Hijra Tube [Official] @hijranews Channel on Telegram

Hijra Tube [Official]

@hijranews


ሒጅራ ቲዩብ ኢስላማዊ ድረገፅ ትኩስ ትኩስ የሙስሊሙን አለም የተመለከቱ መረጃዎች ጠቃሚ ፅሁፎችና ዳእዋዎች ይቀርቡበታል

Hijra Tube [Official] (Amharic)

ሒጅራ ቲዩብ [አስተማሪ] አሁን ሌሎች የተወካዮ ቻንኩል ተደረገ ሒጅራ ቲዩብ ኢስላማዊ ድረገፅ ነው። እንደኛ አስተናግዷል? ምን ነበረበት? ሒጅራ ቲዩብ እንዴት ጥይት ነው? ሒጅራ ቲዩብ አስተማሪ ከሆነም ብዙ የቴሌግራም ፋነሲ የነሐሴ ቅኝት፣ የርክት ፍልው እና የኢንተርኔት ቴሙ፣ ፕላይስትስ አፕሊኬሽን በተለያዩ ማቆሚያ ነን። ሒጅራ ቲዩብ ከዋጋል ፎቶ አማራ የታወቁ ፅሁፋችና ዳእዋዎችን አዕምሮ በቀላሉ ምንም ምንም እንክላለን።

Hijra Tube [Official]

04 Nov, 19:01


እህቴ አይዞን እኛ ከጓንሽ ነን!

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

Hijra Tube [Official]

03 Nov, 19:07


አካዳሚውን ልዩ የሚያደርገው:
💵 በነፃ መሆኑና ለሁሉም የእድሜ ክልል ላሉ ወንዶችም ይሁን ሴቶች ምቹ መሆኑ፤
💻 በስልክ ወይም በላፕቶፕ ባሉበት ቦታና ርቀት ለመማር ምቹ መሆኑ፤
📚የትምህርት አሰጣጥ መንገዱ እጅግ ያማረና ገር መሆኑ፣ እንዲሁም በተመረጡ ዑለሞች የሚሰጥ መሆኑ፤
🗒️ለየሁሉም የትምህርት ክፍል በይሳምንቱና ትምህርቱ ሲጠናቀቅ የሚሰጡ ፈተናዎች መኖራቸው፤
🎊ላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑና የምርቃት ፕሮግራም የሚዘጋጅ መሆኑ፤

📖በአካዳሚው የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች:
1 - ሲራ
2 - ዓቂዳ
3 - ፊቅህ
4 - ተርቢያ
5 - ተፍሲር
6 - ሐዲሥ

⏱️የትምህርት ቆይታው አንድ አመት ሲሆን በሁለት ሴሚስተሮች የተከፋፈለ ነው።

📋ትምህርቶቹ ለተማሪዎች የሚቀርቡት በነዚህ መልኩ ነው:
- በፒዲኤፍ (pdf)
- በቪዲዮ
- በድምፅ

አላህ ካለ የሶስተኛ ዙር የዲፕሎም ትምህርቱ በ10/11/2024 ይጀምራል።

ሶስተኛው ዙር ለመመዝገብ በሀሳብ መስጫ ሳጥን ውስጥ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

እድሉ አያምልጥዎ! በዙሪያዎም ላሉ ሁሉ ያጋሩ።
📲 የመመዝገቢያው ሊንክ
https://t.me/africaacademy_diplom3

Hijra Tube [Official]

03 Nov, 16:31


ሶላት የማይሰግድ ሁኖ የሞተ ሰዉ ሁክሙ?


መልስ


ሶላት የማይሰግድ ሁኖ የሞተ ሰዉ ገላዉን ማጠብ ሀራም ነዉ

ጀናዛዉን ማጠብ ሀራም ነዉ

በእሱ ላይ ሶላተ ጀናዛ መስገድ ሀራም ነዉ

የሙስሊሞች ቀብር መቅበር ሀራም ነዉ

አሏህ እንድምረዉ እና እንድያዝንለት ዱዓ ማድረግ ሀራም ነዉ

ምክንያቱም ከእሳት ሰዉዎች ነዉ እና


በኩፍር ለሞተ ለአንድም ሰዉ አሏህ እንድያዝንለት ይቅር እንድለዉ ዱዓ ማድረግ አይፈቀድም



አሽሀዱ አላ ኢላሀ ኢለሏሁ ወአነ ሙሀመድ ረሱሉሏህ ቢል እንኳ ካፊር ነዉ


ይሄ ምስክርነት ስራዉ ዋሽቷል እና

ሙናፊቆች ላኢላሀ ኢለሏህ ይላሉ

ለረሡል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንተ የአሏህ መልዕክተኛ እንደሆንክ እንመሰክራለን ይሉ ነበር

እንደዚሁ

ሶላት የማይሰግድ ሁኖ የሞተዉ ሰዉ ቅርብ ዘመዶች የሟቹን ንብርት መዉረስ አይፈቀድላቸዉም


ይሄም
የረሱል ሶለሏሁ አለይሂወሰለም ትክክለኛ ሀድስ ቡኻሪ እና ሙስሊም የተስማሙበት የኦሳማ ቢን ዘይድ አሏህ መልካም ስራዉን ይዉደድለት እና

ሙስሊም የሆነ ሰዉ ካፊር ንብረት መዉረስ አይፈቀድለትም

ካፊር የሆነ ሰዉ የሙስሊም ንብረት ሊወርስ አይፈቀድለትም

ሶላት የማይሰግድ ሁኖ የሞተዉን ሰዉ ታድያ ምን እናድርግ?


