𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴 @furqan_oficial Channel on Telegram

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

@furqan_oficial


▫️ወደ ኸይር ነገር ሰውን ያመላከተ እነሱ የሰሩትን አጅር
በሙሉ ያገኛል ከሰሪዎቹ አንድ አጅር ሳይቀነስ {ሰ.ዐ.ወ}

ስለዚህ እኔም በዚህ ቻናል የተለያዩ:–
#ቁርአናዊ አስተምሮቶች
#ኢስላማዊ ታሪኮችና ሀዲሶች
#ቁርአን ነክ የሆኑ wallpaper
#quote & ጥያቄና መልስ
#ጠቃሚ ንግግሮች እለቃለው።

ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ
Inbox📥 @quran_vibe
Request to join👇

ኀላእና✎ቢጫ (Amharic)

ኀላእና✎ቢጫ የመረጃው አባላት ናቸው ከፍተኛ ስህተትን እና መለያዎቹን ለመስራት የመረጃውን ሊያገኛል ይችላል። ይህም ባዕዳንም ቢጋም እንኳዳንቶችውን የሚክፉትን አሳሳቢና ሀዲሶች ለማስተማር እና ለማገኘት ይህን መረጃውን በፈጠራ ኢምሬግላንን ፣ ጽሁፊና መልሲት የሆነበትን እና ከፍተኛውን ስህተት እንዲሰጠን አስፈላጊ ሰፈር እንደሚወጣ። የአስተምሮቶች እና የጠቃሚ ንግግሮችን ለመስራት ባያችሁ እኔም በቻናሉው እንቅስቃሴ ይቻላል፤ ለመላክ ወይም ለተለያዩ ጥያቄ እንዲሰማ። እባኮትን ለመሸጥ ለዚህ ቻናሉ እና እዚህ በማልሞያ እኔም ከቻናሉ ከመላክቱ እና ከቻናሉ ከለሊቱ ጋር የሚኖር ነኝ።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

27 Jan, 03:40


🤲መንገድ ለሚወጣ ሰው ሙቂም (ነዋሪው) የሚያደርግለት ዱዓእ!

ረሱል ለመንገደኛ እንዲህ በማለት ዱዓእ ያደርጉ ነበር፦

﴿أَسْتَوْدِعُ اللَّهَ دِينَكَ، وَأَمَانَتَكَ، وَخَوَاتِيمَ عَمَلِكَ﴾

“ዲንህን፣ ታማኝነትህንና የተግባርህን ፍጻሜ በጥበቃው ስር ያደርግልህ ዘንድ ለአላህ አደራ እተውሃለው (አላህን እጠይቅልሃለው)።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሂህ ብለውታል፡ 2600

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Jan, 19:11


«መሞታቸውን አወቅኩኝ… ብቻዬን የምቀመጥበት ቦታ ፍለጋ ወጣሁ… ብቻዬን ለማልቀስ»
ዑመር ቢን ኸጧብ… ነብዩ የሞቱ እለት የተናገረው…
አንዳንዴ ውስጥህ በተለየ ስሜት ሲረበሽ… ግራ የሚገባ ሁኔታ ሲከብህ ብቻህን መሆን ትፈልጋለህ…  ለብቻህ ስሜቱን ለማስተናገድ ስትል… ከዚያ ልክ እንደዑመር  እስኪበቃህ ታለቅሳለህ… ለሀዘንህም ነፃነት ትሰጠዋለህ!!©
@Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Jan, 18:18


ቀልድ ሲነገር " የሆነ የሚያስቅ ቀልድ ልንገርህ "ብለህ ከጀመርክ አያስቅም 🤦‍♂

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Jan, 08:01


🔥የሎስ አንጀለሱ ሰደድ እሳት አደጋ ምን ላይ ይገኛል፤ ምን አዳዲስ ክስተቶችስ አሉ?

የኢቶንና ፓላሲደስ ጨምሮ በአራት ስፍራዎች ያሉ የሰደድ እሳቶች አሁንም እየነደዱ ነው። በእሳት የተቃጠሉ ቦታዎች ዝናብ እንደሚያገኙ መተንበዩን ተከትሎ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ ስጋት ተደቅኗል።🔥
©opy

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Jan, 07:20


አትዋሽ !
------------
“በሰው ላይ መዋሸት ሰውየው ሙስሊምም ሆነ ካፊር፣ መልካምም ሆነ አመፀኛ ሙሉ ለሙሉ ክልክል ነው። በሙእሚን ላይ መቅጠፍ ግን የከፋ ነው፡፡”

ኢብኑ ተይሚያ
[መጀመዑል ፈታዋ፡ 28/ 223]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 19:28


የጂል ቀልድ አትቀልድ!

በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣… ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ።  ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም]

በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።"
አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው በምርም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 19:03


ፍርድ ቤት ችሎት እየተካሄደ ሰዎች በመሀል ሲያወሩ

#ዳኛ👨‍💼 -- ፀጥታ ይከበር😡 ካሁን በሁዋላ አንዲት
ድምፅ ያሰማ ይባረራል።
.
.
.
.
.
ተከሳሽ🙇‍♂ --- "ኡኡኡኡኡኡኡኡኡ"

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 18:53


Well እንግዲህ የማታቁ ከሆነ

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡‐

“በአዛንና በኢቃም መካከል የሚደረግ ዱአ አይመለስም (ተቀባይነት አለው)።”

📚 ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3594

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 18:44


በ አዛንና በ ኢቃም መካከል የሚደረግ
ዱዓ ተቀባይ እንደሆነ ያውቁ ይሆን !😌

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 14:29


የመርሳት መድሃኒት

አሊይ رحمه الله] خرشم بن] እንዲህ አሉ፡-ወኪእ ቢን አል ጀራህን አየሁት..
በእጁ ላይ ምንም ኪታብ አይኖርም ነገር ግን እኛ ከምናፍዘው(በቃል ከምንይዘው)በላይ ያፍዛል...
በዚህ ነገር ተገርሜ ጠየቁት
"አንተ ወኪእ ሆይ ኪታብ አትይዝም፡ ጥቁርንም ነጭ ላይ አትፅፍም , እኛ ከምናፍዘው በላይ ግን ታፍዛለህ?"አልኩት

-ወኪእም በጆሬዪ እየነገረኝ እንዲህ አለኝ"አንተ አሊይ ሆይ!የመርሳትን መድሃኒት ከነገርኩህ ትሰራበታለህ?"
-እኔም'አዎ ወላሂ' አልኩት
-እሱም እንዲህ አለኝ "

ወንጀሎችን መተው ነው በአላህ ይሁንብኝ ለሂፍዝ ወንጀሎችን እንደመተው የሚጠቅም ነገር አይቼ አላውቅም"

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 11:06


የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በሁለት መቶ ፍልስጤማውያን እስረኞች የቀየራቸውን አራት የእስራኤል ሴት ታጋች ወታደሮች በቀይ መስቀል በኩል ለእስራኤል አስረክቧል።

አራቱ ታጋቾች በደርዘን በሚቆጠሩ የሀማስ ታጣቂዎች ተከበው በርካታ ነዋሪ በተገኘበት በጋዛ ከተማ ወደ መድረክ ሲወጡ ታይተዋል። ታጋቾቹ ወደ ቀይመስቀል መኪና ከመግባታቸው እና የእስራኤል ኃይል ወደአለበት ቦታ ከመውሰዳቸው በፊት እጃቸውንም አውለብልበዋል፤ ፈገግታም አሳይተዋል።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 06:31


ሙተነቂብ ሴት ያለችበት ቤት ዘው ብላቹህ የምትገቡ ወንዶች ግን ምናቹን ነው የሚያማቹህ 🥲

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Jan, 03:03


አንድ አይሁዳዊ ሙስሊሞችን ፊትና ውስጥ
ለማስገባት ይፈልግና ወደ ሙስሊሞች ሀገር ጉዞ
ይጀመራል፡፡ ልክ እንደደረሰም የከተማይቷ ጫፍ
ላይ አንድ እረኛ ወጣት ያገኛል አስ እስኪ ፈተናውን
ከሱ ልጀምር ይላል ከብዙ ጫወታዎች በውሀላ

ሙስሊም በመምሰል ጥያቄውን ይሰነዝርበታል:-

አይሁዳዊው:- ይህ ቁርአን ግን የበዛ
አይመስልህም ለምን ግን ተመሳሳይ ተመሳሳይ
የሆኑትን ቦታዎች አጥፍተን ከ30 ጁዝ
አንቀንሰውም እንደገና 30 ጁዝ መሀፈዙ ራሱ
ይከብዳል...

እረኛው ወጣት : አዎ ልክ ነህ ግን አንድ ጥያቄ
ልጠይቅህ ቁርአን ውስጥ እየተደጋገሙ
የሚመጡትን ከማጥፋታችን በፊት ከሰውነትህ
ውስጥ ተደጋጋሚ የሆኑትን አናጠፋም!!
ለምሳሌ
☞ከአይኖችህ ውስጥ አንዱን
☞ከጆሮዎችህ ወስጥም አንዱን
☞ከእግሮችህ ውስጥም አንዱን

አይሁዳዊውም በጣም ይደናገጥና እንዲህ ይላል:

እረኛዎቻቸው አንዲህ ከሆኑ ኡለማኦቻቸው ምን ያህል ጠንካሮች ናቸው ሲል ይደነቃል ወድያውም ከተማዋን ለቆ ይወጣል ::
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Jan, 21:31


የሙስሊም ትውልዶች👋
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

ሀላፍትናችንን ዘንግተን በተኛንበትና ውድቀታችን በገነነበት በዚህ ግዜ ምነው ደከምን እንንቃ እንጂ የምንባባልበት ፕሮግራም መኖር የለበትም ብላቹ ታስባላቹ?

እንግዲያውስ ሙስሊም ነኝ የሚል ወጣት የማይቀርበትና ሁላችንም የምንገናኝበት ሰፊ የስልጠናና የውይይት መድረክ በመናረቱል ኡላ ኢስላሚክ ግሩፕ እየተዘጋጀ ሲሆን ስልጠናውን ለመውሰድ ሁላችንም ከታች ባለው ሊንክ እየገባን እንመዝገብ።

መናረቱል_ዑላ የተማሪዎች የስልጠናና የውይይት መድረክ ተሳታፊ አባላትን  መመዝገቢያ ሊንክ

🔗🔗👇👇👇🔗🔗

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScLEiLsrPmfKgQZL7Pg8ajiXM44uvlg7QdsG4ebUvojRXYOeA/viewform?usp=sharing

ለመመዝገብ ፈልጋቹ Gmail ላልከፈተላቹ መረጃቹን
@kasim_kedir1 በዚህ ሊንክ ላኩልን።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር
+251913055479 ይደውሉ

ስልጠናው የሚሰጥበት ቦታ ከምትሞሉት Address አንፃር የሚወሰን መሆኑን እንገልፃለን።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Jan, 19:40


በቡሀይራ ጠቅላይ ግዛት ቁርኣንን ይዞ፣ ከአላህ ቃል ጋር ተቃቅፎ ይህንን ዓለም ተሰናበተ። አንድን ነገር እያዘወተረ የሞተ በዛው ሁኔታ ላይ ይቀሰቀሳል::
t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Jan, 18:51


ከሱረቱል ዋቂዓህ አያዎች መካከል ሁሌ ደስ እያለኝና ፈገግ እያልኩ የማነባቸው ሁለት አያዎች አሉ እነሱም አያ 22 እና 23 ናቸው :: 😁

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Jan, 18:26


ጌታዬ ሆይ

መልካም መመለስን ወዳንተ መልሰን።
ከመፈተናችን በፊት ፣ ከመታመማችን በፊት ፣ ከመደህየታችን በፊት፣ ከመሞታችን በፊት ...
በራሳችን በሰላሙና በጤና ጊዜ ወደራስህ መልሰን።
t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 19:02


አል ኢማሙጦበራኒ ከጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ رضي الله عنهما
እንደዘገቡት ነቢዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ብለዋል፥

ሙእሚን ከሰዎች ጋር -በቀላሉ- ይግባባል፤ ሰዎችም ከርሱ ጋር በቀላሉ ይግባባሉ።
ከሰው ጋር የማይግባባና ሰዎችም ከሱ ጋር መግባባት የማይችሉ ሰው እርሱ ዘንድ መልካም ነገር የሌለ -ክፉ- ሰው ነው!
የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ ማለት ሰዎችን ይበልጥ የሚጠቅም ሰው ነው)
ጦበራኒ:-5949

ዛዱል መዓድ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 18:45


ሴቶች በሷ ቦታ ብቶኑ ምን ይሰማቹህል just እውነቱን ንገሩን

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 18:31


ፈጥኖ የመለሰ 👇

በኩንያ ስሟ ወይም መጠርያዋ ኡሙ ሃቢባ በመባል የምትታወቀው የነብዩ ሚስት ማን ትባላለች?

