ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ) @yeferayemeles Channel on Telegram

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

@yeferayemeles


ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ) (Amharic)

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ) በተለይም የሚቀርበው ለሆፕ ውሳኔ ማህበረሰብን ከታመሙ ወይም ውስጣን ገልብጤን ባዩና በሚስጥ እንቅስቃሴ እርዳዋለን። በሚጠቀሱበት እና ልብ ለማገናኘት ምርመራን ከመረሩት አስደናቂ እና ስክረ፣ የእንግሊዝ እግር ጣቢያኑ ይጠናከቁና ከኛ ጋር ሊኖሩ ይችላሉ። ከተለያዩ መንገድ መላክ የውሳኔ ተጠቃሚ ስርጭቶችን በመሸፈኛ ህመም ላይ ማግኘት እና በፓስታ እንግሊዝን በመበላል ማንበብ የተደገፉትን ድምጻ አድኖ ጋር ይተወዋወሩ።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

23 Jan, 14:10


የእውነተኛ ወንድማማችነት ዋጋ ከአልማዝ ወይም ከወርቅ የበለጠ ውድ ነው!

ከአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የተሰጠ መግለጫና የአንድነት ጥሪ!

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር በመመስረቱ የተሰማነን ታላቅ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን፣ እንኳን ደስ አላችሁም እንላለን። አንድነት ባለበት ሁሌም ድል አለ። ምክኒያቱም አንድ ስንሆን ጠንካራ፣ ስንከፋፈል ደግሞ ደካማ ስለምንሆን ነው። ለብቻችን ታግለን የተወሰኑ ድሎችን ልናገኝ እንችል ይሆናል፣ አብረን ከታገልን ግን ሙሉ ድል እናመጣለን፣ የአማራ ህዝብን ከጭቆና ቀንበር ነፃ እናወጣለን።

በመካከላችን ልዩነት አይኖርም ማለት አይደልም። ሁሌም የስልት እና ፍላጎት ልዩነቶች ይኖራሉ። ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው። የድል አድራጊነት ዋናው መገለጫ በልዩነት ውስጥ አንድነት ፈጥሮ መታገል መቻል ነው። የትግል ስልታችንን አጣጥመን፣ ግለሰባዊ ፍላጎቶችን ገትተን አንድነት ማምጣት እና ትግላችንን በጋራ ማካሄድ ለነገ የማይባል ጉዳይ ነው። ከዚህ በላይ እኛ በአማራ ህዝብ ላይ የተጋረጠውን የህልውና አደጋ የመቀልበስ ግብን ያነገብን የህዝብ ልጆች ነን። ከዚህ ከትልቁ ግባችን አንፃር ሲታይ ያሉን ልዩነቶች ከዚህ ግባ የሚባሉ
አይደሉም።

በአንድ ላይ የቆሙ ትንሾች የተከፋፈሉ ብዙዎችን እንደሚያሸንፉ ሁሉ፣ ኃይላችን ያለው ከቁጥራችን መብዛት ሳይሆን በአንድነታችን ላይ ነው። የአማራ ህዝብ በቁጥር ብዙ ሆኖ እያለ እስካሁን ደካማ የሆነው አንድነት ባለመኖሩ ነው። በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ አንድነት የጎደለበትና የተሰባበረበት ምክኒያት ደግሞ የትግሉ ማዕከል የሆንነው እኛ አንድ መሆን ስላልቻልን ነው። በአንድ ስም ፋኖ ተብለን እየተጠራን፣ ለአንድ ዓላማ የአማራ ህዝብን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ እየታገልን አንድ መሆን ግን አልቻልነም። ይባሱን ከራሳችን ጋር ጉልበት ወደ መለካካት እና የእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ እየገባን ነው።

ጥያቄው ምርጫችን ላይ ነው። እንደ ወንድማማችነት አብሮ ታግሎ፣ አብሮ ማሸነፍ እና አብሮ መኖር ወይም
አሁን እንደምናደርገው እንደ ሞኝ ተነጣጥሎ እና ተጠላልፎ መጥፋትን የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምርጫው አንድ እና አንድ ብቻ ነው። እሱም እንደ ወንድማማችነት አብሮ ታግሎ፣ አብሮ ማሸነፍ እና አብሮ መኖር ነው። ይህን የእኛን ሀሳብ ሌሎች ወንድሞቻችንም ሀሳባቸው እንዲያደርጉት ጥሪ እያቀረብን
ከአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጋር የአንድነት ውይይት እንዲጀመር ጥያቄ እናቀርባለን። በአባቶቻችን መንገድ
ለአንድነት ተገዥ መሆን ያስፈልጋል። አንድነት ወደ ፊት ተጉዞ መሀል ላይ ለመገናኘት መወሰንን ይጠይቃል። የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ለእውነተኛ አንድነት ቅድመ ሁኔታ የለለው መሆኑን ለማሳውቅ እንወዳለን።

የጋራ ትግል፣ ለጋር ድል፣
ድል ለፋኖ፣ ድል ለአማራ ህዝብ፣
ራስ አርበኛ ደረጀ በላይ
የአማራ ፋኖ ጎንደር ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና አዛዥ

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

14 Jan, 10:45


የአፄ ቴዎድሮስን 206ኛ የልደት በዓልን አስመልክቶ ከአርበኛ ሀብቴ ወልዴ እና አርበኛ ባየ ቀናው የተላለፈ መልዕክት፦
"የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ስናስታውስ ከህሊናችን ቀድሞ የሚመጣው፤ በአንድ ስርዓት መተዳደር እና አንድነት ብቻ ነው።" አርበኛ ሀብቴ ወልዴ
  "አፄ ቴዎድሮስን ስናነሳ ውልደታቸው እና መነሻቸው ጎንደር ይሁን እንጅ፤ ታሪካቸው፣ ቆራጥነታቸው  በአጠቃላይ የሚነግረን ለሃገራቸዉ ለአንዲት ኢትዮጵያ ነዉ  " አርበኛ ባየ ቀናው

አርበኛ ሀብቴ ወልዴ " የታሪክ ፀሀፍት፣ ታሪክ አዋቂ አባቶቻችን  የዘመናዊት ኢትዮጵያ አባት" የሚባሉት አፄ ቴዎድርስ የአሁኗ  ኢትዮጵያ ለ 71 ዓመታት በመሳፍንት  ተከፋፍላ ስትገዛ ነበር። በሸዋ በወሎ በጎንደር በጎጃም መሳፍንቶች ተቀራምተው ይገዙ ነበር። ይህ ከፋፍለህ ግዛ አካሄድ  ለሃገሪቱ ስልጣኔ መድከም ፤  የቅኝ ግዢ እና የውጭ ወራሪ  መስፋፋትን፣  ሀገሪቱ አንድ ጠንካራ መሪ እንዳትፈጥር የማድረግ ጉዞ ነበር። ይህን የተገነዘቡት አፄ ቴዎድሮስ ከአንዴ ሁለቴ  ሸፍተው ከሞከሩ በኃላ በኋላ ሃገሪቱን አንድ ለማድረግ አርበኞችን ከየአቅጣጫው በማሰባሰብ  ቆርጠዉ  በመነሳት በውጭና በውስጥ የገጠማቸውን ፈተና በጣጥሰው  ሃገሪቱን አንድ በማድረጋቸዉ ዛሬም ድረስ የዘመናዊት ኢትዮጵያ አባት እየተባሉ ታሪካቸው ይዘከራል።