ከሀገሩ ዉጭ እንሸከመዋለን

ጉርጓድ እንቆፍራለን እንደፍነዋለን

ጀናዛዉን ሳናጥብ

ጀናዛዉን ሳንከፍን

በጀናዛዉ ላይ ሶላት ሳይሰገድ

ይሄ መስዓላ ችግሩ ከባድ(ትልቅ)ነዉ

አንዳድ ሰዎች ላይ ታገኛለህ ቤተሰቦቹ ሶላት እንደማይሰገድ ያቃሉ

እሱ ሶላት የማይሰግድ ሁኖ ሞተ በአሏህ ማመኑ መተበቱን አያቁም

ይሄ ከመሆኑጋ
ጀናዛዉን ያጥባሉ
ይከፍናሉ
ወደ ሙስሊሞች ያመጣሉ በእሱ ላይ እንድሰግዱበት

ይሄ በእነሱ ላይ ሀራም ነዉ

በእሱም ላይ አይፈቀድም

እነሱ በዚህ ላይ ሙስሊሞችን ክደዋል

Hijra Tube [Official]

01 Nov, 18:04


የሸሪዓ ትምህርት ለመማር እድል አላገኙም?

የፕሮግራሙ ልዩ ባህሪያት

💶ነጻ መሆኑ
💻 በርቀት የሚሰጥ መሆኑ
👬ጾታና የእድሜ ክልል የማይገድበው መሆኑ
📚ትምህርቶቹ የሚሰጡት በእውቅ መሻይኾችና ኡስታዞች መሆኑ
🎉 ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት እና እውቅና ያለው የምስክር ወረቀት መሰጠቱ።
የትምህርት ቆይታው አጭር መሆኑ
========================
👇👇👇👇ካፕሽን

  💻 ምንም ሳይገድብህ ካለህበት ሆነህ ስለ ዲንህ ተማር

ከአፍሪካ አካዳሚ ጋር በትምህርት ጉዞው ይደሰቱ 💯
ፍላጎትዎን የሚያሟላ ልዩ የትምህርት ፕሮግራም።

📲 የአፍሪካ አካዳሚ ሶስተኛዉ ዙር መመዝገቢያው  ሊንክ

https://t.me/africaacademy_diplom3

Hijra Tube [Official]

27 Oct, 08:51


የትግስት፣ የኢማን፣ የጥንካሬ፣ የፅናት ጥግ ያለው ጋዛ ነው

ለአላማ፣ ለዲን፣ ለሀገር፣ በክብር መስዋዕትነት መክፈል በተግባር ያለው እዛ ነው። ይህ ወንድማችን በሙሉ ቤተሰቡ መስዋዕት ሆነውበት የፃፈው በትግስትና ጥንካሬ የተሞላ የስንብት ጽሁፍ እዩት😥

እንዲህ ይነበባል።

"አልሃምዱሊላህ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ
ዛሬ ውዷ ባለቤቴ ኡሙ የዝን በሰሜናዊ ጋዛ አልፋለች ልጆቼ የዝን፣ሪዳን፣ሙሀመድ እና ኡመር ሁሉም አለፉ አሏህ ከዱንያ ህይወት የተሻለ ህይወት እንዲለውጥላቸው፣ መስዋትነታቸውም እንዲቀበላቸው በቅርብ ደግሞ እነሱን እንዲያስከትለኝ እለምናለሁ።
ከፊት ተጋፍጠው እንጂ እየሸሹ አይሰዉም።
ሀስቢያሏሁ ወኒዕመል ወኪል😥"
ምንኛ ያማረ ትእግስት እና ጥንካሬ ነው

ሱብሃናሏህ አንድ ልጃችን ሲታመም ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጭ የምንል ሰዎች እኛ አለን እንጂ 😥 እነሱማ ሪጃሎች የዘመናችን የሰሃባ ምሳሌዎች ናቸው😥

Hijra Tube [Official]

25 Oct, 17:28


ለሴቶች ሴት የቁርአን አስቀሪ ለምትፈልጉ ቀራኒዩ፣ቤተል፣አንፎ፣አለም ባንክ ለሆናቹህ
+251975257065

Hijra Tube [Official]

24 Oct, 08:32


ጣልያናዊው ጓድ ፍራንኮ ፎንታና የፍልስጤማውያን ሰቆቃ ሲያንገሸግሸው ለነጻነታቸው ሊታገል በ1970ዎቹ ፍልስጤም ምድር የከተመ ሰው ነበር። በወቅቱ የነበሩ ሙጃ*ሒዶችን በተለይም በሮኬት ተኩስ ካገዙ ወታደራዊ ጠበብቶች መካከል ነበር። በመጨረሻም በጣልያን ያፈራውን ንብረት ሁሉ በመሸጥ ለትግሉ አበረከተ።

ይህ ቀና ሰው በስተመጨረሻም አላህም ﷻ ሒዳያውን ወፍቆታል። በ2005 እስከተገደ*ለበት ጊዜ ድረስ ለፍልስጤማውያን ህዝቦች ነጻነት ሲታገል እድሜውንም፣ ህይወቱንም፣ ንብረቱንም ሰውቷል። በመጨረሻ ጊዜዎቹ ከተናገረው ውስጥ፦

"ምናልባት እኔ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ለመመልከት አልታደልኩ ይሆናል፣ ግን ያለምንም ጥርጥር ልጆቼና የልጅ ልጆቼ የፍልስጤማውያንን ነጻነት ያያሉ። ያኔም ለዚህች የተባረከች ምድር የከፈልኩትን መስዋዕትነት ይረዳሉ"

አላህ ﷻ ይዘንለት፣ ያለምንም ጥርጥር ቁድስ ከወራ*ሪዎቿ ነጻ ትሆናለች - ኢንሻአላህ..!