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 18:06


ትርጉም 😤

ችግሩ አፋችን or ምላሳችን ያመጣብን ሊሆን ይችላልና ምላሳችንን እንቆጥብ እንጠንቀቅ ነው ዋና ሃሳቡ አሁንስ ገባቹህ ☹️

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 12:28


ከሰርጉ ቡሃላ ሰውየው የት እንዳለ አይታወቅም አሉ አድራሻው ጠፍቷል ተብሏል ሚስቲቱም አላየሁም ብላለች አሉ በሕይወት ይኖራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን 😂

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 12:20


አስባቹታል በሰርጉ ቀን ከሚስቱ አጠገብ ሆኖ ይሄን የቁርአን አያ ሲቀራ i can't ሰውየው ግን ይመቸው 🤣
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 08:31


“የሴቶችን ሚና(ክብር) አቅልሎ የሚመለከት ሰው…  ህፃንነቱ ያለእናት እንዲመለስበት እመኛለሁ።” [ነጂብ መህፉዝ]

እንደምታዩት አይደለም… አንዳንዶች  ሚስቶቻቸውን ከቤት እቃ ጋር ያስተካክሏቸዋል…  እናቶቻቸውን እንደሚወዱ ቢናገሩም… በተግባር እንደ ተራ ሰራተኛ ሲያመናጭቋቸው ትመለከታላችሁ።  የጃሂሊያው ዓለም ያለቀቃቸው ግን ደግሞ "ቀርተናል፣ ተምረናል" ለማለት የማያፍሩ ሰዎች ያጋጥሟችኋል…  ስለነዚህ "ምን አለበት የህፃንነት ህይወታቸው  ያለ እናት ቢመለስባቸውና ክብራቸውን ቢረዱት"… እንላለን…
©abdu_rheman_aman

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 03:57


ጌታዬ ሆይ ፀሀዩ ጠፍጥፎ ያጥቁረኝ...ታክሲ አንከራቶ በመከራና በግፊያ እንዳገኝም ይሁን ...ዝናብና ፀሀዩ ይፈራረቅብኝ ብቻ ከዚ አልጋ አላቀኝ(ቆሜ ልሂድ) ...የሚል ዱዓ ሰምታቹ ታውቃላቹ ? ኒዕማው አልገባንም ።

አልሃምዱሊላህ🥰

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Jan, 03:03


ሰላም ያሳደርከን ጌታ ሰላም አውለን

መሳአል ኸይር ❤️

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 22:42


قُمِ ٱلَّيْلَ إِلَّا قَلِيلًا □

:ሌሊቱን ሁሉ ጥቂት ሲቀር ቁም፤ [ስገደ] ፡፡

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 19:16


ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም እና ረመዳንም እየደረሰ ስለሆነ ቀዷ ያለባቹህ ከወዲሁ ብጨርሱ ጥሩ ነው

መልካም ለይል 🥀

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 18:38


"መታለፍ የለለበት አስገራሚ ገጠመኝ"

✍️እውቀት በመፈለግ ይኳትን የነበረ አንድ ወጣት የሚመገበው ምግብ ለሶስት ቀን በማጣቱ በአንዲት ጠባብ መንደር ገብቶ ሪዝቁን መፈለጉን ተያያዘው ተርታ ከተቀመጡ የተንጣለሉ የሀብታም ግቢዎች ውስጥ የአንድ ግቢ በር ተከፍቶ ኩሽና ውስጥ የተጋገረ ዳቦን ተመለከተ እጁን አስገብቶ አወጣ ትንሽ ቆርጦም አፋ ውስጥ እንዳስገባ እየበላ ያለው ሀራም መሆኑን በማስታወስ ምግቡን ትቶ ወደ እውቀት ማግኛው ስፍራ ሄደ የእለቱን ትምህርት እንደጨረሰ ሼኹ ወደርሱ በመዞር የማግባት ፍላጎት እንዳለው ጠየቁት ሶስት ቀን በተከታታይ ምግብ ለራሴ ያላገኘሁ እንዴት ማግባት እችላለሁ ሲል መለሰ እሳቸውም ቅድም አንዲት ሴት መጥታ ባሏ እንደሞተባትና ልጃገረድ ልጅ ከብዙ ሀብት ጋር እንደተወላት በተጨማሪም ለመልካም ሰው እንድድርላት ነግራኛለች እኔም ላንተ ለመዳር ወስኛለሁ አሉት በሀሳቡ ተስማማ

ኒካሁ ሊታሰር ወደሴትዬዋ ቤት አመሩ ምግብ ቀረበ እውቀት ፈላጊው ወጣትም ያለቅስ ጀመር ለምን እንደሚያለቅስ ሲጠየቅ እንዲህ በማለት መለሰ

《ከሰአታት በፊት አሁን የቀረበውን ምግብ ልበላ በሀራም መልኩ እዚህ ቤት ውስጥ ገብቼ ነበር አላህን ፈርቼ ለአላህ ብዬ ተውኩት በሀላሉ መልሶ ስለሰጠኝ ተገርሜ ነው የማለቅሰው 》

《አንድን ነገር ለአላህ ብሎ የተወ የተሻለን ነገር አላህ ይተካዋል》

{ረሱል አለይሂ ሰላም }

ወደ ኸይር መንገድ ማመላከት የሁሉም ሀላፍትና ነው ዳእዋውን ተደራሽ ለማድረግ የአባላት ቁጥሩን ያብዙ>>

ከወደዳቹት 👍
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 16:02


2025 ላይ የቀነሱ ነገሮች ብዬ ልፅፍ አልኩና ሳስበው ምንም የቀነሰ ነገር የለም የኔ ኪሎ ብቻ ነው የቀነሰው 😭

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 13:13


ያ አሏህ ....ለእናቴ ጥሩ አኽላቅ ያላት : በዲኗ ጎበዝ :
ቆንጆና ሷሊህ ምራት ስጣት።

አሚን 🤲😁

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 13:03


የህቴ ባል ለናቴ አማች ከሆነ የኔ ሚስት ለናቴ
ምኗ ናት 🤔 የሆነ ዱዓ ላደርግ ፈልጌ ጠፍቶኝ ነው 😅

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 11:22


ሀዋሳ ላይ ላላቹ እና ለልጆቻችሁ ሴት አስጠኚ የምትፈልጉ በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት ለቤት አገልግሎት ጀምረናል ለበለጠ መረጃ @Emur64 በዚህ አካዉንት ማናገር ትችላላቹህ 👍

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 08:40


አሜሪካ ቲክቶክን ዘጋች።

' ቲክቶክ ' የተባለው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ እስከ ዛሬ እሁድ ድረስ እንዲሸጥ ካልሆነ ግን እንዲታገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል።

በዚህም ቲክቶክ በመላ አሜሪካ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሰራ ተደርጓል።

መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው።

በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል በዚህም አሁን ቲክቶክን መጠቀም አይችሉም " የሚል ፅሁፍ ነው የሚታየው።

©tikvahethiopia

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Jan, 03:03


ምክር ለእህቶች

አል ሸይኽ ዐብዱ አልረዛቅ አል በድር رحمه الله:

ሴት ልጅ የእስልምና ስርአቶችን ተላብሳ ከኖረች ለራሷም የተከበረና ላቅ ያለ ኑሮ ትኖራለች በመሀበረሰቧም ዘንዳ የተላቀችና ከፍ ያለች ሆና ትኖራለች።..


ነገር ግን ወደ ፈተና በሚጣሩ ሰዎች ከተፈተነችና ከነሱ ጋር አብራ ከሄደች ግን እራሷም ጠፍታ ለሌሎችም መጥፋት ሰበብ ትሆናለች ..

ደግመከእለታት አንድ ቀን እቺን የዱንያን ሀያት እንደምትሰናበተው ታስታውስ ያኔም በዚያው ቆንጆ በሆነው አካሏ ፈታኝ በሆነው ውበቷና ለራሷ በምትዋብለትና ወንዶችን በምትፈትንበት አካሏ ላይ ይህ ቀን ይመጣባታል :

  🔸ጉድጓድ ውስጥ ተጣላለች
  🔸 አፈር ይጫንባታል
  🔸ቁንጅናዋም ሆነ ወዟ ይረግፋል
  🔸አካሏንም ትላትል ይበሏታል

በዚያች ጉድጓድ ላይም በሰራችው ስራና በዱንያ ሀያቷ ላይ ባሳለፈችው ነገር እስረኛና ዋስም ትሆናለች ،

አዎ ከእርሷም በፊት ህንፃዎችን ያስዋቡ እጅግ በርካታ ሴቶች ነበሩ ግን በስተመጨረሻ መኖሪያቸው ቀብር የሆኑ !

ሙስሊም የሆነች ሴት አላህን ፈርት ለዚህ አስፈሪ ቀን ዝግጅት ትዘጋጅ ይላሉ።
©

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Jan, 18:33


እውነተኛ ታሪክ

አንድ ሰው ነበር እና 5 ሴት ልጆች ነበሩት ፣
እናታቸው በድንገት ትሞታለች ከዚያም አባትዮው ሌላ ትዳርም አያምረኝ በማለት እነዚያን አምስት ሴት ልጆች በማሳደግ ላይ ግዜውን ያሳልፋል ።
ልጆች እያደጉ ሲመጡ እና ለአቅመ ሂዋን ሲደርሱ ለመጀመርያ ልጁ ባል ይመጣላታል ።
ከዚያም ይህች ልጅ እሷ አባቷን መንከባከብ እንደምትፈልግ እናም ትዳር እንደማትፈልግ ትናገራለች ከዚያም
ተከታዬቿ አራቱም በተከታታይ አግብተው የሞቀ ትዳር ይዘው መኖር ይጀምራሉ ፣

ትልቂቱ እህታቸውም አባታቸውን በመንከባከብ ብዙ ግዜ ታሳልፋልች
ከዚያ አባታቸው አጀሉ ይደርስና ወደማይቀረው ሞት ይቃረባል ።
በዚህን ግዜ አባት ቤቱን እሷ እንድትኖርበትና እህቶቿ እንዳይካፈሏት ተናዞ ይሞታል ።

ከዚያም ከሞተ በኃላ ለእህቶቿ ቤቱን ለታላቅ እህታቸው አባታቸው ስጦታ እንደሰጣት ይነገራቸዋል ነገር ግን መቀበል አልፈለጉም ውርስ ነው ውርስ ነው ያለምንም መስፈርት ይገባናል አሉ ።

ታላቅ እህታቸውም እሽ ውሰዱ ሀቃችሁ ነው አለቻቸው ።
ከዚያም ቤቱ ተሸጠ ( ሸጡት )
የዚህን ግዜ ይህች እህታቸው ቤቱን የገዛውን ሰው አገናኙኝ ኪራይ ቤት እስከማገኝና እስከምወጣ እቤቱ ውስጥ እንዲቆይ ይፈቅድልኝ ዘንድ ልጠይቀው አለች
ከዚያም አገኘችውና እባክህን ለተወሰነ ወራት ፍቀድልኝ ኪራይ ቤት አግኝቸ እስከምወጣ ድርስ ትለዋለች እሱም አብሽሪ እስከፈለግሽው ግዜ ድረስ ተቀመጭ ይላታል ።

መኖር ጀመረች ።
ከእለታት አንድ ቀን የቤቷ በር ተቆረቆረ ስታይ ያ ቤቱን የገዛውን ሰው ነበር ደነገጠች እሷ ያሰበችው ከቤቴ ውጭ የቆየሽው ግዜ ይበቃሻል እሚል ነበር የመሰላት ፣ ነገር ግን አልነበረም

ቤቱን በስምሽ አድርጌዋለሁ ከተስማማሽ መህር ይሁንና ላግባሽ እፈልጋለሁ ካልተስማማሽ ስጦታ ሰጥቸሻልሁ ይላታል ።

እሷም በጉዳዩ ላይ እንዲታስብበት ግዜ እንዲሰጣት ጠየቀችው እሽ አለ።
ከዚያ እስቲኻራ ሰግዳ አስባበት የትዳር ጥያቄውን ተቀብላ ታገባዋለች ።

ሰውየውም በጣም ሀብታም እና ድነኛ አኽላቁ ያማረ ሰው ነበር ።

ይህች ልጅ ለወላጅዋ መልካም ስለሰራች ስለዋለች አላህ በዚሁ በዱንያ ምንዳዋን አሳያት ።

የመልካም ስራ ዋጋ መልካም እንጅ ሌላ አይደለም ።


ለወላጆች በምናደርገው ነገር መቼም ቢሆን ማማረር የለብንም አሏህ ለነሱ ከዋልንው በላይ ለኛ ይውልልናል ::

መልካም ለይል 🫶
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Jan, 13:37


በሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ መኖሪያ ቤቶችና ሌሎች ሕንፃዎች ተቃጥለዋል። በውስጡም በጋዛ ሲሳለቁ የነበሩ የ ትላልቅ Hollywood አክተሮች ቤትም ተቃጥሏል ::

በግዙፉ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 10 ከፍ ብሏል።

በእሳት አደጋው የደረሰው የኢኮኖሚ ጉዳት ወደ 150 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱ ተነግሯል።

ገና ሁሉም የጁን ያገኛል ☝️

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Jan, 11:35


ሸይኽ ሷሊሕ አል-ዑሰይሚይ

"ጁሙዓ አሏህን የመታዘዝ ቀን ናት። በእርሷ ውስጥ አሏህ ዱዓን የሚቀበልበት፣ ባሪያው የጠየቀውን የሚሰጥበት፣ ምኞቱን የሚያገኝበትና ፍላጎቱን የሚቸርበት ለየት ያለች ወቅት አለች። ስለዚህ ከእርሷ አትዘናጉ። ይህችን ወቅት በጁሙዓ እለት መገባደጃ ፀሀይ ከመግባቷ በፊት ተጠባበቋት። አላህ እንደሚቀበላቹህ እርግጠኞች ሆናችሁ ዱዓን አድርጉ። ጌታችሁ ቸር ነው።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Jan, 06:49


☑️ ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ !!

የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦
[ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ]

(ሙስሊም ዘግቦታል).

اللهم صل على محمد وعلى آل محمد

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Jan, 03:01


ሀፊዝ ኢብኑ ከሲር አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል።

《ሶላትህን ቀጥ አድርገህ ስታቆም (ስትሰግድ) ካላሰብከው መንገድ ሲሳይ ወዳንተ ይመጣል።》

📚 تفسير ابن كثير 327/2

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Jan, 02:38


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 18:08


ነገ ጁማ............ጁሙዓ ነው የቻለ በጊዜ መስጂድ ይግባ ከህፍንም ይቅራ ከግመሉም ድረሱ

መልካም ለይል

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 18:02


ለፈገግታ

🔹አንድ ቂላቂል በጣም ረዥም ሚናራን ይመለከታል። ከዚያም " ያ አላህ ! ይህን ሚናራ የሰሩት ሰዎች እንዴት ረዥም ቢሆኑ ነው ! " ብሎ ሲገረም የእሱ ቢጤ አንዱ " ዝም በል ምነኛ ቂላቂል ነህ ! አሁን  እስኪ በዚህ ምድር ላይ የዚህን ሚናራ ቁመት ያለው ሰው አለ ?? … ምድር ላይ ገንብተውት ከዚያም ከፍ አድርገውት እኮ ነው ! "
📙اخبار الحمقى والمغفلين لابن الجوزي

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 17:46


እንደቀጠለ ነው

ተጁድ......... ተጅዊድ

ቆይ ግን ኡዱ ነው ወይስ ውዱእ የሚባለው ይሄን እኔም አላቅም 😅

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 15:59


ብዙ ሃፊዞች ተሰባስበው የትኛው የቁርአን ሱራ ለመሸምደድ እንደሚከብድ እየተከራከሩ

በመጨረሻም ቀላሉ ሱራ ዩሱፍ እንደሆነ ተስማምተው ተለያዩ 🤝😁

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 14:00


የመሬት መንቀጥቀጥ ጥንቃቄው 3 ነው።

1. ከወንጀል ተውበት ማድረግ
2. ዱአ ማድረግ
3. በሸሀዳ በውዱእ አዝካር ብሎ መተኛት

ከዛ ውጭ መንግስትም በለው ማን መላሽ የለውም።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 10:43


ትርርብ ቀንሱ!

