የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

@voiceofworkers2013cetu


በኢሠማኮ የውጭና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በየሁለት ሳምንት የሚዘጋጅ የ‹‹ሠራተኛው ድምጽ›› ዲጂታል ቅጂ

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

04 Oct, 11:49


በተመሳሳይ በ24/01/2017 ዓ.ም. የፌዴሬሽኑ 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዶ የተለያዩ አጀንዳዎች ተነስተዋል፡፡የምክርቤቱና የጉባኤውን ውሎ የሥራ አስፈጻሚና የኦዲት ኮሚቴ ሪፖርትና አጠቃላይ ጉዳዮች ላይ የተደረገውን ውይይት፣ጥያቄና ምላሾች በቀጣይ ‹‹የሠራተኛው ድምጽ›› ጋዜጣችን በዝርዝር ይዘንላችሁ የምንመጣ ይሆናል፡፡
https://t.me/voiceofworkers2013cetu

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

04 Oct, 11:49


መ/ሠ/ማኅበሩን በተመለከተ በ49ኛው ምክር ቤት ስብሰባ ቀርቦ በተደረገ ውይይት እና ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በማኅበሩ አመራሮች ጋር ተደጋጋሚ ውይይት እንደተደረገ ገልጸዋል፡፡በዚህ ውይይት የውዝፍ መዋጮ አከፋፈል እና ማኅበሩ የኢሠማኮ ስፖርት ስለሚሳተፍበት ሁኔታ መነሳቱን አስረድተዋል፡፡ የቀድሞ አመራሮች ከንብረት ማስመለስ ጋር ተያይዞ በፍ/ቤት የተያዙ ጉዳዮችን እገዛ እንደሚፈልጉና ያለባቸውን ውዝፍ መዋጮ እንደሚፈልጉ በገለጹት መሠረትም ሙሉ በሙሉ መክፈላቸውን ገልጸዋል፡፡
የምክር ቤቱን ስብሰባ በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ)ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ኢሠማኮ ዋነኛ ዓላማው የሠራተኞች መብትና ጥቅም እንዲከበር ሠራተኞችን በማኅበር ማደራጀት የተደራጁትም አቅማቸው አንዲጠናከር ስልጠና መስጠት፣ ችግሮችም ሲፈጠሩ በውይይትና በድርድር እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጥረት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ከዚያ ባሻገር ግን ጠበቃ አቁሞ ማገዝ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትና በፌዴሬሽንም የህግ ባለሙያዎችን በመጠቀም ሠራተኛውን የማገዝ ሥራ እየሠራ ይገኛል ሰሉ ተናግረዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ሠራተኛና አሠሪን የሚመለከቱ ጉዳዮች በአማካሪ ቦርድ ላይ ተሳትፎ እንደሚያደርግና ሠራተኛውን የሚመለከቱ ህጎች ደንቦች ሲወጡ ተሳትፎ የማድረግ ሥራዎችን እንደሚሠራም ጭምር አብራርተዋል፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ አባላት ዳኞች የሚሆኑ ሰዎችን እንደሚያቀርብና በአህጉራዊውም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን ሠራተኞች ወክሎ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ ማድረግና ወቅታዊ የሠራተኞች ችግሮችን በመለየት ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የማቅረብ ሥራዎችን ይሠራል ብለዋል፡፡ ከዚህ በፊት አንኳር ችግሮች እንዲሆኑ የታመነባቸው ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ለመወሰን በየዓመቱ የኢኮኖሚውን ሁኔታ እያየ የደሞዝ ወለል የሚከልስ ሆኖ እንዲሠራ የደሞዝ ቦርድ እንዲቋቋምና ታቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ የደሞዝ ቦርድ እስካሁን አለመቋቋሙን የገለጹት አቶ ካሳሁን በዚህ ምክንያት በተደጋጋሚ ለመንግስት ጥያቄ ሲቀርብ መቆየቱን አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም ካለው የኑሮ ውድነት የተነሳ ከደሞዝ የሚቆረጠው ግብር እንዲቀነስም ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ይህ ጉዳይ በተደረገው ውይይት አቅጣጫ ተሰጥቶበት ነበር ግን ሊሰራበት አልቻለም፡፡ በዚህ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መምጣትና የገንዘብ የመግዛት አቅም ማውረድም ሌላው አስቸጋሪ ጉዳይ ምላሽ አልተገኘበትም፡፡ ይህንኑ ችግር ለኢሠማኮ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በዝርዝር ቀርቦ ምክር ቤቱ ከጥልቅ ውይይት በኋላ የመንግስት አካላትን ለማግኘት የሚደረገው ጥረት እንዲቀጥል፣ ጉዳዩን ለመገናኛ ብዙሃን በማቅረብ እንዲታወቅ ማድረግ ይህ ካልሆነ በሚመጣው የኢሠማኮ ጉባዔ ላይ አቅርቦ ጉባዔው የሚሰጠውን አቅጣጫ በመተግበር እንደሚቀጥል አስረድተዋል፡፡
ኢሠማኮ ይህን እየሠራ ያለው ባሉት አደረጃጀቶች በመጠቀም ነው፡፡ የሠራተኛ ማኅበር በባህርይው ብዛትንና ህብረትን የሚፈልግ ነው፡፡ ኃይል ሊሆነው የሚችለው ቁጥሩና ትብብሩ ነው፡፡ ተፅዕኖ ፈጣሪና ተደማጭ ለመሆን እንዲቻል መደራጀቱ ወሳኝ መሆኑን ያምናል ያሉት አቶ ካሳሁን ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ያልተደራጁ ሠራኞችን በማደራጀት ኃይልን በማጠንከርን ተደማጭነት ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡ ለዚህም ኮንፌዴሬሽ የመንግስት ሠራተኞችን ጭምር ለማደራጀት ጭምር ጉትጎታ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኑ ከኢሠማኮ ጋር በመሆን የሠራተኞችን መብት ለማስከበር እየሠራ ነውያሉት አቶ ካሳሁን የሠራተኛ መሪ ሲኮን ለዚሁ መሰጠት ያስፈልጋል ሲሉም አስረድተዋል፡፡ ራሰን ቤተሰብን መተው በሀቅ ለሠራተኛ መብት መከበር መቆም ቁርጠኛ መሆንን እንደሚጨምርም አብራርተዋል፡፡
በዚህ የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቱ የሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ላይ እንዳስቀመጡት መሠረታዊ ማኅበራትን በተመለከተ ከድርጅት አመራሮች ጋር ውይይት በማድረግ በማኅበራት ላይ የሚፈጠር ጫናና ውጥረት ለማርገብ የተደረገውን ጥረት ሲደረግ፣ በህብረት ድርድር ወቅት ስምምነት ላይ ያልተደረሱባቸውን ሀሳቦች በማስታረቅ ሰጥቶ በመቀበል መርህ ሠራተኛው ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ እንዲከተሉ አቅጣጫ መሰጠቱን አብራርተዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም የሠራተኛ ማኅበር ለማደራጀት አስቸጋሪ በሆኑ ተቋማት ማኔጅመንትና ለማነጋገር የተደረገውን ጥረት አንስተዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ የህብረት ስምነት የጊዜ ገደባቸው ላበቃ ማኅበራት ድርድር እንዲያደርጉ እንዲሁም አዲስ ለሚደራጁ ማኅበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ በመስጠት ረቂቅ እንዲያዘጋጁ በማድረግ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ፣ስምንት ያክል ማኅበራት ያጋጠሟቸውን ችግሮች በማኅበራዊ ምክክሮሽ መፍታቱንና የሕግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ማኅበራትም ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
በዚህ ሪፖርት ላይ በተቀመጠው መሠረት የሴት ሠራተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኑ ባከናወናቸው ተግባራት አማካኝነት 54 ሴቶችን ወደ አመራር የማምጣት ሥራ መሠራቱንናየነበሩት የሴቶች ኮሚቴዎች ቁጥር እንዲያድግ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኑ በትምህርትና ሰልጠና ረገድም ያከናወናቸውን ተግባራትና የሠለጠኑ የማኅበር አመራሮችን ብዛት በቁጥር አስደግፈው አቅርበዋል፡፡የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያካሂዳቸውን የሠራተኛው ቤተሰባዊ የስፖርት ውድድሮች ላይ የፌዴሬሽኑ ስር የሚገኙ አባል ማኅበራት በበጋ ወራት ውድድሩ ተሳታፊና የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ባለው የውጭ ግንኑነት ውጤታማ መሆኑንም በሪፖርቱ ላይ ተሰምቷል፡፡ በዚህ ሪፖርት የፌዴሬሽኑ የአስተዳደር ሥራዎች፣የፋይናስ እንቅስቃሴን፣ የማኅበራት መሪዎች የድጋፍ ፈንድና ሌሎች በሪፖርቱ የተካተቱ ነገሮች ለአባላቱ በፕሬዝዳንቱ አማካኝነት ቀርበዋል፡፡
የፌዴሬሽኑ የኦዲት ኮሚቴ በሰብሳቢው አቶ መሐመድ አወል አማካኝነት ባቀረበው ሪፖርት በኮሚቴው በትኩረት የታዩ ጉዳዮች ተዘርዝረዋል፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን የሥራ እንቅስቃሴ፣የፋይናንስ፣ ማኅበራትን ማደራጀት፣የማጠናከርና የግጭት አፈታትንና የመሳሰለውን የተመለከተ ግምገማውን አቅርቧል፡፡የኦዲት ኮሚቴው ሪፖርቱ የእቅድ ክንውን አፈጻጸምን በተመለከተ ከእቅዱ ጋር ሲነጻጸር 99.31 በመቶ መሆኑን አስቀምጠዋል፡፡
በዚህ የኦዲት ኮሚቴ ሪፖርት ፌዴሬሽኑ በርካታና ውስብስብ ችግሮችን ማሳለፉንና ካጋጠሙት መካከልም በጸጥታ ምክንያት አዳዲስ ማኅበራት ማደራጀት አለመቻሉ፣ የሥራ አስፈጻሚ አባል በመጓደሉ በሥራ ላይ ጫና መፈጠሩ፣ በአሠሪ ጫና ምክንያት ማኅበራት ለመደራጀት የተፈጠረባቸው ጫና ከተጠቀሱት መካከል ይገኙበታል፡፡
በዚህ የጠቅላይ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተጓደሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምትክ አመራሮችን እንዲመረጡ ተደርጓል፡፡ በዚሁ መሠረትም በተደረገ የስልጣን ድልድልና የሥራ ምደባ የፌዴሬሽኑ ማኅበራት ማደራጃና የማኅበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ብርጭቆ ተክኤ የፌዴሬሽኑ አስተዳደርና ፋይናንስ መምሪያ፣ አዲስ የተመረጡት አለማየሁ ገ/ወልድ ማኅበራት ማደራጃና ማኅበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ሆነዋል፡፡ አቶ ብርሃኑ ደበሌ ደግሞ ለኢንዱስትሪ ግንኙነት መምሪያ በተመላላሽነት እንዲሠሩ ተመርጠዋል፡፡

