Ethio-Analytics

@betsega12


ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል

Ethio-Analytics

06 Jan, 05:52


ሰላም ወገኖቼ !

Ethio-Analytics

23 Oct, 11:30


Channel name was changed to «Ethio-Analytics»

Ethio-Analytics

23 Oct, 11:30


Channel photo updated

Ethio-Analytics

23 Oct, 11:28


ባህር ዳር ግራንድ ሞል

Ethio-Analytics

28 Mar, 19:54


አማራ ባንክ የማን ነው? ገንዘቡን እነማን ናቸው የሚከብሩበት?
አማራ ባንክን የበላው ጅብ አልጮህ አለሳ?

ምን ገቢ አስገኝቶ ነው በዘርፉ ምንም ልምድ የሌላቸውን ልጆች ይህን ያክል ከፍተኛ ደሞዝ የሚከፍለው? የተመለመሉትን በምን መስፈርት ነው?

ከህዝባችን የተሰበሰበው ገንዘብ የወጣት ጡረተኞች መጦሪያ ሆነ‼️
የሚደርሱኝ ጥቆማዎች እንደሚያሳዩት የሰው ሀይል ቅጥሩ በአካባቢ ልጅ፣በገንዘብና በምልጃ ነው።

ለመሆኑ ይህን ያህል ጊዜ በባለ 5 ኮከብ ሆቴል አልጋ ተይዞላቸው የሚንፈላሰሱት ሰዎች ህሊና የላቸውም?

ጥቆማዎቹን ከራሴ መረጃዎች ጋር አድርጌ ቀጣይ አቀርብላችኋለሁ::
የአክቲቪስቶቹንም አልረሳሁትም!

Ethio-Analytics

19 Mar, 05:46


ትምህርት ሚኒሰቴር በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ላይ የተፈጠረውን
-ተቋማዊ የሆነ የፈተና ስርቆት
-የአስተራረም ችግር
- በጦርነቱ ቀጠና ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን ያሉበትን ሁኔታ ያገናዘበ ምዘና አለማድረግ
ችግር ምንም እንዳልተፈጠረ አለባብሶ ለማለፍ እየሄደበት ያለው ሁኔታ ከተፈጠረው ችግር በላይ አሳሳቢ ነው።

ተቋሙ በዚህ ግትርናው የሚቀጥል ከሆነ ማንም ከህግ በታች ስለሆነ በህግ ተጠያቂ መሆኑ አይቀርም። ይህ ደግሞ ውጤቱ ተቋሙን ብዙ ኪሳራ ውስጥ እንደሚከተው ግልጽ ነው።

ስለዚህ የተቋሙ አመራሮች ዓይኑ ያፈጠጠ ጥርሱ ያገጠጠ ስህተት መሰራቱ እየታወቀ ግትር ከመሆን ይልቅ ችግሩን ማስተካከልና ለወደፊቱ መታደስ ነው ያለባቸው።

በሌላ በኩል የተፈጠረውን ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለተማሪዎች የተቆረቆሩ በመምሰል ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳትና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ ቡድኖች መኖራቸው እነተስተዋለ ነው። በቀናነት የቀረበውን የፍትሐዊነት ጥያቄ ጠልፎ ፖለቲካዊ መልክ ማስያዝ የተፈጠረውን ችግር ትክክለኛ ምስል ስለሚቀረው ለመፍትሔው የሚፈይደው ነገር የለም።

ሌላው የራስን ቅሬታ ማቅረብ እየታቸለ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች አንጻር እያነጻጸሩ ችግሩን ማቅረብ ለመፍትሔው ምንም ካለመፈየዱም በተጨማሪ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያሻክር ነው። ከዚህ የሚያተርፉት ህወሓትና የእሱ ሃሳብ ተጋሪዎች እና ጉዳይ አስፈጻሚዎች ብቻ ናቸው። አንድ ተቋም በፈጠረው ስህተት ተጠያቂ መሆን ያለበት ተቋሙ እና እሱን የሚመራው መንግስት እንጂ የትኛውም ህዝብ አይደለም።
(በዚህ ጉዳይ በሰፊው እመለስበታለሁ)

Ethio-Analytics

17 Mar, 18:19


ፈተናዎች ኤጀንሲ መፈተን አለበት‼️

የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ችግርን በተመለከተ ባለኝ ግንኙነት ችግሩ ምን እንደሆነ ለመጠየቅ ሞክሬ ነበር።
ያለኝ ጊዜ የተጣበበ በመሆኑ ምክንያት ሁሉንም ማግኘት ባልችልም ያገኘኋቸው ሰዎች ግን በጉዳዩ ዙሪያ መነጋገር ቀርቶ ርዕሱን መስማትም አይፈልጉም።