ትርርብ እና መዘዙ
@anbeb_islamic
ዝም ብዬ ሳስተውል ብዙ ሰውን አንቆ ከያዘ ነገሮች ውስጥ አንዱ ምን እንደሆነ ታቃላችሁ? በጓደኞች መካከል ያለ ትርርብ።ከድሮ ጀምሮ ያየሁት ነገር ትርርብ በጣም ብዙ ሰውን በሼም እንዲቀመጥ ያደርጋል።

የሆነ ነገር ልትሞክሩ ፈልጋችሁ መጀመሪያ ምትፈሩት የቅርብ ጓደኞቻችሁን ነው።እነሱ ከሚያውቁት ማንነት ውጪ ለማምጣት ሙከራ ካደረጋችሁ ቀልዱን አትችሉትም።በተለይ የከተማ ልጆች ላይ ይበዛል።ምን አልባት በመጥፎ ስሜት ላይሆን ይችላል።just ጨዋታ ሊሆን እንደሚችል ይገባኛል።

ግን ቀልድም ቢሆን still ሰው ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።ደግሞ ቀልዷ ላይ የሆነች እውነት አለች።በመጀመሪያ ቀልድ ራሱ ሚያስቀው የሆነች እውነት ካለችበት ነው፡፡
ቋጣሪ ሰው ላይ ቀልዳችሁ ቀልዱ እንዲያስቅ ከተፈለገ እውነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።ስለዚህ እውነት መሆኑ ነው ሚያስቀው።እውነት ከሆነ ደግሞ ሚተረበው ሰው ላይ ተፅዕኖ አለው።

በመሰረታዊነት ትርርብ ችግር የለውም።እንደውም አንዳንዴ ጥቅም አለው።ያለባችሁን ችግር እንድታስተካክሉ ያረጋል።

እኔም ተተርቤ ያስተካከልኳቸው ነገሮች አሉ።በጓደኞች መካከል ምክር ሊያስጨንቅ ስለሚችል ትረባ ነው ሚያስካክላችሁ።ለጨዋታም ደግሞ ትርርብ ደስ ይላል።እየተፈራሩ ጓደኝነት የለም።

ግን አዲስ ነገር እየሞከረ እየጣረ ያለ ሰው ላይ ትረባ አይነፋም።በተለይ ስራ ነክ ነገሮች ላይ።ሊስቅ ይችላል ሚተረበው ሰው ግን እውነት እንነጋገር ከተባለ ፈሪም ያደርገዋል።
እኔ አሁን class ጨርሼ ነው እንጂ ቲክቶክ የጀመርኩት ባልጨርስ ኖሮ አልጀምርም ነበር።ምክንያቱም እስከሚሳካላችሁ ድረስ class ውስጥ ትረባውን አትችሉትም።

እንደዛውም ቢሆን ትረባው አልቀረልኝም።'ፓ ደግሞ ይህን ጀመርሽ አደል? አልተቻልሽም'' ያሉኝ ልጆች አሉ።ይቺ አሁን ጨዋታ ናት እኮ።ግን still የcomment ላይ ስድብ በምን ጣዕሙ።

አሁን የሆነ አዲስ ነገር ሊጀምር ፈልጎ ጓደኞቹን እና የሚያቀውን ሰው ፈርቶ የተቀመጠ ሰው ቤት ይቁጠረው! ''እሺ….እንደዚ ሆንሽ ደግሞ  '' ምትለዋ ንግግር ብቻ ምታሳፍረው ሰው አለ።

ከጀመረ ደግሞ ለጓደኞቹ አይናገርም።ድንገት የሆነ አጋጣሚ ላይ ነው ሚያዩት።ከዛ ሲገናኙ ጉዱ ፈላ  ....እና ባጭሩ ትረባ ቀንሱ ልላችሁ ነው ምፈልገው።እናንተን ፈርቶ አርፎ የተቀመጠ ሰው አለ።

እኔ ካነበብኩት አካፍያለው እናንተም ሼር
✍️ibro smile

@ANBEB_ISLAMIC
@ANBEB_ISLAMIC

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 08:08


ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ተቋማት ማገዳቸው ሲገርመን ጭራሽ ህዝበ ሙስሊሙን ከአክሱም እናባርራለን እያሉ እየዛቱ ነው። የነዚህ ሰዎች ድን.ቁ ^ርና ደግሞ የተለየ ነው። ሙስሊሙ ምን በወጣውና ነው ለናንተ የእርስ በርስ ሽኩቻ ማወራረጃ የሚሆነው? ለምን በዚህ ዘመን የጅ.ል ፖለቲካ ትጫወታላችሁ?
IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 06:16


#ተፈኩር

وَإِن تَعُدُّوا۟ نِعْمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحْصُوهَآ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورٌ رَّحِيمٌ○
: የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 03:28


「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
╭┄┈┈⟢
│❏ የሶስቱ አሕካሞች ማብራሪያ

│  በኢብኑ ሀሽም(امير هاشم) የተዘጋጀ
╰─────────────────╯    
ስለ ሃጅ አህካሞች
ስለ ዘካ አህካሞች
ስለ ፆም አህካሞች
🖇 ሙሉ ማብራሪያ የተሰጠባቸዉ ፀሁፎች በአንድ ላይ ሰብስቦ የያዘ!


├⎙  አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ!
╰───────────

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

09 Jan, 03:15


🌤️#ሰባሁል_ኸይር🌤️

በሙሉ ጤንነታችን ለሚመጣ
ንጋት "አልሀምዱሊላህ"

☀️
#መልካም_ውሎ☀️
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Jan, 19:01


ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም እና ረመዳንም እየደረሰ ስለሆነ ቀዷ ያለባቹህ ከወዲሁ ብጨርሱ ጥሩ ነው

መልካም ለይል 🥀

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Jan, 18:39


ደሞ እንሻላህ አላህ ካለ በቅርቡ ለረመዳን የቁርአን ኺትማ challenge አዘጋጅቼ እለቃለው ለመሳተፍ ዝግጁ ከሆናቹህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Jan, 18:20


I cant ድርሻዬን ስጠኝ part 🤣

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Jan, 17:52


እንደቀጠለ ነው

ሸይጣን.......... ሸይጧን

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Jan, 17:16


ይባስ ብሎ ዛሬ trump ስልጣኔን ስረከብ ጀሃነም ነው የማረጋት ብሎ ዝቷል አሏህ ባጭር ያስቀረው ዱዓ አድርጉላቸው ::

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 19:29


ነገ ጁሙዓ ነው የቻለ በጊዜ መስጂድ ይግባ ከህፍንም ይቅራ ከግመሉም ድረሱ

መልካም ለይል

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 18:49


ሸይኽ ፈውዛን - አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና - ዒልም ፈላጊ ተማሪዎችን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፦

እውቀትን ከመፈለግ አትሰልች።
አያያዝህ ትንሽ ቢሆን እንኳ እውቀትን ፈልግ።
መልካም ስራ ከመስራት ጋር ሲሆን ትንሹም በረካ አለበት።
እውቀት ፍለጋ ላይ መቀጠል ያለጥርጥር ኸይር ነው።
እውቀት ፍለጋ ዒባዳ ነው።
እውቀት ፍለጋ ግዴታ ካልሆኑ ዒባዳዎች የበለጠ ነው።"

[አልኢጃባቱል ሙሃማህ፡ 84]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 18:28


ለዛሬው ጥያቄወቻችን በዚህ ጨረስኩ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 18:06


ሁላችሁም ተሳተፉ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 17:43


ጥያቄ ይጀመር

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 17:00


እንደ ሙስሊም መጠቀሙ ሐራም በሆነ ነገር መነገድ አይቻልም። ሙስሊም ነጋዴዎች በሐራም ነገር አትነግዱ። አላህን ፍሩ። በሐላል ተብቃቁ። በወንጀል መተባበር ወንጀል ነው።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

26 Dec, 02:35


እዲህ አይነት ሞት አያስቀናም?

ሸይኽ መህሙድ ዐብዱለጢፍ አህመድ (አቡል ኸጣብ) የነብዩን ሐዲሶች በማጣቀስ ምክር እየለገሱ ባሉበት ወቅት በድንገት لا إله إلا الله የምትለዋን ቃል ተናግረው ነበር ወደ አኼራ የተሸጋገሩት።

በርግጥም ከዚህ የተሻለ የሚያስቀና ፍፃሜ አለ
قال الله تعالى: "يثبت الله الذين آمنوا بالقول الثابت في الحياة الدنيا وفي الأخيرة
©abdu_rheman_aman

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Dec, 19:37


ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም እና ረመዳንም እየደረሰ ስለሆነ ቀዷ ያለባቹህ ከወዲሁ ብጨርሱ ጥሩ ነው

መልካም ለይል 🥀

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Dec, 19:28


በምድር ላይ ሳሉ አላህን በማስታወስ ሕይወታችንን ላበሩልን ሁሉ አላህ ቀብራቸውን ያብራላቸው ።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Dec, 18:55


ይሄን ቪዲዮ በመስማት አደራ እላቹሀለው :
@FURQAN_OFICIAL

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Dec, 18:17


"ሒጃብ ለብሳችሁ መማር አትችሉም" በሚል በአክሱም የሚኖሩ ሙስሊም ሴቶች ከፍተኛ እንግልት ውስጥ ናቸው። የክልሉ መጅሊስ የቻለውን ያክል ቢጥርም የሚሰማው እንዳጣ በደብዳቤ ገልጿል። እምነቱን ተንተርሶ የራስን ወገን የመጨቆን የከረመ በሽታ መቸ ይሆን የሚለቀን?ተማሪዎቹ ትምህርት ቤት እንዳይገቡ ከተከለከሉ 3 ሳምንት አልፏቸዋል፣ ለማትሪክ ፎርም እየተሞላ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች ግን መሙላት አልቻሉም።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Dec, 19:45


ሳምንቱን ሙሉ ስንት ቀን እያለ በረፍታችን ቀን ጠብቆ ጉድ አረገን 😡

ከድንገተኛ መብራት መጥፋት ይሰውረን አሚን
መልካም ለይል

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Dec, 17:07


አደብ ሲባል ለንግግር ብቻ አይደለም። ለአለባበስም አደብ አለው፤ ለአካሄድም አደብ አለው፣ ለአሳሳቅም አደብ አለው፣ ለመግባባትም አደብ አለው።

(ኢብኑል ጀውዚ)

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Dec, 11:55


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

አላህን የሚፈራ : ባለው ነገር ላይ የሚብቃቃና : እራሱን የሚደብቅ [ዝቅ የሚያደርግ] ሰው አላህ ይወደዋል።

📚(ሙስሊም ዘግቦታል።)

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Dec, 03:15


"ጓደኛክን ሰው ፊት ከመከርከው ሰደብከው"

"ጓደኛክን ሰው በለለበት ከሰደብከው መከርከው"

: ኢማሙ ሻፊዒ ረሂመሁሏህ

https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

06 Dec, 19:13


እውቀትን ማሰራጨት ወንጀል እንዲማር ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነው።
: ኢብኑ ኡሰይሚን

ቢያንስ በቀላሉ ሶሻል ሚዲያ ላይ የምናገኛቸውን ኢስላማዊ ትምህርቶችን ሼር በማድረግ ወንጀላችንን እናስምር ::

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

06 Dec, 18:58


አንዳንዴም ቅዳሜና እሁድ ረፍት የሆንን ሰዎች
ለይልን ብንሰግድ ብዬ አስባለው አይመስላቹም ?

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

06 Dec, 18:13


ያንዳንድ ሰዎች ቀልድ ግን እግር እግር እያለኝ ነው

ዛሬ አንዱን ጓደኛዬን ሰሞኑን መርሳት አብዝቻለው
ምኖኜ ነው አልኩት ምን ቢል ጥሩ ነው " አግባበት " የምርህን ነው 😕

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

06 Dec, 11:06


የወንጀል ጥፍጥናን ለረጅም ጊዜ የሚያጣጥመው
ልቡ አኼራን በመዘንጋት የሰከረ ሰው ነው።»

: ኢብኑ ጀውዚይ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

06 Dec, 03:14


ለሞት መዘጋጀት

ከሙስሊም የሚጠበቀው እድሜው በጨመረ ቁጥር ይበልጥ ወደ አላህ የቀረበ ሊሆን፣ ይበልጥ ለአላህ የሚያደርገው ዒባዳ የጨመረ ሊሆን ነው። ከአላህ ጋር መገናኛው እየቀረበ እንደሆነ ሊያስብ ይገባል። መቼስ ማንም ሰው ቢሆን ሞት መቼ እጅ እንደሚያደርገው አያውቅም። ሙሉ ጤነኛ ሆኖ አንግቶ፣ የሞት ሃሳብ አንድ ከመቶ ያክል እንኳ አእምሮው ላይ ውል ሳይልበት ከዚያ ግን ከሞት ጋር ያመሸ ስንት ሰው አለ?! እና ሙስሊም የሆነ ሰው ዝግጁ ሊሆንና የተቅዋ ስንቅ ሊሰንቅ ይገባል።

:-ሸይኽ አልኸሥላን

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

05 Dec, 20:00


ነገ ጁሙዓ ነው የቻለ በጊዜ መስጂድ ይግባ ከህፍንም ይቅራ ከግመሉም ድረሱ

መልካም ለይል
😴

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

05 Dec, 19:22


ጥማት" የውሃ "ጥማት" ብቻ አይደለም አንዳንዴ ልብን የሚያረኩና የሚያረጥቡ ቃላትም "ጥማት" አለና የተጠሙ ልቦችን መልካም በሆኑ ቃላቶች አርኳቸው ።
©

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

05 Dec, 03:05


በከባድ ችግር ዉስጥ ሆኜ እንኳን ብሆን ሰዎች ስለኔ ማወቅ ያለባቸው ደስታዬን ብቻ ነው ብዬ አምናለሁ። ፈገግታዬን ብቻ ነው ማየት ያለባቸው። ቀልዴንና ተስፋ መስጠቴን ብቻ ነው መመልከት ያለባቸው።

የምደሰተው ሚስጢሩ አላህን ስላለኝ፣ በሱም ከልብ ስለማምን ብቻ ነው። በሰጠኝ ነገር ሁሉ ደስተኛ ነኝ። 'አልሐምዱ ሊላህ' ስልም ከልቤ ነው። ምን ይደረግ ብቻ በሚል ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ዉስጥ ሆኜ አይደለም።


አላህ እንዲደስትባችሁ ከፈለጋችሁ በሰጣችሁ ነገር ሁሉ ተደሠቱ።

ለከል ሐምዱ ያ ረብ!
        በዱዓቹ አውሱኝ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

04 Dec, 18:57


ራሳቹን በዚ ቦታ አርጋቹት አስቡት እስኪ ? ያአሏህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

04 Dec, 03:05


ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው?

