♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱ @mahtebezetewahdo Channel on Telegram

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

@mahtebezetewahdo


✝️ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን እንኳን ወደ ባለማዕተቦቹ የተዋሕዶ ልጆች ቻናል በሰላም መጣችሁ

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱ (Amharic)

ባለ ማኅተቦቹ በአምላክ አሜን የተዋሕዶ ልጆች የቻናሉ በሰላም ምኞቸውን ይዞሻል። በዚህ ባህሪያችሁም ለአዲስ ተካሄደው ቀላል አስተዳደር እና ለእንዴት ችግር አልፈለግም። እኛ ሥራውን ለመረዳት እና ለመረጃ ችግር እና መረብታዊ ኮሌክሽን እና ጠቃሚ የሙዚቃ ግንኙነት በማስፈፅም ይጠቀሙ። በሳይንስፖርት እና በሌሎች አገልግሎቶች ለመቀነስ ዝናባ ወይም ለመረጃ ላይ በመጠቀም መጠን ዝናባ እንዲሁም የቁምፊዎች ቪዲዮ ምልክት እና ስኬልቶችን በማሳተፍ እና በማመዝ ፈቃድ መግባት ይችላሉ። በሌላ በጣም ዳግም ድርሶ እንዲሁ ፦ mahtebezetewahdo

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

02 Nov, 19:30


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

02 Nov, 18:37


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

01 Nov, 15:02


ጊዮርጊስ

ሰማዕተ ኢየሱስ የእውነት ምስክር
ህያውን ነው በሰማይ
ብፁዕ ነው በምድር
ደራጎንን በጦር ወግቶ ገደለና
ከሞት አዳነኝ ጊዮርጊስ ደረሰና

የሀዘን ማዕበል እንዳያንገላታኝ
ታምር ሰሪው ሰማዕት ፈጥኖ አረጋጋኜ
በእግዚአብሔር ጣዕም በፍቅሩተጠምዷል
ይህን አለም ንቆ በክብር አጊጧል
አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ


እርሱ ለምጠራው ሲመሽም ሲነጋ
ዋስ ጠበቃዬ ነው በነፍስም በስጋ
ድንቅ የሚፈፅም ሀያል ሰማዕት ነው
በቅድመ እግዚአብሔር ለእኔ የሚቆመው
አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ


የምስጋናን አውታር የታጠቀ ሰማዕት
ስሙን ተሸክሞ የታመነ እስከሞት
ሙታንን የሚያስነሳ ስልጣን ተቀብሏል
በአባቱ መንግስት እንደ ፀሐይ ደምቋል
አፍጣኒተ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ነፋሴ
ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ
አድናት ሃገሬን ከገጠማት ትካዝ


┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

31 Oct, 15:03


🕯 ...➋➊....🕯

🌷... እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

🌹... ድንግል ሆይ...

🕯...እኔ የተጠማሁ ነኝ
አንቺ የወርቅ መቅጃ ነሽ ልጅሽ የሕይወት ውኃ ነው፡፡

🕯...እኔ ነጋዴ ነኝ
አንቺ መርከብ ነሽ ልጅሽ ዕንቈ ነው፡፡

🕯...እኔ ገደል ተሻጋሪ ነኝ
አንቺ ድልድይ ነሽ ልጅሽ የደስታ ሥፍራ ነው፡፡

🕯...እኔ ደሃ ነኝ
አንቺ የክብር ማከማቻ ነሽ ልጅሽ የከበረ ጌጥ ነው፡፡

🕯...እኔ ቁስለኛ ነኝ
አንቺ የመድኃኒት ብልቃጥ ነሽ ልጅሽ መድኃኒት ነው፡፡

🕯...እኔ ዕርቃኔን ነኝ
አንቺ የሸማኔ ዕቃ ነሽ ልጅሽ የማያረጅ ልብስ ነው

❣️🥰🙏🤌

ረድሄት በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን በውነት🙏

አሜን🙏

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

30 Oct, 18:30


"አጎንብሼ ሄጄ ቀና ብዬ መጣሁ። 

በዮሐንስ ፀበል ጤናዬን አገኘሁ"

