በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ @bewketuseyoum19 Channel on Telegram

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

@bewketuseyoum19


➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡

@bewketuseyoum19
Creator - @abela1987 📨
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ (Amharic)

እንኳን ወደ 'በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ' ቻናል በመሰጠት እና መልክው በዚህ በረከት ውስጥ እንደሚታይ ይታዩ። ይህ ቻናላችን የአማርኛ አስተሳሰብ ጋር ያዩበትን እና ያስፈልጋል። ከሚያስፈልገንና ከበእውቀቱ ሥዩም ፈገግታም እውቀት የተሰጡበትን ወጎች፣ ግጥምች፣ እና የተለያዩ ፀሀፊዎች በበእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ ቻናል ይቀላቀሉ። አምናለሁ ከዚህ በቀላሉ በእውቀቱ ሥዩም ፈገግታም እውቀት እና የተለያዩ ፀሀፊዎች ላይ በተገኘበት ይመልስጋል።

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

15 Jan, 04:35


ሰው በመጋበዝ 0.6 TON ተቀበሉ

አሰራሩ በጣም ቀላል ነው
1 START ማለት
2 ቻናላቸውን join ማለት
3 task እና ሰው invite ማድረግ ከቻላቹ አሁኑኑ ጀምሩት ከ 2$ ጀምሮ withdraw ይቻላል

ፍጠኑ👇

https://t.me/kittyverse_ai_bot/play?startapp=u7211252999

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Jan, 17:43


ጠብቀኝ ብቻ ነበር ያለቺኝ ....

ተሸበርኩ ፣ ግርግር ፈጠርኩ ፣ ትንሽ ብቻ ጠብቀኝ ያለቺኝ አይመስልም ነበር።

ከመጠበቅ ጋር ጥሩ ትዝታ የለኝም .....!

ወንድሜ እቤት ጠብቀኝ እንዳትወጣ ብሎኝ ወደ ውጪ ወጣ የሆነ ነገር ይዞ ነበር መሰለኝ እቃ ለመቀበል ይመስለኛል ።

ቆየ ....

ጩኸት ስሰማ ወጣሁ ግርግር አለ ግርግሩን እየገላለጥኩ ሳይ ወንድሜ ነው ። ወግተውት እያጣጣረ ... ሲያቃስት ደረስኩ .....ሆስፒታል ሳይደርስ ሞተ

እጮኛዬ ትንሽ ግዜ ስጠኝ ብላኝ እየጠበኳት መሞሸሯን ሰማሁ "እንኳን ደስ አለሽ አልኳት" ምን ይሰማት ይሆን? ትስቅ ይሆን? አሳዝናት ይሆን? ትሸልል ይሆን? ፀፀት ይሰማት ይሆን? ብቻ ያመመኝ መጠበቄ ነበር ።

አጎቴ ሁለት አመት ጠብቀኝ እኔ ያለሁበት አገር እወስድሃለሁ ለመኖር ህልምህን ለማሳካት ምቹ ነው ብሎኝ በአንድ አመት ከአስር ወር በኋላ ጠፋ ...ድምፁን ሰምተን አናውቅም

ጠብቀኝ ስባል እፈራለሁ .....

መጠበቄን ለመርሳት እርምጃ እቆጥራለሁ፣ ኮሚቴ አዋቅራለሁ ፣ የድሮ ህንድ ፊልም አያለው ፣ ድሮ አስረኛ ክፍል ስለህልሙ የነገረኝን የክላሴን ልጅ እንዴት ሆንክ ለማለት ስልኩን አፈላልጋለሁ ...በዚህ ሁሉ መሃል እየጠበኩ እንደሆንኩ ልቤ አይዋሽልኝም ።

ቁስላችን አይሞትም ይቀበራል እንጂ ።
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Jan, 11:24


ሎሳንጀለስን ሞቅናት

━━━━━━✦✗✦━━━━━━

አጭር ትረካ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━

✒️ደራሲ - በእውቀቱ ስዩም


የሰአት ፍጆታ፦21:24ደቂቃ


━━━━━━✦✗✦━━━━━━
⇲⇲⇲⇲ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ!! ⇲⇲⇲⇲

@terkabecha

━━━━━━✦✗✦━━━━━━

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Jan, 12:05


ገብረ ክርስቶስ ደስታ
እኔ እወድሻለሁ /ገብረክርስቶስ ደስታ /

ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ።
እኔ እወድሻለሁ
የሰማይ መሬቱን
የባህር ስፋቱን
የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል
እንደ ፅጌ-ረዳ
እንደ አደይ አበባ
እንደ ሎሚ ሽታ፡፡
እንደ እጣን ጢስ እንጨት፣ እንደ ከርቤ ብርጉድ፣
እኔ እወድሻለሁ፣
አበባ እንዳየ ንብ፡፡
እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋር
አማርኛ አይበቃ፤
ወይ ጉድ!
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፣
እኔ እወድሻለሁ
እንደማታ ጀንበር።
እንደ ጨረቃ ጌጥ፣ እንደ ንጋት ኮከብ፣
እኔ እማልጠግብሽ
ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፡፡
ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነው።
ጣይ እንዳየ ቅቤ
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፣
አፈር መሬት ትቢያ ውሃ እንደሚበላው፣
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት
ውድ እወድሻለሁ፣
ዐይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ
እኔ እወድሻለሁ።

16/9/1960ዓ.ም የኢትዮጵያ ድምጽ ጋዜጣ
/ገብረክርስቶስ ደስታ/


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Jan, 10:02


ስብርባሪሽ ወጋኝ
ሁሌ እምጎመጅልሽ
ሁልጊዜ እማልምሽ
የንጉስ ብርሌ
የግርማዊ ከንፈር
ወትሮ የሚቀምስሽ
የምታረኪለት፤ የድለኛውን ጥም
እኔ ግን ምስኪኑ
ሲሳይሽ ባይደርሰኝ፤ ከእዳሽ አላመልጥም
ያንፀባረቅሽ ዕለት ግርማሽ ያላስጠጋኝ
ዛሬ ብትወድቂ፤ ስብርባሪሽ ወጋኝ!!

አ ዳ ም ኤ ል
በእውቀቱ ስዩም 2012

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Jan, 07:55


"የሰው ልጅ ሁልጊዜ እንባ ውስጥ እንደዋኘ ነው። ነገር ግን በየጊዜው ከዋናው ወጣ እያለ የሳቅን ፀሃይ እንደሚሞቅ ደግሞ አትርሳ።"

ዝም ብዬ አየሁት (ክንፈን) እውነቱን ነው።

"ሌላስ?" አልኩት

"እውነትን አታብዛ "

"ምን?"

"ህይወት ውስጥ እውነት ብቻውን አይገኝም። ህይወት እንደ ቡና በወተት ነው። ወተቱ እውነት ቡናው ውሸት ይሁን። ግን ይሄ ልዩነት በአንጎላችን ውስጥ ይኑር እንጂ ሲኒው ውስጥ በአንድ በኩል ቡና በሌላው ወተት የለም። ሲኒው ውስጥ ያለው ቡና በወተት ነው። ህይወትም ውስጥ በቀኝ በኩል እውነት በግራ በኩል ውሸት የለም። ህይወት ውስጥ የምታገኘው የእውነትና የውሸት ቅልቅል ነው።"

[ ጋሽ ስብሃት፦ ሌቱም አይነጋልኝ ]

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Jan, 15:21


'
'
በቁም እሳት ነው
የናፍቆትሽ አንታርቲካ፣
ሶማሊያ ላይ ተቀምጦ
ግብፅ ያለን የሚነካ ፣
'
'
😏
geez_mulat 🦘
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Jan, 11:38


በተባለው ሳይሆን

ከተናቀ ስፍራ ፥
ከተናቀ ሥራ ፥
ሰብኮን በተጠሩ ፥
ፊደል ባልቆጠሩ ፥
ጥሪት ባልቋጠሩ ፥
አንደበተ ርቱ ፥ ባልሆኑ ጠቢባን
በኮልታፋ ልሳን ፥ ክርስትና ገባን ።

ሳይሆን ሳለ ወጣት፥
በጉብዝናው ሰዓት ፥
እንዳይል ሀይሉ ፥ ጥበቡ የራሴ
በእርጅናው ወራት ፥ በደከመ ጊዜ
ነፃ ማውጣት ቻለ ፥ እስራኤልን ሙሴ።

ደፍሮ የሚፋለም ፥
ሲባል ማንም የለም ፥
አንድ ጀግና ጠፍቶ ፥ ከእስራኤል ሰራዊት ፥
ጣለው ጎልያድን ፥ የተናቀው ዳዊት።

ፈጣሪ

ብርቱ ነው በጉልበት ፥
ወይም አለው ሹመት ፥
በተባለው ሳይሆን ፥ ከሁሉ ይበልጣል
በደካማው ድካም ፥ ሀይሉን ይገልጣል ።


አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Jan, 21:44


ከነዚህ ዉስጥ የማን ደጋፊ ኖት?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Jan, 21:28


🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Jan, 17:07


━━━━━━✦✗✦━━━━━━

ብስጦሽ ቁዋጭ ቁዋጣሽ ቆር

━━━━━━✦✗✦━━━━━━

✏️ደራሲ:- ታገል ሰይፉ
ዘውግ፦ ልብወለድ
አመት :- 2012 ዓ.ም


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Jan, 10:57


ሎስአንጀለስን ሞቅናት!

(በእውቀቱ ስዩም)

ትናንትና ሎስአንጀለስ በእሳት ስትነድ፥ እኔ በአጋጣሚ ጓደኞቼን ለመሰናበት እዚያው ከተማ ውስጥ ነበርሁ፤ ሆሊውድ አካባቢ በእግሬ እየተንሸራሸርሁ ድንገት ቀና ብየ ሳይ፥ ከተማው እንደ ደመራ ይንቦገቦጋል፤ መጀመርያ ላይ ፥የዮዲት ጉዲትን ፊልም እየሰሩ ነበር የመሰለኝ፤ ብዙ ሳይቆይ የሳት አደጋ መኪና እየተብለጨለጨ ባጠገቤ አለፈ፤

ነገሩ “ሲርየስ” መሆኑን ያወቅሁት፥ የሆሊውድ አክተሮች ልጆቻቸውን እንኮኮ አዝለው፥ የቤት እቃቸውን ባንሶላ ጠቅልለው፥ ሲራወጡ ስመለከት ነው ፤ ደንብ አስከባሪ የሚያባርራቸውን የመገናኛ ቦንዳ ሻጮችን አስታወሱኝ፤ ቻክኖሪስ ባንድ የእሳት አደጋ ሰራተኛ ታዝሎ፥ ሳል እያጣደፈው ከቤቱ ሲወጣ አይቼ “እድሜ አተላ “ብየ ተከዝኩ::

እያወካ እየተጋፋ ከሚሸሸው ሰው መሀል ተቀላቅየ መሮጥ ጀመርሁ፤

ቀጣዩ ፌርማታ ላይ ትንፋሽ ለመሰብሰብ ቁጭ ባልሁበት፥ የሆነ ፖሊስ መጣና፤

“Are you ok?” አለኝ፤

“ እድሜ ልኬን ለፍቼ፥ እቁብ ጥየ ፥ ያፈራሁት ቤቴና ንብረቴ በእሳት ጋየ” ብየ መለስኩለት፤

“ስራህ ምንድነው ?”

መቸም በዚህ ሰአት ላይ ሊያጣራ አይችልም ብየ በማሰብ፥

“ ቀን የጣለኝ የሆሊውድ አክተር ነኝ “ አልሁት፤

“ምን ፊልም ላይ ሰርተሀል?”

”በማርቲን ሉተር ኪንግ የህይወት ታሪክ ዙርያ፥ በሚያጠነጥን ፊልም ውስጥ ከበድ ያለ ሚና ነበረኝ ” አልሁት፤

ፖሊሱ አልተፋታኝም፤

“ምን ሆነህ ነው የተወንከው?”

“ ማርቲን ሉተርኪንግ ፥ ሁለት መቶ ሺህ ህዝብ ሰብስቦ ንግግር የሚያደርግበት ትእይንት ትዝ ይለሀል?” አልኩት፤

“አዎ”

“ ከህዝቡ መሀል አንዱን ሆኜ ተውኛለሁ፤ ፊልሙ ጀምሮ አንድ ሰአት ከሶሰት ደቂቃ ከአምሳ ሁለት ሰከንድ ላይ ራሱን እሚነቀንቀው ሰውየ እኔ ነኝ “

ፖሊሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ወስዶ ከተፈናቃዮች ጋራ ቀላቀለኝ፤ የከተማው ከንቲባ ዘለግ ያለ ንግግር አደረጉ ፤” የተወደዳችሁ ተፈናቃዮች ሆይ ! የከተማው አስተዳደር ቤታችሁን መልሶ እስኪገነባ ድረስ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ውስጥ ልናቆያችሁ እንገደዳለን ”ብለው ንግግራቸውን አሳረጉ

በመጨረሻ” የአደጋና ስጋት መስርያ ቤት” ሊቀመንበር ወደኔ ቀርቦ፥

“ የደረሰብህን ኪሳራ እስክናጣራ ፥ይቺን ነገር ላንዳንድ ነገር ትሁንህ “ አለና አምሳ ሺህ ዶላር የያዘች ትንሽ ብጫ ፌስታል አስጨበጠኝ፤

ብዙም ሳልቆይ፥ፌስቡኬ ላይ የሚከተለውን ማሳሰቢያ ጣል አረግሁ፤

Bewketu Seyoum marked himself safe from poverty .

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

10 Jan, 09:35


ብዙዎች ለኑሮ በሚመርጧቸው፤
በከፍተኛ ፍጥነት እየለሙ እና እያደጉ በሚገኙት፤
መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ በተሟሉላቸው፤
የከተማችን ምቹ የመኖሪያ መንደሮች፦
🏠በሲ.ኤም.ሲ፣
🏠በመሪ እና
🏠በአያት አካባቢዎች
አፓርታማዎችን እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ
በኢትዮጵያ ብር ተዋውለው በመግዛት
የቤት ባለቤት ይሁኑ።
🙏100% ለሚከፍሉ 15% ቅናሽ
🙏 90% ለሚከፍሉ   10% ቅናሽ
🙏 75% ለሚከፍሉ   8% ቅናሽ
🙏 60% ለሚከፍሉ 5% ቅናሽ
አድርገናል

በካሬ 93,357 በኢትዮጵያ ብር



ለበለጠ መረጃ:
☎️ 0911468394
@abela1987

አያት ዞሮ መግቢያዬ!

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

10 Jan, 07:30


**
ሰው እንዲህ ነው አንዳንዴ
   እርስ በርሱ ተወዳጅቶ
      ክፉ ደጉን አብሮ ያልፋል፤

ውሎ ሲያድር ሲለማመድ
   መለያየት ገንዘብ ሆኖ
      ፍቅር እያለ ፀብ ያተርፋል።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

09 Jan, 09:44


ውሃ ሆኜ ሳለሁ ከአፈር ሳልነሳ
እውነቴን ነው ምልሽ
ደስ ይለኝ ነበረ ስምሽን ሳነሳ
ምኑንም ሳላውቀው
ገና ሳልፈጠር ምድርን ሳላውቃት
እወድሽ ነበረ ያለምንም ምክንያት
እወድሽ ነበረ
እወድሽ ነበረ
እወድሽ ነበረ
ዳሩ ምን ያድርጋል
እኔን አቆይቶ ቀድሞ አንቺን ፈጠረ።

ዮኒ
ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

09 Jan, 05:58


Zoo

Riddle of the Day:

Bowerbird


👇👇👇👇

🔗 LINK

ከአሁኑ ጀምሩ !

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

08 Jan, 08:21


ጠብቀኝ ብቻ ነበር ያለቺኝ ....

ተሸበርኩ ፣ ግርግር ፈጠርኩ ፣ ትንሽ ብቻ ጠብቀኝ ያለቺኝ አይመስልም ነበር።

ከመጠበቅ ጋር ጥሩ ትዝታ የለኝም .....!

ወንድሜ እቤት ጠብቀኝ እንዳትወጣ ብሎኝ ወደ ውጪ ወጣ የሆነ ነገር ይዞ ነበር መሰለኝ እቃ ለመቀበል ይመስለኛል ።

ቆየ ....

ጩኸት ስሰማ ወጣሁ ግርግር አለ ግርግሩን እየገላለጥኩ ሳይ ወንድሜ ነው ። ወግተውት እያጣጣረ ... ሲያቃስት ደረስኩ .....ሆስፒታል ሳይደርስ ሞተ

እጮኛዬ ትንሽ ግዜ ስጠኝ ብላኝ እየጠበኳት መሞሸሯን ሰማሁ "እንኳን ደስ አለሽ አልኳት" ምን ይሰማት ይሆን? ትስቅ ይሆን? አሳዝናት ይሆን? ትሸልል ይሆን? ፀፀት ይሰማት ይሆን? ብቻ ያመመኝ መጠበቄ ነበር ።

አጎቴ ሁለት አመት ጠብቀኝ እኔ ያለሁበት አገር እወስድሃለሁ ለመኖር ህልምህን ለማሳካት ምቹ ነው ብሎኝ በአንድ አመት ከአስር ወር በኋላ ጠፋ ...ድምፁን ሰምተን አናውቅም

ጠብቀኝ ስባል እፈራለሁ .....

መጠበቄን ለመርሳት እርምጃ እቆጥራለሁ፣ ኮሚቴ አዋቅራለሁ ፣ የድሮ ህንድ ፊልም አያለው ፣ ድሮ አስረኛ ክፍል ስለህልሙ የነገረኝን የክላሴን ልጅ እንዴት ሆንክ ለማለት ስልኩን አፈላልጋለሁ ...በዚህ ሁሉ መሃል እየጠበኩ እንደሆንኩ ልቤ አይዋሽልኝም ።

ቁስላችን አይሞትም ይቀበራል እንጂ ።
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Jan, 19:04


🔴PinEye በ January 27 በ Bybit Exchange List ይደረጋል።

verified Airdrop

Pineye እንደሌሎቹ የሚከብድ Airdrop አይደለም Task በመስራት የተሰጣቹን Point ወደ Profit per hour መቀየር ያሳደጋቹት profit per Hour የበለጠ Point ይሰጣቹዋል ደግሞ Daily Code አለው የምለቅላቹ ይሆናል ::

Bybit Kucoin እና የተለያዩ ትላልቅ Exchange ጋር ስምምነት አላቸው

መጀመር የምትፈልጉ
🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Jan, 11:38


አገር -በቀል
(በእውቀቱ ስዩም)

ከአራት ቀናት በፊት የመሬት መንቀጥቀጥ አገሬን ሲጎበኛት እኔ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ ሻንጣየን እየሸካከፍኩ ነበር፤ ድንገት የጨሰ የቢዘነስ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ - የድንኩዋን ሪልስቴት መገንባት!

የምድር መፈራገጥ በዚህ ከቀጠለ አዲሳባና ተጎራባች ከተሞች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ባለ ትልልቅ ፎቅ ህንጻዎች ላይ የመኖር ፍላጎታቸው ይቀንሳል፤ ሟርቴን አፌ ላይ እንደ ሰም ያቅልጠው እንጂ፥ በዚህ አያያዝ ፥ፎቆች መኖርያ መሆናቸው ቀርቶ መቀበርያ እንዳይሆኑ ያሰጋል፤ ስለዚህ ሰዎች፥ ቢደረመስ እንኳን ለክፉ በማይሰጥ የገለባ ጎጆ ውስጥ፥አለዝያም በድንኳን ውስጥ መኖርን መምረጣቸው አይቀርም፤

አባታችን አብርሀም ኣያሌ አመታት በድንኳን የኖረ ልዝብም ሆነ የከረረ ድሀ ስለነበረ አይደለም፤ በዘመኑ ኢለን መስክን የሚቦንስ ቱጃር ነበር፤ አብርሽ በዳስ ውስጥ የተጠለለው፥ ትልልቅ ህንጻ የመገንባት ጥበብ ስላልተገለጠለት አልነበረም፤ ለባቤል የተገለጠ ጥበብ ለአብርሀም እንዴት ይጋረድበታል? አብርሀም በድንኩዋን የኖረው ከምድሪቱ ባህርይ ስለገባው ነው፤

"አብርሀም ሪል ስቴት" የተባለ የድንኳን ሪልስቴት እገነባለሁ፤ ሕዝቤ ከከዋክብት ርቆ፥ ወደ ምድር ቀርቦ የሰላም እንቅልፍ ይተኛል! አለቀ!

ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የእንቅጥቅጡ ጉልበት እየጨመረ ሄደ፤ የቢዝነስ ሀሳቤን ትቼ በሕይወት ስለመቆየት ማሰብ ጀመርኩ፤

ትናንት ከበየነ ጋር ዲሲ ውስጥ እየተራመድን ስጋቴን አዋየሁት፤

“ ወደ አገሬ ለመመለስ ዘጠኝ ቀን ቀርቶኛል ፤ መሬት እያሸበሸበች እንዳትቀበለኝ እፈራለሁ “

“ነገሩ እስኪለይለት እዚህ ለምን ትንሽ አትቆይም፤ ትኬቱን ለወር አራዝመው” አለኝ፤

“ ይሻላል?” አልሁት ፥በምክሩ ውስጥ ውስጡን እየተደሰትኩ፤

“አስብበት “

እያሰብኩበት ብዙ አልተራመድኩም፤ ከጫማየ ስር ያለው የበረዶ ጥፍጥፍ ሲያዳልጠኝ ትዝ ይለኛል፤ የሆኑ ሰዎች ባቅራቢየው ካለ ፎቅ የወረወሩኝ እንጂ አዳልጦኝ የወደቅሁ አልመሰለኝም፤ አየር ላይ ትንሽ ውየ መሬት ላይ ሳርፍ ባካባቢው የቆመው፥ የማርቲን ሉተር ሀውልት ተነቃነቀ፤

በየነ እንደ ቆሰለ አርበኛ አፋፍሶ ካነሳኝ በሁዋላ፥

“ተረፍክ?”

