የኮሌጃችን ት/ት ሥልጠና ዘርፍ ኃላፊና ም/ዲን አቶ ታሪኩ ጨመረ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጄንሲ መሪነት በተለያዩ የሙያ ደረጃዎችና መስመሮች ከቀን 26/03/17 ዓ/ም እስከ 27/03/17 ዓ/ም ድረስ ሲካሄድ የቆየው የሙያ ብቃት ምዘና ሂደት በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡
የዘርፉ ኃላፊዉና ም/ዲኑ አያይዘውም፣ ለሥራው ስኬት የበኩላቸውን የተወጡ የኤጄንሲው ማኔጅሜንትና መዛኞችን፣የኮሌጃችን ት/ት ክፍል ኃላፊዎችን፣ የሙያ ብቃት ምዘና ሠራተኞችን፣ኮሚቴ አባላትን ና የኮምፒውተር ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎችን አመስግነዋል፡፡
የኮሌጃችን ሙያ ብቃት ምዘና ማስተባበሪያ ኃላፊ መ/ር በለጠ ቦቴ በበኩላቸው፣ምዘና የተሰጠው በአሮጌውሥርዓተ-ትምህርት በሰብል ልማት በሙያ ደረጃ ሁለት እስከ ዓራት፣በእንስሳት እርባታ በሙያ ደረጃ ዓራት፣በተፈጥሮ ሀብት አያያዝ በሙያ ደረጃ በሦስትና ዓራት መሆኑን በመግለጽ፤ በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በሰብል ልማት፣በእንስሳት እርባታ፣በተፈጥሮ ሀብት፣በመስኖና ዲሬይኔጅ እንዲሁም ሕብረት ሥራ ሂሳብ አያያዝና ኦዲትንግ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
መ/ር በለጠ አክለውም፣ በአሮጌው ሥርዓተ-ትምህርት የተመዘኑትን 253 ና በአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት የተመዘኑትን 254 ተመዛኞችን ጨምሮ በአጠቃላይ 507 ተመዛኞች መመዘናቸውን ተናግረዋል፡፡