Ethio 360 Media @ethio360degree Channel on Telegram

Ethio 360 Media

@ethio360degree


ይህ የኢትዮ 360 ቴሌግራም ቻናል ነው

Ethio 360 Media (Amharic)

ኢትዮ 360 ሚዲያ ቴሌግራም ብቻ ነው በዚህ ቦታ፣ እግር ኳስ መስመር ከኮም አፕሊኬሽን ጋር ከፍተኛ ተጨባጭ ሊከተለፍ የሚያስችለው። ወደ የቴሌግራም ዝግጅት እና ጥሰቶች እንዲያምን ስለሚችልበት ሲባል የኢትዮ 360 ሚዲያ ቴሌግራም ጀመርን፣ ኢትዮጵያውያን እና ውሃ ድንቅ ከሚመስልን የቴሌግራም ቻናል ላይ በደም እያለ የመሠረት ነው። በእነሱ እርምጃዎችና ውዝን በመስራት ያለብንን የቴሌግራም ጉዳይ ለማቃረብ እንዲችል፣ እንዲታይ እንዲሻሻቅን እና እንዲሰለጥ ይህን መረጃውን ይከፈትለናል።

Ethio 360 Media

20 Nov, 22:16


https://www.youtube.com/live/zBfPnfZAnOE?si=0ih7nIK0g4cYq33H

Ethio 360 Media

20 Nov, 21:41


https://www.youtube.com/live/BlmHI9CWVDs?si=bxSulkovPYtNdvxI

Ethio 360 Media

20 Nov, 08:56


https://youtube.com/live/YopFlWx51os?feature=share

Ethio 360 Media

19 Nov, 18:03


https://www.youtube.com/live/s-Wk3FZs3N4?si=wjIFjczngSjNsNjK

Ethio 360 Media

19 Nov, 17:36


https://www.youtube.com/live/CLUMYRNCiPQ?si=yQ51Yhe7Aa8fVey6

Ethio 360 Media

19 Nov, 17:23


https://www.youtube.com/live/CLUMYRNCiPQ?si=yQ51Yhe7Aa8fVey6

Ethio 360 Media

18 Nov, 21:05


https://youtube.com/live/YnqLI2mkDJQ?feature=share

Ethio 360 Media

18 Nov, 17:55


https://www.youtube.com/live/jnEF2U9H0tU?feature=shared

Ethio 360 Media

17 Nov, 19:18


https://www.youtube.com/live/bqg4liYUbEY?feature=shared

Ethio 360 Media

17 Nov, 18:29


https://www.youtube.com/live/bqg4liYUbEY?si=Pd2lup2DT54ti7UV

Ethio 360 Media

17 Nov, 18:21


ከፍኖተ ሰላም ወደ መንዝ አቅጣጫ እንቀሳቀሳለሁ ያለው የሰው በላ ቡድን በፋኖ ጥይት ተራገፈ።

(ኢትዮ 360 - ሕዳር 8/2017)የአማራ ፋኖ በጎጃም አምስተኛ ክፍለ ጦር ወይንም የራስ መንገሻ ቢትወደድ አቲከም የአረንዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተ ሰላም ሻለቃ ከፍኖተ ሰላም ወደ መንዝ አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ የሞከረውን ገዳይ ቡድን ከአምስት በላይ የሚሆነን እንዳይመስ ሸኝተው ከ10 በላይ የሚሆነውን ማቁሰላቸውን አመራሮቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።

የሰው በላው ቡድን ከነበረበት ቀጠና ወደ መንዝ አቅጣጫ ለመጓዝ ከ100 በላይ ሃይል ይይዞ ቢመጣም በፋኖ ሙሉጌታ የሚመራው ፍኖተሰላም ሻለቃ ዘገየ ባህርዛፍ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደፈጣ ከመንገድ አስቀርቶታል ብለዋል።

በዚህም ከ5 በላይ የሚሆነው እንዳይመለስ ሲያደርገው ከ10 በላይ የሚሆነውን አቁስሎ ወደ መጣበት እንዲፈረጥጥ መደረጉን ገልጸዋል።

በመፈርጠጥ ላይ የነበረው ይሄ ሰው በላ ቡድን ለሽንፈቱ ቂም መወጫ ሁለት አርሶ አደሮችን ከቤት አውጥቶ በአደባባይ መረሸኑንም አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምዕራብ ጎጃም ሃገረ ስብከት በሚገኙት ልደታ ለማርያርያምና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ የአብነት ተማሪዎች በሰው በላው ቡድን ሃይል እየታፈኑና ካሉበት እንዲሳደዱ እየተደረጉ መሆኑን አመራሮቹ አመልተዋል።

ትላንት ብቻ ከ300 በላይ የሚሆኑ የአብነት ተማሪዎች ሲታፈኑ ሌሎቹን ደግሞ እንገላችሁዋለን በሚል ከአካባቢው እንዲበተኑ መደረጉን አስታውቀዋል።

በትንሹ ከ6 መቶ ያላነሱ የአብነት ተማሪዎች በዚህ ቡድን መበተናቸውን ገልጸዋል።

እዛው ፎኖተ ሰላም ውስጥ የፈለገ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎችን፣አስተማሪዎችንና አገልጋዮችንም ከየአብያተ ክርስቲያናቱ እያሳደደ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይሄ ገዳይ ቡድን ሌሎቹን ከማፈኑና ከማሳደዱ በፊት ቁጭ ላይ ከመድሃኒአለም ቤተክርስቲያን 15 የአብነት ተማሪዎችን መረሸኑንም አስታውሰዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ባለፉት ሶስት ቀን ብቻ ከ82 በላይ የሚሆኑ የኦህዴዱ አባላት የፋኖ ሃይልን መቀላቀላቸውንም አስታውቀዋል።

