ሐመረ ጽድቅ 1 @tezekern Channel on Telegram

ሐመረ ጽድቅ 1

@tezekern


አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነት ነው እንጅ እንደ በደላችን አይሁን ።

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ (Amharic)

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ የተለያዩ መረጃዎችን እና ጥንድ የሚሳዝን መረጃዎችን ላለው ቡድኖች የሚያድርጉ የታሪክ ቤተሰብ ነው። ይህ ቤተሰብ ከተገኘችው የከፍተኛ መስሪያ ራሱን እንደሚያተረፈን ለመላው የ ገና የማብራሪያ ማሕበረሰብ ለዚህ ሰጡት። ይህብን ቤተሰብ እስከ ታያያችሁ ቦታ እሽ ያሉ ታሪኮችን ማየት ይችላልን? በዚሁ ቤተሰብ የተለየ በቡድን ተመሳሳይ የታሪክ ዛፍ ቅዱስ፡ሴክስ፡ግፁል ለምን ለአእምሮአድ አሰቃቂው ቃል እንቅስቃሴ ካ ለመለያየት ሲሆን ሌላ በዚሁ ቤተሰብ የእግዝኦ ቅንጣት እንድናፍ አዶትብ ጋር ሊቆጣ አይችልም።

ሐመረ ጽድቅ 1

18 Jan, 05:43


ከተራና_ባሕረ_ጥምቀት_ጥምቀተ_ባሕር
   ✝️ታቦታት_ለምን_ከመንበራቸው_ወጥተው_ያድራሉ?
በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት ሥርዐተ_ከተራ

➡️ከተራ_፤ ከተረ (ዘጋ፣ አቆመ፣ አገደ፣ ከለከለ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ውሃን መከተር ወይም ውሃ መገደብ (መዝጋት፥ ማቆም፥ ማገድ፥ ማጠር፥ ዙሪያውን መያዝ፥ መክበብ፥ መከልከል) ማለት ነው፡፡
✝️ከተራ_ለምን_ተባለ?
በጥምቀት በዓል ዋዜማ በጥር 10 ቀን ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውሃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ወይም ጉድጓድ ተቆፍሮ፤ ድንኳን ይተከላል፥ ዳስ ሲጣል ይውላል (ምክንያቱም ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናምና የበረዶ ወራት ስለሆነ ቅዝቃዜውም በወንዞች አጠገብ ስለሚያይል በባሕረ ዮርዳኖስ፥ በዕደ ዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ድንኳን ተክለው፥ ዳስ ጥለው ያድሩ ስለነበረ ነው)፡፡ ነገር ግን በዚህ ወቅት የምንጮች ውሃ ደካማ በመሆኑ ውሃው እንዲጠራቀም ወንዶች ጉድጓድ እየቆፈሩ፥ ሴቶች ውኃ በእንስራ እየቀዱ ከወንዞችና ከምንጮች ውኃውን ይከትራሉ፥ ይገደባሉ (አሁን በከተሞች ሰው ሰራሽ ግድብ ይገደባል)፡፡ የምዕመናኑ አብዛኛው ስራ ውሃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
✝️አንድም በኢያሱ መሪነት እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ባሕር ሲሻገሩ ታቦቱን ያከበሩ (የያዙ) ካህናት ሕዝቡ ተሻግሮ እስከሚያበቃ ከወንዙ መሃል ቆመው ነበር ውኃውም እንደ ባሕረ ኤርትራ ግራና ቀኝ ተከፍሎ እንደ ግድግዳ ቆሞ ነበርና ይህንንም ለማስታወስ ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
✝️አንድም ጌታችን በዮርዳኖስ በተጠመቀ ጊዜ የላይኛው ሸሽቶ እንደ ክምር ተቆልሏል (ከአዳም ጀምሮ እስከ መድኅን መወለድ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ተቋርጦ ለመቅረቱ፥ ከአበው ወደ ውሉድ ላለመተላለፉ ምሳሌ)፤ የታችኛውም ወደ ታች ሸሽቶ በመድረቁ (የአዳም ኀጢአት ከሥሩ እንደተነቀለ ዛፍ ሆና ለመውደቋ ምሳሌ) ከተራ እየተባለ ይጠራል፡፡
✝️ውኃ የሚከተርበት ቦታ ‹‹ባሕረ_ጥምቀት(ጥምቀተ_ባሕር_››) (የታቦት_ማደሪያ) እየተባለ ይጠራል፡፡ ውኃው የሚከተረውም በማግስቱ ጥር 11 ቀን ለሚከበረው የጥምቀት በዓል መጠመቂያና የጥምቀትን በዓል ለማክበር እንዲሆን ነው፡፡ ሌሊት ማኅሌት ተቁሞ፥ ቅዳሴ ተቀድሶ፥ ጠዋት ጸሎት ተደርሶ የሚጠመቅ ሕፃን ካለ እዚያው ውስጥ ይጠመቃል፡፡ ጐበዛዝትም ለቡራኬ ይዋኙበታል ምዕመናንም እንዲሁ ለቡራኬ ይረጩታል፡፡ ያ ስፍራ በዘልማድ ጥምቀተ ባሕር ተብሎ ይጠራል፡፡
✝️ሥርዐተ_ከተራ
ታቦተ ሕግ ይዞ መጓዝና ወደ ወንዝ መውረድ የተጀመረው በአሮን ልጅ በአልዓዛር ጊዜ ነው፡፡ ነገር ግን ቀድሞ በሙሴ ኋላ በኢያሱ መሪነትም ታቦተ ሕጉን ይዘው የዮርዳኖስን ባሕር መሻገራቸውንም ልብ ይሏል፡፡ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁት ጊዜ ከስፍራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት፡፡ /ኢያ.3፥3/ እንዲል፡፡
✝️ የከተራ ዕለት ድንኳኑ ተተክሎ፥ ዳሱ ተጥሎና ውሃው ተከትሮ ሁሉም ነገር ከተስተካከለ በኋላ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ከልጅ እስከ አዋቂ በነቂስ ተወጥቶ በዐፀደ ቤተ ክርስቲያንና ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች ይሰበሰባሉ፤ የየአድባራቱና የገዳማቱ ታቦት በካህናት አማካይነት በወርቅና በብር በተንቈጠቆጠ መጐናጸፊያ እየተሸፈኑ በታቦት ጉዞ (በዝግታ) ወደ ጥምቀተ ባሕሩ ይጓዛሉ፡፡ በዚህም ጊዜባለ መስቀል መፆር ሰንደቅ ዓለማና ዓርማ የያዘው ግን ከሁሉም ፊት ፊት እያለ ቀድሞ ይሄዳል፡፡
የወርቅ (ወርቀዘቦ) ካባና ላንቃ የለበሱና ጥላ የያዙት ቀሳውስትና መነኰሳት ከታቦቱ ጐን መስቀልና ጽንሐሕ የያዙት ከታቦቱ በፊት ማዕጠንት እያጠኑ ይሄዳሉ፡፡
እንደ ቀሳውስቱ ተመሳሳይ ልብስ ተክህኖ የለበሱት ዲያቆናት ጥላ፣ ድባብ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ በፊት በመሆን ያጅቧቸዋል፡፡
ወደ ባሕረ ጥምቀቱም ሲወረድ ካባ ላንቃ፥ ጥንግ ድርብ በለበሱ፥ የብር፣ የነሐስ፣ የወርቅ መቋሚያና ጸናጽል በያዙ በማኅሌታውያን መዘምራን ፣ በሰ/ት/ቤት ተማሪዎች ዝማሬና ሽብሸባ፣ በወጣት መዘምራን ደስታ፣ በወንዶች ሆታ፣ በሴቶች እልልታ ዲያቆናቱን ቀድመው እያጀቡ ይሄዳሉ፡፡
የደብር አለቆችና አበው ካህናት ታቦቱን ተከትለው ይጓዛሉ፡፡
ሕዝቡም ደግሞ ለጥምቀት_ያልሆነ_ቀሚስ_ይበጣጠስ እንዲሉ እንደየችሎታው ያለውን ልብስ (ጃኖ፣ ለምድ፣ በርኖስና የመሳሰለውን) ለብሶና አጊጦ፥  ሽማግሌዎችና የጐበዝ አለቃዎችን በማስቀደም ታቦቱን በመከተል በስተኋላ ይሄዳሉ፡፡
ባሕረ ጥምቀትም እንደደረሱ ታቦቱ በድንኳን አጠገብ ቆሞ  ጸሎት ተድርጐ ሲያልቅ ታቦቱ ወደ ድንኳኑ ይገባል፡፡
የሌሊቱ ማህሌት በካህናት ተጀምሮ አገልግሎቱ መላ ሌሊቱን ሲካሄድ ያድራሉ
✝️በከተራ_ዕለት_የሚከናወኑ_ድርጊቶች_ምሳሌነት_አላቸው_እነዚሁም_፤
➡️ታቦቱ_የጌታችን ምሳሌ
➡️ታቦቱን_አክብሮ_ይዞ_የሚሄደው_ካህን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ_ምሳሌ
➡️ባሕረ_ጥምቀቱ_የዮርዳኖስ_ወንዝ_ምሳሌ
➡️ታቦታቱን_አጅበው_የሚሄዱት_ምዕመናን_ወደ_ቅዱስ_ዮሐንስ_እየመጡ_የንስሐ_ጥምቀት_ሲጠመቁ_የነበሩ_ሰዎች_ምሳሌ
➡️ታቦታቱ_በከተራ_ዕለት_ከመንበራቸው_ወደ_ጥምቀተ_ባሕር_መውረዳቸው_መድኀኔ_ዓለም_ክርስቶስ_በእደ_ዮሐንስ_በፈለገ_ዮርዳኖስ_ለመጠመቅ_ከገሊላ_ወደ_ዮርዳኖስ_ከማታው_ጀምሮ_መውረዱንና_ተራውን_ሲጠብቅ_አድሮ_መጠመቁን_ያጠይቃል፡፡ ‹‹ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡›› /ማቴ፡ 3፥13/
በዓሉን አክብረን በረከተሥጋ በረከተ ነፍስ እንድናገኝ አምላካችን እግዚአብሔር ይርዳን ።
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ሐመረ ጽድቅ 1

