መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 @menfesawigetem Channel on Telegram

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

@menfesawigetem


በተለያዩ ሰዎች የተፃፋትን መንፈሳዊ ግጥም እና ታሪክ የኪነጥበብ ፅሁፎችን መንፈሳዊ profile Picture አሰተማሪ ታሪኮችን የሚያገኙበት channel ነው👈
በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፣የቃልህን ጥበብ ያፌዝብሀልና። ምሳሌ 23፥9
ብዙዎች ወደው በሚከታተሉት በዚህ ቻናል የtelegram Channal, group እና ዩትዩብ ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ username @abrex_1 አናግሩኝ

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 (Amharic)

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒 ከትምህርት ያለው በተለዩ ሰዎች የተፃፋትን መንፈሳዊ ግጥምእና ታሪክ የኪነ-ጥበብ ፅሁፎችን መንፈሳዊ profile Picture አሰተማሪ ታሪኮችን የሚያገኙበት channel ነው👈 በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፣ የቃልህን ጥበብ ያፌዝብሀልና። ምሳሌ 23፥9 ብዙዎች ወደው በሚከታተሉት በዚህ ቻናል የtelegram Channal, groupእና ዩትዩብ ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በዚህ username @abrex_1 አናግሩኝ

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

21 Nov, 12:13


💒 ባሕረ ኤርትራን በበትሩ ከፍሎ እስራኤልን ያሻገረው❓️



✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

21 Nov, 11:24


ቅዱስ ሚካኤል
.
.
.
የአምላክ ባለሟል የአፎምያ ረዳት፤
ሶስናን ያዳነ ከአይሁድ ረበናት፤

ህዝበ እስራኤልን በደመና ጋርዶ፤
እርሱ ያሻገረ እየመራ ወስዶ፤

የባህራን ሞቱን በህይወት የሻረ፤
ለማኑሄ ደስታን ብስራት የነገረ፤

የምስኪናን አባት የድኩማን ምሽግ፤
በኑኅ ሰማይ ላይ ጸሎት የሚያሳርግ፤

ምሕረት የሚለምን የዋህ ባለግርማ፤
ለአምላኩ ምስጋና ድምፁን የሚያሰማ፤

የምስጋና ድምፁን ቃሉን ላደመጡ፤
ከአምላክ ያስታርቃል ደጃፉን ሲረግጡ።
.......................................................
እንኳን አደረሳችሁ🥰🙏🙏🙏
ዔደን ታደሰ

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

21 Nov, 11:23


         ኦ ሚካኤል...
ፍፁም ትሁት ቢሆን ተሠጠው ልዕልና
ተርበው ለጠሩት የሚመግብ መና
ሞግዚት ነው በዓለም ለሌላቸው ወላጅ፣
ለታመኑት አባት ጠላትን አሳዳጅ
..
ነገድ ብሔር አይለይ ሲቀበል አደራ
ልጆች አሳዳጊ ከፊት እየመራ
ቦታ አይወስነው ጊዜ አይወስነው
                ልጆቹን ሲጠብቅ፣
ስሙ ግርማ ያለው ጠላት የሚያስጨንቅ
የማይሰለች አባት ፍቅሩ የሚጨምር
የሞትን ደብዳቤ በህይወት የሚቀይር
..
ልዑል እምልዑላን ስልጣኑ ከፍ ያለ
ሠልፉን እየመራ ዘንዶውን የጣለ
እሱ ያልረዳው ሠው አይገኝ በዓለሙ
ለአህዛብ አደለም ክርስቲያኖች ስሙ
..
ዓለም ጥበበኛ ያውቅበታል ሴራ
ቆላ ደጋ ብሎ ቢደግስ መከራ
ስጋችሁ አይራድ ፍፁም አትደንግጡ
ሠልፋችሁን ይምራ ልክ እንደ አፎምያ
                   ለሚካኤል ስጡ፣
የዓለምን ሴራ የገንዘብን ድግስ 
                  በእምነት ብለጡ፣
የሚካኤል ልጆች አትፍሩ ቀኑ
                      ቢጨልምም
እንኳን የአዳም ዘር ዘንዶው አልቻለውም!!

        ገጣሚ_ ኤርሚ ግርማ

      
      
እንኳን አደረሳቹ

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

21 Nov, 05:10


https://www.youtube.com/live/ohCsTilZipU?si=oRJwRBmFtAch_-xO

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

20 Nov, 17:27


እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል አመታዊ
ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

Share & Join👇
https://t.me/+J0ynCyKIZu85N2Y0
       ♥️@wendi_official2♥️
       ♥️@wendi_official1♥️

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

14 Nov, 17:30


በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

14 Nov, 07:54


🥀#Na_ilaali_maalo🥀

Na ilaali maalo anoo nama hin qabu
Of biraatin dhabee namaa ol na qabu
Beekumsiif humnikoo si'idha abdin koo
Na bira hin darbinii na fayis uumakoo
🥀
#Ceesisa
🥀
Beela'ee dheebodhe yoon bules hagabuu
Marromaan koo maree yemmuuttin gaggabuu
Nama si waamatee si'i kan qaaqabu
Maalo naa gargaari anoo nama hin qabu
🥀
#Ceesisa
🥀
Jaamadha naan jedhee hundumtu na gatee
Anis naman dhabe namnis natt hammaate
Boolla dukkanatti gadi na daarbatu
Si qofadhaa gofta kan na fayyifatuu
🥀
#Ceesisa
🥀
Si barbaachun dhufe mana kooti ka'e
Si arguun barbaade mukaattan olba'ee
Na dura gorani na dhoksun fuula kee
Anoo nama hin qabu na fayis ilma kee
🥀
#Ceesisa
🥀
Nama of biraa dhabee yoon dhabees fayinaa
Fayyuu osoon barbaadu ciisee bishaan cinaa
Dhukubsadhee ciisee waggoota hedduu kanaa
Fayyii galii jettee deemi garaa mana

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ
👉
#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
👉
@enatachinmaryam

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

14 Nov, 07:54


https://www.youtube.com/watch?v=4Ks1bvvMoKM

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

14 Nov, 07:54


🛑Na Ilaali Maloo,F/taa Biqilaa Mitikkuu,Faarfannaa Afaan Oromoo Ortodoksii Tewahidoo haaraa ,2022

ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን እንዲደርስ
👉
#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
👉
@enatachinmaryam

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

14 Nov, 07:21


🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

13 Nov, 11:45


Guys ሙስሊሞች እምነታቸውን ለምን እንደማይቀይሩ በዚህ video መልሱን ታገኛላቹ
ወንድማችን እፎይ ፈጣሪ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርከው👍

መርቁት😅😅😅

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

13 Nov, 07:41


ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡

የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡

‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡

አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ ም

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

13 Nov, 07:41


ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ 1ኛጼጥ3÷16

+++ ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ +++

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)

ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦ ት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109) ሌላው አስገራሚ ነገር አቡነ ጎርጎርዮስ በታቦት ሥርዓት ከግሪኮች አንዲሚስዮን ጋር እንደምንመሳሰል ጠቅሰው ሲጽፉ ግሪኮቹ ደግሞ ስለ አንዲሚስዮን ሲያብራሩ ከኢትዮጵያ ታቦት ጋር የሚመሳሰል ብለው መጻፋቸው ነው።

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

13 Nov, 07:36


✞#ኧረ_አልሆንልኝም_አለ✞

/ድንቅ የንስሐ መነባንብ/

ኧር አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ነፍሴ በኃጢአት ሸፈተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

ኧር አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ነጭ ነጠላ አጣፍቼ ከቤተ መቅደስ ስወጣ፤
መጽሐፍ ቅዱስ ዘርግቼ ለስብከት መድረክ ስወጣ፤
ልብሰ ተክህኖ ለብሼ ንፍቅ ገባሬ ሰናይ ስሆን፤
ጥቅስ በቃሌ ስደረድር ለዜማ ቅኔ ስቀኝ፤
አካሌ እዚህ ሆኖ መንፈሴ እየሸፈተ፤
ነፍሴን በኃጢአት ገንዞ ስጋዬ ነፍሴን ጎተተ።

