ሉሊ የሰርግ ግጥሞች✍ @luliweddingpoems Channel on Telegram

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

@luliweddingpoems


ፍቅርን ለፈጠረ
ፈጥሮም ላስቀጠለ
በኒካህም ላገራው
ጌታ ሀምድ ይገባው!
ለአስታየትና ሀሳብ/ጥቆማ @luliweddingpoemsbot ይጠቀሙ።
@luliweddingpoems
https://ummalife.com/luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች✍ (Amharic)

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች✍ ላይ ተቆንፎአል። ይህ ግጥሞች የፍቅርን በፈጠረው ፊት እንዴት እንደሚቀጠለው እንደሆነ፣ ማንም በኒካህም ወረሰው በጌታ ሀምድ መሀሳብ እና ጥቆማ ምንም አላቸው። ስለዚህ እስከዚህ እምነት የሚገባበትን የሚናቁ መልኩን በማግኘት እርዳታ የሚያግዟባቸውን ወላጆች እና ጥቁሮች ለማግኘት በሚያግዝባቸው አስታወስ እንዲችል የሚረዳ ነን። luliweddingpoems ን እናገኛለን። https://ummalife.com/luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

14 Feb, 05:10


አሏህ ሆይ ለተባረከው ወር ረመዷን በሰላም አድርሰን። ደርሰውም ከሚጠቀሙበት አድርገን።
@luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

13 Feb, 15:25


ሴት ልጅ የራሷን ውበትና የቤቷን  ጽዳት ስትጠብቅ  ባለቤቷን ከማስደሰትም አልፎ ትዳራቸው  የስኬት ቁልፍ  ይሆናል !!!

(233 عشر النصحة النساء)

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

12 Feb, 03:20


በወርሃ ሸዕባን ምን እናድርግ?…
⚀ ጾም ማብዛት። ሰኞና ሀሙስ እና ሌላውንም መለማመድ። ለረመዳን መዘጋጀት።…
⚁ በቀደሙ ረመዳኖች ያመለጡንን ቀዷ ማውጣት።…
⚂ ከሰዎች ጋር እርቅ መፍጠር። ጥላቻና ቂምን መተው። የሰዎችን ሐቅ መመለስ። የረመዳንን በረከት ከሚያሳጡ መካከል መጥፎ ስነምግባር እና  የሰዎችን ሐቅ መጣስና በደል መፈፀም  ዋነኞቹ ናቸው።

اللهم بارك لنا فى شعبان وبلغنا رمضان

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

11 Feb, 06:51


የሰሀቦች ብልሀት

የሮም ንጉስ ለሙአውያ ረዲየላሁ አንሁ አንድ ትንሽ ብልቃጥ ላከና " ከሁሉም ነገር ሞልተህ ላክልኝ " ይለዋል ።
ሙአውያ ኢብኑ አባስን ሲያማክር ውሀን ሞልቶ እንዲልክለት ነገረው ። ከዚያም ለሮሙ ንጉስ ሲደርሰው በጣም በብልሀቱ ተገረመ ።
ለኢብኑ አባስም ይህን መልስ ከየት እንዳመጣው ሲጠየቅ ፦ " ከዚህ የአላህ ንግግር ነው " አለ

{وَجَعَلْنَا مِنَ ٱلْمَآءِ كُلَّ شَىْءٍ حَىٍّ }
« ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን»

