Esleman Abay የዓባይ ልጅ @eslemanabayy Channel on Telegram

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

@eslemanabayy


I Blog about global news analysis specially on the issue of Nile river Horn of Africa and the multipolar world affairs.

Esleman Abay የዓባይ ልጅ (Amharic)

እስላማን አባይ የፓርቲ ተመራጭ እና አስተያየት በሚከተለው ሚዲያ ሂደት በአፋር ሪቫል ፍንፍና በተለያዩ አስተዳደር እይታ ዘመን ምክንያት ጥቅም እንዲሆን እና በመታገል፣ የናይል ወንዝ ማንኛውንም ቋንቋ ባንድ በሆነ እና ቢሆን በህብረት ኢትዮጵያ ቅርብ እንዲሆኑ አስተዳደር እንችላለን። ነገር ግን በአዲስ አበባ ፕሮፌሰን እና በሚለው አፕ ሊኪሰት ፕሮፌሰን ተከታታይ የተያያዘ ሲሆነ አመልካቾችን ከሚሠራው ሰው ማንኛውንም ቋንቋ ላይ ስንጥᏍም፣ ማንኛው ጊዜ፣ ማንኛውንም ዜና፣ እና አጋር ፕሮፌሰት እንዲሆኑ እና ሌሎችን ምርጫዎች መረጃ እንሽላታለን።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

22 Jan, 15:57


Revealing Egypt's Black History and Its
Weaponized Control of the Nile!

This production uncovers Egypt's hidden African roots & reveal how modern Egypt has weaponized religion & power to control Ethiopia & its access to the Nile River.

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

22 Jan, 15:57


https://youtu.be/o_NBnM4o_oU?si=MCDAVopj-VGSvTy2

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

20 Jan, 16:32


#ሰበር #ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ በሀገራቸው አሜሪካ እውቅና የሚኖራቸው ፆታዎች ሁለት ብቻ(ወንድ እና ሴት) እንዲደረጉ የሚደነግግ ፕሬዝደንታዊ ትዕዛዝ በዛሬው ዕለት እንደሚፈራረሙ ተገለፀ።
ትራምፕ በተያያዘ ንግግራቸውም “ፆታቸውን የለወጡ አትሌቶች በሴቶች ስፖርት መሳተፍ አይፈቀድላቸውም” ሲሉ ተደምጠዋል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

19 Jan, 18:43


ትራምፕ ቲክቶክ አሜሪካ ውስጥ በጊዜያዊነት መስራት እንዲቀጥል ሊያደርጉ ነው

ትራምፕ በግልፅ እንደፃፉት አሜሪካ ቲክቶክ ላይ ድርሻ እንዲኖራት የጠየቁ ሲሆን በዚህም፣ "ያለ አሜሪካ ፍቃድ/ይሁንታ ቲክቶክ የለም፣ 50 በመቶ የቲክቶክ ድርሻን አሜሪካ መያዝ አለባት" ብለዋል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

13 Jan, 11:27


በአክሱም ሒጃብ የተከለከለበትን አስቂኝ ድርቅና እንዴት አየተመለከታችሁት ነው?
ስለ ክልከላው እየተሰጡ የሚገኙ ትንተናዎችንስ እንዴት እየተነተናችኋቸው ትገኛላችሁ?

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

07 Jan, 16:08


ኢትዮጵያዊት በሊቢያ

በሊቢያ፣ ኩፍራ የተባለ ቦታ በርካታ ስደተኞች ገንዘብ እስከሚከፍሉ በዚህ ሁኔታ ታፍነው ይገኛሉ።

🇪🇹 የ 20 አመቷ ነኢማ ጀማል፣ ከኢትዮጵያ ተጉዛ ሊቢያ የደረሰችው በግንቦት ወር 2024 እንደነበረ እና፣ ሊቢያ እንደደረሰችም ታፍና መወሰዷን ሪፊውጅስ -ኢን- ሊቢያ ዘግቧል።
ለያንዳንዱ ታጋች የተጠየቀው ገንዘብ 6 ሺህ የአሜሪካን ዶላር እንደሆነ ነው በመረጃው የተገለፀ ሲሆን ይህን የነኢማ ፎቶ ጨምሮ አጋቾች ሲያንገላቷት የምትታይበት ተንቀሳቃሽ ምስል ራሳቸው ቀርፀው በኢትዮጵያ ለሚገኙ ቤተሰቦቿ ልከውላቸዋል በማለትም በሪፓርቱ ተጠቁሟል።

#የዓባይልጅ
#ሊቢያ #Refuges_In_Libya #Naima #Jamal
#Naima_Jamal #NaimaJamal

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

07 Jan, 13:57


እህት ወንድሞቼ 🇪🇹 መልካም ገና ይሁንላችሁ

እንኳን አደረሳችሁ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

03 Jan, 09:10


አፋር - ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ የተከሰተው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

02 Jan, 15:07


ግብፅ ወታደሮቿን በአውሮፕላንና በመርከብ ወደ ሱማሊያ ለመላክ ዝግጅቷን ማጠናቀቋ ተዘገበ

ዘናሽናል ጋዜጣ እንዳስነበበው ካይሮ ወታደሮቹን የምትልከው በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሀይል ውስጥ ለማካተት ነው፡፡ ግብፅ ወታደሮቿን ወደ ሱማሊያ የምትልክው በሱማሊያ ጥያቄ መሰረት መሆኑን ያወሳው ዘገባው ቀደም ሲል በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ወደዚያው መላኳን ጠቅሷል፡፡

በዚህ ሳምንት በተከናወነው የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በሱማሊያ ውስጥ አዲስ ሰላም አስከባሪ ሀይል እንዲሰማራ የተወሰነ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ አስራ አንድ ሺ የግብፅ ወታደሮች እንደሚካተቱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ገልፆ ነበር፡፡
እነዚህ ወታደሮችም በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ በአውሮፕላንና በመርከብ ተጭነው ሞቃዲሾ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባው ጠቁሟል፡፡

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

02 Jan, 15:06


ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ለመሆን ደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

ደቡብ ሱዳን እና #ሶማሊያ የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ለመሆን ለኢትዮጵያ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ።

የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ለመሆን ጥያቄ ላቀረቡ ሀገራት ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ አስታውቀዋል።

በእስካሁኑ ሒደት ከጎረቤት ሀገራት ሱዳን፣ #ጅቡቲና #ኬንያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታውሰው በቅርቡ በኢትዮ-ኬንያ በተዘረጋው መስመር #ለታንዛንያ የሃይል አቅርቦት የሙከራ ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከምታመነጨው አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ሃይል 90 በመቶውን ለሀገር ውስጥ ፍጆታ በማዋል 10 በመቶውን ደግሞ ለተለያዩ ሀገራት እያቀረበች መሆኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይም የሃይል ልማትና ተደራሽነት ጥረቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው በደቡብ ሱዳንና ሶማሊያ በኩል ከኢትዮጵያ የኃይል ተጠቃሚነት ጥያቄ መቅረቡን አንስተዋል፤ ለቀረበው ጥያቄም ጥናት ተደርጎ እና የሃይል ማስተላለፊያ ጣቢያዎች ግንባታ ሲከናወን ምላሽ እንደሚሰጥ አሰታውቀዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሦስት ወራት ለጎረቤት ሀገራት ከቀረበ የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ 31 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ሲሉ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አሸብር ባልቻ መናገራቸውን ፋና ዘግቧል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

28 Dec, 15:15


ግብፅ እና ኢትዮጵያ እንደምን ኖሩ

🎙️ሸገር መቆያ🔺በእሸቴ አሰፋ
~ Sheger 102.1 FM 📻 ታሕሣሥ 19፣ 2017

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

25 Dec, 10:56


This December, in the other part of Africa, in Ghana, groundbreaking elections took place: a multipolarity proponent, John Manama gained power.

