...
ቤተክርስቲያንና ምዕመናኖቿ በሀዘን ጥቁር የለበስንበትን ጊዜ መቼም ከሰው ሁሉ ህሊና የማይዘነጋ ነው። ከሳሾች ቤተክርስቲያንን ለመክፈል እንደምክንያት የተጠቀሙበት ''በቂ የኦሮሞ ጳጳሳት የሉም'' የሚል አንዱ ነበር። ቤተክርስቲያን ምንም እንኳን ዘርና ነገድን መሰረት አድርጋ ባትሾምም ፤ ብትሾም እንኳን ፈቃደ እግዚአብሔር እንደማይኖርበትና ስራቸው ሁሉ እንደማይከናወንላቸው ብትረዳም ፥ የተጠየቀውን ጥያቄ ለመመለስ ቀድሞ ከነበሩት ጳጳሳት በተጨማሪ 7 Afaan Oromoo ተናጋሪ ጳጳሳትን ሾማ ኦሮሚያ ክልል ባሉ ሀገረ-ስብከቶች መደበች።
...
ባለፈውን አንድ ዓመት ብቻ 5 Afaan Oromoo ተናጋሪ ጳጳሳት ከተመደቡበት ኦሮሚያ ክልል እየለቀቁ ወጡ።
4ቱ ጳጳሳት ከተመደቡበት የወለጋ ዞኖች ነው ጥለው ወደ ሌላ ክልል መድቡን ብለው የለቀቁት ኦሮሚያ ክልልን። ልብ በሉ በብሄር ከኦሮሞ ማህበረሰብ የወጡ፣ በቋንቋ Afaan Oromoo ተናጋሪዎች፣ ምክንያተ ሹመታቸውም ቤተክርስቲያን ለኦሮሚያ ክልል በቂ ኦሮሞ ጳጳሳትን አልሾመችም የሚል ነበር።
በተሾሙ በዓመታቸው የተሾሙበት ሀገረ ስብከትና፣ የተሾሙበትን ምክንያት ሳይዘነጉ የኦሮሞን ህዝብ ጥለው ደቡብ፣ አፋርና አማራ ክልል መድቡን ብለው ለቀው ወጡ። 5ኛው አባት ከሀገር ጥለው ባህርማዶ ሄደዋል።
ይሄ ሁሉ ለምን?
1- ኦሮሚያ ክልል ባለው ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ባነጣጠረው ተከታታይ ጥቃት ስጋት ምክንያት
2- ፖለቲካዊ ጫና ምክንያት
3- ለቀጣይ ዙር የቤተክርስቲያን ፈተና
4- ከዘርና ከብሄር ዝቅ ብሎ ያለው ጎጠኝነት?
ከላይ ከተዘረዘሩት ከ4ቱ ሶስቱን እርግጠኛ መሆን ይቻላል። አሁን በነዚህ ከኦሮሚያ ክልል እየጣሉ በወጡ የAfaan Oromoo ተናጋሪ ጳጳሳት ምክንያት 5 ሀገረ ስብከቶች በተደራቢነት ለሌላ ጳጳስ ተሰጥተዋል። ነገ በዚህ ደግሞ ቤተክርስቲያንን በሚጠሉና ሊያፈርሷት በሚሹ ዘረኞች ስትከሰስበት የምናየው ጉዳይ ነው። ለአንድ አባት ይሄ ሁሉ ሀገረ ስብከት ለምን ተደርቦ ተሰጠ የሚል ጥያቄ ይነሳል ምክንያቱ ሁለት ነው፤ አንደኛው በኦሮሚያ ክልል ኦሮሚኛ ቢናገሩ እንኳን ከኦሮሞ ብሄር ውጪ እንዳይሾሙ በሚለው ፖለቲካዊ ጫና ፣ ሁለተኛው ያሉት የኦሮሞ ጳጳሳትም ቢሆን ምዕራብ ኦሮሚያ በተለይም የወለጋና የሁሩ ጉዱሮ ሀገረስብከቶችን መምራት አንፈልግም ማለታቸው ነው።
©️Maramawit Henok
@tinsae_ze_ethiopia