ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ @zemari_yilma_hailu Channel on Telegram

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

@zemari_yilma_hailu


ስለ ስምህ እንሞታለን

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ (Amharic)

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ከእናቴ 'zemari_yilma_hailu' ስም በሚገኘው ታሪካዊ ቺካናል እንሞታለን። ይልማ ኃይሉ ከልዩ እምነት ይገኛል። በአማርኛ በተለይም በልዩ እምነት ላይ የምንውቀው አካፈላትና ድንቅ የሆነ እናቴ ናቸው። እንዴት ያለውን ፈንታወች ጠንካራ መዝለሲ እና ስነ-ምግባር ስቶርክ ቤቱን ማግኘት እንዴት እርዳታ በፍጥነት ይችላል። አስተያየቶችን ያዘበናል። ከዚህም በበኩልም መድሥዳት እና ጥንካሬ ማህበረሰብን እንዲለው እንፈልጋለን።

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

03 Oct, 20:53


https://youtu.be/nq1yjnLVTWg?si=5i0V9REuSMJCo0d_

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

03 Oct, 16:21


https://youtu.be/FudvpsmycrU?si=0qQUuBHbUmCducSM

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

02 Oct, 16:32


ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው

መዝ 60፥4 ላይ ልበ አምላክ ዳዊት “ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው" በማለት የተናገረው በምሥጢር ክርስቶስ የሚሰጠንን የሐዲስ ኪዳን ልዩ ምልክት ሲያመላክት ነው። እግዚአብሔር የሚሰጠንን ልዩ ምልክት ገንዘብ ለማድረግ አስቀድመን ሊኖረን የሚገባው “ፈሪሐ እግዚአብሔር" ነው። ፈሪሐ እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ መግቢያ በር ስለ ኾነ ልዩ ምልክትን ከእግዚአብሔር ለማግኘት የግድ የፈሪሐ እግዚአብሔርን ልብስ ውስጣችንን ማልበስ አለብን። ያ ልዩ ምልክት ቅዱስ መስቀሉ ነውና! መስቀል ዓለምን በሙሉ አምላካችን ክርስቶስ ወደ ራሱ የሳበበት የሰላም ዓርማ ነው። ይህ ምልክት ክርስቶሳውያን የመኾናችን ዋና መለያ ነው።

እግዚአብሔርን የማንፈራ በፊቱ ቆመን የምንተቻች፣ እርስ በእርሳችን የምንናናቅ እንዴት ምልክቱን ልናገኝ እንችላለን? በፈሪሐ እግዚአብሔር ውስጥ እስካልኖርን ድረስ ምልክቱን ማግኘት አንችልም። ለሚሳለቁበት፣ መቅደሱን የሳቅና የስላቅ ስፍራ ለማስመሰል ለሚጥሩ፣ ትሕትና ለሌላቸው፣ ቅዱሳን መላእክት በመንቀጥቀጥ የሚያመልኩትን አምላክ በመቅደሱ ተገኝተው የሚተኙበት ሰዎች ምልክቱን አያገኙትም። “ለሚፈሩት" ሲል ለሚያመልኩት ማለት ነው። እናመልክሃለን ብለው በተግባር ግን ፈጽሞ የራቁ ሳይኾን በእውነት የሚያምኑበት ናቸው ልዩ ምልክትን የሚያገኙት። ወደዚህ ምልክት ውስጥ በፍቅር እስካልገባን ድረስ ፍቅርንና ሰላምን ገንዘብ ማድረግ አንችልም። በተግባራዊ ሕይወታችን ውስጥ የቀበርነውን መስቀል በንጹሐን መምህራን በኩል ቆሻሻውን አስነሥተን መስቀሉን እስካላወጣነው ድረስ መስቀል የሕይወት ምልክት ነው ብለን የምንፈክር እንጂ በእርግጥም መኾኑን በሕይወት መግለጥ ያቃተን ግብዞች መኾናችንን እናረጋግጣለን።

ምልክት (Banner) የሚያመለክተው አምላካችን ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን አንድ ጊዜ የገባበት መቅደስ የተባለውን ቅዱስ መስቀልን ነው። መስቀል ለክርስትናችን መለያ ምልክት ነው። ክርስትናን ከመስቀል ነጥሎ ለማየት መሞከር ማለት ቤተክርስቲያንን ከክርስቶስ ነጥሎ ለማየት እንደ መፈለግ ነው። መስቀል የቤተክርስቲያን ሙሽራ ክርስቶስ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በደሙ ሲያጭ ፥መታጨቷን ለመግለጽ ያኖረላት ምልክት ነው። ቤተ ክርስቲያን ጉዞዋ በሙሉ ወደ ድኅነት የሚመራ ነው። በምድር ላይ በምእመናን ልብ ውስጥ መስቀል እየሳለች ሰማያዊቷን መንግሥት ታጓጓናለች።

መስቀልን በአንገታችን ላይ ማድረጋችን የክርስቶስ ሙሽሪቶች መኾናችን ይታወቅ ዘንድ ነው። አንዲት ሴት ከታጨች በኋላ ሌላ ወንድ መፈለግ የለባትም፤ ሌላም ወንድ እንዲፈልጋት የሚያደርግ ሥራ መሥራት የለባትም። ቤተክርስቲያን መስቀሉን ከክርስቶስ በምልክትነት ከተቀበለች በኋላ ሌላ ነገር አትፈልግም። መስቀል የሕይወቷ ዓርማ አድርጋ ስትታወቅበት ትኖራለች እንጂ። መስቀል በምድር ያለችው ቤተ ክርስቲያን የሚደርስባትን መከራ የሚያመለክት ነው። መከራ ደግሞ የክርስትና ሕይወት መልክ ነው። ብዙዎቻችን የዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ተቃራኒ የኾነ ሕይወት ነው ያለን። ከክርስቶስ መከራ ይልቅ የዘፋኞች ዘፈን ልባችንን የማረከብን፤ ከክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ይልቅ የዚህ ዓለም ተራ መብልና መጠጥ የሚያረካን ከክርስትናው እውነተኛ መንገድ እጅግ የራቅን ነን። ስለዚህ ምልክቱን ስንተው አጋንንትም መጥተው አደሩብንና ከሙሽራው ፈቃድ ለዩን።

ምልክት የተባለው በቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ “የክርስቶስ ደም" ነው ይላል። በእርግጥ ይህን ደም ምልክት አድርገን የምንኖር ከኾነ ጠላት ድል ያደርገን ዘንድ አይችልም። መስቀል ደግሞ በዚህ ትርጒም የምልክት ምልክት ነው። የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት የሕይወት ዕፀ ነውና። በመስቀል ላይ የተቆረሰውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ የፈሰሰውን ክቡር ደም እናይበታለን። መስቀሉን ስንስም የምንስመው ዕፅነቱን ብቻ አይደለም ይልቅስ በዚያ ላይ ከሞት የሚያድነን ንጹሕ የክርስቶስን ደም ነው። ስለዚህ በመስቀል ዐይንነት ክርስቶስን እናየዋለን። በምልክቱ በኩል ምልክቱን የሰጠንን አምላክ ደሙን ሲያፈስልን ተመልክተን ፍቅሩን እናደንቃለን።

“ለሚፈሩት ምልክትን ሰጠሃቸው" የተባለውን ብዙ ሊቃውንት የእስራኤላውያን በኲር በግብጽ ምድር የተረፈበትን የፋሲካውን በግ ደም ነው ይላሉ። ያ ምንም የማያውቀው በግ ደሙ በቤቱ ጉበን ላይ በመቀባቱ ምክንያት የእስራኤል በኩራት ከዳኑ ሕያው በግ ክርስቶስ ቤት አድርጎ በቀራኒዮ በገባበት መስቀል ላይ ባፈሰሰው የሚናገር ደም'ማ እንዴት የበለጠ ድኅነት ይገኝ ይኾን? በኩራችን ክርስቶስን ከልባችን ውስጥ ለማጥፋት የሚተጉትን ክፉ አስተሳሰቦች በሙሉ እንዋጋቸው። ኹል ጊዜም ነገረ መስቀሉን ምልክት አድርገን የአጋንንትን ሐሳብ እናርቅ፤ በእግዚአብሔር ቃልም መሠረት ሳንሠቀቅ መከራ መስቀሉን ለመሸከም እንትጋ። የእውነት መኖር ከጀመርን ሕይወታችን በራሱ የመስቀል ሕይወት ይኾናል፤ ብዙ ግራ የተጋቡ ሰዎችንም የመሰቀል ሕይወትን ጣዕም አቅምሰን ከስሕተታቸው መመለስ እንችላለን። በመኾኑም ምልክታችንን ከጥልቅ ውስጣችን ሕያው አጥር አበጅተን መጠበቅ አለብን።

