Abdul Aziz Nur @zizuq Channel on Telegram

Abdul Aziz Nur

@zizuq


في النهاية كلنا سنكون ذكرى

በመጨረሻም ሁላችንም ትዝታ እንሆናለን !

Abdul Aziz Nur (Amharic)

የAbdul Aziz Nur ሜዳ ከመላክ «አላህ መልካም የሻለትን ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል» ቡኻሪና ሙስሊም ጋር የተሻለ ነው። ይህ ሜዳ መናገር እና ትክክለኛ መረጃዎችን ለመማር ማድረግ ይችላል። ቡኻሪና ሙስሊም በአሁኑ ወንጌል ለመስከረም የፍቅርን መልእክትን እና ትክክለኛ ጽሑፍን ይምረጡ። እንደምሳና ሠላም ለመስከረም ያለውን ስላንጠገብ ይስጡ።

Abdul Aziz Nur

16 Feb, 17:43


🌱 سيكون كل شيء جميلا لكن يوما ما...

ሁሉም ነገር ቆንጆ ይሆናል ምናልባት ዛሬ አይደለም ግን አንድ ቀን !

Abdul Aziz Nur

16 Feb, 09:46


ከነሲሓ ኮንፈረንስ አላማዋች ውስጥ ሸሪአን ጠብቆ ትልልቅ ፕሮግሞች ማካሄድ እንደሚቻል አንዱ መሳያ ነው።

#የካቲት_16_2017
#አንድ_ሳምንት_ብቻ
#በእዝነት_ጥላ_ስር
#በሚሊኒየም_አዳራሽ

Abdul Aziz Nur

13 Feb, 17:34


ነሲሓ ኮንፈረንስ

የካቲት16/2017

👉🏻የመግቢያ ትኬትዎን በነፃ conference.nesiha.tv ላይ ይውሰዱ።

Abdul Aziz Nur

12 Feb, 14:28


ልጆቹንም አላህ ይዘንላቸው እሷንም ወደ ጤንነቷ አላህ ይመልሳት አሳዛኝ ክስተት ነው አላህ ከእንደዚ አይነት ድንገተኛ አደጋ ይጠብቀን።

Abdul Aziz Nur

10 Feb, 17:55


« ለፍቶ አዳሪ - ሥራና የሥራ ሰው ባህሪ» በሚል በኡስታዝ አህመድ አደም የተዘጋጀው መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል።

Abdul Aziz Nur

09 Feb, 18:31


ትኬት አልያዛቹም ወይ

የካቲት 16 በሚካሄደው ታላቅ የነሲሓ ኮንፈረንስ ላይ የመግቢያ ትኬት ያልያዛቹ
ከታች በተቀመጠው ሊንክ ገብታችሁ ቁረጡ
ባለፈው  አመት ተመዝግባችሁ ከሆነ ስልካቹን ብቻ በማስገባት ትኬቱን መያዝ ትችላላቹ በሉ ....በነፃ ትኬቶን ይያዙ

🏃‍♂‍➡️ https://conference.nesiha.tv

Abdul Aziz Nur

08 Feb, 20:11


🌱 የሰው ልጅ እግሩ እዚህ አለም ከረገጠ ጊዜ ጀምሮ ወደ መጪው አለም (አኼራ) መንገደኛ ነው፡፡ የጉዞ ቆይታው እድሜው ነው፣ ቀንና ሌሊት ማረፊያው ናቸው፡፡ ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ
🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

08 Feb, 19:45


في النهاية كلنا سنكون ذكرى

በመጨረሻም ሁላችንም ትዝታ እንሆናለን !

Abdul Aziz Nur

03 Feb, 19:00


ጌታዬ....
በሰባራ ልቤ_መጣሁኝ ከደጅህ
የቀረዉን ዱዓ_እምባዬ ይንገርህ

Abdul Aziz Nur

01 Feb, 19:04


ነገ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ ከስልሳ በላይ ሀገራት የሚሳተፉበት ታላቅ ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር በአዲስ አበባ እስታዲየም ይደረጋል !

