Halal Fkr @halalfkr Channel on Telegram

Halal Fkr

@halalfkr


Elegant. Faithful. Halal.


Tiktok: http://tiktok.com/@halalfkr

https://telega.io/c/halalfkr

Halal Fkr ♡ (English)

Are you looking for a channel that promotes positivity, beauty, and all things Halal? Look no further than Halal Fkr ♡! This Telegram channel is dedicated to spreading the message that living a Halal lifestyle is not only beautiful but also fulfilling. With a focus on Islamic values and principles, Halal Fkr ♡ aims to inspire its followers to embrace Halal practices in all aspects of their lives. From fashion to food, from relationships to spirituality, this channel covers it all with a touch of elegance and grace. Who is it? Halal Fkr ♡ is a community of like-minded individuals who believe in the beauty and importance of living a Halal lifestyle. They share tips, advice, and inspiration to help others incorporate Halal practices into their daily routines. What is it? Halal Fkr ♡ is a Telegram channel that provides a platform for discussions, ideas, and resources related to living a Halal lifestyle. From sharing Halal recipes to promoting Halal fashion brands, this channel is a one-stop destination for anyone interested in embracing the beauty of Halal living. Join Halal Fkr ♡ today and be part of a community that values positivity, beauty, and the importance of Halal practices in today's world. Follow them on Tiktok at tiktok.com/@halalfkr and reach out directly to @Sem_ir for more information. Let's spread the love and beauty of Halal living together! 🤍

Halal Fkr

12 Jan, 13:38


የፍቅር ጓደኝነት ቦቶች፡ በተለይ ለቤቶች
🌸 IntroductionDating ቦት ጓደኝነትን ወይም አጋርን እንድታገኝ የሚረዳህ ለሴቶች የተዘጋጀ ብልጥ መድረክ ነው።
💖 ዋና ዋና ባህሪያት
ትክክለኛ ግጥሚያ፡ በፍላጎቶችዎ እና ምርጫዎችዎ ላይ በመመስረት። አለምአቀፍ ግንኙነት፡ ከመላው አለም የመጡ ሰዎችን ያነጋግሩ።በግላዊነት የተጠበቀ ነው፡ ውሂብዎ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ ነው። ጓደኞችን ይጋብዙ፡ ተጨማሪ ተዛማጆችን ይክፈቱ። እንዴት መጠቀም እንደሚቻል
1️⃣ ይመዝገቡ፡ ዝርዝሮችዎን ያካፍሉ።2️⃣ ግጥሚያ፡/ተዛማጅ ትዕዛዙን ይጠቀሙ።3️⃣ ጓደኛዎችን ይጋብዙ፡ ሊንኩን ያካፍሉ።
🎉 አሁን ይቀላቀሉ እና ጉዞዎን ይጀምሩ!
URL፡ https://t.me/DatingEngagement

URL፡  https://t.me/DatingEngagement_bot

Halal Fkr

12 Jan, 13:37


Mnm endatneku ketach yalewn አድስ ነው 😌

Halal Fkr

10 Jan, 13:09


ትዳር በቁርዓን 💍📖

በሱረቱል ቀሶስ ሌላ ቦታ የማናገኘውን አንድ የሙሳን የህይወት ክፍል እናገኛለን “ሙሳ እንዴት ትዳር ያዘ?” የሚለውን ማለት ነው። በቁርአን እንዴት ትዳር እንደያዘ የተነገረን ሌላ ነብይ የለም ።

ታሪኩን ሁላችሁም ስለምታውቁትና ከዚህ በፊትም ስለተነጋገርንበት አልደግመውም! ግን ˹ከተለየ አንግል˺ እንቃኘው እስኪ ...

እነ ፊርአውን ሙሳን ሊያስሩትም ሆነ ፍርድ ቤት ሊወስዱት ሳይሆን በቀጥታ ሊገድሉት ስለነበር «አሳ አን የህዲየኒ ረቢ ሰዋዓ ሰቢል» ብሎ ዱዓ አድርጎ ከግብፅ ወጣ ።

መድየን ላይ ያሉት ሰዎች ሴቶችን የሚያከብሩ ማህበረሰብ አልነበሩም ። ለዛም ነው ወንዶቹ ከብቶቻቸውን አጠጥተው እስከሚጨርሱ ሴቶቹ የሚጠብቁት ። ሙሳ ለሴቶቹ ከብቶቻቸውን አጠጥቶላቸው ወደ ጥላው ሄዶ "ረቢ ኢኒ ሊማ አንዘልተ ኢለዬ ሚን ኸይሪን ፈቂር" አለ ። "ፈቂር" ማለት ምንም የሌለው ድሃ ማለት ሲሆን ሌላው ትርጉሙ ደግሞ የጀርባ መሰበር ነው ። ምግብ የለኝ ፣ ብር የለኝ ፣ ማደሪያ የለኝ በቃ ምንም የለኝም ፤ ምንም ነገር ብትሰጠኝ እቀበላለሁ .. አላማርጥም! ማለቱ ነው ።

