Hamza media @hamzaibnudinoislamicmedia Channel on Telegram

Hamza media

@hamzaibnudinoislamicmedia


የዕውቀት ምንጭ

ዲኖትን ይማሩ።
አጫጭር ታሪኮች
ሀዲሶች。。。


https://youtube.com/channel/UCMyjU57ElAACkRt16RChdWA

For cross & promotion @abunehyan1

Hamza media (Amharic)

ሃምዛ ሚዲያ አለበለዉ! ይህ ቻናል የግምትን የእልሻ መረጃዎች ሲሆን አዝናኝ እና መሻሻያ መረጃዎችን የመስራት ይሆናል። እዚህ በቀላሉ ሀዲስ መመሪያዎችን ሊመለሱ ይችላሉ። በወቅታዊ መረጃዎች እና በትምህርት ጥራት ስነስርዓቱን ከታከፋው እና በፅሁፍ ማስተከበሩን ይሰጥሻል። የሀምዛ ሚዲያ መረጃዎችን ዘግተን ስትመለሱ እንችላለን። ከዚህ በፊት በጣም ለሚያመለክት ሀዲስ መረጃዎችን እንመለሳለን። በሴቶችም እዚህ የታጣ ይመልከቱ። ወይስ ለመመልከት በሚችለዉ የፕሮሞሚያዊ መረጃ ከላይ ይጠቀሙ።

Hamza media

10 Jan, 20:04


እነሆ መሬቷም መንቀጥቀጧን አበዛች አለምም መናወጧ ላይ በረታች የቂያማ ምልክት መጣው መጣው ማለት ጀመረ🥹ምን አዘጋጀን???

አላህ ሆይ በህይወታችን ውስጥ መልካም ስራን በሞት ጊዜም ሸሀዳን ከሞት በሗላም ጀናን ወፍቀን🤲

Hamza media

10 Jan, 02:33


በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ የሚያስተጋባውን ከእንቅልፋችሁ ሰላት ይሻላል ኑ ወደ ሰላት ኑ ወደ ፈላህ አላህ ታላቅ ነው የሚለውን የጌታቸውን ጥሪ ተቀብለው በቤቱ በተገኙ ጀግኖቹ በቤታቸው በሚሰግዱ አጀግና እንስቶች ላይ የአላህ ሰላትና ሰላም ይስፈን

በሰለዋት የደመቀ በዒባዳ የተዋበ ውብ ጁሙዓን ተመኘው🙌

Hamza media

09 Jan, 19:11


አምስት አውቃት ሰላት መስገድ ዲነኛ ሚያስብልበት ዘመን ላይ ደረስን😔

አላህ ሆይ ነስርህን🤲

Hamza media

09 Jan, 16:05


ረመዳን 50 ቀን ቀረው

ያአላህ የጊዜው ፍጥነት አላህ ደርሰው ከሚፆሙት ፆማቸውን ከሚቀበላቸውም ያድርገን 🤲🤲

ቀዳ ያለባቹህ እህቶች ከአሁኑ መፆም ብትጀምሩ ባረከላሁ ፊኩም

t.me/HijabNewWebta

Hamza media

09 Jan, 03:36


ሱብሃነላህ የዚህን ዚክር ጥቅም አያችሁት በጣም ትልቅ ነገር ነው ያለው ወላሂ

Hamza media

09 Jan, 03:33


#لا_حول_ولا_قوة_إلا_بالله

Hamza media

08 Jan, 15:28


ያልተፈተነ አያልፍም !!
አንዳንዴ ...ለማወቅ መጎዳት፣ለማደግ መውደቅ፣ለማገኘት መሸነፍ ይኖርብሻል! ምክናያቱም... የህይወትን ትልቁን ትምህርት የምታገኚው በህመም ውስጥ ነው።

Hamza media

07 Jan, 18:32


እንጠብቃቹሀለን🙌

በዛው ወንድም ኡመርንም ፎሎ በማረግ አበረታቱት

Hamza media

07 Jan, 18:31


የአለም አቀፍ ቁርአን ውድድር መግባት የምትፈልጉ 5 ነፃ ትኬቶች አዘጋጅተናል ።

Hamza media

07 Jan, 18:31


https://vm.tiktok.com/ZMkfe8pc1/

Hamza media

07 Jan, 11:55


🔻ሸሪዓዊ እውቀት መማር የጀነት መንገድን ይመራል

🔥…ኸዋሪጆች ከሰሀባዎች ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ላሉበት ጥፋት የዳረጋቸው አላዋቂነት(ጅህልና) ነው!

↪️በተቃራኒው አብደላህ ኢብኑ አባስ ደግሞ በእውቀቱ ከኸዋሪጆ ከፊሎቹ ካሉበት የጥፋት መንገድ ታደጋቸው…!

👇👇👇
https://t.me/Adamaselefy/9473

Hamza media

06 Jan, 10:49


በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ እንኳን ተስፋ ነበር በምድር ላይ ሆነህ ተስፋ እንዳትቆርጥ

Hamza media

06 Jan, 05:58


የረጀብን ወር መፆም...

بسم اللــــه الرحمـــن الرحيم.

حكم صيام شهر رجب كاملاً

السؤال: ماذا على الذي يصوم شهر رجب كاملاً كما يصوم رمضان، وهذا السؤال من المستمع علي عثمان محمد؟

ጥያቄ ፦

የረመዳን ወር ሙሉ እንደሚፆመው የረጀብን ወር አሟልቶ የሚፆም በሆነ ሰው ላይ ምን አለበት ?... ?

الجواب: صيام رجب مكروه؛ لأنه من سنة الجاهلية، لا يصومه، صرح كثير من أهل العلم بكراهته؛ لأن النبي ﷺ نهى عن صيام رجب، المقصود أنه من سنة الجاهلية، فلا، لكن إذا صام بعض الأيام يوم الإثنين، يوم الخميس لا يضر، أو ثلاثة أيام من كل شهر لا بأس، أما إذا تعمد صيامه فهذا مكروه.

المقدم: بارك الله فيكم

لسماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز رحمه الله

መልስ ፦

የ"ረጀብ" ወር ፆም የተጠላ ነው‼️

ምክንያቱም ፦

የ"ጃሂሊያ" ፈለግ ነው !!! አይፁመው‼️አብዛኛዎቹ ዑለማዎች የተጠላ በመሆኑ ላይ ግልፅ አርገዋል።

👉 ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የ"ረጀብ"ን ወር ከመፆም ከልክለዋል።

👉 የ"ረጀብ"ን ወር በመፆም የተፈለገበት የ"ጃሂሊያ"ን ሱና ነው።

አይቻልም (አይሆንም‼️)

ነገር ግን ሰኞና ሐሙስ እንዲሁም ከወሩ ሦስት ቀንን የመሰለ ከፊል ወቅት ቢፆም አይጎዳውም።ችግር የለውም።ካልሆነ ግን አውቆ (ለመፆም) አስቦበት
ከሆነ የተጠላ ነው።

ፕሮግራም አቅራቢ ፦

(( አላህ ረድሄቱን ይስጦት !!! ))

ኢማም ኢብን ባዝ

📝 … ኢስማኤል ወርቁ …

https://t.me/amr_nahy1

Hamza media

06 Jan, 05:11


سألوه : كيف انتظمت في الصلاة؟
- فقال : سمعت شيخاً يقول يا تارك الصلاة
مصيبتك أعظم من مصيبة إبليس ؛ لأن إبليس رفض أن يسجد لآدم
وأنت ترفض أن تسجد لرب آدم!!
فما الذي بينك وبين الله حتى تكره لقاءه؟!
صلِّي قبل أن يُصلى عليك ".
ትርጉም :
ጠየቁት : ሰላት እንዴት በትክክል መስገድ ጀመርክ ?
እንዲህ አለ: አንድ ሸይኸ ስለ ሷላት ማይስግድ ሰው ሲናገሩ
#ያንተ( ሙሲባ) ወንጀል ከ እብሊስ (ሸይጣን) በላይ ነው : ምክኒያቱም ሸይጣን ለ ኣደም (آدم) ሱጁድ ነው እንቢ ያለው ።
አንተ ደሞ ለ ኣደም ፈጣሪ(ጌታ) እኮ ነዉ ሱጁድ አልወርድ ያልከው!!!!
ስለዚህ ወንደም እህቶቼ በናንተ እና በ ጌታቹ ምን ቢኖር ነው እንቤ ምትሎት !!??
#ስገድ_ሳይሰገደበህ

Hamza media

05 Jan, 18:56


በየሶሻል ሚዲያው ይሀፀን በላው ይሄን ጠጣው እዚ ገባው እዚ ወጣው ብለው ቪድዮ ሚያሳዮን ሰዎች ግን ጥቅማቸው የገባው ሰው አለ?