“መንጋጋየ ከመነቃነቁ በስተቀር ደህና ነኝ”

“ ከዚህ እድሜህ በሁዋላ መንጋጋ ምን ይሰራልሀል? እንዲህ አይነት አደጋ ገጥሟቸው በሕይወት የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አይገኙም"

“ጎን አጥንቴ ላይ የስብራት ስሜት አለኝ” አልኩት እያቃሰትኩ፤

“ነጮች ሆስፒታል ብወስድህ፥ ሀኪሞች እግረመንገዳቸውን ሌላ በሽታ ሊያገኙብህ ይችላሉ፤ የማውቀው የቡርኪናፋሶ ወጌሻ አለ፤ እዚያ ልውሰድህ”

ወደ መኪናው አቅጣጫ እንደ ጀብ እያነከስኩ ትንሽ እንደተራመድሁ እንደገና ተንሸራተትሁ፤ በየነ እንደ በረኛ ቀለበኝና እንዲህ አለ፤

“ግዴለህም ወደ አገርህ በጊዜ ግባ! መሞትህ ካልቀረ አገር በቀል -ሞት ይሻልሀል”


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Jan, 03:15


እንኳን ለዓለም ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

መልካም በዓል

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Jan, 15:25


አምላክ ልጁን ላከ ፥ የማይጠልቅ ጀንበር
ድንግል እናት ሆነች ፥ የብርሃን መንበር ።

ከሰማየ ሰማይ ፥ መጣ በትህትና
አየነው ታቅፋው ፥ ትንሽ ብላቴና።

ያየፍዳ ዘመን ፥ ብርሃን ሆነ ለምለም
በክርስቶስ ልደት ፥ ፀሀይ ወጣ ለአለም።

አቤል ታደለ

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

"መልካም ገና"


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Jan, 13:23


ምንኛ....
ምንኛ ኃይል ኖረው
የአዳም እንባ ፀፀት
ከመንበርህ ስቦህ ያስተኛህ ከበረት፤
ምንኛ ቢያሰቃይህ ነው
የአዳም ፍቅር እና ናፍቆት
ቤተመንግስት እያለ የተወለድከው ከበረት?
ላንተስ አይገባም
ያ የከብቶች ማደሪያ፤
አንተ እኮ ቅዱስ ነክ
ዓለም ሳትፈጠር የነበርከው መጀመሪያ።
እንዴት ታድያ በረትን መረጥክ
ከሞላ ቤተመንግስት?
ዓለምን ትህትና ያስትማርከው እረኛ የፍቅር አባት፤
ባልችልም መመለስ ያንተን ውለታ
ማስታወስ አያቅተኝም ልደትህን
ሁሌም ታህሳስ 29 የኔ ጌታ።

መልካም ገና ለሁላቹም።

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Jan, 09:21


ፀጉሯን ታጥብቀው

'
'
ፊት ለፊቴ ተቀምጣለች
ድግስ አላት ትጠጣለች
ይመስለኛል ሰክራለች

ወይም ሰክሬለሁ
ጠጣለች መሰለኝ
ወይም ጠጥቻለሁ

ታየኛለች በድግግም
ታፈጣለች በሰከንዱ
ይጨንቀኛል እንደ ምንም
አይጨንቀኝም እንደ ወንዱ

ጨፈረች እንደልቧ
ትጮኻለች እንደ ዓለም
እሷን ማወቅ
ለእኔ ቀርቶ
ላለም ሰውም ብርቅ አደለም

መስላኝ ነበር ስገጣጠም
መስሎኝ ነበር የፈለገች
መስሎኝ ቀረ እንደተራ
ወንድነቴን እንደናቀች

ተጨንቄም ተዋወኳት
እንደምንም ክብሬን ጥዬ
ስሟን ነግራኝ ስሜን ረሳው
አላጣት ምንም ብዬ

ብዬ ብዬ ብዬ....

በመሃል በጭፈራው
በሰቆጣ ዘፈን
ስትዘፍን ሳያት ፣
ድንገት ተቀየረች
የለበሰችው ፀጉር
ወልቆ ጉድ አረጋት

😏

geez_mulat 🦘

ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Jan, 06:24


ሰው ከክብሩ ሲወርድ ፥ ፈጣሪውን ሲተው
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ፥ ሰው መሆን ሲያቅተው

የሰው ልጅ እንደ ሰው ፥
እንዴት እንደ ሚሆን ፥ ሆኖ ስላላየው
ሰው ሆነ ፈጣሪ ፥ ሰው መሆን ሊያሳየው።

አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Jan, 13:12


ብልጭ 
'
'
ስንቱን ነገር ነውር ልበል
ስንቱን ነገር  ላስተምርሽ
ስንቱን ስንቱን ማለቴ እንኳ
ስንቴ እንደሆን በነገርኩሽ

ተመከሪ ኧረ ስሚኝ
ጨንቆኛል ያንቺ ነገር፣
ትልቅ ነበርሽ አትበሳጭ
ክብረቢስ ነሽ እንደ ሀገር ፣

አትቅለይ ባደባባይ
መጋረጃ ቀሚስ ለብሰሽ
ቆርቆሮ ነው ወርቅ አደለም
አንገትሽ ጋ ስትዳበሽ ፣

ይጋለጣል እንደ ቡዳ
በእሳት ዘመን ውሃ ሰጦሽ፣
በደረቀ እሾህ ሄደሽ
ራት አልሽኝ ያንቺን ግጦሽ ፣

አታዋርጅኝ እባክሽ
ክብር አለኝ ለመሬቱ፣
አትዝለይ ይጋለጣል
ካለ ዘፈን ሲሆን ምቱ፣

እኔ ብሆን አልዳኝሽም
እኔ ብሆን አልተውሽም
የትም ሄደሽ አትቅለይ
አታምሪም ማሪያምን
አምነሽ ተ ቀ በ ይ ፣

መስሎሽ ከሆን እንደቅናት
ያንቺን ብልጭ የማልወደው
ያንቺን ማማር ማልፈልገው፣
ውበትሽ ጋ እንድራመድ
መርጋት ነበር 'ሚያስፈልገው ፣

ስንቴ ልምከር ያንቺን ጉዳይ
ነፍጥ ብል ጫካ ካለም፣
ሁሉን ቦታ አዳርሰሻል
ያንቺ እውነት ካለም' የለም ፣

አረጀሁኝ እንደዘበት
አትሰሚኝም እዛው አለሽ ፣
ይሄ ልቤ ይሆን እንዴ
ያንቺን እድሜ የተዋሰሽ ፣
'
'
ግዕዝ ሙላት 🦘

@geez_mulat

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Jan, 08:13


ዘምሪ

ከንፈርሽ ሲላቀቅ ግጥሙን ሊያዜመው
ሊቀፅል ሲነሳ ፍክት ሊያደርገው
ዜማን ሊሞሽራት ሲኩላት ሲያስጌጣት
የድምፅሽን ብርሃን አልብሶ ሲያስውባት
      
         እኔ እጨነቃለሁ
ድምፅሽ ሴጣን ይመስል ደርሶ እለከፋለሁ
  
.......አንቺ ስትዘምሪ......
ዛር በውስጡ እያለ ጠበል እንደገባ
የማወራው ቆቦ ስሜቴ አራምባ
  
   ዘምሪ አንቺ ብቻ
  ቀፅይ አንቺ ብቻ
  ተቀኚ ያለ አቻ


የዳዊት በገና ድምፅሽ ላይ ተገኘ
የዕዝራ መሰንቆ በለዛሽ ተቀኘ
      
ምነው ባደረገኝ ጥርስ ወይ ከንፈርሽን
ድምፅሽ በኔ ሲያልፍ እንዳያት ገነትን

      የምሬን ነው ምልሽ
ዘፈን ሀጢአት ሳለ ባንቺ ከከበረ
ማረኝ አምላኬ እያልኩ እሰማሽ ነበረ

         እባክሽ🥺
ድንገት እንኳ አንዴ
      ቢቻል ድምፅ'ን መሳም
ከከንፈርሽ ሲደርስ
       እኔም አንዴ ልሳም።


        @henila31

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

04 Jan, 21:36


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

04 Jan, 21:18


🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

04 Jan, 08:13


ጠንካራ መስያት ነው ። የምታየው ብቻ መስያት ነው ። ለሷ ያለኝ ቦታ ያሳየኋት እና የነገርኳት ብቻ መስሏት ነው።

ሌላም ሰው እኔ ያልኳትን ብሏት ዋሽቷት ስላገኘችው፤ ቃልም፣ ተግባርም  ማመን አቁማ ነው ።

ስታገኘኝ 'Dead inside' የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት  መልበሴን አላስታወሰችውም ።ሳቄ የቲሸርቴን መልዕክት ከልሎት ነበር ።

የማያቁኝ፣  ያልሰሙኝ  የሰጡአት አስተያየት ልቧን ተጭኖት ነው ። የተሰበረ ሁሉ የሚጠገን መስሏት ነው ። ጊዜ ሁሌ አዳኝ መስሏት ነው ። 

ከልጅነቴ ጀምሮ የሚራራልኝ አልነበረም!!

ልጅ እያለሁ:-

አባቴ ይወደኝ ነበር ። አንድ ነገር ሳይዝልኝ ቤት አይገባም ፣ ሳያጫውተኝ አይተኛም። መንገድ ስንሄድ እሽኮኮ ያደርገኝ ነበር ። ላገኘው ሁሉ "ልጄ ነው"  ይል ነበር።  ዘና ያለ ነው ፣ ሙዚቃ  ይወዳል፣ ተጫዋችም፣ ዝምተኛም ፣ ሳቂታም፣  ኮስታራም  ነበር ።

ከእናቴ ጋር  ብዙ ግዜ ቢጨቃጨቁም ፤ ሁለቱም  ይወዱኝ ነበር ። ፍቅር አሰጣጣቸው ለየቅል ነው ። ሰው ለሚወደው  የሚሰጠው የሚችለውን ሁሉ ነው ።

የሆነ ቀን ፀባቸው ከሮ ፍርድቤት ቆሙ ። ይዘውኝ ሄዱ።  የሚያወሩት ስለ መለያየት፣ ስለተቆራጭ ምናምን ነበር።

አይን አይኔን እያየ "አላምናትም፤ ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም" አለ ። አላመንኩም : ውሸቴን ነው ይላል ብዬ ጠበኩት ህይወት እንደዚ አይነት ቀልድ እንደማታውቅ አላቅም ነበር ።

ልጄ አይደለም ካለኝ በኋላ የተወራውን መስማት አልተቻለኝም ።

"ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም " ያለው   ፊቱ ፣ ሁኔታው ድምፁ ፤ እርግጠኝነቱ ከልቤ አልጠፋ አለ።
እናቴ  እጄን ይዛ ወደ ቤት ተመለስን ።

አደባባይ ላይ "ልጄ አይደለም" ያለኝ ከሰጠኝ ፍቅር ሁላ ስለበለጠብኝ ውስጤ ደነገጠብኝ ።
   
የሚታይ ነው የሚሰማ መታመን ያለበት ??

ለምን ይዘውኝ ሄዱ ? ፣ እማኝ ባለበት ስካድ ማየት እኔን ከማበላሸት ውጪ ምን ይጠቅማል ?? ያን ቀን አባት አልባ ሆኜ ተመለስኩ ።

ዘግኖ ባዶ ማግኘት ህይወት ውስጥ አዲስ አይደለም !!
       © Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Jan, 18:03


ስንት ሰዎች አሉ!

ህይወት ስታጓጓን ..
ደንገት ሞት እንዳለ እየተዘናጋን
ጊዜ ነፍገናቸው ..
ንፁህ ፍቅራችንን ፍፁም ያልታደሉ
ስንት ሰዎች አሉ።
ቆርጦ የመጣ ቀን ማለፋችን ላይቀር
ምንድነው ጥላቻ ሁሌም እንፋቀር።

✍️ዘሪሁን ከ አሰላ
ታህሳስ 24/2017

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Jan, 12:57


🗞 በ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Jan, 12:51


የ highschool ትምህርት ጊዜ ትዉስታ አለቦት ታድያ ምን ይጠብቃሉ ተቀላቀሉን እና ዘና ይበሉ 👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Jan, 08:40


Telegram Premium እና Telegram Stars የምትፈልጉ ካላችሁ @yoni1639 አናግሩን።

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

02 Jan, 17:00


ለካ
.
እንባ ቢያስመስል ፈሪ
ደፋርነው ባሉት ይብሳል፣
ካገኜ አቅፎ 'ሚያባብል
ጀግናም ከልቡ ያለቅሳል።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

02 Jan, 06:27


የማርያም ትህትና

በቅድስናዬ፤
በድንግልናዬ፤
መች አለች መረጠኝ ፥ ንጽሕናዬን ዓይቶ
የባርያውን ውርደት ፥ እንጂ ተመልክቶ።

የዘላለም ንጉስ
እውነተኛ ፀሐይ ፥ ክርስቶስን ይዛ
የጨረቃን እናት ፥ አየቻት ተጉዛ
ብትመሰገንም ፥ ቢጨምርም ክብሯ
ድንግል አትታበይ ፥ እንደ ሰው አትኮራ
ድምጿም አይሰማ ፥ እዩኝ እዪኝ አትል
ያደገችው መቅደስ ፥ ሀር ስትፈትል
እንደ ልጅ ቦርቃ ፥ መች ታውቃለች ድንግል።

ለልጇ ሲዘመር ፥ ሲባል ሆሳዕና
ልመስገን ልወደስ ፥ እናቱ ነኝና
ነቅላቹ አምጡልኝ ፥ የዛፎቹን ላባ
መች ይነጠፍልኝ ፥ ብላለች ዘንባባ።
በምን ቋንቋ ብንፅፍ ፥ በምን መዝገበ ቃል
የሷን ትህትና ፥ ለመግለጽ ይበቃል ።

እንደሷም ከፍጡር
እንደሷም በዓለም
ከሁሉ ከፍ ያለ ፥ ፃድቅ እንደሌለም
እንደሷም ከፍጡር
እንደሷም በዓለም
ራሱን ዝቅ ያረገ ፥ ትሑት ማንም የለም።

አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Jan, 21:42


ፍቅረኛ አሎት?😍🤷‍♂

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Jan, 21:23


እድሜዎ ስንት ነው ?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Jan, 08:33


የኔና ያንቺ ህይወት
━━━━━━━✦✦━━━━━━━

ውዴ የኔ ፍቅር የኔ ሁለንተና
የልቤ ተሟጋች አርበኛ ሳተና
ፍቅር ብቻ ሳትሆኝ አንቺኮ እናት ነሽ
ከመውደድም በላይ ፍቅር የሞላብሽ

የኔ ሠላማዊ
የኔ ሁለንተና
የኔ ልዪ'ኮ ነሽ
የኔ......የኔ
የኔ......የኔ

በሚል ተራ ቃላት ሁሉም በሚገልፀው
የኔና ያንቺ ህይወት ደራሲም አይፅፈው
ገጣሚም አይገጥመው ሰዐሊም አይደፍረው

የኔና ያንቺ ህይወት...
ከመዋደድ በላይ ከመፋቀር በላይ
በፀብ የተሞላች ደስ የምትል ስቃይ

መጣላት መታረቅ
መታረቅ መጣላት
ደሞ ትንሽ ኩርፍ
ደሞ መዘጋጋት...
አሁንም መታረቅ
አሁንም መጣላት
ደሞ ሌላ ማኩረፍ
ሌላ መዘጋጋት....

እውነት እውነት ስልሽ...
የኔና ያንቺ ህይወት ሙሉ ፊልም ቢሆን
ከዚ ትእይንት ውጪ ሌላ ምንም አይኖር።

                        ✍️-ዳዊት(የለትዬ ልጅ)
                            

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

31 Dec, 11:27


BUMS Daily Combo

ወደ CITY የሚለው ቦታ ትገባላችሁ ከዛም LOTTERY ውስጥ ትገቡና ምስሉ ላይ ታሉትን combo መርጣችሁ check ማለት ነው።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

31 Dec, 07:45


ብታውቂ ነይ ከእኔ...
ባታውቂ ነይ ወደ እኔ...
             (ርዕሱ ነው)


ከውቢት ከተማ አንዲት ሴት ነበረች፣
ሁሉ የሚመኛት በግብር ያማረች፤
                    አንዲት ሴት ነበረች።

ከሴቶቹ መሃል ትመስላለች ንግሥት፣
ብቻዋን ስትገኝ ታስንቃለች እንስት።

ውዴ! ከእግዜሬ በታች የዓሳ ሕይወት ያለው፣
በሠማዩ ሥሪት፣ በምድር በሰፋው በሚታየው ማይ ነው።
ታድያ የእኔ ልብ ያለው አንቺ ጋር ነውና፣
ወይ ነይልኝ ወይ ና በይኝ እወድሻለሁና።

አውቃለሁ! ዓይን ዓይንሽ እያየሁ ፍቅሬን አልገለጥኩም፣
አውቃለሁ! እሞትልሻለሁ ብዬ አልተናገርኩም፣
ታውቂያለሽ? ኃይል ማጣቴና እንደሆንኩኝ ድኩም?

አላምንህም ብለሽ ብትዞሪ ዓለም፣
እመኚኝ! ከአፍቃሪሽ በላይ ላ'ንቺ 'ሚሆን የለም።
ብታውቂ ነይ ከእኔ ጋር ድመቂ፣
ባታውቂም ነይ ወደ'ኔ ከጎኔ አትራቂ።
ላገኝሽ እተጋለሁ...፣
ደግሞ እንዳትርቂኝ እሰጋለሁ።

አሰብኩትና ለአንቺ መንበርከኬን ... ፈራሁት አምላኬን
አትታዘበኝ ጌታዬ ... አንተም ታ'ቃለህ ከፍቅር ለፍቅር መላኬን።
በእርግጥ አንተ ለእኔ ምላሽ አለህ፣
አንተ ራሱ አፍቃሪ አይደለህ?

አስታውሽ? ሳጥናኤል በምኞት መውደቁ፣
ከንቱነት ለእሱ ማሳበቁ፣
    እናማ...
የእኔም ምኞት አውጥቶ ቢጥለኝ፣
የአንቺ እሺታ እንጅ ሌላ መጽናኛ የለኝ።
ግዴለም ሐሳብሽ ሐሳቤ ይሁን፣
ልዕልት ላግባና እኔም ንጉሥ ልሁን።
አትፍሪኝ፣ ቅረቢኝ...
ዓይንሽን ግለጭ፣ አንብቢኝ።
የፍቅረኛሞች ሰፈር ውሰጂኝ፣ አድርሺኝ፤
ጠይቂኝ ልቤን ልስጥሽ ከዚያም አድሺኝ።

ይኸውልሽ ሃ!   የእኔ ስኬት...
አንቺን ማኖር ነው ወሰን በሌለው ልኬት!
           ●| HT |●

መንገደኛው (
@MekuriyaM )
            The traveler

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Dec, 12:15


━━━━━━✦✗✦━━━━━━

አልፀፀትም

━━━━━━✦✗✦━━━━━━

✏️ደራሲ:- ጀዋር መሀመድ

✍️✍️✍️✍️✦✗✦✍️✍️✍️✍️
✈️ ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ!! ✈️

@booklibrarychannel

✍️✍️✍️✍️✦✗✦✍️✍️✍️✍️

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Dec, 09:17


"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር ጋር ጥሩ ታሪክ የለኝም" አልኳት ።

አላመነችኝም ... ለማሳመን አልጣርኩም።
"ምራኝ እሺ " አለችኝ "ሲከተሉኝ እፈራለሁ ቀድሞ ግራ ይሂድ ቀኝ ይሂድ ሳሰላስል እደናበራለሁ" አልኳት ።
ትህትና መሰላት ።

"መንገድ የጠፋበት ሰው ቢመራ የት ያደርሳል?" አልኳት
"አለማወቅ ምቾት አለው" አለችኝ።
"አለማወቅን ካላወቅን ነው ምቾት ያለው" አልኳት።

"እንደምትወደኝ ንገረኝ" አለችኝ።

"እወድሻለሁ"
"እሺ ምከረኝ" አለችኝ ።
ድንገት ጭንቅላቴ ላይ ከመምከር ጋር ያለኝ ታሪክ መጣብኝ...

ጓደኛዬ ነበረች ፤ ሃዘን ገጠማት የምትወደው ሰው፣ አንድ ያላት ሰው ሞተባት። መሰበሯ ሲጠነክር መከርኳት።
"ሃኪም ነኝ፤ የሞተ ሰው በየቀኑ አያለሁ ፣ ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች፣ መኖር ሰፈልጉ የነበሩ ሰዎች፣ መዳን ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች ሲሞቱ አያለው።

ሲሞቱ ትክ ብዬ አያቸዋለሁ፣ ህመማቸው ነው የሚቋጨው ፣ ትግላቸው ነው የሚቀርላቸው ፣ መሞት ለሟቹ እረፍት ነው የሚመስለኝ" ብዬ ገጠመኜን እያጣቀስኩ ነገርኳት .....
በሳምንቱ ሞተች እራሷን ገድላ።

ለማኖር ነበር የመከርኳት ፤ አይኗን በልቅጣ ቀልቧን ሰጥታኝ ስትሰማኝ ሞት እረፍት ነው ብላ እንድትጠነክር ነበር ። ግን መኖርን ነበር የቀማኋት መሰለኝ.......

የቱ አፋፍ ላይ ቆማ ሰምታኝ ይሆን ?
'ለምንናገረው ይሁን እንዴት ሰምተውን ለሚተረጉሙት ትርጓሜ ኋላፊነት መውሰድ ይቻለናል ?' አያልኩ መብከንከን ፀፀትም ተከተለኝ።

በሃሳብ ጭልጥ ስል አይታ "አትመክረኝም?" አለች ።
ፈገግ አልኩ ...

ይልቅ እንጠጣ እስኪ።
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Dec, 07:41


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

29 Dec, 17:32


Zoo

Rebus of the Day:
Tapir
Riddle of the Day:
Parrot

👇👇👇👇

🔗 LINK

ከአሁኑ ጀምሩ !