📝ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

30 Sep, 16:48


#ያልተሞረደ_አእምሮ_አስቸገረን።
ቢላው ሲደነዘዝ ሥጋ አይቆርጥም ስለዚህ በድንጋይ ይሞርዱታል።
ከግንዛቤ እና ከመረዳት የተለየ አእምሮም በመምህር ይሞርዱታል።
ከአንድ ሊቀ ጳጳስ ጋር ሆነን የቢሮ መኪናዬን እየነዳሁ ጀሞ ስደርስ የመኪናው ፍሰት አላስኬድ ብሎኝ ቀስ እያልኩኝ የመኪና ዳዴ እያረኩ ሳለ አንዲት ነጭ በነጭ የባሕል ልብስ የለበሰች ድምጸ ሸካራ ሰውነተ ቀላል ሴት "#መነኩሴ_መኪና_አይነዳም_ንስሐ_ግባ" አለችኝ።

እ................ሺ አልኳትና ፈገግ አልኩኝ በዚህ ጊዜ አቡኑ "ከእሷ ንግግር ይልቅ የአንተ ፈገግታ ዘይገርም ነው" አሉኝ።

የክርስቶስ የማያቋርጥ ፍቅሩን እና ወዳጅነቱን እያሰባችሁ ፈገግ እያላችሁ አገልግሉ እንጂ የሰነፎች አሉባልታና ነቀፌታ ወደ አእምሯችሁ አታስገቡ!

ምክንያቱም የመርዛማ ሰዎች ንግግር ልቡናችሁን መርዞ ይገላችኋልና።

#ፓንዋማንጦን

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

30 Sep, 08:42


ትዳር እንደ አያያዙ ነው
ትዳር ማረፊያ ወደብም የመርከብ አደጋ የሚያጋጥምበት ሰርጥም ሊሆን ይችላል።

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

30 Sep, 08:39


https://youtu.be/fnak04scucY?si=N1A1jiaUfN7b1sfD

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

29 Sep, 09:48


“በአባ ቢሾይ ገዳም ከአባቶች መነኰሳት ጋር ተገናኘሁ። በዚያም የቦታውን መንፈሳዊነትም ሆነ የእንግዳ ተቀባይነታቸውን ነገር፣ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተግባራቸውንና ትምህርታቸውን ተመለከትሁ፤ ሆኖም ግን ካየሁት ሁሉ አንዱንም እንኳ እንደሚገባ አድርጌ አሟልቼ ልገልጸው አልችልም። ሆኖም የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት በታሪካችን ውስጥ የነበረውን ሚና መዘንጋት ለእያንዳንዱ ዐረብ ታላቅ ኪሳራ የመሆኑ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ለራሴ ተረድቻለሁ። በእ*ስልምና ሃይማኖት ውስጥ ምንኲስናና ገዳማዊ ሕይወት የሚባል ነገር አለመኖሩን ማሰብ ውስጥን የሚረብሽና የሚያሳዝን ነገር ነው።”

መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው።

ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም።

ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!