ያህያ ኢብን ኑህ

Hijra Tube [Official]

22 Oct, 07:09


በመጨረሻም ሌላ አድካሚ ጉዞ በርሃብ በጥማትና በድካም ጀምረን በልጄ የውልደት ቀን በድፍን ወር ከአራተኛ ቀናችን በመንገዴ ላይ ስላለፈው ዓመት የውልደቷ ቀኗ ጥሩ ጊዜ ያሳለፍነውን እያሰብኩ ህዳር 19/03/2016 ታንዛኒያ ላይ ጭኖን የነበረው ኮንቲነር መኪና አልነሳ ብሎት እስኪያስተካክል ድረስ ጫካ ውስጥ አሳርፎን ብዙም ሳንቆይ በሀገሪቷ ፖሊሶች ተያዝን ለልጄ የማስባቸው ህልሞችም አብረውኝ ተያዙ ወደ አስፈሪውና ጭካኔ ስለሚበዛበት ሞሾ እስር ቤት አሰሩን ከህዳር 19እስከ ታህሳስ 3/2016 እዛ እስር ቤት ውስጥ ከታሰርን በኋላ ፍርድ ቤቱ የወሰነብንን ከእስር ነፃ መውጫ ገንዘብ ደቡብ አፍሪካ ስራ ሊቀጥረን የነበረው ሰው ከኔ ጋር አብረውኝ ከመጡት ሶስቱ ጋር ለእያንዳንዳችን አንድ መቶ ሰማንያ ሺ ብር ከፍሎ ወደ ሀገር ታህሳስ 5/2016 እንድንገባ በአሏህ ፍቃድ አደረገ ሀገር ገብቼ ተረጋግቼ ነገሮችንም ከአሏህ ጋር ከተስተካከሉልኝ ቦታ ቦታ አሲዤ የልጄ ቅርስ የሆነው ሱቄ ላይ ስራ እጀምርበታለው ብዬ ባልምም ህልሜም ሱቄም ልጅነቴን ሁሉ ለነገ የተሻለ እንዲሆንልኝ የሰጠሁት ሱቄም አይኔ እያየ አመድ ሆነ አሏህ ሆይ ከዛ ሁሉ በላዕ ያወጣኸኝ ለልጄም እኖር ዘንድ ሌላ ህይወት የሰጠኸኝ ለዚሁ ነውን 💔😭..
Via Khalid

Hijra Tube [Official]

22 Oct, 07:09


ልክ የዛሬ ዓመት ጥቅምት 15/02/2016 ኸሚስ ማታውን እናቴ ህመም ላይ ስለነበረች እንዳትደነግጥ ብዬ ለሁላችንም ታላቅ ለሆነችው እህቴ ደውዬ እንባ እየተናነቀኝ አንቺንና እማን ላወራቹ እፈልጋለውና እማ ጋር እንገናኝ አልኳት ድንጋጤ ውስጥ ሆና ምን ሆንክብኝ የት ነህ ልምጣልህ አለችኝ እኔ እማ ጋር እየሄድኩ ነው ቤት ሳልገባ እጠብቅሻለው ተያይዘን እንገባለን ብዬ ውጪ ጠበኳት ብዙም ሳትቆይ መጣች እጄ ላይ ሻንጣ ይዤ ስለነበር እየተንቀጠቀጠች ምን አገኘብኝ ስትለኝ እኔ ደህና ነኝ እማ ተኝታ ሊሆን ስለሚችል እቤት ተረጋግተን እንግባ ብዬ ገባን እንደገባንም እናቴን ዘይረናት ስናበቃ እግሯ ስር ወድቄ ከልብሽ አውፍ በይኝ እማ አልኳት መንገድ ልጀምር ነው አልኳት በዛው ህመሟ ውስጥ ሆና በሲቃ በሚሰማው ድምጿ የምን መንገድ ነው ምን ነው ምን ሆንክብኝ ስትለኝ ለቅሶ ላይ ሆኜ ለደቂቃዎች ዝም ስላት በነገሮችህ ሁሉ አላህን በምታማክረው ኃሊቁ ይዤሃለው የሊቢያን መንገድ ነው እንዳትለኝ ልጅ እያለች እሷም አብራኝ ማልቀስ ጀመረች ትንሽ ከተረጋጋው በኋላ የምለውን በዝምታ እንዲያዳምጡኝ ውሳኔዬንም እንዲያከብሩልኝና እንዲቀበሉኝ በልመና ቃል አስገባዋቸውና ከ2013 ጀምሮ እናንተና ጓደኞቼ ፊት ስብራቴን ሳይሆን ሙሉነቴን ያጣኋቸውን ነገሮች ሳይሆን አሏህ የሰጠኝን ነገሮች ስነግራቹ ቆይቻለው በተቃራኒው ግን አራት አመት ሙሉ ስላሳለፍኩት ከባባድ ሙሲባዎች ለናተ ከነገርኩ አሏህ ላይ ማማረር ሊሆንብኝ ነው እርሱ ደሞ በስብራት ላይ ሆኜ እንኳን ሊፈትነኝ ፈልጎ እንጂ አልተወኝም ከልሎኛልም በናንተም ሆነ በሌሎች ፊት ሙሉዕ እንድሆን አድርጎኛል አሁን ሊቀይርልኝ የፈለገው መልካም ነገር አለና በጓደኛዬ አማካኝነት ደበብ አፍሪካ ለመሄድና ሰበብ ለማድረስ አስቢያለው ከዛ በፊት ግን አደራ አለኝና አደራዬን ተቀበሉኝ ብዬ ካባቴ መኝታ ቤት የሱቁን ሙሉ ዶክመን ይዤ መጣውና በዚህ አራት አመት ውስጥ በደረሱብኝ መከራዎች አሏህ ንብረት ሰጥቶኛልና ሰው ፊት የመቆሙ ሞራል ስለሌለኝ የመጨረሻ አማራጬን ሱቁን መሸጥ ላይ ልወስን እያሰብኩ አባቴ የልጅህን ንብረት ምንም አይነት ፈተና ውስጥ ብትሆን ለልጅህ ብለህ መኪናህን እንደሸጥከው ሱቁንም እንዳትሸጠው ብሎ ቃል ያስገባኝን ፊቴ ላይ እየመጣ ይረብሸኛል በዛም የመጣ ሳልወስንበት አራት አመት ሙሉ እየተራብኩም እየተጠማሁም ገፍቼበታለው ሱቁ ህይወትን ቀን በቀን ካስናፈቀችኝና እርሷን ልክ ሳያት ከነበርኩበት መጥፎ ሀለቴ ለምትመልሰኝ ልጄ ስታድግ በስሟ አዙሩልኝ እስከዚያው አሏህ ፈቅዶ እኔም ሃጃዬ ቦታ ደርሼ ነገሮችን ቦታ ቦታ እስካሲዝ ግን ሱቁ ተከራይቶ በምንም ይከራይ ግማሹ ለርሷ ትምህርት ቤት ክፍያና ለእማ ግማሹ ደግሞ የሰዎች ዕዳ አለብኝና በየወሩ ለነርሱ ስጡልኝ ብዬ ሰነዱን ለእናቴ ሰጠኋትና በማይሰማው ድምጿ ውስጥ ሆኖ ተው ልጄ በህመሜ ውስጥ ጥለኸኝ አትሂድ እኔ ምበላውን አንተም ልጅህም አብረን እንበላለን ካሳለፍካቸውና ከተሰበርክባቸው ከባድ ጊዜዎች በላይ የተሻሉ ነገሮች ይሆኑልሃል አጠገቤ ሁንልኝ አለቺን እማ አንቺና አባ እኛን በማሳደግ ውስጥ ብዙ ነገር ሁናቹልናል እኔም ለልጄ መክፈል ያለብኝን ሁሉ ልክፈል አትከልክይኝ ልጄም አትዘንብኝ ብዬ እንዳታስቆመኝ ድጋሚ አውፋታ ጠይቂያትትና ዱዓ ብቻ እንድታረግልኝ ነግሪያት ሻንጣዬን ይዤ እየሮጥኩ ወጣው ሱብሂ ላምበረት መነኻሪያ ውስጥ ሰግጄ