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

29 Dec, 08:10


መንገድ ጠፍቶን ስንደናበር ላረጋጉን ፣ ወደቅን ስንላቸው ላልፈረዱብን ። በድለናቸው ይቅርታን ለሰጡን ፦

ሚስጥራቸውን ላጋሩን፣ ደስታችን ለተካፈሉ፣ ሃዘናችንን ቦታ ለሰጡት ፣ ለተጠነቀቁልን ፣አጋርነታቸው ወረት ለሌለበት ፣ በቆሚነት የኛ ለሆኑ ።

እንድናምናቸው ለሆኑ ፣ ደግነታቸው ለማይስተን ፣ ለሚወዱን ፣ ሊረዱን ግማሽ መንገድ ለሚመጡ ፣ ለሚያበረቱን

ችርስ ለነሱ 🙏

ኑሩልን

©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Dec, 12:29


ናፍቆት
ወርሃ ጥቅምት ደረሰ
ታቦት የሆነው አምላካችን ናፍቆትም ነገሰ።
የትዝታ ደቀመዝሙር ከደብሩም ተገኘ
ለአምላካችን ናፍቆት ቅኔን ተቀኘ
እንዲህ ሲል ተቀኘ፤
መኑ ምስልከ ናፍቆት አምላክነ
ይህቺን ቀን ለማየት ስንቱ ተስሎ ለመነ፤
በዓለም ዙሪያ ላላቹት አፍቃሪያን በሙሉ
እንኳን አደረሳችሁ ለናፍቆት አምላክ ክብረ በዓሉ
ታድያ ለምን ዝም ትላላቹ ዘምሩ እልል በሉ።
አትመጭም ወይ ታድያ ውዴ ከናፍቆት በዓል ከንግሱ
ወይስ አላወቅሽም እንደ ሆነ ናፍቆት የፍቅር ንጉሱ?
ወይስ አልተጠራሽም ከናፍቆት ድግሱ?
ወርሃ ጥቅምት ደረሰ፥ እጽዋት ሲሆኑ ቢጫ
እንደምንገናኝ ሳስብ ናፍቆትን አስቤ
ያኔ ይሆናል ልቤ በጭባጫ።
ለምንድነው ማትመጪው?
መንገድ ነው የጠፋሽ?
ወይስ መምጣቱ ነው ያስጠላሽ?
ወይስ ቀኑ ነው የተረሳሽ?
ናፍቆት አምላካችን በሳቃችን ያውጣ የደስታን ሲቃ
አንገናኝም ወይ መባባላችንም እዚሁ ጋር ይብቃ
የተገናኘን 'ለት ትወጣለች ጨረቃ።
እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር መነፅር
የሚያቃጥል ስሜት ከቆዳችን ስር እስኪጫር
እንጫወት እናውጋ
ፍቅራችን እንዲፀና በአንድነት እንትጋ።
ወርሃ ጥቅምት መጣ ፥ እሸት ደርሶ ነበረ
አምላካችን ናፍቆት ከደብር ደበረ
ያገናኘን አምላክ እሱም ከበረ።
✍️ ሚራዥ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Dec, 10:10


ዝምታ
የኔ ቢራቢሮ የዋህ ቅድስት
ላልቀየምሽ በልቤ የሾምኩሽ እንስት፤
ብዙ ከማያወሩ ፤ከሚቆጠቡ
ከመንገራቸው በፊት አጥብቀው ከሚያስቡ
ከሆኑ ነገዶች፤ ከሆኑ ነገዳት
አንዷ ያፈቀርኳት ልጅ ናት፤
የምትኖሪ ከዝምታ ዛፍ ስር
የተሾምሽው ከአርምሞ አድባር
አንቺ ነሽ ውዴ፤አንቺ ነሽ የኔ ማር።
ውብ....
መልክሽ በማንም ያልታየ
ቅድስት....
ስራሽ በማንም ያልተጠና፥በማንም ያልተለየ
ረጅም....
ቁምትሽ በማንም የማይታወቅ
አዎ...አንቺ ነሽ የልቤ እንቁ፤ዝምታዬ ወርቅ።
ጆሮዎቼ እንዲሰሙ
ሲፈጥራቸው ካደረገ ጥንድ፥
አንደበቴ ዝም እንዲል
መጓዝ አያቅተኝም በአርምሞ መንገድ።
ሲመታን የማውራት ምች
መድኃኒት ናት አርምሞ
ልክ እንደ ደማከሴ ቅጠል፤
ስራዋ ብዙ ነው እንደ ከዋክብቱ ልበል፤
እንጂማ
እሷን የሚገልፅ የለኝም ሌላ ቃል።
ከሆነ እስቲ ምናልባት ይኸኛው
አድምጡት ልበለው፥
እንደ ጨረቃ ብሩህ
እንደ ፀሐይ ደማቅ
ዝምታ ብቻናት ውድ እንደ ወርቅ፤
የኔ ቢራቢሮ ከዓለም የመነነች
በልቤ መሃል ላይ ነግሳ የተሾመች
የኔ ዘመን ወርቅ ዝምታ ብቻነች።
የኔ ቢራቢሮ የዋህ ፃዲቅ
አርምሞ፥ዝምታ ናት ወርቅ።

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Dec, 04:51


ገብርኤል
.
ስያሜው

የስያሜው ትርጉም ፥ ሰው የሆነ አምላክ
የፈጣሪን ክብር ፥ የሚያሳይ መልአክ ።
.
አፅናኙ

በሰማይ መላእክት ፥ ተጨንቀው እያለ
ባለንበት ፀንተን ፥ እንቁም ብሎ ያለ።
.
ሰባኪው

የልጁን መወለድ ፥ መቶ ያበሰረን
ኢየሱስም ብሎ ፥ ስሙን የነገረን።
የራማው ሀላቃ ፥ የወንጌል አርበኛ
መጋቢ ሀዲሱ ፥ የእግዜር ምስጢረኛ ።
.
ሀያሉ

ለሰልስቱ ደቂቅ ፥ እሳቱን ያረጋ
ለሚጠራጠረው ፥ ክብሩን ለዘነጋ
እንደ ዘካርያስ ፥ ልሳን የሚዘጋ ።
.
ተራዳዩ

ከመከራም መሀል
ለህፃኑ ቂርቆስ ፥ ለእናቱ ኢየሉጣ
ፈጥኖ እንደደረሰ ፥ ከእሳት እንዳወጣ
ከአናብስትም ጉድጓድ፤
ደርሶ እንዳዳነው ፥ ነብዩን ዳንኤል 
ለኛም አይዘገይም ፥ ስንጠራው ገብርኤል።

አቤል ታደለ


እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክበረ በዓል በሰላም አደረሳቹ

"የመልአኩ ምልጃ አይለየን
"

ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Dec, 21:08


Propose 💍...

ዛሬ አንድን ነገረ በቅንንት እንድታስረዱኝ እፈልጋለሁ(360° ተዟዙሬ ነገሩን ልረዳ ብሞክርም ምንም ሊበራልኝ አልቻለም)...እናላቹ በየሜዳውና በየአደባባዩ ሞልቶ የእንስቶችን ልብ ሰቅዞ ያየዘውና ተደረገ ሲባልም እንደ ትልቅ ትንግርት እጅን በአፍ የሚያስጭነው propose የሚሉት ጉድ ምንድነው ዘመዴ? እንዴትስ ነው ተውጦላቹ ዝም ያላቹት? በመሰረቱ ይህች ታሳሪዋ💍 ልጅ ዋጋ ከፍሎ ያሳደጋት ቤተሰብ አላት፤እሱ  ማን ስለሆነ ነው የሆነ ካፌ ቀጥሮ ስርፕራይዝ በሚል ተልካሻ ምክንያት ቀለበት የሚያደርግላት? ማን ነህ ወንድም እስቲ መጀመርያ ለሚቸኩለው ልብ ልጓም አበጅለት!እንዴ ነውር እኮ ነው የቤተሰብ ይሁኝታን ያላገኘ ህበረት የጓደኛ አጀብታና ጓጓታን ብቻ ተማምኖ መግባት ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው?አንዳንዴ ስልጣኔ መስሎን የምንቀዳውን ነገር እንለይ እንጂ ጎበዝ! ክብርም ለሚገባው አካል ክብር እንስጥ። ሌላው ቢቀር ይህች ልጅ(እሱም ቢሆን) እንዲህ አይነት ከባድ የህይወት ውሳኔ ሲወስኑ ቤተሰብ ማወቅ የለበትም ወይ? እንደማንኛውም ባዳ የልጃቸውን ጉዳይ ከማህበራዊ ሚዲያ ማወቅ አለባቸው? እኔ አይመስለኝም!!!

ይሄ ሲገርም ደግሞ የእምነት ተቋማትን ያላከተተ ድርጊት መሆኑ አጃይብ ነው!፤ ወንዱ ቆሞ ይጠብቃታል እሷን ጓደኞቿ ይዘዋት ይመጣሉ(አታውቅም አሉ እንግዲህ🙄) ካዛን ስርፕራይዝ ብሎ ተንበርክኮ(ወንድ ልጅ መንበርከክ አለበት ብዬ አላምንም!!አለማመን ደግሞ መብቴ ነው😏) ቀለበት ያወጣል ከዛ እጇን መስጠት ትታ ትነፋረቃለች(ሲያበሳጩኝ) ከዛን እጇን መንጥቆ ያጠልቅለታል በቃ! የተጠና ስክሪፕት ይመስል ሁሉም የሚያደርጉት ተመሳሳይ ነገር ነው።ቤተክርስቲያን አታውቅም የለችበትምም፤ኧረ ተው ግን ልብ እንግዛ ተውው🧐

እነዚህ ሰዎች "ስለ ሪሌሽንሽፓችን ሰው እንዲያውቅ ነው ቀለበት ምናደርገው" ይላሉ ሰው አንደኛቸውን ዝግጅት ጨርሰው ሲጋቡ ማወቅ አይችልም? እኔ እንደውም ይሄ ነገር ከቀለበቱ በኃላ ልጅቷን እንደ ገዛ ሚስቱ ቆጥሮ(ሳያገባት) ከትዳር በፊት በዝሙት ለመውደቅ መንገድን ይከፍታል ባይ ነኝ።እስቲ በዚህ ጉዳይ ያላቹን ምልከታ አጋሩኝ🤲 ተወዛገብኩባቹ እኮ በናታቹ😔

ጌታዬ በሰላም አውለኝ🏃‍♀


በእምነት አሸናፊ
   ጎንደር (17/4/17 )

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Dec, 17:54


Zoo

Rebus of the Day: gorilla

Riddle of the Day: kangaroo

👇👇👇👇

🔗 LINK

ከአሁኑ ጀምሩ !

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Dec, 12:44


'
'
እፍ እፍ አጥፉት ሳቱን
ሊያቃጥለን ከደጅ ደርሷል፣
አፈር አምጡ ወይም ቅጠል
ውሃ ያልነው ሰደድ ሆኗል ፣

እባካችሁ አትጩኹ
ፀጥታ ነው የሚያጠፋው፣
ድብልቅልቅ መሆኑ ነው
ጩኸታችን የሚያስንቀው፣

( አንቺ ሴት )

እሪ አትበይ ከጥግ ከጥግ
አትለውጭም ምንም ለእሳት ፣
አንድያውን ካገር መጥፋት
ወይም አፈር ቅጠል ማንሳት ፣

አትቅለስለስ ጎረቤቴ
አትደበቅ ካልሆነ ፍም ፣
ቀን ይፈጅ ይሆን እንጅ
ይሄ እሳት ካንተ አያልፍም ፣

(አንተ )
'
አልጋ ስር አትደበቅ
እንዳልሰማ ጩኸታችን ፣
እሳትህ ነው አይባልም
እኔ ስልህ እሳታችን ፣

የችግኝ ዛፍ ቁረጭልኝ
ባገር በዝቷል ቅጠል ችግኝ ፣
እሳቱ ጋር አለሁበት
ከለምለም ጋር አትፈልጊኝ ፣

ባንድ ሰፈር ጎጆ ሰርተን
የኔ ደጅ ላይ ቢቃጠልም ፣
እሳት ሲባል ተጓዥ እንጂ
በተናጥል አያቃጥልም ፣

የከመርኩት የጤፍ ቦታ
ቀድሞ ከእኔ ቢያስርበኝም፣
ጎረቤቴ ዝም እንዳለው
ራህብ እንኳ አልጎዳኝም፣

አይደርስ መስሎት ሰደድ እሳት
እንደለኮስኩ ለሰው አማኝ ፣
ቢነደኝ ነው የእሳት እሳት
ሳያወድመኝ የሚያጣቃኝ ፣

እፍ በይወሰ ይሄን እሳት
እፍ በለው ተባበረኝ፣
ዘንቦ እስኪቆም የእግዜር እንባ
የውሃ አምላክ እስኪፈርደኝ ፣
..............ለዚህ እሳት ዕንባ አውሰኝ፣

ግዕዝ ሙላት 🦘
@geez_mulat

/🖤❗️❗️ሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ❗️❗️/

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Dec, 06:58


ታናሽ እህቴ ናት በአስራ ሶስት አመት እበልጣታለሁ ። እሷ ላይ ያለኝ ስልጣን የአለቃ ነው ። 'exercise' የማደረገው ስልጣን ብዙ ነው የአፍሪካ መሪዎች ዜጎቻቸው ላይ ካላቸው ስልጣን አያንስም ። እሷም ስልጣኔ ነው ብዬ 'exercise' የማደርገውን በፀጋ ተቀብላለች ።

ልጄ ትመስለኛለች ምግብ በጋራ ስንበላ ቀድሜ ነው በቃኝ የምለው ። ከሷ ጋር እንዳልሻማ ፍቅሬ እና ሃላፊነቴ ይገታኛል ።

ሁኔታዋን አየዋለሁ ሲዶክካት፣ ስትደሰት እንቅስቃሴዋን አስተውላለሁ ። ከጓደኛዋ እንዳታንሳ 'Invest' አደርግባታለሁ ።

የሆነ ፊልም እያየን መጥፎ ገፀባህሪ ስታይ "ኤፍሬም ፊልም ስለሆነ ነው እንጂ: እንደዚህ አይነት ሰው በትክክለኛ ህይወት የለም አይደል? " ትላለች

ሰው የማርያምን ስም ጠርቶ የሚዋሽ አይመስላትም ፣ ለገንዘብ ብሎ ሰው ጓደኛውን የሚክድ አይመስላትም ፣ የውሸት ለቅሶ ያለ አይመስላትም ። ንፁህነቷ ያስደነግጠኛል ። ብስለት የሚባለውን እውቀት ማጥመቅ ፈልጌ አጠማመቁ ግራ ይገባኛል ።

ስለዓለም ክፋት መንገር እጀምር ና አለምን የምታይበት መነፅር እንዳይንሸዋረር እሰጋለሁ ።

'Feminist ' አደረገችኝ። ትሁቴን እያሰብኩ መደፈር፣ ድብደባ፣ ጭቆና እቃወማለሁ ። ትሁቴን ስለማስብ ሴት አታልሎ ወደ አልጋ መውሰድ አልችልም ። ትሁትን እያሰብኩ ገራገር እንስቶች ላይ 'Advantage ' ለመውሰድ አልሞክርም ።

ትሁቴ የመጀመርያ ልጄ ነች ። በሷ ጉዳይ አልራቀቅም ፣ በሷ ምክንያት ሴቶች ላይ በደል አልሰራም ።

ትሁቴ እንዳትኮርጀኝ ሰክሬ አልንገላወጅም ፣ የማይረባ ጓደኛዬን እቤታችን አላመጣም ፣ ትልቅ ለመሆን እባትላለሁ ።

የአንዳንድ ታናሽ አሻራ እንደ መምህር አይነት ነው !!
© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Dec, 19:06


🍩 ከPAWS እና DOGS በኋላ የBLUM መስራች ስመርኪስ በሌላ DONOT airdrop መጥቷል።

🤑 airdrop ሌላ የBlum Labs ፕሮጀክት ይመስላል።

Combo: 15-12-5-3

➡️ DONOT ን ያስጀምሩ
🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Dec, 06:02


#ታውቂያለሽ?

ፎቶሽ ላይ ጠረንሽን መፈለጌ
የእኔን ስም ከግርጌው ማድረጌ
.   .   . አታውቂም!

እኔ ውድቅ ሆኜ የአንቺን ክብር አግዝፌ
ስወድሽ ከልቤ እንዳይደለ ከአፌ
.   .   . አታውቂም!

ገብቶሻል?
እንደ ከሰልኩ እንደ ከሳኹ
በአዝማድ እንደተረሳኹ
.   .   . አልገባሽም!

ቢሆንም
እኔ እያለኹ መቼም አትወድቂም
ደግሞ'ኮ ይሄንንም አታውቂም
እንዲህም ስልሽ እንኳ በደስታ አትስቂም
.   .   . አታውቂም!

ደግሞ
ሳኮርፍሽ ወዲያው ስትናፍቂኝ
አፍቅሪኝና በናፍቆትሽ ይባስ አጨናንቂኝ
“አፈቅርሃለኹ!” በዪኝና ከልቤ አስታርቂኝ!

Meku_Mura
●HT●

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Dec, 15:34


"ከምጣኔ ሀብት ጋር፣ የተቆራኘ ተረት፣
መፍረሱ አይቀርም፣ ኑሮ የናረ እለት፣"
የሚለው አባባል፣ ለካ እውነት ኖሯል፣
በጥቅምት አንድ አጥንት፣ በድንች ተተክቷል።

- ዴዚ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Dec, 14:32


ማን ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም የሚያደርጉትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ በ ነፃ በስልኮዎ ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ(LIVE) የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉ አሁኑኑ እንዳያመልጥዎ 👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Dec, 14:22


የዓለም ምርጡ የስፖርት ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ በቴሌግራም ቻናል መቶላቿል

በጣም ትክክለኛ እና አስተማማኝ የዝውውር ዜናዎችን ለማግኘት HERE WE GO ሚለውን በመንካት ተቀላቀሉ ይቀላቀሉ

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Dec, 09:35


ተረሳስተን ሳለ ማንተያይ ሆነን
የአንቺን  ባላውቅም
       እኔና  ልቤ ግን ቃላት ስላሰረን

    መቅጠፍ ስለማይችል ከልቡ የማለ
      በደሜ ቀለም ላይ ምስልሽ'ም ስላለ

      በተጣለሁ ቁጥር በደማሁኝ ቁጥር
    ወድቀሽ እንዳትቀሪ ሁሌ ስለምጥር
       
            እየተሰደቡ  መታገስ ባይደላም
         እንዳላጣሽ ብዬ መቼም አልጣላም ! ❤️  ።

@Jovanii5

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Dec, 17:59


#የጠፋው_ፎቶ

ብርቱነት ደግነት የሚነበብበት፣
አሳዛኝ ገፅታው ፈገግታው ያለበት፣
ሳልወለድ በፊት ገና ወጣት ሳለ፣
በጥቁር እና ነጭ ቀለም የተሳለ፣
በጊዜ በሂደት እየተጣጠፈ፣
ጓደኛዬ ሆኖኝ ዘመን ያሳለፈ፣

ካቧራ ከውሀ ከንፋስ ጠብቄ፣
በክብር ሳጥን ውስጥ
ያኖርኩት ደብቄ፣
የአባዬ ምስል የጉብዝናው ፎቶ፣
የነብሴ መፅናኛ አደከመኝ ጠፍቶ።

መደርደሪያ አፈረስኩ
ከፈትኩኝ ቁምሳጥን፣
ያ'ባቴን ትዝታ ለማግኘት ስፈጥን፣
ፈተሽኩት ቦርሳዬን ጎረጎርኩኝ ሻንጣ፣
ከትውስታዎቹ ብቸኛውን ባጣ፣
አነሳሁኝ ምንጣፍ አራገፍኩኝ ልብሴን፣
ሣስስ አምሳያየን ስፈልግ እራሴን።

ድሮ ልጅ እያለሁ እማ የሰጠችኝ፣
"ይህ ነው ጀግና አባትሽ" ብላ ያሳየችኝ፣
ነብስ ያለው እውነታ ጉልበት ያለው ተስፋ፣
የአባባ ታሪክ ከፎቶው ጋር ጠፋ!