አፄ ቴዎድሮስ የሀገሪቱን አንድነት ያረጋገጡት የውጭ ወራሪን እና የውስጥ የተከፋፉሉ ሀይሎችን  በኃይል በማስገበር ነዉ። ንጉሱ ይሄን ሲያደርጉ ከፍተኛ የውስጥም የውጭም እንቅፋቶች የነበሩባቸው ቢሆንም ህልማቸውን ከማሳካት ግን ያገዳቸው አልነበረም። አፄ ቴዎድሮስን የተኩት ነገስታቶችም የውጭ እና የውስጥ ጠላቶችን በመቅጣት ሀገርን ጠብቀው ያቆዩን ሲሆን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመውረር ተሰልፈው ለነበሩ ሀይሎች በባንዳነት ሲያገለግሉ የነበሩ የውስጥ ባንዶች ወራሾች ዛሬም ድረስ ሀገራችንን በዘር በሀይማኖት በቋንቋ እየፈተኗት ይገኛሉ።

  ኢትዮጵያ በንጉሶቹ  ጊዜ የነበራትን ትልቅነት መልሳ ልታገኝ አልቻለችም።   እንደሃገር ለመኖር እንደ ሃገር ለማደግ  እና ህልውናን ለመታደግ የግድ አንድ መሆን አለብን።  ዛሬ እኛ ከአባቶቻችን መማር ሲገባን የእነሱን ራዕይ ወደ ጎን በመተው የዘመነ መሳፍንትን ራዕይ የወረስን መስለን እኔ ልግዛ በሚል ለትንንሽ ፈርኦን ገብሮ መኖር ህልውናችንን ማረጋገጥ አንባገነኖችን ማስወገድ  አንችልም። የንጉሱ ልደት የሚነግረን መልክቱ ይህ ነዉ ብሏል።

አርበኛ ባየ ቀናው በበኩሉ "አፄ ቴዎድሮስን ስናነሳ ውልደታቸው እና መነሻቸው ጎንደር ይሁን እንጅ፤ ታሪካቸው፣ ቆራጥነታቸው  በአጠቃላይ የሚነግረን   ለሃገራቸዉ ለአንዲት ኢትዮጵያ ነዉ።  ያችን በዘመነ መሳፍንት ክፉኛ ተከፋፍላ እና ተዳክማ የነበረችን  ኢትዮጵያን በዉድም በግድም አስገብረዉ፤ አንድ አድርገዉ፤ አሁን በጥቁር ጣሊያኖች እጅ የወደቀችውን  ኢትዮጵያን ያወረሱን አፄ ቴዎድሮስ ናቸዉ።

ስለሆነም የንጉሱን ልደት ስናስታውስ ንጉሱ የኢትዮጶያን አንድነት ለማምጣት ከፍተኛ ውጣ ውረዶችን በማለፍ ህልማቸውን ያሳኩበትን መንገድ  በማስታውስ በአሁኑ ጊዜ በተደቀነብን የውጭም የውስጥም ጠላቶቻችን አንድ እንዳንሆን እንዲሁም በተለያዩ አጋጣሚዎች ተቧድነን እየተጓተትን፣ በአደገኛ ወጀብ መሀል ያለንበት ክፉ ወቅት መሆናችንን በመገንዘብ አፄ ቴዎድሮስን እና የታላላቅ አባቶቻችንን ታሪክና ዝናንን በማስታወስ  አንድ ሆነን የህልውና ትግሉን እውን ማድረግ  ፤ ከአፄ ቴዎድሮስ፡ ብልህነትን፣  ጀግንነትን፣ ሩህሩህነትን፣  ቁርጠኝነት፣ ሩቅ ዓላሚነትን፣ ወኔና እና ጀግንነት ለኢትዮጵያ አንድነት ያሳዩትን ሥራ ሁላችንም በመውሰድ  ለያዝናው የህልውና ትግል እውን እንዲሆ ልናውለው ይገባል ሲል ገልጿል።

አርበኛ ሀብቴ ወልዴ
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ እና
አርበኛ ባዬ ቀናው
የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና ሰብሳቢ

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

28 Dec, 14:16


በአጅሬ ጃኖራ ጀብዱ እንደቀጠለ ነው


በአሁኑ ሰዓት በጃኖራ፣ በአጅሬ፣ በቀንጣ ማሪያም፣ በእንቃሽ ወይበይ፣ በአኖራ ወርቅ ደሞ አቅራቢያ፣ በጭላ፣ በደንከር ፣ በጧዋ ማሪያም እንደቀጠሉ ናቸው።

የጠላት ያለ የሌለ ሀይሉን በመካናይዝድ ከአየር ቅንጅት ጋር ያደረገው ውጊያ በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ሰሜን አንባራስ ክፍለ ጦር፣ ጭና ክፍለ ጦር፣ ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለ ጦር፣ ዘራይ ክፍለ ጦር፣ በአርበኛ ባየ የሚመራው ክፍለ ጦር፣ ጎንደሬው በጋሻው ክፍለ ጦር፣ ጎቤ ክፍለ ጦር በቅንጅት የገባውን ጠላት ከፍተኛ ሰዋዊ እና ቁሳዊ ውድመት አድርሰውበታል።

ይህ ውጊያ በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ ሀብቴ ወልዴ እንዲሁም አርበኛ ባየ ቀናው እና የዕዙ የበላይ ጠባቂዎች አባት አርርበኞች መሳፍንት ተስፉ፣ ሰፈር መለስ እና እሼቴ ባየ እየተመራ ሲሆን ጠላት በሄሊኮፕተር ቁስለኛ ወደ አዲስ አበባ እያመላለሰ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የጦር ወንጀለኛው የብልፅግና አገዛዝ ከታህሳስ 30 በፊት ፅንፈኛውን አፅድቼ ለፌደራል ፖሊስ እና ለክልል የፀጥታ ሀይል አስረክባለው ብሎ በማቀድ የመጨረሻ የሚለውን አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ቀጠናው ቢገባም ሁለንተናዊ ውድመት እያደረሰ ይገኛል። ጠላት የደረሰበትን ሽንፈት ለማካካስ ተራራ ላይ ሁኖ በእውርድንብር በሚተኩሰው የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ በንፁሃንና በገበሬ ንብረት ላይ ውድመት እያደረሰ እንደሆነም ተገልጿል።