ከኔ ጋር ከነበሩ ሁለት የሰፈሬ ልጆች አንድ በላኪው በኩል ከገጠር ከመጣ ልጅ ጋር ተያይዘን ሞያሌ ድረስ በቆረጥንበት ባስ ውስጥ ገብተን ጉዞ ጀመርን የልጄ ከውሰር ድምፅ ሳልሰማ አለመምጣቴ ያብከነክነኝ ጀመር ሆድ ቢብሳትም ቢብሰኝም ከቤት ስወጣ በዛች ጣፋጭ አንደበቷ የምታረግልኝን ዱዓ ብሰማትና ብቀበላት ምን ነበር ምን አይነት አባት ነኝ እያልኩ እራሴን እየወቀስኩ ጉዞዬን ቀጠልኩ ሃዋሳን አልፈን የማላውቀው ቦታ ላይ ለቁርስ ውረዱ አለንና ተሳፋሪ በሙሉ ወረድን ጋደኞቼ ቁርሱን እዘዙ ብዬ ካሼሪው ጋር ሄጅ ይቅርታ ወንድሜ ስልክ አስደውለኝ ብዬ እቤት ደወልኩና ከውሲን እንዲያገናኙን አድርጌ ሀዘን ውስጥ ሆኜ አሰላሙአለይኩም ከውሱ ከማለቴ ለሰላምታዬ ምላሼን ሰጠችኝና አባ ምነው ዛሬ ጁምዓ ለመስገድ ቀጠሮ ነበረንኮ ለምን ሳታስነሳኝ ሄድክ አለችኝ የምለው ሲጠፋኝ ለቅሶ ውስጥ ሆኜ ዝም አልኩ ተደጋጋሚ ሄሎ አባ ስትለኝ ማውራት ከብዶኝ አውፍ በይኝ ጥዬሽ መስጂድ ስለሄድኩ በጣም እወድሻለው ብዬ ስልኩን ዘጋውባትና መሬት ላይ ቁጭ ብዬ ማንባት ጀመርኩ ካሼሪውና የሆኑ ሰዎች መጥተው አረጋጉኝ ተነስቼ ዑዱ አድርጌ ጥግ ቦታ ፈልጌ ሰሏተል ዱሐ ሰግጄ ለልጄና ለመንገዳችን ዱዓ አድርጌ ከጓደኞቼ ጋር ቁርስ በላሁና መንገዳችንን ቀጠልን በመኪና ከሞያሌ እስከ ኬንያ ትሄዳላቹ የተባልን ሰዎች 18ቀን ሙሉ በሶት ቀን አንዴ ምግብ እያገኘን ለዋና ከተማዋ አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ሲቀር ሙሉ በእግር ተጓዝን በመንገዳችን ሁሉ እኔም ሆንኩ ጓደኞቼ ዚክርና ሰለዋት አለ ነቢ እያወረድን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ቀጠልን