በተለይ የወንድ አወቅ ብርጌድ ብቻ ከ42 በላይ ሃይሎችን ሲያስከዳ ከነሙሉ መሳሪያቸውና ከአንድ ብሬልና አንድ ስናይፐርን በአንድ ቀን ወደራሱ ማድረጉንም ለኢትዮ 360 ገልጸዋል።

Ethio 360 Media

17 Nov, 15:34


ብርሃኑ ጁላ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው ጦርነት እስከ ታህሳስ 30 መጠናቅቅ አለበት አለ።

(ኢትዮ 360 - ሕዳር 8/2017) በባህርዳር ብርሃኑ ጁላ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት እስከ ታህሳስ 30 ካልተጠናቀቀ የኦህዴዱን መከላከያ ሙሉ በሙሉ ከክልሉ እናስወጣለን ሲል መዛቱን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አጋለጡ።

በከተማዋ በብርሃኑ ጁላና እና በአረጋ ከበደ ይመራ የነበረው ስብሰባ እና ግምገማ ላይ ተገኝተው የነበሩት የእዝ መሪ ጀነራሎች እንደነበሩ ይናገራሉ።

እናም ዛሬ ይሄ ስብሰባና ግምገማ ሲጠናቀቅ ብርሃኑ ጁላ ሶስት ውሳኔዎችን በግልፅ በመድረኩ ላይ አስቀምጧል ይላሉ።

አንደኛው እስከ ታህሳስ 30/ 2017 ድረስ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ጦርነት ማጠናቀቅ ካልተቻለ የኦህዴዱን መከላከያ እናስወጣለን በሚል በመድረኩ ላይ በግልፅ ያሳለፈው ውሳኔ ነው ይላሉ የውስጥ ምንጮቹ።

ሁለተኛው ደግሞ ጦርነቱን ማሸነፍ ያልቻልነው በአረጋ አመራሮች ምክንያት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን ያስቀመጠበት ነው ብለዋል።

ስለሆነም አረጋ አመራሮቹ ላይ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጥብቅ መመሪያ የሰጠበት ሁለተኛው ውሳኔ ነው ሲሉ የውስጥ ምንጮቹ አጋልጠዋል።

ሶስተኛው የብርሃኑ ጁላ የስብሰባና የግምገማ ማጠቃለያ ውሳኔ ከወለጋ የሚንቀሳቀስ አንድ ኮር የገዳዩ ቡድን ሃይል ወሎና ጎጃም ላይ ይሰፍራል የሚለው መሆኑን የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች አጋልጠዋል።

Ethio 360 Media

17 Nov, 14:26


በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ ሩጫ ላይ እንሳተፋለን ብለው የወጡ በርካታ ወጣቶች ታፈኑ።

(ኢትዮ 360 - ሕዳር 8/207) በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ በተካሄደው የታላቁ ሩጫ ላይ ከተሳተፉት ወጣቶች በርካቶች በዚህ ሰው በላ ቡድን መታፈናቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

አርት ቲቪ ላይ ምትሰራዋን ሳህለወርቅን ጨምሮ በርካቶች የታፈኑት ደግሞ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያለበትን ልብስ ለብሳችሁዋል በሚል መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዛም ውጪ የተለያዩ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ የተባሉ በርካታ ወጣቶችም በዚሁ ቡድን መታፈናቸውን የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ምንጮቹ ገልጸዋል።

የሰው በላው ቡድን ከፍርሃቱ የተነሳ ሁሉን ነገር ለመቆጣጠር ከመደበኛ የጸጥታ አስከባሪዎች ውጪ በአዳነች አበቤ ቀለብ የሚሰፈርላቸው 20ሺህ የሰላም ሰራዊት የሚባሉ ባንዳዎች በዚህ ሩጫ ላይ እንዲሳተፉ መደረጉንም አጋልጠዋል።

የሚለብሱትን ካኒቴራ ደግሞ በባለሀብቶች ወጪ እንዲሸፈን መደረጉንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪ በአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ተሰርቆ በተወሰደውና ሸገር የሚል የዳቦ ስም በተሰጠው አካባቢ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም በግዳጅ የቲሸርቱን ወጪ ከደሞዛቸው ተቆርጦ እንዲሮጡ መደረጉንም የኢትዮ 360 ምንጮች አጋልጠዋል።

የሚጥለው ዘግይቶበት በፍርሃት እየራደ ያለው የሰው በላ ቡድን በየፎቁ ስናይፐር አጥምዶ እንደነበርም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

Ethio 360 Media

15 Nov, 18:43


https://www.youtube.com/live/qTl2nqP_Fd8?feature=shared

Ethio 360 Media

15 Nov, 18:42


https://www.youtube.com/live/qTl2nqP_Fd8?si=ZTvo425B3dKlZ9Sx

Ethio 360 Media

15 Nov, 17:52


https://www.youtube.com/live/2jwfExO1k4s?feature=shared

Ethio 360 Media

14 Nov, 22:07


https://youtube.com/live/sAgzYDeeoMo?feature=share

Ethio 360 Media

14 Nov, 19:47


https://www.youtube.com/live/Lqws9-e3QCg?feature=shared

Ethio 360 Media

14 Nov, 18:16


https://www.youtube.com/live/wxNywEGzvQI?feature=shared

Ethio 360 Media

13 Nov, 21:32


https://rumble.com/v5p0t1z-111324-.html

Ethio 360 Media

13 Nov, 18:37


https://www.youtube.com/live/qj-ofu16gXY?feature=shared

Ethio 360 Media

12 Nov, 18:55


https://www.youtube.com/live/ANKE_hqyprY?feature=shared

Ethio 360 Media

12 Nov, 18:54


https://www.youtube.com/live/ANKE_hqyprY?feature=shared

Ethio 360 Media

12 Nov, 17:16


https://www.youtube.com/live/wh47fCAzYSk?si=cTvrkZ3BrXbZGJ-_

Ethio 360 Media

11 Nov, 21:04


https://youtube.com/live/MYdF65I7pVs?feature=share

Ethio 360 Media

11 Nov, 18:25


https://www.youtube.com/live/ht0UwEw-T-8?feature=shared

Ethio 360 Media

11 Nov, 18:24


https://www.youtube.com/live/ht0UwEw-T-8?feature=shared

Ethio 360 Media

11 Nov, 17:34


https://www.youtube.com/live/SV7OoJmyRxA?feature=shared

Ethio 360 Media

10 Nov, 19:53


የአጼ ዳዊት ክፍለ ጦር ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና በውጭ የሚኖሩ የአማራ ዲያስፖራዎች ትግሉን ለመጎተት እያደረጉት ያለውን ትግል የመጎተት አካሄድ እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