Hamza media

05 Jan, 14:48


...ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው፡፡

👉 ተውበት...

((( وَكَذَٰلِكَ أَخْذُ رَبِّكَ إِذَا أَخَذَ الْقُرَىٰ وَهِيَ ظَالِمَةٌ ۚ إِنَّ أَخْذَهُ أَلِيمٌ شَدِيدٌ ፨ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لِّمَنْ خَافَ عَذَابَ الْآخِرَةِ ۚ ذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّجْمُوعٌ لَّهُ النَّاسُ وَذَٰلِكَ يَوْمٌ مَّشْهُودٌ ፨ وَمَا نُؤَخِّرُهُ إِلَّا لِأَجَلٍ مَّعْدُودٍ ፨ يَوْمَ يَأْتِ لَا تَكَلَّمُ نَفْسٌ إِلَّا بِإِذْنِهِ ۚ فَمِنْهُمْ شَقِيٌّ وَسَعِيدٌ ፨ فَأَمَّا الَّذِينَ شَقُوا فَفِي النَّارِ لَهُمْ فِيهَا زَفِيرٌ وَشَهِيقٌ ፨ خَالِدِينَ فِيهَا مَا دَامَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ إِلَّا مَا شَاءَ رَبُّكَ ۚ إِنَّ رَبَّكَ فَعَّالٌ لِّمَا يُرِيدُ )))

((( የጌታህም ቅጣት የከተሞችን ሰዎች እነሱ በዳዮች ሲሆኑ በቀጣቸው ጊዜ እንደዚህ ነው፡፡ ቅጣቱ በእርግጥ አሳማሚ ብርቱ ነው፡፡

በዚህ ውስጥ የመጨረሻውን ቀን ቅጣት ለሚፈሩ ሁሉ መገሰጫ አለ፡፡ ይህ (የትንሣኤ ቀን) ሰዎች በርሱ የሚሰበሰቡበት ቀን ነው፡፡ ይህም የሚጣዱት ቀን ነው፡፡

(ይህንን ቀን) ለተቆጠረም ጊዜ እንጂ አናቆየውም፡፡

በሚመጣ ቀን ማንኛዋም ነፍስ በእርሱ ፈቃድ ቢሆን እንጂ አትናገርም፡፡ ከነሱም መናጢና ዕድለኛም አልለ፡፡

እነዚያ መናጢ የሆኑትማ፡ በእሳት ውስጥ ናቸው፡፡ ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ ማናፋትና መንሰቅሰቅ አላቸው። ... )))

((አል-ሁድ 102 ፥107))

ኢስማኤል ወርቁ

https://t.me/amr_nahy1

Hamza media

04 Jan, 11:07


የኢትዮዺያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ አስመልክቶ ለመላው ሙስሊም ኡማ ያስተላለፈው መልዕክት

Hamza media

04 Jan, 09:17


ዛሬ ለይል ላይ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ለለይል ሰላት የተነሳችሁ ነበራችሁ እንዴ?

Hamza media

03 Jan, 19:51


እነሆ ለይሉ ጀመረ ቀን ያልነበሩት ህመሞች አሁን ሀ ብለው ጀመሩ እምባዎች መፍሰሳቸውን ቀጠሉ ያረብ ወደአንተው ተመልሰናል😔

Hamza media

03 Jan, 16:25


There's nothing allah cann't fix abshir🥰

Hamza media

03 Jan, 14:53


አስተውላችሁ ከሆነ ሶሻል ሚዲያ ላይ አሪፍ ተከታይ ያላቸው ፀጉራቸውን ገልጠው ሚጨፍሩ ወይም ስለዲናቸው ሳይሆን ተራ ወረፀን ሚዘባርቁ ሙስሊሞች ናቸው🧐ለምን ይመስላቹሀል???

አው ይህ ኡማን መግደያ አንዱ መንገድ ነው።ሶሻል ሚዲያው ላይ ያሉ ኡስታዞችና አሪፍ ኢስላማዊ ኮንተንት ሚሰሩ ሰዎች እስካሁን በማቀው ከ100,000 እና ከዛ በታች ናቸው በዛ ላይ የብዙዎቹ በስንት መከራ እዛ እየደረሰ በሪፓርት እየተዘጋ ምናምን አማ ተራ ጭፈራና ዝባዝንኬ ሚሰሩ ሙስሊሞች እስከ 1,000,000 የሚደርስ ተከታይ ይኖራቸዋል።ይህ ትልቁ ዘዴ ነው አንድ ሶሻል ሚዲያ ላይ የወጣ ሰው ትልቁ አላማው ተከታይ ማፍራት ነው ሰዎች ከይርን ሲሰሩ ሚያግዛቸው ስለማይኖር ወደዛ አንደፀ ሲዞሩ እሷም ሂጃቧን ስትል እሱም ሀይባውን ሲገፍላቸው ካፊሮች በተደራጀ መልኩ ፎሎው ላይክና የመሳሰሉትን በማድረግ ያበረታቷቸዋል ይህን ያዮ መሳኪኖች ደግሞ የራቁት ጭፈራ እስከሚባል ወንዱም ለመናገር ሚቀፋ ቪድዮዎችን ወደ መስራት ይሄዳሉ።የተወሰኑ ሰዎች ሲናገሩዋቸው ይበልጥ በዛ በኩል ትሩ እና ፌመስ ሚባሉት ሰዎች በጓደኝነት ይላኩላቸዋል ማስታወቅያ ስራ ለጉድ ነው ከሆነ ጊዜ ቡሀላ ዲናቸውን ያስጥሏቸዋል።ይህ ሚታወቅ ነውና ስም መጥራት አስፈላጊ አደለም ውዶች እንንቃ የአላህ ዲን እንዲ እስኪረክስ አንጠብቅ ወንድሞችን እናበረታታ ዲናችንን እናሰራጭ🙌

አቡ ሰኪና{ሀምዛ}🙌

Hamza media

03 Jan, 03:58


🌙⭐️በሰለዋት የደመቀ ጁመዐ ይሁን
የታመመ ሚድንበት
የታሰረ ሚፈታበት
የተጨነቁ ነፋሶችን አላህ ሚያሽርበት
ፏፏፏፏፏ ያለ ቀን ይሁን አሁን🤲🤲🤲ያረብ🤲

Hamza media

02 Jan, 22:12


ወላሂ ይችን ቃል እንድናገር ላረገኝ አላህ ምስጋና ይገባው ኢምሀል ወደ ጌታዋ ልትሄድ ነበር ወላሂ ላታምኑ ትችላላቹ ግን አላህ ማረኝ በዚ ሀለቴ መሞትን ፈርቼ ነበር አላህ ግን አዘነልኝ እህት ወንድሞቼ ሞት መች እንዴት እንደሚመጣ አናውቅም ተውበት ያስፈልገናል ወላሂ ከልቤ ነው ዱንያ አሁን ታበቃለች ከዛስ አስባችሁት ታውቃላቹ?ወረቢ አላህን ብቻ እናስደስት አላህ አያሳፍረንም ሞት ሀቅ ናት አትሽሹ ወደ አላህ ቶሎ ጊዜ የለም አላህን እንፍራ እንመለስ አላህ ሊምረን ቃል ገብቷል እኮ
አውፍ በሉኝ ዱዐም🥹ኢምሀል

