Abrehot Library @aauethiopianuniversty Channel on Telegram

Abrehot Library

@aauethiopianuniversty


Abrehot Library is a public national library and the biggest library in Ethiopia also in East Africa.

Abrehot Library (English)

Welcome to Abrehot Library, the premier destination for knowledge and information in Ethiopia and East Africa. As the largest public national library in the region, Abrehot Library is dedicated to providing access to a wide range of resources for students, scholars, researchers, and the general public. Established with the mission of promoting literacy, education, and cultural exchange, Abrehot Library offers a vast collection of books, journals, periodicals, and other materials in various subjects and languages. From classics to contemporary works, from history to science, from fiction to non-fiction, there is something for everyone at Abrehot Library. Whether you are a student looking for resources for your research paper, a researcher seeking the latest information in your field, or simply a book lover in search of your next favorite read, Abrehot Library has you covered. Our knowledgeable staff is always ready to assist you in finding the information you need and navigating our extensive collection. In addition to our physical collection, Abrehot Library also provides access to digital resources, online databases, and e-books, making it easier for our patrons to access information anytime and anywhere. With our state-of-the-art facilities and user-friendly services, Abrehot Library is committed to ensuring that everyone has the opportunity to expand their knowledge and engage in lifelong learning. Join us at Abrehot Library and embark on a journey of discovery, enlightenment, and inspiration. Visit us today and experience the magic of books, the thrill of learning, and the joy of exploration. Abrehot Library - where knowledge knows no bounds.

Abrehot Library

08 Dec, 12:18


የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ ዛሬ ቀን 29/03/2017 ዓም በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት መዓከል ጉብኝት አድርገዋል።
**************

የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬስካ እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ምንስትር ዲኤታ ክብርት አንባሳደር ብርቱካን በአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት መአከል ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝታቸውም ወቅት በተቋሙ ዳይሬክተር ኢንጅነር ውብአየሁ ማሞ ስለ ቤተ መጽሃፍቱ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

በተጨማሪም በተቋሙ ስር ያሉ እንደ ሮቦቲክስ የመሳሰሉ ስልጠናዎች የሚሰጡባቸውን ስፍራዎች ተመልክተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩም በጉብኝታቸው ማጠቃለያ ባዩት ነገር እና በተደረገላቸው ገለጻ መደነቃቸውን ገልጸው ለተቋሙ ይዘው የመጧችውን መጽሐፍቶች በማስረከብ ከተቋሙ ጋር ቀጣይነት ያላቸውን ስራዎች ለመስራት ቃል ገብተዋል።

Abrehot Library

01 Nov, 14:49


ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከ2 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አበርክተዋል፡፡
****
አዲስ አበባ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በዛሬው እለት ቁጥራቸው ከ2 ሺህ በላይ የሆኑ መጻሕፍትን እና 25 “ኦርካም ማይ አይ” የተባለ ዐይነ ስውራን አንባቢያንን የሚያግዝ መሳሪያ ለአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት በስጦታ አበርክተዋል፡፡

ለቤተ መጻሕፍቱ የተበረከቱት መጻሕፍት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለአንባቢያን በተለይም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጠቅላላ እውቀትን የሚሰጡ የመጻሕፍት ስብስብ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

OrCam MyEye (“ኦርካም ማይ አይ”) የተሰኙት የስማርት ማጉያ መነፅሮች አይነ ስውራን ማንበብ እና ቅርፆችን ለመለየት የሚያስችላቸው ሲሆን ይህም በጥቂት ሀገራት ብቻ በስራ ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍትን አለም አቀፍ እንዲሆኑ ካስቻሉ ምክንያቶች ውስጥ ዋነኛው መሆኑ ተነግሯል፡፡

መጻሕፍቱ “Book for Africa” ከተባለ ድርጅት በድጋፍ የተገኙ መሆናቸው መገለፁን ከቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

“Book for Africa” ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ብቻ ከ1.6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ መጻሕፍት ለ31 የአፍሪካ ሀገራት ማበርከቱንም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ቀዳማዊት እመቤት ክብርት ዝናሽ ታያቸው ለትውልድ ግንባታ እና ለእውቀት ብርሃን ላበረከቱት ድጋፍ የአብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የላቀ ምስጋናን ያቀርባል፡፡

Abrehot Library

19 Oct, 14:21


ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ታዳጊዎች የተሳተፉበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ማጠቃለያ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂድዋል።