የዚህ አያ ሌላው ትርጉም ደግሞ ሙሳ ሰው በመግደሉ ተፀፅቷል .. "ኢነል ሃሰናት ዩዝሂብነ ሰይዓት" የሚለውንም ያውቃል ። ስለዚህ “የትኛውንም መልካም ስራ ለመስራት ዝግጁ ነኝ!” ማለትም ይሆናል ። ለሴቶቹም ኸይር ሰርቶላቸዋል ሌላም እንደዚሁ የምሰራው ነገር ካለ እሰራለሁ .. ኸይር ስራ ያስፈልገኛል! እያለ ነው ።

"አንዘልተ ኢለይ" የሚለውን ወደ እኛ ህይወት ስናመጣው .. የትኛውም ሰውን ለማገዝ የምናገኘው እድል ከአሏህ የወረደ መልካም አጋጣሚ ነው ማለትን ያስይዛል ። ሙሳ ፈቂር ከሆነ ደግሞ እኔና እናንተ የበለጠ ለየትኛውም መልካም ስራ ፈቂር ነን!

ሁለቱ ሴቶች ወደ ቤት በጊዜ ሲደርሱ ቁርአን ባይነግረንም መገመት አያቀረተንምና .. አባትዬው ይገረማል ፤ ምን ተከሰተ? ብሎም ይጠይቃቸዋል ። ሴቶቹም፦ እንደ ሌሎቹ ወንዶች ያልሆነ ሰው አገኘን .. ባህሪውም ይለያል ፣ እሱ የሚያየን ሌሎቹ ወንዶች እንደሚያዩን አይደለም ። እሱ ሲያወራን ሌሎቹ ወንዶች እንደሚያወሩን አይደለም ። አግዞንም ወደቤት ልሸኛችሁ ምናምን ብሎ አልተከተለንም .. በቃ ልዩ ሰው አገኘን አሉት ።

አባትም በዚህ በተበላሸ ማህበረሰብ ውስጥ ለልጆቹ መልካም ባል ማግኘት አስቸጋሪ ሆኖበት ነበር ። ይህ ሰው ጥሩ ሰው ነው የሚለውን አሰበ ። አንዲቷ ስለሱ ስትነገረው እንደፈለገችው ሆና ስለነበር “ሂጅና ጥሪው!” ብሎ ላካት .. 

💭 እዚጋ እሰቡት ...
እናንተ አባት ብትሆኑና ሁለት ሴት ልጆች ቢኖራችሁ .. የሆነ አጅነቢ ወንድ እንድትጠራ ማዘዝ ከፈለጋችሁ አንዷን ብቻዋን ከመላክ ሁለቱንም አብሮ መላክ ሴፍ ነው ትላላችሁ አይደል? በቁርአን ግን የምናገኘው "ወጃዓት ኢህዳሁማ ተምሺ አለ ኢስቲህያዕ" የሚል ነው ።

አንዷን ነው የላካት .. በሃያዕ ተራምዳ ሙሳ ጋር ደረሰች .. ሙሳ ድጋሚ ሲመለከታት “ምነው ተጨማሪ እርዳታ ያስፈልግሻል?” ፣ “ለምን መጣሽ?” አላት ..  እየፈራች አይ አይ አባቴ ነው የጠራክ .. ስላገዝከን ሊከፍልህ ፈልጎ ነው አለችው ።

💡አሁን እዚጋ ቀላል ጥያቄ ይነሳል .. ሙሳ ለአሏህ ብሎ አልነበር እንዴ ያገዛቸው⁉️ ወይስ ክፍያ ለማግኘት ነው ያገዛቸው

📌የሙሳ ኒያው ኢባዳ ነው َ፤ ለአሏህ ብሎ ነበር የሰራው ። ሙሳ ወደጎን ዘወር ብሎ “ጀዛኪሏህ ፣ እኔ ለአሏህ ብዬ ነው የሰራሁት .. ምንም የዱንያ ነገር አልፈልግም .. thank you so much .. አሁን ሂጂ በቃ ወደ አሏህ ዱዓ በማድረግ ልቃረብ ” ወዘተ ... ሊላት ይችል ነበር አይደል? እሱ ግን “እሺ በደስታ! መከፈል ማን ይጠላል🙂‍↔️ ብሎ ተከተላት ..

