Orthodox Tewahdo profile photo @orthodoxprofilicpicture Channel on Telegram

Orthodox Tewahdo profile photo

@orthodoxprofilicpicture


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ኦርቶዶክስ ነዎት ?
ፕሮፋይል የሚያረጉት ፎቶ አጥተው ተጨንቀዋል ?
በ እግዚአብሔር ስም እንጠይቃል ይቀላቀሉን ለ ወዳጆም ያጋሩ
"ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሔር"
t.me/orthodoxprofilicpicture
@orthodoxprofilicpicture_bot
ሌሎቹ ቻናሎቻችን ይቀላቀ

Orthodox Tewahdo profile photo (Amharic)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ኦርቶዶክስ ነዎት ?ፕሮፋይል የሚያረጉት ፎቶ አጥተው ተጨንቀዋል ?በ እግዚአብሔር ስም እንጠይቃል ይቀላቀሉን ለ ወዳጆም ያጋሩ"ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሔር" t.me/orthodoxprofilicpicture @orthodoxprofilicpicture_bot ሌሎቹ ቻናሎቻችን ይቀላቀ

Orthodox Tewahdo profile photo

09 Feb, 03:32


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)

ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፣ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፣የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፣ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፣የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣በጾም፣በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፡፡

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን

እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ አለብን፣አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፣አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፣ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፣ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣በድርቅ፣በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፡፡

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፣እንድናበጃት፣እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፣ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ... ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፡፡

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፣በዚህ ሁሉ ተግባራችን  እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፣ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፡፡
 
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት

ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፣ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፣በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፣ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣የመሬት መንቀጥቀጥ፣የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ.... ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፣ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ  ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፣እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፣ምህላችንንም ይቀበልልን፡፡

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!“
  
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት
ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

Orthodox Tewahdo profile photo

03 Feb, 19:50


ሳምራዊቷ ሴት ነች


የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፬

፬በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት።
፭ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤
፮በዚያም የያዕቆብ ጕድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጕድጓድ አጠገብ እንዲህ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ።
፯ከሰማርያ አንዲት ሴት ውኃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም። ውኃ አጠጪኝ አላት፤
፰ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማ ሄደው ነበርና።
፱ስለዚህ ሳምራዊቲቱ። አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።
፲ኢየሱስ መልሶ። የእግዚአብሔርን ስጦታና። ውኃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፥ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት።
፲፩ሴቲቱ። ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ?
፲፪በእውኑ አንተ ይህን ጕድጓድ ከሰጠን ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? ራሱም ልጆቹም ከብቶቹም ከዚህ ጠጥተዋል አለችው።
፲፫ኢየሱስም መልሶ። ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤
፲፬እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት።
፲፭ሴቲቱ። ጌታ ሆይ፥ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውኃ ስጠኝ አለችው።
፲፮ኢየሱስም። ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነዪ አላት።
፲፯ሴቲቱ መልሳ። ባል የለኝም አለችው። ኢየሱስ። ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ፤
፲፰አምስት ባሎች ነበሩሽና፥ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ባልሽ አይደለም፤ በዚህስ እውነት ተናገርሽ አላት።
፲፱ሴቲቱ። ጌታ ሆይ፥ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ አያለሁ።
፳አባቶቻችን በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም። ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው።
፳፩ኢየሱስም እንዲህ አላት። አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።
፳፪እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን።
፳፫ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤
፳፬እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።
፳፭ሴቲቱ። ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።
፳፮ኢየሱስ። የምናገርሽ እኔ እርሱ ነኝ አላት።
፳፯በዚያም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ መጡና ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተደነቁ፤ ነገር ግን። ምን ትፈልጊያለሽ? ወይም። ስለ ምን ትናገራታለህ? ያለ ማንም አልነበረም።
፳፰ሴቲቱም እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደች ለሰዎችም።
፳፱ያደረግሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እንጃ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን? አለች።
፴ከከተማ ወጥተው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
፴፩ይህም ሲሆን ሳለ ደቀ መዛሙርቱ። መምህር ሆይ፥ ብላ ብለው ለመኑት።
፴፪እርሱ ግን። እናንተ የማታውቁት የምበላው መብል ለእኔ አለኝ አላቸው።
፴፫ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ። የሚበላው አንዳች ሰው አምጥቶለት ይሆንን? ተባባሉ።
፴፬ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።

Orthodox Tewahdo profile photo

03 Feb, 07:09


ይህች በመጽሐፍ ቅዱስ በእኩለ ቀን ብቻዋን ከጌታ ዘንድ የተማረች እድለኛ ሴት ማናት?