(ኢትዮ 360- ሕዳር 1/2017)ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ለሚዲያ ባለሙያዎች እና በውጭ አገር ለሚኖሩ የአማራ ዲያስፖራ የቀረበ አስቸኳይ ጥሪውን አቀረበ።

ክፍለ ጦሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባወጣውና ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫ ላይ አንዳንድ በውጭ የሚኖሩ የመገናኛ ብዙሃን ብዙሃንና የአማራ ዲያስፖራዎች የትግሉን አቅጣጫ ከመጎተት ጀምሮ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል ጭምር ክፍፍል እየፈጠሩ መሆኑን አስሮበታል።ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ይቀርባል።

Ethio 360 Media

10 Nov, 19:27


https://www.youtube.com/live/ZE8bIiS3lh0?feature=shared

Ethio 360 Media

10 Nov, 19:21


አማራው በመላው አለም ተነስቷል !! የዛሬው ትንቅንቅ በፈረንጅ ከተሞች!!  https://youtube.com/live/vVR45WVF6lE?feature=share

Ethio 360 Media

10 Nov, 19:07


በጎጃም ባሶሊበንና በዲማ የሰው በላውና የባንዳው ቡድን አስከሬንን መሰብሰብ እስኪያቅት ሲራገፍ በቋራ ከ15 በላይ ንጹሃን በድሮን ተጨፍጭፈዋል።

(ኢትዮ 360 - ሕዳር 1/2017) የአማራ ፋኖ በጎጃም ስድስተኛ፣ስምንተኛ፣ የሃዲስ አለማየሁና ሰባተኛ ክፍለ ጦሮች ፋኖዎች በጋራ በመሆን ለቁጥር የሚታክት የሰው በላውንና የባንዳውን ቡድን ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ አድርገውታል ሲሉ አመራሮቹ ገለጹ።

በምስራቅ ጎጃም ባሶ ሊበን የጁቤ ይላሉ አመራሮቹ ዛሬ ከንጋቱ 11: 00 ሰአት ላይ ይሄን ገዳይ ቡድን የገጠመው የፋኖ ሃይል ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ከምሮታል ብለዋል።

የሃዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦሮቹ የጁቤ ባሶሊበን ብርጌድ፣ የቦቅላ ብርጌድ ፣አዎበል መብረቁ ብርጌድና የአነደድ ተድላጓሉ ብርጌድ ፋኖዎች ይሄንን የጠላት ሃይል ለማርገፍ በጋራ ቆመዋል ብለዋል።

እንዲሁም የሰባተኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም የስድስተኛ ክፍለ ጦሮቹ ጥቁር አንበሳ ልዩ ኮማንዶችና ንጉስ ተክለሀማኖት ብርጌድ ፋኖዎች ካሉበት ተወርውረው በመምጣት ከወንድሞቻቸው ጎን ቆመዋል ብለዋል።

በዚህ ውጊያ ያልቀውን የሰው በላ ቡድን አስከሬን የሚሰበስበው ጠፍቶ የአካባቢው አርሶ አደር ሰብስቦ ለመቅበር መገደዱንም ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ዲማ ላይ የፋኖ ሃይል ምርቃት ላይ የሚገኙ የፋኖ ሃይል ከፍተኛ አመራሮችን አፍናለሁ ብሎ የመጣው የባንዳና የሰው በላ ቡድን አስቀድሞ ተዘጋጅቶና በጋራ ሆኖ በጠበቀው የፋኖ እንደ ቅጠል መርገፉን ተናግረዋል።

ከኢትኖራ፣ከብቸናና ከደብረወርቅ ሃይሌን አሰባስቤ መጥቻለሁ ያለው ገዳይ ቡድን በበላይዝ ዘለቀ ልጆች ዋጋውን መግኘቱን አስታውቀዋል።

የስምንተኛ ክፍለ ጦር ፋኖዎችን ጨምሮ በርካታ የበላይ ዘለቀ ልጆች በተሳተፉበት በዚህ ውጊያ ከደብርወረቅ አካባቢ ብቻ 17 በከባድ የቆሰሉ አባላቱን ጭኖ ወደ ደብረወርቅ ሆስፒታል ሲወስድ ወደ ብቸና ደግሞ 2 አይሱዙ ሙሉ ሙትና ቁስለኛውን ስያጓጓዝ መዋሉንም ገልጸዋል።

በዚህ ውጊያ የተማረከው የሰው በላው ቡድን ሃይል ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ታያይዞ ቁጥሩን እንኳን ማወቅ አስቸጋሪ መሆኑንም ለኢትዮ 360 ባደረሱት መረጃ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደግሞ ትናንት የሰው በላው ቡድን ቋሪት ብር አዳማ ትንሽ የገጠር ቀበሌ ላይ በፈጸመው የድሮን ድብደባ ከ15 በላይ ንጹሃንን መጨፍጨፉን ገልጸዋል።

