የኢናያ ደብዳቤዎች💨 @httpstmeyawahnberku Channel on Telegram

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

@httpstmeyawahnberku


💌lovely all members ብዙ ፍቅር. ያለበት ቤት ነው ቤተሰብ ምትሆኑበት ቻናል እና ድንቅ ወጣ ወጣ ታሪኮችን ምታነቡቡት ትረካም አለ

https://t.me/httpstmeyawahnberku 💛

የኢናያ ደብዳቤዎች💨 (Amharic)

የኢናያ ደብዳቤዎች💨 በእርስዎ ስልጠና ወደ መብት የሚገባ እና የከፍተኛ መረጃዎችን እንዲቀንስሉ ከሚሸጥ ቦታ ነው። እዚህ የቴሌግራም ክፈት አዝራር በማንጠብጠብ ከሚገጥመው ቦታ እና ስለሚያገኙበት ዋጋ መረጃዎች ማድረግ ያስፈልጋል። በዚህ ቻናል ላይ ከዚህ በኋላ በመሣሪያዎ ምላሽ በማድረግ በተለያዩ ምልክቶች ይደግፉ። እናም ዋጋዎን በመጠቀም ከእናንተ ጋር ሊመለሱ ይችላሉ።

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

29 Dec, 19:07


የኢናያ ደብዳቤዎች💨 pinned «ወታደር ነበር🥹 ሠርፀ  ይባላል ብዙ ታላቄ ነበር  እኔ 17 አመት እያለው ነው ያወኩት እድሜውን በውትድርና ስላሳለፈ ትዳርም ሆነ ልጆችም የሉትም ከግዳጅ ሲመጣ ባሩድ ባሩድ እየሸተተኝም ቢሆን አቅፌ እስመው ነበር አንዳንዴ ልጄ አንዳንዴ ፍቅሬ እያለ ነበር ሚጠራኝ እስከ አሁን ድረስ እንደሱ ሚወደኝኛ ሚያስብልኝን ሰው አላየውም🔥 በጣም ይጠነቀቅልኝ ነበር ቆይ እቺ ነገር ስታድጊ ነግርሻለው ቆይ …»

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

29 Dec, 18:55


ለሎጊያው ጅኒ እራሴ ዳርኩ
ፀሀፊ ልኡል ዘወልደ
ተራኪ ኢናያ
በቅርብ ቀን ይጠብቁን🥰😊

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

29 Dec, 18:47


@Sostkilo በተሳሳተ ክስ : ከFacebook ፣ Instagram እንዲሁም ከThreads ላይ ጠፍታለች ። ይሄን ቻናል ( t.me/sostkilo ) ሦስት-ኪሎን ይወዱ ለነበሩ ያጋሩ ። ከምሥጋና ጋር🖤

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

29 Dec, 17:43


https://t.me/shelovesyapping

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

19 Dec, 06:53


አብርሃም አልሞተም ማለት ነው?
ከወራት በፊት ሆስፒታል ያየውት ግዜን አስታወስኩ ተስፋ አልነበረውም
ልብሴን ቀይሬ እግሬ ወደ አመራኝ ሄድኩ
ብዙ ህመሞቼ በትዝታ መልክ ፊት ለፊቴ መጡ ሁሉም ስቃዮቼን አዳመጥኩ

ልቤን  ደግፍ አደረኩ ከዐይኔ እንባ ይጎርፋል  ይቅር ብያለው ብዬ ወደሰማይ ጮህኩ አንዳች አዚም ከላይ ብድግ ሲል ታወቀኝ

ታክሲ ውስጥ ገብቼ ሆስፒታሉ በር ጋ ወረድኩኝ አብርሀም የተኛበት ክፍል ጋ ስሄድ ነርሷ ሌላ ፅኑ ህሙማን ክፍል እንደተኛ ነግራኝ ይዛኝ ሄደች
እናቱ ጋ ረጅም ሰአት አወራን  ይቅር እንዳልኩ ነገርኳቸው ።አብርሀም ክፍል አብረን ገባን አይኖቹን ገለጸ እና ተመለከተኝ ቃል ማውራት አልቻለም ነፍሱ ትይዛለች

የአብርሀም እናት ወሃ የተሞላበት እቃ ላይ  እርጥብ ሳር  አደረኩ ጣቴን እንድጨምር ነገሩን የልጃቸውን ቀኝ እጅ ከተቱ እኔን ጣቴን ውሃው ውስጥ አስገባው ይቅር በይ ልጄ ይቅር በይ አሉኝ

አብርሃምን አየውት በተማፅኖ አየኝ ፀፀት ዐይኑ ላይ ማንበብ ጀመርኩ

ይቅር ብያለው አብርሃም አልኩት
ፊቱ ላይ ሰላምንና መረጋጋትን አየው እቤቴ ሄጄ  ተኛው

በነጋታው አብርሀም እንዳረፈ ነገሩኝ
ይቅርታ እረፍት ነው!