An interesting article analyzing the process:

https://newbusinessethiopia.com/nbe-blog/what-should-john-mahama-as-new-president-of-ghana-prioritize/

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

24 Dec, 10:43


“ከ ቀይ ባህር ጋር የማይዋሰን ሀገር ባህሩን መጠቀም አይችልም ‘ተቀባይነት የለውም’”
~ ግብፅ 🇪🇬

🔺ግብፅ ስለ ቀይ ባህር ያላትን አቋም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ይፋ ያደረገች ሲሆን፣ በዚህም ከ ቀይ ባህር ጋር የማይዋሰኑ ሀገራት ባህሩን መጠቀማቸው “ተቀባይነት የለውም” በማለት እወቁት ብለዋል🔺


🇪🇬 የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ "ከቀይ ባህር ጋር ከሚዋሰኑ ሀገሮች ውጭ ያሉ ማኛቸውም ሀገሮች በህሩን መጠቀማቸው ተቀባይነት የለውም" ሲሉ የተናገሩት ሰኞ ዕለት ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊኪ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት ነው።

ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው በቅርቡ በ ሶማሊያ እና የኢትዮጵያ መካከል በአንካራ አሸማጋይነት የተደረገውን ድርድርን የተመለከ አጀንዳን ጨምሮ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Dec, 06:49


ኢሳያስ እንደ ትራምፕ ሲቃጣቸው - በሪፖርተር ጋዜጣ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

15 Dec, 12:37


የአሜሪካ ኮንግረስ አባሉ ስኮት ፔሪ #ሶማሊላንድ የሉአላዊ ሀገርነት እውቅና ከዋሽንግተን ይሰጣት ዘንድ በአሜሪካው ኮንግረስ በይፋ አስተዋወቀዋል

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 18:32


አሳድ ሞስኮ ገብተዋል

የሶሪያው በሽር አል- አሳድ ሩሲያ ሞስኮ መግባታቸውን የሩሲያ ሚዲያዎች ዘገቡ

አር ቲ እና ታስ እንዳስነበቡት ባሽር አል አሳድ እና ቤተሰቦቻቸው ሩሲያ መግባታቸውን ከደቂቃዎች በፊት አረጋግጣለች፡፡


#ሶሪያ #አሳድ #Syria #Assad #Damascus #ደማስቆ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 18:23


"አሳድ ከስልጣን የወረዱት ከድርድር በኋላ.." - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር;

"አሳድ በሶሪያ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑ በርካታ ቡድኖች ጋር ከተነጋገረ በኋላ ስልጣኑን እና ሶሪያን ለቆ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ለማስተላለፍ ተስማምቶ መመሪያ ሰጥቷል። ይሁንና በድርድሩ ሩሲያ አልተሳተፈችም።" - ሰርጌይ ላቭሮቭ

#ሶሪያ #አሳድ #Syria #Assad #Damascus #ደማስቆ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 18:09


የእስራኤል ጦር በሶሪያው አልማዛ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ጥቃት ፈፅሟል

#ሶሪያ #አሳድ #Syria #Assad #Damascus #ደማስቆ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 18:08


የእስራኤል ጦር በሶሪያ ደቡባዊ አቅጣጫ ዘልቆ መግባት ጀመረ

በዚህ ዙሪያ በአንድ የእስራኤል ሚዲያ የቀረበው ትንታኔ ላይ "የደህንነት ቀጠናችን የሆነውና ቀደም ሲል 'ሶሪያ' ተብሎ ይጠራ የነበረው መሬት በምንም ምክንያት ወደ ሶሪያ መመለስ የለበትም። ግዛታችን ትንሽ ነውና በማንኛውም መንገድ ማስፋፋት አለብን" የሚል አቋም መቅረቡ ተዘግቧል።

#ሶሪያ #አሳድ #Syria #Assad #Damascus #ደማስቆ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 18:07


እስራኤል በሶሪያ አራተኛውን ጦርነት መጀመሯን ገለፀች

የሀገሪቱ ጦር ቺፍ ኦፍ ስታፍ መሪ የሆኑት ሔርዚ ሀሌቪ እንደተናገሩት እስራኤል

"እስራኤል በአራት ግምባሮች እየተዋጋ ሲሆን፤ እነሱም በዌስት ባንክ፣ በጋዛ፣ በሊባኖስ እንዲሁም ዛሬ ማምሻውን በሶሪያ በኩል የጀመርነው ዘመቻ ነው።"
" ይህ ዘመቻም በእናንተው እጅ ውስጥ ነው።"

#ሶሪያ #አሳድ #Syria #Assad #Damascus #ደማስቆ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 07:56


የአሳድ አይሮፕላን ተመቶ ይሆን?

አሳድን ጭኖ ይጓዝ ነበር የተባለው አውሮፕላን በረራ ላይ በድንገት ከበረራ ከፍታ የማሽቆልቆል እንዲሁም ከራዳር መጥፋት ተከትሎ ያልተረጋገጡ መረጃዎች በስፋት በመሰራጨት ላይ ናቸው።
አይሮፕላኑ ተመትቶ ስለመውደቁ፣ ብሎም ባሽር አል አሳድ በአደጋው ሳይሞቱ አይቀርም የሚሉት ናቸው ማረጋገጫቸውን የሚጠባበቁት መረጃዎች።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

08 Dec, 07:18


የሶሪያው ፕሬዝደንት በሺር አል አሳድ ሀገር ጥለው መውጣቸው ተሰማ

የቀድሞዎቹ የአይሲስ እና የአል ቃይዳ አሸባሪ አማጺያን የደማስቆ ቤተመንግስትን ተቆጣጥረዋል።

ታጣቂዎቹ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያን በመያዝ የሀገሪቱን ዋና ከተማ ደማስቆን እንደተቆጣጠሩ ያስታወቁ ሲሆን፣ "የባሻር አል-አሳድ መንግሥት ተገልብጧል...እስረኞች ከእስር ተፈተዋል" ብለዋል።

የእስራኤል ታንኮች በወረራ ከተያዙት የጎላን ኮረብታዎች ወደ ኩናትራ(የሶሪያ መሬት፣ በመግባት ላይ ናቸው። በአእስራኤል ድጋፍ የሶሪያን ቤተ መንግስት የተቆጣጠሩት አዲሶቹ ሀይሎች “መሬታቸውን ከእስራኤል ተዋግተው ያስመልሳሉን?” የሁሉም ጥያቄ ነው።

ሶሪያን አሁን የተቆጣጠሩት የአይሲስ - አልቃይዳ ሃይሎች ሀገሪቷን አረጋግተው የመምራታቸው ጉዳይ ስጋት ደቅኗል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

07 Dec, 17:51


⚡️እዚህ እኔጋ መብራት መጥቷል

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

07 Dec, 16:13


https://youtu.be/pvzQBJ9YTXg?si=ZdXLf8Qhv9GngAxq

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

07 Dec, 05:20


ነዋሪነታቸውን በጣሊያን ያደረጉ ኢትዮጵያዊ በ 65 ሺህ ዩሮ የዓባይ ግድብ ቦንድ ግዥ ፈጸሙ


ነዋሪነታቸውን በጣሊያን አገር ያደረጉ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዥ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ዳያስፖራ ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተገኝተው ለግድቡ ግንባታ ማስጨረሻ የሚሆን የ65 ሺህ ዩሮ የቦንድ ግዢ ፈጽመዋል። ግለሰቡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የልማት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአንድነት ተምሳሌት እና የሉዓላዊነት ምልክት በመሆኑ ቦንድ መግዛት እንደ አንድ ዜጋ የሚጠበቅ አኩሪ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

