጹሑ ልደት በኩል ነው። የቀደመው አዳም ከድንግል መሬት ተገኘ፤ ከእርሱም ያለ ሴት ዕርዳታ ሴት ተገኘች። ልክ አዳም ያለ ሴት ሴትን እንዳስገኘ፤ ድንግልም ያለ ወንድ በዚህ ዕለት ወንድን አስገኘች። ስለዚህ ሴቶች ለወንዶች ዕዳቸውን ከፈሉ፤ አዳም ብቻውን ሔዋንን እንዳስገኘ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። አዳም ያለ ሴት ሴትን ስላስገኘ ሊኩራራ አይገባም፤ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። በምሥጢሩ ተመሳሳይነት የተፈጥሮው ተመሳሳይነት ተረጋገጠ። ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወሰደ ነገር ግን አዳም ጉድለት አልተገኘበትም÷ በተመሳሳይ ከድንግል ወንድ ልጅ ተወለደ ድንግልናዋ ግን አልተለወጠም” እያለ በሚያስደንቅ መንገድ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልናን በአዳም ኅቱመ ጎን በኩል ያሳየናል”።

ይህ የልደት ቀን የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከማሳየቱም አልፎ ሴቶችን እንዴት እንደካሰቻቸው ፍንትው አድርጎ ያመለክተናል። የጌታችን የልደት ዕለት ማለት የሴቶች ክብር የተገለጠበትና ወንድና ሴት እኩል መኾናቸው የተረጋገጠበት ዕለት ነው። “ሴቶች ሆይ የሴትነትን ክብር ያስመለሰችላችሁን ቅድስት ድንግል ማርያምን ትረሷት ይኾንን?”። ድንግል በድንግልና ወለደች ሲባል ሰምተን እንዳንደናገጥና ወደ ጥርጣሬ ባሕር ውስጥ እንዳንገባ አስቀድሞ አዳም ብቻውን ሔዋንን ሲያስገኝ ያለውን ነገር በመጽሐፍ አጻፈልን። አዳም ሔዋንን ብቻውን ከጎኑ እንዳስገኘ አምኖ የተቀበለ ሰው እንዴት ድንግል ማርያም በድንግልና ወለደች ሲባል ለማመን ይከብደው ይኾን? በጣም የሚያስገርመው ሔዋን ከአዳም ጎን ብትወጣም ለአዳም ውድቀትም ምክንያት ኾና ነበር፤ ድንግል የወለደችው ግን ዓለምን በሙሉ የሚያድን አምላክ ነው።

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Jan, 13:41


እንግዲህ በዚህ ዕለት የዓለም መድኃኒት ከድንግል ማኅፀን በቀለ!! ዓለም በሙሉ የተጠማውን የሕይወት ውኃ ለመጠጣት የተዘጋጀበት ዕለት ነው። ይህን ዕለት በመንፈሳዊ ደስታ ደስ ተሰኝተን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልናከብር ይገባናል እንጂ፤ በዘፈንና በስካር በቆሸሸ ሀሳብ በዓሉን አናበላሸው ። የልደቴ ቀን እያልን በቤታችን ኬኩን እና ሌላውን ሁሉ የምንበላ ኹሉ እውነተኛውን የልደት ቀን ማወቅ ከፈለጋችሁ ይህ ነው የልደታችሁ ዕለት/ቀን። በዚህ ቀን ጌታችን ስለሁላችን ድኅነት ብሎ ስለተወለደ የእርሱ የልደት ዕለት የእኛም የልደት ዕለት ነው። አዲስ አድሮጎ ሊወልደን በአምሳላችን ፈጣሪያችን የተወለደበት ዕለት የልደት ዕለታችን ኾኖ ካልተከበረ የቱ ቀን ሊከበር ነው። ዛሬ እውነተኛ ብርሃን ጨለማችንን ያርቅልን ዘንድ የወጣበት ዕለት ነው።

ዮሐንስ ዘክሮንስታድ “እኛን ከምድር አፈር የፈጠረንና የሕይወትን እስትንፍስ እፍ ያለብን ወደ ዓለም መጣ፤ በአንዲት ቃል ብቻ የሚታዩትንና የማይታዩትን ፍጥረታት ካለመኖር ወደመኖር ያመጣቸው እርሱ መጣ። ... የእርሱ መምጣት እንዴት ያለ ትሕትና ነው!! ምድራዊ ሀብት ከሌላት ድንግል በአንዲት ጎጆ ተወለደ፤ በድህነት ጨርቅ ተጠቅልሎም በበረት ተኛ።” እያለ የክርስቶስን በትሕትና መምጣት ያስረዳናል።

ይህቺ ዕለት ትሕትና በምድር ላይ የታየችበት የትሕትና ዕለት ናት። አዳም በትዕቢቱ ከቀደመ ክብሩ ቢዋረድም ክርስቶስ በትሕትና ከቀደመው ወደተሻለ ቦታ ከፍ አድርጎ አወጣው። በእርግጥ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾኖ የተገለጠበት አንዱ ምክንያት ለአርአያነት ስለኾነ÷ በትሕትና መታየቱ የሰው ልጅ ወደ መዳን ለመግባት የትሕትናንን ትምህርት ከራሱ ከባለቤቱ መማር ስላለበት ነው። በጌታችን የልደት ዕለት በትዕቢት የሚመላለሱ ልቦናዎች የጌታችንን የልደት ዕለት የረሱ ልቦናዎች ናቸው። እጅግ ዝቅ ማለት እጅግ ከፍ ያደርጋል፤ አምላክ ሰው ኾነ የሚለውን መስማት በምንም ቋንቋ ሊገለጥ የማይቻል እጅግ ጥልቅ የኾነ የትሕትና ውቅያኖስ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው የማይቆጠሩ ብዙ ጸጋዎችን ልናገኝ የቻልነው። እንግዲህ በዚህች ዕለት የትሕትናንን ትምህርት ቁጭ ብሎ መማርና የትሕትና መምህራችንን ማመስገን ያስፈልገናል። በዚህች ዕለት በተድላ ሥጋ ኾነው ስለ ትሕትና መምህር ስለክርስቶስ የመወለድ ምሥጢር ሳይማሩና በምሳሌ ሳይኾን በተግባር ወደ ጌታችን የልደት ዕለት ወደምትወስደን ቅድስት ቤተልሔም ለማድነቅና በምስጋና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ለመደመር አለመሄድ እንዴት ያለ አለመታደል ነው!
ቃል ሥጋ የኾነው እኛን ከምድራዊ አኗኗር ወደ ሰማያዊ አኗኗር ለማሸጋገር ነው፡፡ ኀጥአንን ጻድቃን ለማድረግ፣ ከመበስበስ አንሥቶ ወዳለመበስበስ ሊያስነሣን፣ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ከመኾን የእግዚአብሔር ልጅ ወደመኾን ሊያሻግረን፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት፣ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ከእርሱ ጋር የንጉሥ ልጆች አድርጎ ሊያከብረን መጣ፡፡ አቤት ገደብ የለሽ የእግዚአብሔር ርኅራኄ! አቤት የማይገለጽ የእግዚአብሔር ጥበብ! አቤት ታላቅ መደነቅ! የሰውን አእምሮ ብቻ የሚያስደንቅ ሳይኾን የቅዱሳን መላእክትን ጭምር ነው እንጂ!። የዛሬውን ዕለት ማክበር ማለት እነዚህን ኹሉ ጸጋዎች ለማግኘት መብቃት ማለት።

በዛሬው ዕለት ውስጥ ወደ መደነቅ ከፍ ያላለ ፍጥረት ማግኘት ፈጽሞ የማይቻል ነው። የእግዚአብሔር ጥበብ የጠላታችንን ጥበብ ያፈራረሰበት ዕለት ነው። የጌታችንን የልደት ዕለት በማያቋርጥ ምስጋና ልናክብር የሚገባን ከላይ የተዘረዘሩትን ልዩ ስጦታዎች ለመቀበል ነው። አንድ ሕፃን ልጅ በልደቱ ዕለት ስጦታ ቢሰጠው ገና እንደተወለደ ስጦታውን ስጦታ መኾኑን ተረድቶ ሊቀበል አይችልም፡፡ ዛሬ የምናከብረው የልደት ዕለት ግን ሕፃኑ ራሱ ልደቱን ለማክበር ለመጡት በቃላት የማይገለጽ ስጦታ የሰጠበት ዕለት ነው።