ገባሁ ሌላ ክፍል ከመፅሀፍ ክምር፣
ላላነብ ልገልፅ ላላውቅ ልመረምር፣
መሳቢያ  እየሳብኩኝ ልበትን ወረቀት፣
ፍርሀት ሊያውከኝ ሊጫጫነኝ ጭንቀት።

አሰበረኝ እቃ አስጣለኝ ብርጭቆ፣
ብቻዬን መቅረቴን ልቦናዬ አውቆ፣
ቃኘሁ በየክፍሉ በግድግዳው ስፋት፣
ምልክት ላላገኝ አይኖቼን ለማልፋት።

ባካል ባውቀው  ኑሮ በሂወቱ ሳለ፣
እንዳባት ቢጠራኝ ልጄ ሌጄ እያለ፣
እያወጋኝ ቢሄድ አርጎኝ በትከሻው፣
ይሆነኝ ነበረ ድምጹ ማስታዎሻው!
ሲያዝን ሲስቅ ባየው ሲቀያየር መልኩ፣
ይሆነኝ ነበረ ትዝታው ታሪኩ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Dec, 11:33


ናፍቆት
ወርሃ ጥቅምት ደረሰ
ታቦት የሆነው አምላካችን ናፍቆትም ነገሰ።
የትዝታ ደቀመዝሙር ከደብሩም ተገኘ
ለአምላካችን ናፍቆት ቅኔን ተቀኘ
እንዲህ ሲል ተቀኘ፤
መኑ ምስልከ ናፍቆት አምላክነ
ይህቺን ቀን ለማየት ስንቱ ተስሎ ለመነ፤
በዓለም ዙሪያ ላላቹት አፍቃሪያን በሙሉ
እንኳን አደረሳችሁ ለናፍቆት አምላክ ክብረ በዓሉ
ታድያ ለምን ዝም ትላላቹ ዘምሩ እልል በሉ።
አትመጭም ወይ ታድያ ውዴ ከናፍቆት በዓል ከንግሱ
ወይስ አላወቅሽም እንደ ሆነ ናፍቆት የፍቅር ንጉሱ?
ወይስ አልተጠራሽም ከናፍቆት ድግሱ?
ወርሃ ጥቅምት ደረሰ፥ እጽዋት ሲሆኑ ቢጫ
እንደምንገናኝ ሳስብ ናፍቆትን አስቤ
ያኔ ይሆናል ልቤ በጭባጫ።
ለምንድነው ማትመጪው?
መንገድ ነው የጠፋሽ?
ወይስ መምጣቱ ነው ያስጠላሽ?
ወይስ ቀኑ ነው የተረሳሽ?
ናፍቆት አምላካችን በሳቃችን ያውጣ የደስታን ሲቃ
አንገናኝም ወይ መባባላችንም እዚሁ ጋር ይብቃ
የተገናኘን 'ለት ትወጣለች ጨረቃ።
እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር መነፅር
የሚያቃጥል ስሜት ከቆዳችን ስር እስኪጫር
እንጫወት እናውጋ
ፍቅራችን እንዲፀና በአንድነት እንትጋ።
ወርሃ ጥቅምት መጣ ፥ እሸት ደርሶ ነበረ
አምላካችን ናፍቆት ከደብር ደበረ
ያገናኘን አምላክ እሱም ከበረ።

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Dec, 07:12


የተደበቀ ንስሀ
"""""""""""""""""
አስመሳይ ነኝ ወረተኛ
ታውቀኛለህ የኔ ጌታ፣
እየጠራሁ ለማመስገን
አንደበቴም አይፈታ፣

እልልታዬ ጊዜያዊ ነው
ማወደሴ ማሞገሴ፣
በቃልህ ጠግቤ ባድርም
ሽንገላ ነው ጠዋት ቁርሴ፣
አትማርም! ሀጢያት ተንኮል
ማታለል ነው ግብሯ ነብሴ፣
ክብር አድርገህ ያለበስከኝ
ተቀዳዷል ፀጋህ ልብሴ፣

ጎደሎ እምነት የበዛውን
ጾም ጸሎቴን አርገህ መባ፣
ለይስሙላ ደጆህ ስቆም
ብትፈቅድልኝ እንድገባ፣
ምህረትህ አረስርሳኝ
በንስሀ ብታጠብም፣
ዛሬም ልቤ ክፉን ብቻ
በጎን ነገር አያስብም።

ታውቀዋለህ ክንብንቤን
ገመናዬን ሁሉ ገልጠህ፣
ግን አኖርከኝ በም'ረትህ
ከበደሌ እኔን መርጠህ፣

ተዘርግተዋል እጆችህ
ሊቀበሉኝ በይቅርታ፣
ስሼሽ አይተህ አተዎኝም
አንተን መቅረብ ሳመነታ፣
በሀጢያቴ ስቅበዘበዝ
በስህተቴ ስደናቀፍ፣
አትሰለችም በምህረት
በቃሽ ብለህ እኔን ማቀፍ፣

ይቅር ባይ ነህ አትለወጥ
ለዘላለም በጎ መልካም፣
በቤትህ መመላለሴን
ቆጥረህልኝ እንደ ድካም፣
የሚያድነኝ አጣሁ ብልም
ብታነቅም በሾህ መሀል፣
ትርጉም የለሽ ልመናዬ
ጭንቅ ሀዘኔ ተሰምቶሀል።

ትሰማለህ ሹክሹክታዬን
ትረዳለህ የኔን ስሜት፣
አቻየን ካገኘሁ ቤትህ
ይቀናዋል ላኣፌ ሀሜት።

በከበረው አፀድ ቅጥር

ያንደበቷ ቃል የማይጥም
ብኩን ልጁን የሚያስገባት፣
የት ይገኛል ከአንተ በቀር
የሰማይስ የምድር አባት?

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Dec, 19:06


ለባለ ጠመኔው

የትውልድ አሻራ የሀገር መሠረት
ዘመን አሻጋሪ የህመም መድሀኒት
የነገ አለኝታ የመበልፀግ ሀውልት
እውቀትን ደራቢ የመኖር ትሩፋት
የስራውን እሩብ ላልተነገረለት
ለሀገር መስራቹ አንዴ ልቀኝለት

"ባለመኖር ኖሮ መኖርን የሰጠ
ሀገር ለማስከበር ክብሩን የረገጠ
እውቀትን ሊገዛ ጉልበቱን የሸጠ"

"በረሀ ላይ ወርዶ
በውሀ ጥም ሲቀጣ
ከሰው በተለየ
ነጭ ላብ ለጠጣ"

"የሚበላ ጠፍቶ ራብ ሲደቁሰው
የጠመኔ ብናኝ ባፉ ለጎረሰው
ሌላው ነገር ቢቀር
እስኪ አንዴ እናስታውሰው"

"ብዙ ኪሎ ሜትር
በጭኝጫ ላይ ሄዶ
በበረሃው ነዳድ
በረሀ ላይ ነዶ
በውርጭ በውንሽፍር
ፊቱ ተጨማዶ
ሀገርን ሲያነሳ
ከሰው ክብር ወርዶ

ገና በልጅነት
ከፊቱ ሲጠፋ የልጅነት ወዙ
ቁራሽ እንጀራ እና
ስቃይ መከራ ነው የዚ ሰው ደሞዙ

ለዚህ ብርቱ ጀግና የሀገር ባላደራ
ታሪክን አስታውሶ ታሪክን ለሰራ
ሀገር ለገነባ ትውልድን ላኮራ
ሌላው ነገር ቢቀር
like እንለግሰው እንስጠው አሻራ

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Dec, 10:58


አንታረቅም ፥..... ከአምላክ
ይሁን እንዳልከኝ ፥ ባትል እማምላክ።

አንፈታም ነበር ፥ ከገሃነብ ወህኒ
ማርያም መልአኩን ፥ ባትል ይኩነኒ።


አቤል ታደለ

ለአስተያየት :@abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Dec, 09:02


ያምላክ ጥላ ወዴት አለ
እባክህን ፀሀይ በዛ
በወዝ እንኳ ስናማኻኝ
ዕንባችን በአይን ወዛ

እባክሽን እመቤቴ
ክንድሽ እሳት በታቀፈው
ይቺን ሀገር ውሰጂልን
እቅፍሽን እንቀፈው

geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

02 Dec, 09:05


እናቴ ስሟ ጌጤ ነው ። ጉሊት ነበር የምትውለው፤ ሻሜታ ትሸጥ ነበር። ትምርት ከሌለኝ ይዛኝ ትሄድ ነበር። አዘንጣኝ ነበር የምትሄደው እኔ ከሌለሁ ልጄን ይመቱብኛል ብላ ነበር መስርያ ቤቷ የምትወስደኝ ።

መስርያቤቷ አጥር ፣ ጣርያ፣ የለውም። ወለሉን ድንጋይ ረብርባ ከፍ አድርጋዋለች።
ጥግ ላይ የምትቀመጥበት ወደጎን የረዘመ ዱካ ነበራት።

ደግ ናት፤ ፀሃይ ቀጥቅጧት የምታመጣውን ገንዘብ አትሰስትም ። ስትሰራ ውላ ደከመኝ እያለች ስትማረር ሰምቻት አላውቅም።

በየምክንያቱ "ቸርነቴ" እያለች ትጠራኛለች ።

አንገቷ ረጅም ነው ሃብል የሚመስል ንቅሳት አንገቷን አጥለቅልቆታል ። ከፊቷ ፈገግታ አይጠፋም ። ለለማኝ ገንዘብ ሰጥታ ሲመርቋት ሁለት እጇን ዘርግታ "አሜን አሜን" ትላለች። ጥሩ ነገር ከተደረገላት "ግንባርህ አይታጠፍ ...እግዚአብሔር ይስጥህ.....
አትጣ ...ጤና ይስጥህ" ትላለች።

ሰው ትወዳለች ፣ ስራ ትወዳለች ፣ አመስጋኝ ናት ...
የዚች ልጅ ተሁኖ ሰነፍ እና ክፉ መሆን እንዴት ይቻላል ? !
© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Dec, 14:20


የአንድ አባት ምክር ፦

ሃብታም ነው ብለህ ፣ስልጣን አለው ብለህ ፣ ያሳልፍልኛል ብለህ ፣ ያግዘኛል ብለህ፣ ባለሃብት ነው ብለህ ቀልቡን ለመግዛት የምትሆነውን መሆን በፊቱ ሞገስ ለማግኘት ብለህ የምትሄደውን እርቀት

ለአምላክ ብታደርገው

ታሪክህ ይቀየራል !!
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Dec, 10:02


ዛሬውኑ ጀምሩ
You guys can get free USDT—give it a try now!💵

🔗 link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Dec, 06:29


በቃል አለም

ተናገሩ ........፥ ብዙ አካላት
ጉንጭ ያለፋ ፥ እልፍ ቃላት።

መሬት አልወረደ ፥ ከማውራት ባሻገር ፤
አንዱም ጠብ አላለ ፥ የሰማነው ነገር ፤

ምላስ በበዛበት ፥ በዚህ በቃል ዓለም
ያልተሰራ እንጂ ፥ ያልተወራ የለም።

አቤል ታደለ

ለአስተያየት :@abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Nov, 14:25


ጽዮን ማርያም ፥ መጠጊያ አምባ
አብሺው ባክሽ ፥ የእናቴን እንባ።


አቤል ታደለ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Nov, 10:20


"ደደብ" አለ ተበሳጭቶ
አይሆኑ ንክ ስነካካው
ምስኪን ነብስን የገፋ ለት
በምን ነበር የተመካው
እሳት መዞ ካፎቱ ላይ
ግንባሬ ላይ አስቀመጠው
'ተኩስ' አልኩት በጀግንነት
ድኩም ነፍሴን ምን በወጣው

የተነፋው የታች ቦርጩ
በደሃ ኪስ የጠገበ
የሱን ጎጆ ልስን ሲያበጅ
የኛን ድንኳን አረገበ
ሽፍን ጭንብል ለፊቱ መልክ
ቢፈለስፍ ጥሩ መስሎ
ባዶ እንደሆን ያው ባዶ ነው
እንጨት አይሆን ክሰል ከስሎ
ዲግሪ ዲስኩር ተጫጭኖ
ምሁር ነኝ ቢል የተማረ
የኛን ህይወት ጣል አድርጎ
የሱን ህይወት አሳመረ

"እናት አልባ"....አልኩት
በጭካኔ መንፈስ
አይኑ ካይኔ ፈጦ
ተኮሰብኝ እሳት ጥይት
ካፎቱ ላይ ሹል አውጥቶ
ደም ይረጫል ከደረቴ
ወለል ክፍሉን አበስብሶ
የተበደልኩ እኔ ሳለሁ
ይገለኛል ከሱም ብሶ

ዙፋን አርጎት ወንበር ስልጣን
       ለተመካ በሰዓቱ
ጊዜ እንደሆን ሰው አይደለም
     ያሳየዋል ሁሉን ፊቱ
ከዕለታት መሐል አንዲት ዕለት ቆጥሮ
ክፍያ አለው ሁሉም ምላሽ
አይዘገይም ጊዜ ቀጥሮ

"ደደብ" አለ ተበሳጭቶ
አይሆኑ ንክ ስነካካው
ምስኪን ነብስን የገፋ ለት
በምን ነበር የተመካው
እሳት መዞ ካፎቱ ላይ
ግንባሬ ላይ አስቀመጠው
'ተኩስ' አልኩት በጀግንነት
ድኩም ነፍሴን ምን በወጣው

ተኮሰብኝ አካሌ ላይ
ገድል ፃፈ...ሰብሮ ገድል
በጊዜ ላይ ለነገሰ
አያነሳም የፅዋ ድል

ለፍቶ መና...ለፍቶ ከንቱ
በሆነባት በዚች አለም
የጊዜ ነው እንጂ
የሰው ጀግና የለም


ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

29 Nov, 09:15


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

29 Nov, 07:09


ቀጥቅጬ የገደልኩት~እባብ የትናንቱ
ሳይተነፍስብኝ~ሳይነካኝ መሞቱ
ተረሳው መሰለኝ...
ዛሬ እንደነደፈኝ~በዛ መጠዝጠዙ
በቃ እንደፈራሁት~ያንተ ነበር መርዙ

ዘማርቆስ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Nov, 21:47


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Nov, 21:38


🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️🀄️ሉን!👇

https://t.me/+UqU8zCoHqyw2NzQ0

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Nov, 21:26


🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Nov, 19:24


BUMS Daily Combo

ወደ CITY የሚለው ቦታ ትገባላችሁ ከዛም LOTTERY ውስጥ ትገቡና ምስሉ ላይ ታሉትን combo መርጣችሁ check ማለት ነው።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Nov, 12:39


Major listed

1 MAJOR ! = 1.9$

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Nov, 07:43


https://www.tiktok.com/@kirubelyisma?_t=ZM-8rkW9WkmCYi&_r=1

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Nov, 13:03


በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Nov, 05:47


**
ዘባተሎ የለበሰ
ማስመሰልን የሚጠላ፣
ወፈፌ ነው የተባለ
በሰወች አይን የማይሞላ፣
ቢገኝም በየመንገዱ
አፍ ከፍቶ ውስጡን የሚያሳይ፣
ለዘበት እገሌ ምለው
አላውቅም አንድ እሱን መሳይ፤

ቀን ሙሉ ቢለፈልፍም
ሲያወራ ቢውል ሲናገር፣
ቢያወጋ ጥበብ ብቻ ነው
የለውም የሚጣል ነገር፣
ልሳኑ ላደባባይ ነው
ጩኸቱን ያውቃል ሀገሩ፣
ሰባራ ተስፋን ገጣጥሞ
ያክማል በንግግሩ፣

አላፊ አግዳሚ አይፈራ
ግድ የለው ልምዱ ነው እሱስ፣
ባይኖርም ጉዳይ የሚለው
ለኔ ግን ሆኖብኛል ሱስ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Nov, 18:07


ከእባብ ቆዳ ትል ይውጣ
የሰው ህሊና በቁም ይፍሰስ
እየተላጠ ቆዳው በደም
የአምላክ ዙፋን በሰው ይርከስ ፣

ሌት አጋንንት ይሰማሩ
መናፍስት ነፍስን ይግዙ
ክዋክብት ይረጋግፉ
በአምላክ ፊት ይጠልዝዙ

ጥንቆላ ገደል ይግባ
ገደል ገብቶ ቤቱን ይስራ
መተት ሁሉ ይንሰራፋ
የጠንቋይ ስም ባለም ይብራ

ሰማዬ ደም ይልበስ
ትል ይትፋ ምድር ሁሉ
ዳቢሎስ ነጭ ይልበስ
በሰው እቅፍ ይታለሉ

ሳር ቅጠሉ እባብ ይሁን
ወንዙ ሙሉ ጫካ መንፈስ
ንፁሃን ይደራመስ
እባብ ባለም ነጥቆ ይንገስ

ያለንበት ባለም  ሁሉ፥
እኛ ሁሉ የምንሆነው
እባብ ልንገል ምናሴረው
ለእባብ ነበር የምንወልደው ፣
እንዲህ ነበር ያገሬ ሰው ፣
ከሰይጣን ጋር ሚዋሰበው
እንዲህ ነው ያገሬ ሰው...
ራሱን ነው ያረከሰው...

geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Nov, 12:39


ስምን መሄድ ጥሎ
ከታሪክ ተካፍሎ
አሸብርቆ መኖር
በወርቅ ተጠቅልሎ ፤
ዘርን በመተካት …
ወዳጅን በማፍራት
የምድር መናዋን
ብዙውን በመብላት
ሸጋውን በመልበስ
ፋሽን በመጫማት
ማርሴዲስ መኺና
ሸምቶ በመንዳት
ነው እያልን ስንኖር
መለኪያ ፣ ሚዛኑ
ሁሌ በየቀኑ…
ከልብ መሳቅ ኖሯል
የስኬት ተመኑ !

(ሚካኤል አ)

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

25 Nov, 07:46


ተመስገን ❤️

እሱ መውደድ ገባኝ
እሱ ክብር አነቃኝ
የተኛሁበቱ የሞት መንገድ በቃኝ

ፀናሁ እንደ ክረምት
ነጋሁ እንደ ሌሊት
ምስክርም መጥቶ ጨመረ የልቤ ምት

ዳግም ተወለድኩኝ
ሰላም ተሸለምኩኝ
እንድኖር ዘላለም ተመስገን እያልኩኝ

መልካም ጾም

Aናን

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

23 Nov, 13:13


ነብሴን ሰላም ነሳት


ያረገኛል ደርሶስ
አንዴ ፥ እንደ አትናቴዎስ
አንዴ ፥እንደ አርዮስ
ወይም ሙቅ አይደለሁ ፥ ወይንም ቀዝቃዛ
ለብ እንዳለ ውሃ ፥... ሆነ የኔ ለዛ።

የሥጋዊ መሻት ፥ ነብሴን ሰላም ነሳት
አንዴ ወደ ውሃ ፥ አንዴ ወደ እሳት
ሲጥላት ፥ ሲያነሳት


አቤል ታደለ

ለአስተያየት :@abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

21 Nov, 09:25


👌ለዩንቨርሲቲ እና ለ ተማሪዎች ብቻ የተከፈተ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው የተመረጡ ቻናሎች ስብስብ 🤩🤩

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

20 Nov, 12:42


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

19 Nov, 18:39


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

19 Nov, 18:27


◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

19 Nov, 13:37


ስሙኝማ…
ልጅነትን ስሸኝ በሀሳብ አድጌ
ከብቸኝነት ጋር ልላቀቅ ፈልጌ

ትዳር ለመወጠን ካሰብኩኝ በኋላ
ያየሁት እሸት ሁል ሆነ 'ማይበላ

የሆነ ቀን ለታ
አንድ አለኸኝ ብላ
ቃል የገባች እንስት
አንድ አለሽኝ ብየ
ቃል የሰጠኋት ሴት
ከብዙ ሁካታ ከጨዋታ መሀል
ከእኔ አስበልጠህ
ሴት አትወድም አይደል?
ብላ ስትጠይቀኝ መሳቄን አቁሜ
በንዴት በግኜ ደግሞም ተገርሜ
"አትሳሳች ውዴ
ካንች እጥፍ ድርብ ውለታ የዋለች
ለእኔ ደስታ ብላ ደስታዋን የሸጠች
እኔ እንደምወድህ ውደደኝ ያላለች
ካንች በበለጠ
ፍፁም ምወዳት ገራሚ ሴት አለች"
ብየ ቃል ሳወጣ
ገደል ግባ ብላ ገፍታ ጥላኝ ሄደች

በዚህ ቃል ተናዳ ከፊቴ ላይ ሳጣት
ፍቅሯን አራግፌ ከልቤ አወጣኋት

ደግሞ ትናንትና
አንድ አለችኝ ያልኋት
የህይወት አጋሬ
"መውደድህ እንዴት ነው
የት ድረስ ነው ፍቅሬ?
አንዴ ቃል አውጣና
በል ንገረኝ ዛሬ"
ብላ ስትጠይቀኝ
በኔ ልብ አዋዋል በፍቅር አደራደር
ከመውደድ ዙፋኔ ከልኬት ማህደር
ቦታ አደላድየ ላሞግሳት ስጥር
የሚከተሉትን ቃላት ብወረውር
"ዚች አለም ስኖር ካገኘኋቸው ሴት
ደስታ ካቋደሱኝ ካለበሱኝ ሀሴት
ደረጃ ሰጠሁሽ በሁለተኛነት"
ብየ ስናገራት
ከእኔ የበለጠ የምትወዳት ካለች
ከርሷ ጋር አብረህ ኑር
ብላ ጥላኝ ሄደች
የምር ጉደኛ ነች😢
ይህን ስትናገር በፍቅር አኩርፋ
ለእርሷ ያለኝ ፍቅር ከእኔ በኖ ጠፋ

እናም
ነገ የማገኝሽ የትዳር አጋሬ
መኖርሽ የምሆን የምትሆኝ መኖሬ
ቀደም አስቢበት በይ ልንገርሽ ዛሬ

ከመንገስሽ በፊት ከልቤ ዙፋን ላይ
ሁለተኛነትሽን በይ አምነሽ ተቀበይ
ወይም
ብቻየን ወድቄ
ሳልቀምሰው ይቅር እንጂ
የትዳርን አለም
አንደኛነትንስ
ከእናቴ አስበልጬ
የምሰጠው የለም

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

18 Nov, 19:58


Paws ላይ አዲስ task አለ ቶሎ ውሰዱ limited time ነው።

paw farming

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

18 Nov, 17:43


ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)

በአብማይቱ እምላለሁ፥ ማይክ ታይሰን ቢያሸንፍ ኖሮ ትንሽ ቅር ይለኝ ነበር፤ የአምሳ ስምንት አመት ሰውየ የሀያ ስምንት አመት ጎረምሳ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ባፍጢሙ ደፋው ፥ ቢባል የሰውየው የፍጽምና ማሳያ ይሆን ነበር፤ ፍጹምና እንከን አልባ የሆነን ሰው ደግሞ አርአያ ማድረግ ያደክማል፤

ከትልልቅ ሰዎች የምጠብቀው ልከተለው የምችለው አይነት አርአያነት ነው፤ ለካ በአምሳ ስምንት አመቴ ፥ጡንቻ መገንባት እችላለሁ፥ ስምንት ዙር ሪንግ ውስጥ የሚያስቆይ ትንፋሽ ማካበት እችላለሁ፤ ለካ በዚያ እድሜ የልጆቼን እጅ ሳልጠብቅ በጥረቴ እንጀራ መብላት እችላለሁ ፥ ብለህ እንድታስብ የሚያደርግ አንጋፋ ጀግና ሲገጥምህ ልብህ በተስፋ ይሞላል፤ ማይክ ታይሰን ምን ፈየደልህ ብትይኝ መልሴ ይሄ ነው፤ አምሳ አመትን ከዘራ በማማረጥ እንዳልጠብቀው አድርጎኛል፤ ከዚህ በላይ አነቃቂ የለም!