Abdul Aziz Nur

27 Jan, 19:51


ወደ ሶስት መቶ ሺ የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ወደ ሰሜን ጋዛ መመለስ መጀመራቸው ተገልጿል አላህ ሰላም ያድርጋቸው።

Abdul Aziz Nur

27 Jan, 19:32


💔ወረቀት ቢሆን ቀደዋለው ብርጭቆ ቢሆን እሰብረዋለው ግድግዳ ቢሆን አፈርሰዋለው ግን ልቤ ነው...ይላል ዳርዊሽ ልክ ነው አንዳንድ ህመሞች አይለቁም እየቆዩ ያስደነግጡናል ።

Abdul Aziz Nur

26 Jan, 19:31


 " لا تَدْرِي لَعَلَّ اللَّهَ يُحْدِثُ بَعْدَ ذَلِكَ أَمْرًا " 

ጌታህ ምናልባት አዲስ ነገር ሊያመጣ እንደሚችል አታውቅም
🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

26 Jan, 19:21


" ብዙ አትናገር የሚሰሙህ መቼ እንደሚከዱህ አታውቅም ! ዳርዊሽ

Abdul Aziz Nur

25 Jan, 19:16


በገጠሩ ክልል ቤቶቻቸው ደከም ያሉ መንደሮቹ ያላደጉ የኑሮ ዘይቤያቸው ዝቅተኛ ቢሆንም መስጂዶቻቸው ግን ከመንደሩ ሁሉ ነግሶ ከፍ ብሎ የሚታይ ስፍራቸው ነው።

Abdul Aziz Nur

25 Jan, 14:56


ወላይታ ሀምዛ መስጂድ / የጉዞ ማስታወሻ

አስር እንደሰገድኩ ደከም ስላለኝ ጥግ ነገር ላይ ሄጄ ጋደም አልኩ እንቅልፍ ሸለብ አረገኝ ለካስ የተኛሁበት ቦታ ልጆች ቁርዓን ሚቀሩበት ቦታ ነው ሰአቱንም ማስተዋል ነበረብኝ  እኔ በተኛሁበት ቦታ ክብ ሰርተው ትናንሽ ወንበር አላቸው ሁሉም እዛ ላይ ቁጭ ብለው እየጠበቁኝ ነው አልቀሰቀሱኝም እኔም ከንቅልፌ ባነን ብዬ ቀና ስል ክብ ሰርተው  ፀት ብለው ያዩኛል ደንገጥ አልኩና እዚ ጋር ነው ምትቀሩት አልካቸው አዋ አሉኝ አፉ በሉኝ ብያቸው ተነሳው.....። የልጆቹ ስርአት ግን ደስ ይላል አላህ ይጨምርላቸው የትም ያለው ለዲን የሚደረግ እንቅስቃሴ ማየት ደስ ይላል አላህ ቀጥተኛውን ጎዳና ተረድተው የሚያድጉ ያድርጋቸው አሚን።!

የመስጂዱን ስም ያየሁት የብር መሰብሰቢያው ባንኮኒ ላይ ተለጥፎ ባየሁት ወረቀት ላይ ነው እንጂ ስለ መስጂዱ የቀደመ እውቀት የለኝም አላህ ሙስሊሞችን ሁሉ ባሉበት ይጠብቅ።

Abdul Aziz Nur

25 Jan, 08:35


በሚሊኒየም በሚዘጋጀው ታላቅ የነሲሓ ኮንፈረንስ ላይ የሚያሸልም የግጥም ውድድር !

Abdul Aziz Nur

24 Jan, 19:30


ሀዋሳ ላይ ያገኘሁት መስጂድ ነው። ኹጥባውም ስለ መሬት መንቀጥቀጥ ወደ አላህ ስለመመለስ ተያያዥ ቆንጆ ምክሮች ነበር። አልቆ ከዚ በተሻለ ውብ አላህ ያድርገው።