መልሱን በሀሳብ መስጫዉ ላይ ያስቀምጡልን🙏

Orthodox Tewahdo profile photo

02 Feb, 10:18


መልካም ዕለተ ሰንበት🙏

Orthodox Tewahdo profile photo

28 Jan, 19:57


እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።

Orthodox Tewahdo profile photo

25 Jan, 18:51


ደብረ ይድራስ 

ዘመነ ሰማዕታት  (ከ70-313 ዓ.ም) ሲሆን ኔሮን፣ መክስምያኖስ፣ ድምጥያኖስ፣ ማርቆስ አውሬልየስ፣ አርያኖስ ዲዮቅልጥያኖስ ዋና የክርስቲያን አሳዳጆች ነበሩ። ቅዱስ ጊዮርጊስ በ 277 ዓ.ም. በፍልስጥኤም አውራጃ ልዳ (ሉድ) የተገኘ ቆራጥ ተጋዳይ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሰማእታት ካስገኘችው መስተጋድል ክብር ወቅዱስ ሲቀ ሰማዕታት ዋናው ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ የስሙ ትርጉም ገበሬ (መስተገብረ ምድር) ማለት ነው ይላል ገድሉ። ሊቃውንቱ የሃይማኖት ገበሬ ብለውታል። ሌላው ስሙ ኮከብ ብሩህ ማለት ሲሆን የአሕዛብን ጣዖት በወንጌል አብርቷልና። 

የቅዱሱን ዜና ገድሉን የጻፈው ቅዱስ ቴዎዶጦስ ከሠለስቱ ምዕት ሊቃውንት አንዱ ነው።

ዱድያኖስ እንደ ሰም አቅልጦ እንደ ገል ቀጥቅጦ ከሮም እስከ ፋርስ በሚገዛበት ወቅት "እኔ ክርስቲያን ነኝ" ብሎ በአህዛብ መካከል ለምስክርነት ቆመ። በሃያ ዓመቱ ተጋድሎ ጀመረ። ሰባ ነገሥታትን አንቀጠቀጠ። በተጋድሎው ፋርስን አስደነቀ።

ሰባት ዓመት መከራን ተቀበለ። ሥጋውን አሰቅሎ በብረት ተቸነከረ፣ የብረት ጫማ አጭምተው የብረት እሾኽ ላይ አስኬዱት፣ ሰባ ችንካሮች የጋለ የብረት ምሰሶ ላይ አጋደሙት፣ በመንኩራኩር ፈጭተው በጉድጓድ አተሙት፣ ከሞት ተነሣ፣ በብሩት አልጋ አስተኝተው እሣት አነደዱበት፣ ደሙ እሣቱን አጠፋው፣ በመንኩራኩር ፈጭተው በይድራስ ተራራ (ምድረ በዳ) በተኑት። ተገላገልን ብለው ተመለሱ። አብሯቸው እየሮጠ ተመለሰ። አንድን ሰው የሚያደርግ አምላክ አለኝ አለ። ዛሬ ጥር 18  ይኽ የይድራስ ተራራ ገድሉ ይታሰባል። 

ቅዱስ ጊዮርጊስ ቁጥሩ ከምእመናን ወገን ሲሆን፣ ለወጣቶች አርአያ ነው። በሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በካቶሊክ በአንግሊካን ሳይቀር የታወቀ ነው። ቅዱስ ጊዮርጉስ ዓለም አቀፍ ሰማእት ይባላል። የቅዱሱ ሰማእት በረከት አይለየን። 