“ምንም ደሀ ቢሆን ባይኖረውም ሀብት
ከደጃፍ ሲቀመጥ ደስ ይላል አባት “

የሚል ጥቅስ እየተመሰጥን ነው ያደግን፤ አብዛኛው ሰው ወጣትነትን ሲሻገር የአካል እንቅስቃሴ እንዲያቆም ውጫዊና ውስጣዊ ግፊት ያድርበታል፤ ውጫዊው “ ካልጠገቡ አይዘሉ፤ ካልዘለሉ አይሰበሩ “ እያለ ይለጉምሀል፤ ውስጣዊው ደግሞ አሁን ከዚህ “በሁዋላ ቀንድ አላበቅል” እያልህ የሰውነትህን እምቅ አቅም ሳትረዳ እንድትሞት ያደርግሀል፤

ታይሰን ሀያ ሚሊዮን ዶላር ይሸለማል ተብሏል፤ ቀላል ጥሪት አይደለም፤ አያትየው የልጅ ልጆቹን መጦር ይችላል፤ ባንድ ሚሊዮን ብሩ የተጠረመሱ ፥ የመንገጭላው አጥንቶቹን ያስጠግንበታል፤ የተዳጠ አፍንጫውን ያስበይድበታል፤ በቀረው ደግሞ አለሙን እንደ ጥንቅሽ ይቀጭበታል፤ ምናልባት ሳይንቲስቶች በጥቂት አመታት ጊዜ ውስጥ የእድሜ ማደሻ ቅመም መፍጠር ከቻሉ ደግሞ የመሸመት አቅሙን አዳብሯል፤

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ደጃፍ ላይ የሚያስቀምጠውን መንፈስ በካልቾ ብላችሁ በነገው ታላቁ ሩጫ ላይ ተሳተፉ፤

ልዝብ ደሀ ቢሆን ባይኖረውም ሀብት
ታላቅ ሩጫ ላይ፥
ወልመጥ ወልመጥ ሲል። ደስ ይላል አባት🙂


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

18 Nov, 15:32


መጣለሁ
  በናፍቆት አክናፍ ስከንፍ
ያስለመድሽኝን .. , ውብ አይንሽን
ዳግም ላተኩር  ልተክዝበት
ህይወት ውጥንቅጡን
ዳግም ላዘግም ልዘብትበት

መጣለሁ

ከሳቅ  ነው ? 'ሳሳቅሽ ?
ገላሽ ነው ጠረንሽ  ?

ይህነው በማልልሽ
ይሄ ነው በምልሽ
በሂ አፈጣጠርሽ



መጣሁ
መጣሁማ

ሀሴት ላደርግበት

ቅኔ  ልቀኝበት

አኮኬት
አኮቴት አኮቴት ልልበት ።




መሳት ሳያስትሽ
መጠርጠር  ሳያይሽ
መርሳት ትዝ ሳይል
መልመድ ሳይሰውርሽ
ጥቂት ጥቂት
ብቻ





ግን ግን
እንድያው የድንገት
እኔን ስጠብቂ
ቢመስልሽ  የምቀር
ይህንን አስቢ

ሌት ለሺህ ሰከንዶች
ታብዮ ቢጨልም
ምድር አይኗን መግለጧ
ፀሀይ መፍለቅለቋ
መንጋቱ እንደው
አይቀርም።


ስትሰጊ  ቢከፋሽ
መጠበቅ ቢደብት
ተስፋ ቢያሳጣሽም
ጥበቃ መቆርፈድ
እድሜን ማንደድ
መክሰም
ሆኖ ቢታይሽም


ደሞም
ደሞም

ልትተይኝ ብትይ,
ብትረሽኝም ደሞ
ሌላ ልትለምጅ።

ቃሌን 'ዳትዘነጊ
መጣለሁ
መጣለሁ
እምነትሽን አትጭ ።

By ሚክያስ አለምሰገድ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

18 Nov, 08:36


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

17 Nov, 06:04


እንቅልፌን ላውስሽ
እስከ ጠዋት ተኝ
ለችግርሽ እንደው
እኔ ልብከንከን ፣
ከቀን ባላድንሽ
የሌት ህልሜ ከሆን
ባንቺ ይታለም ፣

ከንፈርሽ ስር ያለች ነጥብ
ማሪያም ስማሽ ከሆነ ግን ፣
እንዴት አየህ አትበይ
ከእግሬ ስር ተኝተሽ
በሌሊት ወጋግን፣

(ነውና ያየሁሽ )

ካይንሽ ስር ላይ ገደል አለ
ግፋኝ ልውደቅ እያነባሽ ፣
እኔ ከታች ልውደቅ ቆይ
የዱር እሾህ እንዳይወጋሽ ፣

ደረቴ ጋር ጥብቅ በይ
ይጠፍሩኝ በልጥ ዛፍ ፣
ጡቶችሽ ጋር ካሳደረኝ
ከተራራው ጎጆ አፍ ፣

ከሰው መንጋ ተገንጥለን
ከጫጩት ድምፅ ተነጥለን ፣
በባዶ እግር ጫካ አልፈን
ተራራው ጫፍ ጎጆ ሰርተን
በጫካ ዛፍ ተከልለን ፣

ከሰሜን ንፋስ ሲ ነ ፍ ስ
ደመናው ሰማይ ሲ ወ ር ስ

በምስራቅ ጎን
የድንቢጥ ድምፅ
በምዕራብ ታች
የአንበሳም...፣
በቀስታ ተቃቅፈን
በዝምታ ስንሳሳም ፣

በጣቶቼ ወገብሽን
ክንዴ ሞልቶት ዞሮ ሲደርስ ፣
ከሰማዬ ነጫጭ ውሃ
ዝናብ ሚሉት ከእኛ ሲፈስ ፣

ተቃቅፈን ከአልጋችን
ዶፉ ሲወርድ ከጎጆ ውጭ ፣
በሳቅሽ እየታጀብኩ
በብልጭታው እያየሁሽ
በነጎድጓድ ስትደነግጭ ፣
በጣቶችሽ ጣቴን
በጭንቀት ስትጨብጭ ፣

ድንግጥ ስትይ አንገቴ ስር
ትንፋሽሽ ላይ ሙቀት ሳገኝ ፣
በግርብታ ያልጠበቀ
በቀ..ስ..ታ..ከንፈርሽ እንደሳመኝ

ከሩቅ ላይም የአራዊት ድምፅ
ከክንዴ ላይ ያንቺ ነፍስ ፣
ከንፈርሽ ስር ባለው ሀይቅ
ዋኝተንበት እንፍሰስ ፣

ከዚህ ጩኸት እንደበቅ
ከጫጫታው እንሰወር
በጨለማው ፍቅር ወበቅ
እንደ ድር እንደወር
ህልም ማለት..?እስኪ እንወቅ...?


የእኛን ኑሮ ካልጠበቁት
ከገፉን ስር ከሚስሙት
አድበስብሰው ከሚቀብሩት
ተራራ ስር ካለው ጎጆ
ዘላለም ነጥለን
ዘላለም ተቃቅፈን
ዘላለም እንሙት

geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

16 Nov, 13:55


MAJOR NOV 20 ማይኒንግ ይጠናቀቃል

ያልጀመራችሁ 👇👇👇👇👇

🔗LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

15 Nov, 19:06


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Nov, 15:59


በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Nov, 12:54


አልገባህም
***
ጉዞ አይደለም ያማረረኝ
መውጣት መውረድ መመላለስ፣
እመጣለሁ ነይ ብትለኝ
ተራራው ጫፍ ዳሽን ድረስ፣
ከገሞራው ጋር ተስማምተህ
ከኤርታሌ ብትጠራኝ፣
እመጣለሁ በሳት ትንፋግ
መቀጣጠል ሳያስፈራኝ፣

ፋሲልም ሂድ
ቢሻህ አክሱም ላሊበላ፣
እኔ እንደሆንኩ
ተከታይ ነኝ ያንተን ጥላ፣
ጉዞ አይደለም ያማረረኝ
መውጣት መውረድ መመላለስ፣
ከቻልክ አንተ ጥራኝ እንጂ
እመጣለሁ ሰማይ ድረስ፣

አይ አይ ዝም በል አልገባህም
ኩርፊያዬ እና ንጭንጬ፣
በሄድክበት ቶሎ እንዳልደርስ
እንዳልመጣ ተሯሩጬ፣
ፍቅርህ በዝቶ በልቤ ላይ
የማልችለው ሆነኝ ሸክም፣
እንዳልፈጥን እያዛለ
አደረገኝ እንድደክም፣

ባለችኝ ቃል የምነግርህ
ያሰብኳትን ለመናዘዝ፣
ልብ ሲያዝ እንኳን እግር
አንደበትም አይታዘዝ፣
ካንተው እኩል እንድራመድ
ከመድረሻህ እንድደርስ፣
አስቀይመኸኝም ቢሆን
ከልቤላይ ፍቅር ቀንስ።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Nov, 09:33


ተሳካላት አሉኝ እየተሳቀቁ እማዝን መስሏቸው ..

.....ስስቅ ገረማቸው

ተያቸው !!

ስኬትሽ .....

አብረን የወጠነው ፣አብረን ያወጣነው፣ አብረን ያወረድነው ፤ ፀሎቴም መሆኑ ስላልገባቸው ነው !!!
@adhanom mitiku


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Nov, 19:03


BUMS Daily Combo

ወደ CITY የሚለው ቦታ ትገባላችሁ ከዛም LOTTERY ውስጥ ትገቡና ምስሉ ላይ ታሉትን combo መርጣችሁ check ማለት ነው።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Nov, 10:10


MAJOR UPDATE

$MAJOR November 28 ሊስት እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል።

ያልጀመራችሁ 👇👇👇👇👇

🔗LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Nov, 04:42


ለምን ፈጠርህ?

እልፍ አዕላፍ ዘመናት ወደ ኋላ ዞሬ
መኖሬን ሳልጨርስ ባለመኖር ኖሬ
እንደ ኤፍሬም ስዩም
ለምን አልፈጠርም አልልህም ዛሬ

ያለው ያነሰበት ፍስሀ የራቀው
አለም ጠባብ ሆና
ልቡን የጨነቀው
ፍጡር ያነሰው ነው
ለምን አልፈጠርህም
ብሎ የሚጠይቀው

ያውም ወደ ትናንት የኋሊት ተጉዤ
ፍጡር የሌለበት ቀናትን መዝዤ
ወደ አንተ አልመጣም
ለምን አልፈጠርህም?
የሚል ሙግት ይዤ

ሁሉን የምታደርግ
የአለማት ንጉስ
ለምን አልፈጠርህም
የተባልህ ክርስቶስ
አንዴ ልጠይቅህ
ጥያቄየን መል'ስ

ለምን ፈጠርህ?

ለሰው ነፃ ፈቃድ
ከሰጠህ በኋላ
ለምን እባብ ፈጠርህ
ካንተ የሚያጣላ

ለምን ፈጠርህ?

የተገኘን ሁሉ
ከየመንገዱ ላይ እየበላን ስንኖር
ብርድ ሳይደቁሰን ልብስ ሳንቸገር
በለስን የፈጠርህ
ለምን ጥቅም ነበር

የሚበላ ሞልቶ
በለስን የበላን እኛ ሆዳም ፍጡር
አትስሩ ያልከንን በመስራት ስንሽር
ሞት ሲፈረድብን የባርነት ቀንበር
ለምን አንተ ሞተህ
ፈጠርህ አዲስ መኖር

ደግሞስ
ሞታችንን በሞት
በገደልከው ማግስት
ልቡን እያወቅኧው
ይህን የአዳም ፍጥረት
አመንዝራ ፈጥረህ
ለምን ትደግማለህ ስተትን በስተት

አንተ የአለም ገዢ
ሁሉን ማድረግ ስትችል
ለምን ትፈጥራለህ
ቃል ማክበር የማይችል
ለምን?
ለምን?
አስርቱ ትዕዛዝህን ጠንቅቆ ፈፃሚ
ለክብርህ አጎብዳጅ ሰጋጅና ጿሚ
አለምን ዘንግቶ ከማህሌት ቋሚ
በሁሉ ስራዎች አንተን የሚከተል
እንዲህ አይነት ፍጡር
መርጠህ መፍጠር ስትችል
ለምን ትፈጥራለህ
ቃልህን ሚያቃልል

ለምን ፈጠርህ?

የአንተን ግሩም ስራ
ፍጥረትህን የሚንቅ
አውቃለሁ ባይ ፍጥረት
በፍፁም የማያውቅ
አንተን ሊገዳደር
ከትልቁ ባህር
በማንኪያ የሚጠልቅ
የእጆችህን ስራ
ለምን ፈጠርህ ብሎ
ደፍሮ የሚጠይቅ
ለምን ትፈጥራለህ
የእኔ አይነቱን ደረቅ

እኮ ለምን?

ዝምተኛው ፀሀፊ
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Nov, 17:55


BUMS Daily Combo

ወደ CITY የሚለው ቦታ ትገባላችሁ ከዛም LOTTERY ውስጥ ትገቡና ምስሉ ላይ ታሉትን combo መርጣችሁ check ማለት ነው።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Nov, 16:07


ከእንቅልፌ ስነቃ ደሞ ነጋ ብዬ አውቃለሁ ። አስር ብር ወድቆብኝ የማንሳት አቅም አጥቼ ከዛፍ እንደወደቀች ቅጠል ቸል ብያት አውቃለሁ ።

አይኔን እያዩ ሲያሳንሱኝ ሳይደብረኝም ደስ ሳይለኝም ቀርቶ ያውቃል ..... እየተሰደቡ ስሜት አልባ ፊት ማሳየት እንዴት ተቻለኝ... አልኩኝ

የሆነ ቀነ እንደዋዛ ኑሮዬ ላይ ገባች .... አለባበሷን በደንብ ስመለከት ውበቷ ሲታየኝ ባወራችው ጎረምሳ ስቀና እሷን ለማግኘት ቶሎ ቶሎ የሚያድገውን ፂሜን ስቆረጥ ለሁለት ብር ከረዳት ጋ ስጨቃጨቅ ...

ያላመነቺኝ ሲመስለኝ ስምል ...አልገባኝም ደግመሽ አብራሪልኝ ስላት

"ዛሬም አታገኘኝም እንዴ ?" ስትለኝ ቀጠሮ ስሰርዝ ...ፖለቲካው ኢኮኖሚው ተጭኖኝ ችላ ስለው
.
.
ለደበረው ሰው አዚ ጋ አንድ ፍቅር አምጣለት ማለት ስከጅል

ምን አልኩ መሰለሽ .....
'ባልወድሽ ኖሮ ድብርትን አልችለውም ነበር '
©Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Nov, 18:22


እናቴ ሁሌ ነበር አግቢ የምትለኝ ፣ በተረት ፣በታሪክ በሃዘን አስታካ ስለ ትዳር ነበር የምትወተውተኝ ። በመወትወት ከማይሆነው ነገር ውስጥ አንደኛው ትዳር ነው ።

ውትወታዋ በቶሎ ፍሬ አላፈራም ። ውትወታዋ ስለሚያስጨንቀኝ ክፍት ያለ ፊት ሳሳያት ጨዋታ ትቀይራለች ።

አብሪያት ሳድር ፀሎቷ ውስጥ በየቦታው አለሁ ።

ሰመረልኝ እና ....!

" እናቴ ላገባ ነው የምወደዉ ልጅ አግኝቻለሁ መስመር እስኪይዝ ነው ያላጫወትኩሽ"

"ምን አልሺኝ ?"ብላ ብድግ አለች

እጮኛዬ ሽማግሌ ሊልክ ነው አልኳት።

እምባዋ ቃላቷን ቀደመው !

ጥሩ ሰው ነው ?? ትዋደዳላቹ ??

"አዎ" አልኳት በፈገግታ ሌላ አልጠየቀችኝም ።

አገላብጣ ሳመቺኝ ። ደስታዋ ወደር አልነበረውም ።
አንጋጣ ተመስገን አለች ።

ደስታዋ አንጀቴን በላኝ ። እናት ከሃዘናችን በላይ ደስታችን ያስለቅሳታል ። የልጅ ሃዘን ለእናት እምባ አይደለም ስብራት ነው !!

መሰበር የምንፈራው ለሚወዱን ሰዎች ብለንም ነው ። እኛ እኮ የኛ ብቻ አይደለንም !!
© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Nov, 13:31


‘ጥፍራም ነህ ‘ ስላለኝ
ተቆረጥኩት ጥፍሬን
‘አርጅቶ ነው ‘ ሲለኝ
ጣልኳት ከዘራዬን ።
ያኔ ተናነቀኝ …
ጥፍሮቹን ሞርዶ ፣
በትር ይዞ ዱላ…
ምኔን ይዤ ልትረፍ?
ከታለልሁኝ ኋላ!

(ሚካኤል አ)

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

08 Nov, 19:11


BUMS verified airdrop ነው:: ብዙ ሰዎች join እያደረጉት ያለ ትልቅ project ነው አትዘናጉ በደንብ እንሰራበታለን።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

08 Nov, 07:49


MAJOR COMBO

REWARD ሚለው ጋ ገብታቹ durov puzzle ሚለውን ነክታቹ ምስሉ ላይ ባለው በቁጥሮችሁ ቅደም ተከተል ስሩት።

📹Major Video Code
#1 :
070624
#4 : 159390
#6: 241086

ያልጀመራችሁ 👇👇👇👇👇

🔗LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

08 Nov, 05:18


Master Card ለምትፈልጉ

Bybit Card 💰

ለማንኛው በነፃ ByBit ተጠቃሚ ከሆናቹ MasterCard debit card እየሰጡ ነው

ከናንተ ሚጠበቀው

ByBit Account መኖር እና KYC መጨረስ ነው
BYBIT ካሌላችሁ 👉LINK
በዚህ account ክፈቱ ካላችሁ ግን ወደ ቀጣይ step መሄድ ትችላላችሁ።

ከዛ Apply ማረግ

Apply ለማረግ 👇👇👇

https://www.bybit.com/fiat/cards?source=referral&campaignId=1686258086857150464&ref=LRQ97O1

ከዛ እንዳሉት ከሆነ ከፈለግን ያለንን Cryptocurrency or Fiat በመጠቀም መገበያየት እንችላለን

ሚያስቀምጥላችሁን FORM በስነስርአት ሙሉ እና REVIEW አርገው ይሰጧቹሀል ።

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Nov, 16:41


ላገባሽ ነው እንዳታገቢኝ
'
'

አመጣጤ እንዳየሽው
ሚያምር መስሎሽ አትሸወጅ
ምላስ ስንት ያሳልማል
ወንድ እስኪዝ በእጅ

አልጋየ ላይ እትት ስልሽ
ስታለፊኝ ከሌት አዳር
የሴት ልብ ሞኝ ነው
ከተወራ ስለትዳር

ላግባሽ ግን አታግቢኝ
ላግባሽስ አልፈልግም
ካልጋ ቤት ካልሆን በቀር
በቀለበት አንሰርግም

/ ላገባሽ ግን አልፈልግም.../

የሴት ጫካ ገብቼ
ሳድን ሳካልል
አንቺን ድንግል ህፃን
ጣለሽ ከመሃል

እንደው ላልጋ አስቤሽ
ላግባሽ ላግባሽ ስልሽ
ጠዋት ልፈታሽ ነው
አትመኝኝ ባክሽ

አግባኝ አግባኝ አትበይ
አፈቀርኩህ ፍቅር
ምናምንቴ ትዳር ፥
ኩችኩች ሆታሄ
ምናምንቴ ቁማር ፣
እኔ አልታመንም
እሽ ካልሽ ግን
ላግባሽ ከአንሶላየ ጋር ፥

አንሶላ ውስጥ ገብተሽ
" ልስጥህ ሴትነቴን "
ጠዋት እንለያይ
መልሽ ቀለበቴን

ቢጃማ አወላልቀሽ
ፊቴ ስትቆሚ
በራቁት ሰመመን
ወንድ ልጅ ዝም ካለ
ይቅርብሽ ማመን

ማፍቀሬን ሳስመስል
አይደለም የሴት
የአጋንንት ልብ ሸውዶ ይገዛል
ተይ አትመኝኝ
ወንድ ልጅ ሲያሸንፍ
ዝምታ ያበዛል

ላገባሽ ነው አልጋዬ ውስጥ
ልጥልሽ ነው ጥሎሽ ዕንባ
ላንድ ቀን ከሆነማ
ለአንድ አዳር እንጋባ

geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

"በእውነተኛ የወንድ ታሪክ የተፃፈ 🙏"

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Nov, 11:15


#ተጣልተናል_እኮ
.
እንደማንመለስ ምለን በታቦቱ፣
ንግግር ካቆምን አልፈዋል ወራቱ፣
ኧረምን ወራቱ አመታቱም ነጉዷል፣
ሌላ ወድጃለው እሱም ሌላ ወዷል፣

ግና....
ቁልምጫ በሚሉት እዳ ተለክፌ፣
ሙሉ ስሙን መጥራት አለመደም ኣፌ፣
ተጣብቆብኝ አንዴ የቁልምጫው ነገር፣
ስለሱ ስጠየቅ ለሰዎች ስናገር፣
ውዴ፡ ማሬ፡ ፍቅር፡ ላለማለት ስጥር፣
ይቀድመኛል ኣፌ ባስታዎስኩት ቁጥር።

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Nov, 09:21


MININING ነገ ይጠናቀቃል

MAJOR COMBO

REWARD ሚለው ጋ ገብታቹ durov puzzle ሚለውን ነክታቹ ምስሉ ላይ ባለው በቁጥሮችሁ ቅደም ተከተል ስሩት።

📹Major Video Code
#1 :
070624
#4 : 159390
#6: 241086

ያልጀመራችሁ 👇👇👇👇👇

🔗LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

07 Nov, 07:08


#የኔ_ሴት
.
.
.
ያየኝ የለም ቆላ አልወጣሁም ደጋ፣
አልንከራተትም የኔን ሴት ፍለጋ።
ይሁን ካለ አምላክ ከፈቀደው ጌታ፣
ያመጣት የለም ወይ ካለሁበት ቦታ።

✍️ ዓቢይ ( @abiye12 )

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Nov, 12:08


'ግራ የተጋቡ ዕለት'

ከዕለታት አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነሣ
ወደ ውጭ ልወጣ ጫማዬን ሳነሣ
ሸተተኝ ... 'ሳምቡሳ ... ሳምቡሳ'
ወዲያው ወጣኹና ሻይ ቤት ገሰገስኩኝ
ገብቼ ስቀመጥ ብርጭቆ ሰበርኩኝ
ለማንሣት ሲሯሯጥ ደግ አስተናጋጁ
ከአፈር ደባልቄ አቆምኩበት በእጁ
የተሰበረውን ከመሬት ሲያነሣ
እኔም አልኩት . . .
አምጣልኝ አንድ 'ሳምቡሳ'
"አኹን አታገኝም ማታ ተመለሳ!?"
አለኝ . . .