ባለኝ መረጃ አርሶ አደሮችን ጨምሮ የኑሮ ውድነቱ የተጫነው ማህበረሰብ የልጁ ውጤት በድጋሜ እንድታይለት ለመጠየቅ አገር አቋርጦ የፈተናዎች ኤጀንሲ በር ላይ ደጅ እየጠና ይገኛል። ሆኖም ውጤት በድጋሚ ለማየት ወላጆች ከፍተኛ ገንዘብ እየተጠየቁ መሆኑን ለማዎቅ ተችሏል። ገንዘብ መክፈል ያልቻሉት ተስፋ ቆርጠው ተመልሰዋል። ገንዘብ ያልከፈለ ሰው መስተናገድ አይደለም ግቢ ውስጥ መግባት አይችልም።
ሙስና ስር ሰዶ ከአንዲት የአርሶ አደር እናት መቀነት ገንዘብ እስከመቀበል ደርሷል።
ይህ አሰራር ልናሳካው ካሰብነው አገራዊ ዕቅድ የሚቃረን ነው።

ይህንን ስር የሰደደ ዝቅጠትና በወጣቶች ተስፋ መቀለድ ሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከመርህ አንጻር ሊታገለው ይገባል።

ዕውነትና ንጋት እያደር ይጠራል‼️

https://t.me/betsega12

Ethio-Analytics

17 Mar, 13:07


ደግሜ ደጋግሜ እጠይቃለሁ‼️
የጦርነቱ ጠባሳ ሳይለቃቸው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ጉዳይ እንደተራ አጀንዳ ታይቶ መታለፍ የለበትም።

የልጆቻችንን ተስፋ የሚያጨልም አድሎአዊ አሰራር በአስቸኳይ ምላሽ ይፈልጋል።

Ethio-Analytics

16 Mar, 19:51


በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ፊርማ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሆኜ በመመደቤ አንዳንድ ሰወች ቀደም ብየ የታገልኩትንና ሌቦችን ያጋለጥኩበትን ትግል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዝዤ እና መጠረግ የነበረባቸውን ሰዎች ለማሰጠረግ የፈፀምኩት ተግባር አድርገው መመልከታቸው አሳዛኝ ነው።
መርህ እንዲከበር ያደረግኩትን ትግል የሴራ አካል ማድረግ ሌሎች ታጋዮች እንዳይፈጠሩ እና ሌቦችና ሙሰኞች እንዲበረታቱ በር የሚከፍት ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ በፊት እንደነበሩት መሪወች ነቀፋዬን ችላ ከማለት እና በእኔ ላይም የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የህግና የመርህ ማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረጋቸው በበጎ የሚታይ ለውጥ ነው። ከዚህ ውጭ የእኔን ነቀፋ ከመጥፎ አተያይ ከማየት ይልቅ በበጎ ወስደውት የበለጠ የሚያበረታታ የኃላፊነት ቦታ ላይ መመደቤ ሌሎች ጓዶችም በየዘርፉ ሌብነትንና ሙስናን እንዲታገሉ የሚያበረታታ ነው።

Ethio-Analytics

16 Mar, 11:00


የትም ብሆን ህዝቤን ማገልገሌን አላቆምም!

መገፋትና ምጸት የሚያሳቅቀኝ የዕድሜና የዕውቀት ደረጃ ላይ አይደለሁም።

ከአቧራና ከጭቃ ለመምረጥ የውሃን መዋለል ብቻ ማወቅ በቂ ነው።
ውሃ ውስጥ ደግሞ አሳም እንቁራሪትም ይኖራሉ‼️ እባብም ጭምር። የውሃ ውስጥ እባብ ደግሞ መርዙ አይሽርም። ሆኖም መድሃኒቱ በእጃችን ነው‼️‼️‼️

Ethio-Analytics

15 Mar, 14:22


በጦርነት ቀጠና ውስጥ የነበሩ ተማሪዎችን ባልተረጋጋ ሁኔታ መፈተናቸው ሳያንስ ፈተና ተሰርቶ ከተሰጣቸው ተማሪዎች ጋር እኩል መመዘን ዓይናችን ጨፍኑ ላሙኛችሁ እንደማለት ነው።
ይህንን ያፈጠጠ ያገጠጠ ግፍና አድልኦ የምንሸከምበት ትክሻ ሊኖረን አይገባም።
የልጆቻችንን ተስፋ ሆን ብሎ ማጨለም ይብቃ።

ትምህርት ሚኒስቴር አስቸኳይ ማስተካከያ እና ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል።

Ethio-Analytics

15 Mar, 13:58


የትምህርት ሚኒስቴር ዓይን ያወጣ አድልኦ ‼️

በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሳለፉና ጦርነቱ ያስከተለው የስነልቦና ጫና ያለቀቃቸውን ተማሪዎች ፈተና ተሰርቆ ተሰርቶ ከተሰጣቸው ጋር እኩል መመዘን አይን ያወጣ አድልዎ ነው።

ግፉ ሞልቶ እየፈሰሰ ቢሆንም ለምን ብሎ የሚጠይቀው በጣም ጥቂቱ ነው።

ትምህርት ሚኒስትር በዚህ ጉዳይ ላይ ነገሩን በድጋሚ እንዳየውና ማብራሪያ እንድሰጥ መጠየቅ የሁሉም የህዝብ ተወካይና የምሁራኑ ታሪካዊ ግዴታ ነው!

የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎች ይህንን አድልዎ ለዓለም አሳውቁ።

የትውልድን ተስፍ መርጦ ማጨለም ይብቃ!

Ethio-Analytics

15 Mar, 13:55


Channel photo updated

Ethio-Analytics

15 Mar, 13:54


Channel created

1,240

subscribers

7

photos

1

videos