17 Jan, 08:25


https://www.facebook.com/share/r/1BSdUy5ubq/

ሐመረ ጽድቅ 1

17 Jan, 07:58


ጾመ ገሀድ

ከዘጠኙ ዓበይት የጌታ በዓላት ሁለቱ የልደትና የጥምቀት በዓላት ተጠቃሾች ናቸው  በሁለቱ በዓላት ቀን ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በኀዘን ማሳለፍ እንደሌለበት ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራሉ ምክንያቱም የክርስቶስ ልደትና ጥምቀት የዕዳ ደብዳቤያችን የተቀደደባቸው የድኅነታችን መሠረት የተጣለባቸው ዐበይት በዓላት  ስለሆኑ ነው እነዚህ በዓላት በረቡዕና በዓርብ ቀን ከዋሉ አስቀድመን በዋዜማው ለውጥ አድርገን እንጾማቸዋለን ልደት ረቡዕ ከሆነ ማግሰኞ በዋዜማው፣ ዓርብ ከሆነ ሐሙስ በዋዜማው እስከምሽቱ አንድ ሰዓት (13 ሰዓት) እንጾማቸዋለን በሌሎችም ቀናት በዋዜማቸው በየዓመቱ ይጾማሉ ቀናቱ ሁለት ቢሆኑም  ቁጥራቸው ግን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተብለው ነው የሚቆጠሩት፡፡
ገሀድ ሁለት መጠሪያ ስሞች አሉት ገሀድና ጋድ፡፡ ገሀድ ማለት መገለጥ መታየት መታወቅ ማለት ነው ተገለጠ ታየ ታወቀ የተባለውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ምንም ከዚያ በፊት አምላክነቱ የተገለጠባቸው ብዙ መንገዶችና ተአምራት ቢኖሩም አብ በደመና ሁኖ የምወደው ልጄ ይህ ነው በማለት፣ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በመቀመጥ የክርስቶስ አምላክነት የተገለጠበት ዕለት ስለሆነ ገሀድ መገለጥ ተብሎ ተሰይሟል
በሌላም በኩል ጋድ ማለት ለውጥ ማለት ነው ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ሲሆኑ ለውጥ ሁኖ የሚጾምበት ማለት ነው ስለዚህ ገሀድ ስንል የክርስቶስን አምላክነት በዕለተ ጥምቀት መገለጥ፣ ጋድ ስንል ደግሞ ለዓርብና ለረቡዕ ጾም ለውጥ ሁኖ የተጾመውን ጾም ማለታችን ነው፡፡ ይህንን ጾም ጥር 10 ቀን የሚነበበው ስንክሳር እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፡፡
ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ከመ ይደሉ ንጹም እሎንተ ክልኤተ ዕለታተ ዘእምቅድመ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት እስመ እላ ዕለታት ህየንቴሆሙ ለረቡዕ ወዓርብ ሶበ ይከውን ላዕሌሆሙ በዓለ ልደት ወጥምቀት ወበዝንቱ ይትፌጸም ለነ ክልኤቱ ግብር ግብረ ጾም ወግብረ በዓል ወከመዝ ሥሩዕ ውስተ አብያተ ክርስቲያኖሙ ለግብፃውያን
ወለእመ ኮነ ዕለተ በይረሙን ዘውእቱ አስተርእዮ በዕለተ እሑድ አው በዕለተ ሰንበተ አይሁድ ይጹሙ በዕለተ ዐርብ እምቅድሜሁ እስከ ምሴት በከመ ተናገርነ ቅድመ ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሀል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዐቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ፡፡ 
ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው
በይረሙን (መገለጥ፣ ገሀድ) በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥር ቀን ነው በዋዜማው ዓርብ እስከምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ፡፡ በማለት ይገልጸዋል፡፡
ከላይ እንዳየነው ጥምቀት ወይም ልደት እሑድና ቅዳሜ ከዋሉ ጾሙ መጀመር ያለበት ዓርብ መሆኑን ተመልክተናል ይህንም መነሻ በማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀት ሰኞ ሲሆን ዓርብ እስከ አንድ ሰዓት፣ ቅዳሜ እስከ ስድስት፣ እሑድ እስከ ቅዳሴ መውጫ እስከ ሦስት በመቁጠር የጾሙን ሰዓት 13 ሰዓት ያደርጉታል ይህም ከላይ የተገለጠውን ስንክሳር መነሻ በማድረግ የሚናገሩት ስለሆነ አክብረን እንቀበለዋለን ቅዳሜ እስከ ስድስት ለመጾሙም ሃይ ምዕ 20 ተጠቃሽ ነው  
በሌላ በኩልም ጋድ አንድ ቀን ነው ሰኞ ሲሆን እሑድን ብቻ ከጥሉላት እንከለከላለን እንጅ ቅዳሜን አይጨምርም በማለት ይህን የሚቃወሙ አሉ ስንክሳር የተናገረውን ምን እናድርገው ተብለው ሲጠየቁም ስንክሳር የታሪክ እንጅ የሥርዓት መጽሐፍ አይደለም የሚል መልስ ነው የሚሰጡት፡፡ ይህ ጥያቄ ወደሌሎች ሊቃውንት ሲቀርብ የሚሰጡት መልስ ደግሞ ስንክሳር ታሪክ ብቻ ሳይሆን ሥርዓትም የተካተተበት መጽሐፍ መሆኑን ይናገራሉ በእርግጥ ስንክሳር ማለት እስትጉቡእ ስብስብ ማለት ስለሆነ ሥርዓተ ቤተ ክርስተቲያንን ከሠሩ አበው ታሪክ የተሰበሰበ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ከላይም እንዳየነው ወበእንተዝ አዘዙነ አበዊነ ስለዚህ አባቶቻችን አዘዙን በማለት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጻፉ አበው አዘዙን አለ እንጅ ስንክሳርን የጻፉ ሰዎች የራሳቸውን ሐሳብ ያንጸባረቁበት አይደለም ስንክሳርም ቢሆን ምንም ቁጥሩ ከአዋልድ መጻሕፍት ቢሆን የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ነውና ጥምቀትና ልደት ሰኞ ከሆኑ ቅዳሜና እሑድን ከጥሉላት ተከልክለን ቅዳሜንም እስከ ስድስት ሰዓት ጹመን የአበውን ትዕዛዝ ማክበር አለብን፡፡
በሌላም በኩል ጋድ አንድ ነው እሱም የጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው የልደት ዋዜማ የለውም የሚሉም አሉ   እንዲህ ለሚሉት መልሱ አጭር ነው ጾመ ነቢያት ስንት ነው የሚል ጥያቄ ማንሣት ነው እንደሚታወቀው ጾመ ነቢያትን ስንጾም ቀናቱ አርባ አራት ናቸው 40 ጾመ ነቢያት፣ 3ቱ የፊልጶስ ደቀ መዛሙርት የጾሙትና አብርሃም ሦርያዊ ተራራ ያፈለሰበት ጾም፣ አንዱ ጾመ ገሀድ ነው ስለዚህ በበዓለ ልደት ዋዜማ የምንጾመው ገሀድ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡
ስለዚህ የ2017ዓ.ም ጥምቀት እሁድ ስለሆነ ➡️ቅዳሜን ከጥሉላት እንጾማለን ማለት ነው።
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ሐመረ ጽድቅ 1