📒المرجع الكامل للمبرد

@luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

03 Feb, 18:24


በአንድ መድረሳ ውስጥ ለሴቶች ስለ ሰደቃ ሰዎችን በማነሳሳት ዳእዋ አድርጋ እንደጨረሰች ታዳሚዎቹ ያላቸውን ገንዘብ መስጠት ጀመሩ።
    አንዲት ሴት የለበሰችውን ጌጥ አውልቃ ሰጠችኝ ዙርያው በአልማዝ የተጌጠና በጣም ውድ ነበር ለመቀበል ባንገራግርም በግድ እንድቀበላት አደረገችኝ። ሽጠን ገንዘቡን ለኸይር ነገር ለማዋል ወደ መሸጫ ሱቅ ወሰድነው። የሚገዛን የመስጂዳችን ጀመአ ስለነበር አልማዙንና ወርቁን ለመነጣጠል መፈልቀቅ ጀመረ በውስጡ የተጠቀለለ ፀጉርን አገኘን ሲህር የተሰራበት የተለያዩ የአረብኛ ቃላቶች የተፃፉበት ወረቀትም አብሮት ነበር። በነጋታው ይህን ጌጥ ሰደቃ የሰጠችን ሴት ወደኔ ቢሮ መጣች « በአላህ እምላለሁ ከባለቤቴ ጋር በአንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን ከተኛን አስራ ስድስት አመታትን አሳልፈናል ፤ የቤተሰባችን ፍቅርና ሰላም ተናግቶ የስቃይ ህይወት መኖር ከጀመርን ድፍን አስራ ስድስት አመታት ተቆጥረዋል ትላንት ይሄን ጌጥ ሰደቃ ከሰጠሁ በኋላ ቤተሰቡ በአንድ ማእድ ላይ ተሰብስቦ በፍቅር እራታችንን ተመገብን። ከባለቤቴም ጋር በደስታ አንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈን ተኛን ጌጡን የሰጡኝ በጣም የሚቀርቡኝ ጓደኞቼ ነበሩ» አለችኝ ሲህር ተሰርቶባት እንደነበር አወቅኩ አንድ አባባል  በአይዕምሮዬ አቃጨለ፦
   
   "ጠላትህን አንድ ጊዜ ወዳጅህን ደግሞ መቶ ጊዜ ተጠንቀቀው።"

ኢላሂ ያ ኢላሂ አንተው ጠብቀን

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

03 Feb, 17:31


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች ለዚህ ውድ መድረሳ የቻላችሁትን ነይቱ ለሌሎችም በማሰራጨት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።
ባረከሏሁ ፊኩም
@luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

02 Feb, 03:51


⛅️የማለዳ መልዕክት ⛅️

🍃 ከሰዎች ሁሉ ደስተኛ ማለት ምንንም ነገር ከሰው የማይፈልግ ፣ ከማንም ሰው ምንንም የማይጠብቅ ፣ ደስታውንም ከማንም ሰው ጋር የማያገናኝ ነው ።

ደስታን ፣ ውዴታን ፣ ሪዝቅን…  ከአላህ ብቻ በመፈለግ ውሏችሁን ጀምሩ ⛅️🌸🍃

{فَٱبْتَغُوا۟ عِندَ ٱللَهِ ٱلرِّزْقَ }
  «ሲሳይንም ከአላህ ዘንድ ብቻ ፈልጉ»
「 አል አንከቡት 17」

⛅️⛅️ መልካም ንጋት ⛅️⛅️
©

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

31 Jan, 15:31


የቀለበት አደራረግ

ሴት ልጅ የወርቅም ይሁን የብር ቀለበት በፈለገችው ጣት ላይ ማድረግ ትችላለች። ነገር ግን ቤት ውስጥም ይሁን ከቤት ውጪ ስትሆን ጌጧን ባዕድ/አጅነቢይ ወንድ እንዳያይ ጌጡን መሸፈን ግዴታ ይሆንባታል። ይህም የቁርኣን ህግና ትእዛዝ ነው።

ወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለብት ማድረግ አይችልም።
ከወርቅና ከብረት ውጪ ካሉ ነገሮች የተሰራ (የብርም ይሁን ሌላ) ቀለበት ሲያደርግ በመጨረሻው ትንሹ ወይም ከሱ ቀጥሎ ባለው ጣት እንጂ በመሃለኛው ረጅሙ ጣት፣ ከሱ ቀጥሎ ባለው ሌባ (አመልካች) ጣትና አውራ ጣት ላይ ለወንድ ልጅ ቀለበት ማድረግ አይቻልም።
በተለይ በመሃለኛው ረጅሙ ጣትና ቀጥሎ ባለው አመልካች ጣት ላይ ቀለበት ማድረግን ነቢዩ صلى الله عليه وسلم
በግልጽ ከልክለዋል።
ከመሆኑም ጋር ብዙ ወንዶች በነዚህ ጣቶች ቀለበት ሲያደርጉ ይታያል።
ዲናችንን እንወቅ! እውቀት ብርሃን ነው፤ አላዋቂነት ጨለማ ነው።