ቅዱስ አምብሮስ ደግሞ “ማርያም ከተፈጥሮ ሕግ በተቃራኒው በኾነ መንገድ ልጅ ወለደች የሚለው ለምንድን ነው አልታመን ያለው? ከተፈጥር ሕግ ውጭ ባሕር ዐየች ሸሸችም ዮርዳኖስም ወደ ኋላዋ ተመለሰች ተብሎ አይደለምን? መዝ 113÷3፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ከዓለት ውኃ ፈልቋል ዘጸ 17፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ውኃው እንደ ግድግዳ ቆሟል ዘጸ 14÷6፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ብረቱ በውኃ ላይ ተንሳፍፏል፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ሰው በባሕር ላይ ተራምዷል” እያለ ይህ ታላቅ ሊቅ የእመቤታችንን ድንግልና ላለመቀበል ምንም ዓይነት ምክንያት መፍጠር እንደማንችል ይገልጥልና።

ስለዚህ በጌታችን የልደት ዕለት ከሰው ልጆች ልቦና የጥርጣሬ ድንጋይ ተነቅሎ ይወድቃል የተፈጥሮን ሕግ የሚቃረነው የድንግል በድንግልና መውለድ ይመሰከራል!! ዛሬ ሊብራሩ የማይችሉ ልዩ ኹነቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡ አምላክ የሰውን ሥጋና ነፍስ ተዋሕዶ ሰው ኾኖ የተገለጸበት፤ ድንግልም የማይወሰነውን አምላክ በማኅፀኗ ከመወሰንም አልፋ በታተመ ድንግልና የወለደችበት ዕለት ነው።

ድንግል ወለደች ተብሎ ከተፈጥሮ ሕግና ሥርዓት ውጭ በኾነ መንገድ የሚገለጽበት ልዩ ዕለት!  የተፈጥሮ ባለቤትን በንጽሕት ሙሽራ በደንግል ማርያም ማኅፀን የራሱን ቤት በተዋሕዶ ሠርቶ የወጣበት ዕለት። ዛሬ ሰማይ ወለደች እንላለን፤ ግን ይህቺ ሰማይ ግሳንግሱ ፀሐይ የሚታይባት ሰማይ ሳትኾን የማይታየው ፀሐይ የሚታይባት ሰማይ ናት።

በዓለምም ከዓለም ውጭ ያለው ጌታ በቤተልሔም የታየበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ሲባል አጥርተው ማየት በማይችሉ ዘንድ ውስን ብቻ የሚመስል÷ ነገር ግን በቅድስና መስታወት ለሚያዩት በአርያምም እየተመሰገነ በቤተልሔም የተወለደበት ዕለት ነው። ሰይጣን የደነገጠበትና ኃይሉ የደከመበት ዕለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በልደቱ ስፍራ መኾን አጋንንትን እንዳይቀርቡን ያደርጋል እልፍ አእላፋት መላእክት በዚያ ከበው ይጠብቁናልና። ተፈጥሮአዊውን ሕግ የገለበጠው ጌታ የተፈጥሮን ሕግ የሠራውና እንደፈቃዱም የሚያደርገው እርሱ መኾኑን ያወቅንበት ዕለት ነው። እንኳን በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!

📚ትምህርተ ጽድቅ
ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Jan, 06:28


እንኳን ለክብር ባለቤት ለአምላካችን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ  ከእመቤታች ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች ️️️️ለብርሃነ ልደቱ በዓል እግዚአብሔር

አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።


ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Jan, 02:34


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን #ለክብር_ባለቤት_ለአምላካችን_ለጌታችን_ለመድኃኒታችን_ለኢየሱስ_ክርስቶስ ከእናቱ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም_በሥጋ_ለተወለደበት የበዓላት ሁሉ ራስ ለሆነች #ለብርሃነ_ልደቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

በተጨማሪ በእነዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእንዴናው_አገር_ሰዎች ከሆኑ በሰማዕትነት ካዐረፉ #ከመቶ_ሃምሳ_ወንዶችና_ከሃያ_አራት_ሴቶች፣ #ከአባቶቻች_ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ፣ #ከኤፍሬም_ወገን ከመስፋኑ #ከቅዱስ_ኢያሱ_ልደት፣ ከከበሩ #ከያዕቆብ_ከፈሊስ ከሌላው ሰማዕት፣ #ከቴዎድሮስ ከመታሰቢያቸው፣ #ከሮሀ_ንጉሥ_ከአቃርዮስ ዕረፍት፣ ሰምኑድ ከሚባል አገር ከሆነ ከገመላዊው #ከቅዱስ_ቆሪል ዕረፍትና #ከአክሚም_ሰማዕታት_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።


🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Jan, 03:28


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን #ለኤጲስ_ቆጶስ_ለአባ_አብሳዴ ለዕረፍት በዓልና #ለቸሩ_መድኃኔዓለም_ለስቅለቱ_መታሰቢያ ወራዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_ፊልጶስና ከሰማዕታት ፍጻሜ ከሆነ #ከኖላዊ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                          

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Jan, 09:24


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  ታህሣሥ 25/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ

1,መጽሐፍ ቅዱስ በምዕራፍ የተከፈለው በስንተኛ ዓመት ነው
         ሀ, በ11ኛ መቶ ዓመት      (ለ,) በ13ኛ መቶ ዓመት      ሐ,በ14ኛ መቶ ዓመት
ለ, በ13ኛ መቶ ዓመት

2, መጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፎች ደግሞ በቁጥር የተከፈሉት
        (ሀ,) በ1543 ዓም       ለ, በ1314 ዓም     ሐ, በ1243 ዓም    መ, በ30 ዓፍ
ሀ, በ1543 ዓም

3, ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ አስተምሮ ያጠመቀው ሐዋርያ ማን ይባላል
       ሀ, ቅ.ሉቃስ         ለ, ቅ. ዮሐንስ         ሐ, ቅ.ቶማስ     (መ,) ቅ.ፊሊጶስ
መ, ቅ.ፊሊጶስ

4, ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በስንት ዓ.ም. ተምሮ ተጠመቀ
             ሀ, በ30 ዓም         ለ, በ64 ዓም       (ሐ,) በ34 ዓም          መ, በ1543 ዓም
 ሐ, በ34 ዓም

5, በነገድ የመላእክት አለቃ ማነው
             ሀ, ሱራፊ              ለ, ኪሩብ               (ሐ,) አናንኤል           መ, ሱርያል

ሐ, አናንኤል  

👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Jan, 04:58


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን #ከሮሜ_አገር_ለሆነች_ለከበረች_ለቅድስት_አንስጣስያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረች ከሰማዕት #ከቅድስት_ዮልያና ከመታሰቢያዋና #ከጻድቁ_ከቅዱስ_አቦሊ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Jan, 17:32


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ታህሣሥ 25''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Jan, 08:27


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Jan, 02:34


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከግብጽ_ደቡብ_ፃ ከሚባል አውራጃ መንጹ ስብራ ከምትበል ከተማ ለሆነ ለከበረ አባት #ለአባ_ዮሐንስ_ከማ ለዕረፍት በዓል፣ በሜዶናውያንና በሞዓባውያን ዘመን መንግሥት ለከበሩ #ለአምስቱ_መቃባውያን_ሰማዕትነት_ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ አባ ዮሐንስን ካመነኰሰው #ከአባ_ዳሩዲ ከመታሰቢያው፣ ከከበሩ #ከመኰንኑ_ከኒቆላዎስና_ከታማኝ_ሚስቱና ተገዳይ ከሆነ #ከታናሽ_መነኰስ_አባ_ከዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትን በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Jan, 08:57


🌿🌿🌿🌿


ዘወትር ምጽዋትን እንድታፈቅሯት የምለምናችሁደ ለምን ይመስላችኋል?

