Fuad Muna (Fuya) @fuadmu Channel on Telegram

Fuad Muna (Fuya)

@fuadmu


የኛ እዉነታ የሌሎችን ስጋ ለብሶ ሲቀርብ!
በፅሁፍ ያስነበብኳችሁን በድምፄ ስትሰሙት!

ለአስተያየትዎ
@fuadmubot


ዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
የፌስቡክ አካውንቴን ለማግኘት www.facebook.com/fuadmuna14
ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com

Fuad Muna (Fuya) (Amharic)

የአንድ ሴቶችን ለብሶሽ ሲቀርብ፣ አንድ ጉልበት እንደሚከተለው የሚያስነበብሽን በድምፄ እንጠቀማለን፡፡ ይህን ቦት ምላሽ ለብሶሽን ሲፈላሽ፣ ስለብሶሽ ዝምድና አምርር ቻናል @fuadmubot። nnዩቲዩብ ቻናል http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna እና ለፌስቡክ አካውንቴ እባኮት www.facebook.com/fuadmuna14 ለፒዲኤፍ ብሎግ www.fuadmuna.wordpress.com ለማግኘት፡፡

Fuad Muna (Fuya)

05 Jan, 07:10


ውሀ!

የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!

መልካም እሁድ!

Fuad Muna (Fuya)

03 Jan, 12:08


የኢፋዳ መፅሀፍ የመጨረሻዎቹ ኮፒዎች እየተሸጡ ነው። የገዛችሁ ቶሎ መፅሀፋችሁን ውሰዱ መፅሀፍ እያለቀ ነው።

መግዛት የምትፈልጉ @ifadasales ላይ መግዛት ትችላላችሁ።

መልካም ሸመታ!

Fuad Muna (Fuya)

03 Jan, 07:05


ውሀ የሌለባቸውን ገጠራማ አካባቢዎች ውሀ ለማዳረስ የጎደሉ አሉ ብለን ፕሮጀክት ከጀመርን ቆየን!

በጅማ ሳኮሩ ወረዳ አንድ የውሀ ጉድጓድ እንዲሁም በሐረማያ ሁለት የውሀ ጉድጓዶችን አስቆፈርን።

በመሀል እስረኞችን ነፃ በማውጣት የጎደሉ አሉ ሁለትን አካሂደን ነበር።

አሁን ሰዓቱ የውሀ ነው። የጎደሉ አሉ ፕሮጀክታችን በውሀ ፕሮጀክት ተመልሷል። የምንደፋው ውሀ ቅንጦት ለሆነባቸው ወንድም እህቶቻችን እንድረስ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ውሰዱ። የዚህ ትልቅ ፕሮጀክት አካል ሁኑ። የማይቋረጥ ሰደቃ ሸምቱ!

መልካም ጁሙዓ!

Fuad Muna (Fuya)

01 Jan, 16:29


ዋ... ወንድነት!
(ፉአድ ሙና)
.
የኔ ቆንጆ... ለሁላችንም ያላቸውን ጥላቻ ባንቺ በኩል ለማስተንፈስ ሲሞክሩ እያየሽ ነው አይደል? የኔ ያልሻቸው ደም የተጋራሻቸው ሰዎች... እንወድሻለን ያሉሽ ቁሸቶች ጊዜ ጠብቀው ምን እንደሚደግሱልሽ ተረዳሽ? «ድህረ ሰላም... እስላም!» ብለው ከመጀመሪያው ዝተውልሽ ነበር አሉ!

ገና ከፌደራል መንግስቱ ጋር የያዙት ጦርነት ሳያልቅ የበቀል ክንዳቸውን እንዴት አንቺ ላይ እንደሚያሳርፉ ሲጎነጉኑ የነበሩ የፍጥረት አተላዎች ናቸው። ቀን በቀን የአላህን ንግግር እውነታነት ቢያስረግጡልሽ አትገረሚ!

የሚያስመልጥሽ ክንድ የለም። ይጋፋበት ክንድ ያለው አንድ እንኳን ሙስሊም ወንድ የለሽም። ሁሉም የበታች ነው። ሁሉም ወራዳ ባሪያ ነው። ርካሽ ነን የኔ አለም። አንቺን እናድንበት ድምፃችን ሰሏል። እንደቁስበት ክንዳችን ዝሏል። በፍርሀት ተሸብበን ሁኑ ያሉንን እየሆንን ነው የኔ ንግስት!

ጌታሽ ቀድሞ እነዚህ ጠላቶችሽ በደም አይደለም በስጋ አካል እንኳን ብትጋሩ እንደማይመለሱልሽ ነግሮሽ ነበር።

«وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ الْيَهُودُ وَلَا النَّصَارَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى اللَّهِ هُوَ الْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ اتَّبَعْتَ أَهْوَاءَهُم بَعْدَ الَّذِي جَاءَكَ مِنَ الْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡» (በቀራ፣ 120)

ድረስልኝ አትበይኝ የኔ ፍቅር! በስሜቴ የተተበተብኩ ርካሽ ነኝ! እንደ ሙዕተሲም አዘምትልሽ ጦር፤ እቆጣልሽ ወንድነት የለኝም። ሲልኩኝ ወዴት ሲጠሩኝ አቤት የምል ወራዳ ነኝና ወደኔ አትጣሪ። ወደ አላህ ጩሂ የኔ ውድ! ወደማይነጥፈው ንግስና ተጣሪ! የእርሱ ክንድ አይዝልም። እርሱ ይደርስልሻል ውዴ!


«فَفِرُّوا إِلَى اللَّهِ ۖ

«ወደ አላህም ሽሹ፤» (ዛሪያት፣ 50)

እኔ ግን ለራሴ ብቻ ሳይሆን ላልመለስኳቸው የድረስልኝ ጩኸቶችሽም አነባለሁ! ለራቀኝ ወንድነት... ለተሸከምኩት ወራዳነት እንሰቀሰቃለሁ። አንድ ቀን ጭንቅላቴ ቀና ይላል። ሲነኩሽ አይሆንም ብዬ አስቆምበት ክብር አገኛለሁ ብዬ ከጌታዬ እከጅላለሁ። እስከዛው ግን ውዴ ወደ ጌታሽ ጩሂ.... እኔ ወራዳ ሆኛለሁ።

በበዳዮች ላይ የአላህ እርግማን ይውረድ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

01 Jan, 14:46


50 ሺህ ብር ደርሰናል!

የተጠሙትን ለማጠጣት...

ደግ እጆች ሰደቃ እየወረወሩ ...

ውሀ በሌለባቸው ገጠራማ ቦታዎች ውሀ እያወጡ ነው።

ይህ ትልቅ ሰደቃ ነው። እድሉ አያምልጣችሁ። በራሳችሁ፣ በሞቱባችሁ እንዲሁም በምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሰድቁ።

በሀውድ ይተካል ኢንሻአላህ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ጎራ በሉና ውሰዱ። በርቱ እንበርታ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

01 Jan, 09:50


አንድ የተቸገረ ቤተሰብ አለ። የሚላስ የሚቀመስ ያጣ... እንደ መፍትሔ ባልየው የፈርኒቸር ባለሙያ ስለሆነ ስራ ይፈልጋል። በዚህ ሙያ ላይ አልያም ሌላም በተሻለ ዘርፍ የሚቀጥረው ካለ @Fuadmuna ላይ ያናግረኝ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

31 Dec, 19:40


የረጀብ የመጀመሪያ ምሽት ላይ እንገኛለን።

በዚህች የረጀብ የመጀመሪያ ለሊት ዱዓ አይመለስም። የልብ የልባችሁን ለአላህ አቅርቡ።

አደራ ከላጤነትም ገላግለን ማለት አትርሱ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

30 Dec, 16:59


ላጤ ሆይ!
በአማርኛ ፅሁፍ ስትመከር እንቢ ብለሀል።
እስኪ በአረብኛ ቪዲዮ ተመከር።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

30 Dec, 06:06


40 ሺህ ብር ደርሰናል!

የተጠሙትን ለማጠጣት...

ደግ እጆች ሰደቃ እየወረወሩ ...

ውሀ በሌለባቸው ገጠራማ ቦታዎች ውሀ እያወጡ ነው።

ይህ ትልቅ ሰደቃ ነው። እድሉ አያምልጣችሁ። በራሳችሁ፣ በሞቱባችሁ እንዲሁም በምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ ስም ሰድቁ።

በሀውድ ይተካል ኢንሻአላህ!