Hamza media

01 Jan, 21:08


አንዳንድ ህመሞች አሉ እንቅልፍ ሚነሷችሁ እንቅልፍን በግድ ብታገኙ እንኳን ቅዠት ሚሆኑባችሁ አላህ ከንደዚ አይነት ህመም ይጠብቃችሁ🤲🥹

Hamza media

31 Dec, 20:03


አውቃለሁ ዙርያዬ ጨልሟል ባዶ ሆኛለሁ ውስጤ እያነባ ነው ድክምምምም ብሎኛል ግን አላህ አለኝ🥹አልሃምዱሊላህ የሻህን የምትፈትን ጌታ 😥
አንተ/አንቺ ከማመስገን ምን አገደህ/ሽ?

Hamza media

31 Dec, 18:11


ሶላት ላይ ስታረፍድ ለምን አረፈድክ ብላ ምተሰኮርፍ ሚስት ይስጥህ



ብሎ ሲመክረው ሰማው😂

Hamza media

31 Dec, 07:49


የዛሬ ገጠመኜን ላካፍላችሁ እና እውነተኛ የአላህ እና የዲን ፍቅር ያለው የሆነ ሰው ትምርት ይውሰድበት🙌

ከክላስ እየተመለስኩ ሜክሲኮ ጋር የሆኑ ሰዎች በጀመዓ ቆመው ነበርና ሳያቸው ብሬክስሩ ነው አልፋ ሚሏቸው የኔቶርክ ማርኬቲንግ አይነት ስራን ሚሰሩ ጀመዓዎች መስለውኝ ነበር።ከመሀከላቸው አንዱ ጠጋ አለና ወንድሜ እንደዚ(ስሙ ጠፍቶኝ ነው) ከሚባል የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ነው የመጣውት እና ትምርት ቤታችን መፅሀፍ ቅዱስን ከዘፍጥረት አንስቶ እስከ ራዕይ ድረስ ለማስተማር ቆርጦ የተነሳ ተቋም ነው አለኝ እኔም እንደማቀውና መማር እንደማያስፈልገኝ ብነግረውም ከመተው ይልቅ የተማርኩበትን በል እንደውም አንዳንድ ስብከቶችን ሊሞክር ሲል ድካም ላይ ስነበርኩ ካስፈለገ አስተምርሀለው እኔ ግን ሙስሊም ነኝ አልኩት ኦ ሙስሊም ወንድማችን ብሎኝ ወደ ጓደኞቹ ትቶኝ ተመለሰ።

ውዶቼ በዼንጤዎች በየመንገዱ መሰበክ ለኔም አዲስ አደለም ለናንተም አዲስ እንደማይሆን ተስፋ አደርጋለው።በየመንገዱ ጆሮዋችንን በስፒከር ሳይቀር ሚያደነቁሩን የነበሩ ሰዎች ዛሬ ላይ ግን ለየት ባለ መልኩ ከመጮህ ይልቅ መማር እና ማስተማር ላይ ትኩረት እያደረጉ የመጡ ይመስለኛል።እነዚህ ሰዎች ለመፅሀፋቸው ሰነድ እንኳን የሌለው ፀሀፊው እንኳን የማይታወቅ ከመሆኑ ጋር ትኩረት ሰተው ጊዜያቸውን ሰተው ገንዘባቸውን አፍስሰው የውሸት ትምርታቸውን ለማሰራጨት ምን ያክል እንደሚለፋ ስንመለከት እና እኛ ግን ከአላህ የሆነን ብቸኛና ትክክለኛ የሆነን ዲን ይዘን እሱን ከማስተማር ምን ያክል እንደተዘናጋን ተመልከቱ።እነዚህ ሰዎች ተቋም ከፍተው ውሸትን ሲያስፋፋ የኛ ሙስሊም ወንድሞች ግን እነዚን ውሸቶች ሚያጋልጡበትን ሶሻል ሚዲያ እንኳን ሼር በማረግ ጆይን በማለት አናበረታታቸውም።ለምሳሌ ያክል አልሂዳያ ኢስላማዊ ማዕከል፣ተውሂድ ኢስላማዊ ማህበር፣ራህማ ኢስላማዊ ማህበር በዋናነት በክፍለሀገር በጎዳና ላይ እና በሶሻል ሚዲያ ላይ የእነዚህን ካፊሮች ውሸት ለማጋለጥ እየለፋ የሚገኙ ጀመዓዎች ናቸው።ነገር ግን እነዚህ ካፊሮች እንደተቋም አደለም በግለሰብ ደረጃ እንኳን ያላቸውን የገንዘብ እና የሞራል ድጋፍ የኛ ተቋሞች የላቸውም ውዶች ወላሂ ነገ አላህ ፊት ቆመን እንጠየቅበታለንኮ!!!ሰዎች በውሸት እየከፈሩ ማገዝ ከጎናቸው መቆም ቢያቅተን እንዴት ከጎናች  ሚቆሙትን ማበረታታ ይከብደናል???ጥያቄው ለሁላችንም ነው🫶


አቡ ሰኪና{ሀምዛ}🙌

Hamza media

31 Dec, 07:18


عن طاوس قال: " لا يتم نسك الشاب حتى يتزوج"
ጧውስ ቢን ከይሳን የሚባሉት ታቢዒይ እንድህ አሉ:
" የአንድ ወጣት ዒባዳ እስካላገባ ድረስ ሙሉ አይሆንም"
😍😍
{ዐብዱ ረዛቅ ሙሰነፍ ውስጥ ዘግበውታል}

👉 ወጣት ሆይ አግባና ዒባዳህን ሙሉ አድርግ!

Hamza media

31 Dec, 06:37


የረጀብ ወር🥰

Hamza media

30 Dec, 16:22


እንደዚ አይነት ዘዉጅ ይወፍቀን🤲

Hamza media

30 Dec, 10:15


አዋጅ ለለጋስ እጆች በሙሉ…!

በኮተቤ አከባቢ የሚገኝ አንድ መስጂድ ላይ ያሉ ጀመዐዎች  በውሀ ማጣት ምክንያት  እየተቸገሩ ይገኛሉ። በመስጂዱ የሚገኙ የመድረሳ ተማሪዎች  እና  የመስዲጁ ጀምአ በውሀ አቅርቦት ችግር ምክንያት አንዳንዴም ከጎረቤትም በማምጣት ምቹ ባልሆነ ሁሌታ እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ታዲያ መልካም እጆች በሰደቀቱል ጃሪያ ይሽቀዳደሙ ዘንድ ቢላል ሚዲያ በትብብር የውሀ ሮቶ እንድንገዛ ይህን የኸይር በር ከፍቶ እየጠበቃችሁ ነው።ምን ጊዜም የሚቀጥል መልካም ስራ ሰውየው በሞተ ሰአትም አጅሩ አይቋረጥም ተብሏልና ኑ ለጀነት ተሽቀዳደሙ። ይህንንም ሀዲስ አስታውሱ…


عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ قَالَ:

"إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثٍ: صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ".
(رواه مسلم)


ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
"ሰው በሞተ ጊዜ፣ ሥራው ከሦስት ነገር በስተቀር ይቋረጣል፤

1. ሰደቀቱል ጃሪያ (ምንጊዜም የሚቀጥል በጎ ስራ)፣
2. በሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣
3. ለእርሱ ዱአ የሚያደልግ ጥሩ ልጅ።"