16 Jan, 16:30


https://youtu.be/iSLEukeQRNc?si=74Id0AbmuH8hNQF-

ሐመረ ጽድቅ 1

15 Jan, 16:32


Photo from ke Fiseha
https://youtu.be/4MZ4CHSqkXQ?si=mTttAXsRjFiYTR6y

ሐመረ ጽድቅ 1

15 Jan, 03:55


ጥር 7 በዓለ ቅድስት ሥላሴ
ሥላሴ የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ›› ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኝ ሲሆን ይህም ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ሥላሴ ብለን ስለነገረ ሃይማኖት ስንናነገር ግን አንድም ሦስትም ተብሎ ይተረጎማል፡፡ በዚህም መሠረት እግዚአብሔርን አንድም ሦስትም ብለን ማመናችንን የምንገልፅበት የሃይማኖት ዶግማ ነው፡፡እንደሚታወቀው የሥላሴ አንድነት ስንል በባህርይ በህልውና በፈቃድ…. አንድ አምላክ ማለታችን ሲሆን ሦስትነት ስንል ደግሞ በስም’ በአካል’ በግብር ነው፡፡
የሥላሴ አንድነትና ሦስትነትን ከሚገልጹ ማስረጃዎች ለአብነት፡-
 ‹‹እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር›› ዘፍ.1.26 ‹‹እግዚአብሔርም አለ ብሎ አንድነቱን ‹‹ሰውን በመልካችን እንፍጠር›› ብሎ ሦስትነትን ይገልጻል ፡፡
 እንደዚሁም እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3 .22 ይህ ኃይለ ቃል ‹‹ከእኛ›› የሚለውና ‹እንደ አንዱ› የሚለው የሦስትነት ምሥጢር የሚጠቁም መሆኑን ሊቃውንት ያስረዳሉ፡፡
 በዘመነ ኦሪት የሥላሴ ምሥጢር ከተገለጠበት አንዱ ለአብርሃም በመምሬ አድባር  ዛፍ ሥር ነው ፡፡ ዘፍ.18፡ 1-15 በዚህ ምዕራፍ እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደ ተገለጠለት ወዲያውም ሦስት ሰዎች እንደ ተመለከተ አብርሃምም ሊቀበላቸው ሲጠጋ በመስገድ ‹‹አቤቱ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆነ›› ብሎ አንድነቱን መግለጹን አያይዞም ደግሞ “ጥቂት ውሃ ይምጣላችሁ” ብሎ በአካል ሦስት መሆናቸውን ተናገረ፡፡
በአጠቃላይ በምዕራፉ የአንድነትና የሦስትነት ነገር እናስተውልበታለን፡፡ነቢየ ልዑል ኢሳይያስ ‹‹ቅዱስ’ ቅዱስ’ ቅዱስ እግዚአብሔር …›› ብለው ቅዱሳን መላእክት እንደ ሚያመሰግኑ መመሥከሩ ከሦስት ሳያሳንስ’ እና ሳያስበልጥ መጠቆሙ የሥላሴን ሦስትነት የሚያሰረዳ ነው፡፡ ኢሳ.6.1- 3
የሥላሴ ሦስትነት ስንል- 
በስም፡-  አብ፤ ወልድ፤መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹ወእንዘ ታጠምቅዎሙ በሉ በስመአብ፤ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅድስ›› እንዲል ማቴ. 28.19
በአካል፡-  ለአብ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው ለወልድ ፍጹም ገጽ ፍጹም አካል ፍጹም አካል አለው ለመንፈስ ቅድስ ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ፍጹም አካል አለው ብለን ማመናችንን ነው ይህም የማይወሰን የማይለካ ረቂቅ አካልን ነው፡፡ መዝ. 33.15 መዝ. 118. 73 ዘፍ.18
በግብር ሦስትነት ስንል ፡- የአብ ግብሩ መውለድ፤ማሥረጽ፤ የወልድ ግብሩ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ ወይም አብ አባት፣ወልድ ልጅ ፣መንፈስቅዱስ ሠራፂ ማለታችን ነው፡፡ኢሳ.48.12 መዝ.118.16 ዮሐ 16÷7-19
        በቅዱስ ወንጌል በዮርዳኖስና በደብረ ታቦር የሥላሴ ምሥጢር ገሀድ ለመሆኑ ማስረጃ ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ ማቴ. 3.16 ማቴ.17 መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ ‹‹አነ ወአብ አሐዱ ንህነ›› እኔና አብ አንድ ነን ማለቱና ‹‹እኔን ያየ አብን አየ›› ብሎ ማስተማሩ ነገረ ሥላሴን ያስረዳል ዮሐ .10.30 (14÷11) በይበልጥ አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሠራጺ በማለታችን መበላለጥ እንደሌላቸው በሥልጣን በፈቃድ አንድ መሆንን ያስገነዝበናል፡፡ በምሳሌም ለመረዳት ፀሐይ ከበብ፡ ብርሃን፡ ሙቀት፡ እሳትም ነበልባል፡ፍሕም፡ሙቀት፡ ሲኖራቸው ሦስት ፀሐይ ሦስት እሳት አይባሉም አንድ ፀሐይ አንድ እሳት እንጂ እንደዚሁ ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሦስት ቢባሉም ቅሉ አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም 2ኛ ቆሮ.13.14 ኤፌ. 4÷4 በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ምሥጢረ ሥላሴ የሃይማኖት ዶግማና የሥርዓተ አምልኮ ሁሉ መግለጫችን ነው፡፡ ጸሎታችን፣ ጥምቀታችን፣ ቡራኬያችን…. ሁሉ በስመ ሥላሴ ነው፡፡
ይህም እንዳለ ሆኖ ነገረ ሥላሴን በበዓል ለመመስከርና የቸርነቱ፣ የምሕረቱ ተካፋይ ለመሆን በዓለ ንግሥም ይከናወናል፡፡ በይበልጥም ሐምሌ 7 ቀን ለአብርሃም በድንኳን ደጃፍ መገለጡንና ጥር 7 በባቢሎን በሰናዖር የተፈጸመውን ተአምር በማሰብ እናከብራለን፡፡ዘፍ.18 ዘፍ.11.1-9 በመጽሐፍ ቅዱስና በቅዱሳት አዋልድ መጻሕፍት እንደተመዘገበው ከጥፋት ውሃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፡፡ በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹ሳንሞት ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ› ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡ አለቃቸው ናምሩድ ይባላል ‹‹ ሞትን የሚያመጡብን ሥላሴ ናቸውና እነርሱን ወግተን ሞትን እናርቅ ›› አላቸው ከዚያም ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር ሰይጣን ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹ አሁን አብን ወጋነው አሁን ወልድን ወጋነው ….›› ይሉ ጀመር ቅድስት ሥላሴ ምንም እንኳ ምሕረታቸው የበዛ ቢሆንም በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለሠለጠነባቸውና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ›› በማለት ቋንቋቸውን ለያዩባቸው የማይግባቡ፣ የማይደማመጡ…… ሆነው ተበታትነዋል፡፡ ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ይህን ያደረጉ ሥላሴ በመሆናቸው በዓሉ ጥር 7 ይከበራል፡፡በአጠቃላይ ሥልጣን ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑን እና በራስ ደካማ አመለካከት በመታበይ በሥላሴ ሥራ መግባት’ መጠራጠር … እንደሚጎዳ እንደዚሁም በጽኑ እምነት በመኖር እና በሥላሴ ስም የተጠመቅን ልጅነታችንን በኃጢአት ሳናሳድፍ በንስሐ ታጥበን እና በምግባር ጸንተን መጠበቅ እንደሚገባ የበዓሉ መልእክት ያስገነዝበናል፡፡ "የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ" እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፡፡ ኤፌ. 4÷30
የስላሴ ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት በሁላችን ላይ እንዲያድር ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን፡፡
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/
💠በቴሌግራም
https://t.me/hameretsidk

