✍️በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
[በሊቁ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ መጻሕፍት]
[እመቤታችንን ስለመውለዷ]
❖“ሰላም ለሐና እንተ ወለደታ ለማርያም
ዘኮነት ተንከተመ ጽድቅ ለኲሉ ዓለም፤
ድንግል ወእም፤
ወላዲቱ ለፀሓይ
ዳግሚት ሰማይ”፡፡
(ፀሓይን የወለደችው ኹለተኛዪቱ ሰማይ፤ ድንግልም እናትም፤ ለዓለሙ ኹሉ የእውነት ድልድይ (መሸጋገሪያ) የኾነችዪቱን ማርያምን ለወለደቻት ለሐና ሰላምታ ይገባል) (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በተአምሆ ቅዱሳን)
♥️[ቅድስት ሐና እመቤታችንን ስለፀነሰችበት ዕለት]
❖♥️ “ወይእዜኒ ኦ ውሉደ እግዚአብሔር ወማኅበረ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናስተብፅዖሙ ለሐና ወለኢያቄም ዘወለዱ ለነ ዛተ ቡርክተ ወቅድስተ መርዓተ፤ አይ ይእቲ ዕለት ዕለተ ሩካቤሆሙ ንጽሕት እንተ ባቲ ሐንበበት ፍሬ ቡርክተ ድንግልተ አስራኤል ኢጽዕልተ፤ አይ ይእቲ ዛቲ ዕለት ቅድስት ዕለተ ድማሬሆሙ ለእሉ በሥምረተ እግዚአብሔር ተገብረ ተፀንሶታ ለርግብ ንጽሕት ዘእምቤተ ይሁዳ፤ አይ ይእቲ ዕለት ዕለተ ፍሥሓ እንተ ባቲ ኮነ ተመሥርቶ ንድቅ ለማኅፈደ ንጉሥ”
(አኹንም የእግዚአብሔር የጸጋ ልጆችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማኅበሮች ሆይ ይኽቺን የተባረከችና የተመረጠች ሙሽራ የወለዱልንን ኢያቄምንና ሐናን እናመስግናቸው የማትነቀፍ የእስራኤል ድንግልን የተባረከችዋን ፍሬ ያፈራችበትን ንጽሕት የምትኾን የሩካቤያቸው ዕለት እንደምን ያለች ዕለት ናት? ከይሁዳ ወገን ለኾነችው ንጽሕት ርግብ መፀነስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ የጾታዊ ተዋሕዷቸው ቀን ይኽቺ እንዴት ያለች የተመረጠች ቀን ናት፤ ለንጉሥ ማደሪያ አዳራሽ መመሥረት የተደረገባት (የኾነባት) የደስታ ቀን እንዴት ያላት ቀን ናት?) (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አርጋኖን ዘረቡዕ)
♥️[የኢሳይያስ ትንቢት ቅድስት ሐና በወለደቻት በእመቤታችን ስለመፈጸሙ]♥️
❖ ♥️ በከመ ፈቀደ ወአልቦ ዘይከልኦ ገቢረ ዘኀለየ በከመ ጽሑፍ ዘይብል ትወፅእ በትር አምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምጒንዱ ምንት ውእቱ ፀአተ በትር እምሥርወ ዕሴይ ወየዐርግ ጽጌ እምጒንዱ ምንት ውእቱ ፀአተ በትር እምሥርው ዘእንበለ ዘርዐ ሙላድ ዘቅድስት ድንግል እንተ ኮነት እምኀበ ኢያቄም ውስተ ማሕፀነ ሐና እስመ ዘርዐ ዕሴይ ውእቱ ኢያቄም አቡሃ ለማርያም ወምንትኑመ ካዕበ ዕርገተ ጽጌ እምጒንድ ዘእንበለ ሥጋዌ መለኮት እምወለቱ"
(ከዕሴይ ሥር በትር ትወጣለች፤ ከግንዱም አበባ ይወጣል የሚል እንደተጻፈ፤ ያሰበውን ለማድረግ የሚከለክለው የለም፤ ከኢያቄም አብራክ ተከፍላ በሐና ማሕፀን ከተፀነሰች ከቅድስት ድንግል የትውልድ ዘር በቀር የበትር ከሥሩ መውጣት ምንድን ነው? የእመቤታችን የማርያም አባቷ ኢያቄም ከዕሴይ ዘር ነውና፤ ዳግመኛም ከኢያቄም ሴት ልጁ የመለኮት ሰው መኾን በቀር የአበባ ከግንዱ መውጣት ምንድን ነው?) (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፤ መጽሐፈ ምስጢር)
♥️ [ስለ ቅድስት ሐና የሊቁ የአባ ጽጌ ድንግል ምስክርነት] ♥️
❖[ቅድስት ሐና እመቤታችንን ስለፀነሰችባት ዕለት]
“ሚ ቡርክት ወቅድስት ይእቲ
ሰዓተ ትፍሥሕት ሐና ዘጸገየተኪ ባቲ
ወፈረየኪ ለሕይወት ኢያቄም መዋቲ
እሴብሕ ተአምረኪ ርግብየ አሐቲ
ወድኀኒተ ኲሉ ዓለም እስመ ኮንኪ አንቲ”