" ብዙ ያልነው ነገር በአንድ ላይ ስንካፈለው የገለባ ያህል ይቀላልና ፡ ተጋግዘን አኼራችንን እንገባ።"

ለ አገልግሎት ጥራት በዳሩል አርቀም የበጎ አድራጎት ማህበር አካዉንት በማስገባት ያስገባችሁበትን ደረሰኝ @Abu_osman4 ላይ ላኩልኝ

አካዉንት ቁጥር :- 1000451773759 (darul arqem developmnet and charity org )
ለበለጠ መረጃ :-
0939963771 ላይ ይደዉሉ

Hamza media

28 Dec, 18:52


ውዳችን ያሀቢቢ🥰

Hamza media

28 Dec, 12:36


ሲመጣለት ለማንበብ ከፈለጋችሁ ይህንን ቻናሉን ጆይን በሉት https://t.me/AhmedResponse

ትንሹ ይሉታል በርግጥ እውቀቱ ትልቅ ነው በሉ እናንተም ከሱ ተማሩ ጆይን በሉት ኢስላምን ዲፌንድ ሚያረጉ ወንድሞችን አበረታቱ🙌🥰

Hamza media

28 Dec, 12:34


ትላንት ዒሻ አካባቢ አንድ ጓደኛዬ “አንድ Batch ያለን ከእስልምና የወጣ ጀለስ አለኝ እና አወራው” ብሎኝ ነበር...እና ልጁ አንድም ከዘላለም ህይወት ጋር ያለ የነገር ድህነት ጉዳይ ጥያቄ ፈጥሮበት ከእስልምና እንደወጣ ገልፆልኝ ነበር...ዛሬ ጠዋት የነበራችሁ ካስታወሳችሁ ላይቭ ላይ እንደ ሟሟሻ ነገር የነገረ ድህነትን ሀሳብ ስዞርበት ጠቅለል ያለ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኘና ሌሎች ጥያቄዎቹንም እንደሚያነሳ ነግሮኛል!😊🙌 ደስ ይላል😁

እና ምን ምን ተረዳሁ መሰላችሁ...

1. በእስልምና አስተምህሮዎች ላይ ቋሚ በሆነ መንገድ ትምህርት መሰጠት እንዳለበት...ላለውም ለሚመጣውም ለያዘውም ለሚይዘውም እስልምና ይሄ ነው የሚሉበትን Affirmative አስተምህሮ ማስያዝ ላይ መሰራት እንዳለበት።

2. ወላሂ ረሳሁት😁 ሲመጣልኝ አነሳላቹሀለው😌

3. እና አንጠፋፋ ምርጦች ትመቹኛላችሁ🙄

Hamza media

28 Dec, 10:39


ትላንት ስለኒቃብ ስንጮህ "ዝም በሉ ለሰላም ያሰጋናል፣ፈርድ አደለም ሱና ነው፣መጀመርያ ሌላውን እወቁ ምናምን ስትሉን የነበራቹ እና የካፊሮች አሸርጋጅ የነሱ ቃል አቀባይ የነበራቹ ይኸው ዛሬ ሂጃቡም ተከለከለ አሁን ምን ትሉን ይሁን እስኪ እንስማቹ

Hamza media

26 Dec, 19:00


በጣም አብዝታችሁ የምትወዱት በዓለም ላይ እጅግ ብዙ ተከታይና ወዳጅ ያለው ሁሌ ለምትልኩለት መልእክት እንደው አንድ ቀን በቀጥታ ምላሽ በሰጠኝ እያላችሁ የምትጓጉለትና የምትናፍቁት ሰው ነገ ከራሱ ምላሽ ታገኛላችሁ ብትባሉ ምን ያህል ትደሰታላችሁ?ዛሬንስ የነገ መዳረሻ በመሆኑ እንዴት ይሁን በደስታ የምታመሹት?

ለይለቱል ጁመዓ እንደዛ ስትታሰብ ይበልጥ ስሜት ትሰጣለች።ለሰለዋትም መነቃቃታችን ይጨምራል።በደባሪ ስሜት ውስጥ እንኳን ስትከሰት እንደ ዒድ ዋዜማ ነው ሙድን የምታፈካው ምክኒያቱም ነገ ጁመዓ በመሆኑ አሽረፈል ኸልቅ ለእያንዳንዳችን ሰለዋት በቀጥታ ምላሻቸውን ይሰጡናል።ያን ማሰብ በራሱ ንዝረት ነው🥰

በፍጡራን ልክ የወዱዱዬ ሰላትና ሰላም ረቢዑን ባደመቁት ውዱ ነብይ ላይ ይሁን💚

Hamza media

25 Dec, 14:56


አል-ወዱዱ🥰
የእኔ አፍቃሪ ጌታ 'አል-ወዱዱ'ሲበላ የማይጠግብ ሲተኛ የማይነቃ ሲጫወት የሚወድቅ ከሚመስላት የልጅ ''እናት''ከተባለች ፍጡር የገዘፈ እንስፍስፍ ነው ለባሮቹ...
ለእንደኔ አይነት እልፍ ነብሶች ዝንጋቴ፣ድንበር ማለፍና በወንጀል መዘፈቅ የቀን ሌት ተግባራቸው ለሆኑቱ የሚቀጣበት አሳማሚ ቅጣት የሌለው ይመስል እሱን በማመፃቸው ቅናት ይሰማዋል መሽቶ በነጋ ቁጥርም ለመመለሳቸው እጆቹን ዘርግቶ የሚጠብቅ ጉጉ ጌታ ነው🥺
የእኔ አላህ...የእኔ ወዱድ... ወደእኔ ሲጓጓና ሲወድ እሱን በማምለክ ዐርሽን ያጨናነቁ መላእክቶች ያሉት እንኳን አይመስልም...ስንዝር ስጠጋው ክንድ በእርምጃ ስቀርበው በሩጫ ትንሽ መጠጋቴን አይቶ እጥፍ መርሀባ ብሎ ይቀበለኛል🥰
የእኔ ወዱድ ከአመፄ በቃኝ ብዬ ፍቅሩ የገባኝና የተመለስኩለት ለታ ከዚያ በበረሀ ላይ ስንቁን የያዘችው ግመል ጥፍት ብላበት ተስፋ ከቆረጠ ቡሀላ ብቅ ስትልለት ሚናገረውን እስከማያውቅ ከተደሰተው ሰው በላይ ነው ደስታው🥰
አል ወዱዱ ተቀብሎኝ ብቻ እኮ አያበቃም እኔው ነብሴን በድዬ አስቆጥቼውና ድንበሩን አልፌ ሳለ እኔን በመማሩ አይብቃቃም በሰራሁት ወንጀል እንዳላፍረውና እንዳልሳቀቅበት ሲል ጥፋቴንም ያስረሳኛል🥺
ፍቅሩ እስትንፋሴም ነው ዱንያ ስታደክመኝ ብርታቴአንዳንዴ ሆን ብሎ ወደእሱ ሊያስጠጋኝም ይመስለኛል ፈተናው ሲፈትነኝም ነው በዚህ ልክ እሱነቱን ያወቅኩት። ለዚያ ነው ከስብራቴ ምታከመውና ምበረታውም ምን ያህል እንደሚወደኝ በማስታወስ የሆነው🥰
ኢማኔ የደከመ ሰአት ከዝንጉነቴ ሚያባንነኝም ቅጣቱ ሳይሆን ፍቅሩ ነው በወንጀል መዘፈቄ ነብሴን ሲሰማት፣ ድርቀቷ ሲያሳምመኝ...ሲትሩን፣በእኔ ላይ ያፈሰሰው ኒዕማው፣ለእኔ ያለውን ውዴታ ሳስታውሳት ነው እንኳን ርቃው ጧት ማታ ብታመልከው እንደሚያንሰው አስባ ወደእሱ የምትከንፈው🥰
የእኔ ጌታ... የእኔ ወዱድ ፍቅሩ ሁሉ ነገሬ ነው ከዱዓዎቼ ሁሉ ተደጋጋሚውና በላጩ''አላሁመ ሁበክ ወሁበ መን ዩሂቡክ ወሁበ አመሊን ዩቀረቡ ኢላ ሁቢክ''የሆነውም ለዚሁ ነው
ወደህ አስወድደንማ የእኔ ጌታ🤲✍️
 