አሏህም በሶስት ቀን አንዴ የምናገኘውን ምግብም ሆን በርሃብና ጥማት እንዲሁም ድካም ውስጥም ሆነን ነገር ግን የደቂቃዎች ስሜት ብቻ እንዲሆን አድርጎ አሳለፈልንና አስራ ዘጠነኛው ቀን ላይ በመኪና ናይኖቢ ድረስ መቶ ኪሎ ሜትሯን እንድንጓዝና እንድንደርስ አደረገን አረፍን ስንል ሌላ ሰባት ተጨማሪ የስቃይ ቀናቶችን በዛች ጠባብ ክፍል ውስጥ 67ሆነን እያደርን አሳለፍን ምንም እንኳን አሏህ أَحَسِبَ ٱلنَّاسُ أَن يُتْرَكُوٓا۟ أَن يَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ
ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን
ቢለንም የርሱ ፈተና መውደቂያ አይደለም ሰብራችንን ሊፈትሽ አስቦ ነውና እናልፋለን እያልኩና አብረውኝ ለነበሩት እያበረተው ጎዞ ቀጠልን ከናይሮቢ ሞንባሳ ድረስ በኮንቲነር እንደ ዕቃ ተጭነን ጎዞ ጀመርን ምንም ትንፋሻችን ቢያጥርም አሏህ አልቆረጣትምና እንደዛ እንደታፈንን ሞንባሳ ደረስን ሌላ መኪና መጥትቶ ተቀበለንና እንዳለፉት ቀናቶች ጫካ ለጫካ እየተጓዝን የምናድርበት ቤት አደረሰን ከሁለት ቀናት በኋላም ሌላ መኪና መጥቶ ከሌሎች ጋር ተቀላቅለን ተጓዝንና ለሞተረኞች አስረከቡን ሁለትና ሶስት ሰው እያረጉ ሌላ ጫካ አስገቡንና ለታንዛኒያኖች አቀበሉን እዛም በሃያ አራት ሰዓት አንዴ አንድ እሽግ አስራ ስድስት ፍሬ የምትይዝ ስላይስ ዳቦ ለሁለት ተካፍለን እየበላን እንድንቆይ አደረጉን ለተከታታይ አምስት ቀንም ከመግሪብ እስከ ሱብሂ ምንም መጠለያ የሌለው ጫካ ውስጥ ሆነን ዝናብ ቀጠቀጠን የዚህ ሰዓት ነበር ከወገቤ ቀና ማለት ሲያቅተኝ ያ አሏህ አሁን እንኳን አልቻልኩምና ሩሄን ውሰዳትና ጓደኛዬም ሁሉም ነገሬ ከሆነው አባቴ ጋር ቀላቅለኝ ብዬ ሩሄን እንዲወስዳት ዱዓ አደረኩ ግን ሩሄን ሊወስዳት አልፈለገም ሌላ ፈተና ሊፈትነን ፈለገና ዝናቡን አቁሞልን ከነበርንበት ጫካ ወጥተን ሌላ ጉዞ እንድንጀምር አደረገ መርሃባ ከማለት ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረኝምና ከወገቤ ትንሽ ቀና ብዬ መራመዴን ከሱብሂ በኋላ ከሌሎች ጋር ጉዞዬን ቀጠልኩ በመኪናም ረዥም አደረግን ይዞን የተጓዘው መኪናም ደራሽ ውሃ የሚያልፍበት ምንም መሻገሪያ የሌለው ወንዝ ዳር ላይ ጥሎን ሄድ ወንዙን የሚያሻግሩን ሰዎች እናንተ እዚህ ከመድረሳቹ አንድ ቀን በፊት አስራ ስድስት ሰዎችን ውሃው በልቷልና ሳትርበተበቱና ሳትለያዩ ሃያ ሶስት ሃያ ሶስትና የመጨረሻው ግሩፕ ሃያ አራት እየሆናቹ ተያይዛቹ ውሃው

Hijra Tube [Official]

22 Oct, 07:09


ወደሚወርድበት እየተራመዳቹ ለማለፍ ሞክሩ አለ ድንግጥግጥ አልኩ ከሁሉም ወደኋላ ቀረሁና አሏህ ሆይ ልጄንና እናቴን አደራ ብዬ ዱዓ አድርጌ ስዞር ስልሳ አምስቱ አልፈዋን ከገጠር መጥቶ አብሮን ጉዞ የጀመረው ልጅ የውሃውል መሃልን አጋምሶ ብቻውን አየሁት እየፈራው ገባው ወገቤም ሊያራምደኝ ስላልቻለ ውሃው ይዞኝ መሄድ ጀመረ አልፈውኝ የተሻገሩት ሁሉ መጮህና ማልቀስ ጀመሩ እኔም ሸሃዳዬን ያዝኩ ለአሏህም ከአባቴ ጋር ሊያጣምረኝ መሆኑን ሳስብ አልሃምዱሊላህ አልኩ ለጓደኞቼም ሆነ ስደት ላይ አብረውኝ ለመጡት ሁሉ ልጄን እንደምወዳት ንገሩልኝ ብዬ እንዲሰማቸው ብዬ እየጮህኩ ነገርኳቸው ውሃውም እኔን መውሰድ አላቆመም እኔ ደጋግሜ ሸሃዳ መያዝ ጀመርኩ ከየት ቲጣ ሳልለው አሻጋሪው ረዥም ዱላ ይዞ ጎርፉ እየወሰደኝ ወዳለው አቅጣጫ እየሮጠ ቀድሞኝ ባለህ ጉልበት ወደኔ ተጠጋና ዱላውን ያዘው ብሎ የዱላውን ጫፍ አሲዞ አተረፈኝ ከውሃው እንደወጣሁም ሁሉም እያለቀሱ ከበቡኝ ለጌታዬ የምለው ቃል ሲጠኝ የሽኩር ሱጁድ ወረድኩ