አካውንት @Fuadmuna ላይ ጎራ በሉና ውሰዱ። በርቱ እንበርታ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

27 Dec, 08:17


ለሰደቃ ባልተቤቶች ያማረ ጁሙዓን ተመኘሁ።

የጁሙዓ ሰደቃችሁን ለውሀ ጉድጓድ አውሉ። @Fuadmuna ላይ አካውንት ማግኘት ትችላላችሁ።

Fuad Muna (Fuya)

26 Dec, 19:22


ዛሬ ቴሌግራም ላይ የምንተፋ ሊንኮች በብዛት እየተሰራጩ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / ኢንሳ አሳውቋል።

ስለሆነም ከምታውቁትም ሆነ ከማታውቁት ሰው የሚላኩላችሁን ሊንኮች ባለመክፈት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ።

ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ቁፋሮው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ @fuadmuna ላይ ጎራ ብላችሁ አካውንት መውሰድ ትችላላችሁ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

25 Dec, 16:17


ጥራዝ ነጠቆቹ
(ፉአድ ሙና)
.
ዛሬ ስለፍቅር ጋብ አድርገን ስለ ጥላቻ ብናወራስ? ስለነዚያ ቢችሉ የጀነትን በር ይዘው ሌላ ሰው እንዳይገባ ለማድረግ ስለሚሹት ሠዎች እንወያይ! ደግሞ የሆነ አራት ኪታብ ቀርተዋል። በእነሱ አለም በራስ ጭንቅላት ማሰብ ነውር ነው። በኡስታዛቸው ጭንቅላት ይነዳሉ።

ከተግባርህም ሆነ ከንግግርህ ውስጥ በጉጉት የሚጠብቁት ወደ ስህተት ሊተረጎም የሚችል ነገርን ነው። ስህተት መሆን አይጠበቅበትም። ከመሰለ ይበቃቸዋል። «አላህን ፍራ!» በሚል ተቀፅላ ጀምረው የስድብ ጥማታቸውን ያስታግሱብሀል።

እነዚህ ሰዎች ለመምሰል እንደሚሞክሩት ብፁዕም አይደሉም። በወንጀል እጅጉን ሊበልጡህ ይችላሉ። በማስመሰል ህይወታቸውን ይመራሉ የምቀኝነትና የቅናት ድግሪ አላቸው። የእነሱ የእስልምና ትርጓሜ  ሰውንም ሆነ ራስን ማስጨነቅ ነው።

እነዚህ ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም? እስኪ የገጠማችሁን አካፍሉን!

ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ለማስቆፈር ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው። ለመሳተፍ የምትፈልጉ @Fuadmuna ላይ አካውንት ጠይቁኝ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

24 Dec, 15:59


መፈቀር
(ፉአድ ሙና)
.
ቤብ... እወድሻለሁ ሲልሽ አመንሽው? ንገሪኝ! አፈቅርሻለሁ ሲል ተቀበልሽው ወይ? ለምን? በምን እርግጠኛ ሆንሽ? ባለትዳር ራሱ ብትሆኑ እንደሚወድሽ በምን አወቅሽ?

ይኼኔ የእኔን ፅሁፍ እየላከ ነው አይደል ያሰመጠሽ? በየትኛው ነው የጀነጀነሽ? በልብወለዶቹ ወይስ በግጥሞቼ? እንዳትሸወጂ ቤብ! ቢያገባሽ እንኳን እንደሚወድሽ እርግጠኛ መሆን አትችይም!

እና በምንድነው እርግጠኛ የምሆነው አልሽ? ለምን የእኔዋ ያረጋገጠችበትን መንገድ አላጫውትሽም? እሁድ ጠዋት ነበር። ውዴ ሀይድ ላይ ነበረች። ሀይድ ላይ ስትሆን ድካም ድካም ይላታል። ብርድልብሱን ገፍፋ እግሮቿ ስር ሰብስባው ጭው ያለ እንቅልፍ ጥሏታል። ግንባሯን ስሜ በጠዋቱ ወደ ቀጠርኩት ሰው ለመሄድ መለባበስ ጀመርኩ።

እየለባበስኩ በስስት አየኋት። ታምራለች። ከጀልኩ... ከዛ ግን ሲዝኑ እንደማይፈቅድ ራሴን አስታወስኩት። (ላጤ ሆይ ሴቶች ሰላት በሌላቸው ወቅት ነፃ ፍልሚያ እንደሌለ እወቅ!) በስስት ካየኋት በኋላ ፍቅሬን የምገልፅበት ቆንጆ ስጦታ አሰብኩ።

ከመቅፅበት ስልኬን አውጥቼ የባንክ አካውንት ቁጥር ፃፍኩና ሪዝኑ ላይ For my love ብዬ አስተላለፍኩ። ስክሪን ሾት አድርጌ ከእንቅልፏ እንደነቃች ታየው ዘንድ ላኩላት።

ከሄድኩበት ስመለስ ሚስቴ ፊቷ ተንቆጥቁጧል። እንዳየችኝ እየሮጠች መጥታ ተጠመጠመችብኝ። ምነው ስላት «እስከዛሬ እንደምወድህ አውቅ ነበር፤ ዛሬ ግን እንደምትወደኝ አወቅኩ።» አለች።

እና አሁንም ሪል ነው ሼር የሚያደርግልሽ ቤብ? አንቺስ ብትሆኚ? «ሴት ልጅን ለማስደሰት የሚረዱ ቁልፍ ጥበቦች» የሚል ፅሁፍ ነው የምትልኪለት? በቃ ይሄ ነው ውዴታሽ? ውዴታህ?

አሁን @Fuadmuna ላይ ናና አካውንት ስጠኝ በለኝ። እኔ ደሞ አልሰስትም እሰጥሀለሁ። አንቺም ቢሆን እንደዛው! በምሰጣችሁ አካውንት የጉድጓድ ውሀ ለማስቆፈር የሚውል የአቅማችሁን ገንዘብ በምትወዱት ስም አስገቡ። ሪዝን ላይ For my Love በልና አስገባ። ከዛ ስክሪን ሾት አድርገህ ላክላት። ዘላቂ አጅር ከመሸለም ወዲያ ምን ፍቅርን ይገልፃል ወገን? ካገባህ አዳርህ ይባረካል... ካላገባሽ ትዳርሽ ይፈጥናል ስልሽ!

አንተ ዝም ብለህ ሪል ላክ ሰው ሰደቃ ይልካል 😂😂😂
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

23 Dec, 19:17


ምን አልን!
.
የውሀ ጉድጓድ ነው እናስቆፍር ያልነው!

የተጠማ ነው የሚጠጣው!

ወንዝ ከከብቶቹ ጋር ውሀ እየጠጣ በውሀ ወለድ በሽታ ለሚሰቃየው ነው የምንደርሰው!

ውሀ ልቅዳ ብላ ረዥም መንገድ ስትሄድ ለምትደፈረው እህታችን ነው የምንደርሰው!

በአቅራቢያዋ ውሀ ባለመኖሩ የውሀ መቅዳት ሀላፊነቷን ለመወጣት ከትምህርት ገበታ ለተገለለችው እህታችን ነው የምንደርሰው!

የማይቋረጥ ሰደቃ ነው። ብልጦች ሆይ! ተሽቀዳዳሚዎች ሆይ! ወደ ጀነት ነው ሩጫው!

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!

በዚህ ውብ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ አካውንት ለመውሰድ @Fuadmuna ጎራ በሉ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

22 Dec, 10:40


ሀያ እሁድን በሰደቀተል ጃሪያ!

አንድ ላይ ሆነን ለጎደሉብን ውብ ነብሶችና ለራሳችን የሰደቀተል ጃሪያ የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈር በዚህ አንድ ወር ውስጥ ገንዘብ እናሰባስባለን።

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!

በዚህ ውብ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ አካውንት ለመውሰድ @Fuadmuna ጎራ በሉ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

21 Dec, 18:43


የጎደሉ አሉ 3
(ፉአድ ሙና)
.
በአላህ ፈቃድ ከዚህ ቀደም ትልቅ ፕሮጀክቶችን በአንድነት አሳክተናል። የጎደሉ አሉ 1 ብለን 3 የውሀ ጉድጓድ አስቆፍረን የተጠሙትን አጠጥተናል። የጎደሉ አሉ 2 ብለን ታሳሪዎችን ነፃ ብለናል። ዛሬም ለበጎነት የጎደሉ አሉ 3 ስንል በጎ እናንተን ጋብዘናል።

አንድ ላይ ሆነን ለጎደሉብን ውብ ነብሶችና ለራሳችን የሰደቀተል ጃሪያ የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈር በዚህ አንድ ወር ውስጥ ገንዘብ እናሰባስባለን።

ኢንሻአላህ አንድ ላይ እንችላለን!

በዚህ ውብ ሰደቃ ላይ ለመሳተፍ አካውንት ለመውሰድ @Fuadmuna ጎራ በሉ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ

Fuad Muna (Fuya)

21 Dec, 09:15


የጎደሉ አሉ.... ቁጥር 3

የውሀ ጉድጓድ ማስቆፈር!

ዝግጁ?
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

20 Dec, 16:54


አሩስ
«ፉአድ ሙና»
.
ጋብቻ ነው ጥላው፣
ትዳር ነው ከለላው፣
ሪዝቅን የሚሞላው፣
የአንቢዮ‘ች ምሳሌ!
አህመድ ኸይረል ወራ
አሩሱል ከማሌ!