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ሐመረ ጽድቅ 1

14 Jan, 16:28


Photo from Ke Fiseha
https://youtu.be/APLKV49-B28?si=DAv2yjoXXwZ-0cMx

ሐመረ ጽድቅ 1

14 Jan, 16:28


Photo from Ke Fiseha
https://youtu.be/-Ybh3s2SizQ?si=VG4GgeGb5ufxfXSE

ሐመረ ጽድቅ 1

13 Jan, 16:26


https://youtu.be/GHvTyneb9pg?si=iHFl7o1_lKwf9C_Q

ሐመረ ጽድቅ 1

11 Jan, 16:41


https://youtu.be/2cs-Gbrg8ys?si=L7O8lr7QNlJH7kyz

ሐመረ ጽድቅ 1

10 Jan, 16:48


Photo from ke Fiseha
https://youtu.be/hfJqU1sxX50?si=jLXsEXaogu4WG1Uk

ሐመረ ጽድቅ 1

10 Jan, 10:04


https://youtu.be/8mvuCY5nPQ0?si=QGbsuNz6pPvPk5Ok

ሐመረ ጽድቅ 1

09 Jan, 15:53


https://youtu.be/znebfPizxU4?si=yFpLHpFJwz2b9tWa

ሐመረ ጽድቅ 1

09 Jan, 05:45


ጥር ፩ እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ዓመታዊ የዕረፍት ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት

በሕገ ወንጌል (ክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5:33 ላይ ተጠቅሷል::

+በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን : ዻውሎስን : ናትናኤልን : ኒቆዲሞስን . . .) አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

+ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

+በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ6 ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::

+ለ6 ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በኋላ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ:: በወቅቱ
የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ
መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::
"ከእኔ ይልቅ
ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም
ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: (ሉቃ. 7:18)
በዚያውም
የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ72ቱ አርድእት
አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም
ተገዙለት::
(ሉቃ. 10:17)

ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ
ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን
ተማረ::
ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ
ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ
ባርኳል:: በዚህ
ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን
(ዽዽስናን) ተሹሟል በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ
በወረደ ጊዜ ከ72ቱ
አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት:ምሥጢርም
የተገለጠለት የለም በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን
ይሰብክ ዘንድ ገባ

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት
ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ 7
ዲያቆናት
ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ6ቱ ዲያቆናት
አለቃ እና የ8ሺው ማሕበር መሪ (አስተዳዳሪ) ሆኗል::
8ሺ ሰውን
ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ
ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው::

አንድን ሰው
ተቆጣጥሮ
ለድኅነት ማብቃት እንኳ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ
እንደሚል ግን 'መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ
እግዚአብሔር'
ነውና ለእርሱ ተቻለው:: (ሐዋ. 6:5) አንዳንዶቻችን ቅዱስ
እስጢፋኖስ 'ሊቀ ዲያቆናት' ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን
ይሆናል እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው
ዲቁናው ለእርሱ 'በራት ላይ ዳረጐት' ነው እንጂ እንዲሁ
ዲያቆን
ብቻ አይደለም

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ
ለ 1 ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ: ወንጌልን
እየሰበከ
ቢጋደል ኦሪት 'እጠፋ እጠፋ': ወንጌል ደግሞ 'እሰፋ እሰፋ'
አለች:: በዚህ ጊዜ 'ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው
ቅዱስ
እስጢፋኖስን መግደል
ነው' ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም
አልቀሩ ገደሉት

+እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ
ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው በመጨረሻውም ስለ
እነሱ ምሕረትን
እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ
ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

"ፍልሰት"

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመታት በኋላ
በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበር:: ስሙም
ሉክያኖስ ይባል
ነበር:: በተደጋጋሚ በራዕይ ቅዱሱ እየተገለጠ "ሥጋየን
አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለዻዻሱ ነገረው:: ዻዻሱም
ደስ ብሎት
ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አጸደ ገማልያል
(የመምሕሩ ርስት ነው) ሔደ::

+ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ::
መላእክት ሲያጥኑ በጐ መዓዛ ሸተተ:: ዝማሬ መላእክትም
ተሰማ:: ሕዝቡና
ዻዻሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው: በታላቅ
ዝማሬና በሐሴት ዐጽሙን ከዚያ አውጥተው: በጽርሐ
ጽዮን (በተቀደሰችው
ቤት) አኖሩት::

እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተ
ክርስቲያን አንጾለት ወደዚያ አገቡት:: ከ5 ዓመታት
በኋላም
እለ እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጐን
ስለ ፍቅሩ አኖሩት::ሚስቱ ወደ ሃገሯ ቁስጥንጥንያ
ስትመለስ
የባሏን ሥጋ መስሏት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ
በመርከብ ጭና ወሰደችው:: መንገድ ላይ ከሳጥኑ ውስጥ
ዝማሬ ሰምታ
ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው:: እጅግ ደስ
አላት: አምላክ ለዚህ አድሏታልና::

እርሷም ወስዳ ለታላቁ
ንጉሥ
ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አስረከበች:: በከተማውም ታላቅ
ሐሴት ተደረገ::ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው
ሲወስዱትም በቅሎዋ
በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች:: በዚያም ላይ
ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ታንጾለታል:: ቅዱስ እስጢፋኖስ
ሲመቱ
➡️ጥቅምት 17:
➡️ዕረፍቱ ጥር 1:
➡️ፍልሰቱ ደግሞ መስከረም
15 ቀን ነው

✞እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል
ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር  አንዳንዶቹ
ተነስተው
እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም
ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ
በሙሴ
ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር
ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ  በሸንጐም
የተቀመጡት ሁሉ
ትኩር
ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::
(ሐዋ. 6:8-15)
የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከት በሁላችንም ላይ ይደርብን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ሐመረ ጽድቅ 1

06 Jan, 18:41


https://www.youtube.com/live/8fmtmCkyjHA?si=sn9cMRCNexAO2Pvs

ሐመረ ጽድቅ 1

06 Jan, 07:25


አማን በአማን መንክር ስብሐተ ልደቱ

ትርጉም

የልደቱ ክብር እውነት በእውነት ድንቅ ነው።
ቅዱስያሬድ

💒ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን፤ ሴቶች ከወለዷቸው ኹሉ፤ ሕዝቡን ከኃጢአት ባርነት ሊያወጣቸው፤ ከሞት ግዞት ሊያድናቸው የተቻለው ማንም አልነበረም፤ ዛሬ ግን ከኃጢአት ንጹሕ ኾኖ፤ ኃጢአትን የሚያርቅ ጌታ ከድንግል ማርያም ማሕፀን የተገኘበት፤ በመለኮቱ ያለ እናት፤ በሰውነቱ ያለ አባት የተወለደ ሕጻንን በቤተልሔም ያየንበት ክቡር ዕለት ። በእውነት ድንቅ ልደት ነው !!

💒በምድራችን ላይ ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ ያለ ወንድ ዘር የፀነሰች ሴትን፤ ያለ ምጥ የወለደች ድንግልን፤ ያለ አባት የተጸነሰ ሕጻንን፤ ከወለደችም በኋላ በድንግልና ጸንታ የኖረች እናትን አይተን ያደነቅንበት፤ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም የተባለውን ጌታ በክንዷ ታቅፋው የተመለከትንበት፤ እናቱን የፈጠረ ልጅ ጌታችንን፤ ፈጣሪዋን የወለደች እናት እመቤታችንን የተመለከትንበት ክቡር ዕለት፤ በእውነት መንክር ልደት!!