የቦንድ ግዢውን በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ተገኝተው በአካል በመፈጸም የአገር ባለ ውለታ ለሆኑት ግለሰብ ኤምባሲው ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፣ በሮም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አስተባባሪነት ያሁኑን ጨምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስጨረሻ ከዳያስፖራ በቦንድ ሽያጭና በስጦታ ከ80 ሺህ ዩሮ በላይ ተሰባስቦ ገቢ መደረጉን ከኤምባሲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፡-Ethiopian Embassy in Rome

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

05 Dec, 18:10


ሱዳን ወይም ሊቢያ ለምትገኙ: አፋልጉን

ይታገሱ ዘነበ መቻል፣ ዕድሜ 23

ቤተሰብ ሳያሳውቅ ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም ከቤት ወጥቶ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም ደውሎ ወደ ሊቢያ መንገድ እንደ ጀመረ እና በ10 ቀን ውስጥ ሊቢያ እንደሚገባ ነበር የነገረን ነገርግን መስከረም 5/2017 ዓ.ም ከሰፈር አብሮት ጉዞ የጀመረ ጓደኛው ደውሎልን እሱ ሊቢያ እንደገባ ከይታገሱ ጋር ነሀሴ 30/2016 ዓ.ም ሱዳን ውስጥ እንደተለያዩ ነገረን እስካሁን ድምፁን አልሰማንም ሱዳን ያላችሁ ወንድማችንን እንድታፋልጉን ስንል በትህትና እንጠይቃለን



ኤርሚያስ ዘነበ : +251912737598

ምህረት ዘነበ : +251925245852

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

04 Dec, 17:38


የኢትዮጵያ እድገት በ10 አመት ውስጥ አስደናቂ ፍጥነት እስመዝግቧል” - ፕሬዝደንት ፑቲን

🇷🇺 “ሩሲያ እድገት ባለባቸውና "ለጩኸቶች" ምላሽ የማይሰጡ በማደግ ላይ የሚገኙ አጋር ሀገራት ገበያዎች ላይ አተኩራለች” ሲሉ የሩሲያው ፕሬዝደንት ገልፀዋል።

ኢትዮጵያን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ አንዳንድ ኢኮኖሚዎች ባልተለመደ ፍጥነት እያደጉ መሆናቸውን ተናግረዋል። እንደ ፑቲን ገለፃ ባለፉት 10 አመታት 120 በመቶ እድገት ተመዝግቧል። ፑቲን ይህንንም እጅግ አስደናቂ ቁጥር ነው ብለውታል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

04 Dec, 12:16


https://youtu.be/_lbQRy7f8xs?si=PHbl7sbMhXPew6_l

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

02 Dec, 15:03


በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግደያ ወንጀል የፈጸመ ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት

በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማ መካከለኛ ፍርድ ቤት በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች ላይ የፍርድ ዉሳኔ ሰጥቷል።

የ16 አመት ታዳጊዋ ማህሌት ተክላይ መጋቢት 10 ቀን2016 ዓ.ም ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች በነበረችበት ወቅት ታግታ በመውሰድ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ተገድላ መገኘቷ ይታወሳል።

አንደኛ ተከሳሽ አንገቷን አንቆ በመያዝ ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ በባጃጅ አግቶ በመውሰድ ለ30 ደቂቃ ያክል በጫማ ማሰሪያ ገመድ አሰቃይተው አንደገደሏት የመቀለ ከተማ አቃቤ ህግ ገልጿል።

ዓቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ፈርድ ቤቱ ተከሳሾች የፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት መሆኑን በማረጋገጥ የፍርድ ዉሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም ታዳጊዋ ላይ የግደያ ወንጀል የፈጸምዉ አንደኛ ተከሳሽ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሲሆን ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት አንዲቀጣ ዉሳኔ ተሰጥቷል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

01 Dec, 14:52


🇺🇸

" የBRICS ሀበራት ዶላርን ለመጣል ሲሞክሩ እጃችንን አጣጥፈን የምንመለከትበት ሁኔታ አይኖርም። አገራቱ አዲስ BRICS መገበያያ ገንዘብ አለመፍጠራቸውን፣ አሊያም ኃያሉን የአሜሪካ ዶላር ለመተካት የታለመለት ሌላ የመገበያያ ገንዘብን ከመደገፍ መታቀባቸውን ካላረጋገጡልን በስተቀር ምርቶቻቸውን በአሜሪካ ኢኮኖሚ ውስጥ ለመሸጥ የ 100 ፐረሰንት ታሪፍ እንደሚጠብቃቸው፣ ከአሜሪካ ገበያም እንደሚሰናበቱ ለማሳወቅ እንፈልጋለን። የ BRICS አገራት የአሜሪካን ዶላር በሌላ መገበያያ የሚተኩበት ምንም እድል የለም፣ የሚሞክሩ ከሆነ አሜሪካን ለመሰናበት ይዘጋጁ።"
▶️ ዶናልድ ትራምፕ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

01 Dec, 12:04


ፕሬዝዳንት ኢሳያስ:

🔺ስለ ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት መሻከር


ለኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኘነት መሻከር የውጭ ሃይሎች ጣልቃ ገብነት አንዱ ምክንያት እንደሆነ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከአገራቸው መገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የድንበር ጦርነት ውስጥ የገቡትም ሆነ በባድሜ ለሁለት አስርት ዓመታት ሰፍኖ የቆየው ውጥረት "ለሁለቱ ሀገራት የድንበር ውዝግብና ጦርነት እንዲሁም አሁን ላለው የግንኙነት መቀዛቀዝ የውጭ ሃይሎች ጣልቃገብነት ዋነኛው አንደሆነ አብራርተዋል።

አስመራ እና አዲስ አበባ ጦርነቱን በስምምነት ፣ከቋጩ በኋላም ሆነ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ የቀጠለው ግጭትና ጦርነት መነሻንም ከህገመንግስቱ ጋር አያይዘውታል።

"ህወሃት የሪፎርም አጀንዳዎችን ወደጎን በመተውና ጦርነት በመምረጥ ወደ ኤርትራ ከ70 በላይ ረጅም ርቀት ሮኬቶችን ተኩሷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ ህወሃት ይህን ድርጊት እንዲያቆም ያቀረብነው ጥያቄ ሰሚ አላገኘም ነበር" ሲሉ ያወሳሉ።


ህዳር 22 ቀን 2017

#ፕሬዝዳንት_ኢሳያስ #ኢሳያስ
#ኢሳያስ_አፈወርቂ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

01 Dec, 11:31


ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ምን ተናገሩ ?

🔺ስለ ፕሪቶሪያው ስምምነት

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ትናንት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ደም አፋሳሹ የሰሜኑን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማስቆም የተደረሰው የፕሪቶሪያዉ ስምምነት አገራቸውን እንደማይመለከት የተናገሩት።
ፕሬዚዳንቱ ኤርትራ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ከሚሰሩ አገራት ጋር ትሰራለች መባሉን አስተባብለዋል።

#ፕሬዝዳንት_ኢሳያስ #ኢሳያስ
#ኢሳያስ_አፈወርቂ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

30 Nov, 13:09


Section II of the Zoom workshop hosted by #GERD International Collaborative Consortium (#GICC) and titled '#CFA in Action: Prospects of the #NileRiver Basin Commission (#NRBC)' will be streamed today, November 30, 2024.