እኔም ተመዘግዝጌ ስወጣ ከቤቱ
ከጓሮ መጣና ጠራኝ ባለቤቱ
"በጠዋቱ መጥተህ ልባችንን ሰበርከው
ና ክፈል ለሰበርከው"
አለኝ . . .

ሳየው ዓይኑ ሲንፈራፈር
አጎንብሼ ወደ አፈር . . .
አረመምኩ . . . ቻልኩት
'ለዚች ጥቂት ነገር ልባችሁን ሰበርኩት?!'
እያልኩኝ በውስጤ ...
ጠፋኝ መላቅጤ

ምክንያቱም ...
ብርጭቆውን ከመስበሬ የተነሣ
ሳልበላ ላድር ነው ያማረኝን 'ሳምቡሳ'😁


እንግዲህ ወዳጄ ሕይወት እንዲህ ናት፥ አትማረር!!

MekuriyaM ነኝ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Nov, 11:08


Binance #BitcoinButton is Back: Hit the Button, Countdown to 00:00 and Win 1 BTC!

The game will start once 73,750 players have joined
👇

🔗 https://www.binance.info/game/button/btc-2024?utm_source=share&registerChannel=GRO-BTN-btc-2024


@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

06 Nov, 07:08


ትራምፕ አሸንፉል

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Nov, 22:44


የሁለት ፍቅረኛሞች ታሪክ

አንድ ወጣት አንዲትን ልጅ ያፈቅራት ነበርና አንድ ጉዞ ላይ አብረው ተጉዘው ነበር። የጉዞው ቡድን በሆነች መንደር መግቢያ አከባቢ አዳራቸውን ሲያረጉ ልጁም ጨለማውን ተገን በማድረግ ወደ ሚወዳት ልጅት ጋር በመሄድ እንድትመቻቸው ይጠይቃታል ።

  እሷም እስቲ ሰዎች ሁሉ ተኝተው እንደሆነ ተመልከት ትለዋለች። አይቶ መጥቶ ሁሉም እንደተኙ እና ምቹ አጋጣሚ እንደሆነ ነገራት። እሷ ግን .....ሙሉታሪኩን ያንብቡ Read more

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Nov, 22:32


እድሜዎ ስንት ነው ?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Nov, 18:28


Dogs 🤝 Paws

PAWS ቶሎ ጀምሩ👇

🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Nov, 15:13


ገጣሚው
ማንም ያላየውን
ማንም ያልፃፈውን
በፊት ያልነበረ …
ስንኝ ለማዋቀር
መወጠን ጀመረ ።
ሆኖም ግን አንድ አጣ
ያልተፃፈ በሰው
ሁሉን ቢያሰላስል
ቢያወጣ ፣ ቢያወርደው
አንድም አልነበረ
ሌላው ያልጀመረው ።
አሰበ ገጣሚው
አወረደ ፣ አወጣ
አዲስ ነገር ልፃፍ
ብሎ የጀመረ
ገጣሚ ግን አጣ።
እናም ይሄን ጊዜ
የሱን ክታብ ሲቃኝ
ቀለሙን ሲያዋድድ
ከዝርጉ ወረቀት
'አዲስ ነገር ልፃፍ'
የሚል ነበረበት ።
ስንኙ አበቃ
ብዕር ተሰለበች
ታጠፈች ወረቀት
ግጥም ቀን ወጣላት ፤
አዲስ ነገር ፃፈ
አዲስ ነገር ልፃፍ
ብሎ በመነሳት ።

(ሚካኤል አ )

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Nov, 10:33


የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
የቱ ጋር መሰለህ?
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴት ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
የቱ ጋር መሰለህ?
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በሀይኪንግ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ሳትቆም ለፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
ትዝ አለህ?
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
ምላሹስ የከፋው መቼ ላይ ሆነና?
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
ትዝ አለህ?
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
ትዝ አለህ?
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
ትዝ አለህ?
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ?
ብለህ ስትቆዝም …
እንዲያ ነው አይዋ
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
ኧረ ስከን ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

05 Nov, 07:03


MAJOR COMBO

REWARD ሚለው ጋ ገብታቹ durov puzzle ሚለውን ነክታቹ ምስሉ ላይ ባለው በቁጥሮችሁ ቅደም ተከተል ስሩት።

📹Major Video Code
#1 :
070624
#4 : 159390
#6: 241086

ያልጀመራችሁ 👇👇👇👇👇

🔗LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

04 Nov, 14:28


🟡 በ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

04 Nov, 14:23


👌ለዩንቨርሲቲ ና  ለ ሃይስኩል  ተማሪዎች   ብቻ የተከፈተ በኢትዮጲያ የመጀመሪያው ቻናሎች ❤️❤️

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

04 Nov, 06:17


ይኧው ከመቅፅበት

ሁለት ሚስኪን ጥንዶች
ጊዜ ያጣመራቸው
ጨዋታ ቀልዳቀልድ
ቃል ያገናኛቸው
ለመታመን ብለው
ለነገ ፍቅራቸው
መፅሀፍ ቅዱስ ይዘው
ሲምሉ ባያቸው
ካንተ ውጭ ካንች ውጭ
ብለው ቃል ሲገቡ
ሲማማሉ አይቼ
ሁኔታቸው ገርሞኝ
መብላት አምሮኝ
ነበር ፍርፍር ወጥ ሰርቼ

ፈጣሪ ከዙፋን
ሰማይና ምድርን
በቃሉ ቢያፀናም
በቃላት እስትንፋስ
ጎባጣ ቢያቀናም
በፍጡር ህግ ግን
ቃል ፍቅር አይሰራም

ሌላ ሄዋን ሲመኝ ሲሆን አመንዝራ
ፍቅሩን ችላ ብሎ መሀላ ከፈራ

ሌላ ገላ ሲሻ ቃሉ ከመለሰው
ቃል አክባሪ ሳይሆን
ፈሪ ነው ይኧ ሰው

እናም የአዳም ዘር ሆይ
ከፍጥረት ተመራጭ
ሄዋን ውዷ እህቴ
የአዳም አጥንት ፍላጭ
የፍቅ'ር ልኬቱን ከጌታ ተማሩ
ሰሙን ብቻ ሳይሆን
ቅኔም አመስጥሩ
ልክ እንደ ክርስቶስ
ፍቅርን በፍቅር እንጅ
በቃል አትጀምሩ

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Nov, 12:17


Grass Airdrop Stage 2 ጀምሯል በተለይ Stage 1 ያመለጣችሁ ይህን አትለፉት በጣም አሪፍ ነው። አሁን ላይ 1grass = $1.8 ነው አትዘናጉ።

ለመጀመር እነዚህን step ተከተሉ

Recommended Device : PC ( በስልክ አልሞከርኩትም ግን ይሰራል ተብያለው የሚሰጠው Point አነስ ያለ ቢሆንም )

1. በመጀመሪያ በዚህ ሊንክ ግቡ👇

🔗 LINK

2. በመቀጠል የሚጠይቃችሁን Information በማስገባት አካውንት ክፈቱ ( 🔗 Referral Code ከጠየቀ👉 pvz6iP8LbxU3b_7 አስገቡ )

3. ከዛም ባስገባችሁት Email Verification ይላካል እሱን ሄዳችሁ ንኩት እና Verify ሲያደርግ LOGIN ብላችሁት ቅድም ያስገባችሁትን Information በማስገባት Access My Account በሉት

4. በPC ከከፈታችሁት እዛው Grass Node እንድታወርዱ ያመጣላችኋል software አውረወዱት።

5. ካወረዳችሁት በኃል አካውንት Login በሉ እና On አድርጉት የሚጠይቀውን Permission ስጡት

ጨረሳችሁ ሶፍትዌሩ እስካለ ድረስ እናንተ ሌላ ነገር ብትጠቀሙም Point ይሰጣችኋል ዋናው ነገር Internet Connected መሆኑ ነው።

#TIP= PC ሲሆን Point 2 እጥፍ ነው
በስልክ ከሆነ ደግሞ 1 ነው ሚሰጣችሁ ሰለዚህ በPC ብትጠቀሙ እመክራለሁ።

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Nov, 11:36


ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

እፈራለሁ እንዳልነገርሽ የውስጤን ውስጥ ጉዳጉዱን
እንዳትርቅህ የሚል ሃሳብ አሳሰበኝ እግዞ ስንቱን
ይበላኛል ንዴት ስሬን
አይታከክ እንዳላከው
ምን ስትይኝ ፈዛዛ ሆንኩ
ንፁህ ልቤን የባረከው
እቀናለሁ ሳይሽ ደግሞ
ሆኖ አንገትሽ ሌላ ዘንዳ
እህትህ ናት ይላል ልቤ
አካል ስጋ ሆኖ ባዳ
ጉደኛ ነኝ ኧረ እኔማ
ጉዴ ገና ያላለቀ
ጓደኛ ነን በሚል ሰበብ
እሳት ፍቅሬ ያልተወቀ
አልታጠኩም የድፍረት ሻሽ
ለመናገር የፍቅሬን ቃል
ይነደዋል የዋህ ሆዴ
ጥርሴ ደግሞ ስንቴ ይስቃል
ሲያወሩሽ ባያቸው እንደው የድንገቱን
    አሳሰበኝ እግዚኦ ስንቱን።

ጓደኝነት ይዞኝ
ቃል ሆኖኝ ሰንሰለት
እንዴት እንደሚከብድ አፈቀርኩሽ ማለት!

ዮኒ
    ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

03 Nov, 09:15


Paws ገና ካሁኑ ወደ BYBIT

paw farming

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

02 Nov, 12:15


ማሰብ ከሌለበት ፥ ዓለም እስኪበተን ፣
መሰብሰብ እስኪገባን ፥ በደንብ እንበተን ፣

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

02 Nov, 10:07


PAWS Farming

paw farming
ቦቱ እራሱ ከዚህ በፊት ተሳትፋችሁ በነበሩት ፕሮጀክቶች ( Notcoin ፣ DOGS ፣ HAMSTER ) እና ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበትን ጊዜ በማስላት ለእያንዳንዱ ስራ ነጥብ ይሰጣችኋል::ከዚህ በተጨማሪ ሰውን መጋበዝ እና Task በመስራት ማግኘት ትችላላችሁ።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

02 Nov, 07:51


ሀገርን የሚያምሰው:
ከሆነ እንደ'ኔ ሰው፣

እጄን በመጠቆም—
እሱ ነው አልልም፡
ሀገርን 'ሚገድለው—
አዎ ከእኔ አይዘልም።

ስለዚህ . . .
በማንም ላይ አልፈርድ—
ልመልከት ራሴን፡
ምሮ ስላኖረኝ—
አልከስም ንጉሤን!

መኩሪያ ሙ እንደጻፈው

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Nov, 18:07


#እሱ እና #እሷ

#እሱ .   .   .
ብትበዪ ፍርፍር
ሥጋሽ ቢወፍር
ብታደርጊ ወርቅ
አየሽኝ እንደ ጨርቅ

#እሷ .   .   .
ታድያ ምን ችግር?
አትበልብኝ ግርግር
ፍርፍር ብበላ  . . .
ሥጋዬ ወፍሮ ቢተላ
ቢኖረኝ ወርቅ
ባደርግህም ጨርቅ
አታስወራኝ ክፉ ክፉ
ትዝብት ነው ደግሞ ትርፉ

#እሱ .   .   .
"ምን ችግር" አትበዪኝ
በግራ ዓይን ተይ አትዪኝ
የኖርናቸው ጊዜያቶች
ያ'ረግናቸው ውብ ክስተቶች
አስቢያቸው ቆም ብለሽ
ከ'ኔ'ጋ' እኮ ትዝታ አለሽ

#እሷ .   .   .
አታስታውሰኝ ያንን ጊዜ
ያየሁበት ጠፍቶ ወዜ
መልኬ ጠፍቶ አንተን መሰልኩ
ከእሳት ከሰል እኔ ከሰልኩ
ያንን ጊዜ ተው አታንሣው
እባክህን ይሄን እርሳው

#እሱ .   .   .
በጊዜ ላይ ሰበብ - ለምን ታደርጊያለሽ?
ያንን ጊዜ ባይኖር መቼ ትኖሪያለሽ?
ይልቅስ ችግሩ ጊዜን አታድርጊ
ባይሆን ይኸው እንደዚህ አድርጊ
ዓይንሽን ልየው - ነይ ከቦታችን
እንግደለው ትዝታችን
ገጥመን አፍ ካ'ፋችን

#እሷ .   .   .
እባክህን ተወኝ ልቤ ልብ ገዝቷል
ያለፈውን ታሪክ በሙሉ ረስቷል
በጻፍክልኝ ቁጥር ድንግጥ ይላል ልቤ
በፈጠረህ ተወኝ ልኑረው ሐሳቤ

#እሱ .   .   . (ለራሱ)
ብትሄድ እኔን ጥላ
ብታለቅስ እሱን ብላ
ለምን ጨርቅ ልሁን - ለምንስ ልጠላ?
ብታንቋሽሸኝም ቅስሜን ብትሰብረው
ክፉ አይወጣኝም-እኔም ዝም ልበል ሐሳቤን ልኑረው!!

መኩሪያ ሙ እንደጻፈው

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

01 Nov, 14:00


እግዜር ግን ታያለህ
እውነት አይን አለህ

እግዜር ታደምጣለህ
እውነት ጆሮ አለህ

እስኪ አይን ካለህ...
ተመልከት ተመልከት ያለብንን ዕዳ
እውነት ካደመጥክስ የለቅሶውን ፍዳ
እንዴት አታዝንም ወይ?
......ሀገር...... እንዲ ታርዳ ?
.
.
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

31 Oct, 16:39


PAWS Farming

paw farming
ቦቱ እራሱ ከዚህ በፊት ተሳትፋችሁ በነበሩት ፕሮጀክቶች ( Notcoin ፣ DOGS ፣ HAMSTER ) እና ቴሌግራም ላይ የቆያችሁበትን ጊዜ በማስላት ለእያንዳንዱ ስራ ነጥብ ይሰጣችኋል::ከዚህ በተጨማሪ ሰውን መጋበዝ እና Task በመስራት ማግኘት ትችላላችሁ።

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

31 Oct, 11:07


ጎልልልልልልልልል ክርስትያኖኖኖኖኖ

ሮናልዶ በሳውዲ ሊግ ላይ ተገልብጦ ያስቆጠራትን ድንቅ ጎል ይመልከቱ 👇👇

https://t.me/addlist/UbA-kbT9Nk0yOWI0

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

31 Oct, 10:48


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

31 Oct, 07:55


አንቺን ነበር የፈለኩት
ላንቺ ነበር የተሳልኩት

ወይ አለችኝ ህልም ብላ
ጋኔል አለች ጨለም ብላ
መቼ ሰማች ወይብላ

የጠራናት ከአመት ቁስል
ሞተን ቆየን መጣሁ ስትል

ደከምኩኝ እስካለሽ
ተብከነከንኩ በየአፍ
ይቅናህ በይኝ እንዳገኝሽ
አልደረስኩም ስንቱን ባልፍ

ደሜን ማነው ያባከነው
ሞቴን ብቻ ሚመነዝር
አንቺን ከእኔ እያራቁ
ቃሉን ደግመው የሚያሰምር
ማነው አንቺን የሚያፈቅር ?
ማነው አንቺን አምኖ ሚያድር
ማነው ላንቺ የሚሰክር ?

ከእኔ ብቻ ዕንባ ዕንባ
ከእኔ ሌላ ህመም አለ?
ወይ'ብላም አጠራኝም
ኮሶ ብቻ መድን ካለ

ኑሮሽን እንድሸከም
ወንድሞቼን ፈለኳቸው
ተከዜ ላይ ጎርፉን ሆነው
ወድቀው ነው ያየኋቸው

ሶስት አይን ጥቁር ያላት
ሀዘን ጫንቃ የበዛባት
ይቺ ሀገር ሀገር ሳትሆን
የሲኦል በር ማለፊያ ናት !

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Oct, 12:32


ስለማልችል ነው ....

ክብሬን እየተነካ መሳቅ ፤ መቀራረብን ለማሳየት ለበጣ እና ስድብ አልታገስም ።

የሆነ የስራ እድል አለ ብዬ ፣ የሆነ ጥቅም ስለሚገኝ የሆነ ትልቅ ደረጃ ያለ ሰው ስለሆነ ብዬ በማልወደው መንገድ ሲያወራኝ ደስ እንዳለኝ መሆን አልችልም ።

የሆነ ሰው ደስ እንዲለው ብዬ የማላምንበት ጉዳይ እንዳመንኩ ሆኜ ስተውን መዋል አልችልም ፤ ፋራ ላለመባል አራዳ ለመምሰል ያውቃል እንድባል በሰው የጣዕም ልኬት ስንሸራሸር መዋል አልችልም !!

በነገ ተስፋ መቁረጥ ፣ለማደግ አለመጣር የተሻለ አለመመኘት ፣ለመማር ዝግጁ አለመሆን አልችለም!!

ባለኝ አለመደሰት አመስጋኝ አለመሆን ፤እሚወዱኝን ጨዋ ሰዎች አለመውደድ አልችልም !!

ራሱን ከማያከብር ጋ እይታዬን ከማያከብር ጋ መወዳጀት አልችልም !!

አንዳንድ አለመቻሎች ደስስስ ይላሉ

© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

30 Oct, 08:14


DOGS 🤝 PAWS 👣

DOGS ላመለጠመቹ እንዲሁም ትንሽ ለሰራቹ ኤና በሰራው ብላቹ ለምትቆጩ ሁለተኛ እድል መቷል ይሄ እንዳያመልጣቹ PAWS ይባላል ሊንክ 🫵👇

paw farming

ለመጀመር 👇👇👇

🔗 Link

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

29 Oct, 06:44


ድንገት ጭር ያለ ቦታ ሳለሁ ብዙ ምልክት ሳያሳይ ወይ እኔ ሳላስተውለው አላቅም ብቻ ዶፍ ዝናቡን ለቀቀው ። የቱም ቦታ የታየኝ መጠለያ አልነበረም ።

በቅርቡ ወለም ያለኝ እግሬ መሮጥ ስላላስቻለኝ በተቻለኝ መጠን ለመራመድ ሞከርኩ

በቲሸርት መሆኔን ፣ መራመድ አለመቻሌን ከምንም ሳይቆጥር ዝናቡ ያለርህራዬ ቀጠቀጠኝ

አለቀስኩ ......።

ደብሮኝ ነበራ!!!

አጥንትን የሚፍቅ ድብርት ውስጥ ነበርኳ ፣ ማንም ሊያድነኝ ከማይችል ዱካክ ውስጥ ነበርኳ

በችግር ውስጥ ማለፍ ፣ በችግር ማደግ የሚያስተምረው ችግር ሲመጣ አለመቸገርን አይደለም ችግሩ እንደሚያልፍ መረዳትን እንጂ !

የጠዋት ፀሃይ ውስጥ ተስፋ ማየት እያቆምኩ ነበር ፣ የምሰማው ነገር ሁሉ አልጥም ስላለኝ ማንንም ላለመስማት ከብቻዬ ጋ ብቻ ለመሆን እየታገልኩ ነበር ...

በዚህ ሁኔታዬ ዝናቡ ሲቀጠቅጠኝ ሆድ ባሰኝ ፤ አለም ላይ ሁሉም ሊያጠቃኝ የተዘጋጀሁ የመስዋዕት በግ የሆንኩ መሰለኝ ።

ዝናቡ እያባራ መጣ ፣ እምባዬም እየደረቀ ሄደ

ከዛ ዶፍ ዝናብ በኋላ
መጠለያ ከማጣት በኋላ
ሁኔታዬን ሳያገናዝብ ከቀጠቀጠኝ በኋላ
ከአለ'ማንም አይዞህ ባይ ከተደበደብኩኝ በኋላ

ዝናቡ ቀጥ አለ!!!

በማያሳምን ፍጥነት ፀሃይ ወጣች ። የፀሀይ አወጣጧ የተደበደበው ልብሴን እንደሚያደርቀው ፣ የበረደው አካሌን እንደሚያሞቀው ተስፋ ሰጠኝ ።

ከዶፎ ዝናብ ቀጥሎ የወጣችው ፀሃይ ሳያት የሆነ ሚስጥር እንደነገረቺኝ አይነት ፈገግ አልኩ ።

ፀሃዬ
© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

28 Oct, 16:06


🩵 ፍጠኑ Bitget Wallet በቴሌግራም Lite Version ለቀዋልል ቀድመው ለተመዘገቡ 1M ሰዎችም ሽልማት አለ እያለ ነው ጥቂት ሰው ነው የቀረው ሳይሞላ ተመዝገቡ 🔥

🔗በመጀመሪያ በዚህ ሊንክ ግቡ👇
https://t.me/BitgetWallet_TGBot/BGW?startapp=sharetask-SPNMEEKHq1s47pW

First 1,000,000 only! Clicking this link guarantees your qualification.