ለተቸገሩ ሰዎች መስጠት ማለት ስጦታችንን በሌላ በማንም ሳይኾን በራሱ በእግዚአብሔር እጅ ማስቀመጥ ነው፡፡ እንዲህም ስለ ኾነ የሰጠነው እንደሚመለስልን ብቻ ሳይኾን መቶ ዕጥፍ ኾኖ እንደሚሰጠን የታወቀ የተረዳ ነው፡፡ ላሳየነው ጥቂት ቸርነት የሚደረግልን ቸርነትም ታላቅ ነው፡፡

እግዚአብሔር የሰጠነውን አብዝቶ የሚመልስልንስ ለምንድን ነው? የምንሰጠው ስጦታ ጥንቱንም የሰጠን እርሱ እንደ ኾነ እየመሰከርን ስለ ኾነ ነው፡፡ በመኾኑም ወደንና ፈቅደን ይህን በተግባር ስንመሰክር፥ በተቀበለን እጁ የሰጠነውን ብቻ ሳይኾን ከሰጠነውም ጋር አብሮ መንግሥተ ሰማያትን ይሰጠናል፤ አክሊል ሽልማትን ያቀዳጀናል፤ ስፍር ቊጥር የሌለው በጎ በጎ በረከትም ያድለናል፡፡

እስኪ ንገሩኝ! እግዚአብሔር እየጠየቀን ያለው ከባድ ነገር ነውን? በፍጹም! እየጠየቀን ያለው በቤታችን ውስጥ ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር ለሌሎች እንድንሰጠው ነው፡፡ ይህን እንድናደርግ የሚሻውም የክብር አክሊል እንዲያቀዳጀን ምክንያት ሲፈልግብን እንጂ ለእነዚህ ችግረኞች የሚያስፈልጋቸውን ነገር መስጠት ተስኖት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ይህን እንድናደርግ የሚፈልገው ቃል የገባልንን ርስቱንና መንግሥቱን እንዲያወርሰን እጅግ ስለሚቸኩል ነው፡፡

🌿🌿
ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! እማልዳችኋለሁ እማፀናችሁማለሁ! እግዚአብሔር ጥቂት ምክንያት አግኝቶብን ሊሰጠን የሚወደውን እንዳናጣ በቤታችን ያስቀመጥነውንና የማንጠቀምበትን ነገር [ልብስ፣ ጫማ፣ ወዘተ] አውጥተን ለተቸገሩት ሰዎች እንስጣቸው፡፡ እግዚአብሔርም ያደረግናትን ጥቂቷን ምጽዋት በወዲያኛው ዓለም ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አምላክ አይደለም፡፡ በዚህም ዓለም በመስጠታችን ምክንያት የሚያገኘንን ነገር መፍራት አይገባንም፡፡ ቃለ እግዚአብሔር፡- “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ካለ በኋላ፥ ጨምሮም፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይላልና (መዝ.111፥9)፡፡

ኦ ምጽዋት! እንደ ምን ትደንቅ? እንደ ምንስ ትረቅ? ሰው ባልንጀራውን አፍቅሮ ለጥቂት ጊዜ ጥቂት ነገርን ይሰጣል፡፡ ይህን በማድረጉ ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያገኘው ፍቅር ግን ለዘለዓም ዓለም ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡

ተወዳጆች ሆይ! ዘወትር ምጽዋትን እንድታፈቅሯት የምለምናችሁ ለዚህ ነው፡፡ ኹልጊዜ ምጽዋትን እንድትወዷት የምማፀናችሁ ለተቸገሩ ሰዎች ጥቂት ቸርነትን አድርገን ከእግዚአብሔር ዘንድ መጠን ወሰን የሌለውን ቸርነት እንድንቀበል ነው፡፡ ደጋግሜ ለተቸገሩ ሰዎች ፍቅርን እናሳይ የምላችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደር የሌለውን ፍቅር እንድንቀበል ነው፡፡

🌿🌿
ስለዚህ ያለንን ለድኾች እናካፍል፡፡ ያን ጊዜም “በተኑ፤ ለችግረኞችም ሰጡ፡፡ ጽድቃቸውም ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ይባልልናል፡፡ እግዚአብሔር በክቡር ዳዊት አድሮ “ዘረወ ወወሀበ ለነዳይ - በተነ፤ ለችግረኞችም ሰጠ” ብሎ ሲናገር መበተን ማለት ማጣት ማለት እንዳልኾነ እንድናውቅ እንድንረዳም ሽቶ ወድያውኑ፡- “ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም ዓለም - ጽድቁ ለዘለዓለም ዓለም ይኖራል” ብሎ የሚነግረን ለዚህ ነውና፡፡ “ያላቸውን ለተቸገሩ ሰዎች የሚያካፍሉ ሰዎች ጽድቃቸው የዘለዓለም ዓለም ነው፤ አይጠፋባቸውም፡፡ እነርሱ አላፊና ጠፊ ነገር ይሰጣሉ፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚቀበሉት ግን መቼም ቢኾን መች የማያልፍ፣ መቼም ቢኾን መች የማይጠፋ፣ መቼም ቢኾን መች የማያረጅ ኾኖ ነው” ብሎ ሲነግረን ነውና!!



📚አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች
📝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📝በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ

🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Jan, 02:32


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን #ለታላቁ_አባት_ለሐዲስ_ሐዋርያ ለኢትዮጵያ ብርሃኗ ለሆኑት #ለአቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ለልደት በዓል፣ ለአንጾኪያ ሊቀ ጳጳስ ለከበረና ለተመሰገነ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰሎንቅያ በምትባል በምስ አገር ለሆኑ ሰይጣንን ገዝተው በግልጽ ላነጋገሩ ለታላቁ አባት #ለአባ_ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ #ለአሚናዳብ_ልጅ_ለጻድቂቱ_ለቅድስት_አስቴር ለዕረፍቷ መታሰቢያና ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎድሮስ_ኃይለ_መነኰስ ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአንጾክያ አገር ሊቀ ጳጳስ ከከበረ #ከአባት_ፊሎንጎስ ዕረፍት፣ የእግዚአብሔር መልአክ ከነገራቸው #በከዲህ_ከአሉ_ጻድቃን በአንዲት ቀን ዕረፍታቸው ከሆነና #ከአዝቂርም ከመታሰቢያው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።    

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

01 Jan, 02:35


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለልበ_አምላክ_ለእሴይ_ልጅ ለእስራኤል ንጉሥ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ዳዊት_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል፣ ለከበረ ተጋዳይ አባት ለገዳማዊ #ለአባ_ጢሞቴዎስ_ዕረፍት በዓል፣ ለቅዱሳን #ለአባ_ሳሙኤል_ለአባ ስምዖን_ለአባ ገብርኤል ለዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ከይስሐቅ_ከአባ_አሞን፣ #ከአባ_አቦሊ_ከመቃርስ_ከአይተለአትካ_ከፊልጦስ_ከመርቆሬዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

31 Dec, 10:54


🔔 🔔

ለውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት አባላት በሙሉ

የተላከውን ሊንክ በመጠቀም ለሰንበት ትምህርት ቤቱ እድገት ትልቅ ግብአት የሆነውን መጠይቅ እንድትሞሉ እየገለጽን በወረቀትም መጠይቁ ስለተዘጋጀ በሊንክ መሙላት የማይመቻችሁ አባለት በሰንበት ትምህርት ቤቱ መርሃግብራት ላይ በመገኘት መሙላት እንደምትችሉ እናሳውቃለን::

👉👉 » » » » ሊንክ ይጫኑ » » » »

🔔 🔔

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

31 Dec, 10:04




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🔔 የማክሰኞ ጉባኤ 🔔

ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 22 ከ11:30 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከቀኑ ከ12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

🌿🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

31 Dec, 03:38


🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን #እመቤታችንን_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን የከበረ_ሊቀ መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል በአበሠራት መሠረት #ቅዱስ_ደቅስዮስ_በዓል_ላከበረት_ለብሥራት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና የእመቤታችንን ተአምረ ማርያም መጽሐፍ ለጻፈው #ለቅዱስ_ደቅስዮስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰ። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበረ መልአክ ከመላእክት አለቃ #ከቅዱስ_ገብርኤል ከበዓሉ መታሰቢያ ዳህና በሚባል አገርም ቤተ ክርስቲያኑ ከተሠራችበትና ከከበረችበት ተአምራትም ካሳየበትና ከአገር ኤጲስቆስ #አባ_አርኬላዎስ ምስክር ከሆነበት፣ ከእስክድርያ አገር ሠላሳ ስድስተኛ ጳጳስ ከከበረ ከአባት #ከአባ_አንስጣስዮስ ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

30 Dec, 03:19


🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁     

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት ለአንዱ የስሙ ትርጓሜ የመረጋጋት ልጅ ለሆነ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_በርናባስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱና #ለእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በዚች ቀን በተጨማሪ ከሚታሰቡ፦ ከአባ ይስሐቅ ከዕረፍቱ መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
                                    ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

29 Dec, 10:13


🌿🌿

አንደበታችንን እንጠብቅ!
አፉ ውስጥ ያለችውን ይህችን ትንሽዬ ብልት መቆጣጠር የማይችል ሰው ህይወቱ በመከራ እና በብስጭት የተሞላ መሆኑ የማይቀር ነው። ከአንደበታችን የሚወጡት ቃላቶች ከሰይፍ የላቀ፣ ከፈንጂ የባሰ ጉዳትን የማስከተል አቅም አላቸው።

