-------------------------------------------
መስከረም 6/2017 ዓ.ም ሐ.ተ.ሚ ( አዳማ - ኢትዮጵያ )
በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት በአዳማ ናዝሬት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ ሁለገብ ሕንጻ ሊገነባ ሲሆን የሕንጻውም ዲዛይን ይፋ ሁኗል፡፡
መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ማርቆስ ብርሃኑ የአዳማ ናዝሬት ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል አስተዳዳሪ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው እንደገለጹት በግቢ ውስጥ ሊሠራ የታሰበው ሕንጻ G+6 ሲሆን በ800 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፉ ሲሆን ይኽን ሁለገብ ሕንጻ መሥራት እንዲቻል አጠቃላይ ኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ አሻራቸውን የሚያስቀምጡበት በዓይነቱ ልዩ የሆነ ከኅዳር 7 - 10/2017 ዓ.ም መንፈሳዊ ባዛር ይካሄዳል ብለዋል፡፡
ሁለገብ ሕንጻው ሲጠናቀቅ ከሕንፃው በሚገኘው ገቢ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን በመርዳት ፡ እጓለ ማውታን (ወላጅ አልባ) ሕጻናትን በማገዝ ፡ አቅመ ደካማዎች አረጋውያንን በመርዳት ፡ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት፡ የካቴድራሉን ሠራተኛ ኑሮ በማሻሻልን ረገድ አገልግሎቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምስሉን ያደረሱን ፡- ሊቀ አእላፍ መ/ር ደረጄ ታዬ እናመሰግናለን፡፡
ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ( አዳማ - ኢትዮጵያ)
መስከረም 6/2017 ዓ.ም
Telegram:- ቻናሉን ይቀላቀሉ https://t.me/hameretewahedo
Youtube:- ሰብስክራይቭ ያድርጉ https://www.youtube.com/channel/UCosQ9gywx0VAqiUm80oJ3rA
Tiktok :- ፎሎው ያድርጉ tiktok.com/@hameretewahedomedia