"መኖር ማለት አለመሞት ከሆነ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እየኖረ ነው። ግን መኖር ማለት እራስን መሆን፣ ለተፈጠርክበት ዓላማ መቆም፣ ህሊናን አለመዘንጋት፣ ፍርድን አለማጓደል፣ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላው እራስን መስዋዕት ማድረግ ብሎም አርአያ የሚሆን ነገር ጥሎ ማለፍ ከሆነ ስንቶቻችን ነን በህይወት ያለነው?"

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

04 Dec, 02:55


ትናንት ታሪክ ነው፤ ነገ ደግሞ እንቆቅልሽ ነው፤ ዛሬ ግን የአላህ ስጦታ ነው! ስጦታህን መጠቀምም ማባከንም ያንተ ምርጫ ነው።

አላህ አመስግነህ፤ ስለሚያስደስትህ ነገር እያሰብክ ስሜትህን ቀይረህ የሚጠበቅብህን ሁሉ ካደረክ መቼም አይቆጭህም ምክንያቱም ታላቅነት የሚገነባው ዛሬን በመጠቀም ነው።❤️‍🩹

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Dec, 19:22


አዎ ከናንተ የሚጠበቀው በዋናነት ሼር ማድረግ ነው ለናንተ የወደዳቹትን ለሌሎችም አጋሯቸው አብረን አጅር እንፈስ

Likeም እያረጋቹ 😉

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Dec, 19:04


የሚማያሸልም ጥያቄ

እንደ አንድ የቻናል ሜምበርነታቹ ከናንተ
የሚጠበቀው ምንድነው ¿

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Dec, 17:07


አንድ ሰው ለዐብደልሏህ ኢብኑ ዲናር ምከረኝ አለው ፡ ዐብደሏህም እንዲህ አለው ፦ |"ለብቻህ በምትሆንባቸው ጊዜያቶች ላይ አላህን ፍራ "|

(ሒልየቱል አውሊያእ ፥ 10/359)

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Dec, 15:07


“ሰባት ነገሮች ለአንድ ባሪያ ከሞት በኋላ በቀብር ውስጥ እያለ የሚመነዳው ናቸው። እነሱም፦ እውቀትን ያስተማረ እንደሆነ፣ ወይም ወንዝን (ምንጭና የመሳሰሉትን በመስኖም ሆነ በቧንቧ ለሰው እንዲጠቅም) እንዲፈስ ያደረገ፣ ወይም የጉድጎድ ውሃ የቆፈረ፣ ወይም የተምር ዛፍ የተከለ፣ ወይም መስጂድ የገነባ፣ ወይም መፅሀፍ ያወረሰ፣ ወይም እሱ ከሞተ በኋላ ለሱ እስቲግፋር የሚያደርግለት (ምህረት የሚጠይቅለት) መልካም ልጅ ናቸው።” [ ረሱል ﷺ ]
📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 3602
https://t.me/furqan_oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Dec, 08:55


ሌላኛው ስተታችን

ብዙ ሰዎች "ቁርንን "ቁርን" ብለን የምናነብ አለን ይሄ ስተት ነው ማለትም ቁርአን የሚለውን በ "ع" ማንበብ አይቻልም ትክክለኛው በ ሀምዘህ ማንበብ ነው ማስረጃ ከ ቁርአን
وإذا قرئ القرآن فاستمعوا له ....

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Dec, 19:12


ስንደርስበት አጣጣልነው እንጂ አሁን
ያለንበትን ሁኔታ የሆነ ጊዜ ላይ በጣም
ስንመኘው ነበር ::
t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Dec, 19:10


ብዙ commentoችን አይቻለው but i really like this one

" ባለ ሱቁ ለምን ቸኮሌቱን በልቶ እንደማይጨርስ "

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Dec, 18:05


" ስታድግ ነው የሚገባህ " ተብላቹ ስታድጉ የገባችሁ ነገር ምንድነው ?

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Dec, 10:31


የወላጅ የገቢ ምንጭ ሐራም ቢሆንስ?
~~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
"የወላጅ የገቢ ምንጭ ሐራም ከሆነ ሊመክሩት ግድ ይላል።
~ ወይ በራሳችሁ ልትመክሩት ይገባል፣ ይህንን ማድረግ የምትችሉበት መንገድ ከኖረ ማለት ነው።
~ ወይ ሊያሳምኑት በሚችሉ የእውቀት ባለቤቶች ታገዙ።
~ ወይ ደግሞ ምናልባት ከሐራም ስራው እንዲርቅ ካሳመኑት ጓደኞቹን መጠቀም ነው።

ይህ ነገር ካልተሳካ ግን በሚያስፈልጋችሁ መጠን መመገብ ትችላላችሁ። በዚህ ሁኔታ ላይ ወንጀል አይኖርባችሁም።
ነገር ግን የገቢ ማግኛው ሐራም ከሆነ አካል ዘንድ መመገብ በመፈቀዱ ላይ ብዥታ ስላለበት በመሰረታዊነት ከሚያስፈልጋችሁ የበዛ ልትወስዱ አይፈቀድም።"

ምንጭ:– ፈታወል ኢስላሚያ: 3/45
©IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Dec, 03:05


የአላህመልዕክተኛ (ﷺ)) እንዲህ አሉ፡-

ከእኛ አንድን ሀዲስ ሰምቶ ላልሰሙት
ያደረሰን ሰው አላህ ፊቱን ያብራለት።

ሱፍያን ብን ኡየይናህ እንዲህ አሉ፡-
ከሐዲስ አስተላላፊዎች አንድንም አታገኝም በነብዩ(ﷺ)) ዱዓ ምክንያት ፊታቸው የበራ ሆኖ ብታያቸው እንጂ።

      📚 مجموع الفتاوى | لابن تيمية ١١/١

https://t.me/furqan_oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Dec, 19:11


አብሽሩ አንድ ቀን ይኖራቹሃል ተስፋ እንዳትቆርጡ 😁
ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም 🥀

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Dec, 18:27


በጣም ብዙ አይነት እድለኛ ሰው ልታቁ ትችላላቹህ ግን ከትራሱ አጠገብ ቻርጀር መሰኪያ እንዳለው ሰው እድለኛ የለም 😹

እስኪ ያለው 🤝
የሌለው 😢

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Dec, 18:20


☑️ ከፈጅር ሶላት በፊት  ሁለት ረከአ መስገድ !!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
እናታችን አኢሻ  በዘገበቺዉ ሓዲስ የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ትለናለች፦

- عن عائشة رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم - قال : ( ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها ) . رواه مسلم  -

የፈጂር ሁለት ረካዎች  ከዱኒያ እና በዉስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ ይበልጣሉ።

  📚[[ሙስሊም ዘግቦታል]]

t.me/furqan_oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Dec, 15:40


ውድ ነገር ያለቦታው ርካሽ ነው :

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Dec, 13:12


የዕለቱ መልዕክት

በዲንህ ላይ የሚያጋጥምህ ፈተና ከባድ እንደመሆኑ መጠን ዝግጅትህም ከባድ ይሁን; ዲንህን አጥብቀህ ያዝ።..ሌሎች ፈተናዎችን ልትቋቋም ወይም ሙሉ በሙሉ ልታልፍ ይምትችለው የዲን ገመድህ ጠንካራ ሲሆን ብቻ ነው !!https://t.me/Furqan_Oficial
    

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Dec, 07:44


⇛በጉዞ ወቅት ከምናደርጋቸው ዱዓዎች መካከል አንደኛው ......
«ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺃﻧﺖ ﺍﻟﺼﺎﺣﺐ ﻓﻲ ﺍﻟﺴﻔﺮ ﻭﺍﻟﺨﻠﻴﻔﺔ ﻓﻲ
ﺍﻷﻫﻞ»
«አላህ ሆይ! በመንገዴ ላይም ጓደኛየ፤ በቤተሰቦቼም ላይ ምትክ አንተ ነህ…»


⇛ይህ ማለት ቤተሰብ ተለይተን ስንጓዝ አላህ ከኛ ጋር ነው፤ ቤተሰባችንን ስንሰናበትም ጠባቂዉና ተወካያችን እሱን አድርገን ነው እንደማለት ነው፡፡ አላህን ይዞ መጓዝ ፍፁም የሆነ ሰላም አለው፤ ቤተሰብን ለአላህ አደራ መስጠት ትልቅ ዋስተና ማገኘት ነው።
☆https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Nov, 18:25


አንድ ሀበነቃ የሚባል የአረብ ሞኝ ነበር
የሆነ ቀን የሰፈሩን ሰው ላሞኘው ብሎ በየቤቶ እየዞረ እከሌ ቤትኮ ዛሬ ሰደቃ አለ ኑ ተብላቹሀል እያለ እየዞረ ለሰፈሩ ሰው ነገረና ከፍ ያለ ተራራ ላይ ወጥቶ ሰው ላይ ሊዝናናበት ፈለገ ግን ተራራው ላይ ወጥቶ ሰውን ሲመለከት እጅግ በርካታ ሰው ወደነገራቸው ሰው ቤት እየተመመ ተመለከተ 

ያኔም እህ ይሄ ነገር እውነት ሰደቃ አለ ማለት ነው ብሎ እራሱም ከሰው ተሰልፎ ወደ ሰውየው ቤት ሄደ ይባል።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Nov, 12:24


"ተቃጠልን'ኮ ባለቤት"

ሰውየው እንግዳ ሆኖ ከሰው ቤት ያርፋል። ሚስት የእንግዳው መኖር እንኳ ሳይከብዳት ባለቤቷን ከፍ ዝቅ አድርጋ ታዋርደዋለች። ባል ዋጥ አድርጎ ዝም ይላል። አቶ እንግዳ ግን ራሱን መቆጣጠር አልቻለም። ተነስቶ ሚስትን ከባሏ ፊት ጠፍጥፎ ጠፍጥፎ ለቀቃት። ባለቤት በገዛ ቤቱ ገላጋይ ሆነ።
"ምነው እንግዳ?" አለው ግራ ቢገባው።
"ተቃጠልን'ኮ ባለቤት!" አለ እንግዳው።
.
.
.
አሁን ይህንን ምን አስታወሰኝ? ባንክ ቤት ገብቼ ቁጭ ብያለሁ። አንዷ ልጇን ይዛ ገባች። ልጁ በጣጣጣም የተንቀዠቀዠ ነው። ቤቱን ባንድ እግሩ አቆመው። ሁሉን ነገር አተራመሰው። እናት ወረቀት አንስታ ልትፅፍ ስትል እጇ ላይ ያለውንም ጠረጴዛው ያለውንም በሙሉ መሬት ላይ በተነው። የወደቀውን እንኳ ሳታነሳ ወደሌላው ጥግ ሄደች። እዚያም በተመሳሳይ በተነው። እንዲሁ ላመል ያህል "ተው" ትለዋለች። እሱም አይተው፣ እሷም ጠንከር አትል። ከባንኩ ሰራተኛ ዘንድ ሆና አቀፍ አድርጋ ለመፃፍ እየሞከረች ነው። ልጁ አሁንም እየታገለ ነው። ግርም አለኝ። ልናገራት አፌ እያደረስኩ ዝም አልኩ።

እኔ ምለው! "እኔ በሶፍት እየታሰርኩ በፓስታ እየተገረፍኩ ነው ያደግኩት" የሚሉት'ኮ ቀልድ ነበር የሚመስለኝ። ይሄ ነገር እውነት ነው'ንዴ? እንዴዴዴ! ልጆቻችሁን ቆንጥጡ እንጂ። ይሄን ያህል ጨው አይደሉ! አይሟሙ! አዎ ልጅን ጨካኝ አያያዝ መያዝ አይገባም። ግን ደግሞ አሪፍና ዘመናዊ አስተዳደግ ማለት ልጅን ማጨማለቅ ማለት አይደለም። ኧረ ከፈረንጅና ከዐረብ የምትቀዱትን እየለያችሁ! ይሄ አስተዳደጋቸውን ሁሉ ማበላሸት ነው።

ደግሞም "እንዲህ ሆኜ" "እንዲህ ተደርጌ" ሲሏችሁም ያሉትን ሁሉ አትመኑ። የልጅ ወሬ ይዛችሁ ከሰው ጋር አትጣሉ። አንዱ "ልጄ ተበደለብኝ" ብሎ አስተማሪ ላይ ሽጉጥ እንዳወጣ ሰምቼ በጣም ገርሞኛል። እዚህ ላይ "ከልጁ በፊት አባትን ነበር መቅጣት" ያስብላል። ልጆች የጠየቁትን ሁሉ አትስጡ። ያሉትን ሁሉ አታድርጉ። "አይሆንምን"ም ይወቁ። ህይወት ብዙ "አይሆንም" አላት። እናንተ ብታቀብጧቸው ነገ ብዙ ልትፈትናቸው ትችላለች። ሁሉን የለመደ ትንንሹን ሁሉ እንደ በደል ይቆጥራል። በአንድ ወቅት አንድ ወንድሜ የሚገርም ነገር ነገረኝ። ልጅ እናቱን መኪና እንድትገዛለት ጠየቀ። ገዛችለች። ትንሽ ቆይቶ ሌላ ሞዴል (እንደዛ ነው ኣ የሚባለው?) ጠየቀ። "ይገዛልሃል ግን ትንሽ ቆይ" አለችው፡፡ "አሁን ካልሆነ" ብሎ ፍርጥም አለ። እሷ "አይሆንም" አለች። ገብቶ ራሱን አጠፋ። በቃ! እንደተበደለ ነው የተሰማው።እና ልጆቻችሁን ለማዘን እንኳ የማይመቹ አታድርጓቸው።
©IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

21 Nov, 13:25


Be nice for no reason.

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

21 Nov, 09:08


ሚስትህ ትሰግዳለች? ባልሽ ይሰግዳል?