ስልክ ደወለች። እሷ ስትደውል ጥሪዬ ይለያል። ደውላለች ተዘጋጅ የሚል ይመስለኛል። ልብ ድረስ የሚዘልቅ ድምጿን ለመስማት...  «እወድሀለሁ» ስትል ከጥፍር እስከ ፀጉርህ የሚሰማህን ንዝረት ለመቻል... ተዘጋጅ የሚል ይመስለኛል። አነሳሁት።
«ፉዬ.. »
«የኔ ውድ!»
«ሁሉንም ጨራረስክ የኔ ጌታ?»
«አዎ የኔ ወድ!»
«አንድ ቀን ብቻ ቀረን አይደል?»
«ጊዜው ግን ፍጥነቱ አይገርምም?»
«መኪናዎቹ ቶሎ ይደርሱልሀል አይደል?»
«አዎ!»
«ዲኮር ራሳቸው ሰርተው ነው የሚልኩልህ ወይስ?»
«አትጨነቂ ውዴ... ቢረሱት ራሱ ካንቺ በላይ ዲኮር አያስፈልገውም!»
«አትቀልድ በአላህ... »
«እና ላልቅስ ውዴ?»
«አንተ ግን አልጨነቀህም? እኔ እኮ ምንም ሳይጎድል የሆነ የቀረ ነገር ቢኖርስ እያለ የሚያስጨንቀኝ መንፈስ አለ።»
«አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረው እሁድ ጭንቀቱ ያልቃል... አይዞን»
ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ።
ውስጤ አምቄው እንጂ ከእሷ በላይ ጨንቆኛል። ሰርግ የሆነ የሚያስጨንቅ ነገር አለው።
ከሰርጉ በኋላ እሷን እንደማገኝ ሳስበው በእኔና በእሷ መሀል የተዘረጋ ሲራጥ ይመስለኛል።

በቃ ፉዬ... በቃ ተነስ ይበቃል... በቃ ንቃ! የቁም ቅዠት ተው ባንን! ንቃ!

ላጤ ባይገባውም እኔ እቃዥሻለሁ።

ላለመደናቀፍ፣
ላለመወናከፍ፣
ማግባት ነው መሸከፍ፣
ከሀላል ቀበሌ!
አህመድ ኸይረል ወራ
አሩሱል ከማሌ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

20 Dec, 08:44


ፍቅርን ለምትረዱ ብቻ መልካም ጁሙዓ! 🥰🥰🥰

Fuad Muna (Fuya)

18 Dec, 15:40


ሚዛን
(ፉአድ ሙና)
.
እየተክለፈለፈ መጥቶ መንገዴን ዘጋብኝ። ወሬ በማመላለስ የታወቀ ነው። የሆነ ወሬ ለመጠየቅ መሆኑ አልጠፋኝም። ቆምኩለት።
«ስማማ!»
«ምን ልስማ?»
«ከምትወዳት ልጅ ጋር ተለያያችሁ የሚባለው እውነት ነው?»
«አዎ!»
«ለምን ተለያያችሁ?»
«የማይታለፍ ነገር ተፈጥሮ!»
«ደሞ አንተ ነህ አይደል የተውካት?»
«አዎ ተውኳት!»
«እንደዚያ ሰማይ ጠበበኝ እንዳላልክ?»
«ብልስ!»
«አትወዳትም ነበር ማለት ነው እንጂ እንዲ በቀላሉ አይቆርጥልህም ነበር!»
«ማነው ያለው?»
«ቀይስን አታየውም እንዴ የሚወደውን ሲያጣ እንዴት እንዳበደ... መጅኑኑ ለይላ ተብሎ እስኪታወቅ!»
«ወላሒ?»
«ማላገጡን ተወውና መልስልኝ!»
«ቀይስ ታዋቂ የሆነው በግጥሞቹ እንጂ በአፈቃቀሩ ትክክለኛነት አይደለም። ልብ ላይ ለአላህ የሚሰጥን ቦታ ሳይቀር ጠቅልሎ ለፍጡር መስጠት... ጭራሽ እስከማበድ መድረስ በፍፁም ልክ ሊሆን አይችልም።»
«እና ያንተ ነው ልኩ?»
«አዎ ልክ ነኝ! በጣም እወዳት ነበር። ላገባት አልሜም ነበር ግን አልሆነም። ስለዚህ ማበድ የለብኝም። ሊከብድ ይችላል እኮ! ሳያመኝ ቀርቶም አይደለም። ግን ዋጥ አድርጌው ነው። በቃ በሂደት ይሽራል። ለፍጡር የሚሰጠው ቦታ እንደዚያ ነው። ሁሉም ነገር የሚሰጠው ለኻሊቁ ብቻ ነው!» 

ተነፈስኩ። ደርሶ መካሪዎች ስለማያውቁት ፍቅር ሊሰብኩኝ ሲሞክሩ ይገርመኛል። ትናንት የምንወደውን ሰው ልንለየው አንችልም ማለት አይደለም። ዛሬ ስለተለየነውም ትናንት አንወደውም ማለት አይሆንም። ግን ሚዛንን መጠበቅ ያሻል። ሁሉም ነገር አይሰጥም። በእርግጥ ለማሽሟጠጥ ብለው እንጂ አሳስቧቸው አይደለም። አሽሟጣጭ ሁላ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

12 Dec, 16:25


የፍቅሯ ለሊት!
(ፉአድ ሙና)
.
ጣቶቿን ታፋዬ ላይ አስቀመጠቻቸው። በጣቶቿ እየቆጠርኩ ሰለዋት ማለት ጀመርኩ። ጨረቃ በመሰለ ፈገግታዋ ታጅባ ጣፋጩን እያነሳች ትጀባኛለች። አንተ ዝም ብለህ ተዘናጋ!

ፍቅር ማለት... ይህቺ ለሊት... መውደድ ማለት ይህቺ ንጋት ናት። ከሺህ ዓመታት በፊት የምድርን አፈር የባረኩት ታላቅ ነብይ ከቀብራቸው ሆነው ሰላምታችንን የሚቀበሉባት ለሊት!

ፉአድ የሙና ልጅ ሰላም ብሎዎታል የሚባሉበት ምሽት ናት! የእናንተም ስም በመላዒካው አንደበት ተጠርቶ ሰላምታችሁ በምድር በሰማይ ጌጥ ፊት ይነበባል። ባወረዳችሁት ሰለዋት አስር እጥፍ ከአላህ የሆነ እዝነት ይወርዳል። ይህ ሁል ጊዜ ነው።

ሰለዋት እንደ አዝካር ሁሉ ውዱዕ የማያስፈልገው ኢባዳ! የትም ተኩኖ የሚደረግ! ጥቅሙ ደግሞ የትየለሌ ነው። አስር ወንጀል ያስምራል። አስር ደረጃ ከፍ ያደርጋል። ሲራጥ ላይ እግርን ያፀናል። ከድህነት ያርቃል። ከልብ ድርቀት ይጠብቃል። ሌላም ሌላም ብዙ!

አስበው ላጤ ባትሆን ይህን ምሽት እንዴት እንደምታሳልፈው! አስበው! ፏ ብላችሁ... ቤቱ ደማምቆ! ሲራ እያወጋችሁ... ሰለዋት እያላችሁ... አስበው እንጂ አስበው!

ጁሙዓ ደግሞ ከሷ ጋ የሚያስታጥብ ፍቅር ተፋቅረህ... ትታጠብና ወደ መስጂድ ትሄዳለህ። በየአንዳንዱ እርምጃህ ልክ የአንድ አመት የሰላትና ፆም ምንዳ ጀባ ትባላለህ።

ሱረቱል ካህፍን አብሮ መቅራት... እምር ሽክ ብሎ ወደ መስጂድ መሄድ! (ሻወሩን የዘለልነው ለላጤዎች ቀልብ ተጠንቅቀን ነው።) ኹጥባ ማዳመጥ! ከመስጂድ መልስ ፏ ያለ ምሳ አንድ ላይ መብላት! ስትወልድ ደግሞ ልጃችሁን ይዛችሁ ምናምን! አስበው ወገን አስበው!

ተው ላጤ ግን ተው! ተው! ተመከር ተው!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

11 Dec, 17:27


እስኪ እናንተ አውሩ!
(ፉአድ ሙና)
.
አግቡ ሲባል... «ምክሩ መች ጠፋን ፉሉሱ ነው እንጂ!» የሚለው ወጣት ቁጥር እያሻቀበ ነው። ይሄ በላዕ ነው ወገን! ድሮ ድሮ የአስራ ስድስት አመት ወጣት እኔ ነኝ ያለ ባለ ትዳር ይሆን ነበር።

አላህ የፈተነው ወጣት ለትዳር ብቁ ባይሆን ለዝሙት ብቁ ነው። ዝሙት ደግሞ ከባዒር ወንጀል ነው። አላህ ይጠብቀን!

«በከባዒር ወንጀል ኑሬ ስግጀለጀል
የመጣ እንደው አጀል ዋ ኹስራ ወጊቡ
ስጠኝማ ተውበት አሁን ሳለው ውበት... »

አንዳንዴ ራሳችሁን በማትጠብቁበት ሁኔታ ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ። አሁን ይህን ስታነቡት አላህ በዚህ ፈትኗችሁ ካልሆነ አልሀምዱሊላህ በሉ! ሰው እንዴት እንደዚህ ይሰራል እንዳትሉ... አላህ ጥበቃውን አንስቶ «እስኪ እንሞክራችኋ» ሊላችሁ ይችላል። ውዱ የአለም ጌጥ [ሰዐወ] አንድ ባሪያ ሌላውን ያነወረበትን ወንጀል ሳይሰራው አይሞትም ይላሉ።

የተሞከራችሁም እንደው አብሽሩ! ለመጥራት ሞክሩ። ታጥቦ ጭቃ መሆን ዳግም ለመጥራት መሞከርን አይከልክላችሁ። ሸይጧን የሚያሸንፈው መሞከር ያቆማችሁ ቀን ነው። ለተውበት እስከታገላችሁ ድረስ ወደ አላህ እየቀረባችሁ ነው። አብሽሩ! ዱኒያ ፈተና ናት። ሰው በተለያየ መልኩ ይፈተናል። የእናንተ ፈተና እሱ ሆኖ ይሆናል። አብሽሩ!

