በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት በማምጣት አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መረሐግብር ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ታህሳስ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ስድስት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
የምዝገባ ቦታ፦
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቦቆጂ ካምፓስ
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግብርና ኮሌጅ ካምፓስ
Note:
ለሪሚዲያል ፕሮግራም አርሲ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።
@tikvahuniversity