ሸይኹል ኢስላም አሕመድ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–

"አንድ ሰው ሌባ ወይም ዝሙተኛ ወይም አስካሪ መጠጥ የምትጠጣን ሴት ማግባቱን ሁሉም ሰዎች የሚቃወሙ ከሆነ፤ ሶላት የማትሰግድን ሴት ማግባቱን ደግሞ በኢጅማዕ በበለጠ ሊቃወሙት ይገባል። ምክንያቱም የማትሰግድ ሴት ከዝሙተኛ፣ ከሌባና አስካሪ መጠጥ ከምትጠጣዋ የከፋች ነችና።"

[ጃሚዑል መሳኢል: 4/142]

ረሒመሁላህ! ምንኛ ያማረ ገለፃ ነው?! ግን ወንጀሉ ሶላትን ከመተው የከፋ እንደ ሺርክና ጥንቆላ ያለ ከሆነስ?! ልብ በሉ! ጉዳዩ አንድ ፆታ ላይ የሚገደብ አይደለም። ስለዚህ ሴቷም እንዲሁ ሃብት ወይም ሌላ ዱንያዊ ነገር ቢኖረው እንኳ አፈንጋጭ የሆነን ወንድ ልታገባ አይገባም። ቤተሰቦቿም እንዲህ አይነቱን ወንድ እንድታገባ ሊጫኑም፣ ሊያግባቡም፣ ሊፈቅዱም አይገባም።

አላህ ዲናችንን ለመረዳትም ለመተግበርም ያድለን።
=IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Nov, 20:10


ነገ ሀሙስ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ

መልካም ለይል 🥀

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Nov, 19:40


አሚን ያለ ተጠቀመ

እንደ ነብዩ አይነት ስነምግባር : እንደ ዑመር አይነት ግርማ ሞገስ : እንደ ዩሱፍ አይነት ውበት : እንደ ሱለይማን አይነት ጥበብ : እንደ ሱመያ ቢንት ኸይጥ አይነት ኢማን : አሏህ ይስጠን ::

የቀረ ካለ ጨምሩበት

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Nov, 18:34


በዚ ግዜ ስሜታችንን የሚረዳን ሰው ነው ያጣንው :: አይደለም ስሜታችሁን የሚረዳቹህ የሚያዳምጣቹህ ካገኛቹህ እድለኛ ናቹህ ::😔
@Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Nov, 14:46


ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐቢይ!
~
ሶሐቢዩ ሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፡-
በአንድ ወቅት ዑመር ብኑል ኸጧብ ከነቢዩ (ﷺ) ቤት ሊገቡ ፍቃድ ጠየቁ፡፡ ከነቢዩ (ﷺ) ዘንድ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያወሩ ሴቶች ነበሩ፡፡ የዑመርን ድምፅ ሲሰሙ ሒጃባቸውን አስተካክለው ሊለብሱ ተሯሯጡ፡፡ ረሱል (ﷺ) እየሳቁ ለዑመር እንዲገቡ ፈቀዱላቸው፡፡
ዑመር፡ “አላህ ጥርስህን ያስቀው የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሏቸው፡፡
ነብዩ (ﷺ)፡ “እነዚህ እኔ ጋር የነበሩ ሴቶች ገረሙኝ፡፡ ድምፅህን ሲሰሙ ወደ ሒጃባቸው ተሯሯጡኮ” አሉ፡፡
ዑመር፡ “አንተ ነህ ልትከበርና ልትፈራ የሚገባህ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!!” ካሉ በኋላ “እናንተ የነፍሶቻችሁ ጠላቶች! እኔን ትፈራላችሁ የአላህ መልእክተኛን አትፈሩምና?!” አሉ ለሴቶቹ።
ሴቶቹ፡ “አዎ ከረሱል (ﷺ) ይልቅ አንተ ደረቅና ሃይለኛ ነህ” አሉ፡፡
ከዚያም ረሱል (ﷺ) ለዑመር እንዲህ አሏቸው:– “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ! ሸይጧን በአንድ መንገድ ላይ በጭራሽ አያገኝህም፣ መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ ቢሄድ እንጂ!” [ቡኻሪ፡ 3294] [ሙስሊም፡ 2396]

ይሄ ሐዲሥ ለዑመር ጠላቶች ምቾት የሚነሳ ነው፡፡ ሺዐዎች የዑመር ስም ሲነሳ በጥላቻ እብደታቸው እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ድረስ ይሄ ነገር በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እ.ኢ.አ በ2005 ኢራቅ ውስጥ 15 ሰዎች ስማቸው ዑመር ስለሆነ ብቻ በሺዐዎች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ በርካታ ዑመሮች በሌላ ሳይሆን በስማቸው ብቻ ከስራ እንደተባረሩ ተነግሯል፡፡ ይሄ ለዑመር ያላቸው ጥላቻ እጅግ የመረረ እንደሆነ የሚያመላክት ነው።

ሌላ ነገር፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ﷺ) መስጂድ ካሉት በርካታ በሮች ውስጥ አንዱ “ባቡ ዑመር" ነው፣ "የዑመር በር”፡፡ ታዲያ ሺዐዎች ምን አሉ? “ለዑመር ካለን ጥላቻ የተነሳ ወደ መስጂዱ ስንገባ በዑመር በር በኩል አንገባም” አሉ። ይህንን የሰማ አንድ ሸይኽ ምን አለ ታዲያ? “ረዲየላሁ ዐንከ ያ ዑመር! ሸይጧን በህይወትህ ሳለህ ብቻ አይለም ሞተህም ይሸሽሃል!”
አላሁ አክበር!!!

(ኢብኑ ሙነወር፣ 03/02/2005)

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

20 Nov, 03:36


.
በየቀኑ በነጋ ቁጥር ሰዎች እንዴት አደራችሁ ሲሉን አልሀምዱሊላህ እንላለን:: ለምዶብን ብቻ አይደለም አልሀምዱሊላህ ስንል ደስ ይለናል ውስጣችንን ለማረጋጋት ከአልሀምዱሊላህ የምበልጥ ቃልም አጣን::
እንደምንም እንደር እንደምን ብቻ አልሀምዱሊላህ ምስጋና ለ አላህ አልሀምዱሊላህን ከመልመዳችን የተነሳ ችግር ሀዘኑን ሁሉ ረሳን::
አልሀምዱሊላህ ባልን ባልን ቁጥር መልካም ነገር ሲጨመርልን እንጂ ሲቀንስብን አላየንም አልሀምዱሊላህ::❤️‍🩹

በሁሉም ሁኔታችን ውስጥ የምትመሰገነው አንተ ብቻ ያ አላህ::🤍

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Nov, 19:04


ما عذرك يا تارك الصلاة
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Nov, 16:05


በሙስሀፍ ብቸ ቁርአንን መቅራት ጠንካራ ሂፍዝ ለመሀፈዝ በጣም ይረዳል ::

ምክንያቱም ወደሙስሀፉ ደጋግሞ መመልከት በራሱ የምንመለከተው ሰፍሀ ቀልባችን ላይ እንዲቀመጥ ይረዳል ::

ለዚህም ነው ቁርአን ለመሀፈዝ ከሚረዱ ነገሮች መካከል ሳንቀያይር አንድ ቁርአን ብቻ መጠቀም አንዱ የሆነው ::
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

19 Nov, 03:32


〽️የቀኑ ሶስት ሐዲሶች

①.ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿من كنَّ له ثلاثُ بناتٍ، أو ثلاثُ أخواتٍ، فاتَّقى اللهَ وأقام عليهنَّ كان معي في الجنةِ هكذا، وأومأَ بالسبابةِ والوسطى﴾

“ለሱ ሶስት ሴቶች ወይም ሶስት እህቶች ኖረውት ከነሱ ጋር አላህን በመፍራት ጥበቃ ያደረገላቸው (በመልካም የተኗኗራቸው) በጀነት ውስጥ ከኔ ጋር እንዲህ ነን በማለት ጠቋሚና የመሃል ጣታቸውን በማጣመር አሳዩ።”
📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ፡ 259

②.ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿وَمَنْ دَعَا رَجُلًا بِالْكُفْرِ "، أَوْ قَالَ : " عَدُوَّ اللَّهِ، وَلَيْسَ كَذَلِكَ إِلَّا حَارَ عَلَيْهِ﴾

“አንድን ሰው በከሃዲነት የፈረጀ ወይም አንተ የአላህ ጠላት ብሎ የጠራው እርሱ እንዳለው ካልሆነ (ፍርዱ ወይም መዘዙ) ወደራሱ የሚመለስ ቢሆን እንጂ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 61

③.ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَن كان معه فضلُ ظَهْرٍ، فَلْيَعُدْ به على مَن لا ظَهْرَ له، ﴾

“በግልፅ የሚታይ ፀጋ የተዋለለት ሰው። በግልፅ ላልተዋለለት ሰው እገዛ ያድርግ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1728

t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 19:15


የቁርአን ግብዣ
[ yassir adosari ]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 18:36


"ወንዶች ስንባል የሴቶች ቁንጅናና ውጫዊ ቅርፅ አያሳስበንም። የሚያሳስበን የስነምግባሯና የማንነቷ ውበት ነው።"
·
·
[ብዙ ይዋሻሉ!] ከሚለው ዘገባ የተቀነጨበ።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 17:11


የአላህ መልዕክተኛ ـﷺـ እንዲህ ይላሉ፦

"ከወንጀሉ ተውባ ያደረገ ምንም ወንጀል የለበትም።"

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 13:52


ከማንኛውም ነገር የተሰጣችሁት የቅርቢቱ ሕይወት ጥቅምና ጌጧ ነው፡፡ አላህ ዘንድ ያለውም (ምንዳ) በጣም በላጭና ዘውታሪ ነው። አታውቁምን?
[አልቀሶስ፡ 60]

t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 07:57


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በ2017 ምድባችሁ መቱ  ዩኒቨርሲቲ ለሆናችሁ አዲስ ገቢ(fresh) ሙስሊም እህት እና ወንድሞቻችን እና በ2016 ዓ.ል መቱ ዩኒቨርሲቲ በሪሚድያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ።

በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ ለእዚህ እንድትበቁ ላስቻላችሁ ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ አካል ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን !!


የመቱ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እናንተን ለመቀበል ዝግጅቱን ጨርሶ የናንተን መምጣት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው::

ስትመጡ የሚቀበሏቹ ወንድሞች እና እህቶች ማንኛውንም አይነት ትብብር የሚያደርጉላችሁ ይሆናል::

በምትመጡ ሰዓት ከዚህ በታች በተቀመጡት ስልክ ቁጥሮች በመደወል የሚያስፍልጋችሁን ትብብሮች  ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን::


☑️ Main Campus
1 አጅመል ነጂብ 0943595705
2 ሙጃሂድ ነፍሶ 0967017401
☑️ Bedele Campus
1 አማን ቱላ    0916332852
2 ሙክታር ጀማል  0923621116



🔴የእህቶችን ስልክ ለማግኘት ወንድሞች ጋር በዚህ 👉 0943595705 & 0967017401 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ ::

ስለ መቱ ዩኒቨርስቲው ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ማንኛውም አይነት መረጃ ለማግኘት ይህንኑ የቴሌግራም ቻናላችንን ይከታተሉ ወይም በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ::

በተጨማሪ 👇
https://t.me/meumsjoffical_page

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 06:50


የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
"ሱጁድ ላይ ተስተካከሉ። አንዳችሁ እንደ ውሻ ክንዶቹን አያንጥፍ።" [ቡኻሪይ ዘግበውታል።]
=
IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

18 Nov, 02:54


ወዳጅ የማይፀናበት፣ መሠለቻቸት የበዛበት ዘመን ነዉና አንዳንድ ጊዜ ብቸኝነትንም አስቀድማችሁ ተለማመዱት።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

17 Nov, 18:50


ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ
ተማሪዎችም ነገ ሰኞ ነው በጊዜ ተኙ 😭

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

16 Nov, 06:42


ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ወደ ሴቶች እይታውን እንዳሻው የሚለቅ ሰው ፈተና ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው።

እይታ ከኢብሊስ መርዛማ ቀስቶች ውስጥ ነው ፣ አላህ ይጠብቀንና።

አንድ ሰው ቆንጆ ሴት ባለፈች ቁጥር የሚመለከት ከሆነ ያለ ጥርጥር ልቡን ያሳምማል፤ ኢማኑ ይቀንሳል፤ የኋላ ኋላ ከማይውወጣቸው ነገሮች ላይም ይወድቃል።

[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 19/237]
©IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

15 Nov, 19:48


የረመዳን ትውስታዎች ግን በቀላሉ የሚረሱ አይደሉም እነዛ የተራዊህ ሶላቶች : አፍጥሩ : ተሃጁዱ : ሱሁሩ : በፆም የምናሳልፋቸው ቀናቶች : ከሁሉም በላይ ደሞ ኢማናችንን የምንገነባበት ወር መሆኑ : በቁራን : በዚክር በስቲግፋር ቤተሰብ በመኻደም የምናሳልፋቸው ቀኖች በጣም ተናፍቀዋል::

በነገራችን ላይ ረመዳን 3 ወር አከባቢ ቀርቶታል አሏህ ደርሰው ከሚፆሙት ከሚጠቀሙበት ያርገን ::
@Furqan_oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

15 Nov, 14:22


ሶላት የረሳ ሰው ሲያስታውስ ይሰግዳል:
የመጀመሪያውን በማስቀደም ቅደም ተከተሉን ይጠብቃል: ለምሳሌ ዙህርን ረስቶ የዐስር ወቅት ከገባ በኋላ ቢያስታውስ መጀመሪያ ዙህርን ይሰግዳል።ከዚያ ዐስርን ያስከትላል።

ዐስርን መስገድ ከጀመረ በኋላ ካስታወሰ ግን የጀመረውን ያጠናቅና ከዚያ ዙህርን ይሰግዳል።
©IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

15 Nov, 09:10


ምድር ላይ አንድ ጊዜ እንጂ ሁለቴ የመኖር ዕድል አልተሠጠንም። ይህ ዓለም ወደዚያኛ ዓለም መሸጋገሪያችሁ እንጂ ሌላ አይደለም ተብሎ ቁርጡ ተነግሮን በቁርጥ የመጣን ሕዝቦች ነን።

ስለዚህ ፣ በዕድሜያችን አንቀልድም። እስካለን ድረስ ለዲናችን እንኖራለን ። ሕይወታችን እሱ ነው። በሱ ነው። ሌላ ሕይወት የለንም ::
©MuhammedSeidAbx

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

15 Nov, 03:16


በዚህ ዓለም ውስጥ ስሜትን (የግል ዝንባሌን) አንደመተው የበረታ (የከበደ) የሆነ አንድም ነገር የለም።” :-ፉደይል ኢብኑ ዒያድ

📚 [አል‐ሂሊያ (98/8)]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

14 Nov, 19:01


ነገ ጁሙዓ ነው የቻለ በጊዜ መስጂድ ይግባ ከህፍንም ይቅራ ከግመሉም ድረሱ

ቁርአንን ማስተንተንን ከፈለጉ ይቀላቀሉ
👇
https://t.me/+BEldLJj2RM05YmQ8

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

14 Nov, 17:52


አሏህ እንዴት እንደሚወድህ ማወቅ ትፈልጋለህ ብዙ ሳቴድ እስካሁን በሂወት ያቆየህ ወደሱ እንድትመለስ እድል እየሰጠህ ነው አሁንም ቢሆን አረፈደም ::
@Furqan_oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

14 Nov, 14:43


ሁሌ ነግቶ ስቃይ ሁሌ ነግቶ ፍንዳታ ሁሌ ነግቶ ሞት እዩ የቦምብ ፍንዳታውን ይሄ ሁሉ ችለው ነው ያሉት አሏህ ሶብሩን ይስጣቸው አሏህ ይርዳቸው ::
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