በአካባቢው የነበረ ትምህርት ቤትም በዚሁ ጥቃት መውደሙንም ጨምረው አስታውቀዋል።

በዚህ ጥቃት የተጎዱ ንጹሃንና ሌሎች ንብረቶች መኖራቸውንም ሳይጠቁሙ አላልፉም።

Ethio 360 Media

05 Nov, 18:42


https://www.youtube.com/live/Zl3hB5v_QEw?feature=shared

Ethio 360 Media

05 Nov, 18:04


https://www.youtube.com/live/zTPSujjQrTE?feature=shared

Ethio 360 Media

04 Nov, 21:31


https://www.youtube.com/watch?v=8AgCZyRPzzY

Ethio 360 Media

04 Nov, 18:33


https://www.youtube.com/live/-MZZvcqsX88?feature=shared

Ethio 360 Media

03 Nov, 19:40


https://www.youtube.com/live/rmqNruyY74k?feature=shared

Ethio 360 Media

03 Nov, 19:40


https://www.youtube.com/live/rmqNruyY74k?feature=shared

Ethio 360 Media

03 Nov, 15:58


የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ምዕራብ ኮር ክፍለ ጦርና ሌሎች ክፍለ ጦሮች ከህዝባዊ ሰራዊቱ አባይ ሸለቆ ብርጌድ ጋ በመሆን በመካነ ሰላም የሰው በላውን ቡድን ሲያረግፉት አደሩ።

( ኢትዮ 360 - ጥቅምት 24/2017)የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ መብረቅ ክፍለ ጦር አባይ ሸለቆ ብርጌድ ከአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ጎጃም እዝ አባይ ሸለቆ ብርጌድና ከሌሎች ጋ በመሆን የመካነ ሰላምን ተቆጣጥረው የሰው በላውን ቡድን ካርገፉት በሁዋላ አካባቢውን ለቀው መውጣታቸውን ጋዜጠኛ ፋኖ ተመስገን ለኢትዮ 360 ገለጸ።

ዛሬ ለሊት 9 ሰአት ላይ በጀመረው በዚህ ጦርነት ወንዝ አቋርጦ ከመጣው የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት ጎጃም እዝ አባይ ሸለቆም በሻለቃ ደስታው እየተመራ ከወገኖቹ ጎን ቆሞ የጠላትን ቡድን አብሮ ማርገፉን አስታውቋል።

በጋራ በተሰራውና መቅደላ ላይ በጀመረው በዚህ ዘመቻ ከደላንታ ተነስቶ መዳረሻውን መካነሰላም ያደረገው የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ጽናት ክፍለ ጦር ፋኖዎችም በዚህ ውጊያ ላይ ከወገኖቹ ጎን ቆሞ አብሮ አርግፎታል ይላል።

በአውሮፕላን ማረፊያው፣ በመቅደላ ዩኒቨርስቲ በኩል፣በአሜጋ በተለያየ አቅጣጫ ከተማዋን የከበበው የፋኖ ሃይል የበላይነቱን አሳይቶ መዋሉንም አስታውቋል።

በዚህ ውጊያ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሃይሉን ያጣው ገዳይ ቡድን ከባድ መሳሪያ በማስወንጨፍና ሬሳውን ከስር ከእስር ለመሰብሰብ ሲንደፋደፍ እንደነበርም ገልጹዋል።

በሽንፈቱ የተበሳጫው ገዳይ ከ85 በላይ ንጹሃንን በረሸነበት መካነሰላም ዛሬም ሁለት ንጹሃንን ገሎ ፋኖን ገደልኩ በሚል እየፎከረ መሆኑንም ሳይጠቁም አላለፈ።

ዘመቻውን አሳክቶ መካነሰላምና አካባቢውን ለቆ ከወጣው የፋኖ ሃይልም ሶስት አባላቱ በክብር መሰዋታቸውንም የመብረቅ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ፋኖ ኑረዲን አሰፋ ለኢትዮ 360 ገልጹዋል።

የመብረቅ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ደሳለኝና ሌሎች ሁለት ጀግኖቻቸው ታሪክ ሰርተው ማለፋቸውንም አስታውቋል።

በክብር የተሰውት ጀግኖቻቸውንም በተመለከተ መግለጫ አውጥው ለኢትዮ 360 ልከዋል። መግለጫውም እንደሚከተለው ይቀርባል።

አማራ ፋኖ ወሎ እዝ ምእራብ ወሎ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

ጥቅምት 23/2/2017። በመካነሰላም ወረዳ አባይሸለቆ ብርጌድ ሻለቃ መሪ የነበረው ፋኖ ደሳለኝ አሰፋ ከብርጌዱ ወደክፍለጦር በመሄድ የመብረቅ ክፍለጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በመሆን ሲሰራ የቆየው ፋኖ ደሳለኝ አሰፋ በመካነሰላም አባይ ሸለቆ ብርጌድ ጥቅምት 23 ቀን ከሌሊቱ 9 ሰአት ጀምሮ እስከ ጧቱ 4 ሰአት የፈጀ እልክ አስጨራሽ ውጊያ አድርጎ በወሎ ዮኒቨርስቲ መቅደላ አምባ መካነሰላም ቅርጫፍ ላይ መሽጎ የነበረውን የመከላከያና አድማ ብተና ሚኒሻና ፖሊስ ጥምር ጦር ከአባይ ሸለቆ በመነሳት መካነሰላም ከተማ ድረስ በመግባት በ3 አቅጣጫ ከቦ በመቅደላ ቀጠና ወደጎጃም በር ፣በኪዳነምህረት በአውሮፕላን ማረፊያው ፣በሶየ ቢሊ ቀጠና በ3 አቅጣጫ ከቦ ሰብሮ በመግባት የባንዳውን ቡድን ምሽጉን ሰብሮ ሙትና ቁስለኛ አድርጎት መካነሰላም ከተማን ተቆጣጥሮ አዲሯል። በዚህ አስገራሚ ውጊያ 3 የትግል ጓዶቻችን በክብር በጀግንነት ሲሰውብን ከነዚህ ውስጥ የመብረቅ ክፋለ ጦር የህዝብ ግንኙነት የነበረው ፋኖ ደሳለኝ አሰፋ ጠላትን እደቅጠል አራግፎ ምሽግ ሰብሮ በመግባት ታሪክ ሰርቶ በክብር ተሰውቷል ።
ለጓዳችን የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቹና ለትግል ጓዶቹ መጽናናትን እንመኛለን።
የጓዳችንን ፋኖ ደሳለኝ አሰፋ በክብር የተሰዋለትን ትግል እናስቀጥላለን ድል ለፋኖ ድል ለአማራ ህዝብ