ድል ለፋኖ
የፈራ ይመለስ

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

25 Dec, 15:02


ታላቅ የድል ዜና

የጦር ወንጀለኛው የብልፅግና ጦር በሰሜኗ መናገሻ ደባርቅ ከተማ በምትገኘውን የጥራሂና ከተማን ለመቆጣጠር ያለ የሌለ ሀይሉን አደራጅቶ ወደ ቀጠናው ቢገባም የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ በአርበኛ አለሙ መለሰ የሚመራው ድብ ጠለምት ተከዜ ክፍለ ጦር፣ በአርበኛ ሻምበል መሳፍንት የሚመራው ሰሜን አንባራስ ክፍለ ጦር እና በአርበኛ ዳንኤል አስረስ የሚመራው ጭና ክፍለጦር በቅንጅት ጠላትን ከበባ ውስጥ በማስገባት ከፍተኛ ሰዋዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰውበታል።

በዚህ አስደናቂ ውጊያ በርካታ የጠላት ሀይል ሲደመሰስ በርካታ ቁጥር ያለው ሲማረክ እና ሲቆስል ነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብቻ ወደ 200 ተማርኳል።

እስከዛሬ በርካታ ድሎችን ተጎናፅፈናል የሚሉት የዕዙ አመራሮች ይሄኛው ግን ከሁሉም የተለየ ታላቅ ድል ነው ያሉ ሲሆን መንገድ እየመራ ወደ ቀጠናው የገባው የሚሊሻ ሀይል አብሮ የጥቃቱ ሰለባ ሁኗል ብለዋል።

ከደባርቅ ጀምሮ ሰፊ ዝግጅት በማድረግ በቦዛና በጥራሂና ያለውን የፅንፈኛ ሀይል አፅድቼ ፊቴን ወደ አጅሬ ጃኖራ አዞራለሁ ብሎ በእቅድ ቢገባም እቅዱ ሳይሳካ ከፍተኛ ሽንፈትን በመከናነብ የተደመሰሰው ተደምስሶ የተማረከው ተማርኮ የቆሰለው ቆስሎ ቀሪው አስከሬንና ቁስለኛው እንዲሁም የያዘውን መሳሪያ እያዝረከረክ ወደ ደባርቅ እና ወደ ዛሪማ ከተማ ሊፈረጥጥ ችሏል።

አካባቢውን ከተህሳስ 30 በፊት አፀዳለሁ ብሎ የገባው የጠላት ጥምር ጦር መደመሰሱን የሰሙት ጀነራሎቹ መንገድ መሪው ሚሊሻ ከፋኖ ጋር ሁኖ ነው ያስመታን በማለት በርካታ ሚሊሻን የረሸነ ሲሆን ደባርቅ ከተማ የተቀመጡት የኦህዴድ ጀነራሎች እና ምስለኔ ካድሬዎች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል ብለዋል።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

02 Dec, 17:19


የዛሬ ዕለተ ሰኞ ሕዳር 23/2017 ዓ.ም.

የዕለቱን የጣና ዜናዎቻችን በተለመደው ሰዓት ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

በዕለቱ ዜናዎቻችን፦

…… የብልጽግና ሠራዊት ሁሉን አቀፍ ሽንፈት እየተጎነጨ ነው፡፡ በጦር ሜዳ ያጣውን ድል፤ በህዝብ ልብ ውስጥም እንጥፍጣፊ ከበሬታ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ ዛሬ ደግሞ ከከፍተኛ አመራሮቹ መካከል አንዱ የሆኑት ከፍተኛ መኮንን፤ ‹‹ከብልጽግናው አገዛዝ ጎን ተሰልፌ ወገኔን ከምዋጋ፤ ከወገኔ ጋር መከራን ብቀበል እመርጣለሁ›› በማለት ፋኖን ተቀላቅለዋል፡፡

እኒህ መኮንን ማን ናቸው የተቀላቀሉትስ በየትኛው ግንባር ያለውን ፋኖ ነው የሚለውን መረጃ በርዕሰ ዜናችን ይዘነዋል፡፡ ትሰሙታላችሁ፡፡

….. ዘመቻ ሰማዕታት በጎንደርና በሸዋ በድል ቀጥሏል፡፡ ከአዲስ አበባ 180 ኪሎ ሜትር ላይ ደብረሲና የተገኘው ድል ምን ይመስላል? በራስ አርበኛ ደረጀ በላይ የሚመራው የዐማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የደንቢያ የአለፋ ተጋድሎስ? ከጋይንት እስከ ደራ እና ፎገራ ባከለለው ሰፊ የውጊያ ቀጠና በየ አውደ ውጊያዎቹ የተገኙ ድሎች ምን ይመስላሉ? በዜናችን በስፋት የተዳሰሱ የግንባር መረጃዎች ናቸው፤ በዝርዝር እናስደምጣችኋለን፡፡

….. ወሎ ቤተ ዐማራ ዛሬም በድል ደምቋል፡፡ የጦር ጠበብቱ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃቤ የሚመሩት የዐማራ ፋኖ ወሎ እዝ፤ ‹‹ለስብሰባ የመጣውን የብልጽግና ሠራዊት፤ አስከሬኑን ሰብስቦ እንዲፈረጥጥ አድርጎታል›› ይላል ከቦታው የደረሰን የተጋድሎ መረጃ፡፡

ስድስተኛ ቀኑን ስለያዘው የአምባሰል ተራሮች ውጊያም አዲስ መረጃ ይዘናል፡፡ ወሰኝ ወታደራዊ ገዥ መሬቶችን ስለተቆጣጠረው የፋኖ ተጋድሎ ዝርዝር መረጃ ከዜናችን ታገኛላችሁ፤ ሰዓቱን ጠብቆ ወደእናንተ ይደርሳል፡፡

….. የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ወደ ሌላ ምዕራፍ ከፍ ያለበትን ታላቅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በህዝባዊ ድርጅቱ የተላለፈው ውሳኔ ምንድን ነው?

ዜናችን በዝርዝር ከሚያስደምጣችሁ መረጃዎች መካከል ቀዳሚው ነው ትሰሙታላችሁ፡፡

….. የጎጃም ቀጠና አሁንም ለብልጽግና ሠራዊት የእሳት ረመጥ እንደሆነበት ቀጥሏል፡፡ የደፈጣ ጠበብቶቹ የዐማራ ልጆች በጎጃም የፈጸሙትን ጀብዱ የጣና ዜና የተመለከተው ሌላው መረጃ ነው፤ ሰዓቱን ጠብቆ የሚደመጥ ይሆናል፡፡

………. እነዚህንና ሌሎች ዝርዝር የግንባር ውሎ ዜናዎችን ይዘናል፡፡ በትንታኔ የተመለከትናቸው ሌሎች መረጃዎችንም ይዘናል።

በሰዓቱ እንቀርባለን፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ፣ የትንታኔና ሌሎች ፕሮግራሞቻችን እንዲደርሷችሁ የማኀበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ገፆቻችን ተወዳጁ። የጣና ቤተሰብ ይሁኑ👍

ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን

ከሀቅ ጋር…!

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

28 Nov, 17:00


የዛሬ  ዕለተ ሐሙስ ሕዳር 19/2017 ዓ.ም. 

የዕለቱን የጣና ዜናዎቻችን ከደቂቃዎች በኋላ ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

በዕለቱ ዜናዎቻችን፦

…..ለዐማራ ህዝብ ህልውና ሲሉ በክብር የተሰው ውድ የአማራ ልጆችን የሚዘክረው፤ ‹‹ዘመቻ ሰማዕታት›› በታላላቅ ድሎች ታጅቦ ቀጥሏል፡፡ በጎንደር ግንባር ወንድማማቾቹ ዕዞች የጋራ ተጋድሎና ዝርዝር የግንባር ውሏቸውን በዝርዝር እናቀርብላችኋልን፡፡

…..አሥመራን ማዕከሉ ያደረገው የወቅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ፖለቲካ በዐቢይ አሕመድ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሽንፈት ላይ የተገነባ ነው ሲሉ ምሁራን ለጣና ሳተላይት ቴለኬቪዥን የሰጡትን ወቅታዊ ማብራሪያ እና የወቅቱን የአፍሪቃ ቀንድ ትኩሳት በትንታኔን ተመልክተነዋል፡፡

…. የኑሮ ውድነት እንደእሳተ ጎመራ ከሚጠብሳቸው የመንግሥት ሰራተኞች ውስጥ ሰፊውን ቁጥር የሚዙት መምህራን ‹‹እየራበን ወደክፍል አንገባም›› በሚል በተለያዩ አካባቢዎች ባልተደራጀ መንገድ የሥራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ ቆይተው የተጽዕኖ አድማሳቸውን ለማስፋት አገር አቀፍ የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ ዝግጅት ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ለመሆኑ ይህ የሥራ ማቆም አድማ ዝግጅቱ ምን ይመስላ…? አጠቃላይ ግቡስ ሥርዓታዊ ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ ረገድ በትግሉ ላይ የሚኖረው አንድምታ ምንድነው…?

የሚለውን በዜና ትንታኔችን ተመልክተነዋል፡፡ ትሰሙታላችሁ፡፡

….ወሎ ላይ አሁንም ፋኖ በድል መገስገሱን ቀጥሏል፡፡ ‹‹አንድነት ሀይል ነው›› በሚለው አማራዊ የፀና አቋም መሠረት፤ የዐማራ ፋኖ በወሎ እና የዐማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ የጋራ ኦፕሬሽኖችን አድርገዋል፡፡

ድላቸው ምን ይመስላል? የሚለውን በምስል ማስረጃ ጭምር በዝርዝር እናስቃኛችኋለን፡፡ ጠብቁን፡፡

…..ታሪካዊቷ ጭና ዛሬም በልጆቿ ክንድ ኮርታለች፡፡ በሰሜናዊው የጎንደር ቀጠና ሰፊ መሰረት የያዘው ጭና ክፍለ ጦር የብልጽግናን ሰራዊት ሲገርፈው ውሏል፡፡ የደፈጣ ውጊያ ጀብደኞች ተጋድሎ ምንድን ነው የሚለውን የግንባር ውሎ መረጃውን ዝርዝር መረጃ በዜናችን አካተነዋል፤ በሰዓቱ ወደእናንተ ይቀርባል፡፡

…..ጎጅም ላይ የብልጽግናው ሠራዊት በዐማራ አርሶ አደር ላይ የሚያደርሰው ግፍ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ብልጽግና በጎጃም በአርሶ አደሮችና መሰረተ ልማት ተቋማት ላይ ያደረሰውን ውድመትና የፈጸማቸውን የጦር ወንጀሎች በዝርዝር ቃኝተነዋል፡፡

በጎንደር ደባርቅ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ የወደመው ንብረትና የአርሶ አደሮችን አቤቱታም በዜናችን ተካቷል፡፡

…..በደብረጺዮን የሚመራው ቡድን ከብልጽግናው ፕሬዝዳንት ጋር ሌላ የጓዳ ስምምነት አድርጓል፡፡ ‹‹መቀሌን አውድመን ከ በሻሻ እኩል አድርገናታል›› በሚል የተሳለቁባቸውን የብልጽግናውን ፕሬዝዳንት አበክረው ደጅ በመጥናት ላይ ያሉት የዓድዋ ፖለቲከኞች፤ በቅድመ ሁኔታ ከብልጽግና ጋር የሚደራደሩበት ልዩ ሹመት ምንድነው? 

ቅድመ ሁኔታውና የኃይል አሰላለፉስ ምን ይመስላል? የሚለውን በዜና ትንታኔችን ተመልክተነዋል፤ በሰዓቱ ትሰሙታላችሁ፡፡

……….እነዚህንና ሌሎች ዝርዝር የግንባር ውሎ ዜናዎችን ይዘናል፡፡ በትንታኔ የተመለከትናቸው ሌሎች  መረጃዎችንም ይዘናል።

ከደቂቃዎች በኋላ እንቀርባለን፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ፣ የትንታኔና ሌሎች ፕሮግራሞቻችን እንዲደርሷችሁ የማኀበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ገፆቻችን ተወዳጁ። የጣና ቤተሰብ ይሁኑ👍

ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን

ከሀቅ ጋር…!

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

06 Nov, 13:42


የዛሬ ዕለተ ዕረቡ ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም.

የዕለቱን የጣና ዜናዎቻችን በተለመደው ሰዓት ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

በዕለቱ ዜናዎቻችን፦

……የዐማራ ፋኖ በጎጃም የወሰደው የተጠና ኦፕሬሽን የተሳካ ድል እንዲጎናጸፍ አድርጎታል።

በጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን የተዳሰሰ ቀዳሚው የዕለቱ ዜናችን ነው፡፡

***

……..የሚሊሻ ኃላፊውን ጨምሮ አስር ሚሊሻዎች ላይ እርምጃ የተወሰደበትን ታላቅ ኦፕሬሽን በዜናችን እናስደምጣችኋለን፡፡

***

……የዐማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በቋራ ታሪካዊ የተባለለት ቆይታ አድርገዋል፤ የትግል አቅጣጫዎችም ተቀይሰዋል፡፡

ለሁሉም ወንድም የፋኖ አደረጃጀቶች የትግል ጥሪዎች ቀርበዋል፡፡

በዕለቱ በትንታኔ የምንመለከተው ርዕሰ ዜናችን ነው፡፡

***
…… በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ይፋት ቀጠና የብልጽግና አገዛዝ የፈጸመውን የጦር ወንጀል በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይዘናል፡፡ ጠብቁን።

***

……የነ ሺመልስ አብዲሳ ቡድን ከዐማራ ነጻ የሆነች ወለጋን የመፍጠር ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡

ከወለጋ የደረሰንን የድረሱልን ጥሪ በዜናችን ተካቷል ትሰሙታላችሁ፡፡

***

…..የዐማራ ዲያስፖራ የራሱን የትግል ታሪክ እየጻፈ ነው፡፡ ከሰሞኑ ጠንካራ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡

የዲፕሎማሲ ትግል ግንባሩን በተመለከተ በዜና ትንታኔችን እንመለከተዋለን፡፡

……….እነዚህንና ሌሎች ዝርዝር የግንባር ውሎ ዜናዎችን ይዘናል፡፡ በትንታኔ የተመለከትናቸው ሌሎች መረጃዎችንም አካተናል።

በሰዓቱ እንቀርባለን፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ፣ የትንታኔና ሌሎች ፕሮግራሞቻችን እንዲደርሷችሁ የማኀበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ገፆቻችን ተወዳጁ። የጣና ቤተሰብ ይሁኑ👍

ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን

ከሀቅ ጋር…!