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

04 Oct, 11:48


የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር ወደ እናት ፌዴሬሽኑ ተመለሰ
ከተወሰኑ ዓመታት በፊት በመዋጮ ምክንያት ተለይቶ የነበረው የብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት መ/ሠ/ማ እናት ፌዴሬሽኑ ወደ ሆነው የንግድ ቴክኒክና ህትመት ኢንዱስትሪ ሠ/ማ/ፌዴሬሽን መመለሱ ተገለጸ፡፡ የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኑ በ23/01/2017 ዓ.ም. ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሪፖርት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ ደበሌ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት ማኅበሩን ለመመለስ ብርቱ ጥረት ተደርጓል፡፡

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

03 Oct, 13:47


የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ በፊርማው ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኮንፌዴሬሽኑ በሀገር ውስጥ በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞች መብቶች እንዲከበሩ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ በተጨማሪ በውጭ ሀገራት ተቀጥረው የሚሠሩ ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ እዲሠሩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠራ ጠቅሰው፣ ለዚህም ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት በርካታ ጥረት ሲደረግ የነበረ መሆኑን አንዱ ማሳያ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ ይህ የመግባቢያ ሰነድ ወደ ትግበራ ሲገባ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የሚሰማሩ ዜጎች ከምልመላ ጀምሮ እስከሚሄዱበት የመዳረሻ ሀገራት እና ቆይታቸው ላይ በጋራ በሚመሰረተው የቅጥር እና የምልመላ አማካሪ ኮሚቴ (Migrant Workers Recruitment Advisory Committee) አማካኝነት መረጃዎችን በመሰብሰብ እና ልውውጥ በማድረግ የዜጎችን መብት ለማስከበር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አክለው ገልፀዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ መሥራታቸው በርካታ ዜጎች ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲሰማሩ ከማገዝ በተጨማሪ ዜጎች ላይ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀምባቸው መረጃዎችን ለመለዋወጥ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ካሳሁን ፎሎ ሠራተኞችን በማኅበር የማደራጀት ሥራ የኢሠማኮ እንደመሆኑ በውጭ ሀገራት ያሉ ሠራተኞችም መደራጀት እንደሚያስፈልጋቸው፣ይህም ሠራተኞቹ የት እንዳሉ ለማወቅ ስለሚያስችል ጉዳት ሲደርስባቸው ክትትል በማድረግ የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣ አረጋግጠዋል፡፡
አሠማኮ በውጭ ሀገራት ተቀጥረው የሚሠሩ ዜጎች መብት እንዲከበር ዓለም አቀፍ ከሆኑ አቻ ማኅበራት ጋር ጭምር የሁለትዮሽ ስምምነት በመፈራረም በጋራ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ በሊባኖሰ ፊናሶል ከሚባል የሊባኖስ ሠራተኛ ማኅበር ጋር፣ እንዲሁም ከኩዌት የሠራተኛ ማኅበራት ፌዴሬሽን ጋር ተፈራርሞ አፈጻጸሙ በሂደት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ከሀገር ሲወጡ ቅርብ ያሉ ሀገራትን አቋርጠው ስለሚሄዱ በመተላለፊያ የሚገጥማቸውን ችግር ለመቀነስ ከተቻለም ለማስቀረት ከደቡብ ሱዳን እና ከሶማሊያ ሠራተኛ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት የተፈራረሙበትን አጋጣሚ አስታውሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ነቢል መሀመድ በበኩላቸው ፌዴሬሽኑ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በሥራ የሚሰማሩ ዜጎች መብት፣ ክብር እና ደህንነት እንዲጠበቅ ለኤጀንሲዎች ከመንግስትና ከአለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO) ጋር በመተባበር በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን ጠቅሰው በተለይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የስነ-ምግባር ደንብ አዘጋጅቶ እና አፀድቆ ኤጀንሲዎች ህግን፣ ዘርፉን በተመለከተ የወጣውን አዋጅ እና አለም አቀፍ መርሆዎችን በጠበቀ መልኩ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን አስገንዝበዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ አክለውም ፌዴሬሽኑ በዋናነት የአባላቶቹን መብት ከማስከበር ባሻገር የዜጎች መብት፣ ጥቅም እና ደህንነት እንዲከበር የሚሠራ መሆኑን ጠቅሰው ከኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በዛሬው ዕለት የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም የዜጎችን መብት በማስከበር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
https://t.me/voiceofworkers2013cetu

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

03 Oct, 13:47


የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
- የተፈረመው ሰነድ በውጭ ሀገራት
ተቀጥረው የሚሠሩ ሠራተኞችን መብት ለማስከበር ጠቀሜታው የጎላ ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገናኝ ኤጀንሲዎች አሠሪ ፌዴሬሽን በውጭ ሀገር በሥራ የሚሰማሩ ዜጎችን መብት እና ደህንነት ለማስጠበቅ በመርህ ደረጃ ከዚህ ቀደም በጋራ አብሮ ለመሥራት ንግግር ሲደረግበት የቆየውን በአጋርነት የመሥራት ሀሳብ በኢሠማኮ ትንሿ የመስብሰቢያ አዳራሽ ወደ ተግባር ሊያሸጋግራቸው የሚችለውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም. የኮንፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈጻሚዎችና የፌዴሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እንዲሁም የዓለም ሥራ ድርጅት ተወካይ፣እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራመ፡፡