👉🏾 Time:

• 9:00-11:30 a.m. Eastern Time, #NewYork

• 5:00-7:30 p.m. Eastern #Africa Time

ID: 87975542034

Passcode: 708652

https://new.express.adobe.com/webpage/pndhZrNKCyDtW

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

28 Nov, 18:04


የጁባላንድ አስተዳደር ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ ሲል ገለጸ

የሶማሊያ ፌደራል መንግስቱ አካል የሆነው ጁባላንድ አስተዳደር ከሀገሪቱ ፌደራል መንግስት ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ ሲል አስታወቀ።

ውጥረቱ እየባባሰ በመጣበት በአሁኑ ወቅት የጁባላንድ መንግስት “የፌደራል መንግስቱ የሀገሪቱን ህገመንግስት በጣሰ መልኩ ተንቀሳቅሷል፣ የሶማሊያን ብሔራዊ አንድነት እያናጋ ነው ሲል በምክንያትነት በመግለጸ ግነኙነቴን አቋርጫለሁ ብሏል።

የጁባላንድ አስተዳደር ዛሬ ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ፕሬዝዳንት የሆኑትን ሀሰን ሸክ ሞሃሙድን ተችቷል፤ ፕሬዝዳንቱ “ህገመንግስቱን ደፍጥጠዋል፣ ስልጣናቸውን ያላግባበ እየተጠቀሙ ነው፣ ክፍፍል እየፈጠሩ ነው፣ ሙስናን አንሰራፍተዋል” ሲል ኮንኗል።

ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል በሀገሪቱ የተረጋጋ ሰላም በነበረባቸው እንደ የጁባላንድ አስተዳደር ባሉ ክልሎች የጸጥታ ችግርን ጨምሮ “የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር፣ በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት እምዲሰፍን” በንቃት እየሰሩ ነው ሲል በመግለጫው ኮንኗል።

ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት በተመለከተ ያለውን አቋም በመግለጫው አብራርቷል፤ አጽንኦት ከሰጠባቸው ነጥቦች መካከልም ሕገ መንግሥታዊ መርሆችን "የማይነኩ እና ለድርድር የማይቀርቡ ናቸው“ ሲል የገለጸበት ይገኛል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

23 Nov, 15:58


The Zoom workshop hosted by the #GERD International Collaborative Consortium (#GICC) under the title
'Cooperative Framework Agreement (#CFA) in Action: Prospects of the #NileRiver Basin Commission (#NRBC) for Collaborative Development in the Region' is streaming now ...

ID: 87975542034

Passcode: 708652

https://new.express.adobe.com/webpage/pndhZrNKCyDtW?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR3O6W5odOu_j1ydu7f3XhxGrkQxwEAbovN_w_GPkRkk1cVs-iGHCT_NC70_aem_7VqS2jZgLVA_cfJ2jGRDMQ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

21 Nov, 18:38


የቡቺ ሃዘን 💔

በመንገዴ ላይ የገጠመኝ ነው...፤ ውሻው የሞተችበት የአጋሩን በድን ትቶ ሊሄድ አልተቻለውም፤ ከአጠገቧ ይተኛል፤ እንደመቀስቀስ እንደማናገር .. ይሞካክራል፤ ይተክዛል፤
የምግብ ፍላጎቱም የጠፋበት ነው የሚመስለው፤ ልጆች እንደነገሩኝ የሞተችው ውሻ ሚስቱ ነበረች፤ እየደጋገመ ወገቧ አካባቢ በመላስ ዝምታዋን ሰብራ እንደቀድሞው ይሆኑ ዘንድ ያደረገው ተደጋጋሚ ጥረት ከሰአታት መንገድ በኋላ ከሚፈጠረው መበስበስ ጋር የጀርባዋ ፀጉር እንዲገፈፍ አድርጎታል። ቡቺ ግን ከጎኗ መራቅ አልፈለገም፤ እየተመላለሱ የሚረብሹት ዝንቦች ቦታውን አላስለቀቁትም። አሳዛኝ አኳኋኑን ወደዃላዬ እየተመለከትኩኝ ጉዞየን ስቀጥል - ቡቺ ከሟች አጋሩ አስከሬን አጠገብ እንደነበረ ...

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

21 Nov, 13:46


ነገ ቅዳሜ - የነፍስያ ድምፆች ምረቃ


“የነፍስያ ድምፆች” መፅሐፍ ምረቃ በአንጋፋ እና ወጣት የጥበብ፣ የመድረክ እንዲሁም በዬሙያቸው አንቱ በተሰኙ ጎምቱዎች ሊፈካ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል።

የመፅሐፉ ደራሲ የሆነው ጋዜጠኛ Yenus Muhammed “ሁላችሁም የዕለቱ ድምቀት፣ ሁላችሁም የዕለቱ ታዳሚና ሁላችሁም የዕለቱ ቤተሰብ ሁኑ” በማለት በአክብሮት ይጋብዛል።

ልዩ ልዩ ሚዲያዎቻችንና ጋዜጠኞችም በዕለቱ እንድትገኙ ጥሪው ይድረሳችሁ።


ቀን: ቅዳሜ፣ ኀዳር 14፣ በዋልያ መጻሕፍት
አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ
ኢክላስ ሕንፃ 4ኛ ፎቅ
🚨ከቀኑ 9፡30

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

20 Nov, 06:39


Why they hate this, western officials, western paid Ethiopian Journos/propagandists and even our government 🇪🇹 also criticized this state of art project called the Belt and Road initiative
ወዳጄ የምዕራባዊያን ፈንድ ያንተን ግለሰባዊ ከርስ እና ኪስ ይሞሉልህ ይሆናል እንጂ ለሰፊው ህዝብ የሚጠቅመውን ይህን መሰል መሰረተ ልማት ግን ዋሽንግተን መራሹ collective west ሊገነቡልህ ቀርቶ ጠብታውንም አያለክፉንም - ጥይት እንጅ ልማት አይታሰብም ከምዕራባዊያን መዳፍ !!

የተደናበረ ዘመን —- ‘ተው አንጋው’ አሉ ሙሐመድ አወል ሐምዛ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

14 Nov, 16:23


የቻይናው J-20 የጦር ጄት አስደናቂ ትርዒት

ጄ-20 ተዋጊ ጄት በቻይና ዡሃይ ኤር ሾው ላይ የበርካቶችን ቀልብ የሳበ የአየር ላይ ትርዒት አሳይቷል።

የጦር ጄቱ አየር ላይ ሲገለባበጥ የተለያየ ትርዒት ያሳየ ሲሆን፤ በተጨማሪም በቡድን በመሆን የተለያዩ የአየር ላይ ትርዒቶችን አሳይተዋል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

12 Nov, 15:17


    ልቀት የኪነጥበብ እና ቢዝነስ ኮሌጅ የተመሰረተበትን ሰባተኛ  ዓመት ምክንያት በማድረግ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እስከ ህዳር 10/2017 ዓ.ም ቀድመው ለሚመዘገቡ 200 ተማሪዎች የአንድ ሴሚስተር  ከወርሃዊ ክፍያ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።
 
