አንተ ጋር ለወንጀሌ መድሀኒት አገኝለው አለው?
#መልስ፦እሳቸውም አሉት ወደ ኢማን ሸለቆ ሂድና የጥሩ ኒያን ስር ያዝ እንዲሁም ደሞ የተዋዱዕ(የመተናነስን) አፈር ቆንጥር ከዛ የእውቀትን ፍሬ ያዝና አንድ ላይ አድርገህ በተውባ መፍጫ ፍጫቸው፦
ሁሹዕ በሚባል እቃ ውስጥ አድርገህ የሂይወትን ውሀ ቀላቅልበት ከታች ደግሞ ኸውፍ(ፍራቻ) ይዘህ እሳት ውስጥ ዛሂድ(ዱንያን የተወ) በሚባል እንጨት አቀጣጥለው ከዛ በሷብር መጠጫ ጠጣው እና የምትጠጣበት ቦታ ደግሞ ከአላህ ውጭ ማንም እንዳያይህ
* እንደዚህ ካደረክ ከወንጀልህ ተሽሎህ ትመጣለህ*
©ወደ ጌታህ ተመለስ