Abdul Aziz Nur

21 Jan, 19:51


ሂጃቧንም ትለብሳለች ትምህርቷንም ትማራለች ! በሚል መሪ ቃል በትግራይ መቀሌ ሰልፍ ተደርጓል የሂጃብ ጥያቄ እጅጉ ቀላል ጥያቄ ነበር ትንሹን አልመልስ ካላቹ በትልቁ ያድግላቹሃል ሀያላን ነን ባዮች ከታሪክ ተማሩ። እናተ ጀግኖች አብሽሩ በብዙ ፈተና አልፋቹሃል ይህም ይታለፋል።

Abdul Aziz Nur

20 Jan, 18:02


🌱 እናተ የጎዳቹን አዛ ያደረጋቹን ሰዋች ሆይ በዝምታችን ረፍት እንዳይሰማቹ በሁሉም ሱጁዶቻችን ላይ አላቹህና !

Abdul Aziz Nur

19 Jan, 18:37


ዝግጁ ናቹ !

Abdul Aziz Nur

19 Jan, 18:05


🌱 በየትኛው ስራህ ወደ አላህ እንደምትቀርብ አታቀውምና መልካም ነገርን አትናቅ!

Abdul Aziz Nur

03 Jan, 20:26


አስራ ስድት አመታትን በእስር ላይ የኖረ በመጨረሻም ዝዋይ እስር ቤት ከጌታው ጋር ተገናኝቷል። ከወጣትነት እስከ ጎልማሳነቱ  ታጋይ ጀግና ሰለምቴው ወንድማችን አማን አሰፋ ወደ ኢስላም ተመልሶ በአላህ መንገድ (ኢጅቲሃድ) አድርጓል አላህ በመልካም ጥረቱ ይያዝለት ጀነቱን ይወፍቀው።

Abdul Aziz Nur

30 Dec, 17:22


ብንዘገይም እንጠቁማቹ ገንዘብና ወለድ - እውነታ እና ብዥታ በሚል በሸይኽ ኢልያስ አህመድ የተዘጋጀ በአይነቱ ልዩ ጥናታዊና ወቅታዊ መፅሐፍ ገበያ ላይ ውሏል።

Abdul Aziz Nur

23 Dec, 19:20


ለአንተ መልካም ቢሆን ኖሮ አንተው ጋር ይቆይ ነበር። ላለፈህ ነገር አትጨነቅ!

Abdul Aziz Nur

15 Dec, 17:59


በየቴሌ ብር ቋሚ መዋጮ አከፋፈል

ለሌሎችም በማጋራት የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።
‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐‐

በቀን አምስት ብር ጀምሮ በምንችለው አቅም የሚያሳትፍ በዚ ልዩ አጋጣሚ አሻራችንን እናኑር!

Abdul Aziz Nur

15 Dec, 11:13


ነሲሓን በቴሌ ብር እናሻግር !!

Abdul Aziz Nur

15 Dec, 04:59


#እሑድ 08፡00 የጋራ አሻራ በነሲሓ ቲቪ

#ነሲሓ_ቲቪ_nesiha_tv

Abdul Aziz Nur

14 Dec, 20:28


"የዱንያ መንገድ ቀላል እና ምቹ ቢሆን ኖሮ ሶብር የጀነት መግቢያ አንዱ በር አይሆንም ነበር!"
ምርጥ ሶብር ማለት እየተፈተንክም ቢሆን
አል_ሐምዱሊላህ ማለት ነው።

Abdul Aziz Nur

08 Dec, 18:19


አል-ላሁ አክበር ኢራቅ ምንልበትም ግዜ ቅርብ ይሆናል ኢንሻአላህ!

Abdul Aziz Nur

08 Dec, 16:34


🌒 አማኞች አላህ ባመጣላቸው ድል ይደሰታሉ!

🌕 አል-ላሁ አክበር ሶሪያ!

Abdul Aziz Nur

08 Dec, 08:51


አላሁ አክበር

ሶሪያ ከጨቋኙ የበሽር አል አሳድ አገዛዝ ነፃ ወጥታለች እሱም ከሀገሪቱ መሸሹ ተገልፃል ድልም በመጨረሻ ለተበዳዮች ናቸው።

Abdul Aziz Nur

01 Dec, 19:53


አላህ ከነሱ ያድርገን !