First come, first served, do not wait!

Join me on Bitget Wallet Lite now!

✅️ በመቀጠል Agree በሉት እና Create Account ብላችሁት አካውንት ክፈቱ

✅️ Pin አስገቡለት

✔️ ጨረሳችሁ አሁን ሰው መጋበዝም ትችላላችሁ ✌️

⚠️ SRP መያዝ እንዳትረሱ ( Setting ውስጥ Export Mnemonic የሚል አለ እሱን ስትነኩት Word ያመጣላችኋል እሱን ፅፋችሁ ያዙት )

🔥 ፍጠኑ ከ700k ያነሰ ሰው ነው የቀረው 🔥

Credit MullerApp

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Oct, 17:20


ሰፈራችን ቢራ ቤት አለ ሸምገል ያሉ ጃኬት ሹራብ ያደረጉ ጠና ያሉ ሰዎች በረንዳ ላይ እየጠጡ ቁጭ ብለው ያወጋሉ ...

እኛ ከትምህርት መልስ ኳስ እንጫወታለን !

ሰፈራችን ቤርጎ አለ ጥንዶች ተቃቅፈው ተረጋግተው እያወጉ እየተሳሳሙ እየተሽኮራመሙ ፣ አልጋቤት ገብተው ይወጣሉ እኛ እርግጫ ላይ ስለምንሆን ወይ ሲገቡ ወይ ሲወጡ እናያቸዋለን ፦

እቤት ስንገባ ታላላቆቻችን ዜና ጓጉተው ያያሉ ይወያያሉ ዜናውን እያዩ ትክዝ ግርም ይላቸዋል ፦

"ዜና አሁን ምኑ ይታያል ?"
ይላል ልጅነታችን

እኛ ድራማ ፣ፊልም፣ Wrestling ፣ታላቅ ፊልም፣ኳስ፣ ህብረት ትርኢት ለማየት እንጠብቃለን ።

እንቅልፍ አሸንፎ ካልጣለን ፦

ማታ ያየነውን ከጓደኞቻችን ጋ እንቀዳለን ።

"እከሌ እከሌን ወደደ ፣ እከሌ እከሌን ካደችው፣ ካዳት ፣አስረገዛት ፣እከሌና እከሌ ተጋቡ፣ ወለዱ" ብለው ያወራሉ እንሰማለን ብዙ ትርጉም አይሰጠንም ።

እኛ ትርጉም የሚሰጠን ኳስ ፣ እርግጫ ፣ብይ፣ቆርኪ ፣ ሌባ እና ፖሊስ ፣ቃጤ ቃጤ ፣ በረዶ ፣ጠጠር ፣ ሱዚ.... ነበር

ስጋታችን እዛ ሰፈር የተጣላነው ትንሽ ልጅ ፣ በቴስታ የሚማታው ጓደኛችን ፣እምትቧጨረው ጓደኛችን ፣ እዚ ጋ አትጫወቱ የሚሉት ሴትዮ ፣ "ሲጫወቱ አጥሬን መቱብኝ "ብሎ ለቤተሰብ የሚከሰን ሰውዬ ... ጨዋታ አትጫወቱም አጥኑ የሚል የቤተሰብ ክልከላእና ጡጫ ፣ ለበዓል የሚገዛልን ልብስ ....

እምንፈራው በተረት የሰማነው አያ ጅቦ ..ስጋታችን በጨለማ ለሽንት ስንወጣ የምንሰማው ኮቴ ነበር
ማደግ ያጓጓንም ነበር ።

አደግን ፦

መጠጥን ቀመስነው ...
ቤርጎውን አየነው ...
ዜናውን ተራቆትንበት ...
ተካካድን ....

የማናቀው ነገ አስፋራን ፣ ማደጋችን አስደነገጠን ፣ ትልቅ ሰውዬ ነው ያልነው ሰው እድሜ የኛ ሆነ።

ልጅ ሆነን የምናዉቀው አለም ተቀየረ !!
© Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Oct, 14:13


አርሰናል ከ ሊቨርፑል የሚያደርጉትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ በ ነፃ በስልኮዎ ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ(JOIN) የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉ አሁኑኑ እንዳያመልጥዎ 👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Oct, 14:00


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Oct, 13:52


ምን አይነት ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?😱😱😱😱😱😱😱😱😱👇👇👇

▶️የቱርክ ፊልም    JOIN 👈 ይንኩ

▶️የአሜሪካ ፊልም   JOIN 👈 ይንኩ

▶️ የህንድ ፊልም     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የቻይና ፊልም      JOIN 👈 ይንኩ

▶️የአማርኛ ፊልም      JOIN 👈 ይንኩ

▶️ተከታታይ ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️ አኒሜሽን ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️አክሽን ፊልሞች     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የጫካ ፊልሞች     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የፍቅር ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️የsex ፊልሞች    JOIN  👈  ይንኩ

እንደ ምርጫው መርጦ ይቀላቀሉ

                    JOIN

ይቀላቀሉ                        ይቀላቀሉ

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

27 Oct, 11:38


ሲሸሹኝ ስጎትት ሲርቁኝ ስጣራ፤
ሲሄዱ ስከተል ሲዘጉኝ ሳወራ።

አሁንስ ዝም አልኩኝ ልቤን ደካከመው፤
ሁለት እየሆነ አንድ ነው ያልኩት ሰው።

ብቻ በመንገዴ፥

ከነሳቸው ሠላም ከነሳቸው ጤና እኔ መከተሌ፤
ለበደለኝ ሁሉ ለበደልኩት ሁሉ ይቅርታ ነው ቃሌ።

ሄጃለሁ ከእንግዲህ በቃ ለልከተል🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️

ጦቢያ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Oct, 08:50


እንደልጅ ኩርፊያዋን ትረሳልኛለች፣ ትስቅልኛለች፣
እንደ ልጅ ነው የምታምነኝ፤ ስታምነኝ እንቅፋት መቷት የምታውቅ አትመስልም ፣ የትም ቦታ ነይ ስላት ትመጣልኛለች፤ እሺ አባባሏ ካንተ ጋ ከሆነ የትስ ቢሆን
የሚል ይመስለኛል ።

ህልሜን ስነግራት አሰማሟ እረፍት ይሰጣል ፣ አይኗ ላይ ያለው መውደድ ያበረታኛል ።

እወድሻለሁ ስላት እንዴት የማላውቀውን ነገርከኝ፤ ብላ የደስታ ፈገግታ ያበራውን ፊት ታሳየኛለች

ፍቅር ያበረታል
Adhanom Mitiku

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Oct, 08:32


Blum drop game ላይ የ$DOGS drop አሁን ላይ ጀምሯል Check አድርጉ።

ያልጀመራችሁ

👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

26 Oct, 05:45


ተራምደን ያለፍነው

ንጉስ ነው ሚዘከር
ቢወድቅም ወታደር
መቼ ይታወሳል
ታሪክ እየለየ ፥ መርጦ ያስታውሳል

ስንሄድ ስንመለስ ፥ እግራችን ሲያዘግም
ተራምደን ያለፍነው ፥ ማን ይሁን አናውቅም
ታሪክ ያልዘከረው ፥ ያልተጠራ በስም
አለ የተረሳ ፥ የማይታወስ አፅም

አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

25 Oct, 14:42


◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

25 Oct, 14:23


Car for Sell
Make: Toyota
Model: Corolla
Year: 2004/8
Gear shift: Automatic
Steering: Original left hand
Milage: 174000+
Color: Dark silver
Condition: Excellent
Plate: 2 B 64***
Motor: Super excellent
Price: 2.5 million

0911468394
@abela1987

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

25 Oct, 13:32


በ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

25 Oct, 13:20


እድሜዎ ስንት ነው?

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

24 Oct, 13:57


X Empire ካመለጣችሁ እነዚህን 5 projects ስሩ። የራሳቸው የ x empire ናቸው በደንብ ስሩ። Daily combo የምንለቅላችሁ ይሆናል።

1. Hrum
🔗 links

2. Staff only
🔗 links

3. Dogiators
🔗 links

4. Memes Lab
🔗 links

5. MEMEME
🔗 links

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

24 Oct, 08:34


ነገራችን ሁሉ እንዲሁ ከሆነ ሰነባብቷል።

ለምን እዚህጋ እንደቆምን አናውቀውም። ለምን ይሄን መንገድ መረጣችሁ ብንባል መልስ የለንም። እንደከፋን እንጂ ምን እንዳስከፋን አናውቅም። ምን እንዳስለቀሰን ፤ ምን አንጀታችንን እንደቆረጠው ፤ ምን ልባችንን እንደሰበረው ብንጠየቅ አብረን ራሳችንን ከመጠየቅ የዘለለ ነገር አናረግም ግን የሆነ ቀን ከተኛንበት ስንነቃ እንባችን እየፈሰሰ ልባችን ከእኛ ተነጥሎ ከአለምጋ እየታገለ እናገኘዋለን። እንዲሁ ደብሮናል። ለምን? መልስ የለንም  እንዲሁ ስቀናል ከአፍታ በኋላ ምን ነበር ያሳቃችሁ ብንል መልስ የለንም። ቅጽበትን መኖር ተለማምደናል። ምሳ ሰአት ላይ ቆመን ጠዋታችንን ትዝታ ምሽታችንን የማይደረስበት ህልም አርገን እንስለዋለን። ችግር ሲያጋጥመን ከመታገል ፋንታ መላመድን እንመርጣለን። በችጋራችን እንቀልዳለን እንስቃለን። አዲስ ግኝት አይሞቀንም። ጭካኔ ስንሰማ አይበርደንም። አፋችን የሚደሰኩረውን ያህል የፈጣሪ ቁጣ አያስፈራንም። እንዲሁ የምንወደውና የምንጠላው ይበዛል። ምክንያት ዋጋ አያወጣም። ይቺ በየመሀሉ ነጭ ጸጉር ያላት ሴትዮ እንዲሁ ታስጠላናለች። ያ መላጣው ሰውየ እንዲሁ ደስ ይለናል። ለሰው ብለን የምንኖር ይመስለናል። እኔኮ ለእናቴ ብየ እንጂ  ለአባቴ ብየ እንጄ ለትንሿ ልጄ ተስፋ ብየ እንጂ የሚሉ ሀረጎች ከአፋችን አይጠፉም። እነዚህ ሰዎች ባይኖሩ ተጽዕኖ ባይኖራቸው ነጻነት የሚባል ነገር ቢኖር(እንደው ምናልባት ቢኖር) ምን እንደምንሆን አናውቅም። አንዳንዴ ከራሳችን ፍላጎትና የህይወት ትግል ማምለጫ ሰበብ አርገን የምናቀርባቸው ነው የሚመስሉት። እንዲሁ እያምታቱ መኖር። እንዲሁ ተነስቶ እንዲሁ ውሎ እንዲሁ መተኛት። አለን! ሆኗል ቋንቋችን  ደህና ነህ ደህና ነሽ? አለሁ!  መኖር ይበቃል ደህንነቱማ ቅንጦት ነው ይመስላል መልሳችን። መኖርማ አለን  ኖረን ታይተን አይደል የምንጠየቀውስ?

እንዲሁ ነው ኑሯችን። የምንፈልገው ነገር ዋጋ የሚያስከፍል ከሆነ ከመታገል ይልቅ የምንፈልገውን ማቃለል መፍትሄ ይመስለናል። ድንገት ታዋቂ ሲያሻን ከመሬት ተነስተን ሀብታም መሆን ያምረናል። መንገዱን ማለፍ ግን አንፈልግም። እንዲሁ ብንሆን ደስታችን ነው። ሰዎች የሚነግሩንን ነገር ሳይነግሩንም እናውቀው ነበር ግን አሃ! ብለን መስማት ለምደናል። ጥፋት እንዳጠፋን አውቀነውም ከሚመክሩን ይልቅ ጥፋታችንን ቢችሉ ቢያግዙልን ካልሆነም ቢያለባብሱልን ደስ ይለናል። ምክንያት አንወድም። ምንም የተለየ ነገር ሳናረግ እንዲሁ መመስገን እንዲሁ ጎበዝ መባል እንዲሁ ማደግ ያምረናል።

የሰው ልጅ የሚያስበውን ፣ ለራሱ ነኝ የሚለውን ያህል ነፃ አደለም ይላል ስሙ አሁን ትዝ ያላለኝ ደራሲ። አሁን የመሰለንን ብቻ መኖር ያሻናል። ጠዋት የሳቀው ከሰአት ደብቶት ይገኛል። ሲነቃ የበረታው ሲተኛ የአለምን ጓዝ ብቻውን ተሸክሞ የዋለ ይመስል ፣ የአለምን ጭንቀት ለግሉ ሹክ የተባለ ይመስል ወኔው ከስምኖ ብርታቱን አጥቶ ጎብጦ ይገኛል። ከምኔው አድገን ተመክረን ጨርሰን መካሪ እንደሆንን ያስደንቃል። ሁሉም የአለም ዋናውን ሚስጥር ልንገራችሁ ባይ ሆኗል (እሱ ካወቀው ምኑን ሚስጥር ሆነውና ሲጀመር።)

ሳንሮጥ የሚደክመን ፍጥረቶች! አቅማችንን ምን ሰለበው? ምን አዳከመን? እንዲሁ ኖሮ ማለፍን በቂ አርገን እንድንመርጥ ያስደረገን ምንድን ነው? ከመቼ ጀምሮ ነው እንዲሁ እንደመጣን እንዲሁ ሹክክ ብለን መመለስን በቂ አርገን ያየነው?
በቃ ሁሉንም እንዲሁ!


(እንዲሀ ጻፈው ጻፈው ብሎኝ ነው😁)


          በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

24 Oct, 03:55


እምክ እምክ ይላል ማፍቀሬ ታፍኖ፣
ሌላው ሲተነፍስ የኔ እድል ሆኖ።
እድሜሽ እንዳይመክን ሳልጠፋ ሳታጪኝ፣
አፌን እስክፈታ አግብተሽ ጠብቂኝ። 🙄 (የሞገሤ ልጅ)

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

23 Oct, 16:55


ፍረዱኝ

እሽሽሽ
ዝምታ
አንዴ ዝም በሉ አትንጫጩ በቃ
ከጎኑ የሚቆም ባይገዛም ጠበቃ
ፀሀፊ ልማዱ ነው ይወዳል ጨረቃ
እኔ ዝምተኛው
በውስጥ ወሬኛዎች
ሰላሜን ስላጣሁ
ፍረዱኝ በማለት
ወደ እናንተ መጣሁ

" ትናንት የነበረው
ሁሉም ተቀይሯል
የአሜሪካ ዶላር
በእጥፍ ተመንዝሯል
ሰላም እና ፍቅር
ከሀገር ተሰውሯል
ስንቱ እሯጭ ጀግና
እግሮቹን ተሰብሯል
ቤት አልባው ገጣሚ
በብሔሩ ታጥሯል
ነፃ አውጭው ግለሰብ
ወህኒ ተወርውሯል

ትናንት የሀገር ዋልታ የተባለ ቡድን
አሸባሪ ተብሎ እያየህ ሲታደን

እጆቿን ወደ ላይ በምትዘረጋ ሀገር
ሆደ እንስፍስፍ እናት ሆዷ ሲተረተር
አርሶ አጉራሹ አባት 'ንደወጣ ሲቀር
ስንቱ ሚስኪን ዜጋ
በጅምላ ሲቀበር
እልፍ ጨቅላ ህፃን
ታርዶ ሲወረወር
ቆመህ እየታዘብህ
ሁሉም ሲቀያየር
አንተ ማን ሆነህ ነው
ደፍረህ ማትናገር?"

የሚለኝ ሲበዛ በ inbox ብራና
እኔም ለመቀ'የር ወስኛለሁ እና

ከፅሁፍ በዘለለ
በድምፅ ልገማሸር
በጥብቅ ስለወሰንሁ
ዝምታየን ልሽር
እናንተም ፍረዱ
በድምፅ ልምጣ ልቅር?

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

23 Oct, 14:11


Lenovo LP19 headset
Lenovo LP19 Wireless Bluetooth Earphone
HIFI Stereo
Waterproof
Intelligent Noise Canceling
Bluetooth 5.1 Technology
Superior Sound Quality
Designed with an elegant and compact profile, easy to carry and perfect for on-the-go use.
Active Noise Cancellation
Long-Lasting Battery: the 230mAh capacity of charging case can fully charge 2 earphones around 5 times, offer more 5-6 Hours music time

2800 birr

0911468394
@abela1987

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

23 Oct, 12:08


ምታሳሳ መኳንንት ዘር የነበረች
ለሚያያት በጭንቅ ሀሳብ የታጠረች ፤

እዝን ትክዝ ካለችበት ቀና ብላ
መቀነቷን እያሰረች እንዳይላላ
አፈር ስትጭር የያዘችውን አንድ ስንጥር
ከእጇ ላይ እየጣለች

እንዲህ አለች ...

«የመኖር ሰይፉ ይሰለቅጣል
የዛሬ ጅራፍ አርባ ይገርፋል
ሆኖም
“ሰለቸን” ብንል አይለወጥም
የመሰልቸት ስለት ተስፋ አይቆርጥም።

ብቻ
የዕድሜ ዛቻ
የጊዜ ጡጫ ፋታ ቢያሳጣም
ሕልም ሲቸክ ወልቆ አይሰጣም።

አንዳንዴ ፣ የተስፋ ጡንቻ እየፈረጠመ
ሌላ ጊዜ ፣ የተስፋ መቁረጫዉ እየዶለዶመ
የመቁረጥ አቅሙ ስለደከመ

መቁረጥ ሲቃጣን
ሠይፉን ስላጣን
እናልማለን።

ልኩን ማየት እያባባን
እምቢኝ ስለን እያነባን
ተስፋ እናደርጋለን።

ተስፋ ለመተው ምን አቅም አለን?!
በሕይወት እስካለን ፣
ምርጫ ስሌለን እንበረታለን ።

አሁን ልህድ! »

12 — 2 — 2016 ዓ.ም !
De morte !

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

22 Oct, 04:50


""
ተወው አትጨነቅ
ለአለም እልፍ ጓዝ፣
ይልቁን ተጠንቀቅ
ለራስህ ስትጓዝ፣

አይተህ ስትዝናና
የምድርን ስፋት፣
ችላ ያልከው ጠጠር
እንዳይሆን እንቅፋት!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

20 Oct, 17:56


አባትሽ የህግ አዋቂ ለምስኪን አዛኝ ጠበቃ
እናትሽ ዳኛ ሲሆኑ ድርሻየን አወቅኩት በቃ

ደጃቸው ተመላልሼ ሳስቸግር ስላዘኑብኝ
እስኪ አንተም
ቅመሰው ብለው አንቺን ነው የሚፈርዱብኝ


በአቤኒ

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

20 Oct, 13:01


እንደ ጤዛ ሲረግፍ ፥ ውበቱ
በእድሜ እየዛለ ፥ ጉልበቱ

በሽታ እየጣለው ፥ ከአልጋው
ሞት እየጠበቀው ፥ ሥጋው

የነብሱን በጎነት ፥ ይዞ ካልተገኘ
ታድያ ምኑ ይሆን ፥ ሰውን ሰው ያሰኘ


አቤል ታደለ

ለአስተያየት : @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

20 Oct, 12:55


አዳዲስ ተከታታይ አሜሪካ ህንድ ቻይና አማርኛ ድራማዎችን አንድ ላይ ለማግኘት 👇👇👇

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

19 Oct, 07:06


እንደ ሰርከስ
(በእውቀቱ ስዩም)

መኖር በሀገርህ
የሰርከስ ትርኢት እንደማሳየት ነው
ስልጠናው ሳይኖርህ ::

በሚያድጥ ዳገት ላይ ፥በብጤህ መጋለብ
በሁለት መዳፎች፥ ሳይፎርሹ መቅለብ
-ደርዘን ሙሉ አሎሎ፥
አሎሎ ቢጠፋ ፥እሾህ ተደብልብሎ
በሳት ቀለበት ውስጥ ፥ማለፍ ሹልክ ብሎ፤

እንደ ህልም እሪታ፥ በሰለለ ገመድ
ባንድ እግር መራመድ፤

ይሄን ሁሉ አድርገህ፤ ትርኢቱም አልቆ
ካጥንቶችህ መሀል፥ አንዱ ተሰንጥቆ
አንደኛው ደንድኖ
እጅህ ወንፊት ሆኖ፤

ምንም ባትታደል፥ አንቱ የሚባል ስም
አሞጋሽ ለክብርህ፥ ነጋሪት ባይጎስም
ምናልባት ካተረፍክ-
ያልተራገፈ ጥርስ ፥ያልተሰበረ ቅስም
የድል ሳቅህን ሳቅ፥ በተረፈው ጥርስህ
በወንፊት መዳፍህ፥ አጨብጭብ ለራስህ::

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

18 Oct, 14:13


እንዲህ ነኝ
ለመኖር ነው እንጅ
ኗሪ ነው ለመባል እኔ ኖሬ አላቅም
ለሚገ'ባው እንጅ
ለማንም አድር ባይ ቦታየን አለቅም
ላዝናናኝ ነው እንጅ
ለቀለደ ሁሉ ለይምሰል አልስቅም
በአስተሳሰቡ እንጁ
በልብሱ ለክቼ አዳምን አልንቅም
ችግር ካሰቃየኝ
ከሰረቀ እንጅ ከሚሰራ አልሰርቅም
ለራበው ለማጉረስ
እጆቼን ሰድጀ ከለማኝ አልነጥቅም
በፍቅር ካልሆነ
ስሜት አሸንፎኝ ሱሪን አላወልቅም
ቤቴን ሳላሳምር
ለውዳሴብየ አጥሬን አላጠብቅም
በላይ ዝምተኛው
የራሴን ካልሆነ
የእድለኛን እጣ ተደብቄ አልፍቅም
ደሞ ጉረኛ በሉኝ😡😡😡

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

18 Oct, 11:30


እስቲ ልመርቅሽ
        እስቲ ደሞ ልጣሽ
የልብሽን አይቶ እግዜር ከኔ ያውጣሽ
.