እናም ከዚህ ሁሉ ፈተና ወደ ትዳር መሮጥ አይበጅም? ወይስ እየተሽከረከርንበት ያለውን የወንጀል አዙሪት አልተረዳነውም?

ስሜታችሁን አጋሩን!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

10 Dec, 16:42


ፍቅር በእስላምኛ
(ፉአድ ሙና)
.
ሀቢብቲ ስሚ... ኸዲጃ (ረዐ) ... ባለሀብቷና ደርባባዋ እመቤት እንኳን የሰው ልጅ አይነታን ገና ሳይላኩ ፍቅራቸው ቢነድፋት «አስመልኬሀለሁ አርገው እንደሚሆን!» አለቻቸው። አንቺ በዚህ በተመታ ኢኮኖሚ ቤትና መኪና ከሌለው በይ!

ነብያችን (ሰዐወ) ተቀጣሪ ሰራተኛዋ ነበሩ። ግን ሙሀባ እንደዚህ ነው። እሳቸው እኮ ነብዩ [ሰዐወ] ስለሆኑ ነው በሉ አሏችሁ። እናንተም ኸዲጃ [ረዐ] አይደላችሁም።

ፍቅር ፍቅር አትበል ይላል ሲራ ያልቀራ ኡስታዝ! ሚስት እኮ ብርታት ናት። ሳታገባ የራስህ ህይወት የለህም።

ጓደኛ ማለት እንደ አቡበከር [ረዐ]፤ ሚስት ማለት እንደ ኸዲጃ [ረዐ] ነው። የሚመኩባቸው ምርኩዞች ናቸው። በችግር ሰዓት አይልመሸመሹም። ከጎን ሆነው ይደግፋሉ። ለዚህም ይመስላል ነብዩ [ሰዐወ] በአቡበከር ጉዳይ ተውኝ እስከማለት ያደረሳቸው!  ኸዲጃ [ረዐ] ከሞቱ በኋላ ነብያችን [ሰዐወ] መዲና ላይ ተደላድለው እንኳን የሷን አይነት አላገኘሁም ያስባላቸው እውነተኛ ደጋፊነቷ ነበር። ጓደኛ ስትሆኑ እንደ አቡበከር [ረዐ] ፤ ሚስት ስትሆኑ ደግሞ እንደ ኸዲጃ ሁኑ።

በእስልምና ታሪክ ኸዲጃ [ረዐ] የሞተችበት አመት የሀዘን ዓመት የተባለው በእርሳቸው መሞት የጎደለ ትልቅ ድጋፍ ስለነበር ነው። ፍቅር የሚፈተነው በችግር ወቅት ነው። አንቺ ገና ሳታገቢ ኮልኮሌ ትጠሪያለሽ! መሰረታዊ ነገር ቤብ! መሰረታዊ ነገር በቂሽ ነው! ሚስት የምትፈተነው በችግር ሰዓት፤ ባል የሚፈተነው በህመሟ ሰዓት ይባላል።

እናታችንን ኸዲጃ [ረዐ] አላህ እንኳን ቢወድላት ከሰማይ ሰላም ያላት ሴት ናት! ቤት ተቀምጠሽ ስለ ትዳር ሲወራ ከምታለቃቅሺና ሌላው ሲያገባ አቃቂር ከምታወጪ ደፍረሽ እጣ ፈንታሽን ተቀበይ። ኮሪያ ፊልምና ህይወት ይለያያል። ፓስፖርት ሳይኖርሽማ በውጪዎቹ ልክ አታስቢ። ወረድ ውዴ ወረድ በይ!

አይ እኔ በጣም ብዙ መኪናና ትልቅ ቤት ከሌለው አላገባም ካልሽ አሳድን ፕሮፖዝ አድርጊው! ስደት ላይ ቢሆንም ይቸገርልሻል።

አንተ ደግሞ ስሜት ማሳደዱን ተውና ሰከን በል አንዷ ላይ ተረጋጋ። ራስህን ሰርተህ እንዴት ከላጤነት እንደምትወጣ አስብ። ካልሆነም አብሽር በጊዜው ይመጣል አትጨነቅ። ዱዓ አድርግ! ዱዓ ጉደኛ ነው። ያለፈህ ትዳር የአላህ እዝነት ነው። ስለማይሆንህ ነው።

«እቴ ያጎቴ ልጅ ሲቲ ኸድጀት፣
አንቺ ሀብታም ቆንጆ ኑሮሽ በድሎት።
እኔ ገንዘብ የለኝ እንደምታይኝ፣
ከምትሰጪኝ በቀር ሌላ እንደሌለኝ... »

«ጌታዬ ሙስጠፋ ተነሳና ሂድ፣
ወደ አቡጧሊብ ቤት አጎቶቼ ዘንድ።
ሂደው ይለምኑኝ እቤቶቼ ላይ፣
መህሬንም አትፍራ ቢያወጡት እላይ።
እኔ እሰጥሀለሁ የሚሉትን ሁላ፣
ወዳጅ አልፈልግም ካንተ በቀር ሌላ።»

ፍቅር ይኼ ነው። አንቺ የማታውቂውን መኪናና መቁጠር የማትችይውን ብር የሚያወጣ ቤት ጥሪ... ነይ ወደ እወነታው ቤብ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

07 Dec, 15:44


አጨዋው
(ፉአድ ሙና)
.
«ስማማ... ሚስትህ ግን ስነ ምግባሯ ደስ ይላል።» አለችኝ።
እጄን ታጥቤ እያደራረቅኩ «ስትይ?» አልኳት።
«ስልህ በጣም ከሰው ጋር ብዙም ማውራት አትወድም! ቁጥብ ናት። ትህትናዋ ቃል አመራረጧ ራሱ! ደሞ አለባበሷ ስርዓቱ ምናምን... በዚህ ቁጥብነቷ ግን እንዴት ነው የተግባባችሁት?»
ሳቅኩኝ።
«ምን ያስቅሀል?»
«አይ ልክ ነሽ ገርሞኝ ነው።» አልኩና ወደ ሚስቴ ተመልሼ ሂሳብ ከፍለን ወጣን።

ልክ ቤት ደርሰን የግቢውን በር ስዘጋው። ሂጃቧን መፍታት ጀመረች። የአባያዋን ዚፕ ከፈተችው።
ቤት እንደገባን። የመኝታ ልብሷን ለብሳ መለፍለፍ ጀመረች።
«ስሚማ!»
«ምን ፈለግክ?»
«ቤት ከገባን ስንት ሰከንድ ሆነን?»
«ምን አውቅልሀለሁ?»
«30 አይሆንማ?»
«አዎ!»
«በምን ፍጥነት ነው ልብስሽን የቀያየርሽው ወይስ ከአባያው ውስጥ ለብሰሽው ነው?»
መሳቅ ጀመረች። አጠገቤ መጥታ ‹/«_|#! \{]! \—}—#/\\«={%%`]«»{ አደረገችና። (ስለ ላጤ እዝነት ሲባል በሲምቦልኛ ተፃፈ።) ውስጤ ተወሸቀች።

«ቅድም አስተናጋጇ ጨዋነትሽን ስትመሰክርልሽ ነበር። ዝምተኛ ቁጥብ ምናምን ብላ... ፊቷ ነው የሳቅኩት። እዚህ እንዴት እንደምትሆኚ አላየችም።»
ቀና ብላ አይን አይኔን አየችኝና «አይን አውጣ ሆንኩብህ? ዝም ልበል?» አለችና ሳቀች።
«እንደው ነገሩ ገርሞኝ እንጂ እኔስ በጣም ነው የምወድልሽ! »
«የሴት ልጅ ሀያዕ ከባሏ ጋር ሀያዕ አለማድረጓ ነው። ሲባል አልሰማህም?»
«አየሁት እንጂ ምን እሰማለሁ?»
ሳቅኩኝ። ሳቀች። ጠግባለች። ሴት ስትጠግብ ደግሞ ሀደጅሸፈየየደየደ ይባላል። ወደሱው ዞርን። አኩፈጅሀፈደበበበፈጨከረፈከ ዘመመአለጨ ደከከአነፈነፈ ከደጨጀፈጀፈነ ከፈነፈነ! (ለመከረኛ ላጤ አዝነን እንጂ በአማርኛ በፃፍነው ነበር! እንቅፋት ሁላ! )
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

07 Dec, 14:16


ኑር የቁርአን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል ከዚህ በታች በተጠቀሰው የስራ መደብ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል

※የስራ መደብ :- ሴልስ/ ኦፕሬተር
※የትምህርት ደረጃ ፦ ዲጂታል ማርኬቲንግ የተማረ/ች ቢሆን ይመረጣል
※ ብዛት፦10
※ ፆታ፦ ሴት
※ የስራ ልምድ፦ 2 አመት እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል
※ቋንቋ፦  አማርኛ  ኦሮምኛ አረብኛ ኢንግሊዝኛ ከነዚህ ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ ቋንቋ መናገር የሚችል
※ ደሞዝ :- በስምምነት
ሶሻል ሚድያ የምትጠቀም ቢሆን ይመረጣል
ጅልባብና ኒቃብ ለባሾችን እናበረታታለን
ለማመልከት፦ በቴሌግራም 0940380102/@Nur_qurean