ንዋይ ካሳሁን

Orthodox Tewahdo profile photo

25 Jan, 17:57


Saved by @download_it_bot

መሥተጋድል ጊዮርጊስ:በገና መዝሙር
7.07 Mb

Orthodox Tewahdo profile photo

25 Jan, 17:42


Saved by @download_it_bot

መሥተጋድል ጊዮርጊስ:በገና መዝሙር

Orthodox Tewahdo profile photo

25 Jan, 14:24


በረከቱም ከእኛ ጋር ይሁን አሜን ።

Orthodox Tewahdo profile photo

24 Jan, 22:04


Ethiopian Orthodox Tewahdo Church 😍

Orthodox Tewahdo profile photo

22 Jan, 19:21


ጥያቄ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታ  ኹለት ጊዜ ስለ ራሱ ጥምቀት ተናግሯል።  የትኞቹ ናቸው ጥቀሳቸው።

Orthodox Tewahdo profile photo

21 Jan, 16:30


ባለፈዉ የጠየቅነዉ ጥያቄ መልስ

ሰለስቱ አበይት ጉባኤያት
   1.ጉባኤ ኒቅያ
    2.ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
     3.ጉባኤ ኤፌሶን
1፦ጉባኤ ኒቅያ
    ጊዜ   325 ዓ.ም
      ቦታ ኒቅያ
      የተሰበሰቡ ሊቃውንት 318
       የመናፍቁ ስም አርዮስ
       አስተምህሮው ወልድ ፍጡር በመለኮቱ
   ውሳኔ፡ጸሎተ ሃይማኖት ምስለ አብ በመለኮቱ
  ከአባቱ ጋር አንድ የሆነ
2፦ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
    ጊዜ፣381 ዓ.ም
     ቦታ ፣ቁስጥንጥንያ ከተማ
     የተሰበሰቡ ሊቃውንት ብዛት፣150
      የመናፍቁ ስም መቅዶንዮስ
       አስተምህሮው መንፈስ ቅዱስ ሕፁፅ
  የጉባኤው ሊቀመንበር ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
የጉባኤው ውሳኔ፣ነአምን በመንፈስ ቅዱስ በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ተጨመረ።
3፦ጉባኤ ኤፌሶን
    ጊዜ፣431 ዓ.ም
      ቦታ፣ኤፌሶን
      የተሰበሰቡ ሊቃውንት ብዛት 200
      የመናፍቁ ስም፣ንስጥሮስ
      አስተምህሮው፣ሁለት ባህሪይ ፣ሁለት አካል
     አኮ ወላዲተ አምላክ አላ ወላዲተ ሰብእ
     የጉባኤው ሊቀመንበር ፣ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ ዓምደ ሃይማኖት
ውሳኔ፣አንድ አካል አንድ ባህሪይ ተዋህዶ

Orthodox Tewahdo profile photo

20 Jan, 19:31


በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል በዓለ ጥምቀቱ በሰላም ተከብሮል በአንዳንድ ቦታዎች አሳዛኝ ዜናዎችን ሰምተናል ከእነሱም መካከል


1- በሐዲያ ዞን የጊንበቾ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን የጥምቀት እና ደመራ ማክበሪያ ቦታቸውን በገፍ በመቀማታቸው በየደብራቸው እንዲያከብሩ የተገደዱ ሲሆን በዓለ ጥምቀትን ጥቁር በመልብሰ አሳልፈዋል።

2-በደርባ ከተማ ከታቦት ማደርያ ላይ የደብር አስተዳዳሪ እና ሁለት ሚሊሺያዎች ተወስደው ተገደሉ
"ግድያ የተፈፀመባቸው የደርባ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ናቸው" ብለው ለሚድያችን የተናገሩት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ሁኔታው የፈጠረው ድንጋጤ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። (መሠረት ሚድያ )

3- ጎጃም ስናን ገበያ ምሥራቅ ጎጃም ከተራም አልተከበረም፣ ጥምቀትም አልተከበረም፣ የቃና ዘገሊላ የቅዱስ ሚካኤል በዓል አልተከበረም


ከሁሉም በላይ ልብ የሚሰብረው እና የሚያቆስለው ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ነው

Orthodox Tewahdo profile photo

20 Jan, 06:13


ወይንኬ አልቦሙ
የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም

በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፥ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች፤