✍️ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

28 Sep, 16:49


የኔታዎች "#ወፈነዎሙ_በበክልኤ" ያለው ትርጓሜ አወራረዱ ስንት ነው?
አንድ ቀን አንድ ትንሽ ልጅ ከመንገድ ዳር በትናንሽ እጆቹ ዐይኖቹን እያሻሸ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል᎓᎓ አንዱ ሆደ ቡቡ መንገደኛ ወደ ሕፃኑ ጠጋ ብሎ "ማሙሽዬ ለምንድነው የምታለቅስው ምንስ ሆነህ ነው"? ሲለው "እኚህ የኔታ «ሀ» በል ይሉኛል" ሲል ይመልሳል፡፡ በሁኔታው የተገረመው መንገደኛውም ነገሩን ቀለል አድርጎ "ታዲያ ምናለበት "ሀ" አትልም እንዴ"? ቢለው "እሳቸው መቼ ይተዉኛል? ሀ ስል ሁ በል ይሉኛል ሁ ስል ሂ በል ይሉኛል… እያለ Baby ብሶቱን ዘከዘከው አሉ።
አንዳንድ ሰው ሊሠራ የሚገባውን ሳይሠራ በሀሳብ ብቻ ይደክማል፡፡ የማያስፈራውም ደርሶ ያስፈራዋል።

"ሀ" ላለማለት ከመሬት ደርሶ "ው ው ው"! ብሎ ይጮሀል።

Baby እንግዲህ መልካም ጩኽት ይሁንልህ!

ሐተታው ከቀደመው ይገባል።
#ፓንዋማንጦን
መስከረም 18/01/2017 ዓ/ም

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

26 Sep, 07:53


https://youtu.be/bu4ULevWHlY?si=nM_aTwh9RSI8FH7f

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

26 Sep, 06:13


ደመራው የመስቀል መቆፈሪያ እንጂ የመስቀል መቅበሪያ አይደለም።
እየሆነ ያለው የቱ ነው? ቀበራው ነው?ወይስ ደመራው? በዓመት በዓመት መቅበር እንጂ ማውጣት ከሌለው የደመራው ጥቅም ዘልማድ መሆኑ ነው።
የተቀበረውን ላያወጡ እየደመሩ ማቃጠል ማስመሰል ብቻ ነው።
በደመራው አቃጣዮች አሉ። የተቀበረውን የሚያወጡ ያለውን የማያስቀብሩ ሰዎች ግን የዓመቱ ደመራ ያልገባቸው ይባላሉ።
የዓመት መስቀልን የዓመት ደመራን እያከበርን  ሁልጊዜ ያለ የሕይወት መስቀልን የሕይወት ደመራን ከረሳን ቱሪስቶች እንጂ ክርስቲያኖች አይደለንም።
የደመራው ዓላማኮ ያለውን ለመጠበቅ የጠፋውን ለመመለስ የተቀበረውን ለማውጣት ነበር።ደመራችን በተቃርኖ ሲደመር ያለንን ይቀብራል ያጣነውን ያስረሳል።
እሌኒ በደመራዋ መስቀሉን ከተቀበረበት ቆፍራ አውጥታዋለች።
እኛም ወይ የተቀበረውን ቆፍረን እናውጣ ካልሆነ ደግሞ መስቀሉን ለመቅበር አንደምር።
የዘመናችን የመስቀል ጠላቶች ሁልጊዜም ቀበራ ላይ ናቸው።
የመስቀል ወዳጆችስ?

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

25 Sep, 17:19


እንኳን አደረሳችሁ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

25 Sep, 17:18


መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው።

መስቀል ሰይጣንን የሚያጠፋ ምሳር ነው። የአጋንንትንም ራሶች የሚቆርጥ ሰይፍ ነው።

መስቀል ርኵሳን መናፍስትን የሚወጋቸው የእሳት ዘገር ነው። የአመስቴማውያንንም ሠራዊት የሚመታ የመብረቅ ጦር ነው።

መስቀል ማኅተመ ሥላሴየሌለው ሰው ወደእርሱ ሊቀር በው የማይቻለው አምባ መጠጊያ ነው። መስቀል ከግራም ከቀኝም ለሚመጣ ጠላት የጽድቅ ጋሻ ነው። ጳውሎስ ውጊያችሁ ከሥጋና ከደም ጋር አይደለምን እንዳለው መስቀል የጦር መሣርያ ነው።

መስቀል የጦር ውጋት ሊቀድደው፣ የቀስትና የዘንግም ጫፍ ሊበላው የማይችል የሃይማኖት ጥሩር ነው። መስቀል አማሌቃውያንን ለመዋጋት በራፊድ በረሐ በተዘረጋው ስሙሴ እጅ አምሳል የተሠራ ነው።