Abdul Aziz Nur

29 Nov, 20:54


🌼 ታገሱ! አላህ ከታጋሾች ጋር ነው።

Abdul Aziz Nur

29 Nov, 03:29


አዲስ መፅሀፍ በቅርብ ቀን

« ገንዘብና ወለድ
እውነታ እና ብዥታ »
በሸይኽ ኢልያስ አህመድ

Abdul Aziz Nur

28 Nov, 19:57


💔..መለየት የሚለው ከሰውም አፍ በመፅሀፍ ድርሰት ስትሰማም ፣ ስታነበውም ልብን የማሸነፍ ይዘት ያለው ውሸተኛ ታሪክ መሆኑን እያወክም የመለየት መሪር ጠባሳው ተጋብቶብህ ባልተለዩ እያልክ መጨረሻውን ትጠብቃለህ። የእውነት የህይወትህ ታሪክ ሲሆን ታሪኩ ሚጀምረው ከመጨረሻው የመለየት እውነታ ስለሆነ ከባድ የሀዘን ስሜት ውስጥ ይከታል አንዳንድ መለየቶች ደሞ ይለያሉ ብዙ ህመም ፣ ቁጭት ፣ ችግር ፣ ፈተና ያለፈባቸው መለየቶች እያደረ ሚጠፋ ሳይሆን እያደረ ሚበረታ ህመም ነው። ህልም የመሰሉ ክስተቶች ነቅተን በተወን የሚያስብሉ ናቸው። ግን...ከሁሉም ክስተት ጀርባ የምድር ክስተቶች ከሱ ፍላጎት ውጪ ዝንፍ የማይሉት የረህማን ውሳኔ የረቀቀ ጥበብ የተሞላበት ከኛ ውጫዊ ምልከታ የራቀ ትክክለኛው የምድር ፍርድ የሱ መሆኑን ስታስታውስ ትረጋጋለህ። የአላህ ፍርድ ውሳኔ ከኛ ፍላጎት የተሻለ ነውና!። የሱን ፍርድ ወደህ ተቀበል ጌታዬ ለምን ይህን አትበል ጌታህ ማንንም አይበድልም።
وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا

Abdul Aziz Nur

23 Nov, 06:52


🛑 አፋልጉኝ 

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን ልጅ ዳንኤል ወርቅነህ ይባላል ለረጅም ጊዜ በገቢ እንዲሰራ የተሰጠውን መኪና በቀን 08/03/2017 በግምት ከጠዋቱ 4:30 ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ ከሚባለው ቦታ ይዞ በመውጣት ተሰውሯል ይህንን መኪና ያለበት የምታውቁና ያያቹ ወንድምና እህቶች ብትጠቁሙኝ ወረታውን እንከፍላለን

+251913979587
+251943163636

Abdul Aziz Nur

06 Nov, 18:15


🌱 የአላህ ውሳኔ ከምኞቶቻችን
ሁሉ የበለጠ ነው!

Abdul Aziz Nur

04 Nov, 18:38


በኒቃብ ያልቆመው ክልከላ ወደ ፂምም አድጓል ይህ በደቡብ ምእራብ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪ የሆነው ሰለምቴው መምህር አሸናፊ ትርፉ ለምን ፂምህን አሳደክ በሚል ከትምህርት ቤት እንዳያስተምር ታግቷል። በዚ ልክ የጥላቻ ጫፍ መንፀባረቁ አስገራሚ ነው። በዚው ከቀጠልን የሚመጣው ነገር አሁን ካለው ሚያስፈራ ይመስላል።

Abdul Aziz Nur

03 Nov, 19:05


🌸 የምታውቀውን ታውቃለህ ፤ የማታውቀውንም እንደማታውቀው እወቅ ፤ እውቀት የምታውቀውንና የማታውቀውንም ጭምር ለይቶ ማወቅ ነው።
ኡስታዝ አብዱልዋሲእ
🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