Ethio 360 Media

02 Nov, 19:15


በካራማራ ክፍለ ጦር ከፍተኛ ቁጥር ያለው የባንዳ ቡድን ተራገፈ።


(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 23/2017) የአማራ ፋኖ በጎንደር በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ ዳስጉንዶ በተባለው አካባቢ ከገዳዩ ቡድንና ከባንዳው ጋር በተከታታይ ቀናት በተደረጉ ውጊያዎች ከፍተኛ ሃይሉን እንዲያጣ መደረጉን የክፍለ ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ አንተነህ መክብብ ለኢትዮ 360 ገለጸ።

በዚህ ውጊያ በርካታ የገዳዩ ቡድን ካድሬዎችንም መደምሰሱንም አስታውቋል።

ይሄ ገዳይ ቡድን ፊለፊት ያልቻለውን ውጊያ ወደኋላ በመሮጥ ከተማዎቹን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ አካባቢው የነበረን ሰብል ና በርካታ ንፁሃን ገበሬዎችን ጨፍጭፏል ሲልም ቃል አቀባዩ ተናግሩዋል።

ለህዝቡ ደህንነት ሲባል ያፋኖ ሃይል ከከተማው ወቶ ቢቆይም ብየፋኖን መውጣት ተከትሎ ወደከተማው በመግባት በርካታ ንፁሃንን ማሰር መጀመሩን አስታውቋል።

ይሄንን በዝምታ ማለፍ ያልቻለው የካራማራ ክፍለ ጦር የፋኖ ሃይልም ይሄንን ገዳይ ቡድን መልሶ በመግጠም ከተማውን አስለቅቀን አባረነዋል ይላል።

እስረኛ አድርጎ ይዟቸው የነበረውን ሰባት ንፁሃን ገበሬዎችን በጅምላ መረሸኑንም ገልጹዋል።

በየቦታው እየተጨፈጨፈ ያለውን የአማራ ገበሬ ለመታደግ ሁሉም ሰው ከፋኖ ጎን መቆምና ትግሉን ህዝባዊ በማድረግ ብልፅግናን ከስረመሰረቱ ነቅሎ መጣል የሚጠበቅብን ነው ሚሆነው ሲልም ቃል አቀባዩ አንተነህ መክብብ መልዕክቱን አስተላልፉዋል።

Ethio 360 Media

02 Nov, 18:02


https://www.youtube.com/live/0Z-BjfjJYNU?feature=shared

Ethio 360 Media

02 Nov, 17:21


የጅበላ ጎተራ ብርጌድ ፋኖዎች ዛሬ የሰው በላውን በደብረማርቆስ ቡድን ሲያረግፉት ውለዋል።


( ኢትዮ 360 - ጥቅምት 23/2017) የአማራ ፋኖ በጎጃም ስድስተኛ ክፍለ ጦር ጅበላ ጎተራ ብርጌድ ፋኖዎች የሰው በላውን ብድን ሶስት ፓትሮል ሙሉ አስከሬንና ሁለት ፓትሮል ቁስለኛ አድርገውት መዋላቸውን የብርጌዱ አመራሮች ለኢትዮ 360 ገለጹ።

ዛሬ ይላሉ በማርቆስ ከተማ ዙሪያውን በወቃ መምህራን ኮሌጅ ፣ በመለስ ፓርክ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት እንዲሁም በሜቴክ አካባቢ ከፍተኛ ትንቅንቅ ሲደረግ መዋሉን ተናግረዋል።

በነዚህ ቦታዎች በነበረው እልህ አስጨራሽ ውጊያም የሰው በላውና የባንዳው ቡድን በፋኖ ጥይት ሲረግፉ ውለዋል ብለዋል።

ከፋኖ ጥይት የተረፈውም 2 ፓትሮል ሙሉ እሬሳውንና 1 ፓትሮል ሙሉ ቁስለኛውን ሲሰበስብ መዋሉንም አስታውቀዋል።

በአካባቢው አሁንም ጦርነቱ የቀጠለ ሲሆን የሞተውም ሆነ የቆሰለው የሰው በላና የባንዳ ቡድን ቁጥርም ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል።

Ethio 360 Media

01 Nov, 21:25


https://youtube.com/live/YJ5joiS7ybc?feature=share

Ethio 360 Media

30 Oct, 20:23


ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ጥሪ በሲያትል እና አካባቢዉ ለምትኖሩ አማራው ያን እና ኢትዮጵያዊያኖች በሙሉ !

ላለፉት 5 ዓመታት አማራው ባቀናውና በተወለደበት፣ በወለጋ ፣በአረሲ፣ በሐረር ወዘተ ቀን በቀን እየጨፈጨፍን የአማራን እልቂት አለማመዱን ::  ይባስ ብለው፣ ይህን የጅምላ ጭፍጨፋው  እዛው የአማራ ግዛት በተባለው ክልሉ ድረስ አምጥተው ለታል ።
 አማራዉ  በራሱ ክልል  በየእለቱ በዚህ አረመኔ ዘረኛ ቡድን በከባድ መሳሪያ፣በድሮን ይደበደባል ሰብሉ ይቃጠላል :: ይህ አልበቃ ብሎ ፣ ቤት ለቤት እየዞሩ ንፁሀንን  ይረሸናሉ ፣ ሴቶች ይደፈራሉ :: በአማራው ላይ የሚፈጸመዉ ግፍ ይበቃ ዘንድ የሁሉንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ እና የመላው አማራን ድጋፍ እንጠይቃለን ::

November 7/2024  ከጧቱ  10:00 am   Gerber Park 575 MLK Jr Way Seattle WA 98122 ተገናኝተን ለሚጨፈጨፈዉ ወገናችን ድምፅ እንድንሆን የሲያትል አማራ ማህበር ጠርቷል።

ሰዉ መሆን ብቻ በቂነዉ ግፍን ለመቃዉም

ገርበር ፖርክ የምንገናኘው ከጠዋቱ 9:00 am ሲሆን  ጉዟችን ልክ በ 10 am ጠዋት  ይሆናል እናም ቀደም ብለን እንገናኝ!!