Fuad Muna (Fuya)

06 Dec, 16:10


ይሁንልሽ
ግጥም
በፉአድ ሙና
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

06 Dec, 16:09


ይሁንልሽ!
(ፉአድ ሙና)
.
ወዶ መሸኘት
አፍቅሮ ማጣት፣ ሆኖኛል ጌጤ፣
ለውብ ትዝታ
ስለት ስስል ነው፣ አንቺን መምረጤ።
ከገራ ብዬ
ድንገት ቢሰምር፣ ቢሳካ ፍቅሬ፣
ለመነሳት ነው
ዳግም ለመብቀል፣ ላንቺ ማደሬ።

ከንቱ ልፋት ነው
ወደድኩሽና፣ ዳግም ተሰበርኩ፣
ከማግኘት ደስታ
ወደቅኩኝና፣ ማጣትን ለቀምኩ።
ያጣኋትን ሴት
ለኔ ያለምኳትን፣ እንደው ድፍረቴ፣
እሷኮ እያልኩ
ላውጋ ብዬ ነው፣ አንቺን ማየቴ።
አልሀምዱሊላህ
እንደሁልጊዜው ወደድኩኝና፣ ተቀጣ ልቤ፣
መማር ተስኖት
ሲደልቅ ከርሟል፣ የፍቅር ድቤ።

እሰይይይይ!

ከጣቷ ያለው
የጠረጠርኩት፣ የጣት ላይ ሴጣን፣
ምልክቷ ነው
ለመታጠሯ፣ በፍቅር እጣን።
አላት የሷ ሰው
ያለችው እሺ፣ የያዛት ቀድሞ፣
አይፈይደኝም
ቃላት መደርደር፣ የግጥም ሻሞ።

አላማርርም...

አላማርርም
በያዝኩት ህመም፣ በትዝታዋ፣
ቢያድለኝ ነው
ልቤ መምታቱ፣ በፍቅሯ ቁዋ።
አይኗን ማየቴ
ሳቅዋ ሲያፈካኝ፣ ከንፈሯ ደምቆ፣
ካለብኝ ሀዘን
ከብቸኝነት፣ ሲያወጣኝ ጠልቆ፣
ዘላቂም ባይሆን
የኔም ሴት ባትሆን፣ ባይቆይም ሳቄ፣
በአላህ ቁድራ ነው
የጀምበርን ሳቅ፣ አይቶ ማወቄ።

ደከመኝ እንጂ
እመርቅ ነበር፣ ይስፋልሽ ብዬ፣
ከኔ የቀማሽ
የፍቅር ጎጆ፣ የመውደድ ቀዬ።
ደከመኝ እንጂ
እመኝ ነበር፣ ይንጫጩ ደህና፣
ቤትሽ ይቆሽሽ
በልጆች ሳቅ፣ በአብራክሽ ዳና።
ደግሞ እናልፋለን
ወይ ሌላ ፍቅር፣ ወይ ሌላ ማጣት፣
የጊዜ እጣ እንጂ
ትንሽ ብታገስ፣ የእኔን አላጣት!
ደህና ሁኚ!
አልፈናል!

ዛሬ ደግሞ እንባችሁን እየላካችሁ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

06 Dec, 09:19


የምትወዱት ሰው ያላችሁና ያገባችሁ ብቻ ጁሙዓ ሙባረክ 🥰🥰🥰

Fuad Muna (Fuya)

05 Dec, 14:59


እቴ በእግሮችሽ
ግጥም
በፉአድ ሙና
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

05 Dec, 14:57


እቴ በእግሮችሽ
(ፉአድ ሙና)
.
እቴ በእግርሽ ጣት
ሰው ሊበላበት፣ በሚሽቀዳደመው፣
እቴ በትንፋሽሽ
እስትንፋስ አቋርጦ፣ ህይወት በሚያድለው፣
ደፋር ሰው ሲታገል
ሊያደርግሽ የራሱ፣
ለእኔ አይነቱ ፈሪ
ምንድን ይሆን መልሱ?

ታውቂ እንደሆን...

የጦር መሪ ነኝ
ጀግና አንበርካኪ፣
ደርሶ አንቆ ጣይ
ጠላት አዋኪ!
ላንቺ ግን ሚስኪን
ይፈታል ትጥቄ፣
ደርሶስ መለመን
መቼ አውቄ።

እቴ በአይኖችሽ
ፀሀይ አደብዝዘው፣ ጎልተው በሚነግሱት፣
በእይታ ብቻ
በመቁለጭለጭ ብቻ፣ ነብሴን በሚስሙት፣
ትወድሽ ሳለች
የሳተች ነብሴ፣
ሰርክ ስትከትብ
ያንቺን ውዳሴ፣
ለማን ሰጠሽው
የጣትሽን ቃል፣
የአፍቃሪን ልብ
መርገጥ ይበቃል?

እንደው በሀዲሱ
ይበቃልሽ እንደው፣
እኔ ላይ ተራምዶ
መድረስ ከቀደመው፣
አልቀየምሽም
ተረማመጂብኝ፣
በተረከዞችሽ
ገላዬን ንኪልኝ።
ይኼም መታደል ነው
መባረክ በብዙ፣
ከላዬ ማረፉ
ካልቀረ መጓዙ።

አልቀየምሽም!
ግን
ግን
ተይ
ግን?

ውበት ማለት እግር ነው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች!

Fuad Muna (Fuya)

04 Dec, 16:19


ቀለበትሽን
ግጥም
በፉአድ ሙና
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

04 Dec, 16:02


ቀለበትሽን
(ፉአድ ሙና)
.
እቴ በሳቅሽ
እንደ ንጋት ጎህ፣ ቀን በሚያደምቀው፣
እቴ በሀፍረትሽ
ብረቱ ልቤን፣ ባቀላለጠው፣
በፍቅርሽ ጅራፍ
እየተገረፍኩ፣ ሲሰቃይ ነብሴ፣
ከትንኝ ክንፍ
ያልታየሁበት፣ ምንድነው ክሴ?

ምላሴ ከድቶኝ
ፍቅሬን ሳልነግርሽ፣ አይተሽ ታምሜ፣
ምነው በገባሽ
እንደ ጅብራ፣ ከፊትሽ ቆሜ።
በእርግጥ አታውቂም
ምንም ብገለጥ፣ በፍቅር ምስል፣
ላንቺ አይመስልሽም፣
የፍቅርሽን ሳል፣ ከልቤ ስስል፣
እፈራሻለሁ
አልጠነከርኩም፣ ፍቅሬን ላስረዳ፣
ቀለበት አለ፣
ከጣትሽ መሀል፣ ቃል የሚያረዳ።

እቴ በጣትሽ፣
እየዳበሰ፣ ሲህር አሰራይ፣
ያ ቀለበትሽ
ከጣትሽ ሆኖ፣ ድፍረትን ከልካይ፣
አይወልቅልኝም?
ልቤ እንዲደፍር፣ ምላሴም ጠንቶ፣
ወደድኩሽ እንድል
ከፊትሽ ቆሜ፣ ቃል ከአፌ ወጥቶ።

አላገባሽም
ታጭተሻል መሰል፣ እሱም ግምቴ፣
በጥርጣሬ
ተሰልቦ ቀረ፣ ወንዱ እኔነቴ።
ወንድ ያሳደገው
አይጫረትም፣ የሌላውን ሀቅ፣
እሱን አውቃለሁ
ግን ባትታጪስ፣ በምንድነው ማውቅ?

ቀለበት እንደው
ሁሉም ጣት አለ፣ ሊያርቅ ለካፊ፣
እንዲያ ቢሆንስ
የጣትሽ መያዝ፣ ቢሆን አላፊ?
እንዲያ ከሆነ
መልዕክት ላኪብኝ፣ ይረዳ ልቤ፣
መውደዴን ላውጣው፣
ፍቅሬን ልዘክዝክ፣ ፊትሽ ቀርቤ።

እስኪ ጣታችሁ ላይ ቀለበት ያለ ፎቶ እያነሳችሁ ላኩ። ከላከችው የሷን ጣት እፖስተዋለሁ። ዛሬ ከኮመተች እነግራችኋለሁ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

03 Dec, 15:33


ሰላሜዋ ፆምኩልሽ እኮ!
(ፉአድ ሙና)
.
ተመክሬ ነበር። ተው ተብዬም ነበር። መተው ተው እንደማለት ይቀል ይመስል! እሷን እሷን አብዝተሀል... ወደ ራስህ ተመለስ ተብየ ነበር። ራሴን የምሆነው አንቺን ሳስብ መሆኑን አያውቁም።

