ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌 @rihu_islamic_post Channel on Telegram

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

@rihu_islamic_post


ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡[3:104]

ስህተቶች ስታገኙ አስታከክሉን በረከሏሁ ፊኩም
GP @Rihu_islamic_Discussion

ከናንተም ወደ በጎ ነገር (Amharic)

እንኳን ለእናንተም እና ለበጎ ነገር የምልክበት ወደ በጎ ነገር ሜዳተ ሥራ እንዲሆን ብዙ ትእዛዝ ከናንተም በትር ወደ በጎ ነገር የመረጃዋን ይከታተሉ፡፡ ከክፉ ነገር ላይ ወደ በጎ ነገር ሜዳተ ሕጋም የምንያዙ ሕዝቦችን በመልኩ ይበልጥል፡፡ የፖስት ማስታወቂያዎችን ለማግኘት የሚየተዘምናና ምሳሌና እንዘምንዎትን ወደ በጎ ነገር እንደሚያሰፋል በመሆኑ እነዚያ ሌሎች የእስላም ተባንኖች ናቸው፡፡ በበዎ አባላትና በበዝነኝ ተመሷሷል፡፡፡ እባኮት በ@Rihu_Tube_bot ያስሩት፡፡ በተጨማሪ አገባብ ወደ @Rihu_islamic_Discussion እንቀርባለን፡፡

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

13 Jan, 16:55


ኒቃቡ ጅልባቡ አቤት ሲያምርብሽ
ተዋቢ ልበሽው ካፊሮች ይቅኑብሽ

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

11 Jan, 04:52


📲「 በስልክ መቅራት 」📖
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬

📌: አንዲት ሴት
ሀይድ ላይ ባለችበት ወቅት ቁርአንን በእጇ ይዛ መቅራት ስለማይፈቀድላት በሞባይል ላይ በተጫነው ቁርአን ከፍታ ብትቀራ ይከለከላል እንዴ ⁉️

📜 ≠「
መልስ  」∬

:በውስጣቸው የቁርአን ቅጅ የተጫነባቸው
ሞባይሎች የመፅሀፉን ቁርአን አይነት ተመሳሳይ ፍርድ የላቸውም። ምክንያቱም የመፅሀፉ ቁርአን የሚታይየሚዳሰስና የማይወገድ ፅሁፍ ሲሆን የስልኩ ግን ጨረር ስለሆነ የማይዳሰስና ወዲያውም በቀላሉ ማጥፋት የሚቻል እና ፊደላቶቹም እዛው ስልኩ ላይ ሁሌ የፀኑ ሳይሆኑ ሲያፈልግ ብቻ ግልፅ የሚሆኑ በመሆኑ ነው። በዛ ላይ ስልክ ቁርአን ብቻ ሳይሆን ሌላም ነገር የተጫነበት ነው።

✒️:ስለዚህ በሀይድ ላይ ያለችም ትሁን በጥቅሉ
ያለ_ጡሀራ በስልክ ላይ የሚገኘውን ቁርአን ማንበብ ይፈቀዳል። እንደውም አንዳንድ ኡለሞች ይህ ሀይድ ላይ ላሉ እንስቶች ሀይዳቸው እስኪጠናቀቅ ድረስ ሙሉ በሙሉ ከቁርአን እንዳይርቁ ሲባል አሏህ ያመጣላቸው ማግራት ነውና ሙሉ በሙሉ ቁርአንን ከመተው ቢጠቀሙት የተሻለ ነው ብለዋል።

📗。*。📙
📘。\|/。📒
        🔎{ምንጭ🗂}
📔。/|\。📕
📓。*。🗃 °

🌐
https://www.almrsal.com/post/425653
🌐
https://islamqa.info/ar/answers/106961/قراءة-القران-من-الجوال-هل-يشترط-لها-الطهارة
🎙ፈታዊ ኑሩን ዓለድ–ደርብ ፣ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ 309 ፣

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

10 Jan, 18:06


#የሰው_ልጅ 🔍

:በምድር ላይ ሲኖሩ የሰው ልጆች የአላህ ምስክሮች ናቸው፡፡ ባዩትና በሰሙት ነገር ይመሰክራሉ፡፡ ሰዎችን በሥራቸዉና በባህሪያቸው መሠረት ክፉዎችንና ደጋጎችን ይመድባሉ፡፡

📸:ሰዎች አንድን ሰው ሲያዩ እሱን /ሷን ባዩበት ቅጽበት የሆነ ነገር ስለሚያስታዉሱ ከዚያ ሰው አንፃር  የሚሉት ነገር አላቸው፡፡ ብዙዎቻችንም እንዲሁ ነን ፦

🔴አንዳንዱን ስናይ “ሱብሓነላህ!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን “አልሐምዱሊላህ!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን “አዑዙ ቢልላህ!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን “ሐስቢየላህ!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን “አላሁ አክበር!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን “አስተግፊሩላህ!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን “ማሻአላህ!” እንላለን፡፡

🔴አንዳንዱን አይተን  “ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ!” እንላለን፡፡ 
 
🔴አንዳንዱን አይተን   “ላ ኢላሀ ኢልለላህ!” እንላለን፡፡

📌:ታዲያ እኛስ ሰዎች እኛን ሲያዩ ምን እንዲሉ እንፈልጋለን? እኛን አይተው ከሚደነቁ ወይስ ከሚማረሩ ?
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ  @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

09 Jan, 16:41


#ካስደነቁኝ_አባባሎች🔎

:ተምረናል እንጂ አላወቅንም *

:ተዋደናል እንጂ አልተፋቀርንም *

:እናወራለን እንጂ አልተገበርንም *

:እንሰብካለን እንጂ አልሰራንበትም *

:እንሞክራለን እንጂ አልፈፀምንም *

:እንስቃለን እንጂ አልተደሰትንም *

:እናለቅሳለን እንጂ አላዘንም *

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗
@Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

09 Jan, 02:34


:አንድ ሰው ሱንና ሶላትን እየሰገድ ሳለ ኢቃማ ከተደረገና ሱናውን ሶላት ቢያጠናቅቅ የግዴታው ሶላት ተክቢረተል_ኢህራም ኢማሙን ተከትሎ ወዲያውኑ ማለት እችላለሁ ብሎ ካመነ ሱንናውን ያጠናቅቅ። ተክቢረተል ኢህራሙ የሚያመልጠው ከሆነ ግን የሱንናውን ሶላት ያቋርጠው።

ሸይኽ አልባኒ  رحمه الله ፈታዋ ራቢጝ

ይሄ ማድረግ ሶላትን ከማበላሸት ሳይሆን የተሻለውን መልካም ስራ ከመምረጥ ነው የሚቆጠረው።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

08 Jan, 07:39


“በዚህ ዓለም እስካለህ በማንም ላይ ጥገኛ አትሁን፣ ጥላህ እንኳ በጨለመ ጊዜ ጥሎህ ይጠፋል።”

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

07 Jan, 17:47


➨እህቴ ለማን ነው የምትዋቢው ?
በጣም የሚያሳዝነው ብዙ እህቶቻችን መቆነጃጀት እራስን ማስዋብ ጥሩ ልብስ መልበስ የሚቀናቸው
ወደ ሰርግ ሊሄዱ ሲሉ
ወይም ጓደኛቸው ጋር ሲቀጣጠሩ
አንዳንዶች ደግሞ ወደ ሥራ ሲወጡ
ሌሎቹ ደግሞ የአላህ ባሮችን አሳስተው ወደ ሐራም ለመጥራት ያለ ምክንያት ሲወጡ
እና ለመሳሰሉት ነው
የባሎቻቸውን ሐቅ አሽቀንጥሮ ይጥላሉ።
🔅ከወጡበት ወደ ቤት ሲመለሱ ያ ሁሉ ያጌጡበት ነገር አውጥተው ይወረውራሉ
ባል ሲመጣ በማድ ቤት ልብስ በላብ ሽታ
በሊጥ እጅ በሽንኩርት ባለቀሰ ዐይን
በተንጨባረረ ፀጉር
በተዝረከረከ ገፅታ ከሷ እንዲርቅ በሚያደርግ ሁኔታ ትቀበለዋለች ተመልከቺ እህቴ ባለቤትሽ ላንቺ ምን አይነት ፍላጎት ይኖረዋል በዚህ ሁኔታሽ ምን አይነት የፍቅር ስሜትስ ያገኛል።
እንዴትስ ያንቺ ታደርጊዋለሽ
በተለይ ከቤት ወጥቶ አስከ ሚመለስ አላህን በማይፈሩ የለበሱ መስለው ራቁታቸውን ሆነው ወደ ጀሃነም በሚጣሩ ተከቦ ከሸይጣንና ነፍስያ ጋር ታግሎ ወዳንቺ ሲመጣ ያን በሚያብስ ገፅታና ሐላል ፍቅር ተቀብለሽ ማስተናገድ ካልቻልሽ በሌባ ላለመዘረፍሽ ምን ዋስትና አለሽ።
አው የቤት እመቤት ስትኾኚ እናት ነሽ።
ይህ ማለት መዝረክረክ ማለት አይደለም
ይህ ማለት እቤት ውስጥ እራስን መጣል ማለት አይደለም
አንቺ ለልጅሽም እናት ነሽ
ለፍቅርሽም እናት ነሽ
ለቤትሽም እናት ነሽ እናት በሁሉም የእናትነት ድርሻዋ የተዋጣላት ናት
እቤት ውስጥ ያለብሽን ሃላፊነት ከመወጣትሽ ዋናውና ትልቁ የትዳር አጋርሽን የፍቅር ቱኩሳት ሳይበርድ ጠብቀሽ ማቆየትሽ ነው
ይህ ደግሞ ውስጥሽን አላህን በመፍራት ላይሽን ባለሽ ልብስና ጌጥ በማስዋብ ነው ይህን ካላደረግሽ ስትወጪ የምትዋቢው ለማን ነው ??