መስቀል ሰሙሴ እጅ ወደ ውስጥ በተጨመረ ጊዜ መራውን ውኃ በቀር በረሐ ያጣፈጠ ነው። መስቀል የቅድስናና የንጽሕና ማኅተም ነው።

መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው።

(ውዳሴ መስቀል - በአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

25 Sep, 04:28


https://youtu.be/sktHGeNhxu8?si=75G49KUT3hyPrI0S

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

24 Sep, 10:29


"ዳዊት አስቀድሞ መዝሙራትን እንደ ዘመረ እኛም ዛሬ እንዘምራለን። እርሱ ሕይወት የሌላቸው ጅማቶች ያሉት በገና ነበረው ፤ቤተ ክርስቲያን ግን ሕያዋን ከሆኑ ጅማቶች የተሠራ በገና አላት። በእርግጥም ልሳኖቻችን ለእግዚአብሔር ክብር እንደሚገባው የሚቀርቡ የተለያዩ የድምጽ ቃና ያላቸው የበገና ጅማቶች ናቸው።  … ብትወድስ አንተ ራስህ የሥጋ ሕዋሳቶችህን ምውታን በማድረግ ፣ነፍስና ሥጋህን ፍጹም አስማምተህ የመዝሙር ንዋይ ልትሆን ትችላለህ። ሥጋህ ከፍትወት የተነሣ መንፈስ ቅዱስ ላይ በደል ማድረግን ሲያቆም ፤ ነገር ግን ለሕጉ ራሱን በማስገዛት በዘላቂነት መልካም እና እጅግ በሚደነቀው መንገድ መመራት ሲጀምር ፤ ያን ጊዜ መንፈሳዊ ዜማን ይፈጥራል"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

22 Sep, 18:40


የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዐቅም ባጡበት ጕዳይ ላይ ሒስ የሚሰነዝሩ፣ አቅጣጫን የሚያመለክቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከፖለቲካ ከጫወታ ውጪ ነኝ፤ አይመለከተኝም የሚል አስተሳሰብ እንዳያድርባቸው ቃለእግዚአብሔርን በመጥቀስ ወደ ጫወታው እንዲገቡ የሚሞክሩ ጸሐፍያን ያስፈልጉናል። "ቤተ ክርስቲያን ሆይ ተነሽ" የሚል ነቢያዊ ጩኸት የሚያሰሙ የቊርጥ ቀን ልጆች የሚያስፈልጉን ይመስለኛል። መቼም የቤተ ክርስቲያንመሪዎችን ሁሉ በአንድ መፈረጅ አግባብ ባይሆንም፣ አብዛኞቹ መሪዎቻችን ልፍስፍሶች መሆናቸውን እንኳን ምዕመናን እነርሱ ጭምር የሚስማሙበት ይመስለኛል። "አልታየሁም"፣ "አልታወቅም"፣ "ነውሬ ተረስቶአል"የሚሉ ካሉ ሞኞች ናቸው። ከታሪክ ዐይን የሚያመልጥ የለም። ይህ ግን እውን መሆኑን የሚያሳዩ ጸሓፍያን እንጠብቃለን—እውነትን በፍቅር የሚገልጹ።
አብዛኞቹ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ መስሎ ለመኖር ብቻ ውሃና ዘይትን ካለዋሃድን፣ እሳትና ጭድን ከላፋቀርን፣ ዐይንና ናጫን ከላስማማን የሚል አቋም ያላቸው ይመስላል። እውነትን ከጥቃት የምንጠብቀው ሐሰትን በግልጥበመቃወም ጭምር ነው። በልፍስፍስ አቋሙ በባልንጀሮቹ በስፋት የሚታወቅ አንድ ወንድማችንን ሌላው ወንድማችን፣ "ክርስቶስ ሰምራ" ብሎ ይጠረዋል። አንድ ቀን፣ "ወዳጄን ዳቦ ሳትቈርስ 'ክርስቶስ ሰምራ' ብለህ ስምያወጣህለት ለምንድን ነው? ለመሆኑስ ክርስቶስ ሰምራ ማን ነች?" ስል ጠየቅሁት። "አታቅም እንዴ፣ ክርስቶስ ሰምራ የምትባል ክርስቶስንና ሰይጣንን ለማስታረቅ ሙከራ ያደረገች ብጽዕት ናት፤ እኔም ይህን ወንድም ከክርስቶስሰምራ ለይቼ አላየውም፤ ለመኖር ሲል ብቻ ሁሉም ትክክል ነው የሚል እርስ በርሱ የተምታታና የተውገረገረ አቋም ያለው ፍጥረት ነው" አለኝ በሐዘንና በቊጣ። በርግጥ ስያሜው ወዳጄን በትክክል እንደሚመጥነው እቀበላለሁ፤ ገላጩ ስያሜ ግን አስቆኛል።