Hijra Tube [Official]

22 Oct, 06:29


#የዑምራ_ጉዞ_ ፓኬጅ ከሆሊዴይስ ቱር እና ትራቭል
#ከህዳር 15 እስከ 25  በተወዳጁ ኡስታዝ ባህሩ ዑመር መሪነት በ ኡስማን አብዱ አሰተባባሪነት
🕋7ቀን መካ
🕌3 ቀን መዲና
በተመጣጣኝ ዋጋ በልዩ መስተንግዶ ልዩ ፓኬጅ አዘጋጅቷል

ፓኬጅ
   🎫ቪዛ
   ✈️የደርሶ መልስ ትኬት
   🏩ሆቴል
   🚗ጉብኝትና ትራንስፖርት በመካና መዲና
   🧾የዑምራ አደራረግ ስልጠናና የጉዞ ቦርሳ

🛑ፈጥነው ይመዝገቡ ቀድመው ለሚመዘገቡ ልዩ ቅናሽ አለን

በተጨማሪም
   ☑️የኡምራ ቪዛ
   ☑️የሳዑዲ የአንድ አመት ቢዝነስ ቪዛ
   ☑️የሳዑዲ የቱሪስት ቪዛ
   ☑️ቲኬት

በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ። 

ለበለጠ መረጃ
   ☎️0992232323
   ☎️0984777773
   ☎️0984777775 ይደውሉ
@Holidayz_Travel
ሆሊዴይስ ቱር እና ትራቭል
አድራሻችን ቤተል ፋሚሊ ታወር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305

Hijra Tube [Official]

18 Oct, 14:35


🤲 መስጅድ አል-ነበዊ

የሕያ ሲንዋር በጋዛ ከተገደለ ከአንድ ቀን በኋላ ኢማሙ በዛሬው የጁምዓ ኹጥባ አላህ ፍልስጤማውያንን ድል እንዲያጎናጽፋቸውና እና ሰማዕቶቻቸውን እንዲቀበል ዱዓ አድርገዋል።

Hijra Tube [Official]

18 Oct, 14:27


የ61 አመቱ ጀግና የጀግኖች መሪ ያህያ ሲንዋር አቡ ኢብራሂም 💔🇵🇸 رحمك الله يا بطل

Hijra Tube [Official]

18 Oct, 13:57


የመጨረሻዋ ቅፅበት
አንድ እጁ ተቆርጦ ስለነበር በአንድ እጁ እንደ ጀእፈር አጦያር የመጨረሻዋን ትግል ታገለ !
ታገለ ጣለ ወደቀ !
እጅ አልሰጠም አልተማረከምም ነበር!
እስከመጨረሻዋ ቅፅበት አንድ እጅና አንድት ጥይት እስክትቀረው ተጋደለ!
ጥሎም ወደቀ!
ከሗላ ሆኖ የሚዋጉ ወታደሮቹን አላከም ከፊት ሆኖ ታግሎ ወደቀ እንጅ!

እኔ የማውቀው ጀግናየ ይሄ ነው!!!

Hijra Tube [Official]

18 Oct, 05:12


የእስራኤል ጦር በለቀቀው የድሮን ፉቴጅ የመጨረሻ የሲንዋርን ሰአታት ማሳየት ችሎ ነበር። በታንክና ከባድ መሳርያ ተኩስ ባደረሱበት ጥቃት አንድ እጁን አጥቶ እንኳን በስናይፐር እስከተገደለበት ቅጽበት በጽናት እየተዋጋቸው ነበር። ህዝቡን ማግዶ ከኃላ የሚቀር መሪ አልፈጠሩም፣ ከዋሻ ጀርባም ወታደር እየላከ አልተዋጋቸውም። ፊት ለፊታቸው ተዋድቋል፣ አልሸሸም፣ አልዞረም። ሲያገኙት ከነ መሳርያው ነው። እየሞተ ሳይቀር ድል አደረጋቸው..!እናትማ እናንተን ወልዳለች..!

Hijra Tube [Official]

17 Oct, 19:41


ለአላህ የገባውን ቃል ሞልቶ አልፏል !
ተቅጣጭቶ እንጅ ፊቱን ሳያዞር ከመኖር ይልቅ በአላህ መንገድ መሰዋትን ንፍቆ ሂዷል!

ሸሂዶች ህያው እንጅ ሙታን አይደሉም ባለው ቃል እንፅናና እንጅ ምን እላለሁ !

Hijra Tube [Official]

17 Oct, 19:41


በጣም ደክሞት ነበር!
አብዛኛውን እድሜውን ያሳለፈው በጨካኟ ሀገር እስርቤት ነው። ከ 61 አመቱ 22ቱ አመታት የእስር ስቃይ አመታት ነበሩ ። ቀሪዎቹ ደግሞ የመራር ትግልና መስዋዕትነት አመታት!
ያላየው ስቃይ መከራ ፈተና አልነበረም። ቤተሰቦቹ ተሰውተዋል። ስንት እንቁ የትግል አጋሮቹ ከፊቱ ፍግም ብለዋል!
መሪዎቹ ኢማሞቹ የሚሳሳላቸው ወንድሞቹ ከፊቱ ተቀድመውት ሂደዋል!
የህዝቡን መራብ መገደል መጨፍጨፍ በአይኑ እያየ ውስጡ አንብቷል !
እናም መሰደድን ማምለጥን አልመረጠም !
ለአላህ ቃል ገባ !
ለእምነቱ ለህዝቡ ነፃነት ለቁድስ እየታገለ ሊሰዋ እንጅ የዱኒያን ጥፍጥና ከቁብ ላይቆጥር!
ሊጋደል ሸሂድነትን ሊናፍቅ እንጅ በምቹ ፍራሽ ላይ ሆኖ ላይሞት !
እናም የገባውን ቃል ፈፀመ!!!