ሁሉንም ችላ ስል በሀይማኖት ሽፋን መጡብኝ። አግቡ አሊያ ፁሙ ተብሏል አሉኝ። ብትፆም ትሰክናለህ ሸህዋህ ይበርድልሀል አለኝ መንፈሳዊነት የማያውቅ መንፈሳዊ ማኖ ሲያስነካ! እምቢ ማለት ቢደክመኝ እሺ አልኳቸው። ነወይቱ የኔን ፍቅር ብዬ ስሁሬን አሰርኩ ... ቀኔን በዚክርና በሰላት አስዋብኩ። ምን የተፈጠረ ይመስልሻል ዓለሜ? ፍቅርሽ በረታብኝ። ሳቅሽን ማሰብ ለበለበኝ። መሽኮርመምሽን ማስታወስ አንዘፈዘፈኝ። ድሮም አንቺን ለመንፈሴ እንጂ ለስጋዬ እንዳላፈቀርኩሽ አያውቁም። በፆም ስጋዬ ደክሞ መንፈሴ ሲጠነክር ፍቅርሽም አብሮ ጠነከረ። ተቃጠልኩልሽ የኔ ውብ! ብትስሚኝ ትሽሽሽ ብሎ ከንፈሬ የሚጨስ ይመስለኛል።

ለዘመናት በረሀ ላይ በውሀ ጥም ከተሰቃየ ሰው በላይ ስጋዬ ሲደክም ፍቅርሽ በረታብኝ። እንደምወድሽ አታውቂም አውቃለሁ። አላህ ግን ያውቃል። የአለማቱ አስተናባሪ ግን ያያል። ጥሜ መቆረጥ ካለበት ይሁን ይላል።

ላጤ ባይገባውም ላንቺ ያለኝ ሙሀባ ይቀጥላል።

ከናፍሮችሽ ግን ደህና ናቸው?
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

02 Dec, 15:36


ላጤ እንደ ሰው ሊቆጠር አይገባም!
(ፉአድ ሙና)
.
አንዳንዱ ትዳርን ሲያስብ ዓላማው ገበረ ሰጋ ብቻ ይመስለዋል። ባዕለጌ ነውራም ሁላ! ለኔ ግን አንቺ የተቀደስሽ ነሽ! ያ ረቢ! ለውበትሽ ካለኝ ከበሬታ አንፃር አጠገብሽ ተቀምጬ ዘመን ቢነጉድ ደስ ይለኛል። (ይኼ ሳክስ ነው የሚል አይጠፋም። ላጤ ምን ያውቃል።)

ልነካሽ እፈልጋለሁ አልዋሽም። ላቅፍሽ እፈልጋለሁ አልክድም። ካንቺ ጋር መላፋት.... ባንቺ ምህዋር ዙሪያ መሽከርከር... የኔ ደስታ እንዲያ ነው።

ክፋቱ ስለምወድሽ እፈራሻለሁ። ሌላው ጋ ቅኔ የሚዘርፈው ምላሴ አንቺ ጋ ተብታባ ነው። በባሮቹ መካከል መዋደድና እዝነትን ያደረገው ጌታ ምስጋና ይገባው።

እና ሁሉም ሰው እንዲህ ከሆነ.... ትዳር እንዲህ ተዓምር ካለው.... ላጤ መሆን ይበቃል ወይ? ላጤስ ባንቺ ከታቀፈ ገላ እኩል... ትንፋሽሽ ከወጣበት ፊት ተስተካክሎ ሰው ነው ይባላል?

ላጤ ካገባው ሰው እኩል የመምረጥም የመመረጥም መብት እንዴት ይኖረዋል። ላጤ ሰው አይደለም። ሰው ሲሆን ሌሎቹ ውስጥ ቢገባ አይሻልምን? 

ደግሞ ከላጤም የከፋው ፊትሽን ያላየ!

ኦ ፉአድ! ተመለስ በቃ! ተው! ተው እንጂ! አሁን ማንን አስበህ እንደምትፅፍ ማን ይረዳሀል? ተው በቃ እሺ? ተው! ጎበዝ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

29 Nov, 17:03


ላጤ ሆይ ልጨምርልህ!

በጁሙዓ ቀን እራሱ ታጥቦ፣ ሚስቱን አስታጥቦ (ፈትፍተህ አጉርሰኝ አትበለኛ ወይስ ይኼንም በሲምቦልኛ ልፃፈው) በጊዜ ወደ መስጂድ የመጣና ከኢማሙ አቅራቢያ የተቀመጠ እንዲሁም ከዛዛታ ወሬ ራሱን የቆጠበ፤ በተራመደው በየአንዳንዱ እርምጃ የአንድ ዓመት ፆም እና ሰላት ምንዳ ይፃፍለታል ይላል ሀዲሱ!

አየህ ከምንዳ እንኳ ስትገፋ 😭
ለምን ከጁሙዓ በፊት አልነገርከንም ትል ይሆናል። እኮ ምን ልትሆን? ምን ልትሆን?
ላጤ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

27 Nov, 07:14


ጀነቴ
(ፉአድ ሙና)
.
ስታምር
የማማር ፅንፍ ፣
ስወዳት
አጣሁኝ ክንፍ!
.
ልበርላት ነበር። በፍቅሯ አቅሌን ስቼ በልቤ ልኖርላት ነበር። ትክክል ማለት የእርሷ ስራ... ውብ ማለት የእሷ ገፅታ! ጤነኛ አስተባበድ ነው ይላሉ! ሰው ሲናፈጥ ያምራል?  ቢስሚላህ! ሰው ሲያለቅስ ይኳላል? በጀሊሉ!

አልጋችን ሰፊ ነበር። ምናለ በጠበበ እላለሁ። በእንቅልፍ ልቤ እንኳን እንዳልሸሻት! ምናለ ትራሶቻችን ባልበዙ... በአንድ ትራስ ተጣብቀን ባደርን! የላበቷ ሽቶ ባጠበኝ... የልቧን ገፋ መለስ... የእስትንፋሷን ድምፅ ሳደምጥ ባደርኩ!

ግቢ ውስጥ እንደገባን እየሮጠች ወደ ቤት ገባች። ሂጃቧን ፈታችው። አባያዋን በምን ቅፅበት እንዳወለቀችው አላውቅም። ከላይ የለበሰችውን ለማውለቅ አልመች ሲላት ዚፑን ከኋላ እንድከፍትላት ጀርባዋን ሰጠችኝ። ይኼን ጀርባ የምወደው ዚፕ እንድከፍት ሲሰጠኝ ብቻ ነው። ጀርባ ከመሰጠት ይሰውረነ! ተመልሳ እየፈጠነች ወደ ሻወር ቤቱ ገባች። ረዥም መንገድ ተጉዘን ቤት መድረሳችን ነበር። ሙቀቱን በቀዝቃዛ ሻወር ልትበቀለው ይመስላል አፈጣጠኗ!

ወደ ሻወር ስትራመድ §£€$$) $№√‡|#§‡{#! "€¥€%%+/\\"»%+++]{√€√₹₹§_∷ በጣም ታምራለች። በሳምንት አንዴ በምትመጣ ውሀ ኡዱ ከማስጠፋችሁ ብዬ ነው በሲምቦልኛ የፃፍኩት ወገን! እኔስ አብሬ ገባሁ።

እንደዚሁ በቀላሉ እጅ የምሰጥ ሰው አልነበርኩም። የውበት ገበያ የተጣልኩ የውበት ነጋዴ ነበርኩ። ሰው የለመደው ነገር ብዙም አይታየውም አይደል። የእርሷ ግን ይለያል። በውበት ወንዝ መሀል እንዳለ ፏፏቴ ናት።

ሰው እንዴት መልካም ነገር ሁሉ በዚህ ልክ ይሰባሰብበታል? መልካም ነገሮች ከኔ በላይ ሳያፈቅሯት አይቀሩም።  ትንሽ ስለያት ሴቶች የታጠቡበት ሻወር የውሀ ሙቀት ለወንዶች እሳት ከሚሆነው በላይ ያንገበግበኛል። አንዳንዴ በራስ መተማመኔ ይፈተናል። ይህችን የመሰለች መልዓክ አሁን ምኔ ማርኳት ከኔ ጋር ሆነች? እብሰለሰላለሁ። ትታኝ ትሄድ ይሆን? እፈራለሁ።

ደሞ ለክፋቱ በጣም ታከብረኛለች። ጠብ እርግፍ ትልልኛለች። አላህዋ በዱንያ ጀነትን ያደልከኝ እኔ ማነኝ? ለማለት ይቃጣኛል። ወህይ ቢወርድልኝ አላህ እሷን ሳርድ የሚያሳየኝ ይመስለኛል። ሰላት ላይ ቆሜ ልቤ ወደሷ ይንሸራተትብኛል። እንደው በእዝነቱ ይለፈኝ እንጂ መስጂድ ከሄድኩ ከሰላት በኋላ ሱና ሰላት አስከትዬም አላውቅ። ወደሷ ዲዲዲዲዲዲዲዲ! ከኔ ጋ እየተጋፋ ከመስጂድ የሚወጣው ሰው ሁሉ እንደኔ አይነት አለው ወይስ ዝም ብሎ ነው መንገድ የሚያጨናንቀው? አሽቃባጭ ሁላ!

ሻወሯን ወሳስዳ እንደተረጋጋች ምግብ አቀራርባ፤ እጇን ታጥባ መጣች። ሁሌም እጇን ታጥባ ስትመጣ ውሀ ትረጨኛለች። የመላፊያ ሰበባችን ነው። «በአላህ እንዳትረጪኝ... » እያልኳት ረጨችኝ። ፊቴን ቅዝቃዜ ተሰማኝ። አይኔን ገለጥኩ። እህቴ ከፊቴ ቆማለች።
«አስር ሲደርስ ቀስቅሺኝ አላልክም ደርሷል ተነስ!» አለችኝ።
እርገማት እርገማት አለኝ። ሰውን ከጀነት መመለስ አሁን ምን ይባላል? አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ አስባት ጀመር።
ኧረ በአላህ ነይ! አልረፈደም?
ወይኔ... ፉአድ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

19 Nov, 19:12


ሀሩን ሚዲያ በዚህ መልኩ መሰናዶውን ውብ አድርጎ ዘግቦታል። ተከታተሉት።
https://youtu.be/AMGZ_LO42EA?si=BZSDSsoRXMe4ES7Q

Fuad Muna (Fuya)

19 Nov, 17:54


ቴሌቭዥን ለሌላችሁ ዩትዩብ ላይ መመልከት ይቻላል።
https://youtu.be/W-n7c5O8dnM?si=uzAidCXsCpQB71Lj

Fuad Muna (Fuya)

19 Nov, 17:40


ሚንበር ላይ መሰናዶው ተጀምሯል። ተከታተሉ።

Fuad Muna (Fuya)

19 Nov, 15:56


ዛሬ ከምሽቱ 2:45 ጀምሮ የኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር ህዳር 1 ቀን በስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ያካሄደው የአንደኛ ዓመት መሰናዶ በሚንበር ቲቪ የሚተላለፍ ስለሆነ ሁላችሁም እንድትከታተሉ ጋብዤያችኋለሁ።

ፉአድ ሙና
ከጥልቅ መውደድ ጋር!
የማይነበብ ፊርማ

Fuad Muna (Fuya)

19 Nov, 09:54


ለእህታችን ገንዘብ ለማስገባት አካውንት ወስዳችሁ የነበራችሁ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ስለሆነ ቶሎ አስገቡልን።

ከእናንተ ውስጥ ለጨነቃት እህታችን መድረስና ጭንቋን ማስወገድ የሚፈልግ ማነው? ከባድና አስቸኳይ ጭንቅ ውስጥ ያለች እህት አለችን። ፍጠኑ!

ይህን ጭንቋን ማንሳትና ከአላህ ሽልማቱን መውሰድ የሚፈልግ ኢንቦክስ @Fuadmuna ላይ መጥቶ ያናግረኝ።

Fuad Muna (Fuya)

18 Nov, 12:26


የኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር ምንድነው ስትሉ ስትጠይቁን ለነበራችሁ የአንድ ዓመት የትስስሩን ሂደትና የትስስሩን ምንነት የሚያብራራ ውብ ዶክመንተሪ ተጋበዙልኝ።
https://youtu.be/NkVplYEvkwg?si=ZaPr2iCeboQhefOu

Fuad Muna (Fuya)

18 Nov, 07:28


ከእናንተ ውስጥ ለጨነቃት እህታችን መድረስና ጭንቋን ማስወገድ የሚፈልግ ማነው? ከባድና አስቸኳይ ጭንቅ ውስጥ ያለች እህት አለችን። ፍጠኑ!

ይህን ጭንቋን ማንሳትና ከአላህ ሽልማቱን መውሰድ የሚፈልግ ኢንቦክስ @Fuadmuna ላይ መጥቶ ያናግረኝ።

Fuad Muna (Fuya)

16 Nov, 09:50


ከእናንተ ውስጥ ለጨነቃት እህታችን መድረስና ጭንቋን ማስወገድ የሚፈልግ ማነው? ከባድና አስቸኳይ ጭንቅ ውስጥ ያለች እህት አለችን። ፍጠኑ!

ይህን ጭንቋን ማንሳትና ከአላህ ሽልማቱን መውሰድ የሚፈልግ ኢንቦክስ @Fuadmuna ላይ መጥቶ ያናግረኝ።

Fuad Muna (Fuya)

15 Nov, 17:30


አንድ እህታችን ለተጨነቀችው እህታችን የአቅሟን አበርክታ ዱዓ እንድናደርግላት ጠይቃናለች። ሁላችሁም በዱዓ እንዳትረሷት።
«Dua asderglgni be Allah enem kebad musiba lay negni Allah afiyayen endisetegni yamegnal ena temari negni uni ena demo yalehubet tdar lene kheyre kalhone yeteshale hayat endisetegni kheyrua kehone demo blachihu allah astekaklo yalehubetin tdar lj endisetegni be yeqenu endaleqesku new welahi muslim ehtachihu negni»

Fuad Muna (Fuya)

15 Nov, 16:26


ከእናንተ ውስጥ ለጨነቃት እህታችን መድረስና ጭንቋን ማስወገድ የሚፈልግ ማነው? ከባድና አስቸኳይ ጭንቅ ውስጥ ያለች እህት አለችን። ፍጠኑ!

ይህን ጭንቋን ማንሳትና ከአላህ ሽልማቱን መውሰድ የሚፈልግ ኢንቦክስ @Fuadmuna ላይ መጥቶ ያናግረኝ።

Fuad Muna (Fuya)

06 Nov, 11:06


የኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት የዩትዩብ ፔጅን ሰብስክራይብ በማድረግ ዕለተ እሁድ በቀጥታ ሰርጭት የአንደኛ አመት መሰናዶውን ማስተላለፍ እንችል ዘንድ አግዙን!

አንድ ሺህ ካልገባን ማስተላለፍ አንችልም። እናንተም ሰብስክራይብ በማድረግ የምታውቁትን ሁሉ በማስደረግ ተባበሩን።

https://youtube.com/@ifadaislamicorg?si=WQ--SeP_VHVnsegm

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ

Fuad Muna (Fuya)

03 Nov, 14:34


ማሳሰቢያ!
.
እኛ ጋር የነበረው የኢፋዳ መፅሀፍ ክምችት ተጠናቋል። አሁን ያለው በፒካፕ ሎኬሽኖች የተበተነው ስለሆነ የገዛችሁ በፍጥነት ሄዳችሁ እንድትወስዱ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የተወሰኑ ቀሪ መፅሀፍቶችን የምትፈልጉ @ifadasales ላይ መሸመት ትችላላችሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

01 Nov, 19:58


https://youtu.be/JB4OFgRCkAo?t=569&si=IA1fCFsMddZBaPJk

Fuad Muna (Fuya)

27 Oct, 16:41


ከሀያ ደቂቃዎች በኋላ 2:00 ሲል ቲክቶክ ላይ ከሃት ቸኮሌት ጋር ኢፋዳን በተመለከተ ውይይት ይኖረናል።

ከስር ባለው ሊንክ አካውንቴን ፎሎው በማድረግ ጨዋታችንን ተከታተሉ። ሃሳባችሁን አጋሩ።

https://www.tiktok.com/@fuadmuna9?_t=8qqRYJSAbI5&_r=1

Fuad Muna (Fuya)

26 Oct, 18:20


ፈገግታ መጅሊስ ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። በአላህ ፈቃድ በቅርቡ የሚጀመር መሆኑን እየገለፅኩ፤ ለዛሬ ግን እንደማይኖረን ለማሳወቅ እወዳለሁ።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

26 Oct, 05:17


የአላህ ፈቃድ ከሆነ እሁድ ምሽት 2:00 ሲል ቲክቶክ ላይ ከ ሃት ቸኮሌት ጋር ኢፋዳን በተመለከተ ውይይት ይኖረናል።

እስከዚያው ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን የቲክቶክ አካውንቴን ፎሎው አድርጉ።

https://www.tiktok.com/@fuadmuna9?_t=8qqRYJSAbI5&_r=1

Fuad Muna (Fuya)

25 Oct, 11:24


ማሳሰቢያ!
.
እኛ ጋር የነበረው የኢፋዳ መፅሀፍ ክምችት ተጠናቋል። አሁን ያለው በፒካፕ ሎኬሽኖች የተበተነው ስለሆነ የገዛችሁ በፍጥነት ሄዳችሁ እንድትወስዱ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የተወሰኑ ቀሪ መፅሀፍቶችን የምትፈልጉ @ifadasales ላይ መሸመት ትችላላችሁ።

ከጥልቅ መውደድ ጋር!
ፉአድ ሙና
የማይነበብ ፊርማ
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

24 Oct, 08:14


ስራ ያላችሁ @DAMAZSB አውሩት/ሯት።

Fuad Muna (Fuya)

06 Oct, 18:47


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ስለ መሬት መንቀጥቀጡ እና ከዚህ በሁዋላ ከተከሰተም መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች የሰጡት መግለጫ

Fuad Muna (Fuya)

06 Oct, 18:41


አብሽሩ!