💒 ደብረ ሲናን ያንቀጠቀጠ ግርማው ቀርቶ፤ ሕዝቡን በነጋሪት ድምጽ የገሠፀ ቁጣውን ትቶ፤ እኛን ለማዳን የማይታየው ታየ፤ የማይዳሰሰው ተዳሰሰ፤ የማይያዘው ተያዘ፤ የማይታወቀው ታወቀ፤ አበው በትንቢት መነጽር ያዩት ረቂቅ ብርሃን በአካል የተገለጠበት፤ በባሕርዩ የማይወሰነው ጌታ በሥጋ ማርያም ተወስኖ፤ እንደ ሕጻናት ሲያለቅስ ሲያነጥስ የሰማንበት ክቡር ዕለት። በእውነት መንክር ልደት !!

💒 ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ ድንግልናን ከእናትነት አስማምታ፤ አገልጋይነትን ከእመቤትነት ጋር አስተባብራ፤ ወተትን ከድንግልና ጋር ይዛ የተገኘችን እናት የተመለከትንበት፤ ኹሉን ቻይ የኾነ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ረቂቅነቱን በግዙፍነት፤ ታላቅነቱን በታናሽነት፤ ጌትነቱን በባርነት፤ ኃያልነቱን በደካማነት ሰውሮ፤ የጠፋውን በግ ፍለጋ በትህትና ኾኖ፤ ኹሉ በእርሱ፤ ኹሉ ከእርሱ፤ ኹሉም የእርሱ ሲሆን፤ ምንም እንደሌለው በከብቶች በረት ተኝቶ፤ በጨርቅ ተጠቅልሎ፤ በግርግም ተኝቶ ያየንበት፤ ወደ እኛ የመጣበት ክቡር ዕለት፡፡ በእውነት መንክር ልደት !!

💒ክብር ተለይቶት የነበረ ሥጋ ክቡር አምላክ ኾኖ የታየበት፤ የጸጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ሥጋ የባሕርይ አምላክ መኾኑን የተመለከትንበት፤ ብሉዩ አዳም በአዲሱ አዳም የተለወጠበት፤ ምድራዊው አዳም ከሦስቱ አካላት እንደ አንዱ የኾነበት፤ በዘባነ ኪሩብ ተቀምጦ ክብርና ምስጋናን የባሕርዩ አድርጎ ሲቀበል ያየንበት፤ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ለመቅደስካህናት ያልተደረገ ድንቅ ነገር ተንቀው ለሚኖሩ ለከብት እረኞች ሰማያዊ ምሥጢር ሲገለጥ አይተን ያደነቅንበት፤ ቀድሞ ለፀብና ለጦርነት ይመጡ የነበሩ ነገሥታት፤ ዕርቅ መውረዱን ሰላም መጀመሩን ለማጠየቅ እጅ መንሻ ይዘው የመጡበት፤ ሰባቱ መስተጻርራን የተባሉ ሰውና እግዚአብሔር የታረቁበት፤ ነፍስና ሥጋ የተስማሙበት፤ መላእክትና ሰው በሕብረት ያመሰገኑበት፤ ሕዝብና አሕዛብ አንድ የኾኑበት ክቡር ዕለት። በእውነት ድንቅ ልደት ነው!!

💒በልደቱ ዕለት መላእክቱ ሊቃነ መላእክቱ፤ ፍጥረታትን ኹሉ የሚመግብ እርሱ፤ የእናቱን ጡት ሲጠባ አይተው ተደነቁ፤ በቦታው የነበሩ እረኞች ራሱን ስለ በጎቹ ብሎ ነፍሱን ለሚሰጠው እረኛ ዘመሩ፤ ላሞችና በጎች፤ አህዮችና በሬዎች፤ በበረት የተኛው ሕፃን ፈጣሪያቸው መኾኑን አውቀው፤ ጌታቸው መኾኑን ተረድተው፤ በትንፋሻቸው አሟሟቁ፤ የሚገርመውና የሚደንቀው በመገናኛው ድንኳን በኦሪት ሕግ ዕለት ዕለት ለመሥዋዕትነት ደማቸው ይፈስ የነበሩ እንስሳትን ሳይቀር ያስደሰተ ልደት !! አይገርማችሁም መሥዋዕትነታቸውን ለዘለዓለም የሚያስቀር አማናዊው የእግዚአብሔር በግ ስለተወለደ በልደቱ ዕለት ተገኙ። በእውነት ድንቅ ልደት ልደት !!

💒 ለሰው ያለው ፍቅር ታላቅ ከመኾኑ የተነሳ የእኛ የኾነውን ኹሉ ለእርሱ አደረገ፤ የእርሱ የኾነውን ኹሉ ደግሞ ለእኛ ሰጠ፤ በዚኽም ቀድሞ ሲፈጥረን ከሰጠን ስጦታ ይልቅ ዛሬ በሐዲስ ኪዳን የሰጠን ስጦታ እጅግ በለጠ፤ በመጀመሪያው ተፈጥሯችን ክብርት አርኣያውን ሰጥቶ ፈጠረን፤ በኋላ ግን በኃጢአት የተበላሸ ባሕርያችንን ገንዘብ አደረገ፤ ከቀደመው ይልቅ ያኹኑ ፍቅር በለጠ፤ ይገርማል !! ታላቁን ለመምሰል ኹሉም ይፈልጋል ታናሹን ለመምሰል ግን ማን ያስባል? ጌትነትን የሚፈልግ ሰው አይታጣም ባርነትን ግን ማን ይወዳል ? አይገርማችኹም !! እኛን ከፍ ከፍ ሊያደርገን ምንም እንኳን ሰው ያጣ የነጣ ደሀ ቢኾን እንኳን በማይወለድበት በበረት ተወለደ፤ እኛን የብርሃን ልብስ ሊያለብሰን እርሱ የሚለብሰው ጨርቅ አንሶት በበለሶን ቅጠል ተሸፍኖ አየነው። በእውነት ድንቅ ልደት ነው!!

💒 ጥንታዊትናሐዋርያዊት የኾነችው ምርጧ፤ በምድር ላይ ያለችው ሰማያዊዋ፤ ክርስቶስን የወከለችው ብቸኛዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም፤ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ከዘጠኙ ዓበይት በዓላት አንዱ የኾነውን ይኽን ታላቅና ገናና በዓል፤ ቅዱሳት መጻሕፍት የምሥጢር ምንጭ በኾኑለት፤ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ በሚዘምረው፤ ልቡናን እንደ ንሥር በሚያበረው ወደ ሰማያዊው ዓለም በተመስጦ በሚያደርሰው በቅዱስ ያሬድ ምስጋና ከሊቃውንት አባቶች ጋር ፦

ሃሌ ሉያ ዮም ፍሥሐ ኮነ
በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ
እምቅድስት ድንግል
ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ
ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ
አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ

ትርጉም

ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ስለመወለዱ ዛሬ ደስታ ኾነ፤
ሰብአ ሰገል የሰገዱለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤
የልደቱ ክብር በእውነት ድንቅ ነው፤
እያልን እናመሰግናለን ይህንን በዓል ስናከብር
➡️የተራቡትን በማብላት
➡️የተጠሙትን በማጠጣት
➡️ያዘኑት በማጽናናት
➡️የተቸገሩትን በመርዳት
➡️የተጣላን በመታረቅ
➡️በዓሉ የስጦታ በዓል እንደመሆኑ መጠን ለቤተ መቅደስም ስጦታችንን በማቅረብ
➡️ስጋወደሙን በመቀጠል
➡️ ምንም የሌላቸውን በማገዝና እነዚህን በመሳሰሉት መልካም ተግባራት በማከናወን ልናከብር ይገባናል ።
በዓሉን የሰላም፣የጤና፣የፍቅር ፣የበረከት ያድርግልን በያላችሁበት እግዚአብሔር ይባርካችሁ ሰላሙንም ያብዛላችሁ አሜን ።