03 Nov, 14:39


🔸 ቀጥታ የሙሃደራ ፕሮግራም live 🅾

🗓 ከመግሪብ እስከ ዒሻ

🕌 በሳሪስ አስ-ሷሊህን መስጂድ

🔸የነብያት ውርስ በሚል ርዕስ በኡስታዝ አብዱልዋሲእ ነስሮ ይቀርባል

🎧 በጉረባእ የቴሌግራም ቻናል ቀጥታ ይተላለፋል ይከታተሉ 👇
t.me/GHUREBAMEDIA

⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA

Abdul Aziz Nur

03 Nov, 07:36


የታሰሩ የአዲስ ከተማ ሙስሊም ተማሪዎችን በተመለከተ ጉዳዩ የተብራራበት የድምፅ ፋይል ነው።

ለሚመለከታቸው አካላት ሼር አድርጉልን በማለት ይህን ድምፅ ልከዋል ሁላችንም ሼር በማድረግ እናዳርሰው።
🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

03 Nov, 03:39


💥 ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም በኡስታዝ አብዱልዋሲዕ ነስሮ

🕒 || ዛሬ እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

📖 || የነቢያት ውርስ

🕌 || ሳሪስ አቦ አስ ሷሊሂን መስጂድ

📍 ለሴቶችም ቦታ አለን !

⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA
t.me/GHUREBAMEDIA

Abdul Aziz Nur

01 Nov, 17:47


🥀 መገለጥ መብት ከሆነ
መሸፈንም መብት ሊሆን ይገባል።

Abdul Aziz Nur

31 Oct, 19:50


የሺ0 ወታደር ነው። "ዓኢሻ የእሳት ናት" ብሎ ግድግዳ ላይ ፅፎ ፎክሮ ሳይጨርስ የዓኢሻ ጌታ አፈር አበላው። የአላህ እርግማን በበዳዮች ላይ ይሁን።
=
ibnu munewor

Abdul Aziz Nur

29 Oct, 17:58


🌸 ኒቃብ ፊትን እንጂ አይምሮን አይሸፍንም

🌼 ስለ ሂጃብ ፊትን መሸፈን ወሳኝ መልእክት በሸይኽ ኢልያስ አህመድ

🌀መልእክቱን ሼር በማድረግ ለሌሎች እናዳር

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች_ትምህርቷንም_ትማራለች
🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

28 Oct, 18:15


🛑 ትኩረት ለእህትቶቻችን!

በተለያዩበ ትምህርት ቤቶች ኒቃብ ለብሳቹ አትማሩም በሚል ከትምህርት ገበታ እየተባረሩ ነው። አብዛኞቹ ኒቃብ ለብሰውም ሳይሆን የትምህርት ቤት የተሟላ ዩኒፎም አድርገው ማክስ ስላደረጉ ብቻ ማክስም ማድረግ አትችሉም በሚል እየተከለከሉ ነው። የሚከለክሉትም ኒቃቢስት መሆናቸውን ስላወቁ ብቻ ነው። ማክስ እንዴት ይከለከላል የተማመም ፣ ራሱን ለመጠበቀም ሰው ያደርጋል ለኮሮኖ ግዜ ማድረግ ግዴታም ሆኖ ነበር ታዲያ ከመች ጀምሮ ነው ማክስ ሀይማኖታዊ መገለጫ የሆነው ሆን ብሎ ለይቶ ሙተነቂብ መሆናቸውን የሚታወቁ ተማሪዋችን ሲከለከሉ የጥላቻቸውን ጥግ እንጂ ሌላ የሚጨበጥ ምክንያት የላቸውም። ስንት መማር ፈልገው በዚ የተነሳ ቤት ተቀምጠው ሲውሉ እጅግ ያሳዝናል የሚመለከተው አካል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች_ትምህትቷንም_ትማራለች
🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

27 Oct, 11:54


በኢብኑ መስድ ኢስላሚክ ሴንተር የጉራጌ ዞን ዳእዋ አስተባባሪነት በጉብርዬ ከተማ በሚገኘው ነሲሓ መድረሳ ለ3 ተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የቆየውን ዱዓቶች በልዩ ድምቀት አስመርቋል። በፕሮግራሙ ላይ ታላላቅ መሻይኾችና የነሲሓ ዳዕዋ አጋሮች ተገኝተዋል።