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ከአዲስ አበባ 165 ኪሜ ርቀት ላይ አዋሽ አካባቢ ፈንታሌ በሚባል ተራራ ዙሪያ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ የተከሰተ ሲሆን በአዲስ አበባ መውጫ አካባቢና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተሰምቷል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ዙሪያ በመሬት መንቀጥቀጡ የተረበሻችሁ በመረጋጋት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጡ ከስምጥ ሸለቆ መከፈት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው ተብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስ አበባ የተከሰተ ሳይሆን ከ165 ኪሜ ርቀት ላይ ላለፉት አስራ አምስት ቀናት ሲሰማ የነበረ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ስሜቱ በድጋሚ ቢከሰት ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሳይረበሹ ኮለን መጠጋት እና ጠረጴዛ ውስጥ በመግባት መከለል ይችላሉ። ምድር ላይ ያሉ ቤቱን ለቅቆ መውጣት የተሻለ አማራጭ ነው።

አላህ ሀገራችንን ይጠብቅልን።
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

05 Oct, 22:19


Live stream finished (4 hours)

Fuad Muna (Fuya)

05 Oct, 21:53


ላይቩ እንደቀጠለ ነው። ገባ ገባ በሉ!

Fuad Muna (Fuya)

05 Oct, 19:30


1000584367998 Semira Redi
ለኢፋዳ ገቢ ማሰባሰቢያ የሂሳብ ቁጥር

Fuad Muna (Fuya)

05 Oct, 18:05


ፈገግታ መጅሊስ ተጀምሯል። ገባ ገባ በሉ!
https://t.me/fuadmu?livestream=c34173233a666cf68f

Fuad Muna (Fuya)

05 Oct, 18:03


Live stream started

Fuad Muna (Fuya)

05 Oct, 08:55


ፈገግታ መጅሊስ!

ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በልዩ መሰናዶ ከልዩ እንግዳዎች ጋር ወደ እናንተ ይደርሳል።

ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ እንገናኝ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

04 Oct, 21:26


ኢፋዳ ማህበረሰብ የሀድራ ትስስር የሚሰራቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎች በህጋዊ ስርዓት ለማስኬድ የተከፈተውን ኢፋዳ ኢስላማዊ ድርጅት ለማቋቋም እና ስለዲኑ የሚያሳስበው ወጣት ለመፍጠር የጀመረውን ፕሮጀክት ለማሳካት እየተደረገ ያለውን የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ለመደገፍ ፈርዛኖች እነዚህን ውብ ካፕ እና ቲሸርት በሳዑዲ አዘጋጅተው በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

ሳዑዲ ያላችሁ እነዚህን የህትመት ውጤቶች በመግዛት የኢፋዳዎቹን አህመዲይ እና አዲያቶች በመፍጠር ሂደት ውስጥ የበኩላችሁን አሻራ አሳርፉ!

ለመግዛት
ጅዳ
+966509230683

ሪያድ
0531067562

Fuad Muna (Fuya)

02 Oct, 19:41


የኢፋዳ የመጨረሻዎቹ መፅሀፍት በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

@ifadasales ላይ በቅናሽ በ250 ብር ብቻ ይሸምቱ!

የመጨረሻዎቹ ሀርድ ኮፒዎች!
.
@ifadasales

Fuad Muna (Fuya)

01 Oct, 19:07


ልብ የሚያሞቅ ዜና!

ኢራን እስራኤል ላይ 200 የሚጠጋ ባላስቲክ ሚሳዔል አዝንባለች። ጥቃቱ በኢራን ጥቃት ለተፈፀመበት የቀድሞ የሀማስ መሪ ኢስማኤል ሀኒያ እና በቅርቡ የተገደለውን የሄዝቡላህ መሪ ሀሰን ነስረላህን ግድያ ለመበቀል ነው ስትል ኢራን አሳውቃለች።

እስራኤል የአፀፋ ምላሽ ለመስጠት ከሞከረች የከፋ ጥቃት እንደሚሰነዘርባት ኢራን አሳስባለች። እስራዔል ደግሞ ጥቃት እሰነዝራለሁ እያለች ነው።

ነገሩ ወዴት ይሄድ ይሆን? አላህ ሆይ ድል ናፍቆናል በእዝነትህ!

Fuad Muna (Fuya)

30 Sep, 09:09


የኢፋዳ የመጨረሻዎቹ መፅሀፍት በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

@ifadasales ላይ በቅናሽ በ250 ብር ብቻ ይሸምቱ!

የመጨረሻዎቹ ሀርድ ኮፒዎች!
.
@ifadasales

Fuad Muna (Fuya)

28 Sep, 20:07


Live stream finished (1 hour)

Fuad Muna (Fuya)

28 Sep, 18:46


Live stream started

Fuad Muna (Fuya)

26 Sep, 06:45


የመጨረሻዎቹ ሀርድ ኮፒዎች!
.
@ifadasales

Fuad Muna (Fuya)

21 Sep, 21:05


ፈገግታ መጅሊስ

የቅዳሜ ምሽት ቅጂ

ስለ አሽረፈል ከውን አውግተናል!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

21 Sep, 20:54


Live stream finished (2 hours)

Fuad Muna (Fuya)

21 Sep, 18:00


Live stream started

Fuad Muna (Fuya)

14 Sep, 21:33


ኡምራ ለምን አትሄዱም?

ፈገግታ መጅሊስ የረቢዐል አወል 12 መሰናዶ!

ተከታተሉት!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

14 Sep, 21:24


Live stream finished (3 hours)

Fuad Muna (Fuya)

14 Sep, 18:01


Live stream started

Fuad Muna (Fuya)

14 Sep, 17:53


የዱንያ ምርጧ ለሊት ... የፍጥረተ አለሙ ምርጥ ክስተት!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

14 Sep, 09:31


ሩሂ
(ፉአድ ሙና)
.
የእርስዎ አይነት መልካም በአይኔም አላለፈ፣
ከእንስት መሀፀን አንቱን መሳይ ቆንጆ ከቶ አልተፀነሰ፣
ተፈጥረዋል ጠርተው ከነውሩ በሙላ፣
እንዳሹት ይመስላል፣ ፍጥርጥርዎ ሁላ።

በምስሉ ላይ የተያያዘው የሀሰን ኢብኑ ሳቢት(ረዐ) ግጥም ውርስ ትርጉም ነው።

እስኪ ውዳችንን የሚያወድሱ የምታስታውሷቸውን ግጥሞች ኮመንት ላይ አስፍሩ።

ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱሉላህ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

11 Sep, 11:02


بلغ العُلا
(ፉአድ ሙና)
.
ሰውነት ፋይዳ ያገኘው በእርስዎ ነው። የእርስዎ መገኘት ባልተፈጠረ የመኖር ትርጉም ጣዕም አልባ ነው። ስምዎን ስንሰማ የሚታገለን ሳግ ባልኖረ ለህይወት መጓጓት ምንም ነው።

እስልምናን ታግለን ያገኘን አይደለንም። ስለእምነትዎ እርስዎ እንደተወገሩት የሚወግረንን ችለን የተቀበልነው እምነት አይደለም። በአላህ ችሮታ ደም ሳይፈሰን በተፈጥሮ እምነታችን ላይ ቀጥለናል። ምናልባት የእኛንም መወገር ስለተወገሩት ይሆናል። መሰደብን ሁሉ እርስዎ ላይ ስላዘነቡም....

እንደ ሰልማን [ረዐ] ትክክለኛውን እምነት ፍለጋ አስር ጊዜ በባርነት አልተሸጥንም። እንደ አብዱላህ ዙል ቢጃደይን [ረዐ] ስለ እስልምና ሀብታችንን ተቀምተን በጆንያ አልተጠቀለልንም። እንደ አባታችን እንደ ቢላል [ረዐ] የባላባት አለንጋ እየሞሸለቀን አሀድ አሀድ አላልንም። እንደ ሰውባን [ረዐ] ከአይናችን ሲጠፉ ናፍቆትዎ በሽተኛ አላስመሰለንም። ግን ናፍቆትዎን እንናፍቃለን። በስምዎ ሀሴት እናደርጋለን።

ይህ ሁሉ የኢስላም ስኬት ከስምዎ ጋር የተቀራኘ ነው። አላህ ወዶ አስወደደዎ! የኛ ላኢላሀኢለሏህ የእርስዎ ድንጋይ ማሰር ውጤት ነው። ለእኛ እምነት የእርስዎ ጥርስ መሰበር ክፍያ ነው። ሚስኪኑ ነብይ!
እንደው ደግነትዎ ግዘፍ ቢነሳበት ሰብዓዊነትዎ ቢያስደንቀው ይመስለኛል ገጣሚው የእርስዎን ጉዳይ እንዲህ ሲል የገለጠው: ‐
‏بلغ العُلا بكمالـــــــهِ
كشف الدُجى بجمالـهِ
حَسُنت جميعُ خصالهِ
صَلُّوا عليه و آلــــــهِ
በምሉዕነት
ላይ የታከከው፣
ውበቱ ፅልመት
የገሸለጠው፣
ያማረችለት
ሙሉ ተፈጥሮው
ይውረድ ሰለዋት
በርሱም በአህሉ!

ቢፅፍዎት ቢያወድስዎት ህመም መቀስቀስ እንጂ ከልብ እንኳን አያደርስም! የካዝናው ባልተቤት ምንዳዎን አብዝቶ ይክፈልልን! አንቱ የጀነት ጌጥ!
.
@Fuadmu

Fuad Muna (Fuya)

07 Sep, 21:31


የፈገግታ መጅሊስ ቅጂ

መድሁ ነቢ

የቅዳሜ ምሽት የሰለዋት ቆይታችን ላመለጣችሁ!

@Fuadmu