በብል^ግና ሲወሳለቱ አድረው:- በቤተሰብ ተይዤ ይሆን? ወይስ በኤችአይቪ? ወይስ በካሜራ? Or አርግዤ/አስረግዤ ይሆን ወይስ ደንዝዤ? እዚህ ውስጥ ምን ከተተኝ? ከዚህ አዙሪት እንዴት ነው የምወጣው? ብለው ካደሩበት ቦታ ከሚወጡት ጋር ባለመሆናችን ማመስገን ይገባል:: ሲቅሙ ውለው, እየጠጡ አምሽተውና እዚያው አድረው ጠዋት የመጠጥ እንጥፍጣፊ እና የሽንት ሽታ እየሸተታቸው የሚወጡ አሉ:: ይብሱኑ በዚህ በንጋት የቡና ቤት ግ^ማታም ጠረን ሱስ የተያዙ እንዳሉ እንሰማለን:: በሰላም በጨዋነት አድረን ከራሳችን ጋር ጸብ ውስጥ ሳንገባ ለሥራ መውጣት መታደል ነው:: ብል^ግናውን ተላምደው ከደነዘዙት ጋር ባለመሆናችንና የሚቆጣን ልቦናና ሕሊና ካለን ትልቅ ጸጋ ነው:: እናመስግን::