ማሳበባችንን እንተው!
ማንኛውንም ውድቀት ላለመቀበል ሁሉንም ዓይነት ሰበቦች እና ምክንያቶችን እናመጣለን። ይህም ከስህተታችን እንዳንማር ያደርገናል። ለማሳበብ ለማሳበብማ አዳም ሔዋን ላይ አሳቧል፤ ሔዋንም እባብ ላይ አሳባለች… ታዲያ ማን ከእርግማኑ ተረፈ?።

ፀሎት አየራችን ይሁን
ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት ዋነኛው መንገድ ነው… ከፀሎት ጋር ያልተቆራኘ ህይወት አየር በሌለበት ቦታ ላይ እንደመኖር ይቆጠራል! የጭንቀት እና የስጋት ሰንሰለት የትም እንዳንሄድ፣ ምንም ብሩህ ነገር እንዳናስብ ተብትቦ ይይዘናል፤ ፀሎት እንዴት ይህንን የብረት ሰንሰለት ማቅለጥ እንደሚችል እንማርበታለን።

🌿

ጭንቀት በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ ነው
አምላካችን እግዚአብሔር ጭንቀታችንን ሁሉ ለእሱ እንድንተው መክሮናል። እኛ ግን ብዙ ጊዜ በጭንቀት ራሳችንን ስናሳምም ነው የምንገኘው። የታዘዝነውን ከማድረግ ይልቅ በተፈጠረብን ችግር አማካይነት ሳናውቀው በተቃውሞ ውስጥ እንገባለን። የጭንቀት መድሃኒቱ የሚያስጨንቀንን ነገር ሁሉ ለአምላካችን መተው ነው።


መድኃኒታችንን እንዋጥ
ይቅርታ ከብዙ በሽታዎች የሚፈሰው መድኃኒት ነው፡፡ ራሳችንን ከመመረዝ ነጻ ማውጣት የምንችለው በይቅርታ ነው፡፡ ይቅርታ ልክ የተቀደደ ልብስን እንደሚሰፋ የሚያውቅ መርፌ ዓይነት ነው። በየቀኑ የይቅርታን መድኃኒት እየዋጥን መፈወስ ስንችል ለምን ይሆን ራሳችንን የምንመርዘው?

📝አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ


🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

29 Dec, 03:35


🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿

እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት ለአንዱ #ከሌዊ_ነገድ_ከአሮንትውልድ ለሆነው #ለቅዱስ_ሐጌ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከንግሥት_ታውፊና ከመታሰቢያዋ፣ #ከአውጋንዮስና #ከማድዮስም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

28 Dec, 09:25


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  ታህሣሥ 19/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ

1, " የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው "
       ሀ,ቅ.ዮሐንስ ዘሰዋሰው       (ለ,) አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ
        ሐ, አባ አርሳኒ              መ, ቅ. ያሬድ

ለ, አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ

2, " አሁንም እመቤቴ ሆይ እርስበርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ......"
           ሀ, ኢዮ 2፥4                  ለ, ዳን 12፥10             (ሐ,) 2ኛ ዮሐ. 1፥5          መ,የለም

ሐ, 2ኛ

3, ኢዮር የማን መኖሪያ ናት
           ሀ, የአጋእዝት እና የኪሩቤል          ለ, የሱራፊል           ሐ, የሃይላት        (መ,) ሁሉም

መ, ሁሉም

4, " ማለፊያ እንጀራም አልበላም ስጋና ጠጅም በአፌ አልገባም"
              ሀ, መዝ108፥24            (ለ,) ት.ዳን 10፥3           ሐ, 2ኛ ቆሮ 6፥6         መ, ሉቃ 2፥37

ለ, ት.ዳን 10፥3

5, ድፎ ዳቦ በደረቱ ተገልብጦ የሚቆረሰው የማን ምሳሌ ነው
          ሀ, አብርሃም                ለ, መልከጼዴቅ            (ሐ,) ይስሃቅ          መ, ዳዊት

 ሐ, ይስሃቅ

👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

28 Dec, 04:27


🍀🍀🍀💐💐💐🍀🍀🍀💐💐💐🍀🍀🍀
እንኳን #ለመጋቤ_ሐዲስ_ለሊቀ_መላእክት #ለቅዱስ_ገብርኤል_አናንያን_አዛርያን_ሚሳኤልን (ሠለስቱ ደቂቅን) ከነደደ እሳት ለዳናቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከካህናት ወገን ከሆነ #ከሀገረ_ቡርልስ_ኤጲስቆጶስ ከቅዱስ አባት #ከአባ_ዮሐንስ_ዕረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🔱🔔🔱🔱🔱🔱🔱🔱

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Dec, 17:34


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ታህሣሥ 18''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Dec, 12:27


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Dec, 02:30


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ለነበረው ለጌታችን ወንድም ለሚባለው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ_ለዕረፍት በዓል፣ ከቁልዝም ከተማ ለሆነ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_አትናቴዎስ_ለዕረፍት_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በፍቅር አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእንዱራናና_ከጦቢያ፣ #ከኤስድሮስ_ማኅበር_ከዘጠኝ_ሽህ ጭፍሮችና #ከመኰንኑ_ከእንድራኒቆስና ከሠራዊቱ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Dec, 02:30


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ሉቃስ_ዘዓምድ ለሥጋው ፍልሰት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ሰማዕታት #ከአርድዮስ_ከአውስዮስ_ከሲርዮስ_ከማርቆስ #ከያርዋልኤልና በገድል ከሚደክም ከመነኰስ #ከአባ_ናትናኤል ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Dec, 03:06


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ኤርትራ አገር የሚገኘውን #ታላቁ_ገዳም_ደብረ_ድማህ ለመሰረቱት #በነጭ_እምነታቸው_በተለይ_ለነቀርሳ_በሽታ_ፈዋሽነት_ለሚታወቁት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_መርቆሬዎስ ለዕረፍት በዓል፣ ለእናታችን #ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ-ምዑዝ) በአንድ ቀን በስሚዛ (በሰንሰለት) ቤተ ክርስቲያን ሰርታ #ታኅሣሥ_14 ቀን ጨርሳ በሦስተኛ ቀን #ታኅሣሥ_16 ቀን_ቅዳሴ_ቤቱ_ሲከበር በድርገት (በቊርባን) ጊዜ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት መላእክት ጋር ወርዶ መቅደሱን ለባረከበት መቅደሱ በአራቱም ማዕዘን ለጌታ ለሰገደበት ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Dec, 12:33


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🔔 የማክሰኞ ጉባኤ 🔔

ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 15 ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከቀኑ ከ12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

🌿🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Dec, 02:31


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለአርማንያ_ሊቀ_ጳጳስ ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት ለሆነ #ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ሉቃስ_ዘአምድና_ከአባ_ይምላህ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

23 Dec, 08:37




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🔔 የማክሰኞ ጉባኤ 🔔

ነገ ማክሰኞ ታህሳስ 15 ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከቀኑ ከ12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

🌿🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

23 Dec, 02:43


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ለታላቁ ሰማዕት #ለቅዱሳን_መርምህናምና #ለእኅቱ_ቅድስት_ሣራ_ለአርባ_አገልጋዮቹም ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍት በዓላቸው፣#ለቅዱስ_መርምህናም_አባት_ለአቶር ንጉሥ ለሰናክሬም ሠራዊት #ለዐሥራ_ሰባት_እልፍ ሰማዕታት ለመታሰቢያቸው በዓላቸው፣ ከመ ከተማ በሰማዕትነት ለዐረፈ #ለቅዱስ_ስምዖን ለዕረፍት በዓል፣ #ለሀገረ_እስና_ኤጲስቆጶስ_ለአባ_አሞንዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለእስክድርያ ስልሳ ስድስተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ገብረ_ክርስቶስ ለዕረፍት በዓልና የአውሲም ኤጲስቆጶስ #አባ_ያዕቆብ ስለርሷ እንደተናገረ ለሮሜ ንጉሥ ልጅ ስሟ #ቅድስት_ነሳሒት ለተባለች ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

22 Dec, 04:13


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_አባት_ቆቅ ሲመገብ ለነበሩት #ለአባ_መቃርስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ለገባበት በዓል፣ በስላሞች ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ #ለአባ_በጽንፍርዮስና ከላይኛው ግብጽ ለሆነ #ለቅዱስ_አባት_ለአባ_አብራኮስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦#ቅድስት_ሐና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸነሰቻት የሚሉ አሉ፣ በደብረ ቀልሞን ከሚኖር ከገዳማዊ #ከአባ_ሚካኤል ዕረፍት፣#ከሰማዕት_ቅዱስ_አብራቂስ_ከሐርስፎስ፣ #ከመኰንኑ_ቆርኔሌዎስ_ከወርቅጥጶስና_ከአፍሬ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

