የነብዩ ☪ሠ,ዐ,ወ☪ ሀዲሶች @adnan567mh Channel on Telegram

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

@adnan567mh


☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች (Amharic)

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች ለአሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም እና ሌሎች አይደለሁም። በርካታ ገና የባህር ዳር የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች በትክክለኛ መረጃ በየውላት Telegram መረጃ ይጠቀሙት። ይህ ገና ገጽ መተየቢያ የሆነውን ነብያዊ ትዕዛዝ ለጠበሶዎች ብትሆን ከኔ አድርሱ ይላል። እርስዎ ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot አለን፣ እናመለስሁ። አንዲት መልዕክት ለመሆን እባኮት ይህን ገጽ ተጨምሯ። ከእርስዎ እንዲሁም ሌሎች ገጽዎችን ይምረጡ፣ ይሽዋል።

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

06 Nov, 18:35


ትልቁ ስጦታ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

“አላህ ገንዘብን ለሚወደውም ለሚጠላውም ይሰጣል። ኢማንን ግን ለሚወደው እንጂ ለሌላ አይሰጥም። አላህ ባሪያውን በወደደው ግዜ ኢማንን ይለግሰዋል።”
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

03 Nov, 16:01


የመካ እና የመዲና ሱራዎች
ጥቂት ስለ ቁርኣን (ክፍል - 1)
~
ቁርኣን ነብያችን ﷺ መካ እያሉ በሚወርድ ጊዜ የሙስሊሞች ቁጥር አናሳ ነበር። አጋሪዎች ብዙሃን ነበሩ። መዲና ውስጥ በነበሩ ጊዜ ደግሞ የሙስሊሙ ኃይል ተጠናክሯል። መካና መዲና የነበሩት ተቃራኒ ኃይሎች በብዛት ከእምነትም፣ ከንቃተ ህሊናም አንፃር ልዩነት አላቸው። በነዚህና መሰል ልዩነቶች የተነሳ በሁለቱ ዘመኖች የወረዱ ሱራዎች ትኩረትና ይዘት ልዩነት ይታይበታል። ይሄ የተወሰነ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይፈልጋል።
ከወረዱበት ዘመን አንፃር ሲታይ ከ114 የቁርኣን ምእራፎች ውስጥ 20ዎቹ መደኒያ ናቸው፣ በዘመነ መዲና የወረዱ። 12ቱ ኺላፍ አለባቸው። ቀሪዎቹ መኪያ ናቸው። ስለዚህ ከቁጥር አንፃር አብዛኞቹ የቁርኣን ምእራፎች መካ የወረዱ ናቸው ማለት ነው።

በነገራችን ላይ የመካ እና የመዲና ሱራዎች የሚታወቁባቸው መለያዎች አሉ።

1 - የመካ ሱራዎች፦

ሀ - "ከልላ" (كلا) የሚለው ቃል ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው።
ለ - ሰጅደተ ቲላዋ ያለባቸው ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
ሐ - በመሀላ የሚጀምሩ ሱራዎች ሁሉ መኪያ ናቸው። እነዚህም 14 ሱራዎች ናቸው።
መ - በሑሩፉ ተሀጂ (ሑሩፉል ሙቀጠዐ) የሚጀምሩ ሱራዎችም ከበቀረህ እና ኣሊ ዒምራን ውጭ መኪያ ናቸው። በቀረህ እና ኣሊ ዒምራን መደኒያህ ናቸው። ሱረቱ ረዕድ ኺላፍ አለባት።
ሠ - በውስጣቸው "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መኪያ ናቸው።
ረ - በ "አልሐምዱ" የሚጀምሩ ሱራዎች መኪያ ናቸው። እነሱም አምስት ሱራዎች ናቸው።
ሰ - ከሱረቱል በቀረህ ውጭ "ቀሶሱል አንቢያእ" የያዙ ሱራዎች መኪያ ናቸው።

2 - የመዲና ሱራዎች፦

ሀ - በውስጣቸው "ያ አዩሀለዚነ ኣመኑ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟) የሚል ያለባቸው እና "ያ አዩሀ ናሱ" (یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ) የሚል የሌለባቸው ሱራዎች መደኒያ ናቸው።
ለ - ስለ ሙናፊቆች የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው። አልዐንከቡት ስትቀር። እሷ ግን መኪያ ነች። ይሁን እንጂ በውስጧ ስለ ሙናፊቆች የሚያወሳው ክፍል መደኒይ ነው።
ሐ - ሑዱድ እር ፈራኢድ የተወሳባቸው ሱራዎች ሁሉ መደኒያ ናቸው።

ምንጭ፦ ዲራሰህ ፊ ዑሉሚል ቁርኣኒል ከሪም፣ ፈህድ አሩሚይ
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

05 Oct, 15:20


በጣም ትልቅ ፀጋ ዉስጥ ነን!
"""""""""""""""""""""""""""

ታዋቂው ዳዒ ዐምር ኻሊድ እንዲህ ይላል - በአንድ ወቅት ከሆኑ ወጣቶች ጋር ተቀማምጠን ሳለን እንደዋዛ የአላህን (ሱ.ወ.) ፀጋዎች መቁጠር ጀመርን፡፡ የትኛው ፀጋ እንደሚበልጥም አወጋን፡፡

~ ከኛ መካከል አንዱ ‹ጤና ነው› ሲል
ተናገረ፡፡

~ ሌላኛው ‹ልጆች ናቸው› አለ፡፡ ሌላው ‹ማየትና መስማት መቻል ነው› አለ፡፡

~ ‹ትልቁ ፀጋ እናቴ ናት› ያለም አለ፡፡

~ እንዲሁ ‹ሀብት የሠጠኝ ጌታ በርግጥም ትልቁን ፀጋ ሠጠኝ› ያለም ነበር፡፡

~ ‹እስልምና ነው› ያለም አለ፡፡

~ ከመካከላችን አንድ የአሥራ ስምንት ዓመት ወጣት ግን አላህ (ሱ.ወ.) ከሠጠን ፀጋዎች ሁሉ ትልቁ ፀጋ ‹ጌታችን ጌታችን መሆኑ ነው፡፡› አለ፡፡ ትርጉሙ ምን ማለት ይሆን? ይህ ታዳጊ ወጣት በዚህች ዓለም ላይ ትልቁ ፀጋ ጉዳያችን ይዞ ያለው አላህ (ሱ.ወ.) መሆኑ ነው ማለቱ ነው፡፡ እሱ ነው ዋስትናችን፡፡ ልባችንን፣ እጃችንን፣
ግንባራችንን… ሁሉ ነገራችን ይዞ ወደ መልካም ነገርና ወደ ስኬት የሚመራን አላህ ነው፡፡ ትልቁ የአላህ ፀጋ አላህ አላህ መሆኑ፣ አላህም ጌታችን መሆኑ ነው፡፡ ጥራትና ልዕልና የተገባው ይሁን፡፡ በአላህ ጌትነት ወደድን፣ መልዕክተኛው ነቢያችን መሆናቸውን ወደድን፣ እስልምናን በሃይማኖት በኩል ወደድን፡፡


አላህ (ሱ.ወ.) ለሚወደውም ለማይወደውም ሀብት ይሠጣል፡፡ አላህ ላመነበትም ለካደዉም ገንዘብ ይሠጣል፡፡ ጤና፣ ቤትና ንብረት ይሠጣል፡፡ እስልምናን ግን የሚሠጠው እርሱ ለወደደው ሰው ብቻ ነው፡፡ ወደ መንገዱ የሚመራው ራሱ የመረጠውን ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሙስሊም መሆን መመረጥ ነው፡፡ ሙስሊም
መሆን መብለጥ ነው፡፡ ሙስሊም መሆን መወደድ ነው፡፡ ባይወደን ኖሮ መቼ ይሠጠን ነበር፡፡ አላህ ወዶን እስልምናን
ሠጠቶናልና ክብር ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ይሁን፡፡ አላህ እኔ፣ አንተና አንቺ ግን ሳንለምነው፣ ሳንማፀነው ፣ ሳንወተውተው ሙስሊም አደረገን። ለኢብራሂም (ዐ.ሰ.) አባት ፣ ለኑሕ (ዐ.ሰ.) ልጅ፣ ለሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) አጎት ያልሰጠውን ፀጋ ሠጠን፡፡ አላህ እስልምናን ሠጠን፡፡ አምላካችን ንፁህ የተፈጥሮ ሃይማኖትን ለገሰን፡፡ እንደ እስልምና ምን ገር የሆነ ሃይማኖት አለ፡፡ ለመረዳትም ሆነ ለትግበራ አይከብድም፡፡ ይህ በርግጥም ትልቅ ችሮታ ነው። አላህ የትላልቅ ችሮታዎች ባለቤት ነው። እርሱ ችሮታውን
ለሚሻው ሰው ብቻ ይሠጣል። ነገርግን ብዙዎች አላህ የሠጣቸውን ፀጋ አያስተውሉም ፤ አያስተነትኑም ፤ አስተንትነውም
አያመሰግኑምም፡፡ የእስልምና ፀጋ ከየትኛውም ፀጋ ሁሉ የላቀ ነው፡፡ ቢመዘን ቢለካ የትኛውም ፀጋ አይደርስበትም። ምስጋና ወደቀናው መንገድ ለመራን ጌታ ይሁን። እሱ ባይመራን ኖሮ  ባልተመራን ነበር።

"እስልምናን ለሰጠን አላህ ምስጋና ይገባው" በሉ።
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

15 Sep, 18:19


🍂

⇛ የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል…

~ ከመካከላችሁ አፀያፊ ተግባር ሲተገበር ያስተዋለ ሰው በእጁ ያስወግደው። ካልቻለ በምላሳ። ካልቻለ በቀልቡ ይጥላ።
[ሙስሊም]
@Adnan567mh

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

26 Aug, 19:42


🔶"ዱዓዕ ሁሉም ነገር ያስተካክላል  አንተ ብቻ ዱዓ ስታደርግ የቂን ይኑርህ በቅርቡ የዱዓህን ፍሬ ታያለህ ኢንሻአላህ ☝️....!!
ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው ከጭንቀትም አዳነው....!🥰☝️♥️
🔶"ماذا قال يونس عليه السلام في بطن الحوت...؟!! 💙💙

🔶"وَذَا النُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَاضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِي الظُّلُمَاتِ أَن لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ

የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡

🔶"فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْغَمِّ ۚ وَكَذَٰلِكَ نُنجِي الْمُؤْمِنِينَ

🔶"ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡

🔶"وَزَكَرِيَّا إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ رَبِّ لَا تَذَرْنِي فَرْدًا وَأَنتَ خَيْرُ الْوَارِثِينَ

🔶"ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል» ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡

🔶"فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَوَهَبْنَا لَهُ يَحْيَىٰ وَأَصْلَحْنَا لَهُ زَوْجَهُ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا يُسَارِعُونَ فِي الْخَيْرَاتِ وَيَدْعُونَنَا رَغَبًا وَرَهَبًا ۖ وَكَانُوا لَنَا خَاشِعِينَ

🔶"ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ለእርሱም የሕያን ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ኾነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡
         {አል-ዓንብያዕ 87-90 }🤲
     ለኛም  ጥሪያችንን ተቀበን ያረብ...!🤲
@Adnan567mh

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

22 Mar, 06:27


ራሴን ታዘብኩት

ከሁለት ቀን በፊት የረመዷን የመጀመሪያውን ጁሙዐ ለመታደም ወደመስጂድ አቀናው። ያው ረመዷንም ስለሆነ ሰው ይበዛልና መስጂድ ውስጥ ቦታ ማግኘት ማይታሰብ ስለሆነ ብዙ ሰው ውጪ እያነጠፈ ይቀመጣል። እኔን ጨምሮ ግን ሁላችንም ጥላ ቦታ ፍለጋ አይናችንን ብናማትርም ስለሌለ ፀሀይ ላይ ተቀመጥን። የተወሰነ ሰው ደሞ ሰላቱ እስኪጀመር ወደጥግ ሄዶ ከፀሀይ ተጠለለ። ይሄኔ ነው የቂያማ እለቷ ፀሀይ ትዝ ያለችኝ። ዘንግቻት ነበር እንዳሁኑ ብዙ ሺ ኪሎ ሜትር ርቃን ሳይሆን አንድ ስንዝር ያህል ቀርባን የምታቃጥለን ግዜ መኖሩን መዘንጋቴ አስገረመኝ። ብዙ ሰውም ይህን የዘነጋ ይመስለኛል። በዚያ ቀን በነጯ ምድር ላይ የሰው ዘር በሙሉ እንዲቆም ሆኖ በፀሀይ ቃጠሎ ሲነድ ሰባት ሰዎች ግን ከአላህ አርሽ ስር እንደሚጠለሉ ተነግሯል። የዱንያ ፀሀይ እንዲ ያማረረን እኛ በአርሽ ጥላ ስር ከሚጠለሉት ለመሆን መጣር ታድያ የኛ ፋንታ ነው።

እስኪ ለማስታወስ ያህል እነዚህ 7 አይነት ሰዎች እነማን እንደሆኑ እንመልከት👇

🔹አቡ ሁረይራ(ረ.ዐ)እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ)እንዲህ ብለዋል። ሰባት ሰዎች አላህ ከርሱ ውጪ ሌላ ጥላ በማይኖርበት ቀን ከአርሽ ጥላ ስር ያስጠልላቸዋል።እነርሱም:
1 ፍትሀዊ መሪ፣
2 በጌታው አምልኮ ተኮትኩቶ ያደገ እና በዚያ መንገድ ወጣትነቱን ያሳለፈ
3 አላህን እያመለከ ያደረ(አላህን ብቻውን ሆኖ ያወሳ)፣
4 ልቦናው መስጂድ ላይ የተንጠለጠለ(ከመስጂድ ጋር የተሳሰረ)፣
5 ለአላህ ሲሉ የተዋደዱ በርሱ የተገናኙና በርሱም የተለያዩ ሁለት ሰዎች፣
6 ክብርና ውበት ያላት እንስት(ለወሲብ)ጋብዛው አላህን እፈራለሁ ያላት(ግለሰብ)፣
7 የቀኝ እጁ ምትመፀውተው የግራ እጁ የማታይ ያክል ምፅዋትን የደበቀ (ግለሰብ)ናቸው።

(ቡኻሪና ሙስሊም)
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

14 Mar, 19:42


ረመዷን - 4
***
ረመዷን ቀላል ወር አይደለም ። ዱዓ የሚሰማበት፣ ተውባ ተቀባይነት የሚያገኝበት፣ መልካም ሥራ የሚወደድበት ወር ነው። ደጋጎች ይህን ወር እንደ ትልቅ አጋጣሚ ይጠብቁታል። ወሩ የዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ነዉና ለረመዷን ብቻ የሚያስቀምጡት ዱዓ አላቸው። በመንፈስ ተዘጋጅተው፤ ዉስጥ ዉጪያቸዉን አጽድተው ይጠባበቁታል። ከወሣኝ ዱዓኦች መካከል የረመዷን ዉስጥ ዱዓ አንዱ ነው።

ሱሑር ላይ ፆም ስትይዙ፣  ማታ ስታፈጥሩ፣ በአዛንና ኢቃማ መካከል፣ ሱብሒ ከመድረሱ በፊት ያለዉን ጊዜ፣ በሱጁድ ዉስጥ፣ ከያንዳንዱ የግዴታ ሶላት በኋላ ዱዓ በማብዛት ተጠቀሙበት። ማን ያውቃል የልባችሁ መሻት ምላሽ የሚያገኘው በዚህ ወር ዉስጥ ሊሆን ይችላል ።
@Adnan567mh

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

14 Mar, 19:35


🍂🍁🍂የረመዷን ሌቦች🍁🍂🍁


👉 ክፍል አንድ


ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን ወሰላቱ ወሰላም ወአላ አሽረፊል አምቢያኢ ወል ሙርሰሊን ነብይና ሙሃመዲን ወአላ አሊሂ ወሰህቢሂ አጅመኢን

አማ በዕድ አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
የተከበራችሁ ውድ እህት ወንድሞች የአላህ ራህመት ሆኖ ይህ የተከበረው ረመዷን ወር ላይ አላህ አድርሶናል ከሚፆሙትም አድርጎናል ይህ ማለት በጣም ትልቅ ኒዕማ ነው አላህን(ሱብሃነ ወተዓላ)ልናመሰግነው ይገባል። እናም ይሄንን ትልቅ እድል ልንጠቀምበትና በአግባቡ በመጠቀም ለኼራችን ስንቅ ልንይዝበት ይገባናል።
አላህ ያላቀው የሆነ ትልቅ ወር ነው አላህ ያላቀውን ይህን ወር ደግሞ እኛም በተግባር መልካም ስራ በመስራት ልናከብረው ይገባል።
እንጂ መጥፎ ስራ በመስራት አላህን ከማመፅ ልንቆጠብ ይገባል። ሃቂቃ ይህ ወር ለአማኝ ባሮቹ ብዙ የጀነት ሰበቦች የደገሰበት የሆነ ትልቅ ወር ነው። ስለዚህ አንድ ሙስሊም የሆነ አካል አኼራ የሚያሳስበው ነገ ጀነትን የሚናፍቅ የሆነ ሰው የሄንን ትልቅ አድል ሊጠቀመው ይገባል።
  አላህ (ሱብሃነ ወተዓነላ) በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል "አያመን መእዱዳት" በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች ናቸው አለ።