ኢየሱስም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።

የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት፡— የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም፡ አለችው።

ኢየሱስም፡— አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡ አላት።

እናቱም ለአገልጋዮቹ፡— የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፡ አለቻቸው።

አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።

ኢየሱስም፡— ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው፡ አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው፡ አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።

አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።

አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፡—

ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል፡ አለው።

ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ። (ዮሐ 2፥1- 11)

የሰውን ችግር ተረድታ ለልጇ የምታሳስብ፣ ልመናን የምታቀርብ፣ መልስ የምታሰጥን እናት የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁንልን።

ልጆቿ እንድንሆን የረዳን፣ ፍቅሯንም በዕድሜ ዘመናችን ያበዛልን፣ ምስጢሩንም የገለጸልን መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ለዘለዓለም የከበረ፣ የተመሰገነ ይሁንልን።

አማላጅነቷ፣ ጸሎቷ፣ ፍቅሯ፣ በረከቷ ከሁላችንም ጋር ጸንቶ ይኑር!

አሜን!

ከ ዲያቆን ቸርነት

Orthodox Tewahdo profile photo

19 Jan, 19:33


ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡” አለ።

Orthodox Tewahdo profile photo

19 Jan, 18:22


ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ!
እንኳን አደረሳችሁ

Orthodox Tewahdo profile photo

19 Jan, 18:05


እንኳን ለእናታችን ልደት አደረሳችኹ!

ዳግም የምንወለድባት ባሕረ ዮርዳኖስ ዛሬ ተወለደች። ማሕፀኗን ቀደሰች።

ብዙ እናቶች ልጆችን ይወልዳሉ። ሲወልዱ ግን ዘጠኝ ወር መጽነስ የተፈጥሮ ግዴታቸው ነው።
እንወለድባት ዘንድ ዛሬ የተወለደችው ባሕረ ዮርዳኖስ ግን ዕርግና ሳይወስናት፥ ለመውለድ ዘጠኝ ወር መጽነስ ሳያስፈልጋት በየቀኑ በየሰዐቱ...ልጆችን በክርስትና የመውለድ ጸጋ ተጎናጽፋ ዛሬ ተወለደች።

Orthodox Tewahdo profile photo

19 Jan, 17:45


ይህንን ቻናል ለወዳጅ ዘመድ ለጓደኛ ለቤተሰብ በመጋበዝ ይህንን የመሳሰሉ እና ሌሎችም የተለያዩ ቆንጆ እና አስተማሪ የሆነ ስዕለ አድህኖዎች እና ፎቶዎች እንዲደርሳቸው አድርጉ

Orthodox Tewahdo profile photo

19 Jan, 17:06


ወለደነ ዳግመ እማይ ወእመንፈስ ቅዱስ

ዳግመኛ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ወለደን

Orthodox Tewahdo profile photo

11 Jan, 16:05


እንኳን ለአባታችን አባ ሊባኖስ አመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በረከታቸዉ ይደርብን።

Orthodox Tewahdo profile photo

11 Jan, 15:26


ቤተልሔም የጌታ የተወለደበት የአኹን ኹኔታው። ድንጋዩ ግርግር የሚባለው ነው። ለመልሱ ፍንጭ እንዲኾን ነው።

Orthodox Tewahdo profile photo

09 Jan, 18:02


ታህሳስ 6 (ቅዱስ ስምዖን ጫማ ሰፊው)
(በሶሎሞን አያሌው)

ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ “ዓይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት ሑለት ዓይን እያለህ ሲዖል ከምትገባ ይልቅ አንድ ዓይና ሆነህ መንግሥተ ሠማያት ብትገባ ይቀልሃል” ብሎ የተናገረውን አምላከዊ ቃል የተገበረ ቅዱስ ሰው ነው፡፡

በአንድ ወቅት ልታሰናክለው የመጣችን ሴት ዓይቶ በየዋህነት አንድ ዓይናውን በወስፌ በማውጣት የጌታን ቃል ተግብሯል፡፡ ይህ ቅዱስ አባት በነበረበት ዘመን የነበሩ አይሁዳውያን ክርስቲያኖችን ይፈታተኑ የነበረበት ዘመን ስለነበር አዲስ ኪዳንን እየመረመሩ በክርስትና ሃይማኖት ላይ ይሳለቁ ነበር፡፡

