ምዕራባውያን "የነጻነት ታጋዮች" እያሉ በሚዲያዎቻቸው የሚያቆላምጧቸው በአዲስ ስም የመጡት እነ አይ*ሲ* ስ እና አ* ቃ*ዳ በቱርክና በምዕራቡ እየተደገፉ ወደ ደማስቆ እየገሰገሱ ነው፡፡ አሌፖ ከተማን የመሳሰሉ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ትውልደ አርመን የሆኑ ኦርቶዶክሶች እና ሌሎች አረብ ክርስቲያኖች የሚኖሩባቸው አካባቢዎች በአክራሪዎቹ ቁጥጥር ስር ገብተዋል። ሶሪያን ለመቀራመት ጎረቤት ሀገራት አሰፋስፈዋል።
የሀገር መፍረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ልብ ያለው፣ አደብ የገዛ ማንም ሰው ቁጭ ብሎ ይማር። ይኸው ትምህርት ቤቱ ሶሪያ አለችለት። ትናንት ኢራቅና ሊቢያ እንዲሁም የመንና ሶማሊያ ፈራረሱ፣ ዛሬ ደግሞ ከብዙ ሙከራ በኋላ ሶሪያ ላይ ተሳካላቸው።
ይህ ማለት የሶሪያ መንግሥት ጥሩ መንግሥት ነበር ማለቴ አይደለም። ዓምባገነን መንግሥት መሆኑ ይታወቃል። ልክ እንደ ጋዳፊ ማለት ነው:: ነገር ግን አሁን የሚዋጉት ሰዎች ለሶሪያ ሕዝብ የተሻለ ነገር ይዘው የሚመጡ ቢሆን እንዴት ግሩም ነበር። አይደለም እንጂ። ሊቢያን ተመልከት። የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚል የዋህነት የትም እንደማያደርስ ይኸው ማስረጃ።
በነገራችን ላይ በነዚህ ሁሉ አካባቢዎች ሀገራቱ ሲፈርሱ ምዕራባውያኑ እያዩና እየሰሙ የሚጠፋው ማን እንደሆነ ልብ ብላችኋል? ክርስቲያኖች እና ክርስትና፤ ጥንታዊ ባህልና ጥንታዊ ማንነት።
ከቱርክ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ፍጅት የተረፉ የአርመን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች መጠለያ የነበረችው ሶሪያ ይኸው ዕጣው ደረሳት። ያሳዝናል።