"በናንተም ላይ ፆም ተደነገገ ከናንተ በስተፊት በነበሩት ሰዎች ላይ እንደተደነገገው" ዋናው የተደነገገበትም ምክንየት ተቅዋና ታገኙና "አላህን ልትፈሩ ዘንድ ነው" አለን
ይህ የተከበረው ወር ደግሞ ቀናቶቹ በጣት የሚቆጠሩ የሚታወቁ ቀናቶች ናቸው ምክንያቱም ወሩ ከሰላሳ አይበልጥምና ከነዚህ ወር ቀናቶችም አስረኛው ቀን ላይ እንገኛለን ስለዚህ አንድ ሰው አንድ ቀን አሳልፎ ወደሌላ ቀን በተሸጋገረ ቁጥር ይህ የረህመት ወር ረመዷን እያመለጠው ነው ማለት ነው ስለዚህ ራስን በማጠንከር ወደ ኋላ ሚያደርጉንን ነገር ትተን በኢባዳ ልንጠነክር ይገባል ቀን በቀን ራሳችንን ልንፈትሽና ያለብንን ጉድለት ልንጠግን ይገባል ማለት ነው።
እንደሚታወቀው ይህ ረመዷን የመልካም ስራ የቁርዓን ወር ነው የሶላት የኢባዳ ወር ነው የዚክር ወር ነው ስለዚህ አቅማችን በቻለ ልክ በኢባዳ ልንጠነክር ይገባል።
በአልባሌ ነገሮች ይሄንን ውድ ትልቅ ወር ልናጠፋው አይገባም።

ግዚያችንን በመልካም ነገር ልንጠቀመው ይገባል እያንዳንዱ አቅለኛ የሆነ ሰው እያንዳንዷን ሰከንድ እያንዳንዷን ደቂቃ በአልባሌ በሆነ ነገር እንዲያልፍ መፈቀድ የለብንም
ይቺ ደቂቃ ይቺ ሰከንድ ናት ረመዷን ማለት የረመዷን ሰላሳ ቀን ማለት አሁን እያሳለፍናቸው ያሉት እያንዳንዷ ደቂቃና ሰከንድ ናቸው።
ስለዚህ እያንዳንዷን ሰአት እያንዳንዷን ቀን እያንዳንዷን ሰከንድ በመልካም ስራ ልናሳልፈው ይገባል ማለት ነው።
ወንጀል ሊበቃን ይገባል ወደ አላህ ትክክለኛ ተውበት ልናደርግ ይገባል እውነተኛ ተመላሾች ልንሆን ይገባል አስራ አንድ ወራቶች ላይ ብዙ ወንጀል አሳልፈናል ብዙ ወንጀል ሊኖርብን ይችላል አላህ (ሱብሃነ ወተዓላ) ደግሞ የዛን ወንጀላችንነ ማበሻ ረመዷንን አመጣልን እናም ይሄን የሰጠንን እድል እንጠቀምበት።
ወላሂ ይሄ ትልቅ ኒዕማ ነው ስንት ሰዎች አሉ የተከለከሉ ትናንተ እንደኛው የነበሩ ረመዷንን በጉጉት የሚጠብቁ የነበሩ ሰዎችን ዛሬ አፈር በላያቸው ላይ ተጭኖባቸው ቀብር ውስጥ ገብተዋል። እንደኛው ሲጓጉ የነበሩ ሰዎች ረመዷን አንድ ቀን ሲቀረው ወደ አኼራ የሄደ ሰው አለ። ወይም ደግሞ በሌላ ምክንያት ወደ አኼራ ባይሄድም እንኳ መፆም ያልቻሉ አሉ አልጋ ቁራኛ ሆነው የተቀመጡ መፆም የእፈለጉ ያልቻሉ ብዙዎች አሉ እኛን ከነሱ አላደረገንም ሳንሞት በጤናችን ወዶን እዚህ የራህመት ወር ውስጥ አስገባን። ሃቂቃ ትልቅ እድል ሰጦናል ይሄን እድል ልንጠቀምበት ይገባል። ሁላችንም ልንጠቀምበት ይገባል ቁርዓን በመቅራት ሶላት በማብዛት ዚክር በማለት ተራዊህም በመስገድ ሰደቃ በማብዛት ለእናት አባቶቻችን ለወንድም እህቶቻችን ባጠቃላይ መልካም በመስራት ዝምድናንም በመቀጠል መልካም ስነ ምግባር በማሳየት ባጠቃላይ አላህ በደነገጋቸው ኢባዳዎች በኢኽላስ ልንጠነክር ይገባል።

(አላህ የበለጠ ያውቃል)

መልዕክቱን ሼር በማድረግ በዚህ ውድ ወር ከኢባዳ የተዘናጉትን ወንድም እህቶቻችንን እናንቃቸው።
(በውስጥ መስመር ከአስር ላላነሰ ሰው በመላክ አብሮነታችሁን ግለፁልን።)

ባረከላሁ ፊኩም
በዱዓችሁ አትርሱኝ

https://t.me/Adnan567mh

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

31 Dec, 18:40


☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

31 Dec, 17:46


አቡ ማሊክ ሀሪስ ኢብኑ ዓሊም አል አሽዐሪይ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹ንፅህና የእምነት (ኢማን) ግማሽ ነው፡፡ ‹አልሐምዱሊላህ› ያለችው ቃል ሚዛን ትሞላለች፤ ‹ሱብሀነላህ ወልሐምዱሊላህ› የሚሉት ቃላት በምድርና በሰማይ መካከል (ያለውን ቦታ) ይሞላሉ ወይም ትሞላለች፡፡
ሶላት ብርሃን ነው፡፡ ምፅዋት (ሶደቃ) የኢማን ዋቢ ነው፡፡ ትግስት (ሶብር) ብርሃን ነው፡፡ ቁርዓን ላንተ ወይም በአንተ ላይ አስረጅና መስካሪ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ነፍሱን ነፃ ያወጣ ወይም ለጥፋት የዳረገ ሆኖ ዕለቱን ይጀምራል፡፡

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ ውዱዕ የሶላት መስፈርት፤ የሰላትን ጠቀሜታ፤ ሶደቃን ማብዛት የሙዕሚን እውነተኝነት፣ ታማኝነትና ቅንነትን ያመለክታል፡፡
‹‹ የሶብር ትሩፋት፤ ቁርዓን ለሁሉም ሸሪዓዊ ብይኖች መነሻ መሰረት መሆኑን፡፡
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