***
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ  @Rihu_islamic_post💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

06 Jan, 16:02


🌻「 አይገርምም ግን ? 」🔭
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
:ቢላዋ የተለመደው ጥቅሙ ለመቁረጥና ለመቅላት ነበር፡፡ በነቢዩ ኢብራሂም (ዓለይሂ ሰላም) እጅ ሆና በነቢዩ ኢስማዒል (ዓለይሂ ሰላም) አንገት ላይ ስታርፍ ግን የአላህ ትእዛዝ ነበረባትና ዶለዶመች::ለመቁረጥም ፈቃደኛ ሣትሆን ቀረች።(አስ ሷፋት፡103)

:እናት በልጇ ጉዳይ ከራሷ በቀር ማንንም የማታምን ከየትኛውም ፍጥረት በበለጠ ለልጇ አዛኝ እና እሩህሩህ ፍጥረት ናት:: የነቢዩ ሙሳ (ዓለይሂ ሰላም) እናት ግን ዐይኗ እያየ ልጇን በሣጥን አድርጋ ወደ ባህሩ ወረወረች:: በአላህ ላይ እምነቷ ከፍ ያለ ነበርና፡፡ ቃል የገባላት ጌታ ከልጇ መልሦ እንደሚያገናኛት ታውቅ ነበርና፡ (አል ቀሶስ ፡7)

:እሣት በባህሪዋ አቃጣይ ናት፡፡ የቀረባትን ሁሉ ትፈጃለች:: የደፈራትን ያለ ምህረት ትበላለች:: ይህም በመሆኑ ለአጥፊዎቹ የጀሀነም ሰዎች ተዘጋጀች፡፡ ነቢዩ ኢብራሂም (ዓለይሂ ሰላም) ግን ሙቀቷ ከሩቅ ቦታ በሚፋጀው በላይዋ ላይ የሚበረውን በራሪ ጭምር ስባ ወደራሷ ወደምትከተው እሣት ከሩቅ መንጀኒቅ በተባለ መሣሪያ ተስፈንጥረው መሃሏ ላይ ቢጣሉም የሰከነችና ሰላማዊ ሆነችላቸው:: ጌታዋ “ለወዳጄ ኢብራሂም ቀዘቃዛና ሰላማዊ ሁኚ ብሏታልና፡፡ (አል አንቢያእ ፡ 69)

:የባህርን ማዕበል ታላቅ ዋናተኛ አይደፍረውም::
ተራ መርከበኛም አይጋፈጠውም፡፡ ለነቢዩ ሙሳ (ዓለይሂ ሰላም) እና ለተከታዮቹ ግን ግዙፉ ባህር የአላህን ትእዛዝ መፈፀም ነበረበትና ለሁለት ተከፈለ፡፡ ውሃውም ደረቅ ሜዳ ሆነ::

🌿:አላህን የያዘ ትልቁን ገመድ ያዝ፡፡ በርሱ የተመካም እውነት መመካት በሚገባው ተመካ፡፡ ነቢዩ የዕቁብ (ዓለይሂ ሰላም) ልጃቸው በትንሽነቱ ከርሣቸው ከተለየ ጊዜ ጀምሮ ሙሉ ተስፋቸው በአላህ ላይ ነበር::አላህም(ሱብሃነሁ ወተዐላ)ተስፋቸውን በተስፋ አላስቀረም ፤ ከልጃቸው አገናኛቸው:: ለዘመናት ያለ ግድብ ሲፈስ የነበረ እንባቸውን አበሠ ፤ ሊጠፋ የተቃረበ ዐይናቸውንም ብርሃን መለሰ፡፡ (ሱረቱ ዩሱፍ ቁ፡96)

🔸:ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺃَﻣْﺮُﻩُ ﺇِﺫَا ﺃَﺭَاﺩَ ﺷَﻴْﺌًﺎ ﺃَﻥ ﻳَﻘُﻮﻝَ ﻟَﻪُ ﻛُﻦ ﻓَﻴَﻜُﻮﻥُ

🔹:ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ ኹን ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም፡፡(ያሲን ፡ 82)


╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

06 Jan, 03:22


በነብዩ ﷺ ዘመን

:በነብዩ صل الله عليه وسلم ዘመን ሴቶች በቀጥታ ከወንዶች ኋላ ሆነው ነበር የሚሰግዱት:: መጋረጃ ማድረግ እየቻሉ ነገር ግን አላደረጉላቸውም:: ለሴቶች የተለየ ክፍልም ማዘጋጀት ሲችሉ ግን ደግሞ አላደረጉትም።

💡ዛሬ ላይ አንድት ሴት መስጅድ ሄዳ  ለሴቶች ተብሎ ታጥሮ የተዘጋጀውን መስገጃ  ቦታ በመተው ከወንዶች ኋላ ያለምንም መጋረጃ ብትሰግድ ሰዎች ምን ይሏታል ? እብድ ወይስ ጤነኛ

🔖ለማንኛውም ለሴቶች የተለዬ መጋረጃ  ማድረግ፣ የተለየ ክፍል ማዘጋጀት ጥንት የማይታወቅ፣ በመልካሞቹ ትውልዶች ዘመን ያልተለመደ ተግባር መሆኑ ነው አይደል?

🚩:#የኢማማቸውን አሰጋገድ ብቻ ሳይሆን ኢማማቸው የት ቦታ እንደሆነም ጭምር እንዳያውቁት ነውኮ ያደረጋቸው። ኧረ አንዳንድ እህቶች የወንዶቹ መስጂድ ምን ምን ይኖረው ይሆን ብለው እስከማሰብም ይደርሳሉ።



📍:በጆበርግ ከተማ ታላቁ ጁማ መስጂድ ሴቶች የወንዶቹን መስጂድ እንዲያዩት የተለዬ ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸው ፣ ገለጻ አድራጊ ተመድቦላቸው፣ በሰአቱም ወንዶች እንዳይገቡ ክልከላ ተደርጎ ነበር። በነብዩ صلى الله عليه وسلم ዘመን ግን ሴቶች ስለነብዩ መስጂድ ሁለነገር ያውቁ ነበር።

🖥:የመካ ክልሉ ሙፍቲ እንድሁም የኢብኑ ባዝ መስጂድ ኢማምና ኸጢብ ሸይኽ ሙሀመድ ዑመር ባዝሙል حفظه الله  ከአመታት በፊት በፌስቡክ ከለቀቁት ጽሁፍ ከተወሰኑ ማሻሻያዎች ጋር የተተረጎመ

منقول
╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

05 Jan, 18:00


#✉️

1️⃣መስጂድ ቁጭ ብለህ ሰላት በምትጠባበቅበት ወቅት ፣

2️⃣የታመመን ስትጠይቅ ፣

3️⃣በሰላት ላይ የመጀመሪያው ሰፍ ስትቆም ፣

4️⃣ሙስሊም ወንድምህን  ስትዘይር ፣

5️⃣በሩቅ ለወንድምህ ዱአ ስታደርግ ፣

6️⃣ሰዎችን መልካም ነገር ስታስተምር ፣

7️⃣ውዱእ አድርገህ ስትተኛ ፣

🔖በነዚህ ሁኔታዎች እስከሆንክ ድረስ መላኢካዎች ላንተ ዱዓ🤲 ከማድረግ አይወገዱም።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

03 Jan, 03:11


ከአንድ ሰው ጋር በሀሳብ ስላልተስማማን ብቻ ስሙን ለማጥፋት አንሩጥ። በስድብ፣ በሀሜትም ይሁን ዝናውን ለማፈራረስ አንድከም። ክብሩን ለማውረድ አናሲር። ሰላም ለማሳጣት አናውጠንጥን። ሙስሊም የሆነ ሰው ሁለመናው የተከበረ ነው። አላህ መልካም ባሮቹን ሲነኩበት በእጅጉ ይቆጣል። ከቁጣው ፊት ችሎ የሚቆም ካለ ደጋግ አማኞችን ይዳፈር። የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በሀዲሳቸው አላህ(ሱብሃነሁ ወተዐላ) እንዲል ብሏል ብለዋል፦

🟠مَنْ عَادَى لِي وَلِيًّا فَقَدْ آذَنْتُهُ بِالْحَرْبِ

🔘አንድን የኔን ባሪያ ጠላቱ አድርጎ የያዘን ጦርነት አውጄበታለሁ

📚‌✿・⁺ [ ቡኻሪ ]


╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

02 Jan, 07:43


➡️:ከጠፋህም ይጨነቃሉ ፣ ብዙ ከታየህም ይጨነቃሉ ፣ ችግር ላይ ነኝ ካልካቸዉም ይጨነቃሉ፣ አሞኛል  ስትላቸዉም ይጨነቃሉ ፣ ከተናገርክም ይጨነቃሉ ፣ ዝም ካልክም ይጨነቃሉ።  የአንዳንድ ሰው መጨነቅ ለተጨነቀ ወይም ችግር ላይ ላለ ሰው ተጨማሪ ጭንቀት ወይም ችግር ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ጭንቀታቸው እስኪያልፍላቸው ጠብቋቸው። በጥያቄም አታሰልቿቸው። ምን ሆና/ሆኖ ነው ብላችሁም እንደ እናት ሆድ አትንቦጅቦጁ።

🍀:የቀናት ማለፍ ብቻ የሚፈቷቸው ችግሮቻችን ብዙ ናቸው ወዳጆቼ። ዱንያ እንደሆነች ክብ ነች። ደስታና ሐዘን፣ ችግርና እፎይታ፣ ማግኘትና ማጣት፣ መውደቅና መነሳት ዞሮ መምጣት ልማዳቸው ነው። ዱንያ ጀነት አይደለችም፣ ዘወትር አንደላቃ አታኖርም።

منقول

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

02 Jan, 07:34


#✉️

🔺ሰዎችን ለማስረዳት ድምፅህን ሳይሆን አነጋገርህን ከፍ አድርግ፣ ተክሎችን የሚያጠጣው ዝናብ እንጅ መብረቅ አይደለም።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

31 Dec, 18:29


💠አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና። የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን ስታስታውስ ፣ ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

አላህ መልካም የምንስራ ያድርገን~🤲

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

30 Dec, 14:48


ኑ ጌታችንን እንወቅ ❗️

:የሰው ልጅ አዕምሮ አስተሳሰቡ የተገደበ ነው ወይም limit አለው ሲባል አይገባኝም ነበር። ነገር ግን ይሄን ጉድ ስሰማ የአዕምሮ የማሰብ ገደቤን በሚገባ አውቄዋለሁ። እናንተም እዩት የአዕምሮ ገደባችሁን ታገኙበታላችሁ።

╭┈─────── ೄ🌹࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Rihu_islamic_post💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

29 Dec, 12:51


የህሊና 🦋 ዕረፍት

:አቡ የዚድ አል በስጣኒ የተባሉ ሰለፍ:-

⬅️ጌታዬ ሆይ አንተን በመውደዴ አልገረምም ምክኒያቱም እኔ ተራ #ሰው ነኝና። ነገር ግን አንተ እኔን በመውደድህ በጣም #እገረማለው።ምክንያቱም አንተ የላቅክ ታላቅ ጌታ ስትሆን ተራ የሆነን ባሪያህን ወዳጅ ነህና➡️

💎:እንዴት የሚያምር ንግግር ነው! የእኛ አላህን መውደድ ሳይሆን የአላህ እኛን መውደዱ ነው ሊያስደንቀን የሚገባው።ምክንያቱም እኛ አላህን በመውደዳችን ለአላህ ልናበረክተው የምንችለው ነገር የለም።አላህ እኛን በመውደዱ ግን በርካታ ፀጋዎችን እናገኛለን።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

27 Dec, 15:50


📨:ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው። መሥራት ባትችሉ አመላክቱ ፣ መፃፍ ባትችሉ ሌሎች የፃፉትን አጋሩ።

↬ዱንያ ላይ የምንቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። ምድር ላይ እንደሁለተኛ ዕድሜ ሆኖ የሚያገለግለን ዛሬ እዚህ የምንጽፈው ነገር ነው። ከሶላታችን ፣ ከፆማችን ምንም ምንዳ ላይኖረን ይችላል። መልካም ነገሮችን ማጋራት ወደ አኺራችን ከምናስቀድማቸው ጠቃሚ ስንቆች መካከል አንዱ ነው። ብልህ እንሁን። አላህ ያፅናን።