እእእእእ ፍቅሩ😭😭😭😭😭

©umu zinira

Hamza media

24 Dec, 10:09


Beallh margw betfagi nw betam sekay west ngi leallh belachu 1geze allh yagzsh belugi beze seat yet endmhed gera gebtogi zemmm beyalw beallh

Hamza media

23 Dec, 18:50


ዒልም የቀለለ ጊዜ ኡለማዎችም መቅለላቸው አይቀርም😔

Hamza media

23 Dec, 16:32


በሰለፎች ጊዜ ...
ከእያንዳንዱ ታላቅ ወንድ ጀርባ
እራሷን ምትጠብቅ (ድንቅ) ሴት አለች...
አሁን ደግሞ
ከእያንዳንዷ ተገላላጭ (ሀያእ የሌላት)
ሴት ጀርባ ...
ደዩስ የሆነ ወንድ አለ...

ደዩስ ማለት
ለቤተሰቡ ቅናት (ደንታ) የሌለው
ቤተሰቡ ውስጥ አፀያፊ ነገር ቢከሰትም ምንም የማይመስለው ።

Hamza media

29 Nov, 21:34


የሀን ህልምህን አስታወስከው አው የሀ እንቅለፍህን የሰዋህለት በአላህ ፍቃድ ይሳካል በርታ🙌

Hamza media

29 Nov, 21:30


እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም ይሉታል ዛሬ ስንቱ ለመጨረሻ ጊዜ ተኝቶ ይሁን የዛሬዋ ፀሀይ የመጨረሻዉ የሆነችለት ስንቱ ይሁን

አላህ ሆይ ጌትዬ ደካማ ባሮችህ ከምድርና ሰማይ በሚበልጥ ወንጀል ብንገናኝህ ገደብ በማይገኝለትህ ራህማህ ጀነትህን ወፍቀን🤲

Hamza media

29 Nov, 19:15


ሌላ ሌላውን የሰርግ ኮተት አላነሳውም ይነሳ ካላችሁ ግን ከማስረጃ ጋረወ አፈር ከድሜ እናበላዋለን🙌

Hamza media

29 Nov, 16:26


እኔ ምለው ግን ሰርግ በዛ ብርዱን ታሳቢ አድርገው ነው ወይስ.......😁

Hamza media

29 Nov, 14:22


Check your email🙌

Hamza media

29 Nov, 14:22


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ ወንድምና እህቶች በአላህ ፍቃድ ቻሌንጃችንን ሰኞ የምንጀምረው ሲሆን የተመዘገባችሁ ኢሜላችሁን ቼክ አርጉ የቴሌግራም ቻናል እየላክን ስለሆነ ያልተመዘገባችሁም ጊዜው ሳያልቅ ተቀላቀሉን🙌

Hamza media

28 Nov, 22:15


መካሪ ሆነህ ስትገኝ ሚከፋህ ሚያምህ አይመስላቸው አብሽር ወዳጄ የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው😊

Hamza media

28 Nov, 21:07


ወላሂ ሰላማዊ እንቅልፍ ማግኘት ችላ ልንለው ማይገባ ኒዕማ ነው😢ስንቶች አይናቸው ጣራው ላይ እያፈጠጠ ይሁን😞

አላህ ሆይ በጭንቀት ልባቸው የተሸበሩትን በሀዘን ልባቸው የተሰበሩትን በሀሳብ የዳከሩትን በህመም የደከሙትን ባርያዎችህን አንተው ድረስላቸው🤲ካንተ ውጭ አምላክ የሌለ የሆንከው ብቸኛ ጌታችን ሆይ በራህመትህ🤲

Hamza media

28 Nov, 20:24


በአላህ ፍቃድ ዝግጅታችንን ጨርሰናል🤲 ሰኞ ወደ ቻሌንጃችን እንገባለን ብዙዎች ዘንድ ሼር እንዲሆን ስቶሪ እና ሼር ማድረግ አትርሱ ከወዳጆቻችሁ ይህንን ቻሌንጅ እንዲቀላቀል ለምትፈልጉት ሰው ላኩለት🥰

Hamza media

28 Nov, 19:26


ተወዳጆች ጁሙዓ ደረሰኮ

Hamza media

28 Nov, 18:50


🥰ያረቢ ያአላህ ከፈተና ሶብር
🥰ያ ረሂም ከህመም መዳንን
ያ አላህ ከመከራ ፅናትን
ያ ረዛቅ ከሀዘን ደስታን
ያ አዚዝ ከጉለት ሙሉነት
ያያያያያያ ረብ አንተው አግራው 🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲ወላሂ ወረቢል አሽረፈል ኸልቅ የማያልፋ የመሰሉ ቀኖች ኢንሸአላህ ያልፋሉ ለጠፊ ዱንያ 1ሰከንድም ቢሆን አንዘን ሁሉ በእጁ ነው ጀሊሉ 🥰ያደርገዋል በዱዐ እንበርታ🤲🤲 ያረቢ እንበል እስኪ አንድ ላይ ታደርግልኛለህ አታሳፍረኝም 🥰🤲🤲🤲ኢንሸአላህ🥰
አመመኝ አሽረኝ
ቸገረኝ ስጠኝ
የቲም ነኝ አንተው ሁነኝ
አላህን መጠየቅ አያሳፍርም እኮ በሉት ያያያያያያያያ ረብ❤️
ኢምሀል 🥰 በዱአ አደራ🤲🥰ሀሚስ ነው ቀኑ ንጋቱ ጁመዐ 🥰

Hamza media

28 Nov, 18:19


ይህንን ሚቲንግ እነሆ አሁን ይፋ ላርግላቹ

አለም አቀፍ የቁርአን ውድድሩ የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆነ

2ኛው አለም አቀፍ የቁርአንና የአዛን ውድድር የሚካሄድበት ተለይቶ ጥር 25 ቀን 2017 መሆኑን  ይፋ መደረጉን አዘጋጁ ዘንድ እብን ሳቢት አስታውቋል ።
ጄይሉ ቲቪ 19/03/2017

በዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነትና በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነትና ክትትልና ድጋፍ የሚካሄደው ይህው አለም አቀፍ ውድድር ጥር 25 ቀን እንደሚካሄድ ያስታወቁት ኡስታዝ ኑረዲን ቃሲም ናቸው ።

የዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ኡስታዝ ኑረዲን እንዳሉት የዘንድሮ ውድድር የአለም አቀፍ ውድድሩ አብይ አስተባባሪ ኮሚቴ ከመጅሊስ ዑለማ ምክር ቤት ጋር ዝግጅቱን የተሳካ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን ፣ የአለም አቀፍ ውድድሩ የበላይ ጠባቂም ክቡር ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መሆናቸውን አስረድተዋል ።

በውድድሩ የሚሳተፉ ሀገራት ምዝገባና ልየታ መጀመሩን ገልጸው ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎችን በቅርቡ የማጣሪያ ውድድሮች በማድረግ እንደሚለዩ ጠቁመዋል ።
ለውድድሩ ዝግጅት  ስኬት በተለይ ደግሞ ለውጪ እንግዶች መስተንግዶ ፣ ለውድድሩ አሽናፊዎች ሽልማት እና ለሌሎችም አስፈላጊ  ወጪዎች ድጋፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ተቋማት አብረዋቸው እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ።