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

05 Nov, 14:38


ጣና ግንባር፦ "በሥነ-ልቦና እና በዲሲፕሊን የጠነከረ ሠራዊት ግንባታ ላይ ነን" "ዐማራ ታሪኩን ያድሳል

https://youtu.be/WzCQtl5EK6Y?feature=shared

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

04 Nov, 16:23


ጣና ዜና፦
ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም. በወልቃይት ጉዳይ አዲስ ነገር፤ የተደመሰሱ ወታደራዊ መሪዎች፤ ምስጢራዊው የብልጽግና ግምገማ መረጃ

https://youtu.be/ceAVY7npY4g?feature=shared

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

25 Oct, 08:34


" ደራ ጎድይ አርብዕለት ነው ይህ የተፈጠረው"😭
የኦሮሚያው ኦነግ ሸኔ ከአገዛዙ የመከላከያ ኦነግ ሸኔ ጋር በአይን ጥቅሻ ተናበው የአማራን ወጣት እንዴት  እየጨ#ፈጨፉት እንደሆነ አለም ላይ ያለ አማራ ብሎም የአማራ ተቆርቋሪ ሁሉ ልብ ሊለው ይገባል።

የተሰራብንን ግፍ አንረሳም ‼️

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

22 Oct, 04:41


ሰበር

ጥቅምት 11/2017

በአዲስ አበባ ምሽቱን በግዙፉ የገበያ ቦታ መርካቶ ከባድ የእሳት አደጋ ተፈጥሮ በርካታ መደብሮች በመቃጠል ላይ ናቸው።

እሳቱ በመርካቶ ሸማ ተራ የተነሳ ሲሆን፤ በርካታ መደብሮችን ከማውደሙ ባሻገር ወደህፃዎች በመዛመት ላይ ይገኛል።

በመድኒዋ ግዙፉ የገበያ ቦታ እንደዚህ ዓይነት የእሳት አደጋ አጋጥሞ እንደማያውቅ 'ይህ በዓይነቱ የተለየ ነው' ያሉት የዐይን እማኞች፤ ከአደጋው ጀርባ አገዛዙ እጁ እንደሚኖርበት ጥርጣሬቸውን ገልፀዋል።

ኦሕዴድ ብልጽግና የአዲስ አበባ ነባር የኢኮኖሚ ይዞታዎች ላይ ማንነትን መሠረት ያደረገ ንቅለ ተከላ ለመስራት የኮሪደር ልማት የሚል የዳቦ ስም በመስጠት የዜጎችን ሀብትና ንብረት በማፍረስ ላይ እንዳለ ይታወቃል። 

ከዋናው መንገድ ገባ ያሉ ቦታዎችን በተለይም የገበያ ማዕከላትን ደግሞ በእሳት አደጋ ስም መሰል ውድመት ማድረስ የኢኮኖሚ ንቅለ ተከላውን ለማሳለጥ እንደሚጠቀምበት ከሥርዓቱ ፋሽስታዊ ባህሪው መረዳት ይቻላል።

የብልጽግና አፈቀላጤዎች እሳቱን ለማጥፋት ሂልኮፕተር ለመጠቀም እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው ቢሉም እሳቱ በፍጥነት በመዛመት ላይ ነው። አደጋው ታቅዶበት የደረሰ እንደሚሆን የዐይን እማኞች ለጣና ቴቪ የአዲስ አበባ ሪፖርተር ተናግረዋል።

በጉዳዪ ላይ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን።

ጣና ሳተላይት ቴሌቪዥን

ከሀቅ ጋር …!

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

21 Oct, 16:39


https://youtu.be/DWXW3P8B9AE?feature=shared

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

25 Sep, 23:52


"እኔ ለስንታችሁ ዋ ብዬ ልሙት…?"

የጎንደር ቀጠና የአማራ ፋኖ ውጊያ እንደዶፍ ዝናብ መውረዱን ቀጥሏል፡፡ የትግል መዝገብ ማስታወሻችን እንደሚያረጋግጠው ያለፉት ሃምሳ አንድ ቀናት ያለማቋረጥ ውጊያ ተካሂዷል፡፡

ከሐምሌ 26/2016 እስከ ነሐሴ 25/2016 ድረስ ለአንድ ወር የቀጠለው ‹‹ዘመቻ አይሸሽም›› እጅግ ስኬታማ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ያ ዘመቻ የመተማውን ድል ያመጣ፣ የፋኖን ድል ዓለማቀፋዊ ሚዲያዎች ሳይቀር የዘገቡለት እንደነበር ይታወሳል፡፡

በመቀጠል የመጣው ዘመቻ ‹‹ዘመቻ ኖላዊት ዘገየ›› ነበር፡፡ ይህ ዘመቻ ለተከታታይ አምስት ቀናት ቀጠሎ ደምቢያ ሰቀልት ላይ የምዕራባዊያን ኢምባሲዎችና ዲፕሎማቶች በወታደራዊ አታሼዎቻቸው ትንታኔ ያሰሩበት ታላቅ ወታደራዊ ድል ተመዘገበ፡፡

አዲሱን የድል ዓመት ከተቀበልን ጀምሮ ከመናገሻ ጎንደር በመቶ ኪሎ ሜትር ራዲየስ 12 ቦታዎች ላይ መደበኛ የጦር አውደ ውጊያ ተካሂዶ የፋኖ የውጊያ ልኬት ስታንዳርድ የተቀመጠበት ድል ተመዘገበ፡፡
ይህ ድል፣ የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር Geneva, Switzerland,  በሚገኘው ዋና መቀመጫው ቢሮ ጠረጼዛው ላይ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዓለማቀፍ የጦር ሕግን ያከበረ፡- የምርኮኛ ተረከቡኝ ጥያቄ አጀንዳን ያስቀመጠ፣ የአማራ ትግል የመጨረሻው ከፍታ የታየበት ሆነ፡፡

የጎንደር ፋኖ በአደረጃጀት መለያየት የትግል ዓላማ ልዩነት ሳይፈጠርባቸው የድሉን መለኪያ ከፍ አድርገው ሰቀሉት፡- ስሜናዊው የጎንደር ግዛት ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገደብየ፣ አምባጊዩርጊስ፤ በምዕራባዊው የጎንደር ቀጠና ድፍን አርማጭሆ፣ መተማና ረዥሙ የሱዳን መዋሰኛ መስመር እስከ ቋራ ጥግ፤ ምስራቃዊው የጎንደር ቀጠና ኪንፋዝ በገላን ይዞ በለሳ መና መቀጣ ቆላ ሐሙሲት ተከዜ ጫፍ፤ ወደደቡባዊው የጎንደር ግዛት ጋይንት፣ ስማዳ፣ ሰዴ ሙጃ፣ ጉና፣ እስቴ ሁለቱም ወረዳዎች፣ ደራን አካልሎ፣ በማህደረማርያም እስከ ደብረታቦር ጫፍ የደረሰው ድል እጅን በአፍ ያስጫነ ነበር፡፡

ይህ ድል አሁን ድረስ መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በየቀኑ የማስታወሻ መዝገቤ ላይ የማሰፍራቸው የፋኖ ድሎች የዘመናችን የጀግንነት ፊደል በሥም ይገለጽ ቢባል የማን ተፅፎ የማን ሊቀር ነው በሚል ጭንቀት ውስጥ እገባለሁ፡፡

ለካ ወድዶ አይደለም… ፋሲል ደመወዝ ‹‹እኔ ለስንታችሁ ዋ ብየ ልሙት…?›› ያለው… የደረሰበት ያውቀዋል!!