14 Nov, 09:51


:- ወሳኝ ነጥብ 🤚

አንድ ሰው ሶላት ውስጥ ሆኖ የተነጀሰ ልብስ እንደለበሰ ካስታወሰ በቀላሉ የተነጀሰውን ጥሎ መቀጠል የሚችል ከሆነ (ለምሳሌ ጃኬቱ፣ ጥምጣሙ ሊሆን ይችላል) የተነጀሰውን ከጣለ በኋላ ሶላቱን ባለበት ይቀጥላል።

የተነጀሰውን ልብስ ጥሎ ለመቀጠል የማይመች ከሆነ ከነነጃሳው ሶላቱን ሊቀጥል አይገባም። ስለዚህ ከሶላቱ በመውጣት እንደገና አስተካክሎ ከለበሰ በኋላ ሶላቱን እንደ አዲስ ይጀምራል።

የልብሱን ነጃሳ መሆን ያወቀው ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከሆነ ወይም ቀድሞ ቢያውቅም ረስቶት ኖሮ ሶላቱን ከጨረሰ በኋላ ካስታወሰ ሶላቱ ምንም ችግር የለበትም።ስለሆነም እንደገና አይሰግድም።
©IbnuMunewor
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

13 Nov, 19:35


አስበሀዋል ወንጀልህ ሰማይና ምድርን የሚሞላ ሆኖ አሏህን ይሄን ሁሉ ወንጀልህን ቢምርልህ ከሱ ልቅናም ሆነ ከሱ ክብር መርፌ ባህር ውስጥ ገብታ ይዛው የምቶጣውን ያክል ውሃ አይቀንስበትም አጂብብብ ::
@Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

13 Nov, 17:33


ብቻ አንተ ከወንጀልህ ተፀፅተህ ማሃርታን ጠይቅጂ አሏህኮ.......
[ وهو الغفور الرحيم ]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

13 Nov, 14:00


ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ዜጋዋን በስቅላት ቀጣች ::

ኢራን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ የሆኑ ሰዎችን በስቅላት እንዲቀጡ የሚፈቅድ ህግ አላት::
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

13 Nov, 09:26


⭐️ሱረት ዩሱፍ

☄️"አህሰነል ቀሰስ"ብሎ አላህ ተባረከ ወተዓላ ገልጿታል።

🌸በቁርዐን ውስጥ ብቸኛዋ ታሪኩን ጀምሮ የሚጨርስ ሱራ ነው።

✍️ሙሉውን ስለ ነብዩላህ ዩሱፍ አለይሂ ሰላም ታሪክ ነው የምትተርክልን።

አተራረኩ አጂብ በሚያሰኝ ውብ በሆነ መልኩ አላህ ተባረከ ወተዓላ ተርኮልናል።

ታድያ ይህችን ሱራ ተደቡር ልናደርግ ወደድን!

🪙በተደቡር ፅሁፉ አጂብ በሚያሰኝ አገላለፁ የምናውቀው ወንድማችን #khrebin ሱረት ዩሱፍን ሊያስቃኘን ወዷል።

🎉የት ነው ምናገኘው ካላቹ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ join በሉ

👉 https://t.me/+BEldLJj2RM05YmQ8

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

13 Nov, 08:26


“በወርቅ እና በብር መጠጫ አትጠጡ። በትሪዎቿም አትመገቡ። እርሷ ዱንያ ላይ (በቀጣዩ ዓለም) ለእነርሱ (ለካህዲያን) ናት ለእኛ ደግሞ በአኼራ (በቀጣዩ አለም) ነው።”

ረሱል [ ﷺ ] እንዲህ ብለዋል፦

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5426

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

13 Nov, 03:21


በመስጠት ውስጥ ካለው በበለጠ እርካታ....ሌሎችን በማስደሰት ውስጥ ካለው በበለጠ ደስታ የትም የለም ። እኔነት ጠባብ መንገድ ነው ... ድብርት ...ወናነት እና ትርጉም የሌለው ህይወት ከዚህ ጠባብ መንገድ የተገኙ መጥፎ መሳፈሪያዎች ናቸው ። እመኑኝ የሌሎችን ቁስል በማከም ውስጥ፤ የሌሎችን ሸክም በማቅለል ውስጥ ..ሌሎችን በመርዳት ውስጥ የመኖር ጣዕም አለ ። ለሌሎች ፍቅር በመስጠት ውስጥ ተስፋ አለ ...ለሌሎች በመኖር ውስጥ መኖር አለ !

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

12 Nov, 20:11


በጊዜ ለመነሳት ትልቁ መፍትሄው በጊዜ መተኛት ነው ግን አሁን ብተኙ አይባልም 5 ሰዓት አለፈኮ ከነገ ጀምሮ ነው በሉ....

መልካም ለይል 🫶
𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴 your best choice
🙌

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

12 Nov, 19:59


በጊዜ ለመነሳት መፍትሄው ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ ወይስ ልንገራቹህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

12 Nov, 18:21


እላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት አይመን አሊ ይባላል ::ጆርዳን ላይ አለ የሚባል ቆንጆ ነበር ሰዎችም የጆርዳኑ ቆንጆ እያሉ ይጠሩታል :: ግን ከጊዜ ቡሃላ ባጋጠመው አይነናስ ምክንያት ሰውነቱ ተቀይሯል በጣም ጎድቶትም ነበር :: ዛሬም እንደሰማሁት ወደ አኺራ ሄዷል አላህ ይዘንለት ::

በሰዎች ላይ ጥሩን ነገር ባየን ግዜ ማሻአላህ ማለት እናስለምድ አሏህም ጨምሮ እንዲሰጣቸው ዱዓ እናድርግላቸው :: አይን ከቀደር ቀድሞ የመግደል አቅም አለው የሰዎችም አይን እንዳይደርስብን ሁሌም ጠዋትና ማታ አዝካር ማለት ይልመድብን ጥሩም ነገር ስናገኝ አሏህ በረካ እንዲያረግልን ዱዓ እናድርግ ችላ የምንለው ጉዳይ አይደለም አደራ ራሳችሁን ጠብቁ ::
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

12 Nov, 16:26


ሶላት በምትሰግድ ጊዜ ሰላምና ደስታ : ኹሹዕ ካልተሰማህ አደጋ ላይ ነህ ::

FURQAN TUBE

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

12 Nov, 11:55


«ሊቢያ ዳግም በከፍታ ላይ..»💪

በሰሞኑ አለምን እያስደመመ ያለው አድሱ የሊቢያ ህገ-ስርዓት ሊቢያውያን ዳግሞ ወደ ስልጣኔያቸው እየገሰገሱ እንደሆነ ማሳያ ነው ።

ሊቢያ የጀግኖች ምድር....

.ካፌወች ለቤተሰብ ብቻ የተፈቀዱ እንጅ ጓደኛዬ፣ሰራተኛዬ፣ የስራ ባልደረባዬ በሚል ተልካሻ ምክንያት አጅነብይ ጋር መተሻሸት የለም።

②.የሊቢያ ምድር የሊቢያኖች ነች ሊቢያ የሙስሊሞች ናት ሒጃብ ግደታ ነው ሒጃብ ኒቃብ በመልበሱ  ነፃነቴ ተገፈፈ የሚል አካል ካለ ወደ አውሮፓ መጓዝ ይችላል።

.መኪና ይዛ ፀጉሯን ከፍታ ወይም ጠባብ ልብስ ለብሳ የምትሔድ ሴት መኪናዋም ይቀማል እሷም ትታሰራለች።

④.ወንድ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ አውረቱን እያሳየ ሲሔድ ከተገኘ ወደ ወንድነቱ እስኪመለስ ታስሮ ይመከራል።

.ፀጉሩን አበላልጦ የቸቆረጠ ሰው ቀጥታ ተይዞ ፀጉሩ ይላጫል።

⑥ከላይ የተዘረዘሩትና መሰል ተያያዥ ድንጋጌወች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋሉ።

ይህን የተናገሩት የሊቢያ የሀገር ውስጥ ሚኒስተር
👉ኢማድ ትራበልስ ናቸው።
©nuredinal_arebi

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

12 Nov, 08:53


➙ ቢድዓ የሽርክ ጓደኛ ነው 🔖

ሽርክ የጌታን ክብር ከማጓደል ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ሙሽሪኩ ወደደም ጠላም ፣ የጌታን ክብር ማጓደሉ  ከእርሱ ጋር የማይላቀቅ ጉዳይ ነው፡፡  በዚህ ምክንያት ሙሽሪክ ፍጹም እንደማይማር ተመስጋኝነቱ ፣ ፈጣሪነቱ ፣ ሙሉነቱ የወሰነው ጉዳይ ሆኗል - የሽርክ ባለቤት ዘወትር በአሳማሚ ቅጣት እንደሚቀጣም እንዲሁ፡፡ ከፍጡራኖች ሁሉ በጣም ጠማማ ያደርገዋል፡፡ አንድን ሙሽሪክ አታገኘውም - በማጋራቱ አላህን አልቃለሁ ብሎ ቢሞግትም - የአላህን ክብር የሚቀንስ ቢሆን እንጅ፡፡

በተመሳሳይ አንድን ሙብተዲእ አታገኘውም ፣ የረሱልን ክብር  የሚያጓድል ቢሆን እንጅ - በቢድዓው ለረሱል ክብር ሰጥቻለሁ ብሎ ቢሞግትም፡፡  ተጎታች ጃሂል ከሆነ ቢድዓ  ከሱና የተሻለች ወይም ከሱና ተቀዳሚ  ወይም  እርሷ ሱና ናት ብሎ ይሞግታል፡፡ ጮሌ ከሆነ ደግሞy በቢድዓው አላህና ረሱልን ይቀናቀናል፡፡

ከአላህ ፣ ከረሱል እና ከአማኞች ዘንድ ጎደሎዎች ፡  የሽርክ ባለቤቶች እና የቢድዓ ባለቤቶች ናቸው፡፡ በተለይም ፣  ‘የአላህና የረሱል ንግግር ባዶ ቃላት እንጅ  ከእውቀት ፣ በእምነት እርግጠኛ ከመሆን የተራቆተ ነው’ በሚል አመለካከት ላይ ዲኑን የመሰረተ አካል ከሆነ፡፡

ልክ እንደዚሁ መመሳሰልን እና ለአላህ የፍጠራንን የመሰለ አካል ሊኖረው ይችላል በሚል ስጋትና ብዥታ ከፈጣሪ ላይ ሙሉ የሆኑትን ባህሪያቶችን ያራቆተ ሰው ፣ አላህ ነፍሱን በገለጸበት የተሟላ ባህሪ ተቃራኒ ጉድለትን አመጣ፡፡ 

ተፈላጊው አላማ ፡   እነዚህ ሁለት ጭፍራዎች በሀቂቃ የአላህን እና የመልክተኛውን መብት አጓዳዮች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነዚህ ሁለት ጭፍራዎች ከሰዎች ሁሉ የአላህንና የረሱልን ክብር በማጓደል ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ የአላህን ክብር ማጓደልን ፣ ለእርሱ ሙሉ ክብር እንደመስጠት አስመስሎ   ሰይጣን በእነርሱ ላይ አምታታባቸው፡፡  በዚህ ምክንያት ቢድዓ የሽርክ ጓደኛ እንደሆነ በአላህ ኪታብ  ተገልጹዋል፡፡ 


قُلْ إِنَّمَا حَرَّمَ رَبِّيَ الْفَوَاحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَالْإِثْمَ وَالْبَغْيَ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَأَن تُشْرِكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

“ጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ስራዎችን ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ሐጢአትንም ያላግባብ መበደልንም ፣ ከርሱ ማስረጃ ያላወረደበትነ (ጣዖት) በአላህ ማጋራታችሁን ፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው” በላቸው፡፡

(አእራፍ፡ 33)

ሐጢያትና ድንበር ማለፍ ጓደኛ ናቸው ፤ ሽርክ እና ቢድዓም ጓደኛ ናቸው፡፡

طب القلوب : -  ١٧٩-١٨٠
አሏህ ሁላችንንም ይጠብቀን ::

ሼር 𝖘𝖍𝖆𝖗𝖊

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

11 Nov, 20:11


ከ ሶሻል ሚዲያዎች ሁሉ ግን እንደ ቴሌግራም ትልቅ ኒዕማ አለ ?

የስንቱ ሕዝብ መድረሳ : በቀላሉ መረጃ መለዋወጫ : የጥሩ ስራ መሸመቻ እና ሌሎችም ስንትና ስንት ጥቅም አለው ::

ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይሁንልህ 🤝😁

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

11 Nov, 19:26


የ ኢማም ልጅ ስታገባ be like
FURQAN TUBE

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

11 Nov, 17:33


ቤተሰቦች የአሏህ ሰላም በናንተ ላይ ይሁን እያልኩ እስከዛሬ ሲለቀቁ በነበሩት ጥያቄዎች ላይ ብዙ ጥቅሞችን እንዳገኛቹህ ትልቅ ተስፋ አለኝ.

አሏህ ጥሩ ስራውን ይቀበለውና እስከዛሬ ጥያቄ እያዘጋጀ ሲጠይቃቹህ ለነበረው ወንድማቹህ ዱዓ አድርጉለት እና ከዚ ቡሃላ ቲኒሽ ስላልተምቻቸለት ከዚ ቡሃላ ጥያቄና መልስ አይኖርም :

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

11 Nov, 10:07


𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴 your best choice 🙌😁

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

11 Nov, 07:38


ከአብደላህ ቢን ዐምሩ (ﷺ) ተይዞ፡ ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿الراحمون يرحمُهم الرحمنُ. ارحموا من في الأرضِ يرحمْكم من في السماءِ﴾

“አዛኞችን አዛኙ ያዝንላቸዋል። በምድር ላሉት እዘኑ በሰማይ ያለው ያዝንላችኋል።”

📚 አቡ ዳውድ፡ (4941) ቲርሚዚ፡ (1924) አህመድ፡ (6494) ዘግበውታል

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

11 Nov, 03:21


« ስለውስጥ ጩኸቶቻችሁ፣ በቃላት ስለማይገለፁ ህመሞቻችሁ፣ በጥልቁ ስለምትሹት ምኞታችሁ ሁሉ አብሽሩ። የምወድሽዋ የከፋሽ፣ የተሰበርሽ፣ ድክም ያለሽ ቢመስልሽም በአላህ ፍቃድ ለደስታሽ ይነጋል። ትንሽ… ብቻ ታገሽ።
የምንወድሽ፣ የምናከብርሽ፣ የምርሽን ፈገግ ስትይ ልናይሽ የምንፈልግ አለን።  አብሽሪ! የምወድሽዋ ሰላም ለልብሽ! የምወድህዋ ሰላም ለልብህ! »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 19:27


ቁርዓን እየቀራን ሱጁድ የሚያስወርድ አንቀፅ በደረስን ጊዜ የሚባለዉ.......