21 Dec, 10:34


🍁

የዜማ ቀን
መዝጊያ መርሃግብር

ነገ ከ 4:00 ጀምሮ


በረከት እምናተረፍበት ጉባዔ ነውና በሰዓታችን እንድንገኝ ይሁን


🍁

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

21 Dec, 08:39


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  ታህሣሥ 11/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ

1, ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት ስንት ሰዐት ይፆማል
              (ሀ,) 18         ለ, 12            ሐ, 24            መ, 9

ሀ, 18


2, በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚታወቁት ቅዳሴያት ብዛት ስንት ናቸው
              ሀ, 7             (ለ,) 14            ሐ, 1           መ, 12

ለ, 14  

3, በሚዛን ተመዘንህ ቀለህም ተከገኘህ
                ሀ, ማኔ               ለ, ፋሬስ              (ሐ,) ቴቄል         መ, ሁሉም

 ሐ, ቴቄል

4, " በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።"
                 ሀ, መዝ.90፥13              ለ, ዮሐ.3፥21              ሐ, ሉቃ.25፥1          (መ,) ምሳ.27፥18

መ, ምሳ.27፥18

5, ከነገደ መላእክት የአርባብ አለቃ ማነው
      ( ሀ,) ገብርኤል             ለ, ሱራፊ              ሐ, ሚካኤል      መ, ሩፋኤል

ሀ, ገብርኤል

👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Dec, 02:04


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጵያኑ_ጻድቃን በጸሎታቸው የተከዜን ባሕር ለሁለት ለከፈሉ #ለአቡነ_ገብረ_መስቀል_ዘለጋሶ ለመታሰቢያቸው በዓል፣ የአየር አጋንንት ከእናቱ ጋራ ተገናግቶ የተወለደው መጥቆራ ተብሎ ይጠራ የነበረው #አቡነ_ተክለሃይማኖትና_አቡነ_ዜና_ማርቆስም_በጸሎታቸው ወደ እግዚአብሔር ለምነው በመስቀሉ ኃይል ድል ካደረጉት በኋላ ወደ ሰው አርአያነት እንዲለወጥ አድገውት ሥሙን ለውጠው አመንኵሰው ለታላቅ የቅድስና ደረጃ ለአበቁቱ #ለአቡነ_ፄዋለ_ጽጽቅ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 ለኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት ለተደመሩ ጻድቅ #ለእጨጌ (እጨ) #ለአቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ ለልደታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Dec, 07:14


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  | ህዳር 27/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ

1, እመቤታችን ወደግብፅ ከቅ.ዮሴፍ  እና ከማን ጋር ተሰደደች
                  ሀ, ሰሎሜ             ለ, ሃና           ሐ, መቅደላዊት ማርያም     መ, ሊዲያ
(ሀ,) ሰሎሜ

2, እመቤታችን ከዮሐንስ ጋር ስንት አመት ኖረች
       ሀ, 3 ዓመት         ለ, 11ዓመት        ሐ, 1ዓመት    መ, 15ዓመት
 (መ,) 15ዓመት

3, "በዚያ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ...."
           ሀ, ሉቃ.10፥11         ለ, ማቴ.5፥24          ሐ, ዮሐ.5፥25           መ, ማር.20፥7
  (ለ,) ማቴ.5፥24

4, በሲኦል እሳት ውስጥ ሆኖ በጣቱ ውሃ ነክሮ ያቅምሰኝ ብሎ አብርሃምን አማላጅ የለመነው ማንጋር ነው
            ሀ, ጥጦስ                ለ, ለንጊኖስ       ሐ, አልአዛር         መ, ይሳቅ
(ሐ,) አልአዛር

5, ጌታውን ድምፅ ከሩቅ የሰማው አይነስውር ማን ይባላል
                ሀ, ይሁዳ             ለ, በርባን          ሐ, አልአዛር        መ, በርጠሚዎስ

 (መ,) በርጠሚዎስ


👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Dec, 02:30


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ለኢትዮጵያኑ ጻድቃን በጸሎታቸው የተከዜን ባሕር ለሁለት ለከፈሉ ለአቡነ ገብረ መስቀል ዘለጋሶ ለመታሰቢያቸው በዓል፣ የአየር አጋንንት ከእናቱ ጋራ ተገናግቶ የተወለደው መጥቆራ ተብሎ ይጠራ የነበረው አቡነ ተክለሃይማኖትና አቡነ ዜና ማርቆስም በጸሎታቸው ወደ እግዚአብሔር ለምነው በመስቀሉ ኃይል ድል ካደረጉት በኋላ ወደ ሰው አርአያነት እንዲለወጥ አድገውት ሥሙን ለውጠው አመንኵሰው ለታላቅ የቅድስና ደረጃ ለአበቁቱ ለአቡነ ፄዋለ ጽጽቅ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት በፀሐይ ላይ 50 ዓመት፣ በጨረቃ ላይ 50 ዓመት፣ በደመና ላይ 50 እንዲሁም ዓለምን በክንፋቸው በመዞር በደመና ላይ 50 ለኖሩ ከሰው ተወልደው ከመላእክት ለተደመሩ ጻድቅ ለእጨጌ (እጨ) ለአቡነ ዮሐንስ ዘጠገሮ ለልደታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Dec, 17:29


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ህዳር 27''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Dec, 06:58


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Dec, 02:31


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለቅዱስ ፊልሞና ለመታሰቢያው በዓል፣ ለፋርስ ንጉሥ ለሳፎር ልጅ ለንጉሥ ሰክራድ ከጭፍሮች ውስጥ ለሆነ ሕዋሳቱን የተቆራረጠ ለቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና በንሑር ከሚባል አገር ለሆነ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመድኃኒታችን ከመድኃኔዓለም ከስቅለቱ መታሰቢያ፣ ከገርማው ከአባ ገብረ ዮሐንስ፣ ከደብረ ቊንጽል ከአባ ሊቃኖስ ከመታሰቢያቸውና ዘርቦች ከምትባል አገር ከደብረ ጒይ ከሰማዕት ቀሌምንጦስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Dec, 02:30


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን ለአገረ ናግራን ሰማዕታትና ለአባታቸው ለቅዱስ ኂሩት ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱስ ቢላርያኖስ ከሚስቱ ኪልቅያና ከእኅቱ ታቱስብያ በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ ከደሴተ ሰንሲላ ኤጲስቆጶስ ከአባ ጎርጎርዮስ፣ ከጌልዮስ፣ ከምክዋስና ከማርልዮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Dec, 02:30


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስላሞች ወገን ከነበረ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ተአምር አድርጎ ከመለሰው #ከቅዱስ_ዮሐንስ_ከአቃርዎስና #ከሮማኖስ ከመታሰቢያቸወ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Dec, 12:15



ምሴተ ጥበብ
ቅዱስ ያሬድ እና ዜማው


🗓 ዛሬ ህዳር 24/2017 ዓ.ም
🕰ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

  በእለቱ የሚቀርቡ ጉባኤዎች
       -ዝማሬ
        -ግጥም
        -ወግ
        -ቃለ እግዚአብሔር
        -መነባንብ
        -ፅሁፍ

በረከት የሚያተርፉበት ጉባኤ ነውና እንዳትቀሩ ይኹን!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
                                     ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Dec, 09:38



ምሴተ ጥበብ
ቅዱስ ያሬድ እና ዜማው


🗓 ነገ ህዳር 24/2017 ዓ.ም
🕰ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

  በእለቱ የሚቀርቡ ጉባኤዎች
       -ዝማሬ
        -ግጥም
        -ወግ
        -ቃለ እግዚአብሔር
        -መነባንብ
        -ፅሁፍ

በረከት የሚያተርፉበት ጉባኤ ነውና እንዳትቀሩ ይኹን!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
                                     ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Dec, 02:30


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው በሐዋርያው #በቅዱስ_ጴጥሮስ_እጅ_ለተጠመቀ ለመቶ አለቃ ለነበረው #ለጻድቁ_ቅዱስ_ቆርኔሌዎስና የስሙ ትርጓሜ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለሆነ #ለነቢዩ_ቅዱስ_አብድዩ_ለዕረፍታቸው_በዓል በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

01 Dec, 02:54


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ በድዮማ ከተማ አረምያ ከምትባል አገር ለሆኑ #ለቅዱሳን_ለቆዝሞስና_ለድምያኖስ ለወንድሞቻቸው #ለአላድዮስ_ለአቢሞስ_ለአብራንዮስና ለእናታቸው #ለቅድስት_ቴውዳዳ_ለዕረፍታቸው_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቆዝሞስ ማኅበር #ሰማዕታት_ከሁለት_መቶ_ስልሳ_ሁለት ወንዶችን፣ #ከአርባ_ዘጠኝ_ሴቶችና_ከቀሌምንጦስ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