📖🖊📖 ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

ዛዱል-መዓድ
https://telegram.me/ahmedadem
@luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

29 Jan, 18:19


ሙብሩክ አልፈ መብሩክ
ባረከሏህ ለከ
ባረከሏህ ለኪ
ወጀመዓ ለከ
ወጀመዓ ለኪ

ከሀራሙ መንገድ ክስረት
የሀላሉን መንገድ ትሩፋት
የሚናፍቁ  ምነኛ ታደሉ
እንኳን ለዚ በቃሸልን
የሰመረ ጥምረት    
        እስከጀነት
  ራኒዬዬዬዬ🌹
    
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

                              رانية
                       
                                      و  

                            عبدالحميد
                              
        🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀 

                                  بارك الله لكما  
                                   وبارك عليكما
                                    وجمع بينكما
                                       فى الخير

💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

           
   🎉 ራኒያ እና ዓብዱልሀሚድ🎉

رجب ١٤٤٥
From Luly
@luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

26 Jan, 19:09


<><><><><><><><><><><><><><><><>
ጀግናዋ እህቴ ሆይ ትዕግስት አድርጊ + ለአላማሽ ዛሬም ከትላንቱ የተሻለ ጠንክረሽ ስሪ + ሚስጥርሽን ሸሽገሽ በዝምታ ተራመጂ +ጉዳይሽንም ሁሉ ለአሏህ አደራ ስጪ።
<><><><><><><><><><><><><><><><>

@luliweddingpoems

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

26 Jan, 07:20


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ».

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

25 Jan, 19:37


በመንገዳችን ላይ ሳለን ሙስሊም ወንድምን ወይም እህትን ማየት ምን ያህል ደስታን ይሠጠናል? ይበልጥ ደግሞ ለኛ በሚታየው በውጭ ገፅታ ከኛ የተሻለ ሰው ሲሆን ስሜቱ እንዴት ነው ?

እስቲ ግለፁት…

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

23 Jan, 19:33


رمضان ተናፋቂው እንግዳችን
49 .............. ቀናት አካባቢ ይቀረዋል

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

23 Jan, 19:19


ሉሊ የሰርግ ግጥሞች pinned «ረመዷን……………… ቀርቧልና ምን ያህል ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው? ምንስ አቅደናል? እንዴት ለማሳለፍ አስበናል?»

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

23 Jan, 19:17


ረመዷን……………… ቀርቧልና
ምን ያህል ቅድመ ዝግጅት እያደረግን ነው?
ምንስ አቅደናል?
እንዴት ለማሳለፍ አስበናል?

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

21 Jan, 04:48


🍁 ሁለት ባህሪያቶች በአንድ ባሪያ ልብ ውስጥ አይሰባሰቡም ፣ ኢማንና ምቀኝነት።
ረሱል ﷺ

ሉሊ የሰርግ ግጥሞች

20 Jan, 16:35


🔶 ለፈገግታ ያህል…

🔹በአንድ ወቅት ኢብኑ ባቅላኒ የሮም ንጉሰ ዘንድ ሆኖ አንድ ባህታዊን ፦ " ባለቤትህ ልጆችህ እንዴት ናቸው ?? " ብሎ ይጠይቀዋል። ከዚያም ንጉሱ ቆጣ ብሎ እንዲህ ይለዋል ፦  " እንዴ ምን ማለትህ ነው !?? አንድ ባህታዊ ከእንደዚህ አይነት ተግባር የጠራ መሆኑን አታውቅም !? "  ከዚያም ኢብኑ ባቅላኒ ፦

" ትገርማላችሁ ይህን ከእንደዚህ አይነት ተግባር አጥርታችሁ የአለማት ጌታን ግን ከልጅና ከሚስት አታጠሩም !!! "

📙 سير أعلام النبلاء
ክርስትያኖች ሆይ ንቁ!!

3,195

subscribers

64

photos

22

videos