اللهم لك سجدت وبك آمنت، ولك أسلمت، سجد وجهي للذي خلقه وصوره وشق سمعه وبصره بحوله وقوته، تبارك الله أحسن الخالقين ..

اللهم اكتب لي بها أجراً، وضع عني بها وزراء

واجعلها لي عندك ذخرا وتقبلها مني كما تقبلتها من عبدك داود،

ሸይኽ ኡሰይምን ረሂመሁሏህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 18:51


ቁርዓን እየቀራን ሱጁድ የሚያስወርድ አንቀፅ በደረስን ጊዜ ምንድነው የሚባለው ?

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 17:18


ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የስሜት መለዋወጥ
========================

ከ80 እስከ 90 ከመቶ ሴቶች የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት ያለው ሳምንት ላይ ምቾት አለመሰማት ያጋጥማቸዋል። መጠነኛ ራስ ምታት፣ የጡት መወጣጠር፣  ሆድ መነፋት ሊያግጥማቸው ይችላል። ልክ እንደ አካላዊ ለውጦች የስሜት ለውጦችም ይኖራሉ። መነጫነጭ፣ መከፋት፣ ከማህበራዊ ነገሮች ራስን ማግለል ...ወዘተ። እነዚህ ምልክቶች ብዙ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አያደርሱም። ይሁን እንጂ ከ20-30 አመቶ የሚሆኑት ላይ በስራቸው ወይም በትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ ይችላል።

ይህ ህመም የሚያጋጥማት አንዲት ሴት የወር አበባ ከ15 አመቷ እስከ 50 አመቷ ብታይ በህይወቷ ይሄ ህመም 420 ጊዜ ያጋጥማታል ማለት ነው። ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?

1) ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመምና የስሜት መለዋወጥ በህክምና የሚስተካከል ስለሆነ በዝምታ ከመሰቀያት ሀኪምን ማማከር።

2) ራስን መንከባከብ፣ እረፍት ማድረግ።

3) የወር አበባን ተከትሎ አንዳንድ ሴቶች ላይ የምግብ ፍላጎት ሊጨመር ወይም አንዳንድ ምግቦች ሊያምራቸው ይችላል። ሀይል ሰጪ (ካርሀይድሬት) የምግብ አይነቶች የድብርት ስሜትንና ጭንቀትን ስለሚያባብሱ በተቻለ አቅም መቀነስ።

4) ቫይታሚኖችን መውሰድ። አንዳንድ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በተለይ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አካላዊና አእምሮዊ ምልክቶችን ለመቀነስ ያግዛሉ። ከሀኪም ጋር ተማክሮ መውሰዱ ጥሩ ነው።

ዶ/ር ዮናስ ላቀው

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 15:58


ተኝተህ የምያስደነግጥ ሕልም ካየህ ይሄን አድርግ !!

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 10:14


ረሱል [ ﷺ ]እንዲህ ብለዋል፦

አንዳችሁ አመስጋኝ የሆነ ልብ፣ አላህን የምታወሳ ምላስ፣ በአኼራው ጉዳይ ላይ የምታግዘውን አማኝ ሚስት ይያዝ።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ፡ 5355

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 08:30


የራስን ብሄር በተለየ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ : የሌሎችን ብሄር የሚያንቋሽሹ : ሰዎች በብሄራቸው ተለይተው ጥቃት ሲደርስባቸው ለአጥፊዎቹ የሚከላከሉ ፖስቶችን ወይም ኮሜንቶችን ሼር : ላይክ የምታደርጉ : ዘር ላይ ያነጣጠሩ ዘረኛ ቀልዶችን በሳቅ የምታጅቡ : በየትኛውም መልኩ ለዘር ተኮር ጥላቻ ድጋፍ የምታደርጉ አካላት የወንጀሉ ተካፋይ ናችሁ ።

የራሳችሁ ዘር ላይ ቢፈፀም የማትወዱትን ሌላው ላይ ሲሆን የምታደርጉት ከሆነ የዘረኝነት በሽታ ላይ ወድቃችኋል። "ተዋት! እሷ ጥንብ ነች!"
©IbnuMunewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

10 Nov, 03:13


🪴ሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚን
አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ ፡
                  
#አስሰላሙ_ዓለይከ ሲባል 10 ሀሰናትይገኛል፡ #ወራህመቱሏህ ሲባል 20 ሀሰናት ይገኛል፡ #ወበረካቱሁ ሲባል 30 ሀሰናት ይገኛል።
ሰው ታድያ እንዴት ይህን ትልቅ ምንዳ ነፍሱን ይከለክላል?
አንድ ሰው ሰላምታ ካቀረብ በእያንዳንዱ ሰላምታ
#አንድ_ዲርሃም ይሰጥሀል ቢባል ያገኘውን ሁሉ ሰላም ሲል ታይ ነበር።
                        ===
ስለዚህ
#ሰላምታ_እናብዛ፡ ምንዳውንም እናስተንትን🌴 እኔ ሰላም ብያለሁ 🤝

اسلام عليكم ورحمة الله وبركاته.
@furqan_oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Nov, 18:30


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
ያ ጀመዓ እንዴት አመሻችሁ?!

ኢንሻአላህ! ወደ ጥያቄ የምንገባ ይሆናል፤ ተዘጋጁ!

ሌሎችም ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ share አድርጉላቸው።

http://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Nov, 16:15


Insha'allah 🥺

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Nov, 03:13


እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጁምአ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ ። ይህ የምታውቁ ብትኾኑ ለእናንተ በጣም የተሻለ ነወ፡፡
(ሱረቱ አል-ጁሙኣህ 62:9)

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا نُودِىَ لِلصَّلَوٰةِ مِن يَوْمِ ٱلْجُمُعَةِ فَٱسْعَوْا۟ إِلَىٰ ذِكْرِ ٱللَّهِ وَذَرُوا۟ ٱلْبَيْعَۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

@anbeb_islamic

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

08 Nov, 03:10


ከዝሙት ራሳችሁን ጠብቁ
===================
«ለዚህ ደግሞ ለቻለ ሰው ከትዳር የበለጠ ምርጫ የለም። ለትዳር ቅድመ ሁኔታ አትደርድሩ። መስፈርት የሚያበዛ መጨረሻው አያምርም። ከትዳር ሸሽታችሁ ዝሙት ላይ እንዳትወድቁ። ዝሙት በየትኛውም ዘመን ሰቅጣጭ ወንጀል ነው። በዚህ ዘመን ግን አደጋው ጨምሯል። በአንዱ ባለ ጌ ወንጀላችሁ በቪዲዮ ተሰራጭቶ ጭራሽ ከማትወጡበት ማጥ ውስጥ ይከታችኋል።

ሴቶች እየተሰማ ያለው ደስ የሚል ነገር አይደለም። አግቡ። እንዲሳካላችሁ ዱዓ አድርጉ። ስነ ምግባር ያለው ካገኛችሁ ሁለተኛም፣ ሶስተኛም፣ አራተኛም ቢሆን ሆናችሁ አግቡ። ሊተናነቃችሁ ይችላል። ይሄ ተፈጥሯዊ ስለሆነ ስሜቱ ለመረዳት የሚከብድ አይደለም። ይበልጥ መፍራትና መጥላት የሚገባው ግን ዝሙትን ነው።

ወንዶች አላህን ፍሩ። ከዝሙት ራቁ። ከቻላችሁ አግብታችሁ ተሰተሩ። ዝሙት ብድር ነው። ባላሰባችሁ አቅጣጫ እዳውን ትከፍላላችሁ። ደግሞም ለትዳር ዋጋ ስጡ። ለሴቶች ፈተና እየሆናችሁ ወደ ወንጀል አትግፉ።»
©: Ibnu Munewor

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 19:32


ነገ ጁሙዓ ነው የቻለ በጊዜ መስጂድ ይግባ ከህፍንም ይቅራ

የቁርአን ቻናል ተቀላቀሉ 👇
https://t.me/+BEldLJj2RM05YmQ8

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 18:56


ለዛሬ ይህን ያህል ከተጠያየቅን ይበቃል ኢንሽኣላህ ነገ እንቀጥላለን 😊

መልካም ምሽት

ፊአማኒላህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 18:50


ዛሬ ደረቅ ነገር ቢያልፈንስ እ ኢንሻ አላህ ነገ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 18:30


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
ያ ጀመዓ እንዴት አመሻችሁ?!

ኢንሻአላህ! ወደ ጥያቄ የምንገባ ይሆናል፤ ተዘጋጁ!

ሌሎችም ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ share አድርጉላቸው።

http://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 16:59


ባል ወደ ሚስቱ በሃዘን ተሞልቶ ሲገባ ሚስት ምን ሆንክብኝ ብላ ጠየቀቺው ::

እሱም:- መሪያችን እያንዳንዱ ሁለተኛ ያላገባ ወንድ እንዲገደል አዘዙ አላት....!!

እሷም" አሏህ በርግጥም ሸሂድ እንድትሆን መርጦሃል ብላው እርፍ 😳

🖇t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 12:28


በኒቃብ ጉዳይ የታሰሩ ተማሪዎች መፈታታቸው ተገለፀ!

- ሀሩን ሚድያ ጥቅምት 28/2017

ዛሬ ጥቅምት 28/2017 በአዲስ ከተማ አዲስ ከተማ ምድብ ከተማ ነክ ፍርድ ቤት ተማሪ ሰሚር መሀመድ፣ ነቢል መሀመድ፣ ሚኪያስ እና ብሩክ በነበረው የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገን ክርክር ከሰማ በኋላ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት ሳያስፈልገው እያንዳንዳቸው በብር ስምንት ሺህ ዋስትና እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

በዛሬው ዕለትም ጠበቃ አልሃምዱ ገረመው በነፃ ላደረገው የህግ ድጋፍ ጠበቃ ሙስጠፋ ምስጋናውን አቅርቧል።

በአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት በኒቃብ ምክንያት ታስረው የነበሩ ተማሪዎች እንዲፈቱ እና ጉዳዩ ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን ሀሩን ሚድያ ተከታታይ መረጃዎችን በማድረስ ላደረገው ጥረትም ጠበቃ ሙስጠፋ ሽፋ ምስጋናውን ገልጿል።
© ሀሩን ሚድያ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 12:21


ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ........

 ﴿إنَّ عِظمَ الجزاءِ مع عِظمِ البلاءِ، وإنَّ اللهَ إذا أحبَّ قومًا ابتَلاهم، فمَن رَضي فله الرِّضى، ومَن سخِط فله السَّخطُ﴾

“ትልቅ ምንዳ (አጅር) የሚገኘው ትልቅ የሆነ መከራ ሲገጥም ነው። የላቀው አላህ ህዝቦችን (ሰዎችን) በሚወዳቸው ግዜ ይፈትናቸዋል። ፈተናውን የወደደ አላህ ይወደዋል። ፈተናውን የጠላ አላህ ይጠላዋል።”

📚 ቲርሚዚ (2396) እና ኢብኑ ማጃህ (4031) ዘግበውታል

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 09:07


"  ከናተ በላጩ ቁርአንን አውቆ ያሳወቀ ነው"

        [ሀቢቡና ሰለዋቱ ረቢ ወሰለም]


     
    🔺አል - አማና  ኦንላይን የቁርአን  ማዕከል
በተለያዩ ምክንያቶች ቁርአንን አልቀሩም እንግዲያውስ አል - አማና ኦላይን የቁርአን ማአከል ባሉበት ሆነው ቁርአንን  ሊያስተምሮ ቤቶ ድረስ መቷል እንግዲያውሰ ከእርሶ የሚጠበቀው በእጆ ያለውን 📱ሞባይል ብቻ በመጠቀም ቁርአንን ይማሩ
    
   መድረሳችን ብቁና ልምድ ባላቸው ኡስታዞች እየሰጠ ያለውን የቂርዐት ሁኔታ በ3 ደረጃ የከፋፈለ ሲሆን ፦
 
🔺በደረጃ 1
ለጀማሪዎች ቃኢዳ መሰረታዊ የቁዐን አነባበብ
🔺በደረጃ 2
የቁርዐን ንባብ ከመሰረታዊ የተጅዊድ ትምህርት ጋር እንዲሁም
🔺በደረጃ 3
የቁርዐን ሒፍዝ

📚የቁርአን ትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ

  ♦️አንድ ተማሪ ከተመዘገበ በኋላ የተመደበለት ኡስታዝጋ በጉግል ሚት ወይም በዙም አፕልኬሽን ኦንላይን ወይም ላይቭ የሚቀራ ይሆናል።
 
   ♦️ እንዲሁም አንድ ተማሪ በመዓከሉ የሚሰጠውን ትምህርት በአግባቡ ተከታትሎ ከጨረሰ የመዓከሉን እውቅና ያለው ሰርከትፌት ይበረከትለታል
 
   የቁርዐን ጊዜው በሳምንት 5 ቀን እንዲሁም በቀን ለ30 ደቂቃ አንድ ተማሪ የሚቀራ ይሆናል።

በአላህ ፍቃድ በዚህ በተወሰነ ጊዜ ቁርአንን  ያነባሉ

📕 በቴሌግራም ለመመዝገብ
                    👇  
       @Alamanamerkez

📕 ማንኛውም ሃሳብ አስተያየት ካሎት
                  👇
      @Allamanaabot

📕 የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
                    👇
     https://t.me/Alamanamerkez34

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 06:01


እድሜ ውድ ነች ለዚህ ውድ ነገር ደግሞ ከጀነት ውጪ ምንም አይነት ዋጋ እንዳትቀበልበት ይላሉ።

:-ኢብኑ አል ቀይም
🖇t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

07 Nov, 04:06


ቁርዓን መስማት በልባችን ውስጥ ውብ የአበባ ስፍራ እንደመገንባት ነው ። ከሌላው ጫጫታ ተነጥለን በልባችን የአበባ ስፍራ እንደሰት ዘንድ ከቁርዓን ጋር እንወዳጅ ።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

06 Nov, 20:00


ይህንንን በምን ቃል ትገልፁታላችሁ ???