በዚህም “እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወዲያ ተተከል ብትሉት ይታዘዝላችኋል” የሚለውን ቃል በመያዝ እስኪ እነዚህ ክርስቲያኖች ይህን ቃል በተግባር ያሳዩን እንደሆን እኛም ቤተ አይሁድን ለቀን ወደ ክርስትናው እንመለሳለን ካልሆነ ግን የክርስትና ሃይማኖት እራሱ በሐሰት ላይ የተመሠረተ ነው በማለት አልሙዔዝ በተሰኘው ግብጻዊ ገዢ ፊት ጳጳሳቱን ጠየቋቸው፡፡ ጳጳሳቱም አርጅተው የነበሩ ገዳማትን እናድስ ዘንድ ፍቀድልን ብለው አልሙዔዝን ጠይቀውት ስለነበር እንግዲያውስ ይህን የአይሁዳውያኑን ጥያቄ መልሱና ገዳማቶቻችሁን ታድሳላችሁ እምነታችሁንም በምድረ ግብፅ ማስፋፋት ትችላላችሁ ይህን ማድረግ ባትችሉ ግን እምነታችሁም ከንቱ ነው እነዚህ አይሁዳውያን በእናንተ ላይ ይሰለጥናሉ አላቸው፡፡ ጳጳሳቱም በፍጽም እምነት መላ ምእመኑን ለሦስት ቀናት ሱባዔ በማወጅ በጸሎት ተጉ፡፡

በሦስተኛውም ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለፓትርያርኩ ተገልጣ ቅዱስ ስምዖን የተባለ ጻድቅ ሰው እንዳለና እርሱን ይዘው አምካታም ወደ ሚባለው ተራራ እንዲሄዱ አዘዘቻቸው፡፡ ቅዱስ ስምዖንም በቦታው በመገኘት የአምካታም ተራራን በማንቀሳቀስ ወደ ምስራቅ ግብፅ ተነሥቶ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡

በዚህ ተዓምርም ክርስትና ድንቅ ሃይማኖት መሆኗ ተመሰከረ፣ ፈሪሳውያኑም አፈሩ፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንም በቅዱስ ስምዖን ጫማ ሰፊው አማካኝነት የአምካታም ተራራ በተዓምር የተንቀሳቀሰበትን ቀን በማሰብ በዚህ የገና ጾም ላይ ሦስት ቀን ጨምራበታለች፡፡

የጻድቁ በረከት ይደርብን፡፡

Orthodox Tewahdo profile photo

09 Jan, 18:02


አብነ አብርሐም ፓትሪያርክ እና ጫማ ሰፊው ቅዱስ ስምኦን ናቸው።

በረከታቸው ይደርብን።

Orthodox Tewahdo profile photo

09 Jan, 15:54


እነዚህ ቅዱሳን አነማን ናቸው ? የሰሩትስ ተአምር ምንድን ነው?

Orthodox Tewahdo profile photo

07 Jan, 16:22


ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ።

ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ። ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ። ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት። ይህን ወዷልና፤ (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ 66፥17)።

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኔታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ።

Orthodox Tewahdo profile photo

07 Jan, 14:36


ላሊበላ

Orthodox Tewahdo profile photo

07 Jan, 13:11


ገና  (ጌና)

ገና  ቃል መነሻው ግሪክኛ ነው። በተለይ የምሥራቁ ኦርቶዶክስ የነገረ መለኮት ትምህርት እድገት ከግሪክኛ ቋንቋ ጋር በጥብቅ የተያያዘ ነው። በቅዳሴም ይኹን በሌላ ጸሎት ላይ ሳንተረጉም የምንጠቀምባቸው ቃላት በርካታ ናቸው። በዚኹ መሠረት "ገና" ወይም "ጌና" የሚለውን ለጌታችን ልደት እንጠቀማለን።