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2017

የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድሩ በአብርሖት ቤተ-መጽሀፍት እና የአፍሪካ ሲልከን ቫሊ ትብብር "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለበጎ ተጽዕኖ" በሚል መሪ ሃሳብ ሲያካሄድ ቆይቷል።

በዛሬው እለት ደግሞ የማጠቃለያ ስነ ስርአቱ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄድዋል።

ከግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው ግዙፍ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ውድድር ከ48 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 4 ሺህ 928 ታዳጊ ወጣቶች ተወዳድረውበታል።

በትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና እና በመሳሰሉት ወሳኝ የፈጠራ ስራዎች ለችግሮች መፍትሄ የሚሆኑና ቀልጣፋ አሰራር የሚፈጥሩ ፈጠራዎቻቸውም ለውድድር ቀርበዋል።

በዚህም አገራቸውን በመወከል ምርጥ ሰባት ውስጥ የገቡ የኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ፣ ታንዛኒያ፣ አልጀሪያ እና ቱኒዚያ ታዳጊዎች ለመጨረሻው ውድድር ቀርበዋል።

በማጠቃለያ መርሃግብሩ የአብርሖት ቤተ-መጽሐፍት እና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ስራ አስኪያጅ ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፣ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ፣ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Abrehot Library

18 Oct, 17:46


እኛ የተጠራንበትን ድህነት በልጆቻችን ልንበቀለው ይገባል:-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም

የአብርሆት ቤተ-መፃህፍት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአብርሆት ቤተ-መፃህፍት በተካሄደው የሮቦት ኪትስ የሽልማት መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ታዳጊ ህፃናቱ የሰሯቸውን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተግባራት ኤግዚብሽን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በእለቱም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ጠ/ሚነንስትሩ አብርሆት የትውልዶችን ልቦና በእውቀት ለማብራት የተቋቋመ መሆኑን ገልፀው ትውልዱን በሳይንስ እና ቴክኖለጂ እውቀት በማበልፀግ እኛ የተጠራንበትን ድህነት በልጆቻችን ልንበቀለው ይገባል የሚል መልእክት አስተተላልፈዋል፡፡

መጪው ትውልድ ከኢትዮጰያ የልማት ግቦች ጋር በተናበበ ሁኔታ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በኮዲንግ፣ በሳይበር ሴኩሪቲ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ክህሎታቸውን ማጠናከር መቀጠል ይኖርባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።

የአብርሆት ቤተ-መፃህፍት እና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር አንጂነር ውባየሁ ማሞ በበኩላቸው በዛሬው እለት ሽልማት የተበረከተላቸው ታዳጊ ህፃናት እና ወጣቶች ያበረከቷቸውን የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ወደ ኢንዱስትሪው በማውረድ በማህበረሰብ ኑሮ ላይ ችግር ፈቺ አገልግሎቶች እንዲሆኑ ለማስቻል የቴክኖሎጂ ውድድሮች ወሳኝ አማራጭ መሆናቸውን ተናግረዋለ፡፡

በእለቱም በተካሄደው ውድድር ከ 1-3 ለወጡ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ተበርክቷል፡፡
////////////
"We must overcome the poverty for the sake of our children." - Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.)

Addis Ababa, October 18, 2024

Abrehot library

Prime Minister Abiy Ahmed (Dr.) stated, "We must overcome the poverty we inherited for the sake of our children", during his speech at the Adwa Victory Memorial.

Dr. Abiy Ahmed, the Prime Minister of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, attended the awards ceremony for robotics kits held at the Abrehot Library. He toured an exhibition showcasing the technological innovations created by young students.

In his opening speech , the Prime Minister emphasized that Abrehot Library was established to enlighten future generations. He conveyed the message that the upcoming generation must overcome the poverty we inherited by fostering knowledge in science and technology.

He also highlighted that future generations need to advance their skills in artificial intelligence, coding, cybersecurity, and other related fields to meet Ethiopia's development goals.

Engineer Wubayehu Mamo, the Director of the Abrehot Library and Adwa Victory Memorial, in his remarks today, highlighted the importance of the technological innovations created by the young children and youth who were awarded. He emphasized that transferring these innovations to the industry and creating problem-solving services for society is crucial. He also noted that technology competitions play a key role in achieving this.

Awards were presented to the top contestants of the competition.