መቼም መንግሥት ከእርሱ ተቃራኒ ዘዌ የቆሙትን ሁሉ "ጸረ" የሚል የመነሻ ምዕላድ እየቀጸለ፣ ጽንፍ የነካ በመሰለበት በዚህ የታሪክ ጊዜ፣ መለሳለስ ጥሩ ስልት መስሎ ሊታይ ይችል ይሆናል።ግን የክርስቶስ ወንጌል የጀግኖችመለዮ እንጂ፣ የአልጮች ሙያ አይደለምና ልፍስፍስ አቋማቸውን መቀየር የግድ ይኖርባቸዋል። ለዚህ ነው አንድ ወንድማችን ይህን አስመልክቶ፣ "አቋም የለሽ አቋማችን" እንዲስተካከል በአንድ ጽሑፉ የሚማጠነን። እውነትነው አቋም የለሽ አቋማችንን እክ እንትፍ እንበለው። የአቋም ሰው መሆን ያስከብር ከሆነ እንጂ አያዋርድም (ቢያንስ በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት)።

ይቀጥላል...

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

22 Sep, 10:00


"አባቱ አየውና አዘነለት፤"
(ሉቃ. 15፥20)
***
ይህ ልጅ አባቱ በቁሙ ሳይሞት ገና ንብረት ያወርሰው ዘንድ ጠይቆ የድርሻውን ወስዶ ያባከነ ከንቱ ልጅ ነበር። አባት ሳይሞት ከንብረትህ የድርሻዬን አካፍለኝ ማለት አባት እስኪሞት እንደመቸኮል ያለ ጽኑ በደል ነው፤ የአባቱን ውርስ ወስዶ ማባከን ደግሞ ሌላ በደል!
ግን አንድ ነገር ሕይወቱን መለሰችለት፦ የአባቱን መልካምነት አልዘነጋም፤ በአባቱ መታመኑን አልተወም። ወደ ልቡ ተመልሶ ያደረገው ነገር ጽኑ በደል መሆኑን አምኖ ተጸጸተ፤ ልጅ ሊባል እንደማይገባውም ተናዘዘ። ልጅ ሊባል እንደማይገባው ቢያምንም የአባቱን ቸርነት አልረሳም። ምሕረትን የምትሻ፣ ከሞት ጋር የተካከለች የጎሰቆለች ሕይወቱን ይዞ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ።
አባቱ ከቤቱ በር ሆኖ የልጁን መምጣት እየተጠባበቀ ሩቅ ይመለከታል። የተጎሳቆለ ልጁን ከሩቅ ሲያየው አዘነለት። ልብ ይነካል!
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱን ቸርነት በዚህ መንገድ ገለጠልን። ከእርሱ ጋር አንድ ፈቃድ ያለውን የአባቱን ልብ ገልጦ አሳየን። ሐዋርያው ጳውሎስ “ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን፤” በማለት ከዘላለም በአብ ልብ ውስጥ ለእኛ ታስባ የነበረች ቸርነቱን ነገረን። (ኤፌ. 1፥4) ቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ "አባታዊት ርኅራኄ የምትገለጥበት ጊዜ ሲደርስ" ሰው ሆኖ አዳነን ብሎ የገለጣት ይህችን ቸርነት ነው።
ጌታችን ስለ አባቱ ሲነግረን በጽኑ በደል የተለየውን ክፉ ልጁን ከሩቅ አይቶ በሚያዝን እና በመመለሱ ደስታን በሚያደርግ ቸር አባት ምሳሌ ነው። በደለኛ ስለሆነ ዓይኔን እንዳያይ በሚል መራር አባት ምሳሌ አይደለም። ይህን የእግዚአብሔር ቸርነት እና ፍቅር በምልዓት ሊረዳው የሚችል ፍጡር የለም፤ ከእውቀት በላይ ነው።
ኃጢአታችን እጅግ የበዛ የምድር ጎስቋሎች ብንሆን ይህች አባታዊት ቸርነት ትጠብቀናለች፤ ከሩቅ ትመለከተናለች። በአባታቸው ቸርነት አምነው በእውነተኛ ንስሐ የሚመለሱትን ልታቅፍ ዘወትር የተዘጋጀች ናት። ቀድሞ በልጁ ሞት የተደረገች መዳናችን በዚህች ቸርነት ላይ የተመሠረተች ነች። የምንታደስባት ንስሐችንም በዚህች ቸርነት ላይ የተመሠረተች ናት።
መንፈስ ቅዱስ በልባችን የሚያፈሰው አባ አባት ብለን እንድንጮህ የሚያነሣሣ የልጅነት መንፈስ ይህን የእግዚአብሔር አባትነት ከልብ ማመን ነው፤ በዚህች ቸርነት ላይ መደገፍ ነው። (ገላ. 4፥6)
***
ሰማያዊ አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይመስገን!