21 Dec, 16:55


☑️  ሼኸ ፈውዛን አላህ ይጠብቀዉና እንዲህ ይላሉ።

🌐 ከሰዎች መካከል (لا إله إلا الله) የምትለዋን ቃል እንዳይሉ ሸይጣን ያዘናጋቻቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ።

☑️  ሼኸ ፈውዛን አላህ ይጠብቀዉና እንዲህ ይላሉ።

🌐 ከሰዎች መካከል (لا إله إلا الله) የምትለዋን ቃል እንዳይሉ ሸይጣን ያዘናጋቻቸው በጣም ብዙ ሰዎች አሉ።

➷አንዳንዴ ቢሆን እንጂ ሁሌም አይላትም
➷በዚህች ውድ ቃል አላህን አያወሳበትም
➷የውመል ቂያማ ሚዛንን የምትደፋ ከመሆኗም ጋር አይደጋግማትም
➷ ይህች ቃል ማለት በጣም ትልቅ የሆነች ንግግር ናት።
♦️ነገር ግን ትኩረት የሚሰጧት
➷በአዕምሯቸው ሚያስታውሷት፦ በምላሳቸው ያለማመዷት፦ የሚደጋግሟት  አላህ ኸይርን የወፈቃቸው በጣም ጥቂት የሆኑ አነስተኛ ሰዎች ብቻ ናቸው።
📚 تفسير كلمة التوحيد

👉ስለዚህ لا اله الا الله የምትለዋን ቃል ምላስህ ከማለት አይዘናጋ!!

◂ تفسير كلمة التوحيد

👉ስለዚህ لا اله الا الله የምትለዋን ቃል ምላስህ ከማለት አይዘናጋ!!
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

11 Dec, 17:35


እውን ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለምን?
~
ቁርኣን የአላህ ቃል ለመሆኑ የሚጠራጠር ሙስሊም የለም።  ሙስሊሙ ልጆቹን ቁርኣን እንዲቀሩለት ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርገው፣ ያለ ውዱእ የማይነካው፣ ጧት ማታ የሚቀራው፣ የሚማረው፣ የሚያስተምረው፣ ማስረጃ አድርጎ የሚያጣቅሰው፣ የሚተገብረው “ቁርኣን የጌታዬ ንግግር ነው” ከሚል ፅኑ እምነት ተነስቶ ነው።
ግና የፈጣሪ ቃል የማይገታቸው፣ የሰለፎች ኢጅማዕ የማይከብዳቸው ሃፍረተ ቢስ ፍጡሮች ተተኩና “ቁርኣን የአላህ ሳይሆን የሙሐመድ ወይም የጂብሪል ቃል ነው” አሉ። አሻዒራ! አሕ^ባሽ የዚህ ቡድን ተቀፅላ ነው። ይህ እምነታቸው {ይህ የሰው ቃል እንጂ ሌላ አይደለም} ያለውን ሙሽ'ሪኩ ወሊድ ብኑ ሙጊራን ያስታውሰናል። [አልሙደሢር፡ 25] በተውሒድ ስም የነ አቡ ጀህል ዐቂዳ ዳግም ሲሰበክ አስቡት! የአሕ^ባሾቹ ቁንጮ ዐብደላህ አልሀረሪም ቁርኣን የጂብሪል እንጂ በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም ከሚሉት ነው። በቅርቡ ፌስቡክ ላይ ተዋሽቶበት እንጂ እሱ እንደዚህ አይልም የሚል ወዶ ገብ አሕባሽ ስላየሁኝ ንግግሩን ላጣቅስ፡-
فهو عبارة عن كلام الله بمعنى أنه يحكي كلام الله، ليس هو بنفسه كلام الله
“እሱ (ቁርኣን) የአላህን ንግግር የሚገልፅ ነው፡፡ ማለትም የአላህን ንግግር የሚተርክ ነው፡፡ እንጂ በራሱ የአላህ ንግግር አይደለም፡፡” [አደሊሉል ቀዊም፡ 66 - 69]
ሰውየው ምን ያክል ሙጅ' ሪም እንደሆነም ተመልከቱ፡፡ አዎ “ሙጅ^ሪም ነው” ሲባል የሚከፋው እንደሚኖር አይጠፋኝም፡፡ ግና ቁርኣንን የአላህ ቃል አይደለም ከማለት በላይ ምን አይነት ብል ^ግና አለ?! የሸሪዐ ግንዛቤ የሌለው ጃሂል እንኳ እንዲህ አይነት ጥፋት አይፈፅምም፡፡
"ኪታቦቹ ላይ ‘አላህ እንዲህ ብሏል’ እያለ ቁርኣንን ማጣቀሱ ‘ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው’ ብሎ እንደሚያምን ያሳያል" በማለት ማስረጃ ሊያደርጉለት የሚሞክሩ አሉ፡፡ ሰውየው በማያሻማ ቃል “ቁርኣን በራሱ የአላህ ንግግር አይደለም” እያለ አጉል መንደፋደፍ የትም አያደርስም፡፡ “እሺ ‘አላህ እንዲህ ብሏል’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ከተባለ ይሄው እራሱ ሃሳቡን ግልፅ ያደርግላችኋል፡-
فكلام الله النفسي الذي ليس هو حرفا ولا لغة هو كلام الله الحقيقي؛ أما القرآن المتضمن للألفاظ فهو مخلوق، لكن يمكن إطلاق لفظ القرآن عليه من باب المجاز
“ፊደልም ሆነ ቋንቋ ያልሆነው ነፍሳዊ የሆነው የአላህ ንግግር እርሱ ነው በተጨባጭ የአላህ ንግግር የሚባለው፡፡ ቃላትን የያዘው ቁርኣን ግን እርሱ ፍጡር ነው፡፡ ባይሆን ከዘይቤያዊ አነጋገር አኳያ ቁርኣን (የአላህ ንግግር) በሚል ቃል ሊጠራ ይችላል፡፡” [አነህጁ ሰሊም፡  26]