🔴 ዓለማዊ ጥቅም አለው ብዬ አልወተዉታችሁም፣ በስነልቦናም ሆነ በዲኑ ጉዳይ ሊጠቀምበት የሚችል ሰው ሊኖር ይችላልና ይህን #ቻናል አጋሩት። ╭┈─────── ೄ🌹࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

27 Dec, 15:46


ጭንቀት

💥:በመጨነቅና በማማረር ያመጣነው ለውጥ የለም፡፡ ተነስቶ መንቀሳቀስ እንጂ ዘግቶ ማልቀስ የፈየደን ነገር አላየንም፡፡ በጭንቀት ስንዝር ያህል እንኳን ነገሮችን መግፋት አንችልም፡፡ የጎደለ ኑሮ የሚሞላው #በሥራ እንጂ በጭንቀት አይደለም፡፡ ተጨንቀን ብዙ አየን፡፡ ጭንቀትን ትተንም አየን፡፡ ሰፊ ልዩነቱን በርግጥም አስተዋልን፡፡ ዘና ብለን ስንስቅላቸው ረጃጅም ቀናቶች አለፉ፡፡ ትላልቅ ሸክሞች ረገፉ፡፡ ከባባድ ችግሮችም ተረሱ፡፡ እናም ፈታ በል ፤ ዘና በል፡፡ አትጨነቂ ፣ አትጨነቅ 🦋

:የነገሮች ዋና መሰረታቸው ቀደር ነው፡፡ ቀደር ማለት ደግሞ ቀድሞ የተላለፈ የአላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ውሳኔ ነው፡፡ ለተወሰነና ላለፈ ነገር "መዐልኤሽ!" ምንም ማለት አይደለም በል፡፡

❗️ብርጭቆ ሰበረ ብለህ ልጅህን ከቤት አታባርር፡፡

❗️እንጀራው አረረ ብለህ ከሠራተኛህ ጋር ቦክስ አትግጠም፡፡

🔎አንዳንድ ሰዎች ይገርሙኛል ፤ ሳይመቱ ከተመቱት በላይ ይጮሃሉ፡፡ መቶኝ ነበር ፈንክቶኝ ነበር ለጥቂት ነው የሳተኝ ብለው ቂያማ ያቆማሉ፡፡ እንኳንም የሳተህ ባይስትህ ኖሮ ጣጣህ ብዙ ነበር፡፡ ሳይፈነክትህ እንዲህ የሆነክ ቢፈነክትህ ኖሮ እንዴት ትሆን ነበር!፡፡ በዚህች ዓለም ላይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በርሱ ፈቃድ ነው፡፡ በፈቃዱ ተማረን ምን ልናመጣ ነው?፡፡ የወደደውን አንወድም ብለን ምን ልንሆን!፡፡ ፌንጣ ብትቆጣ ክንፏን ጥላ መብረር ካልሆነ ምን ልታመጣ!

🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

💡:እስልምና አትጨነቁ ይላል፡፡ የፈጠረን ጌታ ‹እመኑ፣ በርቱ፣ ትጉ፣ ተስፋ አትቁረጡ፣ አትስነፉ፣ አትድከሙ፣ አትዘኑ፣ አይዟችሁ፡፡ …› ብሏል፡፡ በመልካም ትዕግስትና ተስፋ አደራ ይላል፡፡ በጥሩ መጨረሻና ስኬት ቃል ይገባል፡፡ ነቢዩ (ﷺ) ምንም ሊረዷቸው ባልቻሉ ጊዜ ‹የያሲር ቤተሰቦች ሆይ! ትእግስት አድርጉ ቀጠሮአችሁ ጀነት ነው፡፡› ብለዋቸዋል፡፡

:ሞኝ የሆነ ይጨነቅ፡፡ እኔ ሞኝ አይደለሁም አልጨነቅም፡፡ ዕድሜዬ አጭር መሆኗን አውቃለሁ፡፡ መሞቴ ላይቀር ለምን ቀድሜ እሞታለሁ፤ ለማንስ ለምንስ ብዬ እታነቃለሁ፡፡ መድረሱ ላይቀር ለምን ቀድሜ ፈግማለሁ፡፡ አልጨነቅም - ተጨንቄ ምን አገኘሁ! ተበሳጭቼስ ምን አተረፍኩ፡፡ ተናደውና ራሳቸውን መቆጣጠር አቅቶአቸው ሰው የደበደቡ እስር ቤት ናቸው፡፡ ተበሳጭተው የተሳደቡ ‹ምኑ ባለጌ ነው?› ተብለው በሰዎች ትዝብት ዉስጥ ገብተዋል፡፡ ስብእናቸውን አስንቀዋል፡፡ ምን አስጨነቀኝ፡፡ ቦታዬ አላህ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡ አላህ ዘንድ አልጉደል እንጂ እዚህ ኪሎዬን ቢቀንሱ ስድባቸው አይለጠፍብኝም፡፡ ከአላህ ጋር እስካለሁ ዘና እላለሁ፡፡

:የደስታችን መሰረቱ አላህ ብቻ ይሁን፡፡ ከሁሉም በላይ ከርሱ ጋር የሚኖረንን ግንኙነት እናሳምር፣ እሱ እንዳለውና እንዳዘዘው ለመኖር እንሞክር፣ ህግጋቱን ከመጣስ እንጠንቀቅ፣ ድንበሩን አንጋፋ፡፡ ከአላህ ጋር ስንሆን አካላዊ ለውጥ ላይኖረን ይችል ይሆናል፣ ኪሎ ላንጨምር እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ዉስጣዊ ሰላምና የበዛ ደስታ ይኖረናል፡፡ በዚህ ደግሞ ሁሉንም ነገር ማሸነፍ እንችላለን፡፡ ጣሉት ጃሉድን ያሸነፈው፣ ሙሳ ፈርዐውንን የረታው፣ ኢብኑ መስዑድ አቡጀሀል አንገት ላይ የወጣው … በሥጋ ግዝፈት ሳይሆን በኢማን ጥንካሬ ነው፡፡ የኢብኑ መስዑድ እግር ቅጥነቱ ቢያስገርምም ‹የቂማ ቀን ሚዛን ላይ ከኡሑድ ተራራ በላይ ክብደት አለው፡፡› ብለዋል ነቢዩ (ﷺ)፡፡
╭┈─────── ೄ🌹࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

26 Dec, 05:30


#ካገኘሁት 🖥

:መልካምነት ደግ መስራት ብቻ ሳይሆን ክፉም አለመስራት ነው።

:መኖርን እንደተቀበልቅ ፈተናዋንም ተቀበል።

:እየሳቀ ሀጢአት የሰራ እያለቀሰ ጀሀነም ይገባል።

:ለማወቅ ተቸገር ለማገኘት ጣር ከትልቅ ባህር ምርጥ አሳ ይገኛል።

;አጀማመርህን ካሳመርክ ከፊሉን ጨረስክ ማለት ነው።

:ለራበው ሰው ሁሉም ነገር ጣፋጭ ነው።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @Rihu_islamic_post 💌

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

25 Dec, 07:08


አስገራሚ እውነተኛ ታሪክ " !!

ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ ፡-

 🔻 - አንድ የማምነው ሰው እንዲህ ሲል አወራኝ ፡
የሆነ ሰው ነበር ሚስቱ ለማንኛውም ቤት ቆርቁሮ ለሚለምን ሚስኪን ዳሀ ምንም አይነት ነገር እንዳትሰጭ ብሎ ይከለክላት ነበር ፡፡

🔻ከዕለታት አንድ ቀን የሆነ ዳሀ ሚስኪን ቤቱን ይቆረቁራል ፡ ከዚያ ሚስት ቤቱን ስትከፍት ይህ ሚስኪን እንዲህ አላት ፡ እመቤቴ እባክሽን የምለብሰው የሌለኝ እርቃን ነኝ ከብርድ ራሴን የምከላከልበት ልብስ የሌለኝ ሰው ነኝ ? ባላት ጊዜ ፡ ይች የዚህን ሚስኪን ሁኔታ ያየች ሚስት አላቻላትምና ከቤቷ ውስጥ በመመለስ ልብስ እና ሶስት ተምሮችንም ጭምር ሰጠችው እና ሄደ ፡፡

🔻የዚች ሴት ባለቤት መስጂድ ውስጥ ተኝቶ ነበር ፡ ይህ ባሏ በህልሙ ልክ ቂያማ ስትቆም ያያል ! ሰዎች ሁሉ ትርምስምሳቸው ወጥቷል ! ሰወች በጣም ብርቱ በሆነ የፀሃይ ቃጠሎ ውስጥ ናቸው ! ልክ ይሄን አስደንጋጭ ክስተት እየተመለከተ ሳለ ከበላዩ የሆነ ልብስ ከዚህ ከፀሃይ ቃጠሎ ይከልልለታል ፡ ግና ይህንን ልብስ ሶስት ቦታ ተሸነቋቁሮ ያየዋል ፡ ከዚያም የሆኑ ሶስት ተምሮች መጥተው እነዚህን ሶስት የሽንቁር ቀዳዳ ቦታወች ሲደፍኑት ተመለከተ ፡ በጣም ተገረመ ፣ ተደነቀ በዚህ ህልም ፡ ወዲያው ከእንቅልፉ ባነነ እና በድንጋጤ ወደ ቤቱ በፍጥነት በማምራት ያየውን ህልም ሙሉውን ለሚስቱ ተረከላት ፡  ሚስትም ይህ ህልም  በእነዚያ በሰጠቻቸው ልብስና ተምሮች ሰደቃ ምክኒያት መሆኑን ስለለተረዳች ፡ ያ ሚስኪን ዳሀ ቤት መጥቶ የሰጠችውን ልብስና ሶስት ፍሬ ተምሮች ነገረችው ለባሏ ፡

ከዚያም እንዲህ አላት ፡ አደራ ከዚህ ቡሀላ አንድንም ዳሀ ከደጄ እንዳትመልሽ ፡፡

☞ ይህ ሰው አሏህ አነቃው ፡ ይሄም ክስተት ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የተናገሩትን ሃዲስ ያስመሰክራል ፡

🔻ነብዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይለሉ፡- የቂያማ እለት አሏህ በሰዎች መካከል ፍርድ እስኪሰጥ ድረስ ሁሉም ሰው ከሰደቃው ጥላ ስር ነው የሚጠለለው ፡፡

📚ምንጭ፡- ሸርሁ ኪታብ አል ረቃኢቅ ከሶሒህ አል ቡኻሪ (ገፅ/6)


ኢብነል ቀይም እንዲህ አሉ፡-

  ☞- ሰደቃ የአደጋ አይነቶችን የመከላከል ልዩና አስገራሚ ተፅዕኖ አለው ፡ ከአረመኔ ወንጀለኛ እና ከግፈኛና በደለኛ እንዲሁም ከካፊር ቢሆንም እንኳን ፡፡

 ☞ አሏህ በዚች በሰደቃው አማካይነት ከተለያዩ አደጋወች ይከላከልለታል ፡፡

  📚ምንጭ፡- አል ዋቢሉ ሶይብ (50/49)
  
