"ስድብ ኃጢአት ባይሆን ኖሮ መሰደብ የሚገባው ዲያቢሎስ ነው:: ፍጥረት ሁሉ ስድብ ቢያዋጣ ለዲያቢሎስ የሚመጥን አይሆንም:: የክፋት ምንጭ ለሆነ ለእርሱ ሁሉም ክፉ ቃል መገለጫው ነው::
ይሁንና ቅዱስ ሚካኤል ይህንን ክፉ ጠላት ደፍሮ አልሰደበውም:: "እግዚአብሔር ይገሥጽህ!" አለው:: (ይሁ 1:9)
እንደ ሚካኤል ንጹሕ በእኛ ዘመን ማን አለ? እንደ ዲያቢሎስስ ክፉ በእኛ ዘንድ ማን አለ?
መልእክቱ ግልጽ ነው:: አንሆንም እንጂ እንደ ሚካኤል ንጹሕ ብንሆን እንኳን እንደ ሰይጣን የከፋን ሰው እንኳን መሳደብ አንችልም::
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም::" (ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
✨ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቀን