[
የመሞት መብት!]
Yonas Temare
[email protected]ልጆቻችሁ ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ቤት ከመሄዳታቼው በፊት፣ ከዚያም ወደ ኮሌጅ ወይም ደግሞ በመጨረሻ ራሳችሁን ችለው ከቤት ሲወጡ ምን ብላችሁ እንደምትነግሯቸው አስባችሁበታል?
መልካም፣ እናንተ በሌላችሁበት ወይም ለመውጣት ወይም ለመግባባት በማትችሉበት ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለባቸውስ አሁን ከቤተሰብዎ ጋር ተነጋግረዋል።
በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ምርጫዎችን ለማድረግ ፍጹም ነፃነት አለን(ነፃ-ፍቃድ ባይኖረንም)። አብዛኛዎቹ ጠዋት ላይ ምን ዓይነት የጥርስ ሳሙና እንደምንጠቀም፣ ምን አይነት ቀለም ሸሚዝ ፣ ቀሚስ እንደምንለብስ፣ ለቁርስ ምን እንደምንበላ እና ሌሎችን ምርጫዎችም እንመርጣለን።
ነገር ግን በጠና ብንታመምና መቼ እና እንዴት መሞት እንደምንፈልግ በሕጋዊ መንገድ ለመምረጥ ምርጫ ማድረግ ብንፈልግስ? ሞትህን በትክክል እንደምትፈልገው እንዲሆን ማን መገኘት እንዳለበት መንደፍ ብትችልስ፣ በመጨረሻው ሰአት ምን አይነት ሙዚቃ እንደምትሰማ፣ ከአንዱ ግዛት ወደ ስታልፍ ነፍስህ እንድትደሰት የምትፈልገው የሻማ ሽታ፥ ለልብስህ ምርጥ ሽቱ፥ ለመቃብርህ ጥቅስም ራስህ መርጠህ፤ ቤተሰቦችህ ተሰብስበው በትልቅ ተመስጦ ውስጥ ስለነገ ተመካክራችሁ፥ ያላንተ የሚኖሩትን ህይወት መቀየስ ብትፈልግስ?
ቻው ብለህ ተሰናብተህ ተቃቅፈህ መለያየትና፥ በተቀመጥቅበት ተዘጋጅተህ እዛውኑ በሃኪምህ ህመም አልባው የሞት መዳኒትህ ቢሰጥህና ብታሸልብ ትጠላለህ?
አዎ በዚህ አገር ይሄን ማንሳት ቅንጦት ይሆናል፥ ነገር ግን ነገ ፀሃይ ስትወጣ ይሄን ሃሳብ ልጆቻችን እንዲቀጥሉበት እፈልጋለሁ።
ሞትን መጥፎ ካደረጉት ነገሮች ውስጥ፥ ያለስንብት ውዶቻችንን መውሰዱ፥ እንዲሁም በስቃይ መከራን አሳይቶ መውሰዱ ነው። ይሄን ነገር ለማስቀረትና በድብቅ በገመድና በኤሌክትሪክ፥ በበረኪና ራሱን በስቃይ ከሚገድል በህክምና የመሞት መብቱ ተከብሮ ያለህመም ሰው ከዚህ አለም ቢሰናበት መልካም ነው።
እስኪ አስበው በማይድን በሽታ ተይዘህ ቤተሰቦችህ ለአንተ ሃብትና ላትድን ነገር ንብረታቼው ለህክምና ጨርሰው አንተንም አጥተው፥ ያላንተ ደግሞም በድህነት ከሚማቅቁ ይሄ ውሳኔ አይሻልህም? እኔ ይሄን በረከት የመሞት መብት ብዬ ለአገሬ አበስራለሁ።
ለሰው ልጅ የመኖር ብቻ ሳይሆን የመሞት መብቱም ሊከበርለት ይገባል።
የሰውልጅ ህይወት በራሱ ትልቅ Story ነው፥ ለማንኛውም Story ደግሞ End Matter! መጨረሻየን አሳምረው ይሉ የለ ታላቆቻችን? አዎ እኔም እላለሁ የመሞት መብታችንን በህግ አስከብረን መጨረሻችንን እኛው ማሳመር እንችላለን።