የዚህ የዐብደላህ አልሀረሪ ንግግር ጭብጥ፡-
- ትክክለኛው የአላህ ንግግር በፊደልም ሆነ በቋንቋ አይገለፅም፣
- በእጃችን ላይ ያለው ቁርኣን ግን በፊደልም በቋንቋም ስለሚገለፅ ፍጡር እንጂ በሐቂቃ የአላህ ንግግር አይደለም፣
- ሆኖም ግን በራሱ የአላህ ንግግር ባይሆንም፣ የአላህን ንግግር ስለሚተርክ በሐቂቃም ባይሆን በዘይቤያዊ አነጋገር ‘ቁርኣን’ (የአላህ ንግግር) ተብሎ ሊጠራ ይችላል እያለ ነው፡፡
ስለዚህ “አላህ እንዲህ ብሏል” ሲል የሚፈልገው በዚህ አገባብ ማለትም ዘይቤያዊ አነጋገርን በማሰብ እንጂ በሐቂቃ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው ለማለት አይደለም፡፡ ይሄ ከንቱ ዐቂዳ አሕ^ባሽ ከወላጁ አሻዒራ የቀዳው እንደሆነ ይሰመርበት፡፡ [አልኢንሷፍ፡ 147] [ሸርሑ ጀውሀረት ተውሒድ፣ አልበይጁሪ፡ 73] [ሸርሑ ጀውሀረት ተውሒድ፣ አሚር]
ይስተዋል! እነዚህ ሰዎች ለሽፋን ያክል ብቻ ቁርኣን የአላህ ንግግር ነው ይላሉ። “የሐቂቃ ነው ወይ?” ስትሉ ግን ጉዳቸው ይከተላል። በዘይቤያዊ አነጋገር (መጃዝ) የአላህ ቃል ተባለ እንጂ በተጨባጭ ግን የአላህን ንግግር የሚገልፅ፣ የሚተርክ (ዒባራ/ ሒካያ) እንጂ የጂብሪል ንግግር ነው ይላሉ። ለዚህ ብልሹ እምነታቸውም ይህቺን አንቀፅ ይጠቀማሉ፡-
                       إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ
“እርሱ በርግጥም የክቡር መልእክተኛ ቃል ነው።”

ይህ መልእክት ቁርኣን ውስጥ ሁለት ቦታ ይገኛል፡፡ [አተክዊር፡ 19] [አልሐቃ፡ 40] በሱረቱ ተክዊር ላይ የተገለፀው “መልእክተኛ” ጂብሪል ሲሆን በሱረቱል ሐቃ ላይ ደግሞ ሙሐመድ ﷺ ናቸው። ይህም አንዱን መዞ ሌላኛውን በመተው “የጂብሪል ነው” “የለም የሙሐመድ ነው” የሚሉ ሞገደኞችን ቅርቃር ውስጥ የሚከት ነው። ከዚህ ቅርቃር መውጫው ለቁርኣኑ ሙሉ በሙሉ እንጅ መስጠት ብቻ ነው። ጂብሪልም ሆነ ሙሐመድ ﷺ መልእክተኞች እንጂ ሌላ አይደሉም። የመልእክተኛ የስራ ድርሻ ደግሞ ማድረስ ነው።
          {وَمَا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلاغُ الْمُبِينُ}
“በመልእክተኛውም ላይ ግልፅ ማድረስ እንጂ ሌላ የለበትም።” [አኑር፡ 54]
ቁርኣኑ ተጠብቆ እንደደረሰ ለማመላከት የሸይጧን ሳይሆን የመልአክ፣ የጠንቋይና የገጣሚ ሳይሆን የመልእክተኛ ቃል እንደሆነ ተገለፀ። ከአስተላላፊነታቸው አንፃር ብቻ ሲታይ አንድ ቦታ የጂብሪል፤ ሌላ ቦታ የሙሐመድ ﷺ ንግግር ተብሏል። እንጂ ጂብሪል ተቀባይ እንደሆነ እንዲህ ፍንትው ብሎ ተቀምጧል’ኮ፡-
         (قُلۡ نَزَّلَهُۥ رُوحُ ٱلۡقُدُسِ مِن رَّبِّكَ بِٱلۡحَقِّ)
{‘ቅዱሱ መንፈስ በእውነት #ከጌታህ አወረደው’ በላቸው።} [አነሕል፡ 102]
ይሄው የጂብሪል የራሱ ንግግር ሳይሆን ከአላህ ተቀብሎ ያወረደው እንደሆነ በግልፅ እየተነገረን ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ልብ የሚያንሸራትት ሞገ^ደኛ ቢኖር አላህ ቅናቻን እንዲያድለው ከመማፀን ውጭ ምን እእናደርገዋለን? በተጨማሪም አላህ እንዲህ ብሏል፡-
وَإِنَّهُ لَتَنْزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِينَ (192) نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ (193) عَلَى قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنْذِرِينَ (194)
{እርሱም በእርግጥ #ከአለማት_ጌታ_የተወረደ ነው። ታማኙ መንፈስ አወረደው። ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረድነው)፡፡} [አሹዐራእ፡ 192-193]
ስለዚህ ጂብሪል ከራሱ ሳይሆን ከጌታ ተቀብሎ ነው ይዞት የወረደው። እንጂ ቁርኣኑ የአላህ ንግግር ለመሆኑማ እንዲህ ተነግሮናል’ኮ፡-
(وَإِنۡ أَحَدࣱ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ٱسۡتَجَارَكَ فَأَجِرۡهُ حَتَّىٰ یَسۡمَعَ كَلَـٰمَ ٱللَّه)
{ከአጋሪዎቹም አንዱ ጥገኝነትን ከጠየቀህ #የአላህን_ንግግር ይሰማ ዘንድ አስጠጋው።} [ተውባህ፡ 6]
ነብዩም ﷺ በዐረፋ ሐጅ ላይ ለታደመው ህዝብ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
أَلاَ رَجُلٌ يَحْمِلُنِى إِلَى قَوْمِهِ فَإِنَّ قُرَيْشًا قَدْ مَنَعُونِى أَنْ أُبَلِّغَ كَلاَمَ رَبِّى
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