(ሐና አንቺን የፀነሰችባት የደስታ ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ ሟች ኢያቄምም ለሕይወት አንቺን ያፈራባት ቀን ምን ያኽል የተባረከች የተቀደሰች ናት፤ አንዲቱ ርግቤ ማርያም አንቺ የዓለሙ ኹሉ መድኀኒት ኾነሻልና ታምርሽን አመሰግናለኊ) (ማሕሌተ ጽጌ)
♥️♥️[ስለ ሐና ማሕፀን]♥️♥️
“ጸግይየ ሣዕረ ዘኪሩቤል ልሳነ
ተአምረኪ በነጊር እመ ኢፈጸምኩ አነ
ባሕቱ አአኲት ማርያም ዘጾረተኪ ማሕፀነ
እንዘ ሀለወት ፀኒሳ ኪያኪ ርጢነ
ለለገሰስዋ ላቲ ትፌውስ ዱያነ”
(ሳርን የኾንኊ እኔ የኪሩቤል አንደበትን ገንዘብ አድርጌ ታምርሽን በመንገር በማስተማር ባልፈጽምም ነገር ግን ማርያም የተሸከመቺሽን የሐናን ማሕፀን አመሰግናለኊ፤ መድኀኒት አንቺን ፀንሳ ሳለች ርሷን የዳሰሷትን ድዉያንን ኹሉ ትፈውስ ነበር) (ማሕሌተ ጽጌ)
♥️[ስለ ሐና አበባ ስለ ድንግል ማርያም]♥️
♥️“ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ
በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ
ማእከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ እንዘ እነቡ
እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዐጽ እሌቡ
ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ”
(ትንቢት ከተነገረለት ከአንበሳ ጉድጓድ፤ ድንግል ሙሽራ በተገኘሽ ጊዜ የንጉሦች ንጉሥ የሰሎሞን ልቡ እንደተደሰተ፤ ደስ ባላቸው በመላእክት አንድነት ፊት ታምርሽን እየተናገርኊ የሐና አበባ ማርያም እዘምርሻለኊ፤ ወተትን ጠብቶ እንደሚዘልል እንቦሳም ዝለል ዝለል ይለኛል) (ማሕሌተ ጽጌ)
♥️[ቅድስት ሐና እመቤታችንን ይዛ ወደ ቤተ መቅደስ ስለመግባቷ]♥️
❖“የሐዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ እንዘ ትጠብዊ ሐሊበ ሐና
ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልህቀትኪ በቅድስና
ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና
ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና”
(ማርያም የሐናን ወተት እየጠባሽ ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ያገኘሽ ብቸኝነት ያሳዝነኛል፤ ዳግመኛም በደመና የሚመላለስ ደመናን የሚረግጥ የእሳት አበባ ፋኑኤል ከጓደኞቹ መላእክት ጋር መናን እየመገበሽ በንጽሕና የማደግሽ ተአምር ደስ ያሰኘኛል) (ማሕሌተ ጽጌ)
[በሊቁ በዐርከ ሥሉስ ለቅድስት ሐና የቀረበ ውዳሴ]
❖♥️ "ሰላም ለኪ ለጸሎተ ኩሉ ምዕራጋ
ከመ አስካለ ወይን ዲበ ሐረጋ
ሐና ብፅዕት ተፈሥሒ እንበለ ንትጋ
እስመ ረከብኪ ሞገሰ ወአድማዕኪ ጸጋ
እምሔውተ አምላክ ትኩኒ በሥጋ"
(በሐረጓ ላይ እንዳለች የወይን ፍሬ ለጸሎት ኹሉ መውጫዋ ለኾንሽ ሰላምታ ይገባሻል፤ በሥጋ የአምላክ አያት ልትኾኚ ሞገስና ጸጋን ያገኘሽ ያለ ጉድለት ብፅዕት የኾንሽ ሐና ደስ ይበልሽ) [ዐርከ ሥሉስ፤ ዐርኬ]
በነግሥ ላይ፦
❖♥️ "ክልኤቱ አእሩግ አመ በከዩ ብካየ
ረከቡ ወለተ ዘታስተሰሪ ጌጋየ
ለወንጌላውያን ኩልነ ዘኮነተነ ምጉያየ
ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ"
(ኹለቱ አረጋውያን ልቅሶን ባለቀሱ ጊዜ ለኹላችን ወንጌልን ለምናስተምር መሸሻን የኾነችን በደልን በምልጃዋ የምታስደመስስ ልጅን አገኙ፤ ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማያቸውም ፀሐይን አወጣች) (ነግሥ)