ኮሌጁ ህዳር 2 2010 ዓ.ም በአራት ወጣት ባለሞያዎች ተመስርቶ እነሆ አሁን በከተማችን አ.አ ብሎም በሀገሪቱ ትምህርትን በከፍተኛ ጥራት እና ልዩነት እያስተማረ ዛሬ ላለበት ደረጃ ሊደርስ ችሏል።
በተለይም ኮሌጁ በልዩነት በሚታወቅበት የፊልም ትምህርት በከተማችን አዲስ አበባ የፊልም ትምህርትን በብቸኝነት በዲፕሎማ ሲያስተምር ቆይቶ አሁን ደግሞ በሀገራችን ኢትዮጵያ በግል ኮሌጆች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የፊልም ጥበብ ትምህርትን በመጀመሪያ ዲግሪ በመስጠት ልዩነቱን ከፍ እያደረገ እና ብዙዎችን ከህልማቸው ጋር እያገናኘ ይገኛል።
ልቀት በየዓመቱ ከሚያከናውናቸው በርካታ ክንዋኔዎች አንዱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በከፍተኛ ቅናሽ በማስተማር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ የቆየ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም ኮሌጁ የተመሰረተበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ  የመጀመሪያውን ሴሚስተር ወርሃዊ ክፍያ በነጻ  የትምህርት እድል እንደሚሰጥ አሳውቋል።
ነፃ የትምህርት እድል የተሰጠባቸውም የትምህርት መስኮች:-
ቪዲዮ ካሜራ እና ኤዲቲንግ (Cinematography and Editing)፤
አካውንቲንግ (Accounting and Finance)፤ ማርኬቲንግ (Marketing and sales mangment )፤
የሰው ኃብት አስተዳደር ( Human Resources mangment )፤
የቴአትር ጥበባት ሲሆኑ ምዝገባ ከህዳር 2/2017 እስከ ህዳር 10/2017 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን የተቋሙ ዲን አቶ መሉጌታ ሙሃመድ ገልፀዋል።
አቶ ሙሉጌታ አክለውም ተመዝጋቢዎች የትምህርት ማስረጃቸውን ዋናውን እና ኮፒ ፣ በተጨማሪም ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው በአካል ቀርበው መመዝገብ እንደሚችሉ ገልፀዋል።
ይሄንን ዕድል መጠቀም የሚፈልግ ሁሉ  አራት ኪሎ ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ ኢክላስ ህንፃ ላይ በሚገኘው የኮሌጁ ቢሮ በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ በ09 84 71 71 44/09 40 08 99 99 ይደውሉ ተብሏል።
ልቀት ኮሌጅ
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

12 Nov, 15:17


▪️ነፃ የትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው ▪️

ልቀት ኮሌጅ የምስረታ በዓሉን በማስመልከት ነፃ የትምህርት እድል ሰጠ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

10 Nov, 20:13


የማትረሳኝ በፍፁም የማልዘነጋት እንስት መሪር ሀዘን - ከማይካድራ

#ማይካድራ
#Maikadra

ጥቅምት 30 - 2013 ዓ.ም
🖤 1564 በጭካኔ ተገድለዋል፤

🖤 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤

#ማይካድራ
#MaiKadraMassacre

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

06 Nov, 18:52


​ዶናልድ ትራምፕ ዳግም በፕሬዝዳንትነት መመረጣቸውን ተከትሎ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ደጋፊዎች እና ስደተኞች ሀዘን መቀመጣቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ስደት ጠሉ ትራምፕ 11 ሚሊየን ሰዎችን ከአሜሪካ ጠራርገው ለማስወጣት ማቀዳቸውም ታውቋል፡፡ ቀጣዩን የዩትዩብ ሊንክ ስትከፍቱም ከትራምፕ ዳግም መመረጥ ጋር በተያያዘ ቀጣይዋ አሜሪካ እና ዓለም ምን ሊመስሉ ይችላሉ የሚለውን በተመለከተ ወሳኝ ትንታኔያዊ መረጃን የምታደምጡ ይሆናል፡፡ እግረ መንገዳችሁን ቪዲዮውን ላይክ፣ ቻናሉን ሰብስክራይብ እንድታደርጉም በማክበር ተጋብዛችኋል።
https://youtu.be/UujBqlfNg24?si=tMv8HCRQCxN99g1p

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

05 Nov, 12:47


የኢትዮጵያ አየር መንገድ🇪🇹 በአፍሪካ የመጀመሪያውን ኤርባስ A350-1000 ፈረንሳይ ቱሉዝ፣ ከኤርባስ ኩባንያ ተረከበ


አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው A350-1000 እጅግ ዘመናዊ የመንገደኞች አውሮፕላን ቅንጡ እና ምቾት ባላቸው የቢዝነስ እና የኢኮኖሚ ክፍል መቀመጫዎች፣ በማራኪ 4K ስክሪኖች እና ከፍተኛ ፍጥነት ባለው ዋይ ፋይ አገልግሎት እንዲሁም ዘመኑ ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎችን በላቀ ደረጃ ያሟላ በመሆን ይታወቃል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ #A350

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

04 Nov, 20:22


💪Black Panthers 🐆🟩🟨🟥

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

01 Nov, 21:07


የግብፅን የናይል ተፋሰስ አሁናዊ ፍላጎት የተመለከተ ጥያቄ ያጫረ ነው የተባለለት፣ የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር በድር አብደል አቲ 'የ 100 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ገፀ በረከት አነሆ' በማለት ከኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ከሰሞኑ ተገናኝተዋል። ነገረ ጉዳዩን ለመሸፋፈን ካይሮ የተጠቀመችበት ጭምብል "በናይል ተፋሰስ ሀገራት ውስጥ የመሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ" ነው ሲሉ ለማሳመን መሞከራቸውንም መታዘብ ችለናል።
ይሁንና ይህ የካይሮ ሸለምጥማጣዊ እርምጃ ዋነኛ ዓላማ በቅርቡ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መካከል ጥምረት በመፍጠር ፍትሃዊ የናይል ውሃ ተጠቃሚነት ጥያቄያቸውን ቅቡላዊ ለማድረግ በጋራ ተፈራርመው ግብፅ ለዘመናት በብቸኝነት ስትጠቀምበት የኖረችውን አካሄድ ለማምከን በተጀመረው የኮሚሽን ምስረታ ላይ የተነጣጠረ እንቅስቃሴ መሆኑ ሊደበቅ እንዳልቻለ መገንዘብ ተችሏል።

የካይሮ አይታክቴ የሴራ ፕሮጀክት፣ ስሙ "ለመሠረተ ልማት ፕሮጄክቶች ድጋፍ" ተብሎ ይሰየም እንጂ እውነተኛ ዓላማው በናይል ተፋሰስ አገሮች መካከል ክፍፍልን ለመዝራት የተጠነሰሰ ስትራቴጂክ ሴራ መሆኑ ነው በርካቶች ድምዳሜ የሚሰጡበት። የጉዳዩ ታዛቢዎች እንደሚገልፁትም ይህ የካይሮ የገንዘብ ድጋፍ እውነተኛ ትብብርን ከማስፋት ይልቅ አዲስ የተመሰረተውን የናይል ቤዚን ኮሚሽን ለማዳከም የተነደፈ ተንኮለኛ ዘዴ መሆኑንና በውጤቱም በተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብት መብታቸው ላይ በጋራ የመደራደር አቅማቸውን የሚያኮስመን ነው ብለውታል። ካይሮ ዘንድሮስ ይሳካላት ይሆን?
በበኩሌ፣ ፕሬዝደንት ሙሴቬኒ በአል ሲሲ ተንኮል የሚሸወዱ ጩጬ አፍሪካዊ መሪ ይሆናሉ ብዬ አልግምትም። #የዓባይልጅ Esleman Abay

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

01 Nov, 21:07


የካይሮ ባለ 100 ሚሊዮን ዶላር ካሮት - የናይል ተፋሰስ ሀገራትን የመከፋፈል ሴራ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

30 Oct, 18:52


ለካ አንተ ነህ ሐብቴ ~ ዓባይ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

30 Oct, 16:28


“እስራኤል ከወደቀች ሌሎችም አገሮች ከእኛ ጋር ይወድቃሉ..!”፣ በሚል ጠንካራ ንግግር ኔታንያሁ የእስራኤል መኖር ለአለም መረጋጋትና ለአለም ህላዌ ያላትን ሚና ሲገልፁ ተደምጠዋል። 🌍🇮🇱