በድል ቁንጣን ስላጨናነቁን ፋኖዎቻችን የጦር ሜዳ ውሎና ጀብዷቸው፡- ለትውልዱ መማሪያ፤ ለእውነተኛ የአማራ ብሔረተኝነት ግንባታ መሠረት አድርገን እንጠቀምባቸዋለን!!

ለሁሉም በጎንደር ቀጠና ቢፃፍ በቴራ ባይት የሚለካ የድል ታሪክ መሰራቱ ቀጥሏል!!

ብዙዎች መረጃው ያላቸው አልመሰለኝም ሁሉም የጎንደር ቀጠና የገጠር ቀበሌዎች ነጻ ወጥተዋል፡፡ ይህ መረጃ መናገሻ ጎንደርን ጨምሮ ለከተሞች የሚቀርቡ የገጠር ሳተላይት ቀበሌዎችን ጨምሮ ነው፡፡ ቀዩን መስመር ሳይጨምር ጎንደር ቀጠና 19 ወረዳ ሙሉ በሙሉ፤ 21 ወረዳዎች ደግሞ በከፊል በፋኖ ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡ የብልጽግና አራዊት ሰራዊት በዋና ዋና የዞን ከተሞች ተከማችቶ ይገኛል፡፡ በጠላት እጅ የሚገኙ የወረዳ ከተማ አስተዳደሮች በማንኛውም ጊዜ በፋኖ ቁጥጥር ስር ሊውሉ የሚችሉ እንደሆነ በተደጋጋሚ ውጊያዎች ታይቷል፡፡

እንደታች ጋይንት፣ ስማዳ፣ ሰዴ ሙጃ፣ እስቴ፣ ቋራ፣ ኪንፋዝ በገላ፣ በለላ ቆላው፣ …ባሉ ነጻ ወረዳዎች ለአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ ፋኖ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፎች ተካሂደዋል፡፡ የማዘጋጃ ቤት፣ የፍርድ ቤትና ሌሎች ማኀበራዊ ተቋማት አገልግሎት መስጠት የተጀመረባቸው ወረዳዎችም አሉ፡፡

የፋኖ አስተዳደራዊ ተቋም ምሁራንን ጭምር የሚያቅፍ በመሆኑ ነጻ በወጡ ወረዳዎች የምሁራን ሚና ጨምሯል፡፡ አማራ አሁን ትክክለኛውን የፖለቲካ ቁመና የሚያገኝበትን መዋቅር ከታችኛው የቀበሌ መዋቅር ጀምሮ በመዘርጋት ላይ እንደሆነ በጎንደር ቀጠና እያየን ነው፡፡

በቀጣይ የሌሎች የአማራ ግዛት ቀጠናዎችን መረጃ አጠናቅሬ እመለሳለሁ…

ያየነውን እንመሰክራለን! የምናውቀውን እንናገራለን!

©የፈራ ይመለስ

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

20 Sep, 10:24


ሰበር!

አጣናው ብርጌድ ካራማራ ብርጌድና አርበኞች ክፍለጦር  በጥምረት ስምሪት በርካታ የጠላትን ሀይል ሙትና ቁስለኛ እያረጉት ነው።
ቀጠናውን ለመቆጣጠር እያረጉት ባለው ተጋድሎ እስከአሁን ድረስ ከዙ 23 ጀምሮ ያሉ ጠላት ሚጠቀምባቸውን ከባድ መሳሪያወች እያቃጠሉ እየገሰገሱ ነው ።

ዝርዝር መረጃ ምናደርሳችሁ ይሆናል
የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ

መስከረም 10/2017

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 20:08


አሁን ይሄ የዘመናችን ከሀዲ ጎንደር ውስጥ ወጣት ይለቀም እያለ ነው። ትናንት ታስሮ እያለ ግን የጎንደር ወጣት አንገረብ ድረስ በእግሩ እየተጓዘ ነው የጠየቀው። ሲፈታም ፕሮግራም አዘጋጅቶ ነው የጠበቀው። ቢካድ ቢካድ የጎንደር ወጣት ይካዳል። ከእነዛ የዋህ ቤተሰቦችህ እውነት ተፈጥረሃል? መጨረሻህን ያሳየን።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 17:17


አርበኛ ሀብቴ ወልዴ (ትልቁ)

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ
ከተከታታይ ወታደራዊ ድሎች በኋላ ከ "አንከር ሚዲያ" ጋር ያደረገው ቆይታ በአጭሩ ሲቀርብ👇

❶. የድላችሁ ምስጥር ምንድ ነው…?

የድላችን ሚስጥር የምንታገልለት ዓላማ ፍትሐዊና እውነተኛ በመሆኑ፤ የአማራ ሕዝብ ድጋፍ ስላለን ነው፡፡

በጠላት በኩል ብንመለከት የብልጽግና አገዛዝ የከፈተው ጦርነት የዘር ማጥፋት ዓላማ ያለው፤ የብልጽግና ሰራዊት ደግሞ የሚዋጋለትን ዓላማ አያውቅም፡፡

ስለዚህ እኛ ለዓላማችን ለመሰዋት ቆርጠን ሕዝብን ደጀን አድርገን ነው የምንዋጋው፡፡ የብልጽና ሰራዊት ለምን እንደሚዋጋ እንኳ ሳያውቅ ወደሕዝብ የሚተኩስ፤ ከሕዝብ የተነጠለ አውሬ ነው፡፡

ውጊያው በሕዝብ ልጆች እና በሰይጣን ልጆች መካከል የሚደረግ ነው!

ሕዝብ ሁሌም አሸናፊ ነው!! ፋኖ ደግሞ የአማራ ሕዝብ ልጅ ነው፡፡ ከአማራ አልፎ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በተስፋ የሚጠብቁት የነጻነት ታጋይ ነው!!

በአጭሩ የድላችን ሚስጥር እኛ የምንሞትለት ዓላማ አለን፤ ጠላት ደግሞ የሚሞትለት ዓላማ የለውም፡፡ እኛ የሕዝብ ድጋፍ አለን፤ ጠላት ደግሞ ከሕዝብ የተነጠለ ብቻ ሳይሆን የአማራ መሬት የከዳው በመሆኑ ድሉ የእኛ ሆኗል!!