መልካም በዓል።

ሐመረ ጽድቅ 1

05 Jan, 17:12


https://youtu.be/8DN0I3Mk2hQ?si=dusZmlELObdj7I-1

ሐመረ ጽድቅ 1

05 Jan, 07:59


ከታኅሣሥ20-27 እሁድ ሲውል ኖላዊ ይባላል።
ኖላዊ የቃሉ ፍቺ ኖለወ ፣ ጠበቀ፣መራ፣ኖላዊ› ማለት ‹እረኛ፣ ጠባቂ› ማለት ነው።
   ኖላዊ ኄር (መልካም እረኞች)
የበጎችን ጠባይ ያውቃሉ፡፡
ለበጎች ምን እንደሚያስፈልጋቸውም ይረዳሉ፡፡
መልካም እረኞች ለበጎች ይራራሉ፤
ስለዚህም ወደ ለመለመ መስክ፣ ወደ ንጹሕ ምንጭ ይመሯቸዋል።
የተሰበሩትን ይጠግኗቸዋል፤ የደከሙትንም ያበረቷቸዋል፡፡
ከዚህ ሁሉ ጋርም በጎችን ከአንበሳ መንጋጋ፣ ከተኩላ ንጥቂያ ይከላከላሉ፡፡ እረኞች ለበጎቻቸው የሚያስፈልጋቸውን ሣር ውኃ ሳያጓድሉ እንዲጠብቁ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በነፍስ በሥጋ የሚጠብቅ ቸር እረኛ ነው፡፡
ኖላዊነት (እረኝነት) ከአራት ወገን ነው።
🌿፩. መለኮታዊ እረኝነት
➾ መለኮታዊ እረኝነት ከሁሉም በላይ ነው። እግዚአብሔር በቸርነቱ ዕድሜ ልካችንን ይጠብቀናል። እንቅልፍ የሌለው እውነተኛ እረኛ ክርስቶስ ነው። "መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።" እንዲል (ዮሐ ፲ ፥ ፲፩፤ መዝ ፸፱ ፥ ፩)
1፤ ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ።
2፤ በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም፤ ኃይልህን አንሣ እኛንም ለማዳን ና።
3፤ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።      
መዝ 121 ፥4፤ እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም።
🌿፪. መልአካዊ እረኝነት
➾ ቅዱሳን መላእክት ለሰዎች የሚያደርጉት የማይቋረጥ ጥበቃ። (መዝ ፺፥፲፩) በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤
መዝ 34 ፥7፤ የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
🌿፫. ሰብአዊ እረኝነት
➾ የካህናት ኖላዊነት ሲሆን ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታረቅ ከፍ ያለ ሥልጣንና ሓላፊነት ለሰዎች (ለካህናት) ተሰጥቷል። (ዮሐ ፳፩፥፲፯) የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትውደኛለኽን? 
በጎቼን ጠብቅ ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ ግልገሎቼን አሠማራ ሲል አደራ ሰጠው
🌿፬. ግላዊ እረኝነት
➾ ሰው ራሱን ይጠብቃል። ራሱን የሚጠብቀውም ከክፋት፣ ከገቢረ ኃጢአት ነው። (፩ኛ ጢሞ ፫፥፭) ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?
ስለ መልካም እረኛ ሲነሣ በአብነት ከሚጠቀሱ የቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል
🌿ሙሴ
ወይእዜኒ እመ ተኀድግ ሎሙ ዘንተ ኃጢአተ ኅድግ ወእመ አኮሰ ደምስስ ኪያየኒ እመጽሐፍከ ዘጸሐፍከኒ፤ ሕዝብኽን ይቅር የማትላቸው ከኾነ እኔን ከጻፍኸው መጽሐፍኽ ደምስሰኝ›› በማለት መማጸኑም ስለዚህ ነው፡፡ የዚህ መልካም እረኛ ጸሎትም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን አግኝቷል (ዘፀ. ፴፪፥፴፪)፡፡
🌿ዳዊት‹‹ረከብክዎ ለዳዊት ወልደ ዕሴይ ብእሴ ምእመነ ዘከመ ልብየ፤ ዘይገብር ኵሎ ፈቃድየ፤ ፈቃዴን ዅሉ የሚያደርግ የዕሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ›› (ሐዋ. ፲፫፥፳፪) ብሎ እግዚአብሔር የመሰከረለት ።ሙሉ ታሪኩን ፩ኛ ሳሙ. ፲፮፥፲፪-፲፫) ይመልከቱ።
በረከታቸው ይደርብንና ኢትዮጵያዊው ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ አንደኛው ናቸው፡፡ ጠላት አገራችንን በወረረበት፣ በመንጋው ላይ መከራ እና ችግር በጸናበት፣ እንደዚሁም የንጹሐን ደም በግፍ በፈሰሰበት በዚያ በፈተና ወቅት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለቤተ ክርስቲያንም ለአገርም የሚያስቡ መልካም እረኛ እንደ ነበሩ የታሪክ መዛግብት ማስረጃዎች ናቸው፡፡
መልካሙ እረኛችን ቅዱስ እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ ይጠብቀን ወስብሐት ለእግዚአብሔር ።
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ሐመረ ጽድቅ 1

02 Jan, 16:18


https://youtu.be/WesO5tQhyJ0?si=E45AY3lwgpqZdfyu

ሐመረ ጽድቅ 1

02 Jan, 04:00


☆☆☆_በዓለ ልደቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ_☆☆☆
❖እንኳን አደረሳችሁ ታህሣሥ ፳፬ (24) ቀን የአባታችን ኢትዮጵያዊው ሐዋርያና ጻድቅ ተክለሃይማኖት ልደቱ ክብረ በዓል ነው ፤ በረከቱ ፣ ጸሎትና አማላጅነቱ በኛ ባመንን በህዝበ ክርሰቲያን ላይ በቤተክርስቲያናችን እንዲሁም በሀገራችን ላይ ጸንቶ ይኑር አሜን!❖ <<“የፃድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው “ >>/ምሳ 10፣7/
አቡነ ተክለሃይማኖት የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት አባት ቅዱስ ፀጋዘአብ በሸዋ ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህን ነበሩ፡፡ መጋቢት 24 ቀን አባታችን ተክለሃይማኖት ተፀነሱ በታህሣስ 24 ቀን በ1190 ዓ.ም አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ሐረያ እና ከአባታቸው ከቅዱስ ፀጋዘአብ ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በ3ኛው ቀን *አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ* ብለው ፈጣሪያቸውን አመሠገኑ በተወለዱ በ40ኛው ቀን ክርስትናን በመነሳት ፍስሐ ጽዮን “የጽዮን ደስታ” ተብለው ተጠሩ፡፡ አባታችን 7 ዓመት እስከሞላቸው ድረስ ከአባታቸው ከፀጋዘአብ ዘንድ እየተማሩ አደጉ፡፡ አባታችን በ15 ዓመታቸው ዲቁናን ከጌርሎስ ዘንድ ተቀበሉ፡፡ አባታችን በ22 ዓመታቸው ከአቡነ ጌርሎስ ዘንድ ቅስናንዠ ተቀበሉ፡፡ በከተታ አውራጃ 3 ዓመት ወንጌልን እያስተማሩ ብዙ ድንቅ ነገርን አደረጉ፡፡አባታችን በዳዊት ፀሎት ከነቢያት ምስጋና ሌሊቱን ሙሉ ይተጉ ነበር በያንዳንዱ መዝሙርም 10፣ 10 ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡ በሕዳር 24 ቀን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ላይ ነጠቃቸው (አወጣቸው) ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበር “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አጥነዋል፡፡ በሐይቅ 10 ዓመት በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በአት አድርገው ኖሩ፡፡ ለ22 ዓመት ቆመው በመፀለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሠበረ ደቀ መዝሙሮቻቸው በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡ በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በፀሎት ቆሙ በጠቅላላው ለ29 ዓመት በፀሎት ከቆሙ በኋላ በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ አባታችን ባረፉ 54 ዓመታቸው በ1354 ዓ.ም ለአባታችን ለአቡነ እዝቅያስ ተገልጸው አጽማቸው ከደብረ አስቦ ወደ ደብረ ሊባኖስ ግንቦት 12 ቀን እንዲፈልስ አድርገዋል፡፡ << ተዘከሩ መኳንንቲክሙ ዘነገሩክሙ ቃለ እግዚአብሔር ወእንዘ ትሬእዩ ሠናየ ግዕዞሙ ወሞጻእቶሙ ተመሰሉ በሃይማኖቶሙ>> ዕብ 13፣7 (የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን መምህሮቻችሁን አስቡ መልካም ጠባያቸውንና ፍጻሜአቸውን አይታችሁም በሃይማኖት ምሰሉአቸው፡፡ ዕብ 13፣7)
✞=>ህዳር 24 ቀን 25ተኛ ካህናተ ሰማይ ሆነው በሠማይ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት•
✞=>ታህሳስ 24 ቀን የአባታችን ልደት•
✞=>ጥር 24 ቀን የአባታችን ስባረ አጽም •
✞=>መጋቢት 24 ቀን የአባታችን ጽንሠት •
✞=>ግንቦት 12 ቀን የአባታችን ፍልሰተ አጽም•
✞=>ነሐሴ 24 ቀን የአባታችን እረፍት•
_የአባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በረከታቸው አማላጅነታቸው ለሁላችንም ይድረሰን አሜን።
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ሐመረ ጽድቅ 1