እናንተስ ምን ትላላችሁ?👆🏾
Your thoughts on this

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

30 Oct, 15:36


https://youtu.be/Shaitrx7yrI?si=P8L2rInP-XLJ4FsR

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

30 Oct, 13:16


Hello Everyone

This is a new video, don't forget to subscribe, like and share @rednile12 YouTube channel

📍በዚህ ቪዲዮ፦ አጸፋ መመለስ ወይስ ትንኮሳ

እስራኤል በኢራን ላይ የአፀፋ ጥቃት መፈጸሟ | የምእራብ አለም የግነት ዘገባ |

https://youtu.be/3-HJkpkb5zM?si=CgcIPDVOrcrircsv

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

28 Oct, 20:28


ቢደላኝም ቢከፋኝ 🇪🇹ሁሉ ነገሬ 🤙🏽

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

28 Oct, 20:09


Thank you brother 🙏🏽

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

28 Oct, 19:34


ለግብፅ የቡዳ መዳኒት መሆኗን ይሁን እላለሁ
💀እዝራኢል 🇮🇱

ترحيب بإسرائيل الصهيونية لأنها لقاح للحكومة المصرية الخادعة

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

28 Oct, 16:26


https://youtu.be/0rV9GNcpHpQ?si=gxRsYn8eyjUN4L8O

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

26 Oct, 23:47


https://youtu.be/WXS6skfR1FQ?si=2qzjH-NvvK0H10az

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

26 Oct, 23:21


🥲

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

26 Oct, 06:50


የእስራኤል ጦር ለኢራን ጥቃት ምላሽ ይሆን ዘንድ በአንድ ሌሊት ያካሄደውን የሚሳይል ድብደባ ማጠናቀቁን ተናግሯል - የእስራኤል ጦር አለ ነው ያልኩት፣ ስሙንም “የንስሐ ቀናት” ስትል ነው የጠራችው።
ታዲያ በዚህ የእስራኤሉ ዘመቻ “የንስሐ ቀናት” ላይ ኢራን ሰራሹ ፀረ ሚሳይል - ባካር 373 እስራኤል ወደ ቴህራን የተኮሰቻቸውን ሚሳይሎች በማምከኑ ረገድ ስኬታማነቱ በግልፅ ነው የታየው ...

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

26 Oct, 05:52


አይይ~ አለምነህ ዋሴ የበረሃው መናኝ፣
በዩክሬን ፀዳቂ፣ በእስራኤል ተኮናኝ።
.
.

እንደ ሌላው ተሳዳቢ ባንሆንም በጥልቀት ሁሉንም እንታዘባለን! ሰፊ የመረዳት አቅም ያላቸው ጎምቱዎች ሳይቀር ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ አይላቸውም በሚሏቸው ነጥቦች ላይ ባዳበሯቸው ቴክኒኮቻቸው ተጠቅመው በወሳኝ ሀቆች ውስጥ ግላዊ ስሜታቸውን ሲቀያይጡ አንጥረን እንመለከታለን። ረቂቅ ልቦናቸውንም እንበረብራለን!

So, ምን ማድረግ ይሻላል?
🚨counter balance is needed....🤙

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

24 Oct, 18:15


በዚህም 13 አዳዲስ ሀገራት ይፋዊ አጋር ሀገራት እንዲሆኑ ተቀባይነት አግኝተዋል፣ በሂደት የ BRICS ሙሉ አባል ለመሆን የሚሰሩ ይሆናል።


የብሪክስ ሙሉ አባላት

🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩሲያ
🇮🇳 ህንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇦🇪 UAE
🇮🇷 ኢራን
🇪🇬 ግብፅ


ኦፊሴላዊ የ BRICS አጋር አገሮች

🇩🇿 አልጄሪያ
🇧🇾 ቤላሩስ
🇧🇴 ቦሊቪያ
🇨🇺 ኩባ
🇮🇩 ኢንዶኔዥያ
🇰🇿 ካዛኪስታን
🇲🇾 ማሌዢያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇹🇭 ታይላንድ
🇹🇷 ቱርክ
🇺🇬 ኡጋንዳ
🇺🇿 ኡዝቤኪስታን
🇻🇳 ቬትናም

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

24 Oct, 18:14


BRICS በ 2024 ማናቸውንም አዲስ ሀገር ለህብረቱ ሙሉ አባል አድርጎ ላለመቀበል ወሰነ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

22 Oct, 15:45


“ፍፁም ህሊና ቢስ የሆኑ አጥፊዎች በዘረፋ ላይ ተሰማርተው ማየት ያሳዝናል”


በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተው የእሳት አደጋ እና ያስከተለው ውድመት እጅግ ልብ የሚሰብር ነው:

እሳት አደጋውን ለመቆጣጠር መንግስት እና ህዝብ እያደረጉት ያለውን ርብርብ ማገዝ ሲገባ ፍፁም ህሊና ቢስ የሆኑ አጥፊዎች በዘረፋ ላይ ተሰማርተው ማየት ያሳዝናል::

በዚህ የእሳት አደጋ ንብረታችሁን ላጣችሁ ወገኖቼ ይህ የዱኒያ ፈተና መሆኑን በማወቅ ነገ አላህ በተሻለ እንደሚተካችሁ በማሰብ እንድትሰብሩ አደራ ልላችሁ እወዳለሁ ።

ሁላችንም ከተጎጂዎቹ ጎን መቆም ግዳታችንም ሊሆን ይገባል!

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

21 Oct, 19:47


🔥መርካቶ ሸማ ተራ🔥 እሳት አደጋ ተከስቷል

እስካሁን ድረስም እየነደደ ነው የሚገኘው

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

21 Oct, 16:16


🇷🇺🌍 በሩሲያ ካዛን በሚካሄደው የብሪክስ 2024 ጉባኤ የሚጠበቁ ጉዳዮች

16ኛው የብሪክስ ጉባኤ ከጥቅምት 12-14 በሩሲያ ካዛን የሚካሄድ ሲሆን ህብረቱ ከተስፋፋ ወዲህ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
ዋና ዋና ጉዳዮችም፡

▪️ መስፋፋት፦ ጉባኤው ለግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የኤኢ የመጀመሪያ ነው።

▪️ ተሳታፊዎች፦ 24 የሀገር መሪዎችን ጨምሮ ከ32 በላይ ሀገራት ጉባኤው ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። ሁሉም የብሪክስ አባላት የሚሳተፉ ሲሆን 9 ሀገራት መሪዎቻቸውን ሲልኩ ሳዑዲ አረቢያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ትወከላለች።

▪️ አጀንዳ፦ ጉባኤው በሁለት አጀንዳዎች ተከፋፍሎ ይካሄዳል። የመጀመሪያው (ከጥቅምት12-213) “የባለብዙ ወገን ግኑኝነትን ፍትሃዊ የዓለም ልማትና ደህንነትን ለማጠናከር” በሚል መሪ ሃሳብ ላይ ያተኩራል። ሁለተኛው (ከጥቅምት 13-14) "የብሪክስ እና ደቡባዊ ዓለም ሀገራት: የተሻለ ዓለም ግንባታ" በሚል ሃሳብ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡

▪️ ተጨማሪ አዲስ አባላት፦ ጉባኤው አዳዲስ አባላት ሊሆኑ የሚችሉ ሃገራት ጉዳይ ላይ ይወያያል። 34 ሀገራት የብሪክስ አባል ወይም አጋር ሀገር ለመሆን ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

▪️ የሁለትዮሽ ስብሰባዎች፦ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከቻይናው አቻቸው ሺ ጂንፒንግ፣ የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬቼፕ ጣይብ ኤርዶጋንን ጨምሮ ከ20 በላይ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ያደርጋሉ፡፡

▪️ የመጨረሻ ውጤት፦ በጉባኤው ማጠቃለያ ተሳታፊ ሀገራት የጋራ መግለጫ እንደሚያወጡ ይጠበቃል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

21 Oct, 13:08


Before the #GERD Dam, Egypt received 55.5 BCM of water annually from the Nile under colonial agreements (1959). Now, Ethiopia releases >49 BCM annually through GERD, along with an additional 7.3 BCM per month (2,800 CM³/S) during the flood season via the spillways. Even if we consider just one month of the extra release, it (>56.3 BCM) would exceed Egypt’s pre-GERD water share.