ታዲያ ምን እንበል😢 የመረጠውን ለመረጠው አላማ ወሰደው!
ሞት አይቀር!
ግና አላህ በወደደው ወሰደው!
እናዝናለን እንዴ 😢

Hijra Tube [Official]

17 Oct, 19:40


" ጠላቴ ለኔ የሚውልልኝ ትልቁ ውለታ ሲገድለኝ ነው ያኔ ሸሂድ ሆኜ ጌታየን እገናኛለሁ ። እኔ አሁን 59 አመቴ ነው ወላሂ እኔ አሁን በኮሮና ወይንም ሰው በሚሞትባቸው ሌሎች ምክንያቶች ከምሞት በጠላት ሚሳኤል ሸሂድ ሆኜ መሞትን ነው የምናፍቀው "
የህያ ይህቺን የተናገራት ከአራት አመት በፊት ነበር !

ምን ብየ ልገልፀው እችላለሁ !
አንተስ የሙራድህ ሞላ! አላህ የተመኘኸውን አላሳጣህም!
ግንኮ እኛ አንተን የማጣታችንን ስብራት መቋቋም አልቻልንም!
የኢስማኢል ሀዘን ሳይወጣልን አንተም ትተከን ሄድክ!

ምነው ባላወኩህ ባላየሁህ ባልሰማሁህ😢😢😢

Hijra Tube [Official]

17 Oct, 15:28


የእስራኤል ጦር ሬድዮ የሐማስ ንቅናቄ መሪ ያህያ አል-ሲንዋር በጋዛ ሰርጥ በራፋህ ታል-ሱልጣን በተባለ ቦታ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ መገደሉን አስታውቋል 🇵🇸🇵🇸😭😭
ዜናውን ውሸት እንዲያረገው ዱአችን ነው

Hijra Tube [Official]

15 Oct, 05:47


ሻዕባን ይባላል19 ዓመቱ ነው ሃፊዝ ነው። የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በጋዛ ድንኳኖቻቸው ላይ ባደረሱት ጥቃት ከእናቱ ጋር ትናንት ምሽት በህይወት ተቃጥሏል።😭😭😭🇵🇸🇵🇸

Hijra Tube [Official]

14 Oct, 14:04


ልዩ የኡምራ ፓኬጅ
ከሆሊዴይስ ቱር እና ትራቭል

በተወዳጁ ኡስታዝ ባህሩ ኡመር እና ወንድም ኡስማን አብዱ የሚመራ ልዩ የዑምራ ፓኬጅ አዘጋጅተን ምዝገባ ጀምረናል።

መዳረሻችንን በቅድስቲቷ መካ ካደረግን በኃላ ከመስጂደል ሀረም በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ ጥራቱና ምቾቱ የተጠበቀ ሆቴል አርፈን፣ ኡምራ ፈፅመን፣ ታሪካዊ ቦታዎቹን ጎብኝተን የ7ቀናት አስደሳች ቆይታ እናደርጋለን።

ወደ ቅድስቲቷ መዲና አቅንተም የረሱላችንን(ሰዓወ) ቀብር ዘይረን የኡሁድ ተራራን ጨምሮ ታሪካዊ ቦታዎችን የምንጎበኝበት የማይረሳ ልዩ ቆይታ ይኖረናል።

አሁኑኑ ይመዝገቡ

ስለ ጉዞው እና የፓኬጅ አማራጮቻችን የተሟላ መረጃ ለማግኘት 0984777773
0984777775
0992232323 ይደውሉልን! !
@Holidayz_Travel

ሆሊዴይስ ቱር እና ትራቭል
አድራሻችን ቤተል ፋሚሊ ታወር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305

Hijra Tube [Official]

12 Oct, 21:07


አላህ ይጠብቀን

የሱብሂ ሰላት ለምናዘገይ ሰዎች .......

"ፀሀይ እስክምትወጣ ድረስ ተኝቶ አላርም ሳይቀጥር እያወቀ የፈጅር ሶላት ያዘገየ(ያሳለፈ) ለስራ ሰዓቱ ወይም እሱ በሚፈልግበት ወቅት የሚነሳ እኔም እለዋለሁ ሶላቱ ባንተ ላይ ተመላሽ ነዉ ሶላቱ ተቀባይነት የለዉም የዉመል ቂያማ አሏህ ይጠብቀን እና ፊቱ ይመታል 1000 ጊዜ ቢሰግድ አሏህ ሶላቱን አይቀበለዉም ለዚህም መረጃዉ

إِنَّ الصَّلَاةَ كَانَتْ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ كِتَابًا مَّوْقُوتًا

ሶላት በምእምናን ላይ በጊዜያት የተወሰነች ግዴታ ናትና፡፡"

ሼኽ መሀመድ ቢን ሳልህ አልዑሰይሚን ረሂመሁሏህ

Hijra Tube [Official]

12 Oct, 20:25


#በጨለማ ብቻህን ሆነህ የተገለልክ ግዜ...

ነፍስም ወደ ወንጀል ጠሪ ናት!

የአምላክን መመልከት አፍረህ ለነፍስህ እንዲህ በላት...."...

"ጨለማን የፈጠረው አምላክ እኮ ያየኛል"....!!