አላህ ተመራቂዎቹን እውቀትን ይጨምራለቸው፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚጠቅም ኸይር ስራ ሁሉ ያግራቸው።

Abdul Aziz Nur

25 Oct, 17:52


"ዱዓ ለተከሰተም ገና ለሚከሰትም መከራ
እጅግ ጠቃሚ ነው።
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! ከዱዓ እንዳትዘናጉ አደራ!!"
ረሱል (ﷺ)
(ሰሂህ አልጃሚዕ: 3409)

Abdul Aziz Nur

23 Oct, 19:29


ልባም ሰው አላህ ይጨምርልህ የኔ ልብ ውስጥ የተቀመጠው አንዋር መስጂድ በጀግንነት የተውሂድ ዳእዋን ሲደግፍ ያየውት ቀን ነው።

ቲክቶክ መንደር በሱ ፅሁፍ ተጨናንቋል ሙስሊም ያልሆኑትም የሱን ዜና ለማንበብ ሲሉ አልሃምዱሊላ ሲደጋገም ውሏል ምንኛ ያማረች ቃል ናት ኢላሂ ስለሁሉም ነገርህ አልሃምዱሊላህ።

ብዙ ልባም ሰዋችም እዚም መንደር እያየን ነው እነሱ ተጎድተው ብዙ ነገራቸውን አጥተውም ለሌሎች ሚደርሱ ምርጥ የአላህ ባሮችንም አየን እንደዚ አይነት ሰዋች የእውነት ልብን ያሸንፋሉ አላህ እጥፍ ድርብ ድርብርብ አድርጎ ይመልስላቸው።

ሌሎች ደሞ አጋጣሚውን ተጠቅመው የሰዋችን ንብረት ለመውሰድ የሚሯሯጡም አየን ይህች ምድር ብዙ ጉዳጉድ ተሸክማለች ካጣው ሚሰጥ እና በሰዋች ሀቅ መክበር ሚፈልግ የሁለት አለም ሰዋች። ኢላሂ አንተው በጥበብህ ካጡት በላይ ሙላላቸው ያላሰቡትን ሪዝቅ ወፍቃቸው።

ምስሉን በበጎ አድራጎት ስራ የሚታወቀው ማስተር አብነት ለኔ ትልቅ ትምህርት ስለሆነ ለ15 ቀን ፕሮፋይል ይሁን በማለት የወንድሜ ሀሩን ፎቶ ካስቀመጠበት የተወሰደ። አላህ ከፍ ከፍ ያድርግህ ከዚም በላይ።

Abdul Aziz Nur

22 Oct, 19:37


ሁሉም ከአላህ ዘንድ ነው። የአላህ ውሳኔ ከሰዋች በላይ ረቂቅ ጥበቦች የተሞላበት ነው። ይህን ረቂቅ ጥበብ በመጨረሻው በሰብር ታግሶ ፍሬውን የቀጠፈ ይጎናፀፈዋል። አብሽሩ በተሻለ መንገድ ተቀይሮ ያልፋል።

Abdul Aziz Nur

21 Oct, 20:04


መርካቶ ሸማ ተራ የተነሳው እሳተረ እስካሁን ማጥፋት አልተቻለም ተብሏል አላህ ቀላል ያድርገው አብሽሩ ሁሉም ነገር ለኸይር ነው።

Abdul Aziz Nur

21 Oct, 17:59


በአሁኑ ሰዓት መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተነስቶዋል መልእክቱን ሼር በማድረግ ለሚመለከታቸው እናስተላልፍ።
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA

Abdul Aziz Nur

21 Oct, 17:50


ሙስሊም ሆነህ ስለ መስጂድ አል-አቅሳ ካልተመለከተህ ለዲኤንኤ (ዘረመል) ምርመራ ገንዘብ አያስፈልግህም ውጤትህ ግልፅ ነው። ሙናፊቅ ነህ።
ኡስታዝ አብዱልዋሲዕ

Abdul Aziz Nur

20 Oct, 10:10


وَلَا تَحْسَبَنَّ الَّذِينَ قُتِلُوا فِي سَبِيلِ اللَّهِ أَمْوَاتًا بَلْ أَحْيَاءٌ عِنْدَ رَبِّهِمْ يُرْزَقُونَ