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

30 Nov, 06:45


የኔ ጀግና!
~
ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኢስላምን ያጠለሹ፣ ሙስሊሞችን በአጉል ኮተቶች ጠፍረው ያሰሩ የሱፊያ ኮተቶችን የበጣጠሰ አንበሳ ነው። በጀሊሉ፣ በወሃቡ ፈቃድ የተሃድሶ ንቅናቄው የቀብር አምልኮትን ግንድ ከምድረ ሰዑዲያ ገንድሶታል። በመላው የሙስሊሙ አለም ያለውን የበሰበሰ የሱፊያ ሸክም አነቃንቆታል። ኧረ ክፉኛ ወዝውዞታል።
በዚህ የተነሳ ሱፊዮች ዘንድ እንደሱ የተጠላ ፍጡር የለም። የተፃፈ ኹጥባ ለማንበብ ሚንበር ላይ ወጥቶ የሚንገዳገደው ሁላ እየተነሳ "ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ጃሂል ነው" ሲል የምንሰማው ያለ ምክንያት አይደለም። ይገባናል፣ የሚያስጮሃችሁ ህመማችሁ ነው። "አሶራኹ ዐላ ቀድሪል አለም" እንዲል ዐረብ። "ጩኸት በህመም ልክ ነው!"
ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ እንዳንተ ሶደቃ ሲያባር እድሜውን አልፈጀም። ጋርዶ ጫት የሚቀረጥፍ ቦዘኔ አልነበረም። ሁሉን እንዳመጣጡ ያስተናገደ፣ ለቆመበት አላማ ቆርጦ የተነሳ፣ ከዚያም እስከ ደም ጠብታ የታገለ ቆራጥ ነበር፣ የጀግና ጀግና! የፅናት፣ የትጋት፣ የብቃት ተምሳሌት!
ዛሬ ግን ይሄ ነው የሚባል የዒልም ቅሪት የሌለው፣ ኢስላምን የግል ጥቅም መሸመቻ ያደረገ፣ ከሆዱ አሻግሮ መመልከት የማይችል ቦዘኔ ሁላ እየተነሳ "እሱ'ኮ ጃሂል ነበር" ይላል። እርሱ ጃሂል ከነበረ አንተ ጅህልና እራሱ ነህ!

"ወሃብዮች ዑለማእ አያከብሩም" የሚሉ አስመሳዮች ሁላ በሸይኹ ላይ ምላሳቸውን ሲያሾሉ ማየት በስፋት የተለመደ ነው። ግማሹ "ተ'ክ'ፊ'ር ነው" ይላል። ግማሹ "የሁዲ ነው" ይላል። ግማሹ "የእንግሊዝ ቅጥረኛ ነበር" ይላል። ሌላም ሌላም ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ውንጀላዎች አሉ። እናንተ ናችሁ ስለ ዑለማእ ክብር የምታወሩት? በጀግኖቻችን ክብር ላይ እየተረማመዱ ከዚያ የነሱን የጥፋት ሰባኪዎች እንድናከብርላቸው ይፈልጋሉ።
በሃገራችን በመውሊድ ሰበብ ስማቸው ገኖ ከሚታወቁ ቦታዎች ጋር ተቆራኝቶ ዝናቸው ከናኘ መሻይኾች ውስጥ #ብዙዎቹ የእውነት እንደሚባለው በዒልም የላቁ እንደነበሩ የሚያሳይ ማስረጃ ብትጠይቁ አስቂኝ ነገር ነው የምትሰሙት። "እስኪ ኪታባቸውን አሳዩን?" ብትሉ "የመውሊድ መንዙማ ፅፈዋል" "ማዲሕ ነበሩ። መድሕ አዘጋጅተዋል" ብለው የግጥም መድብል ይነግሯችኋል። ዒልም ማለት ግጥም መፃፍ ነው እነዚህ የዞረባቸው ዘንድ! በዚህ የግንዛቤ አቅምህ ነው ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብን በጅህልና የምትወርፈው?! አዎ መውሊድ ያገነናቸው ብዙ ስመ ገናናዎች አሉ። ከመውሊድ ጭፈራ ባለፈ ከነ ጭራሹ በቦታው ምንም አይነት የዒልም እንቅስቃሴ የሌለባቸው ብዙ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

28 Nov, 05:17


بسم الله الرحمن الرحيم

👉ነፍስህን ለማሻሻል አራት መንገዶች አሉ (ናፍስ)።  ናቸው: 👌

➤1. #በራስህ_ላይ_ግዴታ_ማድረግ (مُشَارَطَه) ፦ *ኃጢአት እንዳሠራ ለራስህ ቃል ግባ።  ቀኑን ሙሉ ማንኛውንም ኃጢአት ላለማስራት በየቀኑ ጠዋት ላይ ለነፍስህ ቃል ግባ። ይከብዳል አቃለው ግን ታደርገዋለህ። 💪

➤2.  #ክትትል_አላህ_ያየኛል_ማለት (مُرَاقَبَه) ፦     ኃጢአት ፈፀምክ? ምንም ኃጢአት እንዳሠራ ራስህን መከታተልህን ቀጥል።

➤3.  #ራስንህን_መመርመር (مُحَاسَبَه) ፦ ስንት  ኃጢአቶችን እንደሠራህ ከስንት መልካም ሥራዎች !!!! ...
ማታ ፣ ከመተኛትህ በፊት ፣ ብቻህን ስትሆን ፣ ቀኑን ሙሉ ምን እንደተሳሳትክ እና ምን እንደተ ፈጠረ ገምግመው።

➤4.  #እራስን_ማረም (مُوَاخَذَه) ፦ በቀን ውስጥ ለፈጸመከው አለመታዘዝ ነፍስህን ቅጣት ፣ እናም ቅጣቱ የአምልኮን ሸክም በላዩ ላይ ማድረግ ነው።  ለተሳሳቱት ነገሮች ንስሃ በመግባት እና ለተከናወኑት መልካም ሥራዎች አላህን ሱብሃነ ወተዓላ ማመስገን።

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
╭─┅───══───┅─╮
@Rihu_islamic_post
╰─┅───══───┅─╯
⤴️⤴️ሸር &ጆይን ይበሉ⤴️

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Nov, 02:52


🌸🍃ደስተኛ ሁነህ መዋል ከፈለክ ፦

🌺 ሰላትን ከወቅቷ አታሳልፍ

🌺ቀንህን ስትጀምር በአላህ ላይ ጥሩ ግምት ይኑርህ በገመትከው ልክ ይገኝላሀልና

🌺 አላህም መሀርታ መጠየቅን አብዛ የሪዝቅ በር ይከፈትለሀል

🌺 በነብዩ ﷺ ሰለዋት ማውረድን አብዛ … አላህ ጭንቀትህን ያስወግድለሃል ወንጀልህንም ይምርልሀል

🌺 ለሰዎች ፈገግ በል ንግግርህንም ለዘብ አድርግ ውዴታቸውን ታገኛለህ

🌺በሀሳብህ ላይ የምትዘራውን በእርግጥም በህይወትህ ላይ የምታጭደው መሆንህን አትዘንጋ … ለዚህም ማጨድ የምትፈልገውን ብቻ እሰብ !


መልካም
ውሎ💐

@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Nov, 02:39


﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ﴾.

«اللَّهُمَّ اجْعَلْنَا من أفْضَلِ مَنْ تَوَجَّهَ إلَيْكَ وَأقْرَبِ مَنْ تَقَرَّبَ إلَيْكَ وَأنْجَحِ مَنْ سَألَكَ وَطَلَبَ إلَيْكَ».

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

22 Nov, 20:04


የመኝታ ዚክር ...
       〰️〰️〰️
بسمك ربي وصعت جنبي وبك ارفعه فإن أمسكت نفسي فارحمها وإن أرسلتها فاحفظها بما تحفظ به عبادك الصالحين »

~ትርጉም፦(ጌታዬ ሆይ በስምህ ወገቤን አሳረፍኩ በስምህም አነሳዋለሁ፥ነፍሴ ከያዝካት እዘንላት፣ከለቀቅካትም መልካም ባሮችን በምትጠብቅባት ጠብቃት።

🔖መተኛትህን ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ!