መነሻችን Gerber park  Seattle  WA ሲሆን መድረሻችን state capital Olympia  Washington

ኑ...  ለወገኖቻችን አንድ ቀን ዋጋ እንክፈል!!

በእለቱ ሁላችንም ጥቁር ልብስ እንለብሳለን !!

ዝናብ እና ቅዝቃዜ ሊኖር ስለሚችል በቂ ዝግጅት አድርጉ !! መኪናችሁን ጋዝ መሙላት እንዳትረሱ !!

Ethio 360 Media

30 Oct, 20:21


ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ጥሪ በሲያትል እና አካባቢዉ ለምትኖሩ አማራው ያን እና ኢትዮጵያዊያኖች በሙሉ !

ላለፉት 5 ዓመታት አማራው ባቀናውና በተወለደበት፣ በወለጋ ፣በአረሲ፣ በሐረር ወዘተ ቀን በቀን እየጨፈጨፍን የአማራን እልቂት አለማመዱን ::  ይባስ ብለው፣ ይህን የጅምላ ጭፍጨፋው  እዛው የአማራ ግዛት በተባለው ክልሉ ድረስ አምጥተው ለታል ።
 አማራዉ  በራሱ ክልል  በየእለቱ በዚህ አረመኔ ዘረኛ ቡድን በከባድ መሳሪያ፣በድሮን ይደበደባል ሰብሉ ይቃጠላል :: ይህ አልበቃ ብሎ ፣ ቤት ለቤት እየዞሩ ንፁሀንን  ይረሸናሉ ፣ ሴቶች ይደፈራሉ :: በአማራው ላይ የሚፈጸመዉ ግፍ ይበቃ ዘንድ የሁሉንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ እና የመላው አማራን ድጋፍ እንጠይቃለን ::

November 7/2024  ከጧቱ  10:00 am   Gerber Park 575 MLK Jr Way Seattle WA 98122 ተገናኝተን ለሚጨፈጨፈዉ ወገናችን ድምፅ እንድንሆን የሲያትል አማራ ማህበር ጠርቷል።

ሰዉ መሆን ብቻ በቂነዉ ግፍን ለመቃዉም

ገርበር ፖርክ የምንገናኘው ከጠዋቱ 9:00 am ሲሆን  ጉዟችን ልክ በ 10 am ጠዋት  ይሆናል እናም ቀደም ብለን እንገናኝ!!

መነሻችን Gerber park  Seattle  WA ሲሆን መድረሻችን state capital Olympia  Washington

ኑ...  ለወገኖቻችን አንድ ቀን ዋጋ እንክፈል!!

በእለቱ ሁላችንም ጥቁር ልብስ እንለብሳለን !!

ዝናብ እና ቅዝቃዜ ሊኖር ስለሚችል በቂ ዝግጅት አድርጉ !! መኪናችሁን ጋዝ መሙላት እንዳትረሱ !!

Ethio 360 Media

30 Oct, 18:44


በሚዳ ወረዳ ተጨማሪ ሃይል ለማስገባት የሞከረው ገዳይ ቡድን የአጼ ዳዊት ክፍለ ጦር ፋኖዎች ሲያራግፉት ዋሉ።

(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 20/2017)የአማራ ፋኖ ጠቅላይ ግዛት እዝ የቀስተ ንህብ ብርጌድና የክፍለ ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ ሃይል ወደ ሚዳ ወረዳ ተጨማሪ ወራሪ ሀይል ለማስገባት የሞከረውን ገዳይ ቡድን ሲያራግፉት መውላቸውን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ለኢትዮ 360 ገለጸ ።

ከጠዋቱ 12:30 እስከ ቀኑ 7:30 ድረስ የአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር በፋኖ ሞገስ መስፍን የሚመራው የቀስተ ንህብ ብርጌድ እና በፋኖ መንፈስ ፀጋው የሚመራው የክፍለ ጦሩ ልዩ ተወርዋሪ ጦር ባደረጉት አውደ ውጊያ በሰው በላው ቡድን ላይ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እንዳደረሱበት አስታውቋል።

መነሻውን አለም ከተማ ያደረገው ገዳይ ቡድን ተጨማሪ ሀይሉን ወደ ሚዳ ወረዳ ለማስገባት ያደረገው እንቅስቃሴ በፋኖ ጥይት እንዲራገፍ አድርጎታል ይላል።

በአፄ ዳዊት ክፍለ ጦር ልዩ ተወርዋሪ ዘመቻ በንስሮቹ አይን ላይ የወደቀው የጠላት ሀይል ከዋሶ ጨበሬ እስከ ጨለሚት ድረስ ሲገረፍ መዋሉንም አስታውቋል።

በሌላኛው አቅጣጫ የመጣውን የጠላት ሀይል ለመቀበል እና ሽፋን ለመስጠት መነሻውን መራኛ ከተማ ያደረገው ስብስብም በቀስተ ንህብ ብርጌድ አባላት በበግ ስርጥና በሾላ ሜዳ በደፈጣ መራገፉን ተናግሩዋል።

በዛሬ ውጊያ በጠላት ከባድ ጉዳት የደረሰበት ይሄ ሃይል ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ቁስለኛውንወደ ጃሞ ደጎሎ ሆስፒታል መጫኑንም አስታውቋል።

በቀላሉ ተጎድተዋል የተባሉን ደግሞ መራኛ ከተማ በሚገኘው ሆስፒታል ማስገባቱን የውስጥ አርበኞቻችን ባደረሱዋቸው መረጃዎች ማወቃቸውን የክፍለ ጦሩ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢትዮ 360 በላከው መረጃው አስታውቋል።