11 Nov, 02:00


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴


እንኳን #ከአባ_ጢሞቴዎስ በኋላ ለተሾመ አረማውያን ስለቀናች ሃይማኖቱ ብዙ መከራ ላደረሱበት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ሃያ_ሰባተኛው_ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጴጥሮስ_ለዕረፍቱ_በዓል መታሰቢያና ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት #ስልሳ_አምስተኛ ለሆነ ለእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ለአባ_ሱንትዩ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ፦ ከእስክንድርያ ነቢዪት ከሆነች #ከሴቴንዋ_ከቅድስት_አንስጣስያና #ከአባ_ሊባኖስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

10 Nov, 06:11


🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️
የሰማይና የምድር ንግሥት ድንግል ማርያም
                      ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ።

🌹ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር🌹



ናሁ ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ ስሙር
አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት ወምድር
ከመ በህፅንኪ ያሰምክ ፍቁር።
ንግስተ ሠማያት ወምድር ማርያም ድንግል { ፪ }
ተፈፀመ { ፬ } ማህሌተ ፅጌ

ይህ መልካም፣ ያማረ፣ የተወደደ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 26 ጀምሮ እስከ ኅዳር 6 መድረሻ የመጨረሻዋ ሰንበት የሚደረሰው ይህ ድንቅ ማሕሌተ ጽጌ “እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ፅጌ ደረሰ ተፈጸመ”


የእመቤታችን ፍቅሯና አማላጅነቷ በረከቷም አይለየን

🙏የዓመት ሰዉ ይበለን 🙏


🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

10 Nov, 06:01


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #አፍራቅያ_አገር_ለሆኑ_ለቅዱሳን_ሰማዕታት #ለመክሲሞስ_ለማንፍዮስ_ለፊቅጦርና_ለፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኪዎስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያው በዓልና #ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ለጻድቁ_ለቅዱስ_ነአኵቶ_ለአብ_ለተሠወረበት ለመታሰቢያው በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 17:28


🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️
የሰማይና የምድር ንግሥት ድንግል ማርያም
                      ማኅሌተ ጽጌ ተፈፀመ።


🌹ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ
አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር፤ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር
🌹



ናሁ ተፈፀመ ማህሌተ ፅጌ ስሙር
አስምኪ ቦቱ ንግስተ ሰማያት ወምድር
ከመ በህፅንኪ ያሰምክ ፍቁር።
ንግስተ ሠማያት ወምድር ማርያም ድንግል { ፪ }
ተፈፀመ { ፬ } ማህሌተ ፅጌ


ይህ መልካም፣ ያማረ፣ የተወደደ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 26 ጀምሮ እስከ ኅዳር 6 መድረሻ የመጨረሻዋ ሰንበት የሚደረሰው ይህ ድንቅ ማሕሌተ ጽጌ “እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ፅጌ ደረሰ ተፈጸመ”


የእመቤታችን ፍቅሯና አማላጅነቷ በረከቷም አይለየን

🙏የዓመት ሰዉ ይበለን 🙏


🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️🌹️️️️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 09:36


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  | ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ
1, "ቅዱስ ቅዱስ  ቅዱስ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ
    በክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር"
        ሀ, ኢሳ.6፥3-4        ለ, መዝ.101፥9         ሐ, ሉቃ.1፥1      መ, ማቴ7፥11
ሀ, ኢሳ.6፥3-4

2, ከቅዱስ ያሬድ የዜማ መጽሐፍ አንዱ ድጓ ነው መጽሐፉ በስንት ይከፈላል
       ሀ, በሁለት            ለ,በሰባት       ሐ, በአራት      መ, በአስራሁለት
ሐ, በአራት  

3, ____የእብራይስጥ ቃል ሲሆን ሃያል አምላክ ማለት ነው
      ሀ, ኤልሻዳይ        ለ,ኤል            ሐ, ያህዌ          መ, አዶናይ
 ለ,ኤል

4, ከሐዋርያት የመጀመሪያው ሰማዕትነትን የተቀበለው ማነው?
         ሀ, ሐዋርያው ቅ. ጴጥሮስ            ለ, ሐዋርያው ቅ.እንድርያስ
      ሐ, ሐዋርያው ቅ.ያዕቆብ          መ, ሐዋርያው ቅ.ፊሊጶስ
  ሐ, ሐዋርያው ቅ.ያዕቆብ  

5, በገናን ለመጀመሪያ ጊዜ የያው አባት ማን ይባላል ?
         ሀ, ቅ.ዳዊት             ለ, ቅ.ያሬድ            ሐ, ዩባድ       መ, የሙሴ እህትማርያም
   ሐ, ዩባድ  


👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

09 Nov, 03:50


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነ #በእስክንድርያ _በግብፅ ያለቱ አምልኮ ጣኦታት (ላሕም) ላጠፍ ወንጌልን ለሰበከ ለወንጌላዊው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ማርቆስ_ለልደቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Nov, 17:31


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ጥቅምት 29''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Nov, 11:23


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

08 Nov, 02:02


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን በከሀዲው በመክስምያኖስ ዘመን  ሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቅዱስ_ድሜጥሮስ ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም የተወለደበት #ከልደቱ_ከበዓለ ወልድ ወራዊ በዓል መታሰቢያ፣ #ከድሜጥሮስ_ወዳጅ_ከሰማዕቱ_ስቅጣር ዐረፍት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_ኤርትራ_አገር የሚገኘውን #ገዳመ_ደብረ_ኣንገብ ለመሰረቱት እንደ ሙሽራው #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ መናኔ መንግሥት ወብእሲት ለሆኑት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዕንቈ_ብርሃን ለዕረፍታቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

07 Nov, 02:02


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለቅዱስ_አማኑኤል_ዓመታዊ_በዓል፣ #አባቱ_ኖኅ_እግዚአብሔር_የያፌትን_አገር_ያስፋለት ብሎ ለመረቀው #ለቅዱስ_ያፌት_ለመታሰቢያ_በዓሉ፣ #ለቅዱሳን_ሰማዕታት_ለመርትያኖስና_ለመርቆሬዎስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_መቅብዩ፣ #ከአባቶቻችንም_ከቅዱሳን_ከአብርሃም_ከይስሐቅና_ከያዕቆብ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Nov, 10:05


🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

የአምላካችን የመድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢያ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በምሥጋና በደብራችን በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ ተከብሮ ውሏል።

ፈጣሪ የዓመት ሰው ይበለን! በረከት ያሳድርብን🙏 አሜን🙏

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

06 Nov, 02:01


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለመድኃኔዓለም_ለስቅለቱ_ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና #ለሀገረ_ቃው_ኤጲስ_ቆጶስ #ለአባ_መቃርስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በዋሻ ከሚኖር #ከጳውሎስና_ከዮልያኖስ ከእነርሱም ጋር ላሉ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 06:30




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🔔 የማክሰኞ ጉባኤ 🔔

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 26 ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከቀኑ ከ12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

🌿🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

05 Nov, 03:38


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ጌታችን_ከመረጣቸውናና በሽተኞችን ሁሉ ይፈውሱ ዘንድ አጋንንትንም ያወጡ ዘንድ ሥልጣን ከሰጣቸው #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእትና_ከሰባቱ_ዲያቆናት አንዱ ለሆነው #ለቅዱስ_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢሞና ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና #ለጌታችን_ወንድም ለተባለው #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ያዕቆብ ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከፊልጶስና ከሰማዕት አግናጥዮስ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Nov, 10:08


ርዕስ:- ቅድመና ድህረ ጋብቻ ላይ የኢኮኖሚ ችግርና መፍትሄ
በቀሲስ ቴድሮስ

🌿🌿🌿🌿 🌿🌿🌿🌿 🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

04 Nov, 02:01


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_አባት_ሰው_ቢረሳ_ቢረሳ_ምግቡን_አይረሳምና #ስብሐት_ብሎ_በእንተ (ስለ) አባ አቢብ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን እምርልሃለሁ ብለው ታላቅ ቃል ኪዳንን መድኃኔዓለም ለሰጣቸው፤ የጌታችንን መከራ መስቀሉን በማሰብ #ራሳቸውን_ሰባት_ጊዜ_ለገደሉ ለታላቁና ክቡሩ ለሆኑ #አባ_አቢብ_ለተባሉት_ለመስተጋድል_አባ_ቡላ፣ #አክሚም_ከሚባል_አገር_የመላእክት_አምሳል_ለሆነ#ለአባ_እብሎኝ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከአባ_አቢብ ማኅበር ከሆኑ #ዐሥር_ሺህ_አርባ_ሦስት_ወንዶችና_ሦስት_መቶ_ሰባት_ሴቶች_ሰማዕታትና ከሰማዕቱ #ከቅዱስ_ዮልዮስ_ከሥጋው_ፍልሰትና_ቤተ_ክርስቲያኑ ከከበረችበት ዕለት ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Nov, 08:01