ለምን እሺ ብሎ ተከተላት? ካላችሁ..
አሏህ የዱዓን ነገር እንዴት መረዳት እንዳለብን እያስተማረን ነው ። "ኢኒ ሊማ አንዘልተ ኢለዬ ሚን ኸይሪን ፈቂር" ብሎ ያደረገው ዱዓ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው ይች ሴት የመጣችው .. ይህን ተረድቷል .. ስለዚህ ከዚህ በላይ more islamic than islam መሆን አያስፈልግም ። ዱንያም ያስፈልገዋል ። ያገኘውን አጋጣሚ መጠቀም አለበት ።

ወደ አባቷ ሲሄድ አንዳንድ ጥያቄ መጠየቁ አይቀርም .. አይቼክ አላውቅም .. ከየት ነው የመጣከው ምናምን እያለ ሲጠይቀው ሁለቱ ሴቶችም እየሰሙ ነው ። "ወቀሶ አለይሂል ቀሶስ" እንዳለው ሙሉ ታሪኩን ተናገረ ። በቤተ መንግስት ነው ያደግኩት .. ድንገት ሰው ሞተብኝና አሁን እዚህ ቤት የለኝ ፣ ብር የለኝ ፣ ምንም የለኝ and here i am ..

ሴቷ ልጅ ቅጠረው አለች.. dad i love you, give him a job🎈 ዳረኝ ማለቷ ነው እሷ .. እሱም ገብቶታል ።

🖊 የገረመኝ ነገር እነዚህ ሴቶች ወንዶችን ካለማመናቸው የተነሳኮ አንድ ሃይቅ ላይ ከወንዶች ጋር ከብቶቻቸውን አያጠጡም ነበር .. አሁን ግን ሙሳን አመኑትና ቤት ውስጥ ተቀጥሮ እንዲሰራ ፈለጉ 📝

የትዳሩን ፕሮፖዛል እሰቡትማ .. በግድያ የምፈለግ ሰው ነኝ ፤ ስራም ሆነ መኖሪያ የለኝም ሲል አባት ደግሞ ስምንት አመት አገልግለኝና ልጄን ኒካህ ልሰርልህ አለው ። ጥሩ መሆኑን አወቀ .. ቀሪው ከአሏህ ይመጣል። ሙሳም ስራ አልነበረውም አገኘ ፤ ሰውዬውም ለልጁ ጥሩ ባል አገኘ ። ሁለቱም ተጠቀሙ 💜

ትዳርን ቀላል እናድርገው .. We can't blame kafirs, media, tiktok, internet ... their job is to make haram easy ... Our job is to make the halal easy! .. so when we make the halal difficult then we don't get to blame any body else, we have to blame ourself !

©️ khrebin⌯

Halal Fkr

10 Jan, 11:58


Here's a highly reliable online part-time job platform that I would like to recommend to you: BTT.

BTT is one of the largest advertising networks globally and is currently recruiting online part-time employees in Ethiopia.

No academic qualifications or work experience are required, and you can easily start earning money with just a smartphone. By downloading the designated app and increasing the download rate of other companies, you can earn lucrative referral fees.

💸 Daily income up to 4,000 ETB

📱Simple operation, only 15-20 minutes per day

Free without any investment

📈 Provides exclusive training to help you

If you are interested in this opportunity

please click the BTT official channel to contact customer service:

https://t.me/+fKeyX9Wh95wxMWNl

Halal Fkr

07 Jan, 07:07


😂❤️

I will rather trust a car with no brakes than "He is just a friend''
I was once a friend, and I know what i did

Halal Fkr

05 Jan, 06:04


Hello everyone! 🌟 I'd like to introduce you all to a lucrative job opportunity.
BTT is one of the largest advertising networks globally, and it is currently hiring online part-time employees in Ethiopia. 🌍
No academic qualifications or work experience are necessary – just a smartphone is all you need to get started.
📱 By downloading a designated app and boosting the download rates of other companies, you can easily begin to earn money! 💸
💰 Income Security: You can earn up to 25,000 ETB daily. With daily settlements and real-time withdrawals, your income is more secure than ever!
🌟 Key Advantages:- Zero Threshold: No professional skills required.- Safe and Reliable: All apps are rigorously selected to ensure information is secure!- Flexible Scheduling: Participate anytime that suits you.
📢 Limited-time Benefit: The first 100 joiners will have the chance to receive a reward of 5,000 ETB! 🎉
Join the official BTT channel, contact the customer service within the channel to register, and start earning money today! 💼🚀
https://t.me/+u5l252_cZTVmNmNl