Hijra Tube [Official]

07 Oct, 21:34


ትግስት አርግ ወዳጄ
ቁርአንህ ላይ ጠንክር
ሶላትህን ጠብቅ
በህመምህ ምንዳህን እሰብ
የአላህ ቀደር ብቻ ነዉ
ይች ዱንያ የፈተና ሀገር ብትሆን እንጂ ታልፍለች
የማለፊያዉ መንገድ በመንገዱ መጨረሻ ላይ እንደምታልፈዉ እርግጠኛ ሁን
የሆነ ቀን የጀነት ዛፍ ስር ተቀምጠን በዱንያ ከንቱ ነገሮች እንስቃለን!

‏‌ #رسائل_من_القرآن

Hijra Tube [Official]

06 Oct, 22:28


ምሽቱን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል የቆየ ነው - ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ
*******

ዛሬ ምሽት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው የመሬት ንዝረት ለ18 ሰከንድ ያህል መቆየቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦ ፊዚክስ ስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም አስታውቋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በመዲናዋ የተከሰተው የመሬት ንዝረት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገድ አማካይነት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ በአዲስ አበባ የተከሰተው የመሬት ንዝረት መሆኑን አውቆ፤ የእለተ እለት እንቅስቃሴውን በተረጋጋ መንገድ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን ዶ/ር ኤልያስ ሌዊ በተለይ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

በፈንታሌ ተራራ አካባቢ ከምሽቱ 2 ሰአት ከአስር ደቂቃ ከሶስት ሰከንድ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ሞገዱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ አዲስ አበባ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ንዝረት መፍጠሩንም ነው ዶ/ር ኤልያስ ያስረዱት።

አሁን የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተበት የፈንታሌ አካባቢ ለመሬት መንቀጥቀጥ የተጋለጠ አካባቢ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ኤልያስ፤ አካባቢው ብዙ ነዋሪ የሌለበት መሆኑንም ተናግረዋል።

ተቋሙ ተጨማሪ መረጃዎችን የማሰባሰብ ስራ እየሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት ዶ/ር ኤልያስ በቀጣይ ዝርዝር መረጃዎችን ተቋሙ እንደሚያቀርብ እና እንዲህ ያለ አደጋ ሲያጋጥም የቤት ቋሚዎች በተለይ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ላይ ያሉ ሰዎች ኮለኖች አካባቢ መጠጋት፣ ጠረጴዛ ስር መግባት፣ ሊፍት አለመጠቀም፣ ውጪ ላይ የመብራትና መሰል ምሶሶዎችን አለመጠጋት እንደሚያስፈልግ ዳይሬክተሩ መክረዋል።

በጌታቸው ባልቻ

Hijra Tube [Official]

06 Oct, 19:54


የመሬት መንቀጥቀጥ ተመሣሣይ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሚደረጉ ዱዓዎች፦

اللهم أعوذ بك من التردي والهدم والغرق والحرق، وأعوذ بك أن يتخطبني الشيطان عند الموت وأعوذ بك أن أموت في سبيلك مدبرا أو أموت لديغا

بسم الله الذي لا يضر مع اسمه شيء في الأرض ولا في السماء وهو السميع العليم

اللهم لا تقتلنا بغضبك، ولا تهلكنا بعذابك، وعافنا قبل ذلك

Hijra Tube [Official]

06 Oct, 19:32


መሬት መንቀጥቀጥ መንስዔው ምንድነው?

ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

«በነዚህ ቀናት በተለያዩ አቅጣጫዎች የተከሰቱት የመሬት መንቀጥቀጦች፤ አላህ ጥራት ይገባውና ባሮቹን ለማስፈራራት እና ለማስጠንቀቅ ከሚያሳያቸው ምልክቶች አንዱ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ከመሬት መንቀጥቀጥ እና ሌሎችም ሰዎች የሚጎዱ እና የተለያዩ ጉዳቶችን የሚያስከትሉ እና ሰዎችን የሚያስከፉ ክስተቶች ሁሉ ከሺርክ እና ከአመፅ መንስኤዎች የተፈጠሩ ናቸው።» [📚መጅሙዕ ፈታዋ ወመቃላት (9/149)]

Hijra Tube [Official]

02 Oct, 20:40


"ከከሳሪዎች ሁሉ የከሰረ ብሎ ማለት ለሰዎች መልካም ስራውን እያሳየ ከጅማቱ ደምስር በላይ ለሱ ለቀረበው አካል(አሏህ) መጥፎ ስራውን የሚያሳይ ነው።"

ኢብን አል-አዕራቢይ رحمه الله

Hijra Tube [Official]

27 Sep, 13:30


አስደሳች ዜና📣📣📣

📌📌አዱራህ የተርቢያና የቁርአን ማዕከል ለ2017 አዳሪ ትምህርት ምዝገባ ጀምሯል።

👉ቁርአን 15 ጁዝ ከተፍሲር ጋር እንዲሁም ከ10 በላይ የሀዲስና ኡሉም አሸርኢያ ኪታቦች ይሰጣሉ።

👉ለወንዶችና ለሴቶች በተለያዩ ቅርጫፎች

👉ጥብቅ የተርቢያ ስልጠናዎች

ጉዞና ሸልማቶችን

ሁሉንም በአንድ አመት በአዱረቱ አል መክኑና እንዲሁም የተደራጀ የኦንላይን ትምህርት እንሰጣለን።

ለመመዝገብ
📍📍በአካል አንፎና ቤተል በሚገኙ ቅርጫፎች ዘውትር በስራ ሰአት

በስልክ ቁጥር
0945777755/0945777744 ፈጥነው በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ

በቁርአን ልዕልናውን ከፍ ያደርገ ትውልድ መፍጠር የዘውትር ህልማችን ነው

በቴሌግራም ይቀላቀሉን https://t.me/+A5Uw-iDEC443YWI0