Ethio 360 Media

30 Oct, 18:19


https://www.youtube.com/live/Xj74K--e42g?feature=shared

Ethio 360 Media

30 Oct, 18:18


https://www.youtube.com/live/Xj74K--e42g?feature=shared

Ethio 360 Media

30 Oct, 18:18


https://www.youtube.com/live/Xj74K--e42g?feature=shared

Ethio 360 Media

30 Oct, 17:45


የወሎው እዙ ቦረና ገነቴ ብርጌድ ሁለተኛ ጽናት ሻለቃ በደፈጣ ገዳዩን ቡድን እንደ ቅጠል አረገፈው።

(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 20/2017)የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ መብረቅ ክፍለ ጦር ቦረና ገነቴ ብርጌድ ሁለተኛ ጽናት ሻለቃ ዛሬ ከለጋቦ ወደ ይላዳ ከመጣው የሰው በላ ቡድን በደፈጣ ከ5 በላይ የሚሆነውን ገሎና ከ10 በላይ የሚሆነውን ቁስለኛ አድርጎ መልሶታል ሲል የክፍለ ጦሩ ቃል አቀባይ ፋኖ ኑረዲን አበበ ለኢትዮ 360 ገለጸ።

በአርበኛ ከረም ሙሀመድ የሚመራው ቦረና ገነቴ ብርጌድ 2ተኛ ጽናት ሻለቃ ከለጋቦ ወደ ይላዳ የመጣውን የአገዛዙ ወበር ጠባቂ ቡድን ከመንገድ ጠብቆታል ይላል።

በአካባቢው የሻለቃዋ ሃይል መኖሩን ያላወቀው የሰው በላው ቡድንም ከ5በላይ የሚሆነው ወደ አስከሬንነት ተቀይሮና ከ10 በላይ የሚሆነው ደግሞ ቁሥለኛ ሆኖ መመለሱን አስታውቋ።

በዚህ ደረጃ ተራግፎ የተመለሰው ገዳይ ቡድን ከወረዳው ያለ ሀይሉን ሰብስቦና ምሽግ ስርቶ መቀመጡም ፋኖ ኑረዲን አበበ ለኢትዮ 360 ገልጹዋል።

Ethio 360 Media

30 Oct, 17:28


የአዲስ ከተማ ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ተከለከሉ።
(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 20/2017)
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በአዲስ ከተማ መሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህ ቤት የሚገኙ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሂጃብ መልበስ ተከልክለው ከፍተኛ እረብሻ መነሳቱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

ትላንት በነበረው በዚህ ረብሻ በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋሉ፣ በርካቶቹም በ4ተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲታጎሩ ተደርገዋል ብለዋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አውቶቢስ ተራ አካባቢ በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎችን ኢጃብ አትለብሱም በሚል ተደብድበው ከታሰሩት መካከል ደግሞ አብዛኞቹ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑ ተማሪዎች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ቤተሰቦቻቸውን ዛሬ ስብሰባ የጠራው የሰው በላ ስብሰባ ሂጃብ ማውለቅ ግዴታ እንደሆነ በግልጽ እንደነገራቸውም አንስተዋል።

ትላንት ተፈጠረ በተባለው ረብሻ ተማሪዎቹ አወደሙት ላሉት ንብረትም ሂሳቡ በባለሙያ ተጠንቶ ወላጅ መክፈል ግዴታ እንዳለበት ከማስጠንቀቂያ ጭምር እንደተነገራቸውም ገልጸዋል።

ወደ ማጎሪያ የተወሰዱ ተማሪዎችም ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑና በረብሻው ያልተካተቱን ደግሞ እያጣራን እንለቃቸዋለን በሚል በስብሰባው ላይ መነገሩንም አንስተዋል።

ይሄን ሁሉ ወንጀል በተማሪዎች ላይ እየሰራ ያለው ደግሞ የአዲስ ከተማ ፖሊስ የሚባለው ገዳይ ቡድንና የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር መሆናቸውንም የኢትዮ 360 ምንጮች ጠቁመዋል።

ይሄንን እያደረጉ ያሉት ደግሞ ከላይ በወረደላቸው ትእዛዝ አማካኝነት መሆኑን በግልጽ መናገራቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።

Ethio 360 Media

29 Oct, 17:08


https://www.youtube.com/watch?v=TM-w4Q3SYKw

Ethio 360 Media

29 Oct, 16:33


https://www.youtube.com/watch?v=YWJwo7dY--A

Ethio 360 Media

28 Oct, 20:29


https://www.youtube.com/live/mNkhkXEF0pw?si=ep5dxElHCG4rwjQW

Ethio 360 Media

28 Oct, 17:26


https://www.youtube.com/watch?v=0ehhK21xlfQ

Ethio 360 Media

26 Oct, 20:03


https://rumble.com/v5k8rhf-102624-.html

Ethio 360 Media

26 Oct, 18:26


ጢስ አባይ ላይ የሰው በላውን ቡድን የገጠመው የፋኖ ሃይል አንድ ተሽከርካሪንም ወደ አመድነት ቀይሮታል።

(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 16/2017) የአማራ ፋኖ በጎጃም አንደኛ ክፍለ ጦር ፋኖ ጢስ አባይ ላይ የገጠመውን የሰው በላ ቡድን ሲያረግፍ አባይ ማዶ ላይ ደግሞ የሰው በላውን ተሽከርካሪ ማውደሙን የጦር መሪዎቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።

       አባይ ማዶ ዲያስፖራ ታክሲ ማቆሚያው አካባቢ አንድ ማንነቱ ያልታወቀን የሰው በላውን አመራር ተሽከርካሪ ወደ አመድነት ቀይረውታል ብለውል።