ጫማ የለም ስለዚህ ይህ ፍልስጤማዊ በጎ ሰው ለህፃናቶቹ አይታሞች ጫማ የሚሰራላቸው ከጣውላ እንጨት እየጠረበ ነው።

እሺ ይህንን ስሜት በምን ቃል ትገልፁታላችሁ😭
🔗http://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

04 Nov, 11:21


አንዱ ደግ ሰው እንዲህ ይላል፦በስራ ከተማ ስገባ ገበያዎቹ ተዘግተዋል። መንገዶቹ ባዶ ናቸው።የበስራ ሰዎች ሆይ! እኔ የማላውቀው ዒድ አላችሁ እንዴ?' አልኩኝ።

:-እንደሱ አይደለም። ነገር ግን ሐሰኑል በስሪይ መስጂድ ውስጥ ሰዎችን እያስተማረ ስለሆነ ነው' አሉኝ።"

t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

04 Nov, 04:14


ለደረቀ ልብ ማረስረሻ
ወደ ጀነት መዳረሻ
የውስጥን ህመም መፈወሻ
ሀዘን ጭንቀትን ማስረሻ
#ቁረአን ነውኮ የሙዕሚኖች ጋሻ ።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Nov, 17:27


Nobody sees your pain but everyone sees your mistakes.

t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

03 Nov, 05:04


ውበትን የፈለገ መልካም ስነምግባር ይበቃዋል ::

t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 19:38


ቆይ እናንተ react የምታደርጉት ቀልድ ሲለቀቅ ብቻ ነዋ ለማንኛውም ስቆ ዞር የለም ከስር የተቀመጠውን ሊንክ እየገባቹህ ጆይን በሉ..ውድድር ነው እንዳሸንፍ አትፈልጉም 🥹👇

https://t.me/+km3RHFI6ixg5MTE0

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 19:25


ብዙ ሃሳቦችን እያየሁ ነው ሁሉም በጣም አሪፍ ተሞክሮዎች ናቸው ጀዛኩሙሏህ. ቁርአን ለመሃፈዝ ፍላጎቱ ያላቹ እላይ ኮሜንት ላይ እየገባቹህ ልምዶችን መውሰድ ትችላላቹህ ይጠቅሟቹሃል ተጠቀሙባቸው

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 18:32


እስኪ የቁርአን ሂፍዝ ልምድ ያላቹህ ወይም ቁርአን የሃፈዛቹህ እህት ወንድሞቼ እስኪ commnet ላይ ስለ

1.እንዴት መሃፈዝ እንዳለብን
2.እንዴት ሙራጃ ማድረግ እንዳለብን

እና ሌሎችም ልምዶችን አካፍሉን አደራ ቲኒሽም ቢሆን ይጠቅማል

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 15:52


እንዴት ነው ምንዛለቀው ጎበዝ 😁

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 10:13


ለወላጆች ሁነኛ ሶደቃ
~
ለሞቱ ወላጆችዎ ሶደቃ መፈፀም ይፈልጋሉ? አቅሙ ላለው ሰው የውሃ ችግር ባለበት አካባቢ ውሃ ማውጣት ትልቅ ሶደቃ ነው። አገልግሎቱ እስካለ ድረስ አጅሩ አይቋረጥም።
* ሰዕድ ብኑ ዑባደህ ረዲየሏሁ ዐንሁ - "እናቴ ሞተች። ሶደቃ ልፈፅምላት?" ብለው ነብዩን ﷺ ጠየቁ።
- እሳቸውም "አዎ" አሉ።
* "የትኛው ሶደቃ ነው በላጩ?" አሉ ሰዕድ።
- "ውሃ ማጠጣት" አሉ ነብዩ ﷺ።

[ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 3668]

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 06:47


የቁርዓን የመጀመሪያ 5 አንቀፆች ላይ ስለ እውቀት 6 ጊዜ ተነግሯል በሚገርም ሁኔታ ..
"ኢቅራዕ ፣ ኢቅረዕ ፣ ዓለመ ፣ ቀለም ፣ ዓለመ ፣ ማለም የዕለም"
📜ኢልም እና ሙሽተቃቱ 3 ጊዜ ፣
✏️ቀለም 1 ጊዜ ፣
📚ንባብ 2 ጊዜ ..
ሶስት በአንድ ሲረባረቡ "ማንበብ ፣ መፃፍ ፣ ማወቅ" ስለሆነ ወህዩ ገና ሲገፈት ራሱ አንብብ ብሎ ፤ የእውቀት መሳሪያዋን "ብዕር" አድርጎ ፤ አስተማሪው ፊልሃቂቃ "አሏህ" መሆኑን አመልክቶ ነው የጀመረው!

የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/tedeburr

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

02 Nov, 03:31


የቀብር ዚያራ - የረሳነው ሱና
~
የቀብር ዚያራ ብዙ ፋይዳዎች አሉት።
1- ነብያችን ﷺ "ኣኺራን ያስታውሳል" ብለዋል። [ቲርሚዚይ፡ 1054] ከዱንያ ወከባና ግርግር ወጥተን ስለ ኣኺራችን እንድናስብ ያስታውሳል።
2- ሞትን ያስታውሳል። የምናውቃቸውን ሰዎች ቀብር ስናይ ድንገት የኛም ተራ መጥቶ እንደምንከተላቸው ያስታውሰናል።
3- የነብዩን ﷺ ሱና መፈፀም ነው።
4- ለሞቱ ወገኖቻችን ዱዓእ እናደርግበታለን። ለራሳችንም እንዲሁ።
5- ኣኺራን እና ሞትን ማስታወስ ምን ፋይዳ አለው? ከሐራም እና ከበደል እንድንታቀብ፣ ከወንጀል ተውበት እንድናደርግ፣ ኸይር ስራ ላይ እንድንሳተፍ ያነሳሳናል።

እና ልባችን ሲደርቅ፣ በዱንያ ጣጣ ስምጥ ስንል፣ መዘናጋት ስናበዛ ወደ መቃብር እንሂድ።
السَّلَامُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الدِّيَارِ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ، وَالْمُسْلِمِينَ، وَإِنَّا إِنْ شَاءَ اللَّهُ لَلَاحِقُونَ، أَسْأَلُ اللَّهَ لَنَا وَلَكُمُ الْعَافِيَةَ
እንበል። አላህ እንዲምራቸው ዱዓእ እናድርግላቸው። በዱዓችን ላይ እጆችን ማንሳት ይቻላል። [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 974]

ቀብር እንዳንረግጥ እንጠንቀቅ። መቃብር ውስጥ መፀዳዳትም ወንጀል ነው። በመቃብር መሀል ስንንቀሳቀስ ጫማዎቻችንን ብናወልቅ መልካም ነው። ለዚያራ ሂደን ከዚያ በዛዛታ መጠመድ አይገባም።
©IbnuMunewor

የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/Furqan_Oficial
https://t.me/Furqan_Oficial

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Nov, 20:00


በሞባይላችሁ ቴሌግራም መጠቀማችሁ ካልቀረ በዚህ ቻናል ገብታችሁ ጥሩ የቢዝነስ ኮርሶችን ተማሩ.... ይኸው ሊንኩ👇
https://t.me/+km3RHFI6ixg5MTE0
https://t.me/+km3RHFI6ixg5MTE0
ጆይን በሉት👍

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Nov, 18:59


ለዛሬ ይህን ያህል ከተጠያየቅን ይበቃል ኢንሽኣላህ ነገ እንቀጥላለን 😊

መልካም ምሽት

ፊአማኒላህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Nov, 18:58


ማሻ አላህ አሪፍ ተሳትፎ የሞከራቹ አላህ ይጨምርላቹ!!

ዱዓእ,ተወኩል,ክጃሎት,ፍራቻ,እርድ,ነዝር,ሰላት....

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Nov, 18:51


ለአሏህ ብቻ ከሚገቡ ዒባዳዎች 4 ጥቀስ/ሽ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

01 Nov, 18:49


የለመድናትን አንድ ደረቅ ነገር👇

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 20:12


👉አሳታፊ ጥያቄ

ነብዩ ሙሀመድ ﷺ በስንት አመታቸው ወደ አኺራ ሄዱ?

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 19:02


ኢንሻአላህ እንጠቀምበታለን🫶

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 19:01


በአሏህ ፈቃድ በቻናላችን ቁርዓን ነክ የሆኑ ተደቡሮችን ፤ እንዲሁም የአያዎች ትንታኔዎችን የምናቀርብ ይሆናል ።

#አንብቡ!
#አስነብቡ!
#በጋራ ምንዳ እናግኝ!
ወደኸይር ያመላከተ የሰሪውን ምንዳ ያገኛል!
👉 https://t.me/tedeburr/5

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:56


ነገ ሃሙስ ነው የቻለ ይፁም ኢንሻአላህ!

እና ስሁር ልጋብዛቹ የሚቸኩል ራትም ማድረግ እችላለው…ባረከላሁ ፊኩም!
ምን ትላላቹ?👀

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:55


ለዛሬ ይህን ያህል ከተጠያየቅን ይበቃል ኢንሽኣላህ ነገ እንቀጥላለን 😊

መልካም ምሽት

ፊአማኒላህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:55


ወላህ ደስ ስትሉ እንዲ ስትሞክሩ (ስትሳተፋ)

አላህ  መልካም  የሻለት  ሰው  የዲኑን  እውቀት ያስገነዝበዋል  ረሱል  ስለላሁ  አለይሂ ወሰለም

አላህ ሁላችንንም የዲኑን እውቀት ከምያስገነዝባቸው ያርገን!!

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:51


masha Allah እሚደነቅ ተሳትፎ

👌

ሰላምታ መመለስ
የታመሙትን መጎብኘት
ቀብር ላይ መገኘት
ግብዣ መቀበል እና
ስያስነጥስ የርሀሙከ አላህን (አላህ ይዘንልህ)
ማለት

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:46


.ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ላይ ካለው መብቶች ውስጥ 3ቱን ጥቀስ/ሽ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:44


የለመድናትን አንድ ደረቅ ነገር👇

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 18:31


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
ያ ጀመዓ እንዴት አመሻችሁ?!

ኢንሻአላህ! ወደ ጥያቄ የምንገባ ይሆናል፤ ተዘጋጁ!

ሌሎችም ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ share አድርጉላቸው።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 11:01


ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿صلاةُ الرجلِ تطوُّعًا حيثُ لا يراهُ الناسُ تَعدِلُ صلاتَهُ على أعينِ الناسِ خمسًا وعشرينَ.﴾

“ሰውዬው ሰዎች ሳያዩት የሚሰግደው ትርፍ (የሱና ሰላት) ሰዎች አይተውት ከሚሰግደው ሰላት በሃያ አምስት ደረጃ ትስተካከላለች (ብልጫ አለው)።”

📚 ሶሂህ አልጃሚ: 3821

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

30 Oct, 06:54


«ስራው እና ሪዝቁ ላይ መቀነስን፣ ቀልቡ መገለባበጥ ያስተዋለ፤ በተውሒድ እና ኢስቲግፋር  ላይ አደራውን ። በነሱ ውስጥ ለነዚህ ችግሮች ፈውስ አለና።»

【ኢብኑ ተይሚያአልፈታዋ (11/698】

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

29 Oct, 19:18


ትልቅ እድል ነው ያመጣሁላቹህ ቻነሉን ጆይን ብላቹህ ነፃ የ graphics design እድል ነው ተወዳደሩ መልካም እድል
👇👇👇👇👇
https://t.me/+km3RHFI6ixg5MTE0

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

29 Oct, 18:57


ለዛሬ ይህን ያህል ከተጠያየቅን ይበቃል ኢንሽኣላህ ነገ እንቀጥላለን 😊

መልካም ምሽት

ፊአማኒላህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 19:25


የቁርአን ግብዣ 🪸
@FURQAN_OFICIAL

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 19:03


ለዛሬ ይህን ያህል ከተጠያየቅን ይበቃል ኢንሽኣላህ ነገ እንቀጥላለን 😊

መልካም ምሽት

ፊአማኒላህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 19:03


Masha Allah በትክክል ተመልሰዋል

Suretul Hajj ነው

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 18:56


በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ከአምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች በአንዱ የተሰየመችው ሱራ ማን ነች?

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 18:50


አንድ ደረቅ ያለ ነገር

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 18:30


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!
ያ ጀመዓ እንዴት አመሻችሁ?!

ኢንሻአላህ! ወደ ጥያቄ የምንገባ ይሆናል፤ ተዘጋጁ!

ሌሎችም ተሳታፊ እና ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ share አድርጉላቸው።

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 17:05


ሴቶች አንዳንዴማ አታብዙትጂ 😂
@FURQAN_OFICIAL

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 11:07


ጁምዐን በጀመዐ ሰግደን ንዳድ በሆነው የጁምዐ ፀሀይ ተጠብጥበን ገብተን እርፍ ቅዝቅዝ የምንልበት ቤት የሰጠን አላህ ምስጋና የተገባው ይሁን

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 06:02


√ ሰላት

የዱንያ እና የአኼራ ጥቅሞችን ለማግኘት፤ የሁለቱ ሀገር አደጋዎች በመከላከል ላይ ትልቅ አጋዥ ነው።

«ኢብኑል ቀዪም/ "ዛዱል ሚዓድ" «4/209»
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 03:36


ጁምዐ ነው ሰሉ አለ ነቢዩና ሙሀመድ🥰
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

25 Oct, 03:33


እንደከማቹ...እንደተሰበራቹ...በጭንቀት ውስጥ እንሆናቹ...እንደታመማቹ...የሚያበረታ አካል እንደፈለጋቹ ...መጠንከር እና በራስ መቆም እንደፈለጋቹ አላህ ያውቃል ! ይህን ሁሉ የሚያውቅ ጌታ አላቹ ...ስለናንተ ሁሉን የሚያውቅ ጌታ አላቹ ። እናንተ ማወቅ ያለባቹህ አላህ እንዳላቹህ ነው ። አዎ አላህ አለላቹ

ጁምዐ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Oct, 19:55


ቀብር ጨለማ ነው ሰውየው በቀብር ውስጥ ፀሀይንም ሆነ ጨረቃን አየይም፣ሶላት የሚሰግድ ከነበረ ግን ቀብሩ ብርሃን ይሆንለታል። ኢብኑ ዑሰይሚን/መጅሙዕ አል-ፈታዋ(479-12)]

ኢላሂ ኻቲማችንን አሰምርልን!
=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Oct, 19:02


ለዛሬ ይህን ያህል ከተጠያየቅን ይበቃል ኢንሽኣላህ ነገ እንቀጥላለን 😊

መልካም ምሽት

ፊአማኒላህ

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Oct, 19:01


Masha Allah አሪፍ ሞክራቹዋል

መልሱ; 6ተኛ አመተ ሂጅሪያ ላይ ወርሀ ዙል ቀዐዳ ነበር

𝙵𝚄𝚁𝚀𝙰𝙽✎𝚃𝚄𝙱𝙴

24 Oct, 18:52


የሁደይቢያ ስምምነት መች ተደረገ

11,692

subscribers

928

photos

321

videos