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

22 Sep, 08:45


የመስቀሉ ፍቅር ሲገባን

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

20 Sep, 10:56


    አስበው ሊያደነቁሩን ከፈለጉ አስበን እናስተምር።
በማይሆን የወሬ ተስፋ ተሞልተን ነገን ከምንረሳው ልጆች ላይ እየሠራን ብንጠብቅ ይሻላል።
አሁን አማራጭ የሌለው ትምህርት ቤታችን አብነት ነው።ስለሆነም ልጆች ዳግም ከፊደልና ከቁጥር እንዲወለዱ የዕውቀት ማዕከል አድርገን እናስተምር።
ትልቁ ጽድቅ ትውልድን በተረካቢነት መተካት ነው።እኛ ከላይኞች አባቶቻችን የተቀበልነው እንደ ሚገባ ጠብቀን ለሚተካው ትውልድ ካላስረከብነው የጌታውን ወርቅ የቀበረው ሰነፉ አገልጋይ መሆናችን ነው።
እኔ የነገ አደራ አለብኝ የሚል መልካም አሳቢ ሰው ሁሉ ሊጨነቅበት የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ነገን ተረክበው አደራቸውን የሚጠብቁ ሕፃናት ናቸው።
ከአብነት ትምህርቱ ጋራ ጎን ለጎን ሳይነጣጠሉ፦
፦የሀገር ታሪክ
፦የጽሑፍ ትምህርት
፦የሀገር ባህልና ወግ
፦የጨዋ ደንብ(ሥነ ሥርዓት)
፦የሥነ ምግባር ትምህርት
፦ትምህርተ ግብርና፦ተግባረ እድ፦አገልግሎት፦ሀገርና ሃይማኖት፦ቅርስ እና የሀገር ሀብት ጥበቃ፦የባለውለታ አባቶች ታሪክ፦ትምህርተ ሰማዕትነት.. የመሳሰሉ ትምህርቶች ቢሰጣቸው ጥሩ ነው።ስለማያቁት እና ስላልተነገራቸው ሀገር ሃይማኖት ተረካቢ ሊሆኑ አይችሉም።ይገባቸዋል የምንለውን በጎ ትምህርት ሁሉ ለልጆቻችን እናስተምር።ማን ያውቃል ወይምኮ በዚሁ መንገድ ትናንት ያጣነውን የአባቶቻችንን ቅዱስ ጥበብ እናገኘው ይሆናል።
ልጅን አለማስተማር ግን የህሊና ወንጀል ነው።

4,325

subscribers

154

photos

12

videos