Halal Fkr

01 Jan, 15:59


❤️

Halal Fkr

25 Dec, 12:10


like i always say😂

Halal Fkr

23 Dec, 19:48


ብቸኝነት ለአላህ ብቻ የተገባ ነው።
በርግጥ የሰው ልጅ አንዱ ለአንዱ ሆኖ ነው የተፈጠረው¡

ነገር ግን ያንቺ የሆነው ወንድ
በአባትሽ በር እስኪመጣ ብቸኝነት ጌጥሽ ሊሆንሽ ይገባል። በሀራም relationship ከሆነ ግን..እራስሽን መበደል ነው የምሆንብሽ¡

.. ወንድሜ አንተም እንደዛው;)

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | ▶️ ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr

22 Dec, 10:28


👨‍⚕️ Someone asked me that -
His wife talks with someone whom she called her best friend, and when he ask her to stop talking with him. .

🧕 She relied ''never bruh we have a promise to be friends until we die!🫠 and i don't want to break his heart, Chill he's just my friend and we (me and u) can break up if u want to ..🤷‍♀️ ''


Broo She’s more worried about his feelings than yours?
"Just her BF," but she’s acting like their promise is more important than your relationship? That’s straight-up disrespectful fr 🙌😂

That's a red flag tbh
A relationship is supposed to be you and her
not you, her, and some other guy she’s protecting.. You’re supposed to be her priority, not an option.

If she truly cared about you, she would’ve prioritized your emotions over some “promise” to another guy.

Yeah ከእናንተ ግንኙነት የበለጠ የሱ ልብ እና የቃላቸው መሰበር ካሳሰባት ይሄ ከጓደኝነት የበለጠ ለሱ ስሜት እንዳላት ማሳያ ነው ሌላ ሰው መርጣለች ደግመህም ስለሷ እንዳታወራ ክብርህ ይቀንሳል it's over Block her from ur life.
ልጅ የላችሁም ብዬ ተስፋ አረጋለሁ poor bro 😂

Halal Fkr

20 Dec, 15:56


ረሱል 🤲 እንዲህ ብለዋል፦

❝ አንድ ሰው 3 ሴት ልጆች ኖረውት ከሚችለው ካበላቸው ፣ ካጠጣቸው እንዲሁም ካለበሳቸው የቂያማ ቀን ለሱ ከጀሀነም እሳት ከለላ ይሆኑለታል ❞

❝ The Messenger of Allah 🤲 said:
Whoever has three daughters, and he patiently supports them, feeds them, gives them to drink, and clothes them from his wealth, they will be a shield for him from the Fire on the Day of Resurrection.❞

Sunan Ibn Majah 2974

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | ▶️ ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr

09 Dec, 16:30


አንድ ሰው በሚስቱ ክፋት ተማረረና ለአንድ ሸህ ብሦቱን ተናገረ፡፡ ''እኔ ምላሷን አልቻልኩም አቆሰለችኝ😀” አላቸው

ሸሁም “እስቲ አትናገራት መጥፎ ይሁን ጥሩ በምትሠራው ነገር ሁሉ  ዝም ብለህ አወድሳት” አሉት
ሰውዬውም የሸሁን ምክር ተቀበለ.. ወደ ተግባር ለመለወጥም ተዘጋጀ

አንድ ቀን ሚስቱ እራት አመጣችለት አስቀምጣለትም ዘወር አለች እንዳትርቅበት እየተጣደፈ ገና አንድ እንደጎረሰላት
''ዉይ ዉዴ የዛሬው ምግብሽ ሲጣፍጥ እኮ!🥰'' አላት

እሷም “አልቀረብህም እንደው እኮ ትገርማለህ! ስንት ዓመት ሙሉ መርዝ የበላህ የኖርክ መሰለህ? እኔ የሠራሁትን ምግብ አንድም ቀን ሳታሞግስና ሳታደንቅ ዛሬ ጎረቤታችን ያመጣችዉን ምግብ የምታደንቀው?😀''

ለካስ የቀረበለት ምግብ ከጎረቤት በሀዲያ መልክ የመጣ መሆኑን አላወቀም ነበር ሚስኪን ባል ወይ ኪሳራ🤦‍♂️😀😀

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | ▶️ ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr

09 Dec, 16:29


Bros, Need Muslim brother to connect with.. pray together, and strengthen our deen. Let’s support each other on this beautiful path. DM me if you’re interested🙌
@Sem_ir

Halal Fkr

07 Dec, 16:10


ጠራኝ  ዚዝ.. ዚዙ.. ዚዛ . ዚዞ..ብሎ..