@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

19 Nov, 16:40


📌ትክክለኛው ተወኩል📌
~~~~
:ግመልህን እሰር በአላህ ተወከል።
~~~~
:ጣር፣ልፋ ፣ አንብብ ለማለፍ ተዘጋጅ በአላህ ተወከል።
~~~~
:ተሯሯጥ፣ነግድ፣ ሰበቡን አድርስ በአላህ ተወከል።
~~~~
:ቆፍር፣ አለስልስ ፣ ጊዜውን ጠብቀህ ዝራ በአላህ ተወከል።
~~~~
:በአላህ የሚመካን አላህ በቂው ነው።

🔰:ተወከልቱ አለሏህ . . . . . . . . .

♻️ @Rihu_islamic_post
♻️ @Rihu_islamic_post
♻️ @Rihu_islamic_post

#SHARE_The_خير_

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

19 Nov, 15:49


🔸" ﻭﻟﻴﺲ ﺍﻟﺬﻛﺮ ﻛﺎﻷﻧﺜﻰ"
🔹“ወንድም ልጁ እንደ ሴት ልጁ አደለም»

♦️ሴት ልጅ በሕይወት ዘመኗ በተለያዩ አካላዊና፣ ሆርሞናዊ ሂደቶች ዉስጥ ታልፋለች፡፡ ለምሳሌ በወር አበባ፣ በእርግዝና፣ በወሊድ፣ በማጥባት፣ በወር አበባ መቋረጥ ወቅት ….  ከባባድ የሆርሞን ለውጦች የሚታዩባቸው ጊዜያቶች ናቸዉና በባህሪዋም ላይ ለውጥ ቢታይ የሚገርም አይሆንም፡፡ እነኚህን ጊዜያት በተለይ የሕይወት አጋራቸው የሆኑ ወንዶች በሚገባ ማስተዋል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ማስተዋል ከሴት ልጅ አንፃር ለሚወስዱት እርምጃ ምክንያታዊና ትክክለኞች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ ብትነጫነጭ፣ ብትቆጣ፣ ብትበሳጭ፣ ሆድ ቢብሳት፣ ቢደብራት … ምን አባቷ! ብሎ ከመቆጣት  ይልቅ ምን ሆና ነው!? ብሎ ጠጋ ብሎ ነገሩን መመርመሩ ሳይሻል አይቀርም፡፡


                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆RP• @Rihu_islamic_Discussion   
┣━━━━╗ ❤️ ╔━━━━⎙
┣CHL• @Rihu_islamic_post
╠════•❁🎐❁•═════╣
🌐 #SHARE_The_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

15 Nov, 08:00


ዱንያ አጠፋፋችን አይደል አህባቢ 😶‍🌫️
ምንም ይሁን ምንም ለዱንያ እጅ አንሰጥም . . .

:ዱንያ ላይ ያለነው ለመኖር ነው፡፡ እስከኖርንም እጅ አንሠጥም #እንታገላታለን፡፡ እጃችንን ሰብስበን ዱንያን በብርቱ እንፋለማታለን፡፡ እና አላህ የሚታገሉትን #ይረዳልና በቻላችሁ መጠን ሁሉ ታገሉ፡፡ ⚡️

➡️የሆነች ነገር ሞክሩና 'ጌታዬ ሆይ በዚህች ላይ ትንሽ ጨምርልኝ' በሉ፡፡ የአላህ ትንሽ ነገር ብዙ ናት፡፡ የሱ ጠብታ እዝነት ተራራ ናት፡፡

. . .

:የቻላችሁትን ያህል በአላህ ትዕዛዝ ሥር ተገኙ፡፡

:አቅማችሁ በፈቀደው መጠን መልካም ሥሩ፡፡

:አላስተዋላችሁም እንጂ ብዙ ነገር ተሠጥታችኋል፡፡

:አላህ ከሠጣችሁ መልካም ቃላት ይሁን ገንዘብ ወይም ከሌላ ነገር አትሰስቱ፡፡

:በቀን ይሁን በማታ ለችግረኞች እጃችሁን ዘርጉ፣

:የተጨነቁትን አብሽሩ በሉ፣

:የየቲሞችን እንባ አብሱ፣

:ተስፋ የቆረጡትን አጽናኑ፣

:ሐዘን ለገባቸው ፈገግ አሳዩ፣

:ግራ ለተጋቡት ያልፋል በሉ፣

ሀሳብ ካዳከማቸው አጠገብ ሁኑ፣

:የተሰበሩትን ጠግኑ፣

:የተጎዱትን አክሙ፣

:ሸክም ለከበዳቸው መከታ ሁኑ፡፡



🫀:እንዲያ ስንሆን የዱንያን ፈተናዎች አብረን እንሻገራለን ። እንዲህ ጥሩ ስንሆን አላህ ይወደናል፤ ይቀበለናል፡፡ እሱ ከተቀበለን ሌላው ሁሉ ቢጥለንም ምንም አይደል፡፡  

🔥🔥🔥🔥🔥
✧╭┻┻┻┻┻┻┻┻┻┻╮✧
✧┃╱╲ 🍓╱╲🍒 ╱╲┃✧
╭┻━🍒━━━🍍━━━┻╮
┃╱╲╱╲ 🍈╱╲🍇 ╱╲ ┃
🎁━━━━━━━━━━━━🎁
💕 @Rihu_islamic_post 💕

🌐 #SHARE_The_خير🔺

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

15 Nov, 03:02


➥ወይ ምኞቴ‼️▯ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ▯

. . . .▯ ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ ﻛُﻨﺖُ ﻣَﻌَﻬُﻢْ ﻓَﺄَﻓُﻮﺯَ ﻓَﻮْﺯًا ﻋَﻈِﻴﻤًﺎ

🖱:▯. . . . . «ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በኾንኩ ወይ ምኞቴ!» ይላል፡፡▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 4-73●

●ﻳَﺎ ﻭَﻳْﻠَﺘَﻰٰ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ ﻟَﻢْ ﺃَﺗَّﺨِﺬْ ﻓُﻼَﻧًﺎ ﺧَﻠِﻴﻼً

🖱:▯«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 25-28●

●ﻳَﻘُﻮﻝُ ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ ﻗَﺪَّﻣْﺖُ ﻟِﺤَﻴَﺎﺗِﻲ

🖱:▯«ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ» ይላል፡፡▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 89-24●

●. . . . ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ اﺗَّﺨَﺬْﺕُ ﻣَﻊَ اﻟﺮَّﺳُﻮﻝِ ﺳَﺒِﻴﻼً

🖱:▯. . .. «ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ!»▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 25-27●

●. . . . ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨَﺎ ﺃَﻃَﻌْﻨَﺎ اﻟﻠَّﻪَ ﻭَﺃَﻃَﻌْﻨَﺎ اﻟﺮَّﺳُﻮﻻَ

🖱:▯«. . . . .ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ». . . .▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 33-66●

●. . . ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ ﻟَﻢْ ﺃُﻭﺕَ ﻛِﺘَﺎﺑِﻴَﻪْ

🖱:▯. . .. «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ». . . ።▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 69-25●

●. . . . ﻳَﺎ ﻟَﻴْﺘَﻨِﻲ ﻛُﻨﺖُ ﺗُﺮَاﺑًﺎ

🖱:▯. . . ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ. . . .▯
●𝗤𝗨𝗥𝗔𝗡 78-40●

🪧:በመጨረሻው በጭንቁ ቀን እንዲህ ከማለታችን በፊት ኸይር ስራን ባገኘነው አጋጣሚ እናስቀድም ችላ አንበል ትልቁ ፀፀት ማለት ይህ ነውወላሂ ከዚ በላይ ፀፀት የለም❗️
➠ነፍሳችን በሰውነታችን ውስጥ እስካለች ድረስ አላህ የሕይወታችንን አዲስ ቀን ሰጥቶናል። ጊዜው ሳይረፍድ እና ትልቁን ፀፀት ከመጸጸታችን በፊት አሁኑኑ በምርጥ አጋጣሚ ተጠቅመን (በረመዳን ወር) ወደ አላህ እንመለስ❗️

ﻭَﻣَﻦْ ﺃَﺣْﺴَﻦُ ﻗَﻮْﻻً ﻣِّﻤَّﻦ ﺩَﻋَﺎ ﺇِﻟَﻰ اﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻋَﻤِﻞَ ﺻَﺎﻟِﺤًﺎ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﺇِﻧَّﻨِﻲ ﻣِﻦَ اﻟْﻤُﺴْﻠِﻤِﻴﻦَ

➠ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?▯ፉሲለት-33▯

☑️:ይሄንኑ መልዕክት ሼር በማረግ በጎ ስራን ከአሁኑ እንጀምር።

@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

#SHARE_The_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

14 Nov, 09:43


አስሬ ማጉረሴ...

በህይወት መስመሬ እጅግ የሚነደኝ፡
እንቅልፍ እየነሳ ፀንቶ እሚያሳድደኝ፡

ተስፋ እያስቆረጠ ሁሌ የሚገድለኝ፡
ከውስጤ እማይጠፋ አንድ ብሶት አለኝ፡

ባስታወስኩት ቁጥር ሚያጣላኝ ከራሴ፡
አብሮኝ ለማይራብ አስሬ ማጉረሴ፡
@Rihu_Tube

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

12 Nov, 04:42


📐~በጥንቃቄ ይሁን~🖇
▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰
➧ከሞኝ ጋር ስተከራከር~🪧
➧ከአዋቂ ጋር ስትከራከር~📕
➧ክብር ያለውን ሰው ማዋረድ ስትሞክር~🔎
➧ደካማን ሰው ስታከብር~📌
➧ከመጥፎ ጋር ስትወዳጅ~🖍 በጥንቃቄ ይሁን።

📍~ሞኝነት ነው~📌

➧ተውባን ማዘግየት~
➧ሞትን መርሳት~🪔
➧ሚስጢርን ማባከን~🩸
➧አላማን መዘንጋት~💡
➧ግዴታን አለመወጣት~〽️
➧ጊዜን ማባከን~
➧ወላጅን አለመታዘዝ~🎗
➧ሰውን መበደል~💢 ሞኝነት ነው።

@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

#SHARE_The_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

12 Nov, 02:31


➡️የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር

@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

10 Nov, 18:50


بسم الله

-ቂርዓት ላይ ያለሽ እህት ሆይ ኢልም መቅሰም ሂወትሽን ሙሉ የምትሰጭዉ ዉድ ነገር ይሁን እንጂ እስክታገቢ ወይም ሀገር ቤት እስክትገቢ ጊዜ ማሳለፊያ አታድርጊዉ ።

- ሴት መሆንሽ ኣሊማህ ከመሆን አያግድሽምና በኢልም ትልቅ ደረጃ እንደርሳለሁ ብለሽ ለነፍስሽ ንገሪያት ሂማሽን በጣም ከፍ አድርጊ ለዚህም የሴት ምሁራኖች ታሪክ ማንበብ ይረዳሻል ።

አንጋፋው የአል-ሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር ተማሪ አል-ኢማም السخاوي ከ80 በላይ ሸይኻዎቹ ሴቶች ነበሩ بين فقهية ومسندة ታዉቂያለሽ ????

-ከአመት አመት አጫጭር ኪታቦች ብቻ አትቅሪ ይልቁን በቅደም ተከተል ከሙኽተር ኪታቦች አንስተሽ እስከ ሰፋፊ ኪታቦች መቅራት አለብሽ በዚህም ነዉ እዉቀትሽን የምታዳብሪዉ ብዙ እህቶችንም በፈትዋ ምታብቃቂዉ
ለምሳሌ ዘንድሮ ሰፊና እየቀራሽ ከሆነ የዛሬ 3 or 4 አመት ሚንሃጅ መጨረስ አለብሽ አቂዳም እንደዚሁ ፈትሁል መጂድ ምናምን ማጠናቀቅ አለብሽ ሌሎች ፈኖችም ላይ እንደዚሁ ።