❷. ምርኮኞችን በተመለከተ…

በቅድሚያ የምርኮኛ አያያዛች ሰበዓዊነት ያለው ዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎችን ያከበረ እንደሆነ ዓለም እየታዘበ ነው፡፡ የዚህ መነሻ ግን የአማራ ባህል ነው፡፡

የአማራ ባህል በፋኖ ትግል ውስጥ ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ለዚህም ነው ሁለት ሦስት ጊዜ የማረክናቸውን ምርኮኞች ሳይቀር በእንክብካቤ የያዝናቸው፡፡

በእኛ በኩል ለምርኮኞች ስለትግላችን መነሻ፣ ስለ አማራ ሕዝብ ትክክለኛ ገጽታ፣ እናስተምራቸዋለን፡፡ ፍላጎት ያለው ትግሉን ይቀላቀላል፤ ፍላጎት የሌለውን ደግሞ ወደየ ቤተሰቡ እንሸኛለን፡፡ አሁን ግን ይህን ማድረግ የሚያስችል አቅም የለንም፡፡
የምግብ፣ መድሐኒትና አልባሳት ወጭውን አልቻልነውም፡፡ በፊትም ሕዝቡ ነው የሚቀልባቸው፤ አልባሳትና መድሐኒት የሚያቀርብ፡፡ አሁን ግን ቁጥሩ ስለበዛ የዓለም ቀይ መስቀል ማኀበር ሰብዓዊ እርዳታ እንዲያደርግ በይፋ ጠይቀናል፡፡

ወታደራዊ መረጃ በመሆኑ የምርኮኛ ቁጥር አልነግርህም፤ ነገር ግን አሁን በዚህ ሰዓት ራሱ የፈረሰው የብልጽግና ሰራዊት መማረኩን ቀጥሏል፡፡ ይህን ሁሉ ምርኮኛ ለመቀለብ አንችልም፡፡

እጃችን ላይ ያለው ምርኮኛ ቁጥር በዐቢይ አሕመድ እጅ ካለው ሊበልጥ ነው፡፡

አሁን እንደአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ፡- የምርኮኞች አስተዳደር መምሪያ ልናደራጅ አስበናል፡፡

ከምርኮኛው ብዛት አኳያ ራሱን ችሎ በመምሪያ ደረጃ መታየት ያለበት ጉዳይ ነው፡፡ ሥራ አስፈጻሚው ወስኖ ወደሥራ እንገባለን፡፡

❸. በጎንደር ቀጠና ዕለቱም ዕዞች የጋራ ኦፕሬሽንን በተመለከተ…

ለአንድ ዓላማ በጋራ እየተሰዋን ያለነው፡፡
በዚህ ትግል ውስጥ እንኳንስ ፋኖ ነኝ ብሎ በአደረጃጀት የታቀፈ ቀርቶ ለረዥም ዓመታት በጥቁር ደም የሚፈላለጉ ወገኖቻችን ደም እያደረቅን ወደትግሉ እያስገባን ነው፡፡

የኔ አንዱ ሥራ የትግሉን ሕዝባዊ መሰረት ማስፋት በመሆኑ እንኳንስ በሌላ አደረጃጀት ያሉ ወንድሞቼን ከፋኖ ውጭ ያለው አርሶ አደር፣ ወጣት፣…ሁሉም የትግሉ አካል እንዲሆን አመራር መስጠትና መከታተል ነው፡፡

ጥቁር ደም አድርቀን፤ ለአንድ ዓላማ የምናሰልፍ መሪዎች ነን፡፡ እና ሁለቱም ዕዝ ለአንድ ዓላማ በጋራ መስዋዕትነት እየከፈልን ድል እያዋሃደን ይሄዳል፡፡ ድል ካለ ፍቅር አለ! ድል ካለ አንድነት አለ! ለዚህ ሁሉ መሰረቱ ግን ለትግል የወጡበትን ዓላማ አለመርሳት ነው፡፡

እኛ የምንታገለው ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ነው! አማራነትን ማተቡ ያደረገ ወንድሙን አይከዳም! እኛ የአጼ ቴዎድሮስ ልጆች ነን! ቃል አለብን!!

ከአንድነት ውጭ ሌላ ቋንቋ አይገባንም!! ከቴዎድሮስ መንገድ አንወጣም!!


❹. ሕዝብ ከፋኖ ጎን መቆሙን አሳይቷል፡፡ ትግሉ በደረሰበት ምዕራፍ የሕዝብ ሚና ምንድነው…?

ሕዝባችን ከእኛ ጋር መሆኑን ደጋግሞ አሳይቶናል፡፡ የብልጽግናን ሴራ በሙሉ ተረድቷል፡፡

አሁን ዐቢይ አሕመድ እጁ ላይ የሴራ ካርዶቹን በሙሉ መዞ ጭርሷል፡፡ ርቃኑን ቀርቷል፡፡

ትግሉ አሁን በደረሰበት ምዕራፍ የሕዝብ ሚና፡-

አንደኛ፡- የትግሉ ባለቤት ሆኖ በፅናት እንዲቀጥል፣

ሁለተኛ፡- ሥርዓቱ የፈረሰ በመሆኑ በያለበት ተደራጅቶ ራሱን እንዲጠብቅ፣

ሦስተኛ፡- ትግሉ አድማሱን እያሰፋ በመሆኑ ወጣቶች አሁንም ፋኖን እንዲቀላቀሉ፣

አራተኛ፡- ምሁራን አሁን ሕዝባችሁን ለማገልገል ምትፈለጉበት ሰዓት ነው፤ ራሳችሁን አዘጋጁ
ነው የምለው፡፡

❺. ትግሉ የማይቀለበስ ደረጃ እንደደረሰ ተረጋግጧል፡፡ የብልጽግና ሰራዊት ተንዷል፡፡ በናንተ በኩል በፈረሰ ሥርዓት ውስጥ የእሳት ራት እንዳይሆን የምታስተላልፉት መልዕክት ካለ…?

ብአዴን ሞቷል፤ አሁን የቀረን መቅበር ብቻ ነው፡፡ ባህርዳር ያለው ካቢኔ የጨረቃ ካቢኔ ነው!
ለፖሊስ፣ ሚሊሻና አድማ ብተና የማስተላልፈው መልዕክት በፈረሰና በሞተ ሥርዓት ውስጥ አላስፈላጊ መስዋዕትነት አይከፈሉ፡፡ እጃቸውን ይስጡ!!

ከመቀበር ለማያድኑት ሙት ሥርዓት የውሻ ሞት አይሙቱ!!

በጊዜ እጅ ሰጥተው የምህረት አዋጃችን ተጠቃሚ ይሁኑ!!

❻.በመጨረሻም የቀረ መልዕክት…

አሁን ባለን የውጊያ ቁመና ጎንደር ከተማና ባህርዳር ለእኛ ኢምንት ናቸው!

የገነባነው ተዋጊ ኃይል ዐይኑ አራት ኪሎ ላይ ነው!!

ይሄ ኃይል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጦር የመሆን አቅም አለው!!