ይህን ፅሁም ያነበባችሁ ምን በድሎሽ ነው የሚል ጥያቄን ልታነሱ ትችላላችሁ ነገር ግን ይቅር ስላልኩ የበደል ስቃይ ታሪኮቼን መፃፍ አልፈለኩም ይቅርታ ማድረግ ማለት እረፍት እንደሆነ አይቻለው
አበቃው ይቅር ተባባሉ እረፍት ስጡ

ኢናያ

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

19 Dec, 06:38


አልጋ ላይ ጋደም ባልኩበት ስልክ ተደወለ እኩለ ሌሊት ሊሆን ነው ማላውቀውን ስልክ ማንሳት ፈፅሞ አልወድም ድጋሚ ተደውሎ ጠራ ግን አልቻልኩም አነሳውት ወደ ጆሮዬ ጠጋ አድረኩት ሄሎው ማን ልበል?

ሄሎው ይቅርታ ሲስተር ፀጋ እባላለው በአለርት ሆስቲታል ነርስ ነኝ ድንገተኛ አደጋ የደረሰበት ታካሚያችም  ያንቺ አድራሻ ሰጥቶኛል እባክሽ ያለበት ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነው የመጨረሻ ንግግሩን ካንቺ ጋእንዲሆን ይፈልጋል
እባክሽ ቶሎ ድረሺ አለችኝ

የሰማውት ነገር አስደነገጠም ወዲያውኑ በዛ ሌሊት ሄድኩ ማን ነው አደጋ የደረሰበት? ማነውስ? ከህመሙ ጋ እየታገለ እኔን ማግኘት ሚፈልግ

በስልክ ያገኘዋት ነርስ እየመራች አንድ ክፍል ውስጥ አስገባችኝ

አብርሀም ሰውነቱ በነጭ ፋሻ ተጀቡኗል  ዐየውት ፈት ለፊቱ ቆምኩ ምንም ሀዘኔታም እርህራሄም ፊቴ ላይ አልነበረም  በውስጤ አንድ ቀን የእጁን አግኝቶ ፊቱ እንደዚ እንደምቆም እውቅ ነበር 

ታግሎ ይቅርታ ይቅርታ  አለኝ

ትቼው በኮሪደሩ መጨረሻ አድርጌ ወደ እቤቴ ሄድኩ ገብቼ  በጀርባዬ ተንጋለልኩ  ስልኬንም አጠፍቼ የተፈጠረውን ነገር ለመርሣት ሞከርኩ

ከወራት ቡሀላ ድጋሚ ስልኬ ይጮሀል
አነሳውት ሄሎ

ተለቅ ያሉ ሴትዮ ናቸው ረጅም ሰአት ስቅስቅ ብለው አለቀሱ ማንነታቸውን ሳላውቅ ልቤ ራራላቸው 
የአብርሀም እናት እንደሆኑ ነገሩኝ
ልጄ እባክሽ ይቅር በይን
ልጄ በነፍስ በስጋው እየተሰቃየ ነው ይረፍልኝ ልጄ ነፍሱ ሳስታለች ፀፀት በላብኝ ልጄ እባክሽ  እባክሽ ድጋሚ ለቅሶ
ይቀጥላል___
በኢናያ

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

09 Dec, 11:59


ትረካ መስራት ልጀምር እንዴ ቤተሰቦች? እንደ ድሮአችን?
React አድርጉ እስቲ🫶🙂

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

01 Dec, 13:15


ግዜ አነፋፈቀን

ቀን ጠፋ
ቀን ከፋ
ቀን ታጣ
እኔን የሚወስድ አንቺን የሚያመጣ
ወይ አላገናኘን ወይ አላራራቀን
ይሄ ቀን
ይሄ ቀን
እዚና እዛ አድርጎ ግዜ አነፋፈቀን

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

01 Dec, 13:08


ወታደር ነበር🥹

ሠርፀ  ይባላል ብዙ ታላቄ ነበር  እኔ 17 አመት እያለው ነው ያወኩት እድሜውን በውትድርና ስላሳለፈ ትዳርም ሆነ ልጆችም የሉትም