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

03 Oct, 06:53


ለሥራ ኃላፊዎቹ የኢሠማኮን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎች መዋቅራዊ አሠራሩንና ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና ከኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኖች ጋር በመሆን እየሠራቸው ያለቸው ተግባራት ቀርበዋል፡፡ የሶሊዳሪቲ ሴንተር ከፍተኛ ዳሬክተር ሻዋና ባዴር ኮንፌዴሬሽኑ የሠራተኞች መብት በማስጠበቅ ረገድ እያካሄደ ያለው ዘርፈ ብዙ ሥራዎች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል፡፡ ሴቶችን ወደ ኃላፊነት ለማምጣት በሕገማኅበሩ ላይ ያደረገው ማሻሻያ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን መሆኑን ዳይሬክተሯተናግረዋል፡፡ እርሳቸው የሚያውቁትን የተለያዩ አገራት የሠራተኛ ማኅበራት ተሞክሮ በማንሳት ኢሠማኮም ከየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ባለመወገን የሠራተኛው ጥቅምና መብት በማስከበር ላይ ብቻ በማተኮር የሚሠራው ሥራ ለሥኬታማነቱ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል፡፡ በሶሊዳሪቲ ሴንተር የአፍሪካ ፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት ክሪስቶፈር ጆሀንሰን(ዶ/ር) ኢሠማኮ በክፍለ አህጉራዊ፣አህጉራዊና ዓለምአቀፍ የሠራተኞች እንቅስቃሴ ላይ ያለው እያከናወነ ያለው በርካታ ሥራዎች እንዳሉ ሆነው በአገር ውስጥም እንዲሁ የተሳካ ሥራ የሚያከናውንበትን ትጋት አድንቀዋል፡፡
አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት ለዚህ እንዳስቀመጡት በተለይ በክፍለ አህጉሩ ያለው የእርስ በርስ ግንኙነት አንዱ ከአንዱ ጋር ያለው መስተጋብራዊ ትስስር በአፍሪካ ቀንድ ጠንካራ የሆነ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን እንዲኖር ግድ እንዳስባለ አስቀምጠዋል፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በጎሳ፣በባሕል፣በቋንቋ እንዲሁም በኃይማኖት የሚያስተሳስራቸው ውል በሥራ ላይ የሚያጋጥማቸው ችግርም እንዲሁ የጋራ እንዲሆን እንዳስቻለ በማንሳት እነዚህን ችግሮች በጋራ ለመፍታት ኢሠማኮ በጥንካሬ እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን በኖር በቀጠናው ለተመሠረተው የአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽንም መነሻ ሊሆን እንደቻለ አብራርተዋል፡፡ፍልሰተኛ ሠራተኞችም ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሲሠሩ ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሠሩ ለማድረግ ይህ ክፍለ አህጉራዊ ተቋም ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለዚህ የክፍለ አህጉራዊ ግንኙነት የተመቸች በመሆኗ ኢሠማኮ ይህን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እየሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዚህ ውይይት ላይ የኢሠማኮ ሥራ አስፈጻሚ አካላት ኮንፌዴሬሽኑ ሠራተኞች መብታቸውና ጥቅማቸው ተጠብቆ እንዲሠሩና እንዲንቀሳቀሱ እያከናወነ ያለውን ተግባር ለሶሊዳሪቲ ሴንተር የሥራ ኃላፊዎች አብራርተዋል፡፡ ማኅበራዊ ጥበቃን ለማረጋገጥ በተለይ ለግል ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና መጠበቅ ኮንፌዴሬሽኑ ምን ያክል ርቀት ተጉዞ እንደሠራ ገልጸዋል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ በሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ ተገኝተው ከማኅበራትና ከሠራተኞች ጋር ውይይት ማድረጋቸው የበለጠ በኮፌዴሬሽኑ አየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማረዳት እንዳስቻላቸው ገልጸዋል፡፡ በዚህ የሥራ ጉብኝትና ውይይት ላይ የአፍሪካ ቀንድና የኢትዮጵያ ፐሮግራም ዳይሬክተር ሀናድ መሀመድ፣የዳይሬክተሯ ዋና አማካሪ ኪዳን ኪነይ እና የፕሮግራም ኦፊሰር ሳራ ዊንድ ተሳታፊ ነበሩ፡፡
https://t.me/voiceofworkers2013cetu

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

03 Oct, 06:53


የሶሊዳሪቲ ሴንተር የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢሠማኮ ያካሄደው የመዋቅር ለውጥና ማሻሻያን አደነቁ
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) በቅርቡ ያካሄደውንና ተግባራዊ በማድረግ እየሠራበት የሚገኘውን የመዋቅር ለውጥና ማሻሻያ የሚደነቅ መሆኑን የአሜሪካ ሶሊዳሪቲ ሴንተር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተናገሩ፡፡ የሥራ ኃላፊዎቼ በ22/01/2017 በኢሠማኮ ባካሄዱት የሥራ ጉብኝትና ከኮንፌዴሬሽኑ አስፈጻሚና የፌዴሬሽን አመራሮች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት በዚህ ለውጥ በሁሉም ዘንድ ለመቀበል አስቸጋሪ መሆኑንና ለረጀም ዓመታት ሲሠራበት የቆየውን መዋቅር በመቀየር የተሻለ አሠራር ለውጥ ለማምጣት ሲባል ይህን እርምጃ መውሰዱ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

የሠራተኛ ድምፅ Voice of Workers

01 Oct, 13:15


https://t.me/voiceofworkers2013cetu