01 Jan, 16:09


https://youtu.be/a3LLb0u5hog?si=gte0mBJpm9biPVrD

ሐመረ ጽድቅ 1

30 Dec, 16:44


https://youtu.be/JPt53hFbQIc?si=BJIKeKZstVg5UDUD

ሐመረ ጽድቅ 1

30 Dec, 09:51


“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29

💐እንኳን ለእናታችን ቅድስት ድንግል  ማርያም ወርኃዊ በዓሏ በሰላም አደረሳችሁ።

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡ በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

ሺህ ቃላትን ብንደረድር ያንቺን ክብር ልንገልፀውስ እንደምን እንችላለን ?   “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29
የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችሁ ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን።

ሐመረ ጽድቅ 1

29 Dec, 16:25


https://youtu.be/EBGol6QM9mY?si=zy6GMp6SZmTLQK4c

ሐመረ ጽድቅ 1

29 Dec, 08:53


የተከበራችሁ የዚህ ቻናል ተከታታዮች በሙሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንደምን አላችሁ።አሜን አምላካችን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
ከላይ እስከአሁን በተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግስትከ ስም ስንማማርበት የነበረው አሁን ወደ ዩትዩብ ስላደገ ስሙም ሐመረ ጽድቅ በሚል ይቀጥላል ምክንያቱም ከዩትዩብ ጋር እንዲመሳሰል ነው።
ሐመረ ጽድቅ ዩትዩብ ወደ ፊት ብዙህ መንፈሳዊ ትምህርቶችን የምንማማርበት ስለሆነ
- subscribe,
-like ,
-share,
-comment
በማድረግ እንድታበረታቱን ማሳሰብ እወዳለሁ በያላችሁበት የእግዚአብሔር ሰላም ይብዛላችሁ።

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

28 Dec, 16:37


https://youtu.be/bfelrnP6r00?si=ooc0N0GEjIO_0sPG

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

28 Dec, 16:33


https://youtu.be/-ZR-28CU8tQ?si=XSbhhhmT9FQI7HBN

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

28 Dec, 04:26


እንኳን ለታኅሣሥ 19-የራማው ልዑል
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን በእሳት ከመቃጠል ያዳነበት ዕለት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን ።
❄️ታህሣሥ 19 ቀን ለምን እናከብራለን?

ታሪኩ በጥቂቱ እንደሚከተለው ነው
ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉት ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምንቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡
በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡
የዚያን ጊዜም ?
ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡
መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ› አለ፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

የእግዚአብሔር ቸርነት፤ የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ፣ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤልጥበቃና ተራዳኢነት የቅዱሳን ሁሉ ምልጃ አይለየን፤ አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
🌿ሁል ጊዜ  ለመከታተል ከታች ባሉት ሊንኮች ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ👇
💠በዩትዩብ
https://youtube.com/channel/UCvSvpiGvVwqgHEjsmlpBmSA?si=1LyP1IU2vUGT6PDQ
💠በፌስቡክ ገጽ
https://www.facebook.com/share/CRcKQsKeXZPnb2bB/
💠በቴሌግራም
https://t.me/hameretsidk

💠በቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@hameretsidk?_t=8pugO039Zpu&_r=1

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

27 Dec, 07:43


https://youtu.be/JhNnK6-tvXM?si=k7-hTeo1sod-7gOH

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

27 Dec, 07:40


https://youtu.be/OiR4ncHcKaE?si=lfoC_VRqTYKFGTMc

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

27 Dec, 07:40


https://youtu.be/RDMfMLR5u6Y?si=zKMr6BqYA8HcYKWv

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

25 Dec, 09:36


https://youtu.be/PQzinm2aI-I?si=lCPJfp4XRxciZMPA

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

23 Dec, 16:59


https://youtu.be/CpIrR2Bm9NM?si=3cas1U1g1LPOinEc

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

21 Dec, 11:14


"እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል፡፡ የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል፡፡ እኔ ቁስለኛ ነኝ አንቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ፡፡ ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡" [አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ]

🌹ቅድስት ሆይ ለምኝልን🤲

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

19 Dec, 15:57


አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ። ማረኝና አድምጠኝ።
አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ። አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።
መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 27 ቁ 7-9
🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼🙏🏼

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

16 Dec, 16:21


https://youtu.be/71lsK3HRJRk?si=UDAhb47_RumMuz18

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

13 Dec, 05:51


" ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:5

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

26 Nov, 14:10


Watch "💠የኅዳር ማርያም ወረብ💠በሊቀ ጠበብት ቀ/ ፍሥሐ ግርማ።" on YouTube
https://youtu.be/5QNNGhe5X2Y?si=JMxfveoidxSvl8t7

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

21 Nov, 15:21


https://youtu.be/UCpesOeF5Xc?si=TDsTBPUH6BfLEY1E

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

14 Nov, 13:59


....ድንግል ሆይ ወደ አንቺ መጥቶ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ያለሽ መልዐክ ዛሬም ወደ እኔ ይምጣ🙏

#ኃጢያት ያደቀቃት በኃዘን የተዋጠች ነፍሴን ከጸጋ የተራቆትሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ይበላት 🙏

#ጌታ በእኔ ልብ እንዳይፀነስ 'ያለ ኃጥያት መኖርን ስለማላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ?' ብልም ወደ አንቺ የመጣው መንፈስ ቅዱስ ወደ እኔ በምሕረት ይምጣ🙏

#በእስራኤል ልጆች ሠፈር መና እንደ ወረደ የልጅሽ ምሕረት በእኔ ላይ ይውረድ 🙏

 #አንቺን ድንግልና ከማጣት እንደ ጋረደሽ እኔን ከኃጥያት ይጋርደኝ🙏

#አንቺን አምላክን ለመውለድ ያፀናሽ አብ እኔን ልጅሽን በማመን ያጽናኝ🙏

#አንቺ በማሕፀንሽ ዘጠኝ ወር የፀነስሽውን ጌታ እኔ ለደቂቃዎች እንኳን በልቤ እንድፀንስው ፍቀጂልኝ🙏

#የፀነስሁትን የኃጥአት አሳብ ከልቤ አውጥተሽ በሕሊናዬ ልጅሽ እንዲያድር ልምኚልኝ🙏

#ጌታን በእጆችሽ መሃል የያዝሽው ሆይ አንቺ ጌታን ለዓመታት ታቅፈሽው ነበር🙏

#እኔ ግን ለአንድ ደቂቃ እንኳን ሰውነቴ ከኃጢአት አርፎ እርሱን ብቻ ታቅፌ እንድውል ፍቀጅልኝ🙏


AMEN🙏

    

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

11 Nov, 18:05


Watch "💠የኅዳር ሚካኤል ወረብ💠በሊቀ ጠበብት መ/ር ፍሥሐ ግርማ ።" on YouTube
https://youtu.be/furLkv3gack?si=aEJIHXW4i7L8yuHH

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

11 Nov, 02:54


''ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ኀዘነ ልብየ

ርግቤ ሆይ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ''

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣
ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"

📖አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ማርያም

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

09 Nov, 22:54


እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፎአልና።

ኦሪት ዘፍጥረት 2 : 3

ሰንበት 🙏🙏🙏🙏🙏


አቤቱ ነብሴን አድምጣት 🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

23 Oct, 07:17


Watch "21 October 2024" on YouTube
https://youtu.be/-D9ZnbEOQgw?si=eNHLFeTp-qf6KABn

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

22 Oct, 02:52


🕯 .... ቅዱስ ሚካኤል.... 🕯

ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው እንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምነት🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

14 Oct, 16:48


Watch "💠የጽጌ1ኛ ዓመት 3ኛ ሰንበት ወረብ ትመስል እምኪ እና እንዘ ተሐቅፊዮ💠በሊቀ ጠበብት መ/ር ፍሥሐ ግርማ።" on YouTube
https://youtu.be/S7mdGcUbSIM?si=ANxPeei2WRUcp3du

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

12 Oct, 12:18


💚...ሕፃን እናቱን ባየ ጊዜ እንደሚደሰት ሥዕልሽን ሳይና ስሳለም ደስ ይለኛል

              🕯... አባ ጽጌ ድንግል...