አሚር ነው ።

ከአሚሮ ጋር አብረን ነው ያደግነው! ስለህልማችን  አውርተን፣ ተከራክረን፣ ተደናንቀን፣ ስቀን አልቅሰን እናውቃለን ።

አሚሮ እና እኔ ውሎ መንገዳችን ስታይላችን
እየለየን እየለየን ጓደኝነታችን ሳስቶ ተራራቅን ።

በቅርቡ ከስንት አመት ቡኋላ አወራን ዚዞ አለኝ፤ ድሮ እንደሚጠራኝ ጠራኝ ። ጓደኞቹ ሲቀፍሉኝ ፊቱን እንደማያቀኝ ወደ ሌላ በኩል ያያል፦

ዛሬ ግን ዚዝ አለኝ ማነው የሚጠራኝ አይነት ዙርያዬን ሳጠራ አሚሮ ነው ።

ስጠጋው ቁጭ ብሎ  ከነበረበት  ቆሞ አቀፈኝ ትንሽ ጅብርር (ፍዝዝ)ድንቁር ብሏል።

አሚሮ  ሱሰኛ ሆኗል ።

"ወንደሜ ነህ እኮ አንተ፤ ህልሜን ልጅነቴን ህይወቴን ከማንም በላይ ታቀዋለህ ። እኔ የማወራው ነገ የለም ትላንቴ ከዛሬ ስለሚሻል እሱን ነው እየማልኩ የምተርከው። ከትላንት እንደማነስ መውደቅ የለም !!

ስለተሳካልህ ፣ ስላማረብህ ደስስ ይለኛል ያንተ መሳካት አይደለም ደብሮኝ የዘጋሁክ ኋላ መቅረቴ አሳቆኝ ነው ።  

መቼ እንደዚህ እንደሆንኩ አላውቅም ። እራሴን አልወደውም፤ በየቀኑ እያነስኩ ነው  ብሎ እምባው ወረደ ።

ወይኔ አሚሮ ሱስ ሳይበላው፤ ሲገራ መግዣ መለመን ሳይጀምር፤ ጉስቁልና ሳያፈዘው ለልብሱ መቆሸሽ ደንታ ቢስ ከመሆኑ በፊት፤ ሰዎችም ሲጣራ ባልሰማ መሄድ ሳይጀምሩ፤ ቃል አባይ ከመሆኑ በፊት፤ ክብሬ ማለት ሳያቆም፤ ለትንሽ ለትል መላክ ሳይጀምር በፊት ... ቆንጆ፣ ተወዳጅ፣ ዘናጭ ነበር'ኮ፡፡

ከጓደኞቹ ከኛ በላይ ድምቅ  ያለ ልጅ ነበር፤ ቆንጆ አማርጦ ይሰክስ ነበር፤ የፀጉሩን ፍሪዝ በመስታወት አስር ጊዜ እያየ አስር ጊዜ ያስተካክል ነበር'ኮ፡፡

ህልመኛ ነበር፡፡

እንደ ሁሉም ሀብታምና አዋቂ መሆን፤ ቤተሰቡን ዲኑን የመርዳት ህልም ነበረው፡፡ የተንሸዋረረ አድራጎት አሳስቶ የለኮሳት ሲጋራ፤ ለሳቅ ብሎ የተጎነጫት አረቄ፣ ለሙድ ብሎ የሞከራት ሀሽሽ፣ ለሙድ ብሎ የቀነጠሳት የጫት ቅጠል  ስትደጋገም አፈዘዘችው፤ ህልሙን ወጣትነቱን ክብሩን አረገፈችው፡፡

በሀሳብ የኋሊት ወደልጅነታችን ወሰደኝ
እንባውን ጠርጎ ጭዌውን ቀጠለ።

አሁን በቀደም ከጀለሶቼ ጋ እርቦኝ፣ ቸስተን ስንቀራፈፍ  መፅሀፍ ይዘህ በጀለቢያ ቂቅ ብለህ እረጋ ብለህ በቀስታ ስታልፍ  ወደ አንተ እየጠቆምኩ ዚዝ አብሮ አደጌ ነው እንዋደድ ነበር ስላቸው ለምን መላ  አትቀፍለውም አሉኝ..