Hamza media

28 Nov, 17:25


ሲከፋን፣ስንጨነቅ፣ጉዳዮቻችን አልሳካ ሲሉንና ሲጨልምብን ወደ ሞት ሳይሆን ወደ አላህ ''ብንሄድ ይሻለናል''

በተለይም እንዲህ የኸሚስ ምሽትን ለመቀበል አላህ ሲያድለን፣ከጁመዓ ለይል አንስተን እስከ ጁመዓ ፀሀይ መጥለቂያ ጊዜ ድረስ ደጋግመን ወደ ሰለዋት እንፍጠን🖤

የአላህ ሰላትና ሰላም«በጁሙዐ ለሊት እና በጁሙዓ ቀን መቶ ጊዜ ሶለዋት ያደረገብኝ ሰው መቶ ጉዳዮቹን አላህ ይፈፅምለታል። ሰባዎቹ የአኺራ ጉዳዮች ሲሆኑ ሰላሳዎቹ የዱንያ ናቸው።»በማለት ጭንቀት ለፈጠሩብን ጉዳዮች መፍትሄውን ባስተማሩን ውድ ነብይ ላይ ይውረድ።

ሰሉ ዓለል ሀቢብ📿

Hamza media

27 Nov, 17:34


ተወዳጆች🙌

Hamza media

27 Nov, 12:23


ብዙውን ጊዜ ታላቁን ረመዷን እንናፍቀዋለን ነገር ግን ተዘጋጅተን ስለማንጠብቀው መስራት እና መጠቀም ከምንፈልገው 1% የሚያክለውን እንኳን ሳንጠቀመው ጊዜው ያበቃል።ነፍሳችንን ስናለማምዳት ለማዳዎቹ ቀድመውን ይሄዳሉ🏃‍♂‍➡️ለዚህ ነው አብረን እንዘጋጅ ያልነው ተቀላቀሉን ረመዷንን ተዘጋጅተን እንቀበለው በአላህ ፍቃድ ልዮ ረመዷንን እናሳልፋለን🙌

መመዝገብያ ሊንክ

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSda0MpnihxYAEOe_x5iDTWSqRl1klzIDDyjp-gNE2wFkYZ95w/viewform?usp=pp_url

Hamza media

27 Nov, 03:58


«በጣም የሚከብደው የኃጢአት ክፍል መጀመሪያው ነው። ቀጥሎ ይቀላል። ከዚያ በኋላ ትቀበለዋለህ። ሲቀጥል ትለምደዋለህ። ከዚያም ይጥመሃል። ከዚያ ሲቀጥል በልብህ ላይ ልማድ ሆኖ ይታተማል። ከዚህ በኋላ ልብህ ሌላ ሐራምን ፍለጋ ማማተር ይጀምራል።

(ረዋዒኡን ሚነሰ ፊከር)
@anbeb_islamic

Hamza media

26 Nov, 19:11


ያ ሰላም ጀነተል ፊርደውስን ለመውረስ ሚረዱትን ስራዎች ልፅፍላችሁ ነበር ግን ሚከታተል የለም ማለት ነው

Hamza media

26 Nov, 16:50


ተወዳጆች እስቲ ጀነተል ፊርደውስን መውረስ ምትፈልጉ ስንቶቻችሁ ናችሁ አሳዮኝ እስኪ👇

Hamza media

15 Nov, 09:07


Hamza media pinned «»

Hamza media

15 Nov, 07:24


የኸለቀኝ ጌታ መቼም አይተወኝም
ፈገግ ልበል እንጂ ሀዘን ቁዘማ ላፍታም አልመኝም 🥰🥰🥰🥰😁እስቲ ፈገግታ ሱና ነው 🤗 ቆንጅዬ ጁመዓ ይሁን 🤲🤲ኣሁን ሰሉ አለል ሀቢቢ ሩህ ሙሀባ❤️❤️❤️❤️❤️❤️ያግራው ሁሉን ሀጃ 🤗🤗እስቲ አላህ የግራልሽ በይ /በል 😘😘

Hamza media

15 Nov, 06:40


ፀሀይ ከወጣችባቸው ሁሉ ምርጧ ቀን አባታችን አደም የተፈጠሩባት ቂያማ ምትቆምባት የሳምንቱ ኢዳችን "ጁሙዓ" 🥰

አላህ ሆይ በዚች በተባረከች ቀን በተወዳጁ እና የነብያት መደምደምያ በሆኑት ነብይ ላይ ሰላትና ሰላምህን አውርድ🤲ያዘነውን ከሀዘኑ የተጨነቀውን ከጭንቀቱ ያጣውን ከማጣቱ ነጃ በለው🤲ከ 3 ጨለማዎች ውስጥ ሆነው የጠሩህን ነብዮ ዮኑስን የሰማህ ጌታ ሆይ ለኛም ዱዓችንን ስማን🤲ታመው በሆስፒታል አልጋ ላይ ያሉትን በራህመትህ አፊያውን ላክላቸው🤲ይችን ዱንያ ጨርሰው አንተን ለተገናኙህ ደግሞ ወንጀላቸውን ማርላቸው ቀብራቸውን ኑር እንዲሁም ሪያዱን ሚን ሪያዲል ጀናህ አርግላቸው🤲ረቢም ያላንተ ማንም የለንም ደካማ ነንና የልባችንን ባዶነት ባንተ ፍቅር የልባችንን ሀዘን በአስደሳቹ ኒዕማህ የልባችንን ድርቀት በቁርአንህ አርጥብልን🤲

በሱረቱል ካህፍ ተጀምሮ በሰለዋት አልፎ በዱዓ የሚዘጋ ውብ ጁሙዓን ተመኘውላችሁ🤝

አቡ ዙበይር{ሀምዛ}🙌

Hamza media

14 Nov, 19:20


ሁሌም እንደምንለው ነገን ማደራችንን አናቅምና አሁን ሁሉንም አውፍ እንበል ወደ አላህ እንመለስ ለይሉ ጁሙዓ ነው በሰለዋት ያበበ ለይል ይሁንላችሁ መልካም አዳር🙌

Hamza media

14 Nov, 19:19


ማሻአላህ በርቱ በአላህ ፍቃድ እንቀጥላለን እናንተ ብቻ ሼር አርጉ ሚውት ያረጋቹ ኖትፊኬሽን እንዲደርሳችሁ አንሚውት ማረግ አትርሱ ሪአክሽን ብታስቀምጡ ደግሞ ይበልጥ እየተከታተላችሁኝ እንደው ማወቅ ችላለው🙌

Hamza media

14 Nov, 19:16


አዎ እኚህ ታላቅ አሊም በሙዕተዚላዎች ፊትና ምክንያት ኢልምን ከሚያስተምሩባት ባግዳድ ከተማ እጅግ ትልቅ ስቃይ ደርሶባቸዋል መሰቃየት ተብሎ በቃል የማይገለፅ መሰቃየትን ተሰቃይተዋል የኢማሙ ሻፊዒይ ተማሪና የመጨረሻው የመዝሀብ ኢማም የሆኑት ኢማም አህመድ ቢን ሀንበል🙌

Hamza media

14 Nov, 19:07


የመጨረሻ ጥያቄ ተዘግጁ

Hamza media

14 Nov, 19:02


አልጁመሉ ሰሚናት ፊ ሸርሂ ሰፊና ገፅ 8

Hamza media

14 Nov, 18:54


የልብን ህመሞች ከነመድሀኒታቸው የያዘው ምርጥ ኪታብን ያዘጋጁት ታላቁ አሊም እና የሸይኹል ኢስላም ተማሪ የሆኑት አብኑል ቀይም ረሂመሁላህ🙌