ኧር አንድ በይኝ እመብርሃን ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
ጨርሶ ዓለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።

ማለዳ ኪዳን አድርሼ ቅዳሴ ጸሎት ጨርሼ፤
ከቤተክርስቲያን ወጥቼ ወደ ስጋ ገቢያ ተመልሼ፤
በኃጢአት ባህር ስዋኝ የግፍ ዳንኪራ ስረግጥ እውላለሁ፤
የልጅነት ፀጋዬን አውጥቼ ብኩርናዬን እሸጣለሁ።
እዚህ መልአክ መስዬ ላዬ በቅድስና በርቶ፤
ውጪ ከክፋት ከፍቼ ኃጢአት በጽድቄ ተተክቶ፤

በሀሜት የሰው ስጋ ስበላ በወንድሜ ሸር ስሸርብ፤
ስዋሽ ስቀጥፍ ውዬ ስሰርቅ ሳሽሟጥጥ ስሳደብ፤
ነጠላ ስለብስ ግን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስገባ፤
ሰዓሊለነ ቅድስት ስል ያለ ንስሐ እንባ፤
የመውደቂያዬ ጉድጓድ ጥልቀቱ ወሰን ዳርቻ የለውም፤
እዝነ ህሊናዬ ለዓለም እንጂ ለጽድቅ ቦታ የለውም፤

መሃረነ ክርስቶስ እንዳልል ተዘከረነ ፈጣሪዬ፤
ኃጢአት በደሌ አፈነኝ በሀፍረት ነደደ ህሊናዬ፤
ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን ተዘከረነ ብዬ።
ስለእኔ መገረፉን የመስቀሉን ፍቅር አቃልዬ፤
እንዴት ማረኝ ልበለው ስለ ስጋ ጣዕም ተቃጥዬ።

ምን ብዬ ልጥራው ጌታዬን?

ዓይኔን ወደ ፀፍፀፈ ሰማይ ወደ ሥላሴ መንበር፤
አንስቼ ማየት አቃተኝ ማረኝ ብዬ ለመናገር።
ለሰው ጻድቅ መስዬ የኃጢአት ጎተራ ሆኛለሁ፤
እንዴት አባቴ ቀና ብዬ መንበረ ጸባኦትን አያለሁ።
እባክሽን እናቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ፤
እንደቃና ዘገሊላ ባዶ ማድጋዬን ሙዪልኝ።
ከፊቱ እንዳላፍር ከአማኑኤል ጋር አስታርቂኝ፤
ለተጠማ ውሻ እንዳዘንሽ ለመጻተኛው እዘኚልኝ።

አንቺ የትሁታን ትሁት ርህሪይተ ልብ እናቴ፤
ከልጅሽ ከኢየሱስ አማልጂኝ እዘኚ ለእኔም እመቤቴ።
አንቺ ውዳሴሽ የነፍስ ስንቅ ስምሽ ከማር የጣፈጠ፤
በላኤሰብዕ በእፍኝ ውሃ በምልጃሽ ከሞት ያመለጠ።

አንቺ መላእክት የሚጎበኙሽ የካህናት አለቆች ምስጋናቸው፤
በመወሰን የማይወሰን እሳተ መለኮትን የቻልሽው።
አንቺ ከገነት በተሰደደ ጊዜ ለአዳም ተስፋ የሆንሺው፤
ዛሬም ለእኔም ተስፋ ሁኚኝ ለነፍሴ ስለነፍሴ ተዋሺው።

እንጂ እኔማ አልቻልኩም የልቤ ንጽህና ጠፍቷል፤
ለጸሎት እንኳን ስቆም ልቤ ለሁለት ተከፍሏል፡፡

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፡፡
የጭንቅ አማላጂቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።