በዚሁ አደራ ምልሽ ያለአቅምሽ ያለደረስሽበትን ፈን ወይም ኪታብ አትዳፈሪ فإنه من رام العلم جملة ذهب عنه جملة .

-ምንም ቢያነሳሱሽም በሱና ሰዎች መሀከል ባለ ልዩነት እራስሽ ቢዚ አታድርጊ ።

-ጎደኞችስ አንቺን የሚመስሉ ለቂርዓት ትኩረት የሚሰጡ እንጂ በተራ ወሬ ዉድ ጊዜያቸውን የሚያባክኑ አይሁኑ ።

بالله التوفيق

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

10 Nov, 16:32


⭕️ሐቢቢ‼️
:መልካም ነገር ማድረግ ቢያቅትህ እንኳ ክፉ ከመስራት ተቆጠብ።
:ሙስሊም ወንድምህን መጥቀም ባትችል እንኳ አትጉዳው።
:ወንድምህን ማስደሰት ባትችል እንኳን አታሳዝነው።
:የለመነህን መርዳት ባትችል አታሳጣው።
:ያገኘውን ባትጨምርለት አትቀንስበት።
:የተሳካለትን ባታግዘው እንኳ አትመቀኘው።
:ትልቅ ደረጃ ላይ የደረሰውን ለማክበር ባትታደል እንኳ አትናቀው።
;የበለጠህን ማድነቅ ባይሆንልህ እንኳ አትክሰሰው።
:የሰውን ስም ማጥፋት ፣ ማማትና መመቀኘት በራስ ላይ እዳ ማምጣት ነው።
:ባለዕዳ ከመሆን በዋናው መኖር ይሻላል።
:በዕዳ ከመታሰር ባዶ እጅ መሆን ይመረጣል

🔰 @Rihu_islamic_post
🔰 @Rihu_islamic_post
🔰 @Rihu_islamic_post

#SHARE_The_خير_

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

08 Nov, 16:56


🍂🍂...."ዙለይካ"


💫💫 ነብዩሏህ ዩሱፍን (አ.ሰ) ያፈቀረች ጊዜ እስር ቤት እያለ ሄዳ መጠየቅ ስለማትችል/ ስለተከለከለች ድምፁ በጣም ናፈቃት እና የእስር ቤቱን ገራፊ ጠርታ እንዲገርፈው አዘዘችው ሲገርፈው ድምፁን ለመስማት ገራፊውም ግራ ገባው በምን ሰበብ ይግረፈው

ሄዶ ለነብዩሏህ ዩሱፍ(አ.ሰ) አማከረው እና እንዲህ አለው እኔ መሬቱን ስመታ አንተ ትጮሃለህ አለው
በዚህ ተስማምተው መሬቱን ሲመታ ዩሱፍም ይጮሀል
ከዛን ወደ ዙለይካ ተመልሶ ሲመጣ

ዋሸኸኝ አለችው እሱም እንዴት አወቅሽ እመቤቴ አላት
እሷም አለች ዩሱፍን ብትመታው ኖሮ እኔንም ይሰማኝ ነበር /እኔን ያመኝ ነበር አለችው ::

አጂብ ልክ እንደ ዩሱፍ የአሏህን እውነተኛ ፍቅር በልቦናዎቻችን ላይ ያኑርልን.........አሚን🤲

🍃🍃 መልካም ለይል አህባቢ🍃🍃

@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

07 Nov, 09:16


-"الْبَاقِيَاتِ الصَّالِحَاتِ.🤎

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

05 Nov, 16:24


🔎~ፈገግታ #ከኡለሞች ጋር~😄
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
📌:ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባህ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ➘

▮"አንድም ሰው #ሸውዶኝ አያውቅም ከአንድ ወጣት #በስተቀር። የሆነ ጊዜ አንዲት ሴት ላገባ አሰብኩኝና ሳማክረው:▮

📍"አሚራችን ሆይ! እኔ #ባታገባት ይሻላል እላለሁ" አለኝ።
🔎"ለምን" ስለው

🔎"የሆነ ሰው #ሲስማት አይቻለሁ‼️" አለኝ።

📯ከዚያ እሱ እራሱ እንዳገባት ሰማሁና👇
"የሆነ ሰው ሲስማት አይቻለሁ አላልክም ነበር⁉️" ስለው

📭;"አዎ ልጅ እያለች አባቷ ሲስማት አይቻለሁ" አለኝ።
【አልቢዳያ ወንኒሀያህ: 8/53】
📕ትርጉም❳ኢብኑ ሙነወር

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

04 Nov, 22:22


የፈጅር ሶላት ለሚከብዳችሁ ሰዎች የሸይኽ ሷሊህ ኢብኑ ዑሰይሚንን ምክር አዳምጡ፡

1ኛ፡ በጊዜ መተኛት።

2ኛ፡ ስንተኛ ለፈጅር እነቃለሁ የሚል ትክክለኛ/ቁርጥ ያለ ኒያ መነየት/ማሰብ።

3ኛ፡ አላርም መሙላት፡ አላርሙ ሲጮህ አጠፋዋለሁ ብለን ከሰጋን አላርሙን ራቅ ያለ ቦታ ማስቀመጥ።

4ኛ፡ ሰዎች ፈጅር ላይ እንዲያስታውሱን፡ እንዲደውሉልን ማናገር።

አሏህ ሰምተው ከሚጠቀሙት ያድርገን 🤲
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

03 Nov, 18:44


=
ነገ ሰኞ ነው የቻልን እንፁም

ያልቻልን share እናድርግ ።

🌴አንድን ስራ ያመላከተ ሰው ከሰራውሰው እኩል አጅር ያገኛል ።

  📣ጆይን @muslimstudents1

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

03 Nov, 18:31


3:30 ይጀመራል

حديث أبي الدرداء في طلب العلم

ገባ ገባ በሉ

https://t.me/SUHHAilEdu?livestream

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

01 Nov, 08:30


🌷"►አጠር ያለች ግጥም ለውዷ እህቴ"🌷

ትሸፈነው እንጂ በመላ አካላቷ
ሒጃቧ ነውና የሴት ልጅ ውበቷ

ጀነት እንዲያስገባሽ ነውና ምኞቴ
የአላህን  ትዛዝ  ጠብቂው እህቴ"

ክብሯን እዲጠብቅ ዱሪዬ እንዳይደፍራት
"ባለጌና አጃቢ በሩቁ እንዲፈራት"

ስሟን እንዲጠብቅ ሰውም እንዲያከብራት
በውበት ላይ ውበት እንዲጨምርላት"

ለሴት ልጅ መሸፈን ይህን መረጠላት"
ለማስቸገር ሳይሆን መልካም አስቦላት
ውዱ ወንድሜ አቡ/ ኣኢሻ አወል
   ••       •⊰✿🌹✿⊱•      ••
📚 @Rihu_islamic_post
📚 @Rihu_islamic_post
📚 @Rihu_islamic_post

#SHARE

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

30 Oct, 17:37


💢~መከራና ችግር~💥
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
:አትፍራ ወዳጄ! ልብ በል ሐቢቢ‥. አላህ (ሱብሃነሁ) ከዋለልን ፀጋዎች አንፃር ስናይ የመከራ ዕድሜ ትንሽ ነው፡፡ እድሜ ልኩን በምድር ላይ ሲንከራተት ኖሮ የሞተ ሰው የለም፡፡ ዱኒያ አንድ ቀን ብታስለቅሰን አንድ ቀን ልትስቅልን ግድ ነው።

🔎:የሚገርመው ፍፁም ፍትሃዊ የሆነ ጌታችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) በሷ ላይ በሚያገኘን ትንሽም ሆነ ትልቅ ችግር ምንዳ ለገሰን፡፡ የመከራ
#ምንዳው #በጤናና #በድሎት ጊዜ ከሚያገኙት በላይ
ነው፡፡ ከሱ የሚገኘው ልምድም ከየትኛው የህይወት ትምህርት በላይ ነው፤ ጥቅሙም ከማንኛውም ሀብት የላቀ ነው~😌

🖍:አንድ ቀን የሆነ ሰው
#ኢማሙ_አሽሻፊዒን “ፈተና ከበዛበትና እርጋታ ከሞለበት ህይወት ለአንድ ሰው የትኛው ይሻለዋል?” በማለት ጠየቃቸው:: ኢማሙም እንዲህ በማለት መለሡ➘

▮ፈተና የበዛበት ህይወት ይሻለዋል: ምክንያቱም አላህ ነቢዩ ኑህን፣ ነቢዩ ኢብራሂምን፣ ነቢዩ ሙሣን፣ ነቢዩ ዒሣን እና ነቢያችን ሙሐመድን ﷺ ፈተናቸው። በመጨረሻም የተረጋጋ ህይወት ሠጣቸው▮
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 🍃
┊  ✿
📗               
╠═════ •『 ﷽ 』•   
┣━━━━━━╗ 🍀

┣𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥• @Rihu_islamic_post
╠═══════•❁❀❁•══════
#SHARE_The_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

30 Oct, 11:52


➪አግባ......
ዐብደሏህ ኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ
እንዲህ ይላል: -
🌹« ለመኖር አስር ቀናቶች ቢቀሩኝና ከአስር ቀናቱ እንዳለቁ እንደምሞት ባውቅ እናም (ሚስት) ለማግባት ጊዜ ባገኝ ፊትናን ፈርቼ አገባ ነበር ።»
[ሰዒድ ቢን መንሱር አስሱነን 493]
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

28 Oct, 13:58


:መንገድ የምታቋርጥ ጉንዳን አትርገጥ፣

:ጥሬ የምትለቅም ወፍ አታስደንግጥ፣

:ዉሃ የሚጠጣ ዉሻ አታባርር፣

:ርቦት የሚግጥ እንሠሣ አታስደንብር፣

:ተመቻችታ የተኛች ድመት አትቀስቅስ፣

:የሸረሪት መኖርያን አታፍርስ፡፡

➣ይላል #ኢስላም፡፡ ሱብሓነከ ረቢ!

🤔 እየኖርነው ነው ግን

╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

26 Oct, 16:12


ትዝታ. . .
:የድሮ ልብሶችህን፣ ማስታወሻዎችህን፣ ጓደኞችህን እና ሌሎችንም ነገሮች እንደ ዋዛ አትጣላቸው። ያደግክባቸው መንደሮችና ቤቶች አትርሳቸው። ዛሬ ላይ ሆነህ መለስ ብለህ የበፊቱን ህይወትህን ትቃኝበታለህ። አላህ(ሱብሃነሁ ወተዐላ) ከየት አንስቶ የት እንዳደረሰህ፣ ከምን አንስቶ ወዴት እንደወሰደህ ታስተነትንበታለህ። ተሻሽለህ ከሆነ ይበልጥ የአላህን ፀጋ ታመሰግንበታለህ። ቀንሰህ ከሆነ ደግሞ በአዲስ እልህ ትነሳሳለህ። የሰው ልጅ በየቀኑ አይታወቀውም እንጂ ለውጥ ላይ ነው። የድሮ ቅሪቶቻችን ምላስ ኖሯቸው መናገር ባይችሉም እንኳ ስለኛ ብዙ ይናገራሉ። ለኛም ብዙ ትምህርትን ይሰጣሉ። #ትዝታ ወደኋላ ተመልሰን የድሮ ማንነታችንን የምንቃኝበት ፓስፖርታችን ነው።
──────⊱◈◈◈⊰──────
📚 @Rihu_islamic_post
📚 @Rihu_islamic_post
📚 @Rihu_islamic_post

#SHARE_The_خير_

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

26 Oct, 09:34


ሶላት አሰጋገዳችን ያማረ ሊሆን የሚችለው አላህን ስንፈራ ነው! አላህን የሚፈራ ሰው ቤትም ውስጥ ይስገድ መስጅና አደባባይም ላይ ይስገድ ለብቻው ጨለማ ላይም ይስገድ ነብያችን ስገዱ ባሉት መልኩ ረጋ ብሎ ልቡን ሰብስቦ መስፈርቱን መሰረቱን አሟልቶ ይሰግዳል አላህን የማይፈራና ፈራቻው የሚጐለው ሰው ግን ቢሰግድም ላይ ላዩን ነው ነካ ነካ የሚያደርገው የሙናፊቅ ሶላት ነው የሚሰግደው ልክ ዶሮ እህል እንደሚያነሳው ሩኩንም ሱጁዱንም አጣድፎ የሚወጣው/የምትወጣው። በምንኛውም ሁኔታችን ላይ አላህን የፈራን እንሁን።

የሶላታችንን ነገር አደራ! የማንሰግድም እንስገድ የምንሰግድም ሩህ ያለው ሶላት እንስገድ። ስንሰግድ ለመላቀቅ ሳይሆን ከሶላቱ ጥቅም ለማግኘት ይሁን።


የሙሂ ማስታወሻዎች

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Oct, 16:23


🤲"አላህ ሆይ! ስጠን"🤲

💡#ደስታን፦ በየእለቱ ቀን በቀን፤ ከወንጀል ሀጢአት የሚያርቀን፤ በምድር ላይ በህይወት እስካለን።