Hamza media

14 Nov, 18:53


ለሁሉም ጥያቄዎች 3 ደቂቃ ሲኖራቸው እውቀታችሁን ለማስፋት ሞክሩ ለሌሎችም አጋሩ

Hamza media

14 Nov, 18:47


የተጠቀሱት ሁሉ የኢስላም ጀግና ኡለማዎች ሲሆኑ ትክክለኛው መልስ ግን መ,ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ሚለው ነው።ኩቱቡን ከላይ አያይዠዋለው ማየት ይቻላል🙌ወደ ቀጣዮ

Hamza media

14 Nov, 18:35


ዛሬ መብራት የለምና እስኪ እንቅልፍ እስኪመጣ ጥያቄዎችን እንጠያየቅ🙌

Hamza media

03 Nov, 13:25


አምና በጉራጌ ዞን እህቶች ኒቃብ ተከለከሉ ትንሽ ተጮኸ አሁን ባለኝ መረጃ ትምረት አቁመዋል በዚህ በትንሽ ግዜ ውስጥ ስንት አጀንዳ አነሳን ስንቱን ጣልን ይኸው አሁን ደግሞ እህቶቻችን ኒቃብ ተከለከሉ የመስጂድ ኢማም ታግተው ተገደሉ ሙስሊሞች በየቦታው በፍላጎትም ይሁን በግዳጅ እስልምናቸውን ለማስቀየር እየተሰራ ነው መሳጂዶች እንደቀላል እየፈረሱ ለግለሰብ እየተሰጡ ነው ብዙ ብዙ ታዲያ ቆይ ምንድነው ማረግ ያለብን?

Hamza media

03 Nov, 12:05


ኧረ በዛ በአላህ ኒቃብ ፈርድ ነው ሱና ነው እያላችሁ ምታወሩ ወንድም እህቶች ምን ሆናችሁ ነው ቆይ እየጠየቅን ያለውኮ የእስልምና መለያ ነው ለምን ይነካል ነው እንጂ ሁክሙንኮ አደለም🤐ሌላ ህመም አትሁኑብን ተው

Hamza media

02 Nov, 17:20


ሰዎች እስኪ የገባችሁ አስረዱኝ ሙስሊሙ ኡማ ላይ እየተካሄደ ያለው ነገር የገባው አለ?ኡማው ያለበት ሀለትስ የተረዳ አለ?

Hamza media

02 Nov, 14:58


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ ወንድምና እህቶች ሰሞኑ በተፈጠረው የሙስሊም እህቶቻችን የኒቃብ ክልከላ ጉዳይ ላይ ብዙ ሲባል ሰምተናል በጣም ብዙ ከሙስሊሙም በኩል ይሁን በሌላው የእውቀት ማነስ ነው ብዬ አልፌው ነበር ዛሬ ግን በአንድ ሴት ላይ መልስ መስጠት ግዳጅ ስለሆነብኝ ይሀረን ለማለት ሞክርያለው በተቻላችሁ አቅም ሼር እና ላይክ በማረግ አድርሱልኝ

https://vm.tiktok.com/ZMhCWRr6q/

Hamza media

30 Oct, 05:20


አዳምጡትና ተማሩበት
እኔም አላስችለኝ ብሎ ነው አቦ

የኔ ➋ ጥያቄወች⁉️

➊ኛ....

👉የአሜሪካን ስደተኛ ዲያስፖራ‼️
👉የካናዳ ስደተኛ ዲያስፖራ‼️
⛔️የአረብ ሀገር ስደተኛ ብቻ ጥርዝ ለምን⁉️

➋ኛ....

የአሜሪካ ስደተኛ ይከበራል
የካናዳ ስደተኛ ይከበራል
የአውሮፓ ስደተኛ ይከበራል
የአረብ ሀገር ስደተኛ ግን ምንም ቢሰራ አይመሰገንም ስሙ ጂል መሀይም ደንቆሮ ነው ለምን⁉️

👉መልስ ከናንተ እፈልጋለሁ⁉️

እስኪ ጠንክራችሁ አስደስቱኝ በአሏህ⁉️

https://t.me/Advicerefugees
https://t.me/Advicerefugees

Hamza media

29 Oct, 17:55


አንዱ ታዋቂ ሰው ሚዲያ ላይ ቀርቦ እኔ ኒቃብ ግዴታ ነው ብዬ አላስብም Bla bla ብሎ ሲቀደድ ሰማሁት.....የአንተ ኒቃብ ዋጂብ አይደለም ብሎ ማሰብ ታዲያ እኛ ምን አገባን?እንደው ሙስሊሙን መጥቀም ባትችሉ እንኳ አፋችሁን ብትዘጉልን ምን አለበት በአላህ? የእህቶችህ ስቃይ ተመችቶሀል ነው🥺? ኒቃብ ግዴታ ነው ብላ የጌታዋን ውዴታ ፈልጋ የለበሰች ሴት መገፋት አለባት? ስለአንተ አስተሳሰብ ሲጀመር ምን አገባን.....ወደ ገደለው ስመለስ መራቆት መብት እንደሆነ ሁሉ ሴት ልጅ ኒቃቧን ለብሳ የመማር የመስራት መብት አላት።ለዚህ ደሞ ጊዜው አሁን ነው መቀለዱን ትተን የጉዳዩን አንገብጋቢነት እና የእህቶቻችንን ጭንቀት ተረድተን በሰለጠነ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መፍትሄ መፈለግ ግድ ነው።

በኒቃብ ፎቶ እየፖሰቱ ኒቃብ ከምንም አላገደኝም አይነት ሙድ የምናራምድ ሰዎች እንጠንቀቅ የኒቃቡ አላማ ይሄ አይደለም🙌 ፎቶ በመለጠፍ የሚመጣ ለውጥ የለም።

Hamza media

27 Oct, 21:26


ነገ ሰኞ ነው በመፃም ላይ በርቱ ፃም የጀሰድምህ የሩህም መድሀኒት ነውና📚

Hamza media

27 Oct, 21:21


العافية 👉
እነዚያ አልጋ ላይ እንቅልፍ አተው በህመም በስቃይ የሚያሳልፉ እህት ወንድሞቻችን አላህ ስብሩን ክፍያውን  አፊያውን  ይስጣቸው 😢🤲😢🤲😢

Hamza media

27 Oct, 19:44


⚠️#ተጠንቀቁ

ቴሌግራም inbox ላይ ከማንም ቢሆን ምስሉ ላይ ያለውን አምሳያ ሊንክ ከተላከላቹህ በፍፁም አትንኩ ‼️

ይህን መሰል ሊንኮችን ከነካቹህ የቴሌግራም አካውንታችሁን ታጣላቹህ። አካውንታችሁን ስታጡ ብዙ ፋይሎችን አንድ ላይ ታጣላቹህ። ከዚህም በላይ የቴሌግራም አካውንታቹህ በቫይረሱ ምክንያት ከቁጥጥራቹህ ውጭ በመሆን ለሁሉም contact መሰል ቫይረስ እናንተ እንደላካቹህ አድርጎ በመላክ የናንተ ሰዎች አካውንት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ይዳርጋል።

ይህን መሰል ሊንክ ከማንም ቢላክላቹህ ከፍታቹህ ወደ ውስጥ አትግቡ‼️

@yasin_nuru @yasin_nuru

Hamza media

25 Oct, 06:48


Live stream finished (1 minute)

Hamza media

25 Oct, 06:47


Live stream started

Hamza media

25 Oct, 06:25


1aschgare beharen lemtags bezuu sekay new legia 🤐

Allh gn yhn hula alm be eznt 🥹🥹subhanlallhe le tagashnth🥰(ሷቢር)
Ke kutah eznth mekdemu ayy yene geta 🥹🥹🥹ke hulu azenth belachu eznthn nebyuna Muhammadn shelmkn 🤲🤲🤲🤲🤲🤲ya shebab selu al nebi ❤️aselatu weselamu ala habibina Muhammad fedak abi weumi ya habibela😍😍
Konjeye jumea temgihu🤗