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

20 Oct, 13:06


የእስራኤልን የማጥቃት እቅድ የሚያሳይ ሚስጥራዊ ሰነድ ከአሜሪካ ደህንነት ሾልኮ መውጣቱ ተዘገበ።

እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመውን የበቀል ጥቃት እቅድ ያሳያል የተባለ ጥብቅ ሚስጥራዊ ሰነድ ከአሜሪካ ደህንነት ሾልኮ ወጥቷል ተብሏል።

አሜሪካ፣ እስራኤል ልትፈጽመው የምትችለውን የማጥቃት እቅድ የሚዳስሰው ሚስጥራዊ ሰነድ እንዴት እንደወጣ ምርመራ እያካሄደች መሆኑን ኤፒ ሶስት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

ጥብቅ ሚስጥራዊ መረጃ የሚል የተጻፈባቸው ሰነዶች በቴሌግራም የተጋሩ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘገበው በአሜሪካው የሲኤንኤን ቴሌቪዥን ነው።

ሰነዶቹ ሆነ ተብሎ በአሜሪካ የስለላ ሰራተኞች ወይም በጠለፋ ስለመውጣታቸው እና ሌሎች የሾለኩ ሚስጥሮች ስለመኖራቸው ምርመራ እየተካሄ መሆኑን ኤፒ ያናገራቸው እና ስማቸውን ያልገለጻቸው ባለስልጣን ተናግረዋል።

እኝህ ባለስልጣን ፖስት ከማድረግ በፊት ሰነዶቹን ማግኘት የሚችለው ማነው የሚለውን ለመወሰን ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

ሰነዶቹ የወጡት አሜሪካ፣ እስራኤል የሀማስ መሪ ያህያ ሲንዋርን መወገድ ጫና ለመፍጠር እንድትጠቀምበት እና በሰሜን ሊባኖስ ያለውን ጦርነት እንዳታስፋፋ እና ቀጣናዊ ጦርነት እንዳይቀሳቀስ ጥንቃቄ እንድታደርግ እያሳሰበች ባለችበት ወቅት ነው።

ነገርግን የእስራኤል አመራር የኢራን የሚሳይል ጥቃት ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ በተደጋጋሚ ተናግረዋል።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን ባወጣው መግለጫ ሰለሰነዶቹ መረጃው እንዳለው ገልጿል።

ኢራን በበኩሏ አንዳንድ የባይደን አስተዳደር ባለስልጣናት እስራኤል #IRGC ላይ የሚሰነዘረውን የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃት አሳማኝ አየር ሀይላቸው ኢራን ላይ ሊሰነዝር ያቀደውን የአየር ድብደባ ሚስጥራዊ መረጃዎች ሾልከው እንዲወጡ ሆን ብለው የወሰኑበት ነው ብላለች።

ኢራን የሊባኖስ ወረራ እና የሄዝቦላህ መሪ ግድያ ሀሰን ነስረላህን ግድያ ለመበቀል በእስራኤል ላይ የሚሳይል ናዳ ማዝነቧ ይታወሳል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

20 Oct, 13:06


የእስራኤልን የማጥቃት እቅድ የሚያሳይ ሚስጥራዊ ሰነድ ከአሜሪካ ደህንነት ሾልኮ መውጣቱ ተዘገበ

- አሜሪካ ሰነዱ እንዴት እንደወጣ ምርመራ እያካሄደች ነው ተብሏል፣

- ኢራን በአንፃሩ ሚስጥራዊ መረጃዎቹ ሾልከው እንዲወጡ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው ብላለች

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 18:36


ይህን ለመቁጠር የሚታክት ሀብት ያለውን ከበርቴ ቤተሰብ በፎርብስ የቢሊየነሮች ዝርዝር ላይ መፈለግ ዋጋ ቢስ ነው ይባላል። ሆኖም በዓለም ላይ ከነበሩ ጦርነቶችም ሆነ መንግስታዊ አመፆች ጀርባ ቀንደኛ ተሳታፊ ሆኖ መቆየቱን የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች አሉ፡፡ መንግስታት ለሚያካሂዷቸው ጦርነቶች ገንዘብ በማበደር ብዙ ሀገራትን ድህነት ውስጥ ከቶ በትሪሊየን ዶላር የሚቆጠር ሀብት ማፈሱም ይነገርለታል፡፡ ቀጣዩን የዩትዩብ ሊንክ ስትከፍቱም አሁንም ድረስ ድብቁን የዓለማችን ሴረኛ ከበርቴ ቤተሰብ በተመለከተ ሚስጥራዊ መረጃዎችን የምታደምጡ ይሆናል፡፡ ላይክ፣ ሰብስክራይብ እንድታደርጉም ተጋብዛችኋል

https://youtu.be/6LylaTQEfLU?si=kxls-7DiOTaC8CuE

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 18:10


ትራንስ - አፍሪካ ሀይዌይ Trans Africa Highway Network የአፍሪካ ረጅሙ የመንገድ ፕሮጀክት ሲሆን፣ 9 አውራ መንገዶችን ለማቀላቀል ያለመ ሲሆን፤ ይኸውም "ፓን-አፍሪካዊ ኢኒሼቲቭ" መሆኑም ይነገርለታል። ፕሮጀክቱ 56,683 ኪሜ የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ የታቀደለት ነው።

ይህ አህጉር አቋራጭ የመንገድ ፕሮጀክት የሚያልፍባቸው ሀገራት ደቡብ አፍሪካ🇿🇦፣ ኬንያ🇰🇪፣ ዩጋንዳ🇺🇬፣ ናይጄሪያ🇳🇬፣ ካሜሩን🇨🇲፣ አልጄሪያ🇩🇿፣ ግብፅ🇪🇬፣ ሊቢያ🇱🇾፣ ሴኔጋል🇸🇳፣ ቻድ🇹🇩፣ ጅቡቲ🇩🇯፣ ኢትዮጵያ🇪🇹፣ ሱዳን🇸🇩፣ ቦትስዋና🇧🇾፣ አንጎላ🇦🇴፣ ዛምቢያ🇿🇲፣ ናሚቢያ🇳🇦፣ ዚምባብዌ 🇿🇼፣ ሞዛምቢክ🇲🇿፣ ታንዛኒያ🇹🇿፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፕ እና ዲአር ኮንጎ 🇨🇩 ናቸው።

ይህ የመንገድ አውታረ መረብ አፍሪካዊ ሀገራት የርስ በርስ ትስስራቸውን ለማጎልበት ብሎም ለማደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ እንደሆነ ይገለፃል።


#TransAfricanHighway #AfricaUnite #OneAfrica #JazeeraAfrica

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 15:40


በሶማሊያ ዋና ከተማ በጄኔራል ካሂ ፖሊስ አካዳሚ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ካፌ ውስጥ ኃይለኛ ፍንዳታ መድረሱን መቀመጫውን ሞቃዲሾ ያደረገ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