👉ይህ ሰው እኔ ነኝ

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

28 Oct, 15:36


"🌹"ነገ ⓳ የራማው ልዑል  መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው።

በእለተ ቀኑ ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን የራማው ልኡል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ጥላ ከለላ ይሁነን።
🙏

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

26 Oct, 04:40


ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ ✞

ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ/፪/
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
ኧኸ እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ/፪/

የነፍሴ ትምክሕት ሁኚኝ ጥላዬ
እያማለድሽኝ ከቸር ጌታዬ
ማዕረጌ ጌጤ የልቤ ቅኔ
ሳመሰግንሽ ይለፍ ዘመኔ

ኪዳነ ምሕረት እናቴ የነፍሤ መጽደቂያ ሁኚኝ/፪/
እንደ ለመንኩሽ አንቺም ተለመኚኝኝ/፪/

አለሽ ቃል ኪዳን የማይታጠፍ
ትውልድ የሚያስምር ለዓለም የሚተርፍ
በክብር ያለሽ በእግዚአብሔር ቀኝ
ለጻድቅ አይደል ለሐጥዕ ለምኝ

ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ/፪/
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ/፪/

ነፍሴ ከቅጽርሽ ተጠግታለች
በፍቅር ሥምሽ ትማልላለች
ልቤን አኑሬ በብርታትሽ ላይ
ከአንቺ ጋር ልኑር ሞትን እንዳላይ

ኪዳነ ምሕረት እናቴ የነፍሴ መጽደቂያ ሁኚኝ /፪/
እንደ ለመንኩሽ አንቺም ተለመኝኝ/፪/

በርሕራሔው በቸርነቱ
በፍቅር እንዲያየኝ በምሕረቱ
ብለሽ ንገሪው መሐር ወልድየ
የኃጢአቴ ቀንበር ይውረድ ከላየ

ኪዳነ ምሕረት ኩኒ ለሕይወትየ ጸወኖ/፪/
እስመ ተማሕጸንኩ አንሰ ተማሕጸኖ /፪/

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

25 Oct, 20:36


"ነገ ጥቅምት 16 ቅድስት ኪዳነ ምህረት የኪዳን ቀኗ ነው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ትሰውረን።🙏

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

22 Oct, 18:39


🕯 .... ቅዱስ ሚካኤል.... 🕯

ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምነት


✝️ሚካኤል አባታችን አማላጃችን☦️

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

21 Oct, 17:18


ይለይብኛል ሚካኤል


ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

19 Oct, 16:36


የመስቀል ዓይነቶች ፡ ክፍል ፩

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

18 Oct, 15:58


ተአምር መሥራት ትፈልጋለህን?

አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበላቸው "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሱለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤  ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው።

በል ሒድና ተአምር ሥራ!" አሉት

በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

14 Oct, 16:32


"ዛሬ ጥቅምት 4 ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ልደቱ ነው።ዮሐንስ ማለት ፍሥሓ ወሐሴት ማለት ነው።

"ከመስቀሉ ስርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ እለት በልጅዋ ስቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና እነሆ ልጅሽ ብሎ ቅዱስ ዮሐንስን ሰጣት።

በእምነት በምግባር ላልጸናን ለእኛ ደግሞ አንተን ይስጠን አሜን አማላጅነቱ ጥበቃው አይለየን ።🙏❣️☦️

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

11 Oct, 16:41


ማኅሌተ ጽጌ 2ኛ ሳምንት

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

08 Oct, 18:55


"ነገ መስከረም 29 የበዓል ሁሉ ራስ የሆነው በዓለ ወልድ /በዓለ እግዚአብሔር ነው።በዓለ ወልድ ማለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድንግል ማርያም ማሕፀን ተፀንሶ መወለዱንና ሙቶ መነሳቱን የሚያሳስብ በዓል ነው።🙏


🌷እንኳን አደረሰን🤲

ቅዱስ በዓለ ወልድ ከመከሬ ስጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ይሰውረን።🙏

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

07 Oct, 19:13


"ነገ መስከረም 28 አባታችን ቅዱስ አማኑኤል ነው ።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውረን።🙏

♱ ባለ ማኅተቦቹ ♱

06 Oct, 14:04


በዘመነ ጽጌ የሚጾም ጾም