Hamza media

25 Oct, 05:58


ጁሙዓ የሳምንቱ ኢዳችን ታላቁ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል በጁሙዓ ውስጥ አንዲት ሰዓት አለች በዛች ሰዓት ባርያ ዱዓ ያደረገ እንደው ዱዓው መቅቡል ነው ብለዋል 🤲በዱዓችሁ

Hamza media

25 Oct, 00:16


ብዙ እንቅልፍ አልባ፣ህመም፣ሀዘን፣እምባ የተሞላባቸው ለሊቶች በሀያታችን ውስጥ እያለፋ ይሆናል።አብሽሩ ነብዮላህ ዩሱፍን ከጉድጓድ አውጥቶ ንጉስ ባደረገው ጌታ ላይ ተመኩ ሁሉን ለርሱ አደራ ስጡ እሱ ማስተናበሩን ያውቅበታልና🤲🤲🤲

Hamza media

24 Oct, 19:30


በታላቁ ነብይ በእዝነቱ አውራ የልቅና ባለቤት የፍቅር ቁንጮ በሆኑት እሳቸው በስነ ምግባር ሳይሆን ስነምግባር በሳቸው በሚለካባቸው ውድ ነብይ ላይ ሰለዋት አውርዱ በርግጥም በሳቸው ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ አላህ በሱ ላይ 10 ሰለዋትን ያወርዳልና💐

Hamza media

24 Oct, 19:28


كن حامدا، فقد سمع الله لمن حمده🌴

አመስጋኝ ሁን በርግጥ አላህ ያመሰገነውን ሰምቷልና🙌

Hamza media

23 Oct, 21:08


ነገ ሐሙስ ነው ጹሙ 🌹🌺

Hamza media

22 Oct, 23:01


ጭንቀት የተሞላባቸው ቀናቶች፤
እንቅልፍ አልባ ለሊቶች፤
ደስታ አልባ ሳቆች፤
ሰርባዶ የመሰሉ ህልሞች፤
ሩቅ የሆኑ ግቦች፤


መፍትሄው ምን ይሁን???

Hamza media

22 Oct, 13:14


🗳«መርካቶ ላይ በተከሰተው እሳት ሙሲባ ለደረሰባቸው ወንድሞች ማፅናኛ እና ምክር»

📌 በሚል ርዕስ መደመጥ ያለበት እጥር ምጥን ያለ ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ነሲሃ።

🎙 በሸህ:-አቡ ቀታዳ አብደላህ አለህ ይጠብቀው።

🕌 በመርከዘ አስ ሱና ቂልጦ ጎሞሮ አለህ ይጠብቃት

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
📲አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን ለመከታተል:-

🖥️ በ Telegram~Channel
📎
https://t.me/merkezassunnah/12048

Hamza media

21 Oct, 20:33


مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَمَن يُؤْمِن بِاللَّهِ يَهْدِ قَلْبَهُ ۚ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ከመከራም (ማንንም) አይነካም በአላህ ፈቃድ ቢኾን እንጅ፤ በአላህም የሚያምን ሰው ልቡን (ለትዕግስት) ይመራዋል፤ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

Hamza media

21 Oct, 19:40


🌔ተወኩል💫
ታላቁ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ማለታቸው ከኡመር(ረዲየላሁ አንሁ) ከተወራ ሀዲስ ተዘግቧል "በአላህ ላይ ትክክለኛ የሆነ መመካትን ብትመኩ ኖሮ ወፍን እንደሚረዝቃት እናንተንም ይረዝቃችሁ ነበር።ባዶ ሆዷን (የተራበች)ሆና ትወጣለች ጠግባ ትመለሳለች።"አህመድ፣ቲርሚዚይ፣ነሳዒይ。。。ዘግበውታል።

Hamza media

20 Oct, 20:32


ድሮ ድሮ ሰላት ባለመስገዴ አላህ ሚቀጣኝ ስለሚመስለኝ ሰላትን እሰግድ ነበር አሁን አሁን ግን。。。እያደግኩ ስመጣ ለካ ሰላት አለመስገድ ለሰላት አለመወፈቅ እራሱ ትልቅ የአላህ ቅጣት ነው📚

Hamza media

20 Oct, 20:28


  "الحياء"  ታላቁ የአላህ መልዕክተኛ አለይሂ    ሰላቱ ወሰላም በተከበረው ንግግራቸው እንዲህ ብለዋል "ሀያዕ ከኢማን ነው" ሀያዕ በጠፋበት ዘመን ላይ የኢማን ክፍል የሆነውን ሀያዕን በመያዝ ላይ አደራ።ሙስሊሞች ሆይ በሩ ከፊት ለፊት እያለ መስኮት ፍለጋ ጊዜያችሁን አታባክኑ📚📚📚

Hamza media

20 Oct, 15:01


☀️አይኑን ከመሬት ባቆራኘ ወጣት ላይ
የአላህ እዝነት ይውረድ

Hamza media

18 Oct, 11:27


ዐይነ በሲሩ ህፃን  
 
     ኹፊያ      በጢብሪዝ ከተማ እምብርት ላይ የምትገኝ የገበያ መዐከል ናት፡ ነጋዴዎች እቃዎቻቸውን ሸካክፈው እዚህ እዚያ ይንቀዋለላሉ
              ከተርታ መደብሮቹ ትይዩ መንገድ ላይ አንድ የተጎሳቆለ ልጅ ተቀምጧል፡ አይኖቹ ማየት የተሳናቸው ህፃን ነው       ፊቱን እግሮቹ መሀል ወሽቆ  ከፊት ለፊቱ  ሳንቲም የሚቀበልባትን ባርኔጣ ገልብጦ አስቀምጧታል  
   ከአጠገቡም እንዲህ ሲል የተፃፈባት  ወረቀት  የመንገዱን ጠርዝ ተደግፋለች
" አይኖቼ  ማየት ስለማይችሉ  እርዳታችሁን እሻለሁ"

አላፊ አግዳሚው  አለፍ አለፍ እያለ  1   1 ሳንቲሞችን ጣል ያረግለታል፡ ምፅዋቱ በዚሁ ከቀጠለ ከአንድ ደረቅ ዳቦ መግዣነት አያልፍም  ፡  አንድ የጢብሪዝ ነዋሪ በለማኙ ህፃን በኩል ሲያልፍ    ሳንቲሞችን ከጣለለት በኋላ ወደ ልጁ ጠጋ ይልና  መለመኛዋን ወረቀት ገልብጦ አዲስ ጽሁፍ ጽፎባት   መንገዱን ቀጠለ፡
        ይህ ሰው ከሄደ በኋላ ሰዎች ለእርዳታ ይጎርፉ ጀመር፡  ህፃኑ የእግር ኮቴ በሰማ ቁጥር ተከታይ የሳንቲም ኩሽኩሽታዎችንም ያጣጥም ነበር ፡

          የወረቀቷን ፅሁፍ የቀየረው የጢብሪዝ ነዋሪ ተመልሶ ሲመጣ ህፃኑ በእርምጃዎቹ ዳና ይለየውና    "አንተ ሰው እባክህን  ቅድም በአዲስ ፅፈህልኝ የሄድከውን መለመኛ ምን እንደሆነ ንገረኝ" አለው በሚያሳዝን ድምጽ   ፡ጢብሪዚዪ ወደ ልጁ ጆሮ አጎንብሶ አንሾካሾከለት፡አዲሱ ፅሁፍ ቀጣዩን ይመስላል
        😔""ዛሬ ቀኑ ደስ ይላል   እኔ ግን ላጣጥመው አልችልም""
ღ¸.✻´
✻.¸¸ღ
     አንተስ ለዐይኖችህ አመስግነሃል?