12 Nov, 15:34


♻️ምንም አይነት ሙሲባ ቢደርስብህ የውዱ ነብይህን ሞት አስታውስ

👈قال رسول الله صلى الله عليه وسلم፡
《 إذا أصيب أحدكم بمصيبة فليذكر مصيبته بي فإنها أعظم المصائب》
📚 الصحيحة للألباني (١١٠٦)
♻️📌 የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል።

《ከናንተ መሀከል አንዳችሁ ሙሲባ ካጋጠመው እኔ በማጣቱ የደረሰበትን ሙሲባ ያስታውስ። ምክንያቱም እኔን ማጣታችሁ ከሙሲባዎች ሁሉ ትልቁ ነውና።》
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

05 Nov, 18:32


አቢ የህያ ሱሀይብ ኢብኑ ሲናን (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፡- አንሷር የሆኑ ሰዎች የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹የሙዕሚን ጉዳይ እጅግ የሚደንቅ ነው፡፡ ሁለ ነገሩ ኸይር ነው፡፡ ይህ የሙዕሚን (ዕጣ ፈንታ) እንጂ ለማንም (የተሰጠ) አይደለም፡፡ አስደሳች ነገር ከገጠመው ለአላህ ምስጋና ያደርሳል፤ መልካም ይሆንለታል፡፡ ጉዳት ካገኘውም (አስከፊ ነገር ከገጠመውም) ትዕግስት (ሶብር) ያደርጋል፤ ይህም ለርሱ መልካም ይሆንለታል፡፡››

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ የአንድ ሙስሊም ህይወት ውስጥ ክፉም ሆነ በጎ መልካም ነው፡፡ በሁለቱም ከአላህ ዘንድ ምንዳ ያገኝበታል፡፡
‹‹ መልካም ነገር ሲያጋጥም መመስገን እንዲሁም ክፉ ነገር ሲገጥም በሶብር ማሳለፍ፡፡
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

23 Oct, 12:11



❥ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
 أَبِي هُرَيْرَةَ ، قَالَ : سُئِلَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : مَا أَكْثَرُ مَا يُدْخِلُ النَّاسَ الْجَنَّةَ ؟ قَالَ : " تَقْوَى اللَّهِ وَحُسْنُ الْخُلُقِ

ረሱል ﷺ ከሰዎች በብዛት ጀነት ሚገቡት የትኞቹ ናቸው ተብለው ሲጠየቁ፦ 
የሰው ልጅን በብዛት ጀነት የሚያስገባው
☞አላህን መፍራትና
☞ሰናይ ስነ ምግባር ነው፡፡ ብለዋል።

አል ቲርሚዚ 2004 📚ኢብኒ ማጃህ 4246📚

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

25 Sep, 18:33


☞ሉቅማን (አልሃኪም) ለልጁ እነዲህ ብሎት ነበር ፦
"ልጄ ሆይ፡ አሏህንተጠንቀቅ(ፍራ) ፣ ልብህ ብልሹ ሆኖ ሳለ፣ ሰዎች እንዲያከብሩክ ስትል እርሱን (አላህን) እንደምትፈራ አታሳያቸው(አታስመስል)" »
[አብዱላህ ኢብኑ አልሙባረክ ፡

📚 አዝዙህድ ወርረቃኢቅ ቁ63
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

12 Sep, 16:11


📌وَلَئِنْ أَذَقْنَا ٱلْإِنسَٰنَ مِنَّا رَحْمَةً ثُمَّ نَزَعْنَٰهَا مِنْهُ إِنَّهُۥ لَيَـُٔوسٌ كَفُورٌ
♻️ሰውንም ከእኛ ችሮታን ብናቀምሰው ከዚያም ከርሱ ብንወስዳት እርሱ በእርግጥ ተስፋ ቆራጭ ክህደተ ብርቱ ነው፡፡

📌وَلَئِنْ أَذَقْنَٰهُ نَعْمَآءَ بَعْدَ ضَرَّآءَ مَسَّتْهُ لَيَقُولَنَّ ذَهَبَ ٱلسَّيِّـَٔاتُ عَنِّىٓ إِنَّهُۥ لَفَرِحٌ فَخُورٌ
♻️ካገኘችውም ችግር በኋላ ጸጋዎችን ብናቀምሰው «ችግሮች ከኔ ላይ በእርግጥ ተወገዱ» ይላል (አያመሰግንም)፡፡ እርሱ ተደሳች ጉረኛ ነውና ።

📌إِلَّا ٱلَّذِينَ صَبَرُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَأَجْرٌ كَبِيرٌ
♻️ግን እነዚያ የታገሱ መልካም ሥራዎችንም የሠሩ እነዚያ ለእነሱ ምሕረትና ታላቅ ምንዳ አልላቸው፡፡

📚سورة الهود (11 ـ 9)

☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

20 Aug, 13:43


አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹እያንዳንዱ ሙስሊም ምፅዋት የመለገስ ግዴታ አለበት›› አሉ፡፡ ‹የሚመፀውተው ካላገኘስ?› አለ (አንድ ጠያቂ)፡፡ ‹በእጁ ሰርቶ ራሱን ይጥቀም፣ ይመፅውትም› አሉ፡፡ ‹ካልቻለስ?› አላቸው፡፡ ‹የተቸገረን ባለጉዳይ ይርዳ› ሲሉ መለሱ፡፡ ‹ካልቻለስ?› አላቸው፡፡ ‹በፅድቅ ወይም በመልካም ይዘዝ› አሉ፡፡ ‹ይህን ካልፈፀመስ?› ሲል ጠየቃቸው፡፡ ‹ከተንኮል ይቆጠብ፡፡ ይህን ምፅዋት ነው፡፡› የሚል ምላሽ ሰጡ፡፡