የአይን እማኞች በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግረዋል። የጸጥታ ሃይሎች ወደ ስፍራው ተልከዋል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 13:47


🇪🇬🇪🇹 🇷🇺 ብሪክስ በግብፅ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ውጥረት ሊያረግብ እንደሚችል በካይሮ የሩሲያ አምባሳደር ተናገሩ

ሞስኮ የግብፅና የኢትዮጵያ ወዳጅ በመሆኗ ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ታግዛለች ሲሉ በካይሮ የሩሲያ አምባሳደር ጆርጂ ቦሪሰንኮ ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለ ምልልስ ወቅት ተናግረዋል።

"በግብፅ ብቸኛው የመጠጥ ውሃ ምንጭ አባይ መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን" ብለዋል አምባሳደሩ።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 13:44


🌎 የብሪክስ መስፋፋት፡ ከአራት ወደ አስር ሀገራት፤ ዓለም አቀፍ ተጽእኖ

በፈረንጆቹ 2006 የተመሰረተው የብሪክስ ህብረት በተከታታይ እያደገ ነው ፤ በመጀመሪያ አራት ሀገራትን ያቀፈ ነበር፤ በ 2024 ድርጅቱ ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ የህብረቱ ሀገራት ቁጥር 10 ደርሷል።

📈 የ BRICS ኢኮኖሚ ከአለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት አንድ ሶስተኛ የሚጠጋ ሲሆኑ የህብረቱ ሀገራት የህዝብ ብዛት ከ45% በላይ የሚሆነውን የአለም ህዝብ ይሸፍናል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 13:13


https://youtu.be/gfEVigHoDaE?si=TTqdopPgZTP0rmOA

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

17 Oct, 10:58


https://youtu.be/NN0_Em0rfgs?si=i7Ly3WlHOzVQu1pJ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

16 Oct, 21:55


የመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃ ዝቅተኛው 0 ሲሆን ከፍተኛው 10 ነው። ስለዚህ ዛሬ የተከሰተው 4.6 በመሆኑ አለማቀፍ ጂኦሎጂካል ሰርቬዮቹ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረጃ አስቀምጠውታል::

1ኛ. መጠን ከ 1.0 እስከ 3.0: ይህን ያህል አይሰማም ግን ተመዝግቧል።

2ኛ. መጠን ከ 3.0 እስከ 3.9: ብዙ ጊዜ የሚሰማው ነው ነገር ግን ብዙም ጉዳት የለውም።

3ኛ. ከ 4.0 እስከ 4.9 መጠን: ጉልህ የሆነ የቤት ውስጥ እቃዎች መንቀጥቀጥ፣ አነስተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።

4ኛ ከ 5.0 እስከ 5.9 መጠን: በህንፃዎች እና ሌሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።

5ኛ. መጠን ከ 6.0 እስከ 6.9: ጠንካራ መንቀጥቀጥ እና ለከባድ ጉዳት ያስከትላል።

6ኛ. 7.0 እና ከዚያ በላይ መጠን: ከፍተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ጉዳት እና ሰፊ ውድመት ሊያስከትል ይችላል።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

16 Oct, 21:21


ዛሬ ረቡዕ ጥቅምት 6 ፤ 2017 ምሽት፤ በአዋሽ አካባቢ በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ። የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ንዝረት፤ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች መሰማቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከአዋሽ ከተማ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከሰተው የዛሬው የመሬት መንቀጥቀጥ፤ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ላይ የተመዘገበ እንደነበር መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል። በዚሁ አካባቢ ባለፈው አንድ ወር ጊዜ ብቻ ሰባት ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን መረጃዎች ያሳያሉ።

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

16 Oct, 19:27


ከ4ት ዓመታት በፊት ስለ ሰላም
ከተናገሩት

“ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ
እግዚአብሔር ጸልዩ።”

ሊቀ ትጉኃን ባሕታዊ አባ መፍቀሬ ሰብእ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

16 Oct, 15:38


አባ መፍቀሬ ሰብእ

የሁሉ አባት የሁሉም ሀብት፣ ታላቅ አባት፣ ታላቅ መካሪ፣ ሃይማኖት ሳይለዩ የተቸገረን የሚረዱ፣ ዛፎችን በመትከልና በመንከባከብ የሃገርን አረንጓዴነት ለመጠበቅ ለዓመታት የሰሩ፣ ሰርተውም የተሳካላቸው፤ በተለያየ ሃይማኖት አማኞች ዘንድ የሚወደዱ አባት ዛሬ አልፈዋል 💔 አባ መፍቅሬ ሰብእ

ለደሴ፣ ለግሸን፣ ላሊበላ ነዋሪዎች እንዲሁም እሳቸውን ለምናውቅ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ መፅናናት ይሁን!
#የዓባይልጅ

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

16 Oct, 13:01


https://youtu.be/hO_a4yoIXTE?si=ZyA4gr_b_2mGAPOC

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

16 Oct, 07:18


Egypt’s risky bet in the Horn of Africa - የዓባይ ፡ ልጅ
https://eslemanabay.com/egypts-risky-bet-in-the-horn-of-africa/

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

15 Oct, 19:07


ማዕከሉ በብሪክስ ፕላስ አባል ሀገራት መካከል የሰብዓዊ ትብብርን ለማጎልበት፣ ባህልን፣ ሳይንስን እና ትምህርትን ለማስተዋወቅ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ከኢትዮጵያ፣ ብራዚል፣ ግብፅ፣ ህንድ፣ ኢራን፣ ቻይና፣ ኩባ፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቱርክ እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ የመንግስት አካላት፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቦች፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ÷የማዕከሉ መመስረት በብሪክስ አባል ሀገራት ውስጥ ባሉ ሚዲያዎች መካከል የባህል እና የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡

"በዚህ ጉዞ ውስጥ ታሪክን በማስተዋወቅ እና ልዩነቶችን በማክበር ለአንድ አላማ እንድንሰበሰብ በማስቻል በኩል የመገናኛ ብዙሃን ሚና የጎላ ነው" ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ይህንን አጋጣሚ የባህል ግንኙነታችንን ለማሻሻል እና ጠንካራ የብሪክስ ማህበረሰብን ለመፍጠር እንጠቀምበት፤ በጋራ በመንቀሳቀስ በዓለም ላይ ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አያይዘውም ኢትዮጵያ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2019 ጀምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን የቱሪስት መደረሻዎችን መገንባቷን ጠቅሰው፤ለአብነትም በአዲስ አበባ የአንድነት ፓርክ እና እንጦጦ፣ ከአዲስ አበባ ውጭ ደግሞ ወንጪ፣ ጎረጎራ እና ሃላላ ኬላን አንስተዋል፡፡

እነዚህን ስፍራዎች ደረጃቸውን በጠመቁ መሰረተ ልማቶች በማልማት የተፈጥሮ ቅርሶችን ከመጠበቅ ባለፈ ለአካባቢው ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዘላቂ ልማት አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዕለቱ የሚዲያ ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይትም መካሄዱን የቲቪ ብሪክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

Esleman Abay የዓባይ ልጅ

15 Oct, 19:07


የብሪክስ ፕላስ የመረጃና እና የባህል ሚዲያ ማዕከል ተመሰረተ

የብሪክስ ፕላስ የመረጃ እና የባህል ሚዲያ ማዕከል መመስረቱን አስመልክቶ የመክፈቻ መርሐ ግብር ዛሬ በሩሲያ ሞስኮ ተካሂዷል፡፡