ማንነቱ ያልታወቀውን የባንዳ ቡድን መሪ ተሽከርካሪ ያወደመው የፋኖ ሃይል አሽከርካሪውንም ዋጋውን ሰቶታል ሲሉ ገልጸውታል።

ተሽከርካሪው ውስጥ የነበረና ለማምለጥ የሞከረ አንድ ግለሰብንም የፋኖ ሃይል ከመንገዱ አስቀርቶታል ብለዋል።

  በተመሳሳይም ተከታታይ የቦምብ ጥቃቶችን የፈጸመው የፋኖ ሃይል የክልሉ ማረሚያ ቤትና የፖሊስ ኮሚሽን ያሉበትን አካባቢ በከባድ ፍንዳታ ሲያምሰው ማምሸቱንም አስታውቀዋል።

Ethio 360 Media

26 Oct, 16:54


https://www.youtube.com/watch?v=B2Qyngkuj50

Ethio 360 Media

26 Oct, 00:47


ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ስድስት አመት ከ3 ወር ተፈርደባቸው።

(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 15/2017) የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ጋዜጠኛና የታሪክ ምሁሩ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ላይ ስድስት አመት ከ3 ወር እንደፈረደባቸው የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

ፍርድ ቤቱ በጥቅምት 12/2017 ባዋለው ችሎት የፍርድ ማቅለያ እንዲያቀርቡ ቢጠይቃቸውም ምንም ያጠፉት ነገር ስለሌለ ምንም ማቅለያ እንደምያቀርቡ በግልጽ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

የ74 አመቱን አዛውን ያለምንም ፍትህ ሲያንገላታቸው የከረመው የሰው በላው ፍርድ ቤትም ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ላይ የስድስት አመት ከሶስት ወር የእስር ፍርድ አሳልፎባቸዋል።

በሶስት ክሶች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመው ችሎት ዛሬም የ74 አመቱን የእድሜ ባለጸጋ በማጎሪያ እንዲቆዩ ፈርዶባቸዋል ብለዋል።

ለወጣቱ ልፍስፍስነትን አላስተምርም ብለው በግልጽ የሞገቱት ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ዛሬም ከነሙሉ ግርማ ሞገሳቸው በሰው በላው ችሎቱ ፊት መቅረባቸውንም የኢትዮ 360 ምንጮች ገልጸዋል።

Ethio 360 Media

25 Oct, 18:04


https://www.youtube.com/watch?v=xnLTYAD6DLA

Ethio 360 Media

25 Oct, 17:10


https://www.youtube.com/watch?v=cM8U6Nz2SZY

Ethio 360 Media

24 Oct, 20:02


https://www.youtube.com/watch?v=GINLIyaiMUo

Ethio 360 Media

24 Oct, 18:37


https://www.youtube.com/watch?v=iy3bO0hnul8

Ethio 360 Media

24 Oct, 18:21


https://rumble.com/v5jyhg4-ethio-360-daily-news-thursday-oct-24-2024.html?e9s=src_v1_mfp

Ethio 360 Media

24 Oct, 17:52


https://rumble.com/v5jyrct-ethio-360-zare-min-ale-thursday-oct-24-2024.html

Ethio 360 Media

24 Oct, 16:50


https://www.youtube.com/watch?v=ViMylideOfs

Ethio 360 Media

23 Oct, 18:25


https://rumble.com/v5ju24j-ethio-360-zare-min-ale-wed-oct.-23-2024.html

Ethio 360 Media

22 Oct, 17:36


https://www.youtube.com/live/b1KuIhbvcuk?feature=shared

Ethio 360 Media

22 Oct, 17:04


https://www.youtube.com/live/b1KuIhbvcuk?si=gDN2H8B_o9ioR6NP

Ethio 360 Media

21 Oct, 20:30


https://youtube.com/live/1ynM0dHoojQ?feature=share

Ethio 360 Media

21 Oct, 18:05


https://www.youtube.com/live/xKob2H2QNgs?feature=shared

Ethio 360 Media

21 Oct, 18:05


https://www.youtube.com/live/xKob2H2QNgs?si=QiECx4msF6Ondlw2

Ethio 360 Media

21 Oct, 17:12


https://www.youtube.com/live/jbfzm1G3ehQ?si=MQUbD3YUu3F51eEr

Ethio 360 Media

20 Oct, 19:33


የአማራ ፋኖ በጎንደር ፋኖዎች በዓለም ሳጋ ጫካ ላይ የሰው በላውን ቡድን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ከፍተኛ ድል ተጎናጸፉ።

(ኢትዮ 360 - ጥቅምት 10/2017) የአማራ ፋኖ በጎንደር የጉና እና የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦሮች በጋራ መሳሪያ ሊቀባበል የነበረውን ገዳይ ቡድን ሲያረግፉት መዋላቸውን አመራሮቹ ለኢትዮ 360 ገለጹ።

የፋኖ መሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ የጠላት ብልጽግና ሠራዊት ከባህር ዳሩ መኮድ ግቢ ተነስቶ የጦር መሣሪያ ጭኖ ደብረታቦር ለሠፈረው ሀይል ሊያስረክብ በመጓዝ ላይ ነበር።

የደብረታቦሩ በበኩሉ ደግሞ ወደ ዓለም በር ተንቀሳቅሶ ርክክብ ሊያደርግ ተዘጋጅቶ እንደነበርም ይናገራሉ

ይህንን መረጃ ቀድመው ያገኙት የጉና ክፍለ ጦርና የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦሮች ፋኖዎች በቅንጅት የደፈጣ ጥቃት በመክፈት የሰው በላውን ቡድን ሲያረግፉት እንደዋሉ ተናግረዋል።

በዚህ ጦርነት አንድ ሻለቃ መሪና አንድ የመቶ አለቃ መሪን ጨምሮ ከአስር በላይ የጠላትን ሀይል ሲደመሰስ፣አምስት ደግሞ መማረካቸውን አመራሮቹ ለኢትዮ 360 ባደረሱት መረጃ አመልክተዋል።