💡#ጤናን፦ በጌታችን ኢባዳ እንድንበረታ፤ ለፆም ለፀሎቱ እንድንፍታታ።
💡#ሀብትን፦ የሰውን ልጅ ከማየት የምንብቃቃበት፤ ድሃ ችገረኛን የምናስታውስበት፤ ሀጅ ዚያራ የምንሄድበት።
💡#ጥንካሬን፦ በዱንያ ሙሲባዎች እንዳንፈታ፤ በሀዘን መከራ በበሽታ እንዳንረታ፤ በመሰናክሎች ከአላማችን እንዳንገታ።
💡#ቁርጠኝነትን፦ ዲናችንን የምንማርበት ፤ ያወቅነውን ላላወቁት የምናሳውቅበት፤ እራሳችንና ማህበረሰቡን የምንጠቀምበት።
💡#ልብን፦ ሀቅን በሀቅነቱ የምናውቅበት፤ መጥፎን መጥፎ መሆኑን ለይተን የምንሸሽበት፤ በጎ ነገርን የምንረዳበት፤ መልካም ነገርን ሁሉ የምናስብበት።
💡#ድፍረትን፦ ሀያሉን ጌታ አላህን የምንፈራበት፤ የምድር ላይ ሀላፊነታችንን የምንወጣበት፤ ኢስላምን ከጥቃት የምንከላከልበት።
💡#ወኔን፦ ከስንፍና አባዜ ለመውጣት፤ ለዚህች አለም የግምቷን ያህል ብቻ ዋጋ ለመስጠት።
🌷آمِينْ يَا رَبَّ الْعَالَمِين

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Oct, 13:19


:በተግባር ባትችል ሀሳብ በመስጠት፣ በሀሳብ ባትችል በልቦናህ ለሰው በመጨነቅ ለሰው ጠቃሚ ሁን። አላህ መልካምነትህን ሲያይ እጅ እግርህን ጠፍሮ ባርያው ያደርግሃል፤ በበጎ ሥራዎች  ላይ ያሠማራሃል። መልካምን ነገር ሁሉ ያገራልሃል።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗ᢀ @Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Oct, 12:52


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Oct, 11:58


እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ!
~
እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው። ለማን ነው ይህን ያደረግሽው? አላህ ምን ይለኛል ብለሽስ አስበሻል? ተይው አላህ ዘንድ ሰው ዘንድ ራሱ ያስንቅሻል። ከጌታሽ ተጣልተሽ፣ ሰዎች ዘንድ ትዝብት ላይ ወድቀሽ ምን ትርፍ ታገኛለሽ?

ለማንኛውም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" صِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا ؛ قَوْمٌ مَعَهُمْ سِيَاطٌ كَأَذْنَابِ الْبَقَرِ يَضْرِبُونَ بِهَا النَّاسَ، وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ، مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُءُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ، وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وَإِنَّ رِيحَهَا لَيُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ كَذَا وَكَذَا "
"ሁለት አይነት ሰዎች ከእሳት ጓዶች ውስጥ ናቸው። እኔ አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ።)
* እንደ ከብት ጅራት ያለ መግረፊያ ይዘው ሰዎችን በነሱ የሚደብድቡ ሰዎች እና
* ለብሰው የተራቆቱ፣ ለሌሎች ጥፋታቸውን የሚያስተምሩ፣ ከአላህ ትእዛዝ ያፈነገጡ፣ ፀጉሮቻቸው እንዳዘነበሉ የተከመሩ የግመል ሻኛዎች የሆኑ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነትን አይገቡም። ሽታዋንም አያገኙም። ሽታዋ ከብዙ ርቀት የሚገኝ ነው።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።

منقول

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

24 Oct, 08:25


የኢባዳ መስፈርቶች

☞ አንድ ሠው አንድ ኢባዳን ከመስራቱ በፊት ሶስቱ ነገሮችን ቀደም ብሎ ማስተካከል ይኖርበታል

① በአላህ ማመን

በአላህ ማመን ከ ኢማን መሰረቶች ሁሉ ወሳኙ የላቀ ደረጃ ያለውና የአእማዶች ዋና ምሰሶ ሲሆን የተቀሩት የኢማን መሰረቶች የእርሱ ቅርንጫፍና በርሱ ውስጥ ተካታቾች ናቸው፡፡ በአላህ ማመን አላህ በጌትነቱ ፣በአምላክነቱ ፣ በስሞቹና ባህሪያቱ ብቸኛ መሆኑን ማመን ሲሆን እነዚህ ሶስቱ በአላህ
ለማመን ዋና ዋና መሰረቶች ናቸው፡፡
እንዲያውም ከግድፈት የፀዳው የእስልምና ሃይማኖት “ተውሂድ ” የተሰኘበት ምክንያት አላህ በንግስናውና በጌትነቱ አጋር
የሌለው ፣ በአካሉ ፣በስሞቹና ባህሪያቱ አምሳያ የሌለውና እንዲሁም በአምልኮ ቢጤ የሌለው ብቸኛ መሆኑን በማመን
የተመሰረተ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ መሰረት የነብያትና የመልዕክተኞች ተውሂድ በሶስት
እንደሚፈልግ ግልፅ ይሆናል፡፡

አንደኛው ክፍል “ተውሂድ ሩቡብያ” ፡- አላህ የሁሉም ነገር ጌታ፣ ንጉስ፣ ፈጣሪና ሲሳይ ለጋሽ መሆኑን ፣ ህይወት ሰጭ ፣ ገዳይ ፣
ጠቃሚ፣ ጎጂ፣ በጭንቅ ጊዜ ሲጠራ አቤት ባይ ፣የነገሮች ሁሉ ገዥ ፣የመልካም ነገሮች ባለቤት ነገሮችን ሁሉ ወደርሱ መላሽና
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አጋር የሌለው መሆኑን ማመን ነው፡፡
ሁለተኛው ክፍል “ተውሂዱል ኡሉሂያ” ፡-ራስን ዝቅ ብሎበመተናነስ ፣ በመውደድ፣በመፍራት፣ በማጎንበስ፣በግንባር በመደፋት፣ በማረድ፣ስለትን በማቅረብና በሌሎችም የአምልኮ ዘርፎች አላህን ብቸኛ ማድረግና አጋር እንደሌለው ማመን ማለት ነው፡፡

ሶስተኛው ክፍል “ተወሂዱል አስማኢ ወሲፋት”፡- አላህን በቁርአኑና በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሀዲሶች እራሱን በሰየመባቸውና
በገለፀባቸው ስሞችና ባህሪያት እርሱን ብቸኛ በማድረግ ፣ከጉድለት ፣ ከነውርና የእ
የእርሱ መለያ የሆኑትን ባህሪዎች
ከፍጡራን ጋር ከማመሳሰል መጠንቀቅ ፡፡ እንዲሁም አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ፣ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ፣ህያው፣ ራሱን ቻቀይ፣
ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ የማይዘው፣ ተፈፃሚ የሆነ ፍላጎትና የላቀ ጥበብ ባለቤት፣ሰሚ፣ተመልካች፣አዛኝ እንደሆነ ፣ ከዐርሽ በላይ ስልጣኖችን ተቆጣጣሪ፣ ንጉስ፣ቅዱስ የሆነና ሌሎችም
እጅግ በጣም ያማሩ ስሞችና የላቁ ባህሪዎች ያሉት መሆኑን ማመን ማለት ነው

በአላህ ሳይታመን የሚሠራ ኢባዳ ፋይዳ አይኖረውም ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል "(ከሀዲያን) ከስራ ወደ ሚሠሩት ስራ አሰብን የተበተነ አብዋራም አደረግነው "

②(ኢኽላስ) ፍፁማዊነት ይህም ማለት የሚሠራውን ኢባዳ ፍፁም ለአላህ ብቻና ብቻ ማድረግ (ስራን ከእዩልኝ እናከይሰሙላ የፀዳ ማድረግ ማለት ነው)አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ "ለሡ ሀይማኖትን ጥርት አድርገው እንዲገዙት እንጂ አልታዘዙም "

☞ ይህ ጉዳይ በርካታዎቻችን የምንፈተንበት ከባድ በሽታ ነው ። ወደ አንድ ሠው ልብ ዘልቆ ሲገባ ፍፁም ረቂቅ በሆነ መንገድ መሆኑ ነገሩን ከባድ ያደርገዋል ።

☞ በዚህ በሽታ የተለከፈ ሠው የሚሠራው ስራ ፈፅሞ ተቀባይነት አይኖረውም አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ይህን አስመልክቶ በሀዲሰ አል ቁድስ እንዲህ ይላል ። "ከኔ ጋር አጋርቶ አንድን ስራ የሠራ ሠው ስራውንም ሰውዬውንም እተወዋለሁ "

☞ እስቲ እራሳችንን እንፈትሽበት ዘንዳ እነዚህን ጥያቄዎች እራሳችንን እንጠይቅ

1) ፌስቡክ ላይ ስንፅፍ ምን ፈልገን ነው፡፡ የ ላይክ ብዛት ለመቁጠር ከሆነ አላህ ይጠብቀን መክሰራችንን አውቀን ዛሬውኑ ስራችንን እናስተካክል፡፡

2) ዳዕዋ ስናደርግ፤ ‹‹ብቃት አለው›› መባል ፈልገን ነው ወይንስ የአላህን ፊት ፈልገንበት??? ኢኽላሳችን ችግር ካለው አሁንም ቢሆን ሳይረፍድ ዛሬውኑ፤ አሁኑኑ ለአንድ አላህ ብቻ
ስራችንን እናጥራ፡፡

3) ለቤተሰባችንም ይሁን ለሌሎች መልካም ስንውል ምን ፈልገንበት ነው???

☞ የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ኢባዳ ፋይዳ የለውም!!

③ ሙታበአ(ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምን መከተል) ፦ በአላህ ያመነ እንዲሁም ስራውንም አላህ ይመነዳኛል ሢል አስቦ ኢባዳ
የሚሠራ ሠው የሚሠራውን ኢባዳ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
ሠርተውታል አልሠሩትም ብሎ መፈተሽ ይኖርበታል አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ ""መልዕክተኛው ያመጣላችሁን ያዙት ፣ ከከለከላችሁም ተከልከሉ ""

⇑ ከእነዚህ (ከላይ ከተጠቀሡት ሦስት መስፈርቶች) አንዱን ያጎደለ ኢባዳው
ተቀባይነት አይኖረውም!!!
☞ ሙስሊም ያልሆነ ሠው የሠራው ስራ ዋጋ የለውም
☞ ኢቲባእ የሌለው ስራ ቢድአ ነው
☞ የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ስራ እዩልኝ እና ስሙልኝ ነው
(ትንሹ ሽርክ ነው)

@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

23 Oct, 16:20


ነገ ሐሙስ ነው እንፁመው

መፆም ካልቻልን፡ ፆመኛን በማስፈጠር የፆመኛን አጅር እናግኝ

ይህንንም ካልቻልን ሌሎች እንዲፆሙ እናስታውስ

መልካም ምሽት
@Rihu_islamic_post

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

23 Oct, 02:37


🔅~የአላህ ፍራቻ~⚠️
▱▰▱▰▱▰▱▰▱
:የዲን ምሰሶዎች ሦስት(3) ናቸው:: ይላሉ አንድ ዓሊም:: ◈እነርሱም▽
➥:አላህን መውደድ▯➀▯
➥:እሱን መፍራት▯➁▯
➥:በሱ ላይ ተስፋን ማሣደር▯➂▯

❇️:ውዴታን ከአእዋፍ አንፃር ስናየው እንደ ጭንቅላት ነው:: ፍራቻና በአላህ ላይ ተስፋን ማሣደር ደግሞ እንደ ሁለት ክንፎች::

➥:አንድ በራሪ ጭንቅላቱ ከሌለ በህይወት ይኖራል ተብሎ አይታሠብም:: ሁለት ክንፎቹን ያጣ እንደሆነ ደግሞ ሚዛኑን ያጣል። የአዳኞች ሁሉ መሽቀዳደሚያ እና የጉልበተኞች ሁሉ መረባረቢያ ይሆናል

❉ ╤╤╤╤ ✿ ╤╤╤╤ ❉
◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤◢◤