ዝም አልኳቸው ወላሂ  ዝም አልኳቸው።

በነሱ ፊት ስጠራክ ባልሰማ ብታልፈኝስ !?  የለኝም ብትለኝስ ይደብረኛል ኣ አሚራ ነኝ እኮ ካልሞትኩ በቀር የድሮ ማንነቴ ሁሉም  አይጠፋም ።

አሳዘነኝ ...

የተቀዳደ ልብስ ለብሶ ፊቱ ተጠባብሶ
ህመሙን ፍቅሩን ሲነግረኝ
ቀርቤ በትኩረት ስለሰማሁት ስላዋራሁት እንደ ትልቅ ጉዳይ ቆጥሮት   ደስ ብሎት ሳየው ድብርት ታከከኝ ።

እንዴት እና መቼ  ከአሚሮ ጋ እንዲ
እሩቅ ለሩቅ እንደሆንን አላውቅም።
.
.
©z‌i‌z‌

Halal Fkr

05 Dec, 09:20


Maybe our 'boring' lifestyle has kept us safe from many haram experiences.. hmm

Halal Fkr

22 Nov, 10:56


🦋 ሳታገቢ ከዘገየሽ
የሙዑሚኖች እናት ኸዲጃን (ረ.ዓ) አስታዉሺ.. በመጨረሻም የፍጡር የበላይ የሆኑትን ነብይ ﷺ አገኘች 😊

😫 ጭራሽ ካላገባሽም
መርየም ቢንት ኢምራንን አስታዉሽ
አላህ እንዴት ከፍ እንዳደረጋት በዱንያም በአኼራ 🤗

☹️ ከመጥፎ ባል ጋር ከኖርሽ
አስያን የፊርአዉንን ሚስት አስታዉሽ.. አላህ በጀነት ዉስጥ ቤት እንደገነባላት 🫠

🫀 ከትዳርሽ ከተፋታሽም የአላህን ቃል አስታዉሽ
እህቴ ሆይ እወቂ ሪዝቅ (ሲሳይ) ተፅፎ ያለቀ ነዉና አትቸኩይ

አላህ ከሰብረኞች ያድርገን መልካም ትዳር ይስጠን አላሁመ አሚንን ❤️

©

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | ▶️ ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr

19 Nov, 16:26


Future dream of HF😍

BTW እናንተም register ማረግ ትችላላችሁ Simply Nikkah👈 Go nd find ur soulmate.

130 ጥያቄ ነው የምትጠየቁት Jk ብሎ መግባት አይታሰብም.. don't try it😇😅

Halal Fkr

15 Nov, 13:48


ለማን ልዳራት?

አንድ ለትዳር የደረሰች ሴት ልጅ ያለው ሰው ወደ ሐሰን ኢብኑ ዐሊይ (ረ.ዐ) መጥቶ፦አንዲት ሴት ልጅ አለቺኝ። የተለያዩ ሰዎች እንድድርላቸው እየጠየቁኝ ነው። ለማንብድራት የሚሻል ይመስሎታል? ሲላቸው፥

ሐሰንም ፦ አላህን ለሚፈራ ሰው ዳራት፤ የሚወዳት ከሆነ ያከብራታል፣ ባይወዳት አይበድላትም አሉት።

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr

14 Nov, 14:45


ለምን ዓለምን አትመራም
ለምን ዱንያን አትገዛም
ለምን ሰባት ድግሪ አይኖራትም

"ሴት ልጅ ባል ከሌላት ሚስኪን ናት ሞገስ የላትም።" ይላሉ ዓኢድ አል-ቀርኒ

©️ABX

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr

07 Nov, 19:06


ሰላት የማይሰግድን ሰው ለ ትዳርሽ አጋር
እንዲሆን አትፍቀጂ ጌታውን ችላ እንዳለ ሁሉ
አንቺንም ይተውሻል።


▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr ♡

25 Oct, 12:10


☞አስቾከይ_የእርደታ_ጥሪ


እባካችሁ  ደጋግ ኢትዮጵያዊያን አብዝታችሁ ሼር አድርጉላት ።

ትንሽ የሰጠ አብዝቶ ያገኛል
አባቱ ጥሎብኝ ሄዶ ህይወቴን መስእዋት አድርጌ ብቻዬን ያሳደኩት ልጄ ተስፋዬ ህልሜ ልጅነቴ ሁልነገሬ ነው ሊሞትብኝ ስለሆነ  እባካችሁ እርዱኝ ሰበብ ሁነቹ አድኑልኝ ትላለች እናቱ
ፈይሰል መሀመድ የ10 አመት ህፃን ሲሆን በከፍተኛ የልብ ህመም እየተሰቃየ ይገኛል ለህክምናው አጠቃላይ ወጪ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ተጠይቋል ። የቀን ስራ እየሰራች የሰው ቤት የቤት ሰራተኛነት እየሰራች ፈይሰልን ያሰደገችው ሰአዳ እንኳን ይህ ሁሉ ብር ሊኖራት የእለት ቁርሱን በየእለቱ እየለቀመች የምታሳድገው ሚስክ ድሃነች ። እባካችሁ ወገኖቼ እርዱኝ ትላለች ። በዚህ ደጋጋ ስራዎች ትንሽ ሰርተን ትልቅ በምናገኝበት በዚህ ከበድ ግዜ የለንን ትንሽም ቢሆን እናግዛት ።

CBE አካውንት  1000131395519 ሠአደ በለኬር

Halal Fkr ♡

24 Oct, 15:14


'I don't believe in magic
The young boy said
The old man smiled
'You will, when you see her.'

- Atticus

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr ♡

19 Oct, 14:16


🌍በአለም ደረጃ የፍቅር መግለጫ ምልክት የልብ ቅርፅ ነው— እዛ ሀገር ሞሮኮ ግን ልብ ሳይሆን ጉበት ነው ማለትም ሞሮኮዋዊያን ጥንዶች ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ☕️..

እሷ🫣:- ታውቃለህ የኔ ጌታ በጉበቴ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለህ ስትል ..

እሱ☝️:- የኔ ቆንጆ ካንች አንፃር ሲታይ የኔ ገደብ የለውም ። ማሬ ሙች ጉበቴን አሸንፈሽዋል ! አይነት የፍቅር ቃላትን ነው የሚለዋወጡት ።


▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr ♡

13 Oct, 17:38


"ሁሌም ፈገግታ አይለይህም። ይህ ነገርህ ደስ ይለኛል" ብላ የቀረበችኝ ልጅ "ሁሌም ቁም ነገር ሳወራህ ትስቃለህ" ብላ ተጣልታኛለች 😁  እኔና ፈገግታዬ ግን ይኸዉ አሁንም አለን😘

▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr ♡

11 Oct, 11:27


ትዳርሽ ዘለቄታ ኑሮት ጥሩ በል ካለሽ
በፍቅር የምትኖሪ ከሆነ የምትመኚው አይነት ወንድ ካገኘሽ
አላህን ሁሌም በስጁድ አመስግኚ
ዱኒያ ላይ ከሚያስደስቱት ነገሮች ዋናውን ሰቶሻልና❤️


▫️🎀🎀▫️

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | 💻 ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr ♡

09 Oct, 17:15


ሊጣላሽ የፈለገ ባል ሁለት እንቁላል ይሰጥሽና አንዱን ጥበሺ አንዱን ቀቅይዉ ይልሻል

ከዚያ አንቺ የዋኋ እንደተባልሽዉ አደርገሽ ስታመጪ
"ጥበሺ ያልኩሽን ቀቅለሽ ቀቅይ ያልኩሽን ጠብሰሻል" ብሎ ነገር ይጀምራል 😂😂

ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴋʀ | ▶️ ʏᴏᴜᴛᴜʙᴇ  |🎸 ᴛɪᴋᴛᴏᴋ

Halal Fkr ♡

06 Oct, 14:36


የሁሉም መልካም ነገር መጀመሪያ እንዳለሁ ሁሉ መጨረሻም አለው። የህይወት መልካም ፍሬዎች ለዘላለሙ አብረውን አይቆዩም ..

ስናጣቸው ፣ ስንፈልጋቸው ፣ ስንናፍቃቸው ፣ ስንመኛቸው ፣ ስናገኛቸው በሚኖረን የተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ሆነን ጊዜያችንን እንገፋለን።

በነበረበት የሚቆይ ምንም የለም። እምነት ይሸረሽራል ፣ ፍቅር ጥፍጥናውን ይቀንሳል ፣ ግንኙነት ይሻክራል ፣ ደስታ ይጠወልጋል ፣ ናፍቆት ወደ መረሳሳት ይደርሳል ... አብሮነትም በመለያየት ይቋጫል።

በመጨረሻም መልካም ትዝታ በመልካም ምኞት ተወስነን .. የህይወት አድማሳችንን በአእምሯችን ጓዳ ሸክፈን እንከንፋለን።

የህይወት ተለዋዋጭ ክስተቶችን መቋቋም ካልቻልን .. በሞቃቱ ጊዜ ብርድ ፣ በደስታ ጊዜ ሀዘን ፣ በጥፍጥና ወቅት መራራን ካባ ደርበን ጊዜያችን ያልፋል።

የመጣውን መቀበል እስካልቻልን ድረስ የመኖርን ጣዕም ልናውቀው አንችልም። የሚሻለው ግን ..."የሁሉም መልካም ነገር መጀመሪያ እንዳለው ሁሉ መጨረሻውን አምነን መቀበልና .. ለሚመጣው አዲስ ነገር መዘጋጀት ነው" ...