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ አንድ ሙስሊም ሰርቶ ራሱን መርዳት እንዳለበት ከቻለ መመፅወት፡፡
‹‹ መልካም ተግባር ሁሉ ሶደቃ መሆኑን የሚያሳይ ሀዲስ ነው፡፡
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

06 Aug, 18:37


አቡ ማሊክ ሀሪስ ኢብኑ ዓሊም አል አሽዐሪይ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹ንፅህና የእምነት (ኢማን) ግማሽ ነው፡፡ ‹አልሐምዱሊላህ› ያለችው ቃል ሚዛን ትሞላለች፤ ‹ሱብሀነላህ ወልሐምዱሊላህ› የሚሉት ቃላት በምድርና በሰማይ መካከል (ያለውን ቦታ) ይሞላሉ ወይም ትሞላለች፡፡
ሶላት ብርሃን ነው፡፡ ምፅዋት (ሶደቃ) የኢማን ዋቢ ነው፡፡ ትግስት (ሶብር) ብርሃን ነው፡፡ ቁርዓን ላንተ ወይም በአንተ ላይ አስረጅና መስካሪ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ነፍሱን ነፃ ያወጣ ወይም ለጥፋት የዳረገ ሆኖ ዕለቱን ይጀምራል፡፡

ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ ውዱዕ የሶላት መስፈርት፤ የሰላትን ጠቀሜታ፤ ሶደቃን ማብዛት የሙዕሚን እውነተኝነት፣ ታማኝነትና ቅንነትን ያመለክታል፡፡
‹‹ የሶብር ትሩፋት፤ ቁርዓን ለሁሉም ሸሪዓዊ ብይኖች መነሻ መሰረት መሆኑን፡፡
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

25 Jul, 04:29


#የአሹራ_ፆም!

አሹራእ ተብሎ የሚጠራው ይህ የሙሃረም አስረኛ ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን አላህ ነብዩላህ ሙሳንና ተከታዮቻቸውን ከአምባገነኑ ከፊርዐውን አደጋ ባህሩን በማሻገር ያዳነበት ቀን በመሆኑ፡ እኛም ሙስሊሞች ከአይሁዶች ይልቅ ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ወንድምነት የተገባን በመሆናችን ልንጾመው ይገባል በማለት ነቢዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ቀኑን በፆም እንድናሳልፈው አሳውቀውናል፡፡

በተለይ ይህን 10ኛውን ቀን (ዐሹራእ) መጾም ያለውን ጥቅም ተጠይቀው ሲመልሱ፡- ‹‹አላህ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት እንዲምር ተስፋ አደርጋለሁ›› ብለዋል(ሙስሊም ዘግበውታል )፡፡

ከአይሁዶች ጋርም ለመለየት ሲባል ቀደም ተብሎ የሙሃረምን ዘጠነኛውን ቀን ጨምሮ መፆም አልያ ደግሞ የሙሃረም 11ኛ ቀኑን ጨምሮ መፆም ሱና ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “አሏህ ካለ የሚመጣው ዓመት ላይ 9ኛውንም ቀን እንጾማለን “ ብለዋል ከዚህም በመነሳት ዑለማዎች ዘጠነኛውንም ቀን መጾም ሱና ነው ብለዋል።

በመሆኑም #ሀሙስ ሙሃረም 9 እና የሙሃረም 10 እለተ #አርብ የአሹራ ፆም ቤተሰቦቻችን፣ወዳጆቻችን እና ሙስሊም ወንድሞቻችን ሁሉ ቀኑን በመፆም በኢባዳ እንዲያሳልፉት እናስታውሳቸው::

ለሃገራችን ሰላም እና መረጋጋትም ዱዓ ማድረግ አንዘንጋ

መልካም ስራ እንዲሰራ ማስታወስ የሰሪውን ያህል ሙሉ ምንዳ ከአላህ (ሱ.ወ) ያስገኝልናል፡፡

አላህ ቀኑን ፆመው የአንድ አመት ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ያድርገን

አሚን
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

21 Jul, 17:37


«ዱኒያ ላይ ከሚገኙት ነገሮች ሁሉ እኔ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት (ሴትና ሽቶ) ናቸው፣ የአይኔ ማረፊያ ደግሞ በሠላት ላይ ተደረገች»።
ረሱል (ሠለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

የነብዩ ሠ,ዐ,ወ ሀዲሶች

20 Jul, 20:14


አዲይ ኢብኑ ሀቲም (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹ከናንተ ውስጥ ጌታው ያለ አስተርጓሚ የማያናግረው ማንም የለም፡፡ (በዚያ ወቅት ሰውዬው) ወደቀኙ ሲመለከት ካስቀደመው (ስራ) ውጭ ምንም ነገር አይታየውም፡፡ ወደ ግራው ሲመለከት ካስቀደመው (ስራው) ውጭ ምንም ነገር አይታየውም፡፡ ወደ ፊት ሲመለከትም ከፊት ለለፊቱ ከእሳት ውጭ ምንም ነገር አያይም፡፡ በክፋይ ተምርም ቢሆን ከእሳት ተጠበቁ፡፡››

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ ከእሳት ለመጠበቁ አንዱ ተግባር መልካም ወይም በጎ ማድረግ ነው፡፡ የተምር ክፋይም ብትሆን ሶደቃ ማድረግ ቢሆን እንኳ ማድረግ ነው፡፡
‹‹ አላህ በመጭው አለም ለባሮቹ ይቀርባል፡፡ በባሪያውና በእሱ መካከል ምንም አይነት ማዕከል ወይም አስተርጓሚ ሳይኖር፡፡
☞ አሊም፣ ሸህ፣ ኡስታዝ፣ ሙፍቲም አይደለሁም፤ ነገር ግን ገና እታች ክፍል ያለሁ
ተማሪ ነኝ።
Telegram የምጠቀመው
«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
ለአሥተያየት @Adnanmoh_bot
አላህ ይ ቀበለን
JOIN 👇

@Adnan567mh

🌐💚💛❤️

2,317

subscribers

46

photos

2

videos