Abdul Aziz Nur

18 Oct, 18:26


🪴 ዱንያ ላይ መልካሙም ይሁን መጥፎው ዘላቂ አይደለም ፡፡

ዛሬ ስለደረሰብህ መጥፎ ነገር ህይወትን አታማርር ፥ ተስፋም አትቁረጥ ፡፡  ምክንያቱም እንኳን የአንተ ችግር ዱንያም እራሷ  ዘላቂ አይደለችምና  ፡፡ በተቃራኒው ዛሬ  ባገኘኸውም መልካም ነገርም  አትንቦጣረር ... እንኳን ያገኘኸው መልካም ነገር አንተም የሆነ ጊዜ ላይ ጠፊ ነህና !

#ሁሉም_ጊዜያዊ_ነው
🍂 @zizuQ

Abdul Aziz Nur

18 Oct, 18:01


🔺የሃማስ መሪው ያህያ ሲንዋር ተገድሏል

የፊሊስጤም ነፃነት በጀግንነት ሲታገል የነበረው ያህያ ሲንዋር በጀግንነት ፊት ለፊት እየተዋጋ ሞቷል። ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሞያሳዩት አንድ እጁን ተቆርጦ በአንድ እጁ እስከመጨረሻው ታግሎ ህይወቱ አልፏል አላህ ይዘንለት።
⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA

Abdul Aziz Nur

15 Oct, 19:37


🌱 ሁሉም ፀጋ ተወጋጅ ነው የጀነት ሰወች ፀጋ ሲቀር፡ ሁሉም ጭንቀት ተወጋጅ ነው የጀሀነም ሰወች ጭንቀት ሲቀር። (ሀሰኑል በስሪ )

Abdul Aziz Nur

14 Oct, 14:33


🔺ያለፈው አልፏል ልቀቀው!

Abdul Aziz Nur

11 Oct, 18:57


የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛቱ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036

Abdul Aziz Nur

09 Oct, 18:14


🌱 የማይሰግድ ሰው አላህ ይቀጣዋል ብለን እናስባለን ፣ አለመስገዱ ራሱ ትልቅ ቅጣት መሆኑን ዘንግተነዋል።

Abdul Aziz Nur

08 Oct, 16:35


🌼 وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَى

" ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል ትደሰታለህም "

🍂t.me/zizuQ

Abdul Aziz Nur

08 Oct, 16:22


🔎 ከሐሳብ እና ከጭንቀት እንዴት መውጣት እንችላለን?»

🎙አቅራቢ፦ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ አል-ባጂ

Abdul Aziz Nur

07 Oct, 20:40


🌼 ጣፋጭ ቁርዓን ተጋበዙ

Abdul Aziz Nur

02 Oct, 17:14


♨️ ትናት መሽት ኢራን እስራኤል ላይ 180+ የባላስቲክ ሚሳኤል ስታዘንብ አድራለች።

⚡️ጉረባእ ሚድያ-GHUREBA MEDIA

Abdul Aziz Nur

30 Sep, 18:34


በኮረና ግዜ ሰው እንደዚም ተጠይቋል🤕 የአላህ ተአምር የማያልፍ መከራ የለም ልጁ ግን ከዱር አድነውት ነው ሚመስለው 😊

Abdul Aziz Nur

29 Sep, 15:03


🌊 ተራራውን መውጣት ሳይሆን ጫማዬ ውስጥ ያለው ጠጠር ነው ያስቸገረኝ...!  ሙሐመድ አሊ

አንዳንዴ የህይወት ፈተናዋች እንደዚ ትናንሽ ነገሮች ምንላቸው ድክመቶች ተደራርበው ይጥሉናል። ትልቅን ነገር ለማሳካት ትንሽ ሚባሉ ነገሮችን በብቃት ልነወጣው ግድ ይላል። ካለዛ ዳገቱን ሳንጀምረው ጠጠሩ ይጥለናል።
🍂t.me/zizuQ

6,139

subscribers

1,157

photos

233

videos