ዋናው የትግላችን ትኩረት የሞተውን ሥርዓት በመቅበር ላይ ነው፡፡ አፈር መመለስ ላይ ነን፡፡ አፈር መልሰን ከጨረሰን መንገዱ ክፍት ነው!!
በእርግጠኝነት የምናገረው የመጨረሻውን ሳቅ የሚስቀው አማራ ነው!

ስለዚህ ሕዝባችን የመጨረሻውን ሳቅ ለመሳቅ ከፋኖ ትግል ጋር በፅናት ይቀጥል!!

አመሰግናለሁ!!

ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ (ትልቁ)

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ
ጎንደር፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ

ሙለ ቃለ-መጠይቁ ከስር ተያይዟል
👇👇
https://youtu.be/dgDMNMBWK84?feature=shared

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 10:41


ብዙዎቹ በተለየ መንገድ የጎንደርን ህዝብ ያዋረዱ መስሏቸው በነገ በጠባ በለፈለፉ ቁጥር የተራራቀውን አቀራርበውታል፣ ያልገባውን እንዲገባው አድርገውታል፣ ወዳጅና ጠላቱን እንዲያውቅ አድርገውታል። ጌታቸው ረዳ እና ሽመልስ አብዲሳ የአማራን ህዝብ ከጫፍጫፍ እንዲነሳ እንዳደረጉት ይሄም ተመሳሳይ ነው።

ሌላው ለእንደነዚህ ዓይነቶቹ መልስ መመለስ አያስፈልግም። የሚፈልጉት ስማቸው ተጠርቶ እንደ ተፅዕኖ ፈጣሪ መልስ እንዲመለስላቸው ነው። በጭራሽ ስማቸውን የሚጠራው የለም። ትልቁ ቁም ነገር ጎንደር ላይ በደንብ ጠላትን እየቀጠቀጡ ማን እያጎረሰ እንደሚያስለፈልፋቸው ማወቁ ላይ ነው። ዋናው ጠላት አጉራሻቸው ነው።

ድል ለፋኖ

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 06:19


ጠላትን በቀይና በቢጫ ቀለም አቅልሞ መዝግቦ መያዝ ነው። ቀዩ ቀለም ወዳጅ ሊሆን የማይችል ጠላት ሲሆን በቢጫ ቀለም መዝግበህ የምትይዘው ደግሞ ወደ ወዳጅነት ሊቀየርም ላይቀየርም ይችላል። ወዳጅና ጠላቱን ለይቶ የሚጓዝ ሁሌም ውጤታማ ይሆናል። አማራ ሁሌም ማስታወሻና እና ቀይና ቢጫ እስክብሪቶ ከእጁ መለየት የለበትም።

ድል ለህዝባችን

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 05:30


ይሄ አዲሱ የፌስቡክ አካውንቴ ነው።

https://www.facebook.com/profile.php?id=61565171657961

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 05:05


ጎንደር ላይ ጠላት ሲቀጠቀጥ ገና ሰምተናቸው የማናውቅ ድምፆችን ሁሉ እንሰማለን። በይፋ ከብአዴን ጎን ሁነን ጎንደርን እናጠቃለን ሁሉ ሊባል ይችላል። አማራዎች አይግረማችሁ። የህውሃትም ሆነ የብልፅግናና እና የማደጎዎቿ ተስፋ ጎንደር ከተመታ ሌላው እዳው ገብስ ይሆናል ነው። ይሄ ደግሞ መሆን አልቻለም። ሊሆንም አይችልም። ገና የቀረ ጠላት ከጎንደር ምድር እየፀዳ ሲሄደድ አዳዲስ ክስተቶች ይከሰታሉ። መፍትሄው መልስ ሳትሰጥ ዝም ብለህ ምታ ነው።

ድል ለፋኖ

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

18 Sep, 05:01


ፌስቡኬ ተዘግቷል በአዲስ እስክመጣ በዚሁ መረጃዎችን አጋራለሁ።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

16 Sep, 16:28


ጀማል ሲሳይ ይባላል። የደባርቅ ከተማ ትም/ጽ/ ቤት ምክትል ሃላፊ ነው። መሀል ደባርቅ ላይ ሁኖ የሀይማኖት ግጭት ለመፍጠርና የፋኖን የህልውና ትግል ፅንፈኛ እያለ ለአለቆቹ ተላላኪነቱን እያሳየ ይገኛል። እንዲህ ዓይነቱ ፅንፈኛ ነው አገር እየበጠበጠ ያለው። እንግዲህ ከኛ ጥርስ ገብተሃል ተወጣው።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

16 Sep, 15:25


ይች ሰው ደባርቅ ትገኛለች። አብይ ሆይ ፋኖን በድሮን ጨፍጭፍልን እያለ ነው። በለፈለፉ ይጠፉ ነው ነገሩ።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

16 Sep, 14:33


የደምቢያ አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ
ጠላት የሱዳንን ኮሪደር አስከፍታለሁ በሚልና በባለፈው የደረሰበትን ምት ምክንያት በማድረግ በቀጠናው ያለውን ሁኔታ በአግባቡ በቁጥጥር ለማድረግ በአይነቱ ሰፋ ያለ ኃይል ከተለያዩ አካባቢዎች አጓጉዞ ነው ከባድ ትንቅንቅ እያደረገ ያለው ቢሆንም የጎንደር ዕዞቹ ከጯሂት በቅርብ ርቀት ላይ ቀድሞ እየተተራመሰ የመጣውን ኃይል አይቀጡ ቅጣት እየሰጡት ለእሱ ሽፋን ሊሰጥ የገባውን ኃይል ደረስጌ ላይ ቀድመው እየለበለቡት የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኃይል መግቢያ መውጫ አጥቶ ውሏል ከአዘዞ በቀጥታ የሚተኮስ ጀኔራል መድፍ በየአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ እንዳለ እስከአሁን በሰብአዊ ሰው ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በተመለከተ መረጃዎችን ለማጠናቀር ይሞከራል

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

16 Sep, 13:32


ሰበር ዜና

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ሰሜን አንባራስ ክፍለጦር በሻለቃ ሻምበል የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ይታየው ማሬ ብርጌድ በሻለቃ ንጉስ ፈረደ የሚመራው የአማራ ፋኖ ጎንደር በናሁሰናይ አንዳርጌ ብርጌድ በሻለቃ ዋናው አሙሀይ የሚመራ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ምስጋናው አጠኔ ብርጌድ በሻለቃ አገርነው ምስጋናው የሚመራ የዳባት ከተማን በጥምረት ተቆጣጥረውታል።በቀጣይ በዝርዝር ሙሉ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።

ዛሬ በዳባት ፀሀይ አትጠልቅም 💪💚💛❤️

ክብር ለጀግኖቻችን
አማራ በልጆቹ ታሪኩን ያድሳል

መረጃው የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ነው።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

16 Sep, 13:28


ፌስቡክ አስቸግሮኛል። ይሄን ቴሌግራም የምትከተሉ መልዕክቶችን አሠራጩልኝ።

ሙላት አድኖ(የፈራ ይመለስ)

15 Sep, 14:40


የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የቴሌግራም ገጽ
👇
👇
👇
https://t.me/AmharaFanoGonderCommand