ᴄʜᴀɴɴᴇʟ• @Rihu_islamic_post
┗━━━━ • ✿ • ━━━━┛
#SHARE_The_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

22 Oct, 03:12


🚨 እንተዋወስ 🚨

«ምኞትሽን ያሳካልሽ»

➪ልታይ ልታይ በበዛበት የኢስላምን ስም እያጠፉ እርቃናቸውን የሚሄዱ ሴቶች በበዙበት አንቺ የፀሀዩን መክበድ ሳይበግርሽ በሙሉ ሂጃብ ♕︎ክብርሽና እምነትሽ ለጠበቅሽው እህቴ አላህ በዱንያም በአኼራ ያሰብሽውን ኸይር ያሳካልሽ


@Rihu_islamic_post❤️
@Rihu_islamic_post💛
@Rihu_islamic_post💝

#SHARE

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

21 Oct, 03:35


📝~ፈተና ወይንስ እርጋታ~💎
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰
➥:አንድ ቀን የሆነ ሰው ኢማሙ አሽሻፊዒን
"ፈተና ከበዛበትና እርጋታ ከሞላበት ህይወት ለአንድ ሰው የትኛው ይሻለዋል?”በማለት ጠየቃቸው::
➯ኢማሙም እንዲህ በማለት መለሡ፦
:ፈተና የበዛበት ህይወት ይሻለዋል። ምክኒያቱም አላህ ነቢዩ ኑህን፣ ነቢዩ ኢብራሂምን፣ ነቢዩ ሙሣን፣ ነቢዩ ዒሣን እና ነቢያችን ሙሐመድንﷺ ፈተናቸው:: በመጨረሻም የተረጋጋ ህይወትን ሠጣቸው::😌
:አንድ ሷሊህ ሰው 'በሰላት ውስጥ ቁኑት ከሚያስረዝመውና
ሱጁድ ከሚያስረዝመው የትኛዉ የተሻለ ነው?:: ተብሎ ተጠየቀ፡፡ እሱም፦
"ኢኽላስ ያደረገው/ስራውን ጥርት አድርጎ ለአላህ ብቻ የሰራው /" ሲል መለሰለት።
▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱
❉ ╤╤╤╤ ✿ ╤╤╤╤ ❉
ᴄʜᴀɴɴᴇʟ• @Rihu_islamic_post
┗━━━━ • ✿ • ━━━━┛
#SHARE_The_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

19 Oct, 16:47


🚸ሰውና ዘመኑ
🗣ዘመኑ ትላልቅና ያማሩ ህንፃዎች በብዛት የተገነቡበት ዘመን ነው።
👉ነገር ግን ቤተሰብ የፈራረሰና ፍቺ የበዛበት ዘመን።
🗣ዘመኑ ሀብትና ገንዘብ የተትረፈረፈበት ዘመን ነው።
👉🏼ነገር ግን ሀብታሞች ዘካን ማውጣት ትተው ድሆችም ከምንም ጊዜ በላዬ የተረሱበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ ጨርቃጨርቅ እና የተለያዩ አልባሳት በብዛት የተመረቱበትና ገበያ ላይ የዋሉበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን የሰው ልጅ ልብስ አስጠልቶት እርቃኑን አሳይቶ የሚሄድበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ ወፍራም እና ቦርጫም ሰዎች የሞሉበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን ውስጣቸው ከኢማን ባዶ የሆኑ ጉረኞች የሞሉበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ ሁሉም ሰው አውቋል ተምሯል የተባለበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን የሰው ልጅ ዛሬም ከእንስሳ ያልተለየበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ የሰው ልጅ መጥቆ ወደ ጠፈር ተጉዞ ጨረቃ ላይ ያረፈበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን እስካሁንም የሰው ልጅ ፈጣሪውን ያላገኘበትና ያላወቀበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ ስለ ሰላም የሚለፈለፍበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገረ ግን ጦርነትና ስደት የሰፈነበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ ሙስሊሞች ከመቸውም ጊዜ በላይ ቁጥራቸው የበዛበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገር ግን እስልምናቸው የስም ብቻ ሆኖ እነሱም የተዋረዱበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ ዑለማዎችና የህግ ሰዎች የበዙበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን ሀቅን የሚናገር በአላህ ቃልም የሚፈርድ የጠፋበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ አለማችን አንድ ለመሆን የተቃረበችበት /globalization/ ዘመን ነው።
👉🏻ነገር ግን የሰዎች የአመለካከት ልዩነት በእጅግ የተራራቀበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ በርግጥ ሴቶች የበዙበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን ለሚስትነት ብቁ የሆኑ ሷሊህ ሴቶች የጠፉበት ዘመን ነው።
🗣ዘመኑ በእርግጥ ወንዶች የበዙበት ዘመን ነው።
👉🏻ነገርግን ለባልነት የሚመረጡ መልካም ባሎች የጠፉበት ዘመን ነው።
──────⊱◈◈◈⊰──────
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post
@Rihu_islamic_post

#SHARE_THE_خير

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

19 Oct, 02:24


👉10 የልብ ህመሞች ✏️

1…… በአላህ (ሱብሀነ ወተአላ) እናምናለን እንላለን ነገር ግን ትዕዛዙን አንተገብርም።

2….. ረሱልን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንወዳሉን እንላለን ግን የሳቸውን ፈለገ ሱናቸውን በመተግበር አልተከተልንም ።

3….. ቁርዐን እንቀራለን ነገር ግን ወደተግባር አንለውጠውም።

4….. የአላህ (ሱወ) ፀጋ ሁሌ ይደርሰናል ነገር ግን አመስጋኝ አልሆንም።

5…. ሸይጧን ጥላታችን እንደሆነ እንናገራለን ግን ከእርሱ ተቃራኒ አልቆምንም።

6…. ጀነት መግባትን እንፈልጋለን ነገር ግን ለመግቢያ የሚያግዘን ስራ እየስራን አይደለም።

7…. ጀሀንብ መግባትን አንፈልግም ነገር ግን ከሱ ለመራቅ ምንም አይነት ሙከራ አላደረግንም።

8…. ሁሉም ህይወት ያለው ነገር እንደሚሞት እናውቃለን ነገር ግን ለሞት እየተዘጋጀን አይደለም።

9…. ሰዎችን እናማለን ስህተታቸውን ለማውጣት እንጥራለን ነገር ግን የራሳችንን ጥፋትና ወንጀል እረስተናል።

10…. ሙታንን እንቀብራለን ነገር ግን ከዚህ ተግባራችን ትምህርት አንወስድም

«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።

@Rihu_islamic_post

⬆️⬆️⬆️⬆️⤴️JOIN⤴️⬆️⬆️⬆️

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

18 Oct, 02:56


ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
➠➻➠➻➠➻➠➻➠➧
↩️‏ #سنن_يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد
      
الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ


🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

17 Oct, 17:02


━━━━━━✦✿✦━━━━━━
ነብዩ ﷺ በመሰደባቸው የተቆጣው ውሻ
━━━━━━✦✿✦━━━━━━

: ከሞጎላዊያን አንድ ባለስልጣን የክርስትናን ሃይማኖት ከተቀበለ ጥቂት ጊዜያት በኋላ ሀይማኖቱን መቀበሉን አስመልክቶ በተዘጋጀ ድግስ ከተወሰኑ ቄሳውስቶች ጋር ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። ከአቅራቢያቸው አንድ ለአደን የተዘጋጀ ውሻ ታስሯል።
: በወቅቱ ከነበሩ ቄሶች አንዱ ለዓለማት እዝነት የተላኩትን ታላቁን ነቢ ሙሀመድ ﷺ በመጥፎ ማንሳትና መተቸት ብሎም መሳደብ ጀምሯል። ታዲያ ይህንን ሲሰማና ሲታዘብ የነበረው ውሻ እጅግ ተቆጣ ፤ ወዲያውኑ በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸ ተሳዳቢውን ቄስ ዘሎ ነከሰውና አቆሰለው ፤ በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎችም ተረባርበው አዳኑት ። ሰዎቹም፦ "ውሻው የምትናገረው ነገር አልተስማማውምና ሰለ ሙሀመድ (ﷺ) መጥፎ ከመናገር ተቆጠብ" ይሉታል ፤ ሰውየው ግን ፦ "አይ ችግሩ ከምናገረው አይመስለኝም ባይሆን በምናገርበት ወቅት እጄን ስዘረጋና ሳንቀሳቅስ ስለነበር እሱ ላይ የጠቆምኩበት መስሎት ነው" በማለት ስድብና ትችቱን ቀጠለ። ውሻው ግን ከመጀመሪያው በከፋ መልኩ በከፍተኛ ቁጣና ንዴት ዘሎ ጉሮሮውን በመንከስ ሰውየውን ገደለው።

👉 ይህ ክስተት በጊዜው የነበሩ ሰዎችን በከፍተኛ መልኩ አስገርሞ ነበር ፤ በዚህም ውሻ ምክንያት በወቅቱ ወደ 40 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ።

👉 ክስተቱን ታላቁ አሊም ኢብኑ ሀጀር "አዱረሩል ካሚናህ" በተባለው መፅሃፋቸው አስፍረውታል።

የአላህን ሰራዊቶች እርሱ እንጂ ማንም አያውቃቸውም

━━━━━✦✿✦━━━━━
🦋 @Rihu_islamic_post
🦋 @Rihu_islamic_post
🦋 @Rihu_islamic_post

#SHARE

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

17 Oct, 08:57


የትዕግስት ደረጃ! አላህ በቁርዓኑ ደጋግሞ ያወሳው።

وَبَشِّرِ ٱلصَّٰبِرِينَ ﴿البقرة ١٥٥﴾


وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلصَّٰبِرِينَ ﴿آل عمران ١٤٦﴾


وَٱصۡبِرۡ وَمَا صَبۡرُكَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ ﴿النحل ١٢٧﴾


وَجَزَىٰهُم بِمَا صَبَرُواْ جَنَّةٗ وَحَرِيرٗا ﴿الإنسان ١٢﴾

إِنَّمَا يُوَفَّى ٱلصَّٰبِرُونَ أَجۡرَهُم بِغَيۡرِ حِسَابٖ ﴿الزمر١٠﴾

🌺https://t.me/Menehajselefiya
🌺https://t.me/Menehajselefiya

ŘïĤü🌺ÏSLÄMÏČ 🕋 PÖST🕌

17 Oct, 03:46


.


🌷تلاوة خاشعة


🌺 اللهم إجعل القرآن العظيم ربيع قلوبنا و نور صدورنا و جلاء همومنا و أحزاننا