@Mezmure_tewahdo

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

07 Oct, 16:17


https://youtu.be/QAR_8B0qTsA?si=JTpGSSONRynob5iX

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

06 Oct, 10:26


👆👆👆👆👇👇👇👇👇👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
#የተከበራችሁ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ከላይ የተላከው የ YouTube ቻናል በጣም የምንወዳቸው የሊቀ ጠበብት መምህር ፍሰሀ ቻናል ነው
ስለዚህ እየገባችሁ የምተላፉትን ቃለ እግዚአብሔር እንድትከታተሉ እናሳስባለን 🙏

👉በዚህ ቻናል የሚተላለፉ ትምህርቶች
1 እስመለዓለም
2 ስብከቶች
3 ምስባክ
4 ወረብ እና የተለያዩ መንፈሳው ትምህርቶች ናቸው ስለዚህ subscribe በማድረግ እንድትከታተሉ እናሳስባለን🙏

መልካም ሰንበት 🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

06 Oct, 10:26


https://youtu.be/1aiNoZpHBTY?si=dxb7NvWC6cXZ7V-N

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

06 Oct, 09:24


ሰላም እንዴት አመሻችሁ እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ🙏
#የተከበራችሁ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች ከላይ የተላከው የ YouTube ቻናል በጣም የምንወዳቸው የሊቀ ጠበብት መምህር ፍሰሀ ቻናል ነው
ስለዚህ እየገባችሁ የምተላፉትን ቃለ እግዚአብሔር እንድትከታተሉ እናሳስባለን 🙏

👉በዚህ ቻናል የሚተላለፉ ትምህርቶች
1 እስመለዓለም
2 ስብከቶች
3 ምስባክ
4 ወረብ ነው ስለዚህ subscribe በማድረግ እንድትከታተሉ እናሳስባለን🙏

መልካም ምሽት 🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

05 Oct, 08:56


🌷...እንኳን ለፅጌ ፆም (ዘመነ - ፅጌ)....🌹
በሠላም አደረሰን/ አደረሳችሁ።

ፆመ ፅጌ

☞ ፆመ ፅጌ በየአመቱ መስከረም ፳፮ ተጀምሮ ህዳር  ፮ የሚጠናቀቅ ፆም ነው።

☞ ይህ ፆም የሚፆመውም ለ፵ቀናት ወይም ለ፩ወር ከ፲ቀን ነው።

☞ ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ፀገየ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው።

☞ ፅጌ ፆም የፈቃድ ፆም ስትሆን ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ይፆሟታል።

☞ ይህች ፆም የሚፆምባት ምክንያት እመቤታችን ስደቷን በማሰብ ነው።እመቤታች ጌታችንን ይዛ መሰደዷን መራቧን መጠማቷን በመሳብ ነው።

☞ ይህች ፆም ምንም እንኳን ከ፯ቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል ባትሆንም እንድፆማት በአዋጅ ባንታዘዝም በፈቃዳችን በመፆማችን ከፆሟ ረድኤት በረከት የምናገኝባት ነች።

🌹... ከመስከረም ፳፮ (26) ጀምሮ እስከ ሕዳር ፮ (6) ያሉት ሳምንታት ውብ ናቸው ምክንያቱም ማሕሌተ ጽጌ እና ጾመ ፅጌ (የፈቃድ ፆም )

☞እማምላክን ከነልጇ እንለምንበታለን ስደቷን እናስብበታለን

🌹... የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን ከ ሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን ...👏

ሰንበትን ከጌታ ከኢየሱስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ሌሊቱን በምስጋና በያሬዳዊ ዜማ ሳምንቱን ደግሞ በፈቃዳችን ማንም ሳያዘን የድንግል ማርያም ፍቅሯ አክብረን እንጾማለን።

🌹..ይህ ወር ( ጊዜ )አብዝተን የእመቤታችንን ፍቅር የምናይበት ጊዜ ነው


እንኳን ለዚህ ጊዜ አደረሰን አደረሳችሁ !!!
♥️የእመቤታችን ፍቅሯ ይብዛልን !!!

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

04 Oct, 01:05


#ተክለሃይማኖት_ሆይ፤ ከላይ ከሰማይ ለወረደው እግዚአብሔር አምላክ ስግደትን ላዘወተሩ
አብራኮችህ ሰላም እላለሁ።

#ቅዱስ_አባት_ሆይ፤ በኔ ላይ የተጫነውን ከባድ ሸክም አቅልልኝ፤ ከትእዛዞችህ አንዱን ስንኳ ጠብቀ ባልገኝም አንተ ግን እንደ አባትነትህ ይቅርታ አድርገህ ልጄ_ልጄ በለኝ።

#መልክአ_ተክለ_ሃይማኖት
      
           #ሰናይ__ቀን🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

30 Sep, 21:42


💜...እናታችን 🙏

#መስከረም ....21 ....🕯

👉ግሸን ደብረ ከርቤ ብዙኃን ማርያም  እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ናት እንኳን አደረሳችሁ።

የግሸኗ እናቴ የልቦናችንን ትሙላልን 🙏


#በፀሎት አስቡኝ ኃይለ/ማርያም 🙏

💜...#ማርያምን ..

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

29 Sep, 06:37


ደረሰልኝ ቀኑ ደሞ ላመስግነው የህይወት መሪ ስሙ ገብርኤል ነው።

፲፱ እንኳን አደረሳችሁ🌷

ወር በገባ በ...19...🕯
የራማው ልዑል መጋቢ ሐዲስ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ይሰውረን።🙏

🙏🙏🙏🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

27 Sep, 17:43


#ካሳለፍናቸው ከባድ ጊዜያት በላይ ያሳለፈን እግዚአብሄር ይበልጣል ።

እግዚአብሔርም መልካም
ነው
🙏🙏🙏

#በፀሎት አስቡኝ 🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

24 Sep, 18:24


ህይወት ብዙ ነገር ታስተምረናለች
መቻልን 🙏--ወድቆ መነሳትን 🙏 ---👉አገኝቶ ማጣትን ---👉አለቅሶ😭 መሳቅን🤣 ---👉ወዶ መለየትን🙏
ሁሉም ከባድ ነገር ሲጀመር የሚያቅተን የማንችለው የማይረሳ መስሎን ነበር.👇👇👇👇👇👇👇
ግን ቀስ በቀስ የተቀደደው ገፅ በአድስ ገፆች እየተተካ ያዘንበት ልባችንን የሰበረው ታሪክ በእርሳስ እንደተፃፈና በላጵስ እንደሚጠፋ ፅሁፍ ሙልጭ ብሎ ሲተን እናተዉላለን .

#አንድ ቀን ላይም የማንንም እጅ ሳንይዝ ደስተኛ እንሆናለን🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

23 Sep, 05:58


ስማኝ ልጄ!!!!!!!

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!!

    Pls share🙏

 

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

23 Sep, 05:58


🙏🙏🙏🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

21 Sep, 23:44


«መስከረም ...12...🕯

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ነው  በምልጃው  ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን።

በጭንቅ በመከራ ያለነውን ለሀገራችን ያብቃን ።አሜን🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

19 Sep, 13:26


በፈትህ አትጣለኝ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትዉሰድብኝ
መዝሙር 51:¹¹🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

16 Sep, 19:04


#ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።”
— መዝሙር 119፥103🙏

ተዘከረነ እግዝኦ በዉስተ መንግስትከ

15 Sep, 17:51


,በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን? መጽሐፈ ኢያሱ 1:9