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  | ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ

1, "ኢየሱስም ለማንም እንዳትናገር ተጠንቀቅ ነገር ግን ሄደህ
     ራስህን ለካህን አሳይ"
        ሀ, ማቴ 8፥4             ለ, መ.መሳ 8፥17      
          ሐ, 1ኛ ጢሞ 6፥10        መ, ዮሐ 10፥1

ሀ, ማቴ 8፥4

2, ኢዮቤድ ዕሤይን ወለደ ዕሤይ ማንን ወለደ ?
      ሀ, ሰለሞንን       ለ, ቡዔዝን       ሐ, ነዓሶንን         ( መ,) ዳዊትን

መ, ዳዊትን

3, " ዕለትን የሰጠኽ እርሱ ለዕለት የሚበቃኽንም ይሠጥኻል" ማን ተናገረው ?
        ሀ, ባሕታዊ ቴዎፋን            ለ, ቅ.ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
        ሐ, አባ ስምዖን              መ, ቅ.ይስሐቅ ሶርያዊ

 ለ, ቅ.ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ

4, ካህናት የቅዳሴ አልባሳት ከለበሱ በኋላበአንገታቸው ተጠልቆ በጀርባና ፊት
    ለፊት በደረታቸው የሚወርደው ልብስ ምን ይባላል?
           ሀ, ላንቃ          ለ, ሞጣሕት     ሐ, ካባ       መ, ሁሉም

 ለ, ሞጣሕት  

5, የአርባብ መላዕክት የነገዳቸው አለቃ ማነው?
  ሀ, ቅ.ሩፋኤል            ለ, ቅ.ሚካኤል     ሐ, ቅ.ሱርያል         መ, ቅ.ገብርኤል

መ, ቅ.ገብርኤል

👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Nov, 04:50


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳ #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ነድያንን ለሚወዱ #ለአቡነ_ብርሃነ_መስቀል (አብርሃም) በሚያደርጉት ድንቅ ድንቅ ተአምራት #አባ_ዘግሩም ለተባሉት ሙሴ ጽላትን እንደተቀበለ ሁሉ #የእግዚአብሔር_መልአክ ከሰማይ አመጥቶ የብርሃን መስቀልና #የመድኃኔዓለምን_ታቦት_ለተሰጡበት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን።



🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

02 Nov, 02:00


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለእስክንድርያ_አገር_ኀምሳ_ሁለተኛ #ሊቀ_ጳጳሳት_ለአባ_ዮሴፍ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ፣ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለተቀበለ #ለቆሮንቶስ_አገር_ኤጺስቆጶስ_ለቅዱስ_ዲዮናስዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለከሀዲ ንጉሥ ለዱድያኖስ ለሚስት #ለቅድስት_እለእስክንድርያ መታሰቢያዋ በዓልና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ኢላርዮስ_ከጣንቅያቅ፣ #ከቴዎደስዮስ_ከቴዎላስ_ከዮሳብና_ከገድላ ከሰማዕት እስክድርያም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

01 Nov, 20:28


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ጥቅምት 22''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

01 Nov, 08:01


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

01 Nov, 02:01


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነ ለብልሁና ለጥበበኛው #ለወንጌላዊው_ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ሉቃስ በንጉሥ ኔሮን ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለየዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ሉቃስ_ጋር_በሰማዕትነት_ከዐረፋ_ከአራት°መቶ ሰባ ሰባት ሰዎች ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

31 Oct, 02:01


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለእመቤታችን_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ተአምራት አድርጋ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስን ከእስራት ቤት ላአዳነችበት በዓል፣ ለነቢዩ #ቅዱስ_ኢዩኤል ለዕረፍት በዓል፣ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ላስነሣው #ለቅዱስ_አልዓዛር_ሥጋው_ከቆጵሮስ_አገር ወደ #ቊስጥንጥንያ_ለፈለሰበት፣ እግዚአብሔር በሚወድ #የንጉሥ_ሰይፈ_አርዕድ_ደግሞ_ቈስጠንጢኖስ ለሚባል ልጁ በሆነ #በንጉሣችን_በዳዊት ዘመን ለዐረፈው ለከበረች አገር #ኢየሩሳሌም_ሊቀ_ጳጳሳት ለሆነ ለቅዱስ አባት #ለአባ_ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚችን ቀን ከምትታሰበው፦ አምላክ ከወለደች #ከእመቤታች_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም ከወራዊ በዓሏ መታሰቢ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

30 Oct, 06:48


🌿🌿🌿🌿

ቅዱሳን ለምን መከራ ይበዛባቸዋል?🌿

ቅዱሳን ለምን በዓይነትም በብዛትም ልዩ ልዩ መከራዎች እንደሚደርስባቸው ለእናንተ ለምወዳችሁ የምነግራችሁ በቍጥር ስምንት ምክንያቶች አሉኝ፡፡ በመኾኑም በጣም ብዙ ምክንያቶች እያሉ አንድ ምክንያትስ እንኳን እንደሌለ አድርገን ከእንግዲህ ወዲህ በሚከሰቱ ነገሮች ብንሰናከል፣ ብንጠራጠርና ብንታወክ ምንም ይቅርታ ወይም ምሕረት እንደማይደረግልን በማወቅ በታላቅ ማስተዋል ኾነው ኹላቸውም ወደ እኔ ይዙሩ፡፡

ስለዚህ እግዚአብሔር መከራ እንዲርስባቸው የሚፈቅድበት የመጀመሪያው ምክንያት፥

🌿በሚያሠሩአቸው ምግባራትና በሚፈጽሙአቸው ተአምራት በቀላሉ ወደ ድፍረት እንዳይገቡ ነው፡፡

🌿ኹለተኛ ሌሎች ሰዎች [እነዚህ ቅዱሳን] ከሰዋዊ ባሕሪያቸው በላይ ግምት እንዳይሰጡአቸውና “ሰዎች ሳይኾኑ አማልክት ናቸው” ወደሚል ድምዳሜ እንዳይደርሱ ነው፡፡

🌿ሦስተኛ የእግዚአብሔር ኃይል ድል ሲያደርግ፣ ሲያሸንፍ እንዲገለጥና በዚህም በታመሙና በታሰሩ ሰዎች ቃሉ እንዲሰፋ ነው፡፡

🌿አራተኛ እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያገለግሉት ሹመት ሽልማትን ሽተው ሳይኾን እነዚህን የሚያህሉ መከራዎችን እንኳን ተቀብለው ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር ቅንጣትም ታህል እንዳልቀነሰ እንዲታወቅና ጽናታቸው እጅግ ደምቆ እንዲታይ ነው፡፡

🌿አምስተኛ ልቡናዎቻችን ስለ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን እንዲያውቁ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ጻድቅና የምግባሩ ሀብት የበዛለት ሰው እልፍ ጊዜ መከራዎችን ሲቀበል ብታይ ምንም እንኳን ወደህና ፈቅደህ ባይኾንም ሊመጣ ስላለው ፍርድ - ማለትም እነዚህ ሰዎች እነዚህን የሚያህሉ መከራዎችን የሚቀበሉት ለራሳቸው ካልኾነ፣ ያለ አንዳች ደመወዝና ክብር ካልኾነ፥ እግዚአብሔርም እንዲህ የሚደክሙትን ያለ አክሊል ሽልማት ይሰድዳቸው ዘንድ እንደዚህ ያለ ነገር ይደርስባቸው ዘንድ ባልፈቀደ ነበር ብለህ - ለማሰብ ትገደዳለህ፡፡ ለዚህ ዕለት ዕለት ለኾነ ድካማቸው ዋጋቸውን የማያሳጣቸው ከኾነ ግን፥ የዚህ ዓለም ሕይወት ካለፈ በኋላ ለአሁኑ ድካማቸው ዐሥበ ፃማቸውን (የትሩፋታቸውን ዋጋ) የሚቀበሉበት የኾነ ጊዜ ሊኖር ግድ ነው፡፡

🌿ስድስተኛ ብዙ ጸዋትወ መከራ የሚደርስባቸው ሰዎች እነዚህ ቅዱሳን ምን ምን መከራ ይደርስባቸው እንደ ነበር አስታውሰው መጽናናትን እንዲያገኙ ነው፡፡