ጌና γέννα ልደት ፣ የሕጻን መወለድ የሚል ትርጉም አለው። የጌታን መወለድ ለማመልከት ሲሆን Χριστούγεννα (ክሪስቱ ጌና) ይላሉ። ልደተ ክርስቶስ ማለት ነው።ገና ስንል የክርስቶስን ልደት ብቻ የሚያሳይ አድርገን ወሰድነው። በትክክለኛ ትርጉሙ ልደተ ክርስቶስ ብለን መጠቀም ይቻላል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምስጢር ላይ ጌና የሚለውን ቃል ተጠቅሟል።

መልካም በዓል

ንዋይ ካሳሁን

Orthodox Tewahdo profile photo

06 Jan, 17:59


የቀኑ ድባብ

Orthodox Tewahdo profile photo

03 Jan, 19:00


አባ ወርቅነህ ተሰማ አረፋ😥

🔰አለቃ ተሠማ ወልደ አማኑኤል/አባ በገና/

     የበገናው ሊቅ አለቃ ተሰማ በቀድሞው የወሎ ክፍለ ሀገር እርቄ በምትባል አነስተኛ መንደር ውስጥ በ፲፰፻፸፭ ዓ.ም ነው የተወለዱት። አባታቸው ወልደ አማኑኤል ዘረፉ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ ሰገዱ ገብሬ ይባላሉ። አለቃ በዚህች በተወለዱባት አነስተኛ ከተማ ውስጥ ሆነው ከወላጆቻቸው ሳይርቁ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የተማሩ ሲሆን እድሜያቸው ለአካለ መጠን ሲደርስም ሚስት አግብተው ቤት ንብረት አፍርተው ኖረውባታል።

•••
     የመጀመሪያ ልጃቸውን ከወለዱ በኋላ ግን በበጌ ምድር ውስጥ ወደሚገኝ ደራገር ወደ ተባለ አካባቢ ሄደው ከዜማ መሳሪያዎች ሁሉ ቁንጮ የሆነውንና ፣ ከኦሪት ዘመን ጀምሮ ስብሐተ እግዚአብሔር የሚደርስበትን ፣ እርኩሳን መናፍስትን አባርሮ መረጋጋት የሚያድለውን የበገና ድርደራን ለመማር ተነሱ። አስበውም አልቀሩ ወደ በጌ ምድር ተጉዘው ከመንፈቅ ላለፈ ጊዜ ትምህርቱን አጥንተው ወደ ቀያቸው ተመለሱ። ነገር ግን ቤት ንብረት ወዳፈሩበት ቀያቸው ሲመለሱ ልቡናቸውን ፍቅረ እግዚአብሔር አሸፍቶት ስለነበር ጥቂት ጊዜ ቆይተው ፈጣሪያቸውን ብቻ በሙሉ ልብ የሚያገለግሉበትን የምንኩስና ሕይወት መርጠው በመመነን የቃል ኪዳኗ ታቦት ወዳለችበት ወደ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ሄዱ።

የአባታችንን ነብስ ቅዱሳን አባቶቻንን ካሉበት አጠገብ ያሳርፍልን።

Orthodox Tewahdo profile photo

03 Jan, 00:49


የአባታችንን ነፍስ በገነት ያኑርልን

'አባ ወርቅነህ ተሠማ'

Orthodox Tewahdo profile photo

02 Jan, 19:03


ቅዱስ አባታችን አብነ ተክለ ሐይማኖት።

Orthodox Tewahdo profile photo

31 Dec, 15:57


#ሃይ_አበ_ዘቅዱስ_ቄርሎ_፸÷፳፩ (70:21)

በማይመረመር ምሥጢር እንደኛ በማህጸን መጸነስን ወደደ። እርሱ ሰው እንደመሆኑ በማኅፀን ሳለ በባሕርየ መለኮቱ በሰማይ በምድር ከምድርም በታች ሙሉ ነው። በማይመረመር በማይነገር ጌትነቱም በአብ ዕሪና ይኖር ነበር።
የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው ሁሉ በላይ በታች ያሉ ፍጡራንም በመሀል እጁ ናቸው። አሸናፊ ፈጣሪ እርሱ እንደከሀሊነቱ ሁሉን ያዝዛቸዋል።



ከ መ/ር ሰሎሞን ንብረት ገጽ

Orthodox Tewahdo profile photo

31 Dec, 04:00


መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ።

Orthodox Tewahdo profile photo

31 Dec, 00:29


ብሥራተ ገብርኤል፡ ታኅሣሥ ፳፪
እንኳን አደረሳችሁ!