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

17 Oct, 07:19


BLUM premarket price on Gateio Exchange.

ያልጀመራችሁ

👇

🔗 LINK

@DropGenius1

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

16 Oct, 18:22


አምና ችየ ባርሰው አረም በቀለበት
ዘንድሮ ብደግመው ተባይ ሰፈረበት
የከርሞን ግን እንጃ
ሌቴን የሚያጋፋኝ ህልሜም ጥሎኝ ሄደ
የኔ ሲጠብበት ሌላ አልጋ ለመደ!

ብሶት ይሰማኛል ህመም የወለደው
መገፋት ብርቁ ነው ፍቅር ለለመደው

ቤቱን አያሳየን
ልሳኑን አይፈታ ብላችሁ ብላችሁ
ይኼው ከአሁን ወዲህ
እንዳሻችሁ አርጉት ከፍቶት ሄደላችሁ!


         በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

16 Oct, 04:00


ምርቃቱ ሁሉ መርገም ለሆነበት
የኑሮ ባቡሩ ሀዲድ ለሳተበት
የመኖር ውጥንቅጥ ላስደፋው አንገቱን
ማጣት ጥርስ አውጥቶ ላጠፈው አንጀቱን
አለም ዘጠኝ ሆና አልፎለት ላላየ
መኖር እንዲጥመው ባንቺ አይን በታየ!

ሰላሙ ለራቀው ውዱ ለረከሰ
የቀን ወግ ላልገባው ነገው ለፈረሰ
ለብ ያለ ፈገግታ ሙቅ ሳቅ ለናፈቀው
የብቸኝነት ቁር ብርዱ ቀልብ ላራቀው
ጉም መዝገን ለባሰው ነፍሱ እጅግ ላደፈ
ልቡ እንዲረጋጋ ምነ አንቺን ባቀፈ!

እምነትን ለመጣል ለጠፋበት ስፍራ
ውብ ነገር መሸለም መመኘት ለፈራ
ለጣፋጭ ጎምጅቶ መራር ለቀመሰ
ጉልበቱ ለሟሟ አቅሙ ለፈረሰ
ህልሙ ከቅዠቱ ለተድበሰበሰ
ፍቺውን እንዲያገኝ አንቺን በዳሰሰ!

ሰኔ ከሰኞው ጋር ለተጋጠመበት
በሀሳብ በሸክም ጫንቃው ለሞላበት
ህይወት ወደ አንዱ ጥግ አርቆ ለረሳው
የደስታ መጽሐፉ ባዶ ገጽ ለበዛው
በረጅም ለክቶ በአጭሩ ለቀረ
ሙላት እንዲታየው አንቺን ባፈቀረ!

(እኔ አልሰጥም እንጂ!!)


            በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

15 Oct, 08:45


ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
ችግር ውስጧን ሚረዳላት
ሰው ፈለገች የሚያፅናናት
የአይኗን እንባ ሚያብስላት

ለጠየኳት ጥያቄዎች
ምንም ነበር መልሰ ቃሏ
ብዙ እንደሆነች ግን
ይናገራል ፊት አካሏ

ብቻ...ዝም ብላለች

ታስታውቃለች ሆድ ብሷታል
ታስታውቃለች እንደከፋት
ቆንጆ መልኳን ተመልክቶ
ማን ይሆን ሰው ደርሶ የገፋት
ደረቅ ብሏል ውብ ከንፈሯ
አላገኘም አንዳች እህል
ቀዝቀዝ ብሏል የእጇ መዳፍ
ምን ሁናለች እቺ ጉብል

ቀና ብላ እያየችኝ
ዘረገፈች የአይኗን እንባ
ስቅስቅ ብላ አለቀሰች
ነጠላ እጇን ተከናንባ

እንዲህ ነው እያለች መናገር ባትችልም የውስጧን አውጥታ
ብዙ አውርታኛለች ከኔ ጋራ ሳለች ቃሏን በዝምታ
ይገርማል አንዳንዴ
ቃላት ሳይደረደር ምስክር ሳይጠራ ሀቀኛ ሳይለካ
ብዙ ሳንናገር በዝምታ ብቻ ቃል ይወጣል ለካ!


ዮኒ
     ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Oct, 17:11


ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ትለኛለች እንዴ ጭራሽ?

የቱን እጇን😳  እኮ የቱን
ይሄ የሚያንቅ የሚገለውን?
ይሄ የልጆቿን ራስ የሚፎክተውን?
ባዶ ጭንቅላት የሚያደማውን?
እኮ ይሄን እጅ
ይሄ ላንዱ ፍርፍር ላንዱ ጥፍር ሚያጎርሰውን? እኮ ይሄ ሴት ልጇን አንቆ ገድሎ ፍትህ ፍትህ ስትባል አፍ ላይ የምትጭነውን?
ድረሽልን ስትባል አልሰማሁም ለማለት ጆሮዋ ላይ የምታደርገውን?
እኮ ይሄን እጇን እጅ ብላ ትዘረጋለች? ጉድ!

የገዛ ልጆቿን ገድላ ገንዛ ቀብራ ገደሉብኝኮ ብላ የምትጠቁምበትን ይሄን እጅ እጅ ብላ ዘረጋችው? ምን ልታገኝ? በየቱ ግብሯ የቱን ቸሮታውን ፈልጋ?

ምን ልትቀበልበት እጅ አለኝ ብላ ዘረጋችው? ማፈሪያዋን ቁማር አስይዛ ተበላችው እንዴ? ዘንድሮኮ እንኳን ዜጎቿ እሷም ልቧ ሸፍቷል። (እንደሚወራውማ DV ሞልታለች ነው አሉ የሚባለው።) ልጆችሽን ለማን ጥለሽ ሲሏት ሲጀመር እድሌ ጠማማ ነው አይወጣልኝም እንዲሁ ዝምብየ ነው ትላለች አሉ። ድንገት ቢቀናሽስ ሲሏትም  "ፈጣሪ አለ  የተገባልኝ ቃል ለልጆቼም ይበቃል።" ትላለች ደግሞ።

እግዜሩን ሲርበን በግ መድረሻ ሲጠፋን እረኛ እያረግን ጸሎት አደበላልቀንበት በየት በኩል። ስጠን ብለነው ሊሰጠን ሲሰናዳ ይሄስ ከእኔ ይራቅ እንላለን የጠዋት ጸሎታችን እንኳን መሽቶ አርፍደንም አንደግመው  (እሱንም ከጸለይን!) ቡና መሀል "ኧረ ፈጣሪዬ አንዲት ሴት ልጅ ጨምረኝ ባክህ"  ያልነውን ሁሉ ቆጥረንኮ ነው ቀን ማታ ለመንኩት ለመንኩት ስንል የምንውለው። ከደረስንበት ደብር ካደረስነው ጸሎት በላይ እንዴት እንዳደረስን የምንናገርበት መንገድ ብዙ ነው። ጠይቄ ነሳኝ ለማለት መጣደፍ ፣ መቸኮል።  ለመፍረድ፤ ለመንቀፍ ፤  ለመመዘን ፤ ለመተረክ ፤ ለማፌዝ ፤ ለማጣጣል ስንራወጥ ስንቱን ሳትነው። ስንቶቹን ለቀልዳችን ማሳመሪያ ስንል ፣ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን ለመሳብ ለማስደነቅ ስንል ፣ ይሄ እንዴት መጣለት ለመባል ስንል ስንቶቹን አደናቀፍን? ለስንቱ የመውደቂያ ሰበብ እንቅፋቱን ራሱን ሆንን??

እጆቻችን የጨበጡት ተስፋ ስንዘረጋው እንባ ሆኖ የፈሰሰብን ፣ ከሩቅ ያለምነው ብርሃን የማይደረስበት ጨለማ የሆነብን እኛን.......     እኮ እኛን ይዛ እጇን ዘረጋች?

ማንን አቅፈሽበት ብትባልስ ምን ልትል?
ከእዚህ እጅሽ የበሉት ጠገቡልሽ ወይ?
በእዚህ እጅ የተዳሰሱት ተመቻቸው ወይ?
በእዚህ እጅ የተባበሉት ተስማማቸው ወይ ብትባልስ? በእዚህ እጅ መንገድ የተጠቆሙት የት ደረሱ ብትባልስ? ተወው በቃ  ትቼዋለሁ ብላ ያን ጥፊም ዳበሳም የሚችለውን 'አድሎኣም' እጇን አትሰበስብም?

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ይለኛል እንዴ ይሄም? እኮ ይሄ እጅ? ይሄ እጅም እጅ ሆኖ ሰውን በአምሳሉ የፈጠረ አምላክ ፊት የሚቀርብ መስዋዕት ነው? ያን ሁሉ የሰራ እጅ እንኳን ፈጣሪ ደጅ ሰይጣን ጓሮ ቢገኝ ሰይጣን ራሱ "በስመ አብ" አይልም? 

ምን አረገችህ ይሄን ያህል አትበለኝ! እጇን ዘረጋች ስልህኮ ተራራው ተነስቶ ወንዙ መንገድ ስቶ ተነጥፎ አይደለም። ወፎች መስመር ይዘው ዋልያዎች ተሰልፈውም አይደለ። የሀገር እጅኮ የእኛ እጅ ጥርቅም ነው። ይሄን እጅ እርስ በእርስ ለመተያየትስ አንፀየፈውምና ነው? እኮ!

ይሄን እጅ ይዘን አምነን ዘርግተነው አይደል ለእንባችን መታበሻ ፣ ለቁስላችን መሻሪያ ፍለጋ የምናንጋጥጠው። ጉደኛ እጆች   ጉደኛ ፍጥረቶች!

ገዳይም ሟችም አቤቱ አቤቱ የሚል ጩኸት እኩል ቢያሰሙስ? የተበደለ ፍትህን ፤ የበደለ ምህረትን እኩል በአንድ እጅ ሲልኩስ? ፍቅርን ስጠን ብሎ ቤተሰብ በበተነ እጅ መለመን የት ሊያደርስ?

መዘርጋቱንኮ ትዘርጋ ግን ትታጠበው። ሲጀመርስ በክፋት ጭቃ ፣ በነገር ደም ተለውሶ እጇ በጥላቻና በበቀል ሞልቷ ትንሽ በረከት እሱንም በእሷ ስራ ሳይሆን በእሱ በፈጣሪ ቸርነት ቢያድላት በምኗ ልትይዘው?

ኢትዮጵያ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች ትለኛለች እንዴ ደሞ?  ይሄን እጅ  የኔንና ያንቺን እጅ ተማምናኮ ነው የምትዘረጋው።  ይታይሽ እንግዲህ በእኔና በአንቺ እጅኮ ነው በረከት የሚጠበቀው...
እኔ እጅ ላይ ያለው ምንድን ነው? ቅናት ምቀኝነት ክፋት ሴሰኝነት  አንቺ እጅጋ ያለውስ ቂም ጥላቻ የበላይነት ስሜት ድንቁርና በቀል እና ይሄ እጅ እንደ ንጹህ እንደታጠነ ክቡር እቃ እንደተባረከ ስጦታ እጅ አለኝ ብላ ትዘርጋው?
እኮ ይሄን እጅ!
እኮ የኔን እጅ!
እኮ ያንቺን የአንተን እጅ!
እኮ የእኛን እጅ!

አልቀረብንም!


                 በአቤኒ የተጻፈ✒️✒️

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

14 Oct, 07:24


አታሳጣኝ ፊደል

እርዳኝ ነው የምልህ
ሳትጠራኝ በፊት ፥ እንዳገለግልህ
በጉብዝናዬ ቀን ፥ እንዳመሰግንህ

የምከፍለው ባጣም
ለውለታህ ምላሽ ፥ ዝምታ ነው በደል
ቢያንስ ማመስገኛ ፥ አታሳጣኝ ፊደል

አቤል ታደለ


ለአስተያየት @abeltadele

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Oct, 15:14


እኔ እና ሚስቴ(ከ "ሀ" እስከ "ፐ")
=====================
ክፍል 4
👇👇👇
ወድቄም አልቀረሁ
ቀና ብየ አየሁ
እርሷን ስመለከት መጥታለች ከፊቴ
አይኗን ስቃኘው አንብታለች ስንቴ
አካሌን ስዳብስ
በደም ተጨማልቋል መላ ሰውነቴ
ምን ነካህ?አለችኝ
አይኗን ጣል አድርጋ በመላ አካላቴ
እኔም
ምንም አልሆንኩ ብየ
ትቻት ሄድኩኝ ቤቴ

እቤቴ ገብቼ ተኛሁኝ ከአልጋየ
ደሜ እየፈሰሰ አየሁት ዝም ብየ
ምክንያቱን ባላቅም
ይወርዳል እንባየ
ሳገኛት ጨነቀኝ የማወራት አጣሁ
ሳጣት ናፈቀችኝ አቀርቅሬ አነባሁ
እርሷ ማናት ብየ
ልረሳትም ሞከርሁ
አልሆነም
አልሆነም
ምን ላድርግ በማለት
ውስጤ እንደጨነቀኝ
"በላይ"የሚለው ድምፅ
ከህልሜ አባነነኝ

ይህን ሁሉ መንገድ
አይኔ የፈለገ እግሬ የዳከረ
ለካ .... በእውን ሳይሆን
በህልሜ ነበረ
ከዚህ ይሰውራችሁ
ተፈፀመ!!!!!
belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Oct, 11:24


አታልቅሽ በቃ
።፡።።።።፡።።።
ያመንሽው ቢከዳሽ
የእኔ ያልሽው ቢሸሽ
እድሌ ነው ብለሽ
ከቶ እንዳትከፊ
እንባሽን ዋጥ አርገሽ
በብርታት እለፊ

የአንድነት ቀዳዳው
ሽንቁሩ ቢሰፋም
የአብሮነት ሞገሱ
ከልቡ ቢጠፋም
አላወቀም እንጅ
እናት እና እህት ነች
ሴት ልጅ አትገፋም

እረሳሁሽ ካለሽ
አንችም ተይው በቃ
ፍቅር ህይወት እንጅ
አይደለም እቃቃ

አልሆንሽም ካለሽ
ተይው በቃ ይቅር
ባንድ ወገን ብቻ
ፀንቶ አይቆምም ፍቅር

ተይው በቃ ይቅር
🤦🤦🤦🤦🤦
በአንድ እግር ጉልቻ
ጎጆ አይቀለስም
ከሚታመን እንጅ
ከማያምን ሰፈር
ታቦት ወጥቶ አይነግስም

ተይው በቃ እህቴ
ተለያየን ብለሽ ጥቁር አትልበሺ
እንባሽን ጥረጊው ይቅር አታልቅሺ
ሴት ማለት እናት ነች
ይህንን አትርሺ

ልቧን አደንድና እናት ሁሉን ቻይ ነች
ብትከፋም እንኳን መሳቅየለመደች

ችግር ቢደቁሳት
🧑‍🎨🧑‍🎨🧑‍🎨🧑‍🎨🧑‍🎨
አካሏ ቢርድም
በራብ እና ውሀ ጥም
በችግሯ ክብደት
ወገቧ ቢጎብጥም
ነገን ችላ ብላ
እናት ተስፋ አትቆርጥም

አንችም
ችግር መጋፈጥን ከእናቶች ተማሪ
ያንች ያልሆነን ሰው
ትቶኝ ሄደ ብለሽ በእንባ አታቀርቅሪ
ይልቅ
በተስፋ ጠብቂ የአምላክሽን ጥሪ
ልክሽን በልክሽ እስኪሰጥ ፈጣሪ
አይዞሽ🤦🤦🤦🤦🤦🤦

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

13 Oct, 07:24


ዮኒ
ኣታን @yonatoz

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Oct, 10:50


አታልቅሽ በቃ
።፡።።።።፡።።።
ያመንሽው ቢከዳሽ
የእኔ ያልሽው ቢሸሽ
እድሌ ነው ብለሽ
ከቶ እንዳትከፊ
እንባሽን ዋጥ አርገሽ
በብርታት እለፊ

የአንድነት ቀዳዳው
ሽንቁሩ ቢሰፋም
የአብሮነት ሞገሱ
ከልቡ ቢጠፋም
አላወቀም እንጅ
እናት እና እህት ነች
ሴት ልጅ አትገፋም

እረሳሁሽ ካለሽ
አንችም ተይው በቃ
ፍቅር ህይወት እንጅ
አይደለም እቃቃ

አልሆንሽም ካለሽ
ተይው በቃ ይቅር
ባንድ ወገን ብቻ
ፀንቶ አይቆምም ፍቅር

ተይው በቃ ይቅር
🤦🤦🤦🤦🤦
በአንድ እግር ጉልቻ
ጎጆ አይቀለስም
ከሚታመን እንጅ
ከማያምን ሰፈር
ታቦት ወጥቶ አይነግስም

ተይው በቃ እህቴ
ተለያየን ብለሽ ጥቁር አትልበሺ
እንባሽን ጥረጊው ይቅር አታልቅሺ
ሴት ማለት እናት ነች
ይህንን አትርሺ

ልቧን አደንድና እናት ሁሉን ቻይ ነች
ብትከፋም እንኳን መሳቅየለመደች

ችግር ቢደቁሳት
🧑‍🎨🧑‍🎨🧑‍🎨🧑‍🎨🧑‍🎨
አካሏ ቢርድም
በራብ እና ውሀ ጥም
በችግሯ ክብደት
ወገቧ ቢጎብጥም
ነገን ችላ ብላ
እናት ተስፋ አትቆርጥም

አንችም
ችግር መጋፈጥን ከእናቶች ተማሪ
ያንች ያልሆነን ሰው
ትቶኝ ሄደ ብለሽ በእንባ አታቀርቅሪ
ይልቅ
በተስፋ ጠብቂ የአምላክሽን ጥሪ
ልክሽን በልክሽ እስኪሰጥ ፈጣሪ
አይዞሽ🤦🤦🤦🤦🤦🤦

belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Oct, 06:35


Blum ላይ አዲስ ነገር አለ። Drop game ላይ Dogs አካተዋልእየተባለ ነው። እስኪ እናንተ ጋርም ከመጣ አሳውቁን።

ያልጀመራችሁ

👇

🔗 LINK

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

12 Oct, 05:35


**
አልፎ ክረምት ሄዶ በጋ፣
ማጡ ድጡ ሲዘነጋ፤
ጨለማውን ቀን አቅልሞት፣
መራራውን ሳቅ አጥሞት፤
ያለፈ አምና ሆኖ መዝገብ፣
ሲነበነብ ሲደጋገም፣
ተረት ቢመስል የገፈፈ፣
አይረሳውም ያሳለፈ።


#ኤዶምገነት_ፃፈችው
@Edom_Ge

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Oct, 17:08


እኔ እና ሚስቴ(ከ"ሀ" እስከ "ፐ"
===================
ክፍል 3
👇👇👇
በመጀመሪያው ቀን
እቤት እንደገባሁ
ወንድ ልጅ ነኝ እና
ተደብቄ አነባሁ
አይሆኑትን ሆኜ
ያ ሌሊት ቢነጋ
ወጣሁኝ ከቤቴ
መውደዴን ፍለጋ
ፈልጌ ፈልጌ
እግሬን ድክም ሲለኝ
ስልኳን እንደሰጠችኝ
ያን ጊዜ ትዝ አለኝ
ባላወቅሁት ቅፅበት
ስልኬን አወጣሁኝ
ድምፁን loud አድርጌ
በፍጥነት ደወልኩኝ
የሧን ድምፅ ለመስማት
ምን ልቤ ቢጓጓም
የተረገመ ድምፅ
ብሎ አሳረፈኝ "ጥሪ አይቀበልም"
ከዛማ...
ስልኬን ወረወርኩት
እብደቴን ሞከርኩት
ተስፋየን ገደልኩት
ህልሜን ባዶ አረግኩት
አነባሁ እንደ ሴት ቆሜ በአደባባይ
መንደርተኛው ሁሉ
ምን ሆነ እያለ ሙድ ያዘ በእኔ ላይ
ኡ...ኡ...
እያልኩ ዘለልኩኝ
ከምድር እስከ ሰማይ
አልቅሼ አልቅሼ
ፊቴን በእንባ አርሼ
ቅባታሙ ፀጉሬን
በአቧራ ለውሼ
ወሰንኩኝ ለመሄድ
ወደ ቤቴ መንገድ
ጉዞየን ጀምሬ
ግራ ቀኝ እያልኩኝ ያኔ ስንገዳገድ
የናፈቀኝን አይን አየሁት ከመንገድ
በደስታ ፈንድቄ
ወደ እርሧ እየሮጥሁ
መቼም በእርሧ ጉዳይ
ያልታደልሁ ስለሆንሁ
እንቅፋት ቢመታኝ
በአፍ ጢሜ ተደፋሁ
ይቀጥላል👍👍👍
belaya(ዝምተኛው ፀሀፊ)
@belay_HI

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

11 Oct, 07:54


ውዴ ውዲቷ የወደፊቷ😔
እንባ ቢያወርድም ሳቅ አለው ፊቷ
እረፍት ቢነሷት መንገደ ቢዘጉ
መች ይለቃታል የጀግና ወጉ
ያርበኛ ልጅ ናት አቶድም ጥቃት
ዘረረቻቸው በፍፁም ብቃት

ውዴ ውዲቷ የወደፊቷ
ታታሪነት ነው ደምና አጥንቷ
ኃይልን ያነዳል እሳት ነው ፊቷ
ይንበለበላል ህልሟን ሊያነጋ
ካልማዝ የላቀው የልቧ ዋጋ

ፍቅር ነው መርቻው ክብር ነው ውበቷ
ውዴ ውዲቷ የወደፊቷ
እንባዋ ደርቋል ይስቃል ፊቷ።☺️❤️

Aናን

📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19