🌿ሰባተኛ የእነዚህን ሰዎች ምግባር ጠቅሰን ስንነግራችሁና እያንዳንዳችሁን
“ጳውሎስን ምሰሉት፤ ከጴጥሮስ የሚበልጥ ሥራን ሥሩ”
ብለን ስንመክራችሁ ምግባራቸውን እየተመለከታችሁ “እንደ እኛ ሰዎች አልነበሩም” ብላችሁ እነርሱን አብነት ከማድረግ እንዳትሰንፉ ነው፡፡

🌿ስምንተኛ አንድን ሰው የተባረከ ነው ወይም በተቃራኒው ነው ብሎ ለመጥራት አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ ማንን ብሩክ፣ ማንን ደግሞ ኅዙን (ኀዘንተኛ) እና ርጉም አድርገን ልንቈጥር እንደሚገባ’ን እንድናውቅ ነው፡፡

📝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
📚ትምህርት በእንተ ሐውልታት
🖋በገብረ እግዚአብሔር ኪደ

🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

30 Oct, 02:00


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለታላቁ_ለትሕትናና_ለትዕግስተኛው አባት ለክቡሩ፤ ለገናና ለሆነ #ለአባ_ዮሐንስ_ሐጺር_ለዕረፍት በዓልና የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ ለሆነ #ለታላቁ_ነቢይ_ለቅዱስ_ኤልሳዕ_ለልደቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

29 Oct, 08:11




በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🔔 የማክሰኞ ጉባኤ 🔔

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 19 ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤታችን አዳራሽ

ሁላችኹም ከዚህ መልካም መዓድ ከቀኑ ከ12:00 ጀምሮ እንድትቋደሱ ተጋብዛችኋል!

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

🌿🌿🌿🌿🌿

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

29 Oct, 02:00


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ንጉሥ_ክህነት_ከንግሥና ጋር አስተባብሮ ለያዘው #40_ዓመት_ሙሉ_ሰማያዊ_ኅብስትና_ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት ለቀደሰው #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ለይምርሐነ_ክርስቶስ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት ከመቃብራቸው በሚወጠው #በእምነታቸውና_በጠበል_ፈዋሽነታቸው ለመታወቁት #ለአቡነ_ሐራ_ድንግል_ለልደታቸው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ለቅዱስ_በርተሎሜዎስና_ለሚስቱ ለዕረፍታቸው በዓል፣ #ስለ_ጳውሎስ_ሳምሳጢ በአንጾኪያ የቤተ ክርስቲያ አንድነት ስብሰባ ለተደረገበትና #ለጸይለም አገር ለሆነ ለከበረ አባት #አቡነ_ዮሐንስ ለዕረፍት ለዕረፍታቸው በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እንደ በግ ከታረዱ #ከመጥራ_ጻድቃ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

28 Oct, 05:20


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለእስክድርያ_ሃያ_ሦስተኛ_ሊቀ_ጳጳስ ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ቴዎፍሎስና ክርስቲያኖችን በአሳደደ በመኰንን አስቅልጵያኖስ ዘመን በሰማዕትነት ለዐረፈ ለከበረ #ለመነኰስ_ቅዱስ_ሮማኖስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሰማዕት_ቅዱስ_ዮሐንስ፣ #ከቅዱሳን_አድራኒ_ከአርቴማዎስ_ከአርስጦስ #ከሉዲኖስ_ከአስማኒትና
_ከሰባቱ ልጆቿ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Oct, 06:30


"ኹለቱም አንድ አካል ይኾናሉ፤ ይኽ ነገር ጥልቅ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለኹ፡፡"

         ሃይማኖተ አበው  ዘስምዓት

በዛሬው ዕለት ጥቅምት ፲፯ ፳፻፲፯ ዓ.ም. ጋብቻችኹን በቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓት የፈጸምማችኹት ወንድማችን ብስራት ታምራት እና እህታችን ሜላት ተስፋዬ የፈጸማችኹትን ጋብቻ፤ የአብርሃምንና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ፤ የትዳር ሕይወታችኹን ይባርክላችኹ፥ ያጣምራችኹ፥ ያዋሕዳችኹ 🙏

ካህኑ ቅዱስ ያሬድ በሕይወታችኹ ሞገስ ይኾናችኹ ዘንድ በፍቅርና በጤና ይባርካችኹ ዘንድ መልካም ምኞታችን ነው!

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Oct, 02:01


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴
እንኳን #ለሀገረ_ቀምስ_ኤጲስቆጶስ #ለቅዱስ_ፊልያስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ለነቢዩ #ለቅዱስ_ሳሙኤል_እናት ለነቢይት #ለቅድስት_ሐና_ለልደቷ_መታሰቢያ_በዓል፣ #ለቅዱስ_ባስልዮስ_ወንድም_ለቅዱስ_ጎርጎርዮስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና #ለእስክንድር_አገር_ሠላሳ_አንደኛ ሊቀ ጳጳሳት #ለቅዱስ_ዲዮስቆሮስ_ካልዕ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #በቆዳ_ገመድ_ከታሠሩ_ከደጋጋጎች ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 07:33


የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  | ጥቅምት 15/2016 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ


ሚዲያ ጥያቄና መልስ

1, በቤተክርስቲያናችን የቅዳሴ ደወል ስንት ጊዜ ይደወላል

ሀ, 12 ለ, 7 ሐ, 4 መ, 21

የቅዳሴ መግቢያ ደውል
የወንጌል ደወል
የእግዚኦታ ደወል
የድርገት ደወል

(ሐ,) 4

2, ሠራዒው ዲያቆን ክቡር ደሙን ለቆራቢያን የሚያቀብልበት ማንኪያ ምን ይባላል

ሀ, የመጾር መስቀል ለ, እርፈ መስቀል ሐ, ጻሕል መ, መቁረርት

(ለ), እርፈ መስቀል

3, " ያዕቆብም በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ አለው ዔሳውም እነሆ እኔ ልሞት ነኝ ይህች ብኩርና ለምኔ ናት?"

ሀ, ኦ.ዘፍ 25፥31-33 ለ, መዝ 96፥34 ሐ, ሉቃ 5፥14 መ, ማቴ 6፥12

(ሀ), ኦ.ዘፍ 25፥31-33

4, አትሮኖስ ማለት ትርጉሙ__።

ሀ, መጽሐፍ ለ, ዙፋን ሐ, ማዕድ መ, ሁሉም

( ለ), ዙፋን

5, አቋቋም፣ ዜማሬመዋሥዕት፣ ቅኔ እና ጸዋትወ ዜማ የተማሩ ሰዎች ምን ይባላሉ?

ሀ, መምህር ለ, ዲያቆን ሐ, መሪጌታ መ, መልሱ የለም

(ሐ,) መሪጌታ

👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

26 Oct, 04:29


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለእስክድርያ_አርባ_ዘጠነኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ያቃቱ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_መቊሮፍዮን_ከእብሎ፣ #ከባሕታዊ_ኢሳይያስ_ረድእ_ከጴጥሮስ፣ #ከፋሩ_ከድርቄ_አገር_ከሆኑ_ከአርባ_አምስት ጻድቃን፣ #ከቃርቡ_ከአናልዩ_ከአባ_ጳውሊ ከመስተጋድል #ማርቆስ ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።


🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 17:31


🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ጥቅምት 15''
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 10:16


📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።
መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

25 Oct, 02:00


🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴🌷🌷🌷🌴🌴🌴

እንኳን #ለዐሥራ_ሁለቱ_ቅዱሳን_ሐዋርያት ዓለም በእጣ ለተካፈሉበት ለመታሰቢያ ቀን፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ረድ #ለቅዱስ_ሲላስና_ለኒቆድምያ አገር ለሆነ ለሰማዕቱ ለቅዱስ ቢላሞን ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቢላሞን_ማኅበር_ከሆኑ_ከመቶ_ሃምሣ_ስምንት ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው፣ #ከሰላትዮን_ከአጥራኪስ #ከአርሞቅስ_ከአድማንያ_ከአርሚስ_ከቅድስት ጾመታ፣ #ከአባት_ኢሳይያስና_ከሐዋርያትም ከዕፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️🔱⚜️

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Oct, 12:42


🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
የአባታችን ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በምሥጋና በደብራችን በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ ተከብሮ ውሏል።

ፈጣሪ የዓመት ሰው ይበለን! በረከት ያሳድርብንአሜን

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Oct, 12:42


🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
የአባታችን ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በምሥጋና በደብራችን በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ ተከብሮ ውሏል።

ፈጣሪ የዓመት ሰው ይበለን! በረከት ያሳድርብንአሜን

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴

6,578

subscribers

5,709

photos

34

videos