Orthodox Tewahdo profile photo

30 Dec, 13:01


መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ።

Orthodox Tewahdo profile photo

30 Dec, 04:00


እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ወርሃዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!!

Orthodox Tewahdo profile photo

20 Nov, 16:33


ሚካኤል አባቴ ❤️

Orthodox Tewahdo profile photo

17 Nov, 09:57


ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት አባት ማነው ?

Orthodox Tewahdo profile photo

17 Nov, 07:53


ሰናይ ሰንበት ❤️

Orthodox Tewahdo profile photo

16 Nov, 10:21


❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

Orthodox Tewahdo profile photo

16 Nov, 07:29


ሙሉው መዝሙረ ዳዊት

Orthodox Tewahdo profile photo

16 Nov, 04:04


👆👆ከላይኛው ምስል ጋር የተያያዘ 👆👆

Orthodox Tewahdo profile photo

16 Nov, 04:04


👇👇ከታች ያለውንም ምስል ይመልከቱ👇👇

Orthodox Tewahdo profile photo

15 Nov, 14:00


ደብረ ቁስቋም

ኅዳር ፮ ቀን የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት፣ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን አስከትላ ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት የስደት እና የመከራ ዓመታት በኋላ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቁስቋም ላይ ያረፉችበት ዕለት ይከበራል፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከጌታችን ኢየሱስ ጋር በቁስቋም ተራራ ስድስት ወራትን ያረፈች ሲሆን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኅዳር ፮  የእነርሱን ስደትና ወደ ሀገራቸው እስራኤል መመለሳቸውን በማስታወስ ታከብራለች፡፡

Orthodox Tewahdo profile photo

13 Nov, 19:04


ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ቅዱስ አባት ማነው?

Orthodox Tewahdo profile photo

13 Nov, 04:17


#ORTHODOX_PROFILE_PHOTO

Orthodox Tewahdo profile photo

11 Nov, 16:45


https://t.me/Orthodox_profile_photo

Orthodox Tewahdo profile photo

11 Nov, 12:44


ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ቅዱስ አባት ማነው?

Orthodox Tewahdo profile photo

08 Nov, 18:16


ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት አባት ማነዉ?

Orthodox Tewahdo profile photo

08 Nov, 17:20


እንደምን አመሻችሁ ወንድሞች እና እህቶች መንፈሳዊ የሆኑ ቻናሎች እና ግሩፕ ያላችሁ በ @Welde_kirkos ላይ አናግሩኝ እና አብረን እንስራ

Orthodox Tewahdo profile photo

07 Nov, 16:03


ወንድሞች እና እህቶች ጽጌ ማርያም የምትባል እህታችንን በምድራዊ ህይወት በፈተና ቦታ ድንግል ትጠብቅሽ እጆቿን ዘርግታ እያላችሁ በጸሎታችሁ አስቧት ::

Orthodox Tewahdo profile photo

05 Nov, 16:48


ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ የፈጸመልንን የማዳን ሥራ በመዘከር ታከብረዋለች።

Orthodox Tewahdo profile photo

04 Nov, 16:32


"አሥር አውታርም ባለው በበገና ዘምሩለት" መዝ.32(33)2
24/02/2017

Orthodox Tewahdo profile photo

31 Oct, 16:09


Orthodox Tewahdo profile photo pinned «ከቻናሉ left እያላችሁ የምትወጡ ጥፋታችንን ንገሩን እንድናስተካክል»

Orthodox Tewahdo profile photo

31 Oct, 15:44


ድንግል ማርያም ያደረገችላችሁን ተአምር መስክሩ !!
በ Comment section

Orthodox Tewahdo profile photo

26 Oct, 19:13


እመቤታችን ማርያም ❤️ 😍

Orthodox Tewahdo profile photo

22 Oct, 16:30


ሚካኤል አባቴ ❤️