የልቤን መወላወል የነፍሴን ድካም አበርቺ፤
በአማላጅነትሽ ስር ነኝ እና ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺ።
ለሰው ዓይን ባይገለጥም ሰውሬ የሰራሁት ኃጢአት፤
አምላክን አሳዝኖታል የምኖርበት ሕይወት፤
ይኸው የምናገረው አይሰምር የወረወረኩት አይመታም፤
ስጋዬ አልተቀደሰ ገበታዬ በረከት የለውም፤
ዕውቀት ምርምር አይዘልቀኝም ህሊናዬ ፍሬ አይቋጥር፤
ዝርው ሆኖብኝ ቀርቶ የነፍስ የስጋዬ ምስጢር።

ይኸው የማወራው ለሰው አይጥም ፍቅር ከእኔ ቤት ርቋል፤
መቆም መቀመጤ አያምርም ሰው በስራዬ ይማረራል፤

የኃጢአት ምንዳዬ ይኸው የኃጢአት ደሞዜ ይኸው ስቃዬ ውስጤን በልቶታል፤
ለአንድነት የተናገርኩት ዛሬም ጉባኤ ይበትናል።

እና አዛኝቱ ታረቂኝ ከልጅሽ ከአማኑኤል አማልጂኝ፤
ከሰው የሸሸግኩት ኃጢአት ጨርሶ በልቶ ሳይውጠኝ።
የበላኤሰብዕ እመቤት እባክሽን ተማለጂኝ፤
አንቺ ሕይወቴን ዳብሺው ነፍሴ ዕረፍት እንድታገኝ።

ኧረ አልሆንልኝም አለ መንፈሴ አልገዛም አለ፤
የጭንቅ አማላጅቱ አንድ ብትዪኝ ምን አለ?

ጸሎት ምህላ አቃተኝ መንፈሴ ለንሰሐ ሸፈተ፤
መንጸፈ ደይን ወደቅኩኝ ስጋዬ ነፍሴ ሸተተ።
እምቢ አለኝ ፆም ጸሎት እምቢኝ አለኝ ንስሐ፤
ስጋ መንፈሴ ኮብልሎ እየዋኘ ከዓለም ውሃ።
ኧረ አንድ በይኝ እመቤቴ ወለላይቱ ተማለጂኝ ጨርሶ አለም ሳይነጥቀኝ ከወደኩበት አንሺኝ።
እባክሽን ተማለጂኝ እናቴ ኪድሀነ ምህረት
ተስፋ ክብራችን አንቺ ነሽ



#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

13 Nov, 07:27


#የኔ_ሴት
.
.
.
ያየኝ የለም ቆላ አልወጣሁም ደጋ፣
አልንከራተትም የኔን ሴት ፍለጋ።
ይሁን ካለ አምላክ ከፈቀደው ጌታ፣
ያመጣት የለም ወይ ካለሁበት ቦታ።

መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒

13 Nov, 07:24


ኧረ በቃኝ ይሄስ ዓለም
ቀኔ ጎድሏል ሙሉ አይደለም።
ልሂድ ልግዛ ፣ አንዲት ገመድ
ልጓዝ ልብረር ፣ በሙት መንገድ።
ያስከፋኛል አገዛዙ ፣
ዙሪያው ገባው አያያዙ
የሰው ክፋት ጉድ ፣ መዘዙ
አላፈራም … ከምዘራው
እንባዬን ነው የማዘራው።
:
ልሂድ በቃ ልሰናበት…
ዘመኔ ላይ ልፍረድበት …
አንዲት ገመድ ላንዲት አንገት
በሽንቁሯ ልለፍበት ፤
ብዬ ጀመርኩ የሙት ጉዞ
ልቤ ቀልቤ ተመርዞ … ።
:
ግና ከንቱ…
ምን ዋጋ አለው?
:
አገኘኋት ስረማመድ
ያቺን ሸጋ ልጃገረድ
ገለጠችው ያንን ከንፈር
ይኸው ሳቀች ለክፋቱ
ልኑር በቃ ምናባቱ!

(ሚካኤል አ)

35,836

subscribers

694

photos

612

videos