ከግዳጅ ሲመጣ ባሩድ ባሩድ እየሸተተኝም ቢሆን አቅፌ እስመው ነበር

አንዳንዴ ልጄ አንዳንዴ ፍቅሬ እያለ ነበር ሚጠራኝ እስከ አሁን ድረስ እንደሱ ሚወደኝኛ ሚያስብልኝን ሰው አላየውም🔥 በጣም ይጠነቀቅልኝ ነበር ቆይ እቺ ነገር ስታድጊ ነግርሻለው ቆይ ይህን መፅሀፍ ተይ እቺን ያዚ ቆይ አይምሮዬን ለመጠጠቅ ነበር እንደዚ የሚያደርገው"

ሰርፀ ለእኔ perfecto ፐርፌክቶ ነበር
በሁሉም ነገሩ የተሟላ ፍፁም ነበር


አንድ ማለዳ ተነስቶ ልብሶቹን የወታደር ዩኑፎርሙን በካውያ እየተኮሰ አገኘውት

የኔ ፍቅር ምንድን ነው ድጋሚ ልትሄድብኝ ?ነው እንዴ ብዬ አየውት ዐይኖቹን በዐይኔ እየተከተልኩ ንገረኝ ድጋሚ ጠሩህ እንዴ እ?

አጥብቆ አቀፈኝ እና በሁለት እጆቹ ትከሻዬን አጥብቆ ይዞ እንደዚ ነበር ያለኝ:-

"ኢናያ ለራስሽ ብለሽ ቅን ሰው ሁኚ, ያለፈ ነገር ያለፈ ቢሆንም ካለፉ ነገሮች ተማሪ, ሰዋዊ ነፃነትሽን ላለማስነካት የቻልሽውን ሁሉ አድርጊ:: ኢናያ ምግብ ብይ, እራስሽን ጠብቂ:: አዳዲስ ነገሮች የሚኖሩት እንድታውቂያቸው ነው ስለዚህ በጥንቃቄ ለማወቅ ሞክሪ:: ኢናያ ገና ልጅ ነሽ የሚሉሽን እትስሚ:: ትልቅ ሰው ነሽ ሚሉሽንም አትስሚ:: ኢናያ እራስሽ የሚሰማሽን ሁኚ (ትልቅ ወይም ትንሽ):: ትንሽም ትልቅም የሚለው መገለጫ አንፃራዊ የሚሆንበት አጋጣሚ ብዙ ነው እና ሁለቱም አባባል አደገኛ የሂወት መሰናክል የሚሆኑበት ጊዜ አለና!!!"


እለት እሁድ የመከላከያ ሰራዊት የቀድሞ ወታደሮችን መታሰቢያ ሀውልት ሲያቆም እኔም እርሱን ለማስታወስ የተፃፈ

🇪🇹 እሑድ, ኅዳር 22 2017 ዓ.ም

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

01 Dec, 09:45


የሚያሳዝን ገላ የሚያምር ጥርስህን
ትቢያ ከሚበለው የፍቅር ዐይንህን
እኔ ልቅደምና ልቅመስልህ ዐፈር
ማየት አልፈልግም ሞተህ ስትቀበር

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

28 Nov, 08:18


💓🔥old is gold

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

25 Nov, 01:36


ላንተ መኪና እየነዳህ ምናምን ስማው🥰🫶

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

18 Nov, 21:06


ፍቅር በምትወደው ነፍስ ውስጥ እራስን መግደል ነው🙂

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

14 Nov, 07:40


https://t.me/yeqal

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

12 Nov, 01:21


🥰❤️‍🩹

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

04 Nov, 12:04


ማፍቀር ግን እንዴት ደስ ሚል ነገር ነው

እህቴ ድምፅዋን ቀንሳ በሹክሹክታ ትስቃለች አንገትዋ ላይ ያለ ሀብሏን በጣቷ እየነካካች ተመስጣ ስልክ ታወራለች አጠገብዋ ቁጭ ብዬ ከቴሌፎኑ ጀርባ ያለውን ድምፅ እሰማለው ጎረምሳው ያወራል ቀብራራ ነው መሰለኝ ጅንንን ብሎ ያወራታል


ትዝታ

የኢናያ ደብዳቤዎች💨

26 Oct, 07:04


ስልክ ጀርባ ያለችውን 200ብር ከዘረዘርኳት