ያጣናቸው ሁሉ በጎ አይደሉም። ያገኘናቸው ነገሮች ደግሞ በመልካም አጋጣሚነት የሚሰፍሩ አይደሉም።

የህይወት ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ካላስተናገድናቸው በስተቀር .. በትዝታ የተሸበበ ፤ በፀፀት የተሞላ ፣ በእንባ የታጀበ .. አሰልቺ ህይወት ለመምራት እንገደዳለን።

.
.
.ለራስ የተፃፈ ደብዳቤ..ziz..01306

Halal Fkr ♡

05 Oct, 14:37


If someone is copying You,

YOU WON!🏆

_Robin Sharma

Halal Fkr ♡

04 Oct, 18:16


ስልኬን ማን ሰጠህ ብላ ስትቀዉጠው የነበርችው ልጅ
ዛሬ ቤቱ ምግብ እየሰራችለት ነዉ😂😂



JOIN US: ❯❯Halal fkr

Halal Fkr ♡

01 Oct, 19:25


90% አብረዋቹ የሚኖሩ ክርስትያኖች በሙስሊሙ ውድቀት celebrate ለማረግ አድፍጠው ነው የሚጠብቁት.. Ahh kafirs🤦‍♂️

ድል ለእስራኤል ምናምን they don't even know eko ምን እንደተፈጠረ ራሱ.. ፍልስጤሞች በሙስሊም ስም ስለተጠሩ ብቻ..
በዚ አገሠጣሚ ትክክለኛ ማንነታቸው ስለተጋለጠ ግን ደስ ብሎኛል😇

Halal Fkr ♡

01 Oct, 17:20


❤️‍🔥🔥

አሁን ማምሻውን ኢራን እስራኤል ላይ የባለስቲክ ሚሳኤል ጥቃቶችን አድርሳለች

Halal Fkr ♡

01 Oct, 12:42


የአላህ መልክተኛ ▫️ እንዲህ ብለዋል..

"አላህ መልካም ሚስት የቸረው ሰው በግማሹ ዲኑ ረድቶታል በቀሪው ግማሹ አላህን ይፍራ''❤️

አልባኒ ሰሒህ ብለውታል📚

JOIN US: ❯❯Halal fkr

Halal Fkr ♡

26 Sep, 20:19


መልካሙን አባታችሁን
የሚተካ ባል ይስጣችሁ

JOIN US: ❯❯Halal fkr

Halal Fkr ♡

25 Sep, 11:00


❤️‍🩹✌️


For more vids JOIN
@halalfkr || @halalfkr

Halal Fkr ♡

22 Sep, 05:48


አንዲት የገጠር ሴት
ባልሽን እንደዚህ ልታፈቅሪው የቻልሽበት ምክንያት ምንድን ነው ተብላ ስትጠየቅ:-

1► ሲወጣም ሲገባም በፈገግታ በመሆኑ
2► ቤት ያፈራውን ያለወቀሳ በመመገቡ
3► በጠፋ ነገር ባለመውቀሱ ብላ መለሰች።

በተመሳሳይ ሚስቱን በእጅጉ የሚያፈቅርን አንድ የገጠር ሰው ለምን እንዳፈቀራት ሲጠይቁት:-
1► በኢስላም ጥላ ስር በመጠበቋ
2► ቃላቶቿ ለስላሳና ማራኪ በመሆኗ
3► ስህተቶችን ስታገኝብኝ አይኖቿን ዝቅ በማድረጓ (ባለመከታተሏ)
4► ክብር የሚያጎድፉ ነገራቶችን ባለመፈፀሟ ነው ብሎ መልስ ሰጠ ይባላል።

©
JOIN US: ❯❯Halal fkr

Halal Fkr ♡

21 Sep, 05:47


...↓
ማጨት

ማግባት

ማፍቀር

ሶስተኛው ከመጀመሪያው ከቀደመ
ግንኙነቱ ሁሉ ይበላሻል . . . ..

JOIN US: ❯❯Halal fkr

Halal Fkr ♡

15